የሰሜን ዕዝና የአየር ኃይል ዋና አዛዦች በሌሎች ተተኩ
የፓርላማው አባል የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕግ አማካሪ ሆኑ
በዮሐንስ አንበርብር
(ሪፖርተር ረቡዕ ጥቅምት 20 ቀን 2006 ዓ.ም. Oct. 30, 2013)፦ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አቅራቢነትና በፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ አማካይነት የጄኔራል መኮንኖች ሹመት ከተካሄደ በኋላ፣ በመከላከያ ሠራዊቱ አመራሮች ላይ የኃላፊነት ሽግሽግ ተካሄደ።