ጥቅምት ፳፪(ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ሌተናንት ጄኔራል ሆነው የተሾሙት በሱዳን የሚገኘውን እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር በመሆን  በጸጥታ መስከበር ስራ ላይ የተሰማራውን የኢትዮጵያ ጦር የሚመሩት ምናልባትም ጀኔራል ሳሞራ የነሱን ሊተኩ ይችላሉ የሚባሉት ሌተናንት ጀኔራል ዮሀንስ ገብረመስቀል ተስፋማርያም በአዲስ አበባ የገነቡዋቸው የንግድ ህንጻዎች በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዋጋ እንደሚያወጡ ለእርሳቸው ቅርብ የሆኑ ሰዎች …

ጥቅምት ፳፪(ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሀኪሙላ መሱድ የሚባለው የፓኪስታን ታሊባን መሪ የተገደለው በአሜሪካ ሰው አልባ የጦር ጅቶች መሆኑን አለማቀፍ ሚዲያዎች ቢዘግቡም እስካሁን ከአሜሪካ መንግስት በኩል የተሰጠ ማረጋገጫ የለም። ግለሰቡ በአሜሪካ ከሚፈለጉ አሸባሪዎች ማካከል አንዱ ነው። አሜሪካ ግለሰቡ ያለበትን ለጠቆመ 5 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገብታ ነበር። የመሱድ ምክትል ባለፈው ግንቦት ወር በተመሳሳይ …

ትላንት ዘሄግ ኔዘርላንድ ውስጥ ያስቻለው ዓ/ዓቀፉ የወንጀል ፍ/ቤት በኬኒያው ፕ/ት ኡሁሩ ኬኒያታ ላይ የተያዘውን የክስ ሂደት እስከሚቀጥለው የካቲት ወር ድረስ ለሶስት ወር ማራዘሙን ኣስታወቀ። የኣፍሪካ ህብረት ግን በቂ ኣይደለም እያለ ነው።

እንግዳችን የኤሌክትሪላል ኢንጂነሪንግ ምሩቅ ነው። በተማረበት ሙያ ሥራ አግኝቶ ነበር ይሁንና በፍላጎት ወደ ንግድ ሥራ ነው የገባው። ለምን? ስለዚህ ወጣት ማንነት እና ከሌሎች አራት ባልደረቦቹ ጋ ተደራጅቶ ስለሚሠራው ያስረዳናል።

በአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት የተዘጋጀው የ5 ሳምንት ስልጠና የመጀመሪያው ክፍል (1) እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ረጅም የነፃነት ዘመን ሲኖራት በስልጣኔ ግን ብዙም እንዳልገፋችም። ስለዚህ ስልጠና ክፍል አንድ “ኢትዮጵያ ምን ስትሰራ ነበር?” የሚል ጥያቄ አንስቶ ሁለት አብይ ክሎች ያሉት ሰፊ ታሪካዊ መልሶች ሰጥቷል። በመቀጠል ክፍል አንድ (2) የሰላማዊ ትግልን እድገት አስመልክቶ ከክርስቶስ ልደት በፊት አንስቶ ዛሬ እስካለንበት ዘመን […]

ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምክንያቱ በውል ባይታወቅም ካለፉት 4 ቀናት ጀምሮ በከተማዋ ከፍተኛ ፍተሻ እየተካሄደ እንደሆነ የዘጋብያችን መረጃ ያመለክታል። በተለይ ዛሬ በከተማዋ መውጫና መግቢያ በሮች ላይ ሰዎች ከመኪናዎች እና ባጃጆች ላይ እንዲወርዱ እየተደረገ በጥብቅ ተፈትሸዋል። አንዳንድ ወገኖች  መንግስት ጸረ ሰላም እና አሸባሪዎች በከተማዋ ገብተዋል የሚል ወሬ እንደሚያስወራ ሲገልጹ፣ ሌሎች ነዋሪዎች ደግሞ …

ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዓመት 50ሺ የኮንዶምኒየም ቤቶችን ለመገንባት የያዘው ዕቅድ ከባድ ትችትን ያስከተለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዓመት ከ 100ሺ በላይ የቤቶች ግንባታ ለማከናወን ፊቱን ወደቻይና ኩባንያዎች ማዞሩ ተሰማ፡፡ አስተዳደሩ ከ800ሺ በላይ የኮንዶምኒየም ፣ ከ 136 ሺ በላይ የ40 በ60 ቤት ፈላጊ ነዋሪዎችን የመዘገበ ሲሆን ከዚህ ፍላጎት ጋር በማይጣጣም መልኩ …

ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በከፍተኘው ፍርድ ቤት ባለው የአስተዳደር ቊንጮ ማለትም በዋናው ፕሬዚዳንት በዳኛ ውብሸት ሽፈራውና በምክትሉ ማሃል ያለው አለመስማማት እየጨመረ በመሄዱ የፍርድ አሰጣጥ ሂደቱን እያበላሸው መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች ገለጹ ። አሁን ባለው አሰራር ተሰሚነት ያለው የኢሃዴግ አባል የሆነው ምክትሉ ሲሆን ፣  ፕሬዘዳንቱ የኢሃዴግ አባል ባለመሆኑ ተሰሚነት አጥቷል ይላሉ …

ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቅዱስ ሲኖዶሱ ሰሞኑን ሲያደርግ የነበረውን ምልዓተ ጉበኤ ሲያጠናቅቅ ባወጣው የአቋም መግለጫ ፣ በውጭ አገር ከሚገኙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ጋር ተጀምሮ የነበረው እርቀ ሰላም ወደ ፊት እንዲቀጥል እና ቤተክርስቲያን አንድነት እንዲጠናከር ወስኗል። የኦሮቶዶክስ ሀይማኖት ተከታዮች ቆጠራ እንዲካሄድና  የቤተክርስቲያኒቷ ታሪክ በደንብ ተጠንቶ እንዲቀርብም ወስኗል። ከፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ተወክለው የመጡ …

ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ እና በአማራ ክልሎች ያሉ አርሶ አደሮቹ ለኢሳት እንደተናገሩት ውጤታማ ባልሆኑበትና በግዴታ እንዲገዙ በተጠየቁት የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ እዳ እየተዋከቡ ነው። እዳችንን መክፈል አልቻንም የሚሉት አርሶ አደሮች መንግስት መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ጠይቀዋል። ግብርና ሚኒስቴር ለረጅም ጊዜ በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ የዋለውን ዳፕ የተባለውን ማዳበሪያ ውጤታማ አልሆነም በሚል እንደሚቀይር ማስታወቁ ይታወቃል። …

ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቁም ነገር አዘል በሆኑ ቀልዶቹ የሚታወቀው ኮሜዲያን አብረሀም ከጀርባ ህመም ጋር በተያያዘ ሲሰቃይ ቆይቷል። ከጥቂት ወራት በፊት ወደ አውሮፓ በመምጣት በጀርመን አገር ህክምናውን ተከታትሎአል። አብርሀም በማእደ ኢሳት ዝግጅት ላይ ቀርቦ ለኢትዮጵያ ህዝብና የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ የረዱትን ወገኖች ማመስገኑና ጤናውም መሻሻልእያሳየ እንደሆነ መግለጹ ይታወሳል ፡፡ ከዲስከ መንሸራተት ጋር  …

ባሰላው ባሰላው እንቢ አለኝ እንዝርቱ፣ ከታችም አይደለ ከላይ ነው ጥመቱ። የጎንደር ሕዝብ እንጉርጉሮ ኦክቶበር 28 እንደ ሃገሩ አቆጣጠር ጠዋት ጉልበተኛ ነፋስ ከባሕር ተነስቶ በደቡብ እንግሊዝ በኩል አድርጎ እያቆራረጠ ወደ ሰሜን ተፈተለከ። የባሕሩ ሰይጣን የላከውን ጉልበተኛውን ነፋስ የፈራው አዳሜ ፈረንጅ ሁሉ ተርበትብቶ እኛንም በሬዲዮንና በቴሌቪዚዮን ሲያርበተብተን ሰነበተ። “ይህንን ቀን ከቆመ የተቀመጠ፣ ከተቀመጠም የተደበቀ ነው የሚያልፈው። ደፍሮ […]

