Tag: Ethiopia
የ365 ቀናት ፈተና እና ተስፋ – የአንድ ዓመት ማስታወሻ
የመታሰራችንዜና ከተሰማ ጀምሮ ብቻችንን አልታሰርንም፡፡ ብዙዎች አኛን ከከለለን አጥር ውጪ አብራችሁን ታስራችኋል፡፡ ስለዚህ የእስርቤት ጌጥ የሆኑት የመረሳትና ተስፋ የማጣት ስጋቶች እንዳይጎበኙን ያደረገንና በብርታት ያቆመን የእናንተው በእሳት የተፈተነ አብሮነት ነውና ሁላችሁም ምስጋና ይገባችኋል፡፡#Ethiopia #FreeZone9Bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsemamaw
የአንድነት ፓርቲ አባል የነበረው እስማኤል ዳውድ መታሰሩ ተሰማ
የአንድነት ፓርቲ አባል እና የሚሊየኖች ድምፅ አምደኛ የነበረው እስማኤል ዳውድ ትላንትና ከጠዋቱ ሁለት ሰአት ሲቪል በለበሱ ሰዎች ከመኖሪያ ቤቱ ተወስዶ ለእስር መዳረጉን ወላጅ እናቱ አስታወቁ፡፡ እስማኤል፣ ከጠዋቱ ሁለት ሰአት ሲቪል የለበሱ ሰዎች ቤቱ በመምጣት ‹‹ቃል ሰጥተህ ትመለሰላህ›› በማለት ከቤቱ ወደ አራዳ ፖሊስ ጣቢያ ከወሰዱት በኋላ ‹‹ቃሉን ሰጥቶም ቢሆን መለቀቅም እንደማይችል አስታውቀውት ወደ ወረዳ 9 ፖሊስ […]![]()
የወያኔ ደህንነቶች ሰማያዊ አዋሳ ከተማ ውስጥ እንዳይቀሰቅስ ከለከሉ
የገዥው ፓርቲ ደህንነቶች፣ ካድሬዎችና ፖሊሶች ሰማያዊ ፓርቲ አዋሳ ከተማ ውስጥ እንዳይቀሰቅስ እንደከለከሉ የሰማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስለሽ ፈይሳ ለነገረ ኢትዮጵያገልጸዋል፡፡ ባለፉት ሁለት ቀናት በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ሲቀሰቅስ ቆይቶ ወደ አዋሳ ያቀናውን የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ዛሬ ጠዋት አዋሳ ሲደርስ እንዳይቀሰቅስ እንደተከለከለ የገለጹት አቶ ስለሽ ደህንነቶች የመኪናውን ባለቤት በማስፈራራት በእጅ አዙር ቅስቀሳችንን […]![]()
ልብሴን እንዳወልቅ ከታዘዝኩ በኋላ ራቁቴን በወንድ መርማሪዎች ፊት ስፖርት እንድሰራ እገደድ ነበር›› ትላለች የዞን ዘጠኟ ማህሌት ፋንታሁን፡፡
ጋሻው መርሻ . ፈቃዱ የተባለ በአሁኑ ሰዓት ቂሊንጦ ታስሮ የሚገኝ የሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪ የነበረ ወጣት ማዕከላዊ በተባለ ማጎሪያ ቤት ታስሮ በነበረበት ወቅት ራቁቱን እንዲቆም ይደረግ እንደነበር ተናግሯል፡፡ ‹‹ወንድ መርማሪዎች ፊት ለፊት ራቁቴን ስቆም ሀፍረት እንደሚሰማኝ የተረዱት መርማሪዎች ይድነቅህ ብለው ሴት መርማሪዎች ፊት ከ3 ሰዓት ላላነሰ ጊዜ እርቃኔን እንድቆም እገደድ ነበር›› ይላል ፈቃዱ በወቅቱ […]![]()
በአማራ ክልል የሚገኙ የብ.አ.ዴ.ን/ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ስጋት የወለደው ስብሰባ አካሄዱ
በአማራ ክልል የሚገኙ የብ.አ.ዴ.ን/ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ስጋት የወለደው ስብሰባ ሲያካሂዱ መሰንበታቸውን የደረሰን መረጃ አመለከተ፣እንደምንጮቻችን መረጃ።- የብ.አ.ዴ.ን. /ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ አመራሮች ሚያዝያ 6 እና 7 2007 ዓ/ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት በተካሄደ ስብሰባ የአካባቢያችን ደህንንትና ሰላም ምን ይመስላል? የዚህ ክልል አለመረጋጋት ምክንያቱ ምንድን ነው? በሚሉና በሌሎችም ጉዳዮች ሲከራከሩ መቆየታቸውን የገለፀው መረጃው። በተለይ የትጥቅ ትግል የሚያካሂደው የአርበኞች ግንቦት […]![]()
የወንድሞቻችን ደም ምክንያት ኾኖ አንድነታችን ቢጸና… አንድ መኾን በቀል ነው
‹‹የኢራቅ እና የሶርያ እስላማዊ መንግሥት›› (Islamic State in Iraq and Syria) የሚል መጠሪያ ለራሱ የሰጠው ታጣቂ ቡድን፣ ጸጥታቸው የደፈረሰ አገሮችን የወታደራዊ ኃይሉ እንዲኹም እስከ ኹለት ቢልዮን ዶላር የሚገመተው የገንዘብ እና የንብረት ሀብቱ ማጠናከርያ በማድረግ ወደ ግዙፍ ዓለም አቀፋዊ አሸባሪነት እየተሸጋገረ ይገኛል፡፡ ‹‹የጥንቱን ገናና የእስልምና ሥርዐት›› በ፳፩ኛው ምእት ዳግም ለማስፈን የአምስት ዓመታት ግብ ያስቀመጠው ቡድኑ÷ መካከለኛው …![]()
