ደቀ መዛሙርቱ በቅ/ሲኖዶሱ ውሳኔዎች ተፈጻሚነት ስጋት ገብቷቸዋል

  • ሓላፊዎቹን የተመለከቱ የቅ/ሲኖዶሱ ውሳኔዎች በደብዳቤ ወጪ አልተደረጉም
  • ንቡረ እዱ÷ አቡነ ጢሞቴዎስ ‹‹በሚሰጧቸው መመሪያ›› እንደሚሠሩ ተናግረዋል
  • ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መምህራንና ሠራተኞች የሥራ ዋስትና አደጋ ላይ ነው
  • ዋነኛ ጥያቄያችን አልተመለሰም ያሉ መምህራን በተቃውሟችን እንቀጥላለን እያሉ ነው
  • ነገ ፈተና የሚጀምሩት የዘንድሮ ምሩቃን ፈተናቸውን በጨረሱ ማግሥት ይመረቃሉ!
  • ‹‹የተያዘው ጨዋታ ነው፤ መፍትሔ እንደሚሰጡን ከተናገሩ በኋላ እንደ ልጅ ሊያታልሉን እየሞከሩ ነው›› /ደቀ መዛሙርቱ/
  • ‹‹ከዚህ በኋላ አቡነ ጢሞቴዎስ ሊቀጥሉ አይችሉም፤ የእኛ ሥራ ነው፤ ለእኛ ተዉት›› /የቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት ለደቀ መዛሙርቱ/