የፖለቲካው ስር ቁማርተኞች!
(ተመስገን ደሳለኝ)
በሀገራችን መንግስታዊ አስተዳደር የ‹‹ቁማር ህግ››ን ችግር መፍቻ አድርጎ መጠቀም የ መረበትን ጊዜ ለማስላት ንጉሰ ነገስት ዳግማዊ ምንሊክ እንደ”ተበሉበት” ከሚነግረን የሽኩሹክታ ታሪካችን አንስቶ አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት… እያልን ለመቁጠር እንገደዳለን፡፡ ይሁንና ባለሙያ (በንባብ የደረ ) ቁማርተኛ ፖለቲከኛ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛበት ድንገቴ ክስተት የ1966ቱ አብዮት ዋዜማ ነው ቢባል ወደ እውነታው ይጠጋል፡፡