ኢህአዴግና የሃይማኖት ነፃነት
(ተመስገንደሳለኝ)
…ኢሠፓ መራሹ መንግስት በኢህአዴግ ከተተካ ጥቂት ወራት ቢያልፈውም፣ የተራዘመው የእርስ በእርስ ጦርነት ያልደረሰባቸው በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ ከተሞችን ገና በቅጡ አልተቆጣጠራቸውም፤ በአናቱም በኢሠፓ መንግስት ሽንፈት ሳቢያ እንዲበተን ከተገደደው የ ገሪቱ መደበኛ ወታደር፣ አብዛኛው ከእነ ትጥቁ የትውልድ መንደሩንና ቤተሰቡን መቀላቀሉ በ ገሪቱ ላይ ከባድ ፍርሃት አንብሯል፤ በሰላም ወጥቶ ለመመለስ እርግጠኛ መሆን የማይቻልበት ከበባዊ አየርም አስፍኗል፡፡ በበርካታ ቦታዎች ተጠንተውና ታቅደው የሚፈፀሙ ወን ሎችም፣ ከአምስት እስከ አስራ አምስት በሚደርሱ ወታደሮች የተደራጁ ልዩ ልዩ ህገ-ወጥ ቡድኖች በየማዕዘኑ እያቆጠቆጡ መሆኑን አመላክቷል፡፡