ውሃ በበቂ ሁኔታ አለመጠጣት የሚያመጣው ጉዳት
አብዛኞቻችን ፈሳሽ ነገሮች የፍራፍሬ ጭማቂ፣ ሻይ እና የመሳሰሉትን መጠጣት ለሰዉነታችን የሚያስፈልገዉን ዉሃ እንደሚተካ እናስባለን፡፡ እዉነታው ግን እነዚህ ፈሳሾች ስኳር እና ጨው በውስጣቸው ስለሚይዙ በሰውነታችን ተመጠው በዉሃ እርዳታ ከእንሽርሽሪት ይወገዳሉ፡፡ በየቀኑ 8 ያህል ብርጭቆ ዉሃ መጠጣት ለጤና ተስማሚ ነው የአፍና ጉሮሮ ድርቀት እንዳይከሰት ከማድረጋቸው በላይ የተለያዩ በሽታዎችና ህመሞችን…
የኢህአዴግ መንግስት የአንድ ቀን የሰላም ጉባኤ ጠራ
ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በመላው አገሪቱ በሚታየው የሕዝብ ቁጣ ስጋት ላይ የወደቀው ኢህአዴግ መራሹ መንግስት፣ በምርጫ ቦርድ አማካይነት ግንቦት 16 ቀን ሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ በሠላም ስለሚጠናቀቅበት ለመምከር የአንድ ቀን ስብሰባ ጠርቷል፡፡ በሒልተን ሆቴል በሚካሄደው ስብሰባ ላይ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች እንዲገኙ ተጋብዘዋል፡፡ በተቃዋሚዎች ሁልጊዜም ቅሬታ የሚቀርብበት …
በሊቢያ ሚስቱንና የሶስት ወር ልጁን ትቶ የደረሰበት ያልታወቀው ሰው ከእስር ቤት አምልጦ ከቤተሰቡ ጋር ተቀላቀለ
ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያ ቤንጋዚ የሚኖር አንድ ሙስሊም ኢትዮጵያዊ በጦርነት መሃል አልፎ ከ3 ወር ልጇ ጋር ለሶስት ቀናት ቤት ዘግታ የተቀመጠቸውን ኢትዮጵያዊት ማዳኑን ኢሳት በልዩ ዘገባ ካቀረበ በሁዋላ፣ ባልየው ከ4 ቀን በሁዋላ ከእስር ቤት አምልጦ ከቤተሰቡ ጋር ተቀላቅሏል። በቀሌ አስፋው የተባለው ኢትዮጵያ ወደ ሊቢያ የሄደው በቅርብ ሲሆን፣ የሊቢያ ፖሊሶች መንገድ …
በማምረቻ ዘርፍ የመንግስት ዕቅድ አልተሳካም
ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በማምረቻ ወይንም በማኒፋክቸሪንግ ዘርፍ መንግስት በያዘው የአምስት ዓመት የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ መሰረት መከናወን ካለባቸው ትልልቅ ፕሮጀክቶች መካከል ከሲሚንቶ በስተቀር አለመሳካቱን አንድ ሰነድ አመልክቷል፡፡ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተገኘ ሰነድ እንዳመለከተው በሰኔ ወር 2007 ዓ.ም በሚጠናቀቀው የአምስት ኣመት እድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ ከተካተቱት መካከል ጥቅም ላይ የዋሉ ወረቀቶችና ከነባር ፋብሪካዎች …
አቶ ስንታየሁ በደህንነነቶች ታፍኖ ተወሰደ
ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ የነበረው እና በአሁኑ ወቅት የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ሚያዝያ 20/2007 ዓ.ም በደህንነቶች ታፍኖ ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ አራት ሲቪል የለበሱ ደህንነቶች ‹‹ትፈለጋለህ!›› በማለት በመኪና አፍነው ወዳልታወቀ ቦታ …
ኢትዮጵያ ከ15 አመታት በሁዋላ የነፍስ ወከፍ ገቢዋ 1 ሺ ዶላር እንደማይደርስ አንድ የኢኮኖሚ ትንበያ አመለከተ
ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአሜሪካ የግብርና ዲፓርትመንት ባወጣው ጥናት በፈረንጆች አቆጣጠር በ2030 ወይም ከ15 አመታት በሁዋላ የኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢ 820 ዶላር ይደርሳል። ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በቅርቡ ኢትዮጵያን መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ እንደሚያሰልፋት በተደጋጋሚ ቢናገርም፣ የጥናት ውጤቱ እንደሚያሳየው በ2030 ኢትዮጵያ ፣ የመካከለኛ ገቢ ዝቅተኛ መነሻ ከሆነው 1 ሺ ዶላር ለመድረስ …
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ሚያዚያ 28, 2015
