የዩክሬይን ጠ/ሚ የዋሽንግተን ጉብኝት
የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የዩክሬይንን የሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚንስትር አርሴኒ ያዜንዩክ ትናንት በዋይት ሀውስ ቤተ መንግሥት ተቀብለው አነጋገሩ። ግዛቷ ክሪሚያ በሩስያ የተያዘባትን ዩክሬይን ዩኤስ አሜሪካ እንደምትደግፍ ኦባማ ለያዜንዩክ አረጋገጠዋል።
የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የዩክሬይንን የሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚንስትር አርሴኒ ያዜንዩክ ትናንት በዋይት ሀውስ ቤተ መንግሥት ተቀብለው አነጋገሩ። ግዛቷ ክሪሚያ በሩስያ የተያዘባትን ዩክሬይን ዩኤስ አሜሪካ እንደምትደግፍ ኦባማ ለያዜንዩክ አረጋገጠዋል።
የዓለም ዜና
የካቲት 30 ቀን 20006 ዓ.ም በታሪካዊቷ የሐረር ከተማ በጀጎል ሸዋበር በደረሰው ቃጠሎ እና ከዚያም በኋላ የክልሉ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ በዜጎች ላይ ጉዳት መድረሱ የፓርቲያችንን አመራሮች፣ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ያሉ አባላትና ደጋፊዎችን በእጅጉ አሳዝኗል፡፡ ምንም እንኳን የቃጠሎው መንስኤ ተጣርቶ ይፋ ያልተደረገ ቢሆንም በጀጎል ሸዋ በር እየደረሰ ያለው ተደጋጋሚ ቃጠሎ ድንገቴ ነው ለማለት የሚያስደፍር አይደለም፡፡ […]
አንድነት ን በተመለከተ ============= አንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ ወይም አንድነትን በተመለከተ የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነቱ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው በበኩላቸው ተጠይቀው በቅድሚያ ፓርቲያቸው በምርጫ የሚያምን ፓርቲ እንደመሆኑ ሕዝቡ ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ ተጠቃሚ መሆን አለበት ብሎ እንደሚያምን ገልፀዋል። ለ2007ቱም ምርጫ ፓርቲያቸው የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች እያደረገ መሆኑን፣ የመጀመሪያው ፓርቲው የቆመለትን ፖሊሲ ለሕዝብ ለማቅረብ በሚመች መልኩ የአማራጭ ፖሊሲ ትንተና […]
የፖለቲካ ምህዳር መስፋት፣ የ2007 ምርጫ፣ የታሳሪዎች ጉዳይ በአጀንዳነት ተነስቷል በአውሮፓ ኅብረት የአፍሪካና የኢትዮጵያ ቋሚ አምባሳደር የኢትዮጵያ መንግስትንና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን እያነጋገረ ነው። የኅብረቱ ቋሚ አምባሳደር አማካኝነት መካሄድ የጀመረው ውይይት በሀገሪቱ የፖለቲካ መህዳር መስፋት፣ በ2007ቱ ምርጫ፣ ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች እንዲሁም በሀገሪቱ ስላለው የሰብአዊና የዴሞክራሲ መብቶች ዙርያ መሆኑ ታውቋል። ባለፈው ዓመት የኅብረቱ ቋሚ አምባሳደር በመሆን […]
“ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ” ማለት ይሄ ነው፡፡
ለጋራ ጥቅማችን ብሎ ለራሱ ከሚጠቀምብን ያድነን፡፡ ከሃዲዎች የዕጣ-ፈንታቸዉን ያገኛሉ::
ተነስ ሲሉት የሚነሳ፣ ተኛ ሲሉት የሚተኛ …” ዞሮ ዞሮ ወዶ-ገባ ያሉትን መፈፀም ግዴታው ነው፡፡ ወዶ-ገባ ዝርያው ብዙ ነው፡፡ የፖለቲካ ወዶ-ገባ አለ፡፡ ፖለቲካው ምንም ይሁን ምንም ለጥቅሜ እገባበታለሁ ይላል፡፡ የኢኮኖሚ ወዶ-ገባ አለ፡፡ ኢኮኖሚው ምንም ይሁን ምን ሆዴን እሞላበታለሁ ይላል፡፡ የማህበራዊ ወዶ-ገባ አለ፡፡ ከማናቸውም ማህበራዊ ቀውስ እኔ ጥቅሜን ካካበትኩ ያሉኝን አደርጋለሁ ባይ ነው፡፡ ብልህ ሰው የውሾቹን ዓይነት ዕጣ-ፈንታ ያስተውላል፡፡ አበሻ፤ “አብዶም ሠግዶም ውሉን አይስትም” የሚል አባባል አለው፡፡ ይሄንንም ልብ-ልንበል፤ የህግ-ወዶ-ገባም አለ፡፡ በፍትሕ ሽፋን ጥቅሙን የማያጋብስ፡፡
