ፒያሳ የሙስሊም ኢትዮጵያውያንን የተቃውሞ ድምጾች አስተናግዳ ዋለች
ሐምሌ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፒያሳ ከሚገኘው ኑር መስጊድ አንስቶ ዙሪያውን ባሉ መንገዶች ላይ ቆሞ የረመዳንን ጁመዓ ስግደት ሲሰግድ የዋለው ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ ፣ ከአንድ አመት በላይ ሲያሰማው ነበረውን ድምጻችን ይሰማ የሚለውን ተቃውሞ በከፍተኛ ድምጽ በማሰማት የፒያሳን አየር ተቆጣጥሮት ውሎአል። ድምጻችን ይሰማ፣ የተነጠቅነውን መስጂዶቻችን ለህዝቡ ይመለሱ፣ የተባረሩ ኢማሞች ይመለሱ፣ አሸባሪ አይደለንም፣ ኢማሞቻችን ይፈቱ፣ ጥያቄው …