የምርጫ ሽር ጉድ በ2015ቷ ኢትዮጵያ
ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሀገሬ)
በ2015 በሚካሄደው ፓርላሜንታዊ “ምርጫ” መቅረብና መወሰን ያለበት አንድ ጥያቄ ይህ ነው፤ “የኢትዮጵያ ህዝቦች አሁን እ.ኤ.አ 2014 ያሉበት የኑሮሁኔታ ከቀድሞ 2010 ወይም 2005 ከነበሩበት የኑሮ ሁኔታ ይሻላል ወይ?” ህዝቦች ካለፉት ዓመታት በተሻለ ሁኔታ ላይ የማይገኙ ከሆነ አንደ አሮጌ ሸማ መቀየር መቀየር ይኖርባቸዋል። የፖለቲካ ሰዎችና እንደ አሮጌ ሸማ ናቸው። በየጊዜው ካልታጠቡና ካልተለወጡ ይበሰብሳሉ ይገማሉም። በጣም የሚገርም ነገር ነው! ምስኪን ኢትዮጵያውያ አንድ የበሰበሰ የገማ ሸማ ለሌላ 5 ዓመታት በጠቅላላው ለ25 ዓመታት ስትለብስ አያሳዝንም?