UTC 16:00 የዓለም ዜና 230713
የዕለቱ ዜና
የዕለቱ ዜና
በብሪታንያ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የወጣቶቹ ልዑል ዊልያም እና የባልተቤታቸው ልዕልት ካትሪን(ኬት)ሚድልተን ወንድ ልጅ ትናንት በለንደን የሴይንት ሜሪ ሀኪም ቤት ተወልዶዋል።
በቅርቡ ለንባብ የበቃው “ድርጅታዊ ምዝበራ” የተሰኘው መጽሃፍ ደራሲ ዶክተር ኣክሎግ ቢራራ ጎንደር ተማሪ በነበሩበት ወቅት በኣንድ ነገር ተመስጠው ነበር። ይህ ምናባቸውን የገዛው ነገር በጎንደር ውስጥ እድሜው የትየለሌ የሆነ የኣንድ የዋርካ ዛፍ ተፈጥሮ ነበር። ይህን ዋርካ ባዩት ቁጥር ምናባቸው ተዛምዶን ይፈጥራል። ግዙፉ ዋርካ ዙሪያውን ያሉትን ቅርንጫፎችና ቅጠሎች ይዞ ዝንት ዓለም ይኖራል። ከምድሪቱ የሚያገኘውን ኣስፈላጊ ነገር እያመላለሰ […]
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ከሐምሌ አንድ እስከ ሐምሌ ሰድስት 2013 እ ኤ አ፣ ለኢትዮጵያውያን ሰላሰኛውን ዓመት ለሚያከብረው የእግር ኳስ ውድድር በዲሲ ተገኝቼ ነበር። ይህ በዓል በኢሳት ተነግሮ ሰለነበር በዓለም ዙሪያ ከኢትዮጵያ ሣይቀር ዲሲን እንደ ቁለቤ ገብርኤል ልንሣለማት እንደ ድሬ ሼክሁሴን ሙዳ ልንላት ተገኝተናል። በአገራችን ከማንኛውም ክፍለሃገር ዛሬ ጎረቤት አገር ከተባለችው ኤርትራ ሣይቀር የሐረሩን የቁልቤ ገብርኤል የባሌውን ድሬ ሼክሁሴን እስላም […]
ለማንበብ እዚህን ይጫኑ
በደቡብ ወሎ ዞን በረባቡ ወረዳ በስግደት ላይ የነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ አብዱ መሐመድ እና አቶ እንድሪስ አህመድን ጨምሮ 45 ወጣቶች መታሰራቸውን ምንጮቻችን ከስፍራው በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡ ከታሰሩት መካከልም ወጣት ሱልጣን መሐመድ በከፍተኛ ህመም እየተሰቃየ እንደሚገኝና እስካሁንም የህክምና እርዳታ እንዳልተደረገለት ተጠቁሟል፡፡ መንግስት የወረዳውን ነዋሪዎች የደሴው ሼህ ኑሩ ይማምን መገደል በሰላማዊ ሰልፍ ካላወገዛችሁ የመሬት […]
ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ አቶ ተሻለ በካሻ መዝገብ ተከሰው ከሁለት አመታት በላይ በእስር ቤት የቆዩት እስረኞች ሰሞኑን ከፍተኛ ድብደባ ከተፈጸመባቸው በሁዋላ ለተከታታይ ቀናት ምግብ ባለመመገባቸው ህይወታቸው አደጋ ላይ መውደቁን በመግለጽ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደርስላቸው አቤት ብለዋል። እስረኞቹ በጻፉት ደብዳቤ ላይ ከውጭ የመጡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በፌሮ ክፉኛ እንደደበደቡዋቸውና ህክምና በማጣታቸው ከፍተኛ ስቃይ …
ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አንድነት የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በማለት የጠራው ህዝባዊ ንቅናቄ ገዢውን ፓርቲ በማስደንገጡን አዲስ ከጀመራቸው ግምገማዎችና የህብዕ እንቅስቃሴዎች ለመረዳት ተችሎአል። በደሴ እና በጎንደር የተካሄደውን ስላማዊ ሰልፍ ተከትሎ የፖሊስ እና የቀበሌ የፖለቲካ አመራሮች በጠንካራ ግምገማ ተይዘው መሰንበታቸውን ከኢህአዴግ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ስማችን እና ድምጻችን አይተላለፍ ያሉት ምንጮች እንደገለጹት በ1ለ5 አደራጃጀት …
ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የግንባሩ 9ኛ ጉባዔ ሪፖርት እንደሚያሳየው በ2003 እና በ2004 ዓ.ም ግንባሩ 88 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ገቢ ያገኘ ሲሆን ቀድሞ በባንክ አካውንት ውስጥ ከነበረው ሒሳብ ጋር ሲደመር ገቢው 171 ነጥብ 2 ሚሊየን መድረሱንም ይፋ አድርጓል፡፡ 46 በመቶ የሚሆነው ገቢ የተገኘው ከ“አዲስ ራዕይ” እና “ህዳሴ” ከተሰኙ ሕትመቶች ሽያጭ ነው ፡፡ …
ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህር ዳር ከተማ በህዝበ ሙስሊሙ መካነ መቃብር አጠገብ የሚገኘውን ትንሽ ቦታ መንግስት ሞይንኮ ለተሰኘ የመኪና ጋራጅ ድርጅት አሳልፎ መስጠቱን ተከትሎ የአካባቢው ሙስሊም ባነሳው ተቃውሞ ምክንያት ድርጅቱ ቦታውን እንደማይወስድ እና እንደማይረከብ አስታውቆ ነበር። ትናንት ህዝበ ሙስሊሙ ቦታውን ለማጠር እና አታክልት ለመትከል ሲሰባሰብ የፌደራል ፖሊስ በፍጥነት በመምጣት ያስቆማቸው ሲሆን እርምጃውን …
ከተመስገን ደሳለኝ
ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ
…አራት ኪሎ በሚገኝ አንድ ካፍቴሪያ ከጓደኞቼ ጋር የደራ ወግ በመያዜ፣ የእጅ ስልኬ የ‹‹መልስ ስጠኝ›› ጩኸቱን ደጋግሞ ሲያሰማ ልብ አላልኩትም፤ እናም ጮኾ ጮኾ ሲጨርስ፣ እንደገና ይ ምራል፡፡ ይኼኔ ጥሪውን እንዳላስተዋልኩ የተረዳው ጓደኛዬ ወደ ስልኩ ሲያመላክተኝ፣ ቁጥሩን አየሁት፤ አውቀዋለው፡፡ የእስክንድር ነጋ ባለቤት የጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ነው፤ አነሳሁት፡፡
ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ በጆሐንስበርግ ደቡብ አፍሪቃ ፤ ወደ 500 የሚጠጉ ኢትዮጵያዉያን በአንድ ዉይይት ላይ መገኘታቸዉ ታውቋል። በዉይይት መድረኩ የተለያዩ ምሁራንና የሲቪክ ማሕበራት ተሳታፊዎች እንደነበሩ ለመገንዘብ ተችሏል።
News, Sports, African Topics and Health
የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዶክተር እንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ፤በዛሬው ዕለት የግብዕን ጊዜያዊ መንግሥት ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ሞና ኦማርን አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የኅብረቱ ዋና ጽ/ቤት ተቀብለው ማነጋገራቸው ተመለከተ።
ሥለ NSA የተለያዩ መፅሐፍት ያሳተመዉ ጋዜጠኛ ጀምስ ባምፎርድ እንደሚለዉ፥ እርስዎ ከዱባይ ወይ ከለንደን አዲስ አበባ ላለች ፍቅረኛዎ የፍቅር ኢሜል ይመይላሉ እንበል።ስኖዳን እና ብጤዎቻቸዉ ሐዋይ፥ ሜሪላንድ ወይም የፈለጉበት ቦታ ሆነዉ-ከፍቅረኛዎ እኩል ምናልባትም ቀድመዉ ኢሜልዎን ያነባሉ።ስልኩም—
የታላላቅ ሃይቆች አካባቢዉ ሀገራት ሚኒስትሮች፤ በአፍቃ ህብረት አዳራሽ በችግሮቻቸዉ ላይ ተወያይተዋል።