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና
የለውጥ ሃይሎች አባል የሆነው ስንታየው ቸኮል በደህንነቶች ታፈነ::

Minilik Salsawi የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ም/ ቤት የወጣቶች ጉዳይ ሰብሳቢ የነበረው በአሁን ጊዜ ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል በመሆን የወያኔን ስርዓት እየታገለ የነበረው ስንታየሁ ቸኮል ከመኖሪያ ቤቱ በር ገንጥለው በገቡ ፖሊሶችና የደህንነት ኋይሎች የፍርድ ቤት ማዘዣ ሳይዙ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈፀመበት ወደ አልታወቀ ቦታ ተወስዶዋል።
ስንታየሁ ቸኮል ለረጅም ዘመን በተቃውሞው ጎራ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የወያኔን ስርዓት ለመጣል በሚደረገው ትግል ላይ ትግል እራሱን ሰጥቶ ይታገል የነበረ ጠንካራና ለትግሉም በምንም የማይደለል ታማኝ ወጣት ታጋይ ነው።

በISIS የተገደሉት ኤርትራውያን
Rest in Peace brothers
የሰማያዊ ፓርቲ መግለጫ
ባለሥልጣናቱ አክለዉ እንዳሉት የታሠሩ አባላቶቻቸዉን ለማስለቀቅና በፓርቲዉ ላይ ተከፈተ ያሉትን የሥም ማጥፋት ዘመቻ ለማስወገድ ፓርቲዉ በፍርድ ቤት ክስ ይመሰርታል።
በ40/60 የቤቶች ፕሮግራም ሰባት ሺሕ ተመዝጋቢዎች ውል አቋረጡ 7,000 people canceled their registration in 40/60 condominium home scheme
ከስምንት ሺሕ በላይ የሚሆኑት ሙሉ ክፍያ ፈጽመዋል
የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅፈር ይፋ ከተደረጉት አራት ፕሮግራሞች አንዱ በሆነው 40/60 ከተመዘገቡ 165 ሺሕ ተመዝጋቢዎች ውስጥ ሰባት ሺሕ ያህሉ ውላቸውን ሲያቋርጡ፣ 8,329 ተመዝጋቢዎች ደግሞ ሙሉ በሙሉ ክፍያ ፈጽመው ቤታቸውን ለመረከብ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸው…
በስዊድን ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በጋራ ኀዘናቸውን ተወጡ
“እያንዳንዳችን ወደልቦናችን መመለስ አለብን“ የክርስትና ተወካይ
“ቀዳዳውን አብረን እንድፈን“ የእስልምና ተወካይ
“በሰሃራ በረሃ አካላታቸው ለተበለተ ወገኖቻችን ዝም ማለት የለብንም“ የኤርትራ ተወካይ

Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. April 27, 2015)፡- ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከ10 ሰዓት (16፡00) ጀምሮ በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም ከ2000 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በሰርገልስ አደባባይ በመሰብሰብ በሊቢያ እና በደቡብ አፍሪካ አሰቃቂ ግድያ የተፈጸመባቸውን ወገኖቻቸውን በማሰብ ኀዘናቸውን እና ተቃውሟቸውን በጋራ ገለጡ።
ስቃይና መብት ጥሰት -አጥናፍ ብርሃኔ
አጥናፍ ብርሃኔ
ስቃይና መብት ጥሰት ያደረሱብኝ ሰዎቸ ስም ዝርዝር ( ሁሉም የፌደራል ፓሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል አባላት) በተለይ
– ሳጅን ምንላድርግልህ
-ታደሰ ወይም ጥጋቡ ( የሽፋን ስም )
– ኢንስፔክተር አሰፋ
– ም/ሳጅን መኮንን
– ኢንስፔክተር ገብሩ
ዋና ዋና የማሰቃየት ተግባር የተፈጸመበት ቀንና ሰአት – ሚያዝያ 17 እስከ ሃምሌ 11 /2006 አም
የማሰቃየት ተግባራት የተፈጸመበት ቦታ – የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ህንጻ በተለይ ቢሮ ቁጥር 5.፣ 32
ዋና ዋና ማሰቃየት ተግባራት
– ታደሰ የተባለው መርማሪ ፓሊስ ያለምንም ምክንያት ምርመራ ክፍል ውስጥ እያነቀኝ በተደጋጋሚ “እውነቱን የማትናገር ከሆነ ሽባ ነው የምናደርግህ ፣ እኛ ለግለሰብ መብት አንጨነቅም” በማለት በጥፊ ሲደበድበኝ ነበር