አገርን የሚያጠፋ ማንኛውም ጥፋት ጥፋት ነው፡፡ ሚሥማርም አቀበልን ድንጋይ ያው ነው፡፡ በወገናዊነት ላንድ ቡድን መጠቀሚያ አመቻቸንም፣ በሙስና ውስጥ ተዘፈቅንም፤ ዞሮ ዞሮ “ጌታ ተሰቅሏል”፡፡ አገርና ህዝብ በድለናል፡፡ እገሌ አድርግ ብሎኝ ነው እንጂ እኔ በራሴ አላደርገውም ነበር ማለት የኋላ ኋላ ከተጠያቂነት አያድንም፡፡ በሥርዓቱም ማሳሰብ በግልና በቡድን ከሠራነውና አንዱን የእናት ልጅ፣ አንዱን የእንጀራ ልጅ አድርገን ካጠፋነው ጥፋት ተጠያቂነት አያድንም፡፡ ሰው ሰውን መበዝበዙ ነው ሀቁ፡፡ ፊት ለፊቱም ግልባጩም ያው ነው እንደ ማለት ነው፡፡
ስለዚህ ሥርዓት ሰበብ አይሆንም፡፡ ዕውነቱ ሰው ሰውን መበዝበዙ ነው፡፡ ሊበራል፣ ኒዮ ሊበራል፣ አብዮታዊ፣ ኮሙኒስታዊ፣ ፋሽስታዊ፣ ቦናፓርቲዝማዊ፣ ልማታዊ፣ ሉአላዊ፣ ፀረ-ሽብራዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ኢጋዳዊ፣ … ሁሉም የሰውና ሰው ተቃርኖና ፍጭት መልኮች ናቸው፡፡ ዋናው ከህዝብና ከሀገር ጥቅም አኳያ ምን ይመስላሉ ተብሎ መመርመር ያለባቸው ናቸው፡፡ የሰውና ሰው ግንኙነት የጨቋኝና ተጨቋኝ፣ የወገናዊና ኢወገናዊ፣ የፍትሐዊና ኢፍትሐዊ፣ ወይስ ቡድናዊና ኢቡድናዊ? ምን ይመስላል፡፡ የሳንቲሙ ገፅ ምን ዓይነት ነው? ዘውድ? ጎፈር? ወይም በሠያፍ የቆመ? መፈተሽ አለበት፡፡
አንዱ ለአመራሩ ሚሥጥር ቅርብ በመሆኑ አስቀድሞ ኢንፎርሜሽን ያገኛል፡፡ ቤቱን ከውርስ ያድናል፡፡ ሌላው ለኢንፎርሜሽኑ እሩቅ ነውና ላዩ ላይ ይታወጅበታል፡፡ ለብዙሃኑ ጥቅም ሲባል ጥቂቶቹ ቢጎዱም ምንም አይደለም የሚለውም አስተሳሰብ መመርመር ይኖርበታል፡፡ የአብዮቱ ጦስ ይሁን የካፒታሊዝም ጦስ ባልለየበት አገር አዋጆችና መመሪያዎች ሲከለሱ ማየት ቢያንስ ያስገርማል፡፡ አቀንቃኙ Protagonist እና ተቃራኙ antagonist በቀላሉ አይለዩም፡፡ ከሥልጣን ይባረራሉ፡፡ ተባራሪዎቹ ያወጡት ህግና መመሪያ ምን እንደሚሆን ዕጣ-ፈንታው አይታወቅም፡፡ ከሁሉም ይሰውረን! ህዝብ ብቻ ግራ እንደተጋባ ይቀጥላል፡፡ “ሰው ይጫኑብህ ግንድ? ቢሉት፤ ግንድ ከተጫነኝ ሰው ያነሳልኛል፣ ሰው ከተጫነኝ ማን ያነሳልኛል፤ አለ” የሚባለው ግራ-ገብ ዘመንን የሚያመላክተን ነው፡፡ ከዚህም ይሰውረን! ከሚጫነን ይገላግለን፡፡ ከወዶ-ገባነት ይቅር ይበለን!!#MinilikSalsawi
አገራችን ኢትዮጵያ ያለችበትን አሳዛኝ ሁኔታ ከማንም የበለጠ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይረዳዋል ብለን እናምናለን። የኢሕአዴግ መንግስት፣ ላያ ላዩን «በዴሞክራሲ አምናለሁ» ቢልም፣ ፍጹም አምባገነን በሆነ መልኩ ፣ ሕዝቡን አፍኖ፣ እያሰራ፣ እየገደለ፣ ዜጎችን እያፈናቀለ፣ ከሃያ አመታት በላይ ቆይቷል። በአብዛኛዉ ሕዝብ ዘንድ እየተጠላ፣ ይሄን ያህል አመት በስልጣን መቆየት የቻለው፣ አገዛዙ በዋናነት ኢትዮጵያዊያን መከፋፈል በመቻሉና ዜጎች ደፍረው ለመብታቸው እንዳይቆሙ በፍርሃት እንዲተበተቡ በማድረጉ ነው። ይሄንን ለማስቆም ሕዝቡን ማስተባበርና ማደራጀት ቀዳሚና ብቸኛ አማራጭ ነው።
አገር ቤት በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ በርካታ የፖለቲካ ድርጅቶ አሉ። ከነዚህ ድርጅቶች መካከል አንዱ የአንድነት ፓርቲ ነው። የአንድነት ፓርቲ «የሚሊዮኖች ድምጽ ለፍትህ» እና «የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት» በሚል ሰላማዊ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ተዘጋጅቷል። ይህ እንቅስቃሴ የአንድ ፓርቲ እንቅሳቅሴ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንቅስቃሴ እንደመሆኑ፣ በአገራችን ዴሞክራሲና የስርዓት ለዉጥ እንዲመጣ የሚፈልጉ ዜጎች ሁሉ ሊቀላቀሉት፣ ሊደግፉት፣ የራሳቸው ሊያደርጉት የሚገባ እንቅስቃሴ ነዉ። ይህ እንቅስቃሴ የሚሊዮኖች እንቅስቃሴ ነው። የእያንዳንዳችን እንቅስቃሴ ነው።
በቅርቡ በባህር ዳር አስደናቂ ሰልፍ መደረጉ ይታወሳል። በቦታዉ የተገኙ ወገኖች ድምጻቸውን ያሰሙት አንድን ፓርቲ ብለው አልነበረም። ኢትዮጵያን ብለው ነዉ እንጂ። የባህር ዳሩ ሰልፉ ያማከለው በአንድ ድርጅት ዙሪያ አልነበረም። ነገር ግን በኢትዮጵያ ዙሪያ እንጂ። ይህ በባህር ዳር የተደረገውን አይነት የነጻነት እንቅስቃሴ በተጧጧፈ መልኩ በመላው አገሪቷ ማድረጉ አስፈላጊ ነው።