Yemillionoch Dimtse-andinet ende Gandi
News, Radio Magazine or Mestawot
መድረክ በመቀሌ የጠራው ህዝባዊ ስብሰባ በስኬት እንደተጠናቀቀ የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ጸሀፊ ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡ የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ጸሀፊ አቶ ክብሮም ብርሃነ ለፍኖተ ነፃነት እንዳስታወቁት መድረክ ዛሬ ሐምሌ 14 ቀን 2005 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ቀኑ 7 ሰዓት ያካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ከአንድ ሺ በላይ ሰዎች የተገኙበት ነበር፡፡ በአብዛኛው […]
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ኢትዮጵያ ዉስጥ በ1997 የተደረገዉ ምርጫ ዉጤት ደም ባፋሰሰ ግጭት ካሳረገ ወዲሕ መንግሥትን በአደባባይ ሠልፍ መቃወም ለኢትዮጵያዉያን ዝግ ሆኖ ነበር።
«ነጻነትን ማንም አይሰጥህም። እኩልነትና ፍትህንም ማንም አይሰጥምህ። ሰው ከሆንክ፣ አንተዉ እራስህ ተቀበለው» ነበር ያሉት፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ማልኮም ኤክስ። ነጻነትና ሰላም፣ ዴሞክራሲና ፍትህ፣ እኩልነትና መልካም አስተዳደር፣ ሌሎች የሚሰጡን ሳይሆን፣ ፈጣሪ በቸርነቱ የለገሰን፣ ደፍረንና ፈቅደን የምንቀበላቸው፣ የኛዉ የሆኑ በረከቶች ናቸው። ነገር ግን ለአመታት መብታችንና ነጻነታችን፣ በጥቂቶች ተገፎ፣ ሁላችንም በየጓዳችን ስንናደድ፣ ስናማርር፣ ስናዝን፣ ስንራገም፣ ልባችን ሲደማ፣ «እንደዉ […]
በቅድሚያ ርዕሰ-ጥያቄው አንፃራዊ መልስ የሚሻው በጣም አሳሳቢ እና :- የአገር ፍቅርን:-የሚገድል ዝምታ በኢትዮጵያውያን ላይ ሃያ ሁለት ዓመታት በመንገሱ ነው።ይህ አቢይ ጉዳይ እና ወሳኝ በመሆኑ ዝምታውን ለመስበር ደግሞ ወቅታዊነቱን እንረዳለን።የኢትዮጵያውያን እስልምና ዕምነት ተከታዮችን አንድነት እና ጥንካሬ በአፅንኦት ይመለከቷል:: እኛ ኢትዮጵያውያን ከሁሉም በፊት አስቀድሞ:- “እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ ነው።”{መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ-፻፲፩ ከቁጥር-፲ ፤መጽሐፈ ምሳሌ ም፩ ቁ፯ […]
UDJ Fundrising
በማለዳው ከእንቅልፍ ስነቃ ለዛሬው ለማለዳ ወግ ቅኝቴን ሁለት ሰሞነኛ ትኩስ ወጎች ከፊ ለፊቴ ገጭ ብለው ጠበቁኝ ! . . አንዱ ሰሞነኛ ወግ ስልጣኔ ዘመነኛ የመገናኛ ዘዴዎችን ማግኘት የታደለው የሃገሬ ሰው አይኑን አፍጦ በማህበራዊ ገጾች እና በተለያዩ የኢንተር ኔት ድህረ ገጽ ስር ባሉ የመረጃ መረቦች ሲከታትለው የሰነበተው የጁሃር መሃመድ ሃይማኖትና ዘርን ቀላቅሎ የተናገረበት አሳፋሪ፣ አሳዛኝ እና […]
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