– ሳጅን ምን ላድርግልህ የተባለ መርማሪ “ጦማር ምን ማለት አንደሆነ ተናገር” ሲለኝ ጦማር ማለት መጻፍ ነው ብለውም ፡።፡።”ምህጻረ ቃል ነው እያንዳንዷ ምጻረ ቃል ምን ማለት አንደሆነች ካልተናገርክ አንላቀቅም” በማለት ከግርግዳ ጋር እያጋጨ ደብድቦኛል፣ ከግርግዳ ማጋጨት ብቻም ሳይሆን ረጅም ሰአት ከአቅሜ በላይ የሆነ የአካል አንቅስቃሴ እየሰራሁ የተመረመርኩ ሲሆን ምራቁን እየተፋብኝ አጸያፊ ስድብ ሲሰድበኝ ነበር፡፡
– ግንቦት ወር ላይ ሳጅን ምን ላድርግልህ የተባለው መርማሪ “ ኢህአዴግን ለምንድነው ተችታችሁ የምትጽፉት ?” “ከአገር ውጪ የምትሄዱት የመንግሰትን ስም ለማጥፋት ነው አንጂ የአባይ ግድብ ቦንድ ለመግዛት አይደለም” በማለት እጄን ወደላይ አድርጌ አንድመረመር አንዲሁም ጆሮዬን እየጎተተ በጥፌ ሲደበድበኝ ውሏል፡፡ ከዚህ ቤት ደንቁረህ ነው የምትወጣው በማለትም ያስፈራራኝ ነበር፡፡ እየተፋብኝ አጸያፊ ስድብ እየተሰደብኩ አካላዊና ስነልቦናዊ ጥቃት ተፈጽሞብኛል፡፡
– በሰኔ ወር ኢንስፔክተር አሰፋ የሚባለው መርማሪ ሌሊት 6 ሰአት አካባቢ ጠርቶኝ አላማችሁን ካልተናገርክ ጭለማ ቤት ነው የምትገባው በማለት ከማስፈራራቱም በላይ ሌሎች እስረኞች ሲደበደቡ እና ሲጮሁ ሲያለቅሱ በማሰማት እነደነሱ አንዳትሆን በማለት ዛቻ ተፈጽሞብኛል።
– ሰኔ ወር ላይ ኢንስፔክተር ገብሩ የታሰርኩበት ክፍል ውስጥ በመግባት ወረቀት ጽፈሃል የሚል በውል በማላውቀው ምክንያት ከሌሎች እስረኞች ለይቶ በተኛሁበት በተደጋጋሚ ከባድ የእርግጫ ደብደባ ፈጽሞብኛል። ሲደበድበኝም ህዝብ ልታጫርስ ነው እያለ ነበር፣ አስካሁንም የዛን ቀኑን ድብደባ ምክንያት ነው ያሉትን ነገር አላውቀውም፡፡
– በማእከላዊ ቆይታዬ 4በ4 በሆነች ክፍል ውስጥ በቀን ሁለቴ ብቻ ለ15 ደቂቃ ወደውጪ በመውጣት ከአስር ሰው ጋር ተቆልፎብኝ ታሬያለሁ ፡፡ የመጸዳዳት እድልም ቀኑን ሙሉ አልነበረኝም ፡፡ በየቀኑ ከባድ የአካል አንቅስቃሴ መስራት የምርመራው አካል ነበር፡፡
– በሃምሌ ወር ከምሽቱ 2.30 አካባቢ ሳጅን ምንላድርግልህ ፣ ም/ሳጅን መኮንን እና ሌላ የማላውቀው መርማሪ በመሆን ጭንቅላቴን በሃይል ከግንብ ጋር በማጋጨት እና የኮምፒውተር ኬብል በማሳየት አንደምገረፍ በመንገር ሳጅን ምንላድርግልህ የተባለው መርማሪ ፓሊስ የጻፈው የእምነት ቃል ላይ በግዳጅ አንድፈርም ተገድጃለሁ፡፡
*ይህ ጽሁፍ ለኢትዬጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከገባው አቤቱታ ተቀንጭቦ የተወሰደ ነው
በሊቢያ በደቡብ አፍሪካና የመን ለተገደሉ ወገኖቻችን በሲድኒ የሻማ ማብራት ሥነሥርዓት ተከናወነ
አቢይ አፈወርቅ
በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ ያስቆጣቸው የሲድኒ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን እሁድ ኤፕሪል 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ልዩ የሻማ ማብራት ስርአት አካሂደዋል። በዚህ በኒው ሳውዝ ዌልስ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር አስተናባሪነት በተዘጋጀው ሥነሥርዓት ላይ ቁጥራቸው ከ350 በላይ የሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን ተገኝተው ነበር።
ክርክር 6፡ ኢህአዴግ እና 1997 ስብርባሪዎች!!!! ግርማ ሠይፉ ማሩ
በዛሬው ሰድስተኛ ዙር የምርጫ ተብዬ ክርክር ጉዳዩ በመሰረተ ልማት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ኢህአዴግ ጎምቱ ያላቸውን ሹሞቹን ለክርክር ይዞ የቀረበበት ቢሆንም ለእኔ ግን ትኩረቴን የሳበው የተከራከሩበት ርዕስ ሳይሆን ተከራካሪዎቹ ሰዎች እና ፓርቲዎች ናቸው፡፡ ማለት የፈለኩት የመሰረተ ልማት በሚል ርዕስ ክርክር ስመለከት የተገነዘብኩት ጉዳይ ቢኖር ኢህአዴግ ክርክር እያደረገ ያለው የዛሬ አስር ዓመት ለሚዲያ ክርክር ድመቅት ይሰጥ ከነበረው […]
ስቃይና መብት ጥሰት – ኤዶም ካሳዬ
ኤዶም ካሳዬ
ስቃይና መብት ጥሰት ያደረሱብኝ ሰዎቸ ስም ዝርዝር ሁሉም የፌደራል ፓሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል አባላት እና የፌደራል ደህንነት መስሪያ ቤት አባላት መርማሪ ደስታ በዋናነት