በአዲስ ግንኙነት ዓለምን መቀየር በሚል መሪ ሃሳብ በታላቋ ብሪታንያ ዋና ከተማ ሎንዶን ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየዉ የዘጠነኛዉ የዓለም ዕስልምና ምጣኔ ሃብት መድረክ ዛሬ ተጠናቋል።

« በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያዊ ሕጻናት ስሞችን ስንመለከት በአብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ ይዘት እንደሌላቸዉ እንረዳለን፤ አብዛኞች ስሞች ቅላጼያቸዉ ለጆሮ እንዲጥሙ እንጂ ፤ ታሪኩ ምን ማለት ነዉ ብለን ጠይቀን ለልጆቻችን ስም ስንሰጥ አንታይም። ይህ ደግሞ የባህል ወረራ እንዳያመጣብን እሰጋለሁ» ያሉን

ቅ/ሲኖዶስ ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪካዊነትና ቀዳሚነት እውነታውንና ትክክለኛውን የሚገልጽ ጽሑፍ እንዲዘጋጅ መመሪያ ሰጠ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት ለምልአተ ጉባኤው ስብሰባ የሰጠው ሽፋን ‹‹የጉርሻ ያህል ነው›› በሚል ተነቀፈ ‹‹ጉባኤው አገር አቀፍ ብቻ ሳይኾን ዓለም አቀፍም ነው፤ የምንሰጠው ትምህርት ነው፤ የምንወድቀው የምንነሣው ስለ ሀገር ጉዳይ ነው፤ ቤተ ክርስቲያን በዐይን የሚታይ በእጅ የሚጨበጥ ታሪክ ነው …

በአገልግሎት ጥራት /በሰው ተኮር ነፍስ የማዳን አገልግሎት/ ምእመናንን ማብዛትና ማጽናት፣ ቤተ ክርስቲያንን ከባይተዋርነትና ጠባቂነት ወደነበራት ሚና መመለስ፣ አስተምህሮዋን ከማይቃረኑ ጋራ ዓለም አቀፍ አጋርነትን በማጠናከር የሰላምና አንድነት ተምሳሌት ማድረግ፣ ለሙስና ችግሮች በንስሐ መንገድ መፍትሔ ማበጀት የቤተ ክርስቲያናችን ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማሕቀፍና ቊልፍ ጉዳዮች ኾነዋል፡፡ በቡድን እየተደራጁ የመንግሥትን ወቅታዊ አጀንዳዎች በአሉታዊ መንገድ የሚጠቀሙ አሉባልተኞችና ሙሰኞች እንዲሁም በቤተ ክህነቱ …

Prof. Al Mariam ፕ/ር ዓለማየሁ ገብረማርያም ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም፦ ነጻነት ለሀገሬ)
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ሕገመንግሥት በሕግ ከለላ ጥላ በቁጥጥር ስር የሚውሉ ዜጎችን አስመልክቶ የሚከተሉትን መብቶች ያጎናጽፋል። “በሕግ ከለላ ጥላ በቁጥጥር ስር የዋለ ማንኛውም ሰው በሕግ አግባብ መብቱ ተጠብቆ ይያዛል። ማንኛውም ሰው በሀሰት ለመረጃ ጠቀሜታ ተብሎ በማስገደድ እንዲያምን ወይም የተባለውን እንዲቀበል አይገደድም። ማንኛውም በማስገደድ የተገኘ መረጃ ተቀባይነት አይኖረውም።” ይላል አንቀጽ 19(2)(5)። እውነታው ሲታይ ግን ይህ የይስሙላ ሙበት የተጻፈበትን ወረቀት ዋጋ ያህል የለውም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

 

ኢትዮጵያዊያን በፍርዱ ረክተዋልወ/ሮ ሙሉመቤት ረታ (በሲያትል ኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር)