መድረክ ነገ ሐምሌ 14 በመቀሌ ከተማ ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ በመኪና ሲቀሰቅሱ የነበሩት የአረና ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሱልጣን ህሺ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ጸሀፊ አቶ ክብሮም ብርሀኔ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ በህገወጥ መንገድ መታሰራቸውን የአረና ፓርቲ ለፍኖተ ነፃነት አስታውቋል፡፡ ፓርቲው ጨምሮ እንዳስታወቀው ለነገው ስብሰባ ቅስቀሳ እንዳይደረግ የክልሉ መንግስት ሀላፊዎች ክልከላ ቢያደርጉም በነገው እለት […]
News, Call-in show or special interviews and Ye Musica Qana
ባለፈዉ የካቲት ኬንያ ዉስጥ በተደረገዉ ፕሪዝዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉት ቃለ-መሃላ ፈፅመዉ የፕሪዝዳንትነቱን ሥልጣን ከያዙ በኋላ አዲስን ካቢኔ ሾመዋል። ኬንያታ የሾምዋቸዉ ባለስልጣናት በአብዛኞቹ ከአሁን ቀደም በኬንያ የፖለቲካ መድረክ እንብዛም ያልተሳተፉ መሆናቸም ተነግሮአል። ይህ የኬንያታ አዲስ ጅማሮ ኬንያዉያን አዲስ ተስፋን አሰንቆላቸዋል።
ያሬድ ክንፈ ከኒዮ፣ ስዊዘርላንድ (ጥቂት ፎቶግራፎች ይዘናል)
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሐምሌ 13 ቀን 2005 ዓ.ም. July 20, 2013)፦ ረቡዕ ሐምሌ 10 ቀን 2005 ዓ.ም. (ጁላይ 17፣ 2013) በኒዮን የስዊዘርላንድ ከተማ የተጀመረው 11ኛው የአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ዛሬ ቅዳሜ ይጠናቀቃል። ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት፣ ከሰሜን አሜሪካ፣ ከኢትዮጵያ እንዲሁም ከተለያዩ አህጉራት የመጡ በርካታ ኢትዮጵያውንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለበዓሉ ድምቀት አስተዋጽዖ አድርገዋል።
አቡነ ጢሞቴዎስ ጉዳያቸው ከሚታይበት ስብሰባ ላለመውጣት ሲለመኑ ውለዋል ኣቦይ ስብሐት አቡነ ጢሞቴዎስን ለማግባባት በቅ/ሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ ተገኝተዋል ፓትርያሪኩ ስለ አቡነ ጢሞቴዎስ ብዙ ከመናገር ተጠንቅቀዋል፤ ተቆጥበዋል ደቀ መዛሙርቱና መምህራኑ ደስታቸውን በቅኔ፣ ወረብና መዝሙር እየገለጹ ነው የንቡረ እድ ኤልያስ ምደባ ግዙፍ ከሚያስነሣው ግዙፍ ጥያቄ ጋራ የምረቃው ቅድመ ዝግጅት ይቀጥላል. . .![]()
ኢትዮጵያንና ህዝቧን የአብሮነትን መሠረት ለመሸርሸርና ብሎም ለማጥፋት ሌተ ቀን የማይተኛዉ የህወሀት ኢህአዴግ አሸባሪ መራሹ መንግስት በህዝብ ጫንቃ ላይ ተቀምጦ ዜጎችን ማሰቃየት ከጀመረእነሆ ፪፪ አመት ተቆጥሮዋል።ነገር ግን የ፪፪ አመት ቆይታዉ ህዠብን ከማሸበር፣ ከመግደል፣ከማሰር ከማሰደድ፣ከመግረፍና ከማፈናቀል አልፎ በተመቸዉና የጥፋት ምርቃናዉ በመጣለት ቁጥር በዘረኞች መሪዎቹአማካይነት በፈለገዉ ሰዐት ከራሱ ህግና ስርአትዉጪ ከእንቅልፋ እንደሚነቃና የሚያደርገዉን እንደማያቅ ህፃን ልጅ የተለያዮ ህጎችን […]