ዋና ዋና የማሰቃየት ተግባር የተፈጸመበት ቀንና ሰአት – በተያዝኩባቸው ቀናት በሙሉ በተለይ ሚያዝያ 18 ,20, 21, 22, 23
የማሰቃየት ተግባራት የተፈጸመበት ቦታ – የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ህንጻ ቢሮ ላይ
ዋና ዋና ማሰቃየት ተግባራት
-መርማሪዬ ደስታ በተደጋጋሚ በጥፊ ይመታኝ ነበረ ሲሆነ ከዚህ ቤት የፈለግነውን ልናደርግሽ እንችላለን በአካል አትወጪም እያለ አስፈራርቶኛል
-የዞን 9 አባል አይደለሁም በማለቴ ፌቴን አዙሬ ከባድ የአካል አንቅስቃሴ የሰራሁ ሲሆን በተጨማሪም አላማቸውን ተናገሪ ሲለኝ የተለየ አላማ እንዳላቸው አላውቅም በማለቴ ሳታውቂ አንዴት አብረሻቸው ትውያለሽ ሸርሙጣ ብሎ በተደጋጋሚ ሰድቦኛል፡። ሌሎቹ መርማሪዎች አብረው ተቀምጠው በስድቦቹ ይስቁ ነበር
-ሌላኛው ተከሳሽ አጥናፍ መደብደቡን ፍርድ ቤት በመናገሩ አንቺ ትሞክሪውና ዋጋሽን ታገኛለሽ እኛ ፍርድ ቤት አያዘንም የግለሰብ መብትም አያሳስበንም ብሎኛል
-ጥጋቡ የሚባለው መርማሪ ምርመራ መሃል ደንገት በሩን ከፍቶ ገብቶ በጥፊ መቶኝ ይወጣ ነበር ( ስለምናወራው ጉዳይም ሆነ ስለምርመራው ሳይሰማ) እምቢ ካለችህ ልብሷን አስወለወቀህ ግረፋት ብሎ እኔን የተለመደውን ስድብ ሰድቦኝ ሄዷል
-በምርመራ ወቅት የዞን አባል ነኝ ብለሽ እመኚ ተብዬ ልብሴን አውልቄ ሙሉ እርቃኔን አንድመረመር ተገድጃለሁ ፡። በጥፊ እመታ የነበረ ሲሆን በዚህ ቀን ምርመራው ምሽት ላይ ጀምሮ እስከ ሌሊቱ 6 ሰአት ቆይቷል
-በተለምዶው ከምመረመርበት ቢሮ ውጩ አንደኛ ፎቅ አዳራሽ ውስጥ ለምርመራ ተወስጄ ልብሴን እንዳወልቅ እና የተለያዬ ለመናገር የሚከብዱ ስፓርታዊ አንቅስቃሴዎችን እንድሰራ ተገድጃለሁ፡፡ እንዲህ ከምትዋረጂ አመጽ ልናስነሳ ነበር ብለሽ ለምን አታምኚም እያለ ይመታኝ ነበር ፡፡ በጥፊው ተደጋጋሚነት የተነሳ ታምሜ ክሊኒክ ተመላልሻለሁ::
-በጋዜጠኝነት ሞያየ የተሳተፍኩበትን ስልጠናዎች ስናገር አንቺ ለምን ተመረጥሽ የኢቲቪ ጋዜጠኞች ለምን አይሄዱም አንቺ ለፈረንጅ ስለምትሰልዬ ነው ብሎኛል፡፡ በተጨማሪም ዞን9 ላይ የሚወጡት ጽሁፎች አንድ ገጠር ያለ ሰው ቢያነበው ለአመጽ የሚያነሳሳው ልማቱን የሚያጣጥል ነው ብሎ በተደጋጋሚ በጥፊና በካልቾ ተመትቻለሁ፡፡
-በተጨማሪም በተፈቺ እስረኛ ወደውጪ መልእክት ልከሻል በሚል ሰበብ ሌሊት ተጠርጬ በዱላ ሲዛትብኝ አርፍዷል
-በእስሩ ወቅት ከማህሌት ፋንታሁን ጋር ለብቻችን ከሰው አንዳንገናኝ ተደርገን ቆይተናል፡፡
*ይህ ጽሁፍ ለኢትዬጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከገባው አቤቱታ ተቀንጭቦ የተወሰደ ነው
የ“ቆንጆ” መፅሄት ባለቤት ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ካሳ አገር ጥሎ ተሰደደ
ላለፉት አራት ዓመታት ለንባብ ሲበቃ የቆየው የ“ቆንጆ” መፅሄት ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ካሳ አገር ጥሎ ተሰደደ፡፡ ጋዜጠኛው በተለያዩ ጊዜያት የመንግስት ደህንነቶች ቢሮው ድረስ በመሄድ ዛቻና ማስፈራራት ስላደረሱበትና ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ በመሆኑ አገሩን ጥሎ ለመሰደድ መገደዱን እንደነገራቸው ምንጮቹ ገልፀዋል፡፡ የደህንነት ኃይሎች በየጊዜው ወደ ቢሮው እየሄዱ “ክስና እስር ይጠብቅሃል” እያሉ ያስፈራሩት እንደነበር የተገለፀ ሲሆን፤ ፕሬሱን የሚወነጅል […]![]()
ስቃይና መብት ጥሰት – ዘላለም ክብረት
ስቃይና መብት ጥሰት ያደረሱብኝ ሰዎቸ ስም ዝርዝር ሁሉም የፌደራል ፓሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል አባላት እና የፌደራል ደህንነት መስሪያ ቤት አባላት መርማሪ ታደሰ ወይም ጥጋቡ ( ስሙ በትክክል የማላውቀው) በተለይ መርማሪ ምን ላድርግልህ መርማሪ ጽጌ መርማሪ አብዱልመጂድ
– በታሰርኩነት ወቅት ህጋዊ የእስር እና የብርበራ ትእዛዝ አልነበረም፡፡ ህጋዊ ያልሆነ ፍተሻ ከ12 ሰአት በኋላ አታድርጉ ብልም የሚሰማኝ አላገኘሁም ፡። ፍተሻው በከፍተኛ ማስፈራሪያ የታጀበ ነበር፡፡ ፓሊስ ጣብያ እሄዳለሁ ብለህ እንዳታስብ ራስህን ለምትሄድበት ቦታ አዘጋጅ እያሉ ከፍተኛ ስነልቦና ጫና አድርሰውብኛል