በአገሪቷ ሕገ መንግስት አንቀጽ 30 መሰረት፣ የዜጎች የመሰባሰብ ፣ በሰላም ትእይንተ ሕዝብ የማድረግ ሙሉ መብት የተረጋገጠ ነው። በመሆኑም ይህ የሚሊዮኖች ለነጻነት ንቅናቄ ሰላማዊና የአገሪቷ ሕግ በሚፈቅደው መሰረት የሚደረግ በማንም ዜጋ ወይንም ቡድን ላይ ያላነጣጠረ፣ የተወሰኑትን ጠቅሞ ሌላዉን የሚጎዳ ያልሆነ፣ በዘር፣ በሃይማኖት፣ በመደብ፣ በጾታ ልዩነት ሳያደርግ፣ ኢትዮጵያዉያንን በሙሉ ለፍትህና ለነጻነት ለማሰባሰብና ለማንቀሳቀስ ታሰቦ የታቀደ እንቅስቃሴ ነው።
በዳያስፖራ ያለው ማህበረሰብም የኢትዮጵያ ሕዝብ አካል እንደመሆኑ፣ የድርሻዉን መወጣት ይጠበቅበታል። በመሆኑም ይሄን የሚሊዮኖች ድምጽ ወይንም በባህር ዳር የተደረገዉን አይነት እንቅስቃሴ በሌሎች ከተሞች እንዲደረግ ለመርዳትና ለማጠናከር፣ የዳያስፖራ የሚሊዮኖች ድምጽ ግብረ ኃይል ተቋቁሟል። ይህ ግብረ ኃይል በዳያስፖራ ባሉ የአንድነት ፓርቲ ድጋፍ ማህበራት አነሳሽነትና በዉጭ ካሉ የአንድነት ፓርቲ ድጋፍ ማህበራት በተጨማሪ፣ ከተለያዩ የሲቪክ ማህበራት፣ አገር ቤት የሚደረገዉን ሰላማዊ ትግልን በሚደገፉ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሲቪክ ማህበራት ፣ ፓልቶክ ክፍሎችና ግለሰቦች ተባባሪነት፣ «እኛም የሚሊዮኖች አንዱ አካል ነን» እያሉ ቀናና የሚያኮራ ኢትዮጵያዊ ምላሽ እየሰጡ ያሉና ለመስጠትም የተዘጋጁ፣ በአለም ዙሪያ ሁሉ ያሉ ኢትዮጵያዉያንን ለነጻነትና ለፍትህ ለማሰባሰብ የተዋቀረ ነው።
የሚሊየነሞች ንቅናቄ አዲስ አበባ እና ድረደዋ አስተዳደሮችን ጨምሮ፣ በኦሮሚያ የአዳማ፣ የላፍቶና የነቀምቴ ከተሞችን፣ በደቡብ ክልል፣ የአዋሳ፣ የጂንካና የቁጫ ወረዳዎችን፣ በትግራይ ክልል የመቀሌ ከተማን፣ በአማራዉ ክልል ደሴ፣ የወልዲያ፣ ደብረ ታቦር ፣ ደብረ ማርቆስ እና በምእራብ አርማጭሆ የአብርሃ ጅራ ከተማን ፣ በቤኔሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳን ከተማ፣ በጋምቤላ ክልል የ ጋምቤላ ከተማ የሚያዳርስ ይሆናል።
የሚሊየምን እንቅስቃሴን በተመለከተ በየጊዜዉ ወቅታዊ መግለጫ የምንሰጥ መሆናችንን እየገለጽን። በዉጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ እንደከዚህ በፊቱም ታላቅ ድጋፉን እንዲያበረክት በአክብሮት እንጠይቃለን። አገራችን ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ አገር ናት። ለአገራችን መነሳታችን ሊያስከፋ የሚችለው፣ ወይንም ዝምታን ተስፋ ቆርጠን መቀመጣችን ሊያስደስት የሚችለው አምባገነኖችን ብቻ ነው። በሕዝባችን ላይ ግፍ የሚፈጽሙ አይደሰቱ። እንነሳ። የድርሻችንን እንወጣ። ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁን !
በምትኖሩበት ከተማ ተደራጅታችሁ፣ ከዚህ ግብረ ኃይላ ጋር በመስራት በአገር ቤት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ስፖንሰር ማድረግ የምትፈልጉ በሚከተሉት አድራሹ ሊያገኙን ይችላሉ
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !
[email protected]
404- 518-7858
“ዳውድ ኢብሳ ሲሞት ጥሩኝ” በሚል ርዕስ በለጠፍኩት አነስተኛ ሐተታ ላይ ሁለት ዓይነት ተቃውሞዎች ቀርበውብኛል፡፡ አንደኛው “ኦነግ በአማራው ላይ የሰራውን ሴራ እና ሸፍጥ እያወቅክ ጥብቅና ቆመህለታል” የሚለው ሲሆን ሁለተኛው “የኦፒዲኦን ድርጅታዊ ህልውና አንኳሰስክ፤ አቶ አለማየሁንም ረገጥክ” የሚል ነው፡፡ ስለ ኦፒዲኦ የጻፍኩት አዲስ ነገር አይደለም፡፡ የድርጅቱ አባላት እራሳቸው በየአጋጣሚው የሚናገሩትን ነው በፌስቡክ የደገምኩት፡፡ በተለይ ደግሞ አባላቱ ከስራቸው ሲባረሩ፣ ወይ ደግሞ ከድርጅቱ ከድተው ወደ ውጪ ሀገር ሲኮበልሉ “ኦፒዲኦ የኦሮሞን ህዝብ ለማጭበርበር ሆን ተብሎ የተፈጠረ ድርጅት ነው” የሚል ጩኸት በማሰማት ነው የሚታወቁት፡፡ እነ ዮናታን ዲቢሳ፣ ዱባለ ጃሌ፣ ኢብራሂም መልካ ሲያደርጉት የነበረው ይህንኑ ነው፡፡ ነገር ግን እኔ የነርሱን ፈለግ በመከተል አይደለም እንዲያ ብዬ የጻፍኩት፡፡ ከነርሱ በፊትም እንደዚያ ስል ነበር፡፡
——
ኦነግን ለመጀመሪያ ጊዜ ካየሁበት ግንቦት 1983 ጀምሮ የድርጅቱን የፖለቲካ መስመር ስደግፍ ቆይቻለሁ፡፡ ዩኒቨርሲቲ ስገባ ግን ድርጅቱ በሚያራምደው ርዕዮተ ዓለምና በፖለቲካ ፕሮግራሙ ላይ ጥያቄዎች ማንሳት ጀመርኩ፡፡ በዋነኛነትም “የመገንጠል ፖለቲካው የኦሮሞን ጥያቄ የትም አያደርሰውም” የሚል ሀሳብ አነሳሁ፡፡ እንዲሁም የሚከተላቸው ስትራቴጂዎቹ ፍጹም ሊዋጡልኝ አልቻሉም፡፡ በዚህም ከኦሮሞ ወንድሞቼ ጋር ብዙ ጊዜ እነታረክ ነበር፡፡ በተለይም በዚያ ጊዜ ኦነግን መተቸት Taboo ተደርጎ ይቆጠር ስለነበር ከቅርብ ጓደኞቼ ጭምር እስከመጣላት ደርሰናል፡፡ እናም ከ1990 ጀምሮ የድርጅቱ ተቃራኒ እንጂ ደጋፊ አይደለሁም፡፡
