ተማጽኖ ለጠ/ሚ ኃይለማርያም – ሳውዲን በተመለከተ
ግርማ ጌታቸው ካሳ
አይኖቼ በደም ቀሉ። ልቤ ተሰበረ። ከሳውዲ አረቢያ፣ ከባህር ማዶ፣ የወገኖቼ ጩኸትና ሮሮ፣ ከጣራዬ በታች የመነጨ ይመስል፣ በጆሮዬ በቅርበት ያቃጭላል። በርግጥ እንደ አገር፣ እንደ ሕዝብ፣ እንደ ኢትዮጵያዊ መዋረዳችንን አየሁ። በተለይም ደግሞ በአሁኗ ሰዓት፣ እንደ ወገን ምንም ማድረግ ባለመቻሌ ውስጤ ደበነ። የማድርገውን ሳጣ መሬት ተንበረከኩ። አይኖቼን ወደ ላይ አንስቼ፣ እጆቼን ዘረጋሁ።