አልሸባብ አይሲስን ሊቀላቀል ነው ተጨማሪ የሽብር ስጋት በኢትዮጵያ
በሶማሊያ የሽብር ተግባራትን በመፈጸም የሚታወቀው አልሸባብ ደመኛና አረመኔውን አይሲስን ሊቀላለቀል መሆኑ ተሰማ፡፡አገራችንን በተጨማሪ የሽብር ስጋት ውስጥ እነደሚጥላት ተገምቷል፡፡ የሶማሊያን ስፊ ግዛት የሚቆጣጠረው አልሸባብ የማእከላዊ ስልጣኑን ካጣ ወዲህ በደረሰበት ወታደራዊ ኪሳራ የአለም አቀፍ አሸባሪው አልቃይዳ ክንፍ በመሆን እያካሄደ ባለው የደፈጣ ውጊያ ሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት ርቋት በንጹሃን ደም የታጠበች መንግስት አልባ ጦር ሜዳ ከሆነች ከሁለት ዓስርት አመታት […]![]()
ሰበር ዜና ወያኔ ሕዝቡን እያሸበረ ነው
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ም/ ቤት የወጣቶች ጉዳይ ሰብሳቢ የነበረው በአሁን ጊዜ ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል በመሆን የወያኔን ስርዓት እየታገለ የነበረው # ስንታየሁ_ቸኮል ከመኖሪያ ቤቱ በር ገንጥለው በገቡ ፖሊሶችና የደህንነት ኋይሎች የፍርድ ቤት ማዘዣ ሳይዙ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈፀመበት ወደ አልታቀቀ ቦታ ተወስዶዋል። ስንታየሁ_ቸኮል ለረጅም ዘመን በተቃውሞው ጎራ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የወያኔን ስርዓት ለመጣል […]![]()
መብት ጥሰትና ስቃይ – ተስፋለም ወልደየስ
ስቃይና መብት ጥሰት ያደረሱብኝ ሰዎቸ ስም ዝርዝር ( ሁሉም የፌደራል ፓሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል አባላት) መርማሪ የህይስ መርማሪ ጽጌ መርማሪ ታደሰ ( ስሙን እርግጠኛ ያልሆንኩት)
ዋና ዋና የማሰቃየት ተግባር የተፈጸመበት ቀንና ሰአት ማእከላዊ ምርመራ በቆየሁበት ጊዜ ሁሉ
የማሰቃየት ተግባራት የተፈጸመበት ቦታ – ማእከላዊ ወንጀል ምርመራ
ዋና ዋና ማሰቃየት ተግባራት
-በውል በማላስታውሳቸው ቀናት እስከእኩለ ሌሊት ድረስ የቆየ ምርመራ ተደርጎብኛል
-ለ75 ቀናት በተለምዶው ሳይቤሪያ የሚባለው ቦታ በቀን 15 ደቂቃ ብቻ የጸሃይ ብርሃን ለማየት ተፈቅዶልኝ ከዚያ ውጪ ያለውን ጊዜ 24 ሰአት አንድ በር ተዘግቶብኝ ቆይቻለሁ፡፡
-አራት በአራት በሆነ በዚህ ክፍል ውስጥ ቁጥራቸው አስር ከሚደርሱ ተጠርጣሪዎች ጋር ጤናዬን ለከፋ አደጋ የሚያጋልጥ ሁኔታ ውስጥ ነበርኩ
-በእስር በቆየሁባቸው ቀናት በቀዝቃዛው ሳይቤርያ ውስጥ በማሳለፌ በከፍተኛ ቅዝቃዜው የተነሳ ለጤና ጉዳት እና ለበሽታ ተዳርጌያለሁ
-ከፍተኛ እና ከአቅሜ በላይ የሆነ የአካል እንቅስቃሴ ያደረኩ ሲሆን በምርመራ ወቅት በተደጋጋሚ እመታ ነበር
-በዚህም የተነሳ ከፍተኛ የስነልቦና ጉዳት ደረሰብኝ ሲሆን በስተመጨረሻም ያላልኩትን አለ ተብዬ ፣ የማላምንበት እና ያልፈጸምኩትን ጥፋተኛ ነኝ ብለህ ፈርም በመባሌ ለመፈረም ተገድጃለሁ
*ይህ ጽሁፍ ለኢትዬጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከገባው አቤቱታ ተቀንጭቦ የተወሰደ ነው
ስቃይና መብት ጥሰት – ናትናኤል ፈለቀ
ስቃይና መብት ጥሰት ያደረሱብኝ ሰዎቸ ስም ዝርዝር ( ሁሉም የፌደራል ፓሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል አባላት) በተለይ ሳጅን ምን ላድርግልህ ፣ ም/ሳጅን አብተው
ዋና ዋና የማሰቃየት ተግባር የተፈጸመበት ቀንና ሰአት – ሚያዝያ 22 ( ከምሽቱ 2 ሰአት ገደማ)፣ ሚያዝያ 23 ከጠዋቱ 4 ሰአት፣ ግንቦት 6( ከምሽቱ 3 ሰአት ገደማ)፣ ሚያዝያ 24 ከጠዋቱ 4 ሰአት እና ከሚያዝያ 22 እስከ ግንቦት 6/2006 ድረስ ባሉት ቀናት ከእሁድ በስተቀር
የማሰቃየት ተግባራት የተፈጸመበት ቦታ – የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ህንጻ ላይ ቢሮ ቁጥር 30፣ 32 በ1981 አም በተሰራው ህንጻ ላይ 2ተኛ ፎቅ በስተግራ ጥግ በኩል ያለ ቢሮ
ዋና ዋና ማሰቃየት ተግባራት