እንዲህ በመሆኑ ግን ድርጅቱን በሐሰት መክሰስ ያለብኝ አይመስለኝም፡፡ ድርጅቱን በሰራው ጥፋት ብወቅሰው ማለፊያ ነው፡፡ ባልሰራው ወንጀል መክሰስ ግን ለማንም የሚበጅ አይሆንም፡፡ እንደምሳሌም ኦነግ የሚከሰስባቸውን ጭፍጨፋዎች እንመልከት፡፡ በደኖ፣ አርባ ጉጉ፣ ወተር፣ አረካ፣ አሰቦት ገዳም ወዘተ…
እነዚህ ጭፍጨፋዎች መከሰታቸው ሁላችንንም ያሳዝነናል፡፡ አንድ ቀን እውነቱን ፈልፍለን የማውጣት ግዴታም ተጥሎብናል፡፡፡ ነገር ግን በርካታ ሰዎች በሁሉም ጭፍጨፋዎች ኦነግን ተጠያቂ ሲያደርጉ በጣም እገረማለሁ፡፡ በተለይም ዛሬ በህትመት ላይ የሌሉ ሁለት የግል ጋዜጦች ይህንን ፕሮፓጋንዳ እየደጋገሙ ሲያስተጋቡት ሳይ “ስለ የትኛው ሀገር ነው የሚያወሩት” እያልኩ እደነቅባቸው ነበር፡፡ እንዲህ የምለው ጋዜጦቹ የመረጃ እጥረት የነበራቸው መሆኑን በማወቄ ብቻ አይደለም፤ የጂኦግራፊ እውቀትም ያጠራቸው ስለሚመስለኝም ጭምር ነው፡፡ ለምሳሌ “አረካ”ን እንውሰድ፡፡ ይህቺ ከተማ የት ነው ያለችው? ኦሮሚያ ውስጥ ነው? ወይስ ሌላ ቦታ?
ይገርማል! አረካ ማለት በደቡብ ክልል በወላይታ አውራጃ ከሶዶ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ ያለች ከተማ ናት፡፡ እኔ እስከማውቀው ድረስ ኦነግ እዚያ ድረስ ሄዶ ሀገር አላስተዳደረም፡፡ “አረካ የኦሮሚያ ግዛት ናት” ብሎ የሚያውቅም አይመስለኝም፡፡ እናም ጂኦግራፊን በትክክል የሚያውቅ ጋዜጠኛ የአረካውን ግጭትና ጭፍጨፋ ለኦነግ አይሰጥም ነበር፡፡ በተጨማሪም የአረካው ግጭት የደረሰው ኦነግ የሽግግር መንግሥቱን ለቆ ከወጣና በእጁ የነበሩት መሬቶች በሙሉ በኢህአዴግ ቁጥጥር ስር ከወደቁ በኋላ ነው፡፡
የአረካው ግጭት በሽግግሩ ዘመን ለነበረው የተወካዮች ምክር ቤት የውይይት አጀንዳ ሆኖ እንደቀረበ ይታወሳል፡፡ በከተማዋ ያለቁት የ31 ሰዎች ግድያ በመከላከያ ሰራዊቱ እንደተፈጸመ መንግሥቱ በይፋ አምኗል፡፡ ዳሩ ግን ለግድያው የተሰጠው ምክንያት በጣም አነጋጋሪ ነበር፡፡ መንግሥት ያቀረበው ምክንያት “ሰልፈኞቹ የተገደሉት ቦንብ በመወርወራቸው ሳቢያ የመከላከያ ሰራዊቱ ራሱን ለመከላከል በወሰደው እርምጃ ነው” የሚል ነው፡፡ ይሁንና ይህንን ምክንያት ብዙዎች አልተቀበሉትም፡፡ ብዙዎች እንደተጠራጠሩት እስከ ዛሬ ድረስ ቆይቷል፡፡ በነገራችን ላይ በአረካ የሞቱት የቀድሞ መንግሥት ወታደሮች ነበሩ፡፡ እነዚያ ወታደሮች “የጡረታ መብታችን ይከበርልን” በማለት የተቃውሞ ሰልፍ በማድረጋቸው ነው ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር የተጋጩት፡፡
——–
በሚያዚያ ወር 1984 በወተር ከተማ በተካሄደ ጭፍጨፋ የሞቱትም በተመሳሳይ መልኩ በመከላከያ ሰራዊቱ እንደተገደሉ የሽግግር መንግሥቱ በወቅቱ አምኗል፡፡ ይሁን እንጂ በወተር የተገደሉት 230 ሰዎች በሙሉ ኦሮሞዎች እንጂ አማራዎች አልነበሩም፡፡ እነዚያ ሰዎች የተገደሉት ኢህአዴግ ከከተማቸው ወጥቶ ኦነግ ወደ ከተማዋ እንዲመለስ በመጠየቃቸው ነው (ወተር ለአንድ ዓመት ያህል በኦነግ ቁጥጥር ስር ነበረች፤ ኦነግ ከከተማዋ ሲወጣ ኢህአዴግ ገብቶባታል፤ ነዋሪዎቹ “እንደ ቀድሞው ጊዜያችን ኦነግ ወደ ከተማዋ ይመለስ” በማለታቸው ነው ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር የተጋጩት)፡፡ ጋዜጦቹ ግን “ኦነግ አማራዎችን ጨፈጨፈ” እያሉ ነበር የሚዘግቡት፡፡
——-
በ1984 (ወሩን አላስታውሰውም) በአሰቦት ገዳም በተካሄደ ግድያ ሰባት መነኮሳት ሞተዋል፡፡ ይህንን ግድያ የፈጸሙትም በወቅቱ የአሰቦት ከተማን ለትንሽ ጊዜ ተቆጣጥሮ የነበረው የኦሮሞ ነጻነት እስላማዊ ግንባር (IFLO) ታጣቂዎች ነበሩ፡፡ ግድያው ስር ሳይሰድ በአፋጣኝ ያስቆሙት ደግሞ ኢህአዴግና ኦነግ ነበሩ፡፡ ሁለቱ ድርጅቶች አንድ ጥምር ኮሚቴ በማቋቋም በወሰኑት ውሳኔ መሰረት IFLO ከከተማው ተባርሮ አካባቢው በኢህአዴግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል፡፡
——