ሐምሌ ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት በረመዳን ጾም ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የጀመሩት ተቃውሞ ይበርዳል የሚል እምነት የነበረው ቢሆንም፣ ተቃውሞው ከሳምንት ሳምንት እያየለ በመምጣቱ፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት በአንዳንድ አካባቢዎች የሀይል እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል። ከሀሙስ ጀምሮ በፌደራል ፖሊስ አባላት ክትትል ስር የነበሩት የወልድያ ሙስሊሞች በዛሬው እለት በመስጊዳቸው ውስጥ ታግተው መዋላቸውና አንዳንዶች መደብደባቸውን ሌሎች ደግሞ መታሰራቸው …
ሐምሌ ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው ባወጣው የህዝባዊ ንቅናቄ እቅድ መሰረት ባህርዳር፣ ጅንካ፣ አርባምንጭ፣ አዳማ፣ ባሌ፣ ወሊሶ፣ ፍቼ፣ ጋምቤላ፣ አሶሳ እና አዲስ አበባ ለህዝባዊ ሰልፎች ሲመረጡ፣ መቀሌ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ አምቦ፣ ደብረማርቆስና አዲስ አበባ በድጋሜ ለህዝባዊ ስብሰባዎች ተመርጠዋል። ሀምሌ 21 እና 28 በአዲስ አበባ 2 ቦታዎች እንዲሁም ሀምሌ 28 በወላይታ ሶዶና …
ሐምሌ ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አጠናቅሮ ለክልሉ ባለስልጣናት ባቀረበው ሪፖርት ላይ እንተመለከተው የክልሉ ቅርስ ጥበቃ ቢሮ ታሪካዊ ቦታዎችን በመንከባከብና የቅርስ ዘረፋ እንዳይካሄድ በመከላከል በኩል በቂ ጥረት አላደረገም። በክልሉ ከ3000 በላይ የቅርስ መገኛ ተቋማት ቢኖሩም ሙዝየም በማሰራት ቅርሶቻቸውን በጥንቃቄ ለእይታ የቀረቡት 13 ብቻ መሆናቸውን የኦዲት ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡ በተለያዩ …
ሐምሌ ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ረቡእ 78 ሰዎችን አሳፍሮ ከአዲስ አበባ ወደ አክሱም ይበር የነበረው ቦምባርዴር ኪው 400 አውሮፕላን ማረፊያ ቦታው ላይ ሊደርስ ደቂቃዎች ሲቀሩት የጭስ መቆጣጠሪያው በመጥፋቱ፣ ፓይለቱ አውሮፕላኑን በአስቸጋሪ ሁኔታ በማሳረፍ የሰዎችን ህይወት እና የአየር መንገዱንም መልካም ስም ታድገዋል። ሱዳን ትሪቢውን አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ባለስልጣንን ጠቅሶ እንደዘገበው የጭስ …
Oromo Prisoners, OFC, Bekele Nega
Blue Party, call for a new demo
Ditroit, Bankrupcy
News, Community Heroes or Call-in, Crossfire and African Topics
የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ጦር ሠራዊት M-23 በሚል መጠሪያ በሚታወቀው አማጺ ኅይል ላይ መልሶ የማጥቃት ዘመቻውን አጠናክሯል። በታንክ፣ በሄሊኮፕተር ፤ አዳፍኔና ከባድ አውቶማቲክ ጠብመንጃ ፣ ወታደሮቹ ከጎማ ከተማ በስተሰሜን ፣ የአማጽያኑን ምሽግ መደብደባቸውን የዜና አውታሮች አስታውቀዋል።
በማዳመጥ መማር የተሰኘው በዶቼ ቬለ እና በጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትብብር የሚቀርበው አዝናኝ እና ትምህርታዊ ተከታታይ ድራማ 6ኛ ዙር ቀረፃ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።