– በምርመራ ወቅት ዛቻ እና ማስፈራሪያ የደረሰብኝ ሲሆን በተጠራሁባቸው ቢሮ ውስጥ ሁሉ በጥፌ ተደብድቤያለሁ ፡፡ በጥፌ መመታት የተለመደ ነበር ፡። በተደጋጋሚ ክፍተኛ ስፓርት የሰራሁ ሲሆን በቀን 10 ደቂቃ ብቻ የፀሃይ ብርሃን እያየሁ በጠባብ ክፍል ውስጥ ያለምንም ተፈጥሮ ብርሃንና መጸዳጃ ለ 76 ቀናት ቆይቻለሁ፡፡
– ጫማዬን አውልቄ በባዶ እግሬ አንድቆም ከተደረኩ በኋላ እግሮቼ ጣቶች ላይ መርማሪዎቹ በጫማቸው በሃይል በመርገጥ እግሬ ላይ ከባድ ድብደባ አድርሰውብኛል፡፡ ምርመራው እስኪጠናቀቅ ድረስም እጄ እንደታሰረ አናቴ ላይ አድርጌ እንድመረመር ተገድጄ ነበር፡፡
– የምሽት ምርመራዎች ወቅት በአብዛኛው ጊዜ እጄን ወደላይ አድርጌ እንድመረመር እገደድ ነበር ፡። ምርመራው ቀኑን ሙሉ የሚቆይ ሲሆን ምሽት እስከ ሌሊቱ ስድስተ ሰአት ድረስ ስፓርት በመስራት እና ፌቴን በማዞር እንድመረመር እገደድ ነበር፡፡
– ሰብአዊነቴን የሚነኩ ስድቦች ልክስክስ ፣ ውሻ መሳሰሉትን ስድብ በምርመራ ወቅት እሰደብ የነበረ ሲሆን አካለ ጎዶሎ ሆነህ ነው ከዚህ ቤት የምትወጣው ፣ ለግለሰብ መብት አንጨነቅም አንተን አንደፈለግን እነድናደርግ አሰራራችን ይፈቅድልናል የሚሉ ተደጋጋሚ ማስፈራሪያዎች ነበሩብኝ ፡፡
*ይህ ጽሁፍ ለኢትዬጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከገባው አቤቱታ ተቀንጭቦ የተወሰደ ነው
ስቃይና መብት ጥሰት – አቤል ዋበላ
ስቃይና መብት ጥሰት ያደረሱብኝ ሰዎቸ ስም ዝርዝር ( ሁሉም የፌደራል ፓሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል አባላት) በተለይ
– ምን ላድረግልህ
– ታደሰ ወይም ጥጋቡ ( የሽፋን ስም )
– ደስታ ወይም ሃሰን ( የሽፋን ስም)
– ዬሃንስ
– ፈይሳ
ዋና ዋና የማሰቃየት ተግባር የተፈጸመበት ቀንና ሰአት – ሚያዝያ 18(ከሰአት ከ8-10) ፣ ግንቦት 11 ( ከምሽቱ 2 ሰአት- ሌሊቱ 6 ሰአት) እና ሰኔ 26 ( ከምሽቱ 4 ሰአት -ሌሊቱ 7 ሰአት) እና በማእከላዊ ምርመራ በልዬ ሁኔታ በቆየሁባቸው 76 ቀናት
– የተያዝኩበት ማግስት አቶ ምን ላድርግልህ የተባለ የምርመራ ክፍሉ አባል ብሄሬን ጠይቆኝ ኢትዬጲያዊ መሆኔን እና በተለያዬ ብሄሮች ስር ራሴን አንደማልገልጽ እና በጥቅል ኢትዬጲያዊ መባል አንደምመርጥ ነገርኩት ተነስቶ ድብደባ ጀመረ ፡፡ በጥፌና በእርግጫ በተደጋጋሚ መታኝ፡፡ ሌላው መርማሪ ንግግራችንን ያልሰማ ከውጪ መጥቶ ያለምንም ጥያቄ ድብዳባውን ተቀላቀለ ፡፡ ከዱላው በተጨማሪ በጣም አጸያፌ ስድቦችን ሰደቡኝ፡፡ ብሄርህን የካድክ በብሄርህ የምታፍር ይሉኝም ነበር፡፡
በቫንኩቨር የሻማ ማብራት ስነ ስርአት ተካሄደ
“የታረዱትንና በጥይት የተደበደቡት ኢትዮጵያዊያን ሰማእታት ናቸው ‘ነፍስ ይማር’ ወይንም RIP ሊባልለት የሚገባው በቁሙ ለሞተው አይሲስ ነው።” ዲያቆን መምህር አድማሱ ዘባን
Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዚያ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. April 25, 2015)፦ ራሱን የእስላም መንግስት በማለት የሚጠራው እና ዘግናኝ ግድያዎችን በንጹሃን ዜጎች ላይ በመፈጸም ላይ በሚገኘው ቡድን እጅ ህይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያዊያኖችና በሳውዝ አፍሪካ የሚገኙ ወገኖች ላይ የሚፍጸመውን ሰብአዊነት የጎደለው አስከፊ ድርጊት በመቃዎም በቫንኩቨር (ካናዳ) ታላቅ የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት ተካሄደ።
በሜልቦርን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን ኢሰብዓዊ ጥቃት ተቃወሙ
ሚያዝያ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. (April 24, 2015) የሜልበርን ኢትዮጵያዊያን ኮሚኒቲ እና ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ቡድን በሕብረት ባስተባበሩት የተቃውሞ ሰልፍ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር የነበረው ኢትዮጵያዊ ተሳትፎ ቁጣውን በመረረና እልህና ቁጭት በተንጸባረቀበት መልክ ሲገልጽ አርፍዷል።
የአሳዛኙ ብላቴና የመሀመድ እና የወላድ እንግልት !
* ኢትዮጵያዊው ታዳጊ በህክምና ስህተት ለ9 ዓመታት ለከፋ አደጋ መዳረጉ ተረጋግጧል ! * የሳውዲ ጤና ጥበቃ ልዩ አጣሪ ኮሚቴ የሰጠው ውሳኔ ግን አሳዝኖናል * የብላቴናው ቀሪ ህይዎቱም ውስብስብ ሆኗል * አሰልችውን የዘጠኝ አመታት ፍትህ ፍለጋ ግን አልሰመረም * ” ከሬሳ የማይተናነስ በድን አድርገው አኮላሽተው ውስጅ ይሉኛል ፣ እንዴት ይህን ውሳኔ ልቀበል ? ፍትህ እሻለሁ! እርዱኝ! […]![]()
በስደት በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸሙትን አሰቃቂ ድርጊቶች የሚያወግዙ ሰልፎችንና የሻማ ማብራት ስነስርአቶች ተካሄዱ
ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባሳለፍነው ሳምንት በሊቢያ፣ በደቡብ አፍሪካና በየመን በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግፍ የሚቃወሙ ሰልፎች፣ የሻማ ማብራት ስነስርአቶችና ጸሎቶች በአውሮፓ፣ በአሜሪካና በእስያና በአውስትራሊያ ተካሂዷል። በለንደን ሰኞ ሚያዚያ 19 ቀን 2007 ዓም በተካሄደው ከፍተኛ ተቃውሞ ኢትዮጵያውያን በወገኖቻቸው ላይ የደረሱትን በደሎች አጥብቀው ኮንነዋል። ጋዜጠኛ ወንድማገኝ ጋሹ በስፍራው ተገኝቶ እንዳለው …
መሰቦ ስሚንቶ ለአባይ ግድብ ስሚንቶ ማቅረቡን ማቋረጡ ተሰማ
ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህወሃት የልማት ድርጅት ፣ ኢፈርት ንብረት የሆነው መሶቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ላለፉት ሶስት አመተት ያለተቀናቃኝ በከፍተኛ ዋጋ ለአባይ ግድብ ስሚንቶ ሲያቀርብ ከቆየ በሁዋላ ፣ ስራውን አቋርጧል። የአባይ ግድብ ግንባታ የኢኮኖሚ አዋጭነት ጥናት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ይፋ ከተደረገ በኃላ በባለስልጣናት መካከል ውዝግብ መነሳቱ ታውቋል። ጉባ የሚገኘው የስሚንቶ ማምረቻ …
ሼክ ሙሃመድ አላሙዲ በኢትዮጵያ መንግስት ስም 20 ሚሊዮን ዶላር ለክሊንተን ፋውንዴሽን መስጠታቸው ተጋለጠ
ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፒተር ስዋይዘር የተባሉ ጸሃፊ በቅርቡ በሚያሳትሙት መጽሃፍ ላይ ሼክ አላሙዲን ለክሊንተን ፋውንዴሽን 20 ሚሊዮን ዶላር እኤአ በ2006 መስጠታቸውን አጋልጠዋል። የሼክ አላሙዲን ድርጅት ለክሊንተን ፋውንዴሽን በጻፈው ደብዳቤ፣ እርዳታው የተሰጠው በኢትዮጵያ መንግስት ስም ሲሆን፣ የቡሽ አስተዳደር የውጭ ፖሊስ በክሊንተን አስተዳደር ጊዜም እንዲቀጥል ያስስባል። በባለቤታቸው ስም ገንዘብ የተቀበሉት ሂላሪ …
የኢህአዴግን የምርጫ ምልክት ቀደዋል የተባሉ ግለሰብ በአንድ አመት እስር ተቀጡ
ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከጎንደር ከተማ አስተዳደር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው አቶ ቀናው ክንዴ የተባሉ የከተማው ነዋሪ ሚያዚያ 6/2007 ዓም ከጧቱ ሁለት ሰአት ላይ የብአዴን ኢህአዴግን የምርጫ ምልክት ቀደዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። ግለሰቡ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ በመሆናቸው ብቻ የሃሰት ክስ እንደተመሰረተባቸው ቢናገሩም የጎንደር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በማግስቱ ሚያዚያ 7/2007 ዓም …
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ሚያዚያ 27, 2015
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና
ስለ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የተደረገ ትንተና
ወደ ሊብያ የተሰደዱት ኢትዮጵያውያንና ሌሎች እስላማዊ መንግስት ነኝ በሚለው ጽንፈኛ ቡድን አስቃቂ በሆነ መንገድ መገድላቸውን መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያ ህዝብ ሀዘን ላይ መሆኑ የሚታወቅ ነው። ኢትዮጵያውያንና ሌሎች አፍሪቃውያን ስደተኞች ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ በየመንና በሊብያ እንዲሁም በሌሎች አገሮች ለመውጣት በሚያደርጉት ጥረት ለአስከፊ ሁኔታ እየተዳረጉ ነው።
ለስደቱ ምክንያት የሆነውንና መፍትሄ ሊሆን ይችላል የሚሉትን እንዲያብራሩልን ዶክተር መሐሪ ታደለንና ፕሮፌሰር መረረ ጉዲናን ጋብዘናል። ዶክተር መሐሪ በአፍሪቃ ህብረት የፍልሰት መርሀ-ግብር ሃላፊ ሆነው ሰርተዋል። በአሁኑ ወቅት የአፍሪቃ ሰላምና ጸጥታ ተቋምን ይመራሉ። ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ደግሞ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀ-መንበርና የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራስያዊ አንድነት መድረክ የአመራር አባል…
UTC 16:00 የዓለም ዜና 270415
የዕለቱ ዜና
መንግስት በሰማያዊ ፖርቲ ላይ የከፈተውን የስም ማጥፋት ዘመቻ በአስቸኳይ ያቁም!!! – ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ሰማያዊ ፓርቲ በየመን፣ ደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል እየተከታተለ መንግስት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ሲያሳስብ ቆይቷል፡፡ በእነዚህ ሀገራት ችግር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን በደል በማውገዝና መንግስትም መፍትሄ እንዲሰጥ መግለጫ ከማውጣት ባለፈ የደቡብ አፍሪካ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን በደል እንዲያስቆም አዲስ አበባ ለሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ደብዳቤ በመጻፍ ፓርቲያችን የቻለውን ሁሉ ሲያደርግ […]