በአርባ ጉጉ የተፈጸመው እልቂት በሁለት ተጎራባች መንደሮች መካከል በተካሄደ ግጭት ነበር የተለኮሰው፡፡ እያደር ግን መርቲ ጀጁ እና አሰኮ የሚባሉ የአርባ ጉጉ ወረዳዎችን አዳርሷል፡፡ በግጭቱ የኦሮሞ እና የአማራ ተወላጆች በእኩል ደረጃ ተጎድተዋል፡፡
በአርባ ጉጉ ግጭት የራሳቸውን የፖለቲካ ትርፍ ለማጋበስ የፈለጉ ወገኖች እጃቸውን አስገብተውበታል ይባላል፡፡ በመሆኑም በውጤቱ ከሁሉም ግጭቶች የከፋ ሊሆን ችሏል፡፡ በዚህ ግጭት ከሁለቱም ወገን እስከ ስድስት መቶ ያህል ሰዎች መሞታቸው ይነገራል፡፡ ከመቶ ሺህ ያላነሰ ሰው ወደ ሀረርጌና ሸዋ ክፍለ ሀገሮች ተፈናቅሏል፡፡ ሆኖም ኦነግ በዚህ ግጭት ውስጥ እጁን ማስገባቱን የሚያረጋግጥ ፍንጭ እስከ አሁን ድረስ የለም፡፡ ኦነግ በወቅቱ በአርባ ጉጉ አውራጃ ምንም ይዞታ አልነበረውም፡፡ የመላው አማራ ህዝብ ድርጅትም ቢሆን በግጭቱ የከሰሰው ኦህዴድን (OPDO) እንጂ ኦነግን አልነበረም፡፡ በተለይም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የምዕራብ ሸዋ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ የነበረው ኮሎኔል ዲማ ጉርሜሳ ከግጭቱ ጋር ተያይዞ ስሙ በሰፊው ይነሳ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ በዚያን ጊዜ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ሐሰን ዓሊ ከእፎይታ መጽሔት ጋር (ግንቦት 1985) ባደረጉት ቃለ-ምልልስ “አቶ ዲማ ጉርሜሳ ንጹሕ ነው” በማለት ከመከላከላቸውም በላይ ለግጭቱ ዋነኛ ተጠያቂ ያደረጉት መአሕድን እንጂ ኦነግን አልነበረም፡፡
የግል ጋዜጦች ግን ነገሩን አራግበው በኦነግ ላይ አላከኩት፡፡ ነገሩን ሳያውቁት ቀርተው የተደረገ አይመስለኝም፡፡ አንዳንድ ጋዜጦች -ተከፍሎአቸው እንዲህ እንደሚያደርጉ በደንብ እናውቃለን፡፡
——–
የበደኖ ጭፍጨፋ! አዎን! ኦነግ ሊጠየቅበት የሚገባው ብቸኛው ትራጄዲ ይህኛው ነው፡፡ በርግጥም እልቂቱ በተፈጸመበት ወቅት በደኖ በኦነግ ቁጥጥር ስር ነበረች፡፡ የሞቱት ሀምሳ ያህል ሰዎች ለምን እንደተገደሉ ባይታወቅም አድራጎቱ በኦነግ ወታደሮች እንደተፈጸመ ድርጅቱ ራሱ አምኗል፡፡ ኦነግ በወቅቱ በወታደሮቹና በአዛዦቹ ላይ እርምጃ ወስጃለሁ ቢልም የተወሰደውን እርምጃ ምንነት አልገለጸም፡፡ በነገራችን ላይ በዚህኛውም እልቂት ከሞቱት መካከል ግማሽ ያህሉ ኦሮሞዎች ነበሩ፡፡
—–
ከላይ በዝርዝር እንዳስረዳሁት የኦነግ ጭፍጨፋ ተብለው ከሚጠቀሱ ትራጄዲዎች መካከል አብዛኛዎቹ በኦነግ የተፈጸሙ አልነበሩም፡፡ ኦነግ ሊጠየቅበት የሚገባው ብቸኛው ድርጊት በበደኖ የተፈጸመው ነው፡፡ የእውነት ቀን ሲመጣ ያንን ፋይል ማውጣታችንም አይቀሬ ነው፡፡ ይሁንና በኦነግ ያልተፈጸመውን ከርሱ ጋር አያይዞ መጻፍ ጥቅሙ ምን እንደሆነ ሊገባኝ አይችልም፡፡ እንዲያውም የያኔዎቹ የግል ጋዜጦች የሚያራግቡት ወሬ በተወሰነ መልኩ የኦነግ ጨካኝነትን ከመግለጽ ይልቅ “ኦሮሞ ጨካኝ ነው” የሚል እድምታ ለመፍጠር የታለመ ነበር የሚመስለው፡፡
እርግጥ የኦነግ ወታደሮች በብዙ አጋጣሚዎች ልዩ ልዩ የጭካኔ ተግባራትን ሲፈጽሙ ተስተውለዋል፡፡ እርሱን አንክድም፡፡ የነርሱ ገፈት ቀማሽ ሆኖ የዘለቀው ግን በአብዛኛው ኦሮሞው ነው እንጂ የሌላ ብሄረሰብ ተወላጅ አልነበረም፡፡ በተለይ አንዳንዶቹ የኦነግ ወታደሮች “ጎበና፤ ቢተምቱ.፤ ወዘተ..” ለሚሏቸው ግለሰቦች ምህረት አልነበራቸውም፡፡ እንዲሁም ተጻራሪ ድርጅት ሊያቋቁሙ ነው በሚል ፍርሃት አባላቶቻቸውን ጭምር እስከ መግደል ይደርሱ ነበር (የኦነግ የሀረር ቢሮ ሃላፊ የነበሩትን አቶ አራርሶ ወዳይን እና በመቻራ ከተማ የተገደለውን የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ካሊድ ሃጂ ኑራን መጥቀሱ ይበቃል)፡፡ ሆኖም ጋዜጦቻችን ድርጅቱ የፈጸመውን ማውራት ይተውና ድርጅቱ ያልፈጸመውን ወንጀል ይነግሩን ነበር! ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ማለት ይህ ነው፡፡
ለማጠቃለል ያህል እኔ ለኦነግ አልተከላከልኩለትም፡፡ አንዳች ጥብቅና አልቆምኩለትም፡፡ የጻፍኩት የማውቀውን ሐቅና የማምንበትን አቋሜን ነው፡፡ ይሁንና ይህ አባባሌ ኦነግን ከመፍራት እንዳይወሰድብኝ አደራ እላለሁ! አስፈላጊ ከሆነ በኦነግም የተፈጸሙ ስህተቶችና ጥፋቶችን አንድ በአንድ መዘርዘር እችላለሁ፡፡
ሰናይ ቀን ይሁንላችሁ!!