በእኔ አስተያየት ፍትህ ተበይኗል፤ ዳኛዋም ሆኑ ፍርድ ሰጭዎቹ (ጁሪዎቹ) በትክክል ጉዳዩን አይተው ወስነዋል ብየ አምናለሁዶ/ር ሸክስፒር ፈይሳ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥቅምት 20  ቀን 2006 ዓ.ም. October 30, 2013)፦ ከሁለት ዓመት በፊት ሃና ዊሊያምስ የተባለችውን ታዳጊ በቅዝቃዜ ደጅ ላይ በማዋልና በማሳደር አሰቃይተው ገድለዋል የተባሉት አሳዳጊዎቿ ኬሪ ዊሊያምስና ባለቤቷ ላሪ ዊሊያምስ የ37 ዓመትና የ29 አመት ጽኑ እስራት የተወሰነባቸው ሲሆን በሲያትል አካባቢ የሚኖሩ ትዮጵያዊያን በፍርዱ መደሰታቸውን በተለይ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጥቅምት ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሪፖርተር ዛሬ ባወጣው ዘገባ በአገሪቱ የሚገኙ ሶስቱ ታላላቅ ስሚንቶ ፋብሪካዎች በአመት 12 ሜትሪክ ቶን ሲሚንቶ የማምረት አቅም ቢኖራቸውም በገበያ ውስጥ የሚገኘው ስሚንቶ ድምር ከ5 ሚሊዮን አይበልጥም። አብዛኛውን ስሚንቶ የሚገዛው መንግስት ሲሆን፣ የግሉ ዘርፍ ድርሻ ቀዝቃዛ መሆኑ ተዘግቧል። የሼክ ሙሀመድ አላሙዲን ንብረት የሆነው ደርባን ኩባንያ የዋጋ ቅናሽ በማድረግ በኩንታል …

ጥቅምት ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጥሬ ቆዳና ሌጦ ኤክስፖርት ባለፉት አምስት ዓመታት የተሻለ ገቢ ያስገኘ ቢሆንም ግብይቱ ኃላቀር፣ሰንሰለቱ የተንዛዛና ከፍተኛ የግብይት ወጪዎች የሚታዩበት እንዲሁም በምርት ጥራት በኣለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቱ እጅግ አነስተኛ መሆኑን ከንግድ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ አመለከተ፡፡ የጥሬ ቆዳና ሌጦ ኤክስፖርትን በማቆም እሴት የተጨመረባቸውን የተለያዩ የቆዳ ውጤቶች ለውጪ ገበያ በመላክ የተሻለ የውጪ …

ጥቅምት ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት በልመና የሚተዳደሩ አረጋውያን ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሯል። አረጋውያኑም ከክልል ከተሞች ወደ አዲስ አበባ እንደሚጎርፉ ነዋሪዎች ይናገራሉ። መንግስት የገጽታ ግንባታ በሚል አረጋውያንን ሰብስቦ ወደ ክልል ቢበትናቸውም፣ አረጋውያኑ ተመልሰው በምጣት በልመናው ቀጥለዋል። አንድ ነዋሪ እንዳሉት ቀድሞ ” አብያተ ክርስቲያናት ቅጥር ግቢ ውስጥ አይለመንም ነበር፣ አሁን ግን …

ጥቅምት ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዘውዲቱ ሆስቲታል መድሀኒቱን ለመቀበል ከሳምንታት በላይ ሲጠባበቁ የነበሩ የስኳር ህመምተኞች በመጨረሻ መድሀኒት የለም መባላቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚሰጠው እርዳታ መቋረጥ ለችግሩ መፈጠር ምክንያት ነው ቢባልም፣ አንዳንድ ወገኖች ደግሞ የችግሩ ምንጭ መድሀኒቱ አየር ባየር ስለሚሸጥ ነው ብለዋል። ህመምተኞች እንደሚሉት መድሀኒቱን በግላቸው ገዝተው ለመጠቀም ዋጋው የሚቀመስ አይደለም። ብዙዎቹ መድሀኒቱን …