[ውንብድና ካርቱም በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ]
ሁዳ የሚባል እስር ቤት 35 ጠያቂ የሌላቸው እስረኞች ይማቅቃሉ – አብርሃ ደስታ ከመቀሌ
በዓለም ዉድድር አለ። ዉድድሩ በህዝቦች መካከል ነው። ህዝቦች ዉድድሩን ለማሸነፍ አብሮነትን ይፈልጋሉ። በአብሮነት የራሳቸው ደህንነትና ጥቅም ማስከበር ይሻሉ። ደህንነታቸውንና ጥቅማቸው ለማስከበር ሀገር ይመሰርታሉ። ሀገር መስርተው በመንግስት ይወከላሉ። የመንግስት ተግባር ታድያ የህዝቡን ጥቅምና ደህንነት መጠበቅ ነው። በዚሁ መሰረት መንግስት የህዝቦች ተወካይ ጠበቃ መሆን ይጠበቅበታል።
የህዝቦች ወኪል (ጠበቃ) ለመሆን መንግስት በተለያዩ ሀገሮች ኤምባሲ ይከፍታል። የኤምባሲው ሰራተኞች የሚወክሉትን ህዝብ ጥቅምና ደህንነት ይጠብቃሉ፣ ያስጠብቃሉ። ለዚሁ ተግባራቸው ሲባል ህዝብ ደሞዛቸውን ይከፍላቸዋል። ደሞዛቸው የሚከፈላቸው ከመንግስት ካዝና ነው። የመንግስት ገንዘብ የሚሰበሰበው ከህዝብ ነው፤ በግብር መልክ።
ካርቱም የሚገኙ ጓደኞቼ እንደላኩልኝ ከሆነ የኢትዮጵያ ኤምባሲ (በካርቱም) ሰራተኞች በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ተግባር ተሰማርተው ኢትዮጵያውያንን አደጋ ዉስጥ እየጣሉ ይገኛሉ። የሰዎች ደህንነት ከመጠበቅ ይልቅ ሰዎችን አደጋ ዉስጥ ማስገባት ምን ይሉታል? የመንግስት አካላት ወንጀልን ከመከላከል ይልቅ ቁማርተኞች ሲሆኑ ምን ማድረግ ይቻላል?!
የኢትዮጵያ መንግስትም (መንግስት ልበለው) ከህዝብ ኪስ የሚከፈሉ የኤምባሲ ሰራተኞች አሉት። በተለያዩ ሀገሮች ያሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች በህዝብ ገንዘብ እየተዳደሩ የሚከፍላቸውን ህዝብ የሚበድሉ መሆናቸው እናውቃለን። ዛሬ ትኩረቴ የሳበ ግን በካርቱም ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነው።
የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች ሱዳን ዉስጥ የሚቸገሩ ዜጎቻችንን ደህንነት ከመከታተል ይልቅ ከሱዳን መንግስት ጋር በመተባበር ኢትዮጵያውያን እስርቤት ይከታሉ። እስካሁን ድረስ በሱዳን ብዙ ኢትዮጵያውያን ያለ ምንም ጠያቂ በወህኒቤቶች እየማቀቁ ነው። የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች በሱዳን ሀገር የሚደርስባቸው ችግር፣ እስር፣ እንግልት እያወቁ በሰዎች ንግድ መሰማራታቸው ይገርማል። የኤምባሲው ሰራተኞች በሀገራቸው ሰዎች ንግድ ነው የተሰማሩ።
በሱዳን ያሉ ኢትዮጵያውያን መንግስት እንደሌላቸው (መንግስት አልባ እንደሆኑ) ነው የሚቆጠረው። “ሑዳ” በሚባል ወህኒቤት 35 ጠያቂ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን አሉ። እነዚህ እስረኞች ያለ ምንም የፍርድቤት ዉሳኔ የተያዙና ከ8-12 ዓመት በወህኒቤቱ የቆዩ ናቸው። ተሰቅለው የተገደሉም መዓት ናቸው። በሱዳን የኢትዮጵያውያን ህይወት ርካሽ ነው። መስከረም አያሌው የተባለችም በሰባት ሱዳናውያን መደፈሯ ይታወሳል።
ኢትዮጵያውያን መንግስት አልባ (stateless) ሁነው ሲሰቃዩ የኤምባሲው ሰራተኞች ግን ሰዎች እየገዙና እየሸጡ (በሰዎች ንግድ ተሰማርተው) ገንዘብ ይሰበስባሉ። ዘመናዊ መንግስታዊ የንግድ ባርያ መሆኑ ነው።
ኢትዮጵያውያን ክብራችንን የምናስመልስበት ግዜ ሩቅ አይሆንም። አቶ መሐመድ ቱፋና አቶ በላቸው ግን ተግባራቹሁ ሁሉ እየተከታተልነው እንገኛለን።

በርካታ ሀገራዊ ቁምነገሮችን ይዛ በገበያ ላይ ውላ የተነበበችውን “ነገረ ኢትዮጵያ “ ቁጥር 3 ዕትም እንሆ በ PDF
በ ፒዲኤፍ (PDF) ለማንበብ ይሄን ይጫኑ
ነገሩ የሆነው አዋሳ ዩኒቨርሲቲ ነው። ቆነጃጅት ወጣት ሴት ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውጭ ባሉ የከተማው ደለላዎች ጋር በመተባበር እጅግ ዘግናኝ ስራ ይሰራሉ። ደላሎቹ የቆነጃጅቶቹን ተማሪዎች ፎቶ የያዘ ትልቅ ካታሎግ ይዘው ከአዲስ አበባም ሆነ ከአቅራቢያው ከተሞች አለዚያም ከዚያው ከአዋሳ ከተማ ብቅ የሚሉ ሃብታም ደንበኞቻቸውን የተማሪ ኮረዶችን ፎቶ በመስጠት ያስመርጣሉ። ሰውየው ውብ ወጣት ተማሪ ኮረዳ እንደሚፈልግ በሰው […]
አገራችን ኢትዮጵያ ያለችበትን አሳዛኝ ሁኔታ ከማንም የበለጠ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይረዳዋል ብለን እናምናለን። የኢሕአዴግ መንግስት፣ ላያ ላዩን «በዴሞክራሲ አምናለሁ» ቢልም፣ ፍጹም አምባገነን በሆነ መልኩ ፣ ሕዝቡን አፍኖ፣ እያሰራ፣ እየገደለ፣ ዜጎችን እያፈናቀለ፣ ከሃያ አመታት በላይ ቆይቷል። በአብዛኛዉ ሕዝብ ዘንድ እየተጠላ፣ ይሄን ያህል አመት በስልጣን መቆየት የቻለው፣ አገዛዙ በዋናነት ኢትዮጵያዊያን መከፋፈል በመቻሉና ዜጎች ደፍረው ለመብታቸው እንዳይቆሙ በፍርሃት እንዲተበተቡ […]
በዴሞክራሲያዊ መንገድ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ህገመንግስታዊ መብቴን ጥሰውብኛል ሲል አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ክስ የመሰረተባቸው ሶስት የመንግስት ተቋማት በትናንትናው ዕለት በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 8ኛ ፍትሃብሔር ችሎት ቀርበው መቃወሚያቸውን አሰሙ። ፓርቲው ክስ የመሰረተባቸው የአዲስ አበባ ከንቲማ ጽህፈት ቤት ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የአዲስ አበባ ፖለስ ኮሚሽን ሲሆኑ በጠበቆቻቸው በኩል የክስ መቃወሚያቸውን በፍ/ቤቱ አቅርበዋል። […]
አትክልት አሰፋ (ቫንኩቨር)
ነገሩ የሆነው ዲላ ዩኒቨርሲቲ ነው። ቆነጃጅት ወጣት ሴት ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውጭ ባሉ የከተማው ደለላዎች ጋር በመተባበር እጅግ ዘግናኝ ስራ ይሰራሉ። ደላሎቹ የቆነጃጅቶቹን ተማሪዎች ፎቶ የያዘ ትልቅ ካታሎግ ይዘው ከአዲስ አበባም ሆነ ከአቅራቢያው ከተሞች አለዚያም ከዚያው ከዲላ ከተማ ብቅ የሚሉ ሃብታም ደንበኞቻቸውን የተማሪ ኮረዶችን ፎቶ በመስጠት ያስመርጣሉ።
«ሃኪምዎን ይጠይቁ» በተከታታይ በሚያቀርባቸው ቅንብሮች፤ ሱስ በአንጎልና በባሕሪ ላይ የሚያሳድረውን ጫና እና የጤና ጉዳቶች፤ እንዲሁም የሕክምና አማራጮች ይመለከታል።
በህክምናው አነጋገር በእንግሊዝኛ Dependancy በመባል የሚታወቀው የጤና ሁኔታ ምንነትና ዓይነተኛ ጠባይም ይመረምራል።
በሱስና በአንጎል አሠራር ላይ ለሚያተኩሩት ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡት በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ በአሪዞና ክፍለ ግዛት ሜዮ ክሊኒክ፥ የነርቭና የአዕምሮ ሕክምና ባለሞያው ዶ/ር ዮናስ እንዳለ ገዳ ሲሆኑ፤ በተለይ ሱሰኝነትንና ባሕሪን አስመልክቶ በቀረቡ ጭብጦች ዙሪያ ሞያዊ ትንታኔ የሚሰጡት ደግሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው የአእምሮ ሃኪሙ ዶ/ር አታላይ ዓለም ናቸው።
ዘወትር ቅዳሜ ማታ ከደሳለኝ መኮንን ጋር፣ምርጥና አዳዲስ የካንትሪ ማለትም የአሜሪካ አገር ሰብእ፣ የሮክ፣ተሶል፣የፖፕ፣የአር-ኤን-ቢ፣ብሉዝ፣የሬጌና የሂፕ-ሃፕ ዜማዎችን እንዲያደምጡ ተጋብዘዋል።
ከሰባት መቶ የንግድ መደብሮች በላይ ባወደመዉ እሳት በብዙ መቶ ሚሊዮን ብር የሚገመት ኪሳራ ደርሷል
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ የትምህርት ክፍል በተማሪዎች ብዙም የማይመረጥበት ሁኔታ የትምህርት ዘርፉን ሕልዉና ሳይፈታተን እንደሚይቀር እየተገነገረ ነዉ።
ባለፈው ዓመት ፣ የዩናይትድ ስቴትስና የብሪታንያ የስለላ ድርጅቶች ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ የድርጅቶችን ፣ የግለሰቦችን የታወቁ የሀገር መሪዎችን የግል ተንቀሳቃሽ ስልኮች የድምጽ፤ የጽሑፍና ስዕል አገልግሎት ጭምር ይጠልፉ ነበር ተብሎ፣ ዜናው በዓለም