ጥቅምት ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የ42 አመቷ ካሪ ዊሊያምስ የ13 አመቷን ታዳጊ ሐና ዊሊያምስን በረሀብና በብርድ በመቅጣት ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን ፍርድ ቤቱ አረጋግጧል። የገዳዩዋ ባለቤት በ28 አመታት እንዲታሰር ተፈርዶበታል። ሌላው የ10 አመቱ የማደጎ ታዳጊ ኢትዮጵያዊም ለሌሎች አሳዳጊዎች እንዲሰጥ ተደርጓል። ፍርዱን የሰጡት ዳኛ ከፍተኛ የሚባለው ቅጣት ማስተላላፋቸውን ተናግረዋል። ሁለቱም ሰዎች ከሁለት አመታት በፊት መታሰራቸው …

የሃዋሣ ዩኒቨርሲቲና የከሰሣቸው ጋዜጠኞች የችሎት ውሎ

የሃዋሣ ዩኒቨርሲቲ በመሠረተባቸው ክሥ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት የኢትዮ-ምህዳር ጋዜጣ ሁለት አዘጋጆች ወደ ዋናው ጉዳይ ገብተው እንዲከራከሩ ብይን ተሰጠ።

ሃዋሳ የሚገኘው የሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን የማየት መብት እንደሌለው ያቀረቡት መከራከሪያም ተቀባይነት አላገኘም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሁለቱ የጋዜጣው አዘጋጆችና ጉዳዩን ለመከታተል አብሯቸው የነበረው ባልደረባቸው እዚያው ሃዋሳ ከተማ በባጃጅ በመጓዝ ላይ እንዳሉ ባጋጠማቸው አደጋ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት እንደደረሰባቸው አስታውቀዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

“የአፄ አብርሃም ያዬህን ጽሑፍ አንብበን ስንጨረስ ነገር ማብላላታችንን ትተን ዝም ብለን መጋደም አልቻልንም፡፡ ዘመናችን ብዙ የሚሠራበት ሣይሆን ብዙ የሚወራበትና የሚጻፍበት መሆኑን እናውቃለንና አግራሞታችን ወሰን አልነበረውም፡፡ ጥሎብን ‘ሌላ ሥራ የላቸውም ወይ?’ እስክንባል ድረስ በዬቀኑ ብዙ እናነ(ብ)ባለን፤ ይህም ሲሆን በምንታዘበው ሁሉ እናነባለን፡፡ ሕዝባችንን የሚጠቅም ነገር ለማከናወን የዛሬ አሥራ ሁለት ዓመት ገደማ ብዙ ብንጥርም የአማራ ኤሊቶች እያወኩን ጥረታችን […]

እረፍት አደርግ ብየ ከማህበራዊ መገናኛ መድረኩ ገለል ባልኩባቸው እንደ ብርሃን ፍጥነት በሚወረወሩት ባለፉት ጥቂት ቀናት ከበርካታ ወዳጆቸ በርካታ መልዕክቶች ይደርሱኛል ። ብዙው መልዕክት ደግሞ የሚያጠነጥነው በጅዳ እና በአካባቢው በተፈናቃይ የኮንትራት ሰራተኞች አሰቃቂ ስቃይ ላይ ያተኮራል …ለነገሩ የአብዛኞቹ መልዕክቶች ብቻ ሳይሆኑ ከመልዕክቶች ጋር የሚላኩልኝ መረጃዎች እረፍት የሚነሱ ናቸው! … አዎ ተንቀሳቃሽ ምስል ጭምር በመረጃነት የታጨቀባቸውን የመልዕክት […]

አየር መንገዱ ወደ ፍራንክፈርት ጀርመን በረራ የጀመረበትን 55 ተኛ ዓመት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ፍራንክፈርት ውስጥ ባሰበበት ወቅት የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም እንደተናገሩት ድርጅታቸው 2025 በተሰኘው እቅዱ በርካታ ውጥኖቹን ተግባራዊ አድርጓል ።

አደጋው ከደረሰባቸው ጋዜጠኛ አንዱ ጌታቸው ወርቁ እንዳስታወቀዉ ለአደጋ የተጋለጡት የተሳፈሩበት ባጃጅ በሞተር ብስኪሌት በመገጨቱ ነዉ።የሃዋሳ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን የለውም መከሰስ ያለበትም ዋና አዘጋጁ ነው ሲሉ ጋዜጠኞቹ ያቀረቡትን ጥያቄ ዛሬ ከሰዓት ውድቅ አድርጓል።

የአውራምባ ታይምሱ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ Dawit Kebede of Awramba Timesጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ከስደት ለምን ተመለሰ?
“እኔ ወደ ሀገሬ ለመምጣት ከማንም ጋር አልተደራደርኩም” ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ

የአውራምባ ታይምሱ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ወደ ሀገር ቤት መመለሱን ኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ መዘገቧ አይዘነጋም። ዳዊት ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ በሀገር ውስጥ የሚታተመው ሰንደቅ ጋዜጣ በ8ኛ ዓመት ቁጥር 425 የረቡዕ ጥቅምት 20/2006 ዓ.ም. ዕትሙ ከዳዊት ጋር ያደረገውን ቆይታ እንደወረደ እንደሚከተለው አቅርበነዋል። ቃለምልልሱን ያደረገው ጋዜጠኛ ዘሪሁን ሙሉጌታ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የፓርላማው አባል የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕግ አማካሪ ሆኑ

በዮሐንስ አንበርብር

(ሪፖርተር ረቡዕ ጥቅምት 20 ቀን 2006 ዓ.ም. Oct. 30, 2013)፦ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አቅራቢነትና በፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ አማካይነት የጄኔራል መኮንኖች ሹመት ከተካሄደ በኋላ፣ በመከላከያ ሠራዊቱ አመራሮች ላይ የኃላፊነት ሽግሽግ ተካሄደ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አቶ በረከት ስምኦን Bereket Simonየሹመቱ አግባብነት ጥያቄ አስነስቷል
አፈጉባዔ አባዱላ ጠ/ሚኒስትሩ በሹመቱ ላይ ማብራሪያ ለመስጠት አይገደዱም አሉ

በፍሬው አበበ
(ሰንደቅ ጋዜጣ ረቡዕ ጥቅምት 20 ቀን 2006 ዓ.ም. Oct. 30, 2013)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ለኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ ኃላፊነት ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ያቀረቡትን ሹመት ተቀብሎ አጸደቀ። በዚሁ መሠረት ድርጅቱን ለረዥም ጊዜ በቦርድ ኃላፊነት ባገለገሉት በአቶ በረከት ስምኦን ምትክ አቶ ሬድዋን ሁሴን የድርጅቱ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው፣ ጥቅምት ፳ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ዘጠነኛ ቀን የቀትር በፊት ውሎው የኤጲስ ቆጶሳትን ምርጫ የሚያስፈጽም አስመራጭ ኮሚቴ ሠየመ፡፡ አስመራጭ ኮሚቴው ስድስት ሊቃነ ጳጳሳት በአባልነት የሚገኙበት ሲኾን የትግራይ፣ ወሎ፣ ጎንደር፣ ጎጃም፣ ሸዋና ኦሮሚያ አህጉረ ስብከትን በመወከል የተመረጡ ናቸው፡፡ በዚህም መሠረት÷ ከትግራይ ብፁዕ አቡነ፣ ከወሎ የደቡብ ወሎ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ፣ …

የአቡነ ጢሞቴዎስ ዐምባገነንትና የኮሌጁ ጉዳይ ምልአተ ጉባኤውን ሲያወያይ ዋለ ሊቀ ጳጳሱ በበላይ ጠባቂነት ተወስነው የሽግግር ዋና ዲን እንዲሾም ሐሳብ ቀርቧል የኮሌጁ ሥራ አመራር ቦርድ ዛሬ ለምልአተ ጉባኤው ማብራሪያ ይሰጣል የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ከእናት ቤተ ክርስቲያን መዋቅር ወጥተው በገለልተኛ አስተዳደር ለሚመሩ አብያተ ክርስቲያን የአንድነት ጥሪ ሊያስተላልፍ ነው፡፡ ምልአተ ጉባኤው በትላንት፣ ጥቅምት ፲፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ውሎው …