ፕሬዝዳንት ኪር ባለፈዉ ታሕሳስ በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሐላፊዎችን ከመንግሥት እኩል ሐገር ለመምራት ይሞክራሉ በማለት ወንጅለዋቸዉ ነበር።በቀደም ጁባ ዉስጥ ለተሰለፉት ወጣቶች ንግግር ያደረጉት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄምስ ዋኒ ኢጋ የአለቃቸዉን አባባል ደገሙት
የአፍጋኒስታን ምርጫ ከመካሄዱ አንድ ወር በፊት ታዛቢዎች በዚህ አጋጣሚ ለፉክክር የሚቀርቡ 11 እጩዎች ሶስቱ የሕዝቡን ቀልብ እንደያዙ ያመለክታሉ። የፕሬዝደንት ሃሚድ ኻርዛይ ወንድም ቃዩም ኻርዛይ ከፉክክሩ ራሳቸዉን አግልለዉ የቀድሞ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩትን ዛልማይ ራሶልን እንደሚደግፉ ገልጸዋል።
በማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ በቀድሞ የሴሌካ ሙሥሊም ዓማፅያን አንፃር የሚንቀሳቀሱት ራሱን ፀረ ባላካ ብሎ የሚጠራ የወጣት ክርስትያን ሚሊሺያ ቡድን አባላት ሽብራቸውን አስፋፉ። ሚሊሺያዎቹ ሙሥሊሞቹን ዜጎች መግደል ብቻ ሳይሆን
በጀርመናዊቷ የሀኖፈር ከተማ ባለፈው እሁድ የተከፈተው እና አምስት ቀናት የሚቆየው ትልቁ የኮምፒውተር ትርዒት የመረጃ ቴክኖሎጂን አጠባበቅ እንዴት አስተማማኝ ማድረግ ይቻላል ለሚለው ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ የትምህርት ክፍል በተማሪዎች ብዙም የማይመረጥበት ሁኔታ የትምህርት ዘርፉን ሕልዉና ሳይፈታተን እንደሚይቀር እየተገነገረ ነዉ።
የዕለቱ ዜና
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ !

ለኢትዮጵያ የዛሬ አርባ አመት ነው አዲስ ህይወትና ምዕራፍ የተከሰተው፡፡ ሆኖም 1966 ዓ.ም የነገሮች ሁሉ መነሻ አልነበረም፡፡ በዛች ወቅትና አመት በተከሰተው ሁኔታ ብቻ አይደለም ወጣቱ ህይወቱን ለመስጠት የተሰናዳው፡፡ ነገር ግን የአብዮት መፈንዳት የእያንዳንዳችን የውስጥ ስሜት ስለነካ ይመስለኛል፡፡ ለዚህም ምሳሌ የማደርገው ራሴን ነው፡፡ ማህበረሰብ እንዲለወጥ የአንድ ጊዜ የጋራ እርምጃ ሳይሆን የተጠራቀመ ነገር ያስፈልገዋል፡፡ በወቅቱ ወደ 11ኛ ክፍል አልፌ ነበር፡፡ እኔ እኖር የነበረው ከአዲስ አበባ ውጭ ፍቼ ከተማ ነው፡፡ ይህም ለገጠሩ ህዝብ ቅርብ እንድሆን አድርጎኛል፡፡ ቤተሰቦቼ የሀይማኖት ሰዎች ናቸው፡፡ አባቴ ቄስ ነው፡፡ የአባቴ ወንድሞች፣ የአባቴ አባት፣ የእናቴ ወንድሞች፣ የእናቴ አባት…ብዙዎቹ ቄስና የሀይማኖት ሰዎችና ቤተሰብ ነበሩ፡፡ እንደሚታወቀው በነበረው ስርዓት የቤተ ክርስትያን ሰዎችና የመንግስት አስተዳደር ቅርብ ነበር፡፡ በመሆኑም እኔም ለሀይማኖት ቅርበት ነበረኝ፡፡ ቅረበቴ ግን ለእኔ የሰጠኝ ከስርዓቱ ጋር መሳሳብና መዋደድ አልነበረም፡፡ እኔ የቄስ ልጅ እንደመሆኔ የሀብታም ልጅ አልነበርኩም፡፡ (መቼም ዛሬ ካልሆነ ቄስ ሀብታም ሆኖ አያውቅም፡፡)
ለቤተ-ክርስቲያን ቅርብ ስትሆኑ ለጪሰኛውና ለመሬት ቅርብ ትሆናላችሁ፡፡ ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን ‹‹እኩል ከእርስት›› የሚባል ነገር ስለነበራት ነው፡፡ እኔ ቤት ባይሆንም የአባቴ ቤተሰቦች ቤት ይህን ስርዓት በግልጽ ማየት ችያለሁ፡፡ ገና 6ኛ እና 7ኛ ክፍል ሆኜ ጭሰኞች ከገጠር እህል ሲያመጡ፣ ግብር ሲበላ፣ ድግስ ሲደገስ፣ ሲስተናገድ (እንዴት ህዝብ በየ ደረጃው ይስተናገድ እንደነበር) በቅርብ ማየት ችያለሁ፡፡ በነገራችን ላይ ገና 6 እና 7ኛ ክፍል ሆኜ ይመስለኛል ፍቅር እስከ መቃብር የታተመው፡፡ ፍቅር እስከ መቃብርን አነበብኩ፡፡ ፍቅር እስከ መቃብር ላይ የፊውዳልና የጭሰኛውን ግንኙነት ሳነብም በስርዓቱ የተማረርኩት እኔ ብቻ አለመሆኔን አመንኩ፡፡ ፍቅር እስከ መቃብር ለልቤ ጥያቄ መልስ ሰጠኝ፡፡ ከእኔው ውጭ ሌሎች ሰዎች እንደሚከፋቸው ማየት ችያለሁ፡፡ ከዛ በፊት ግን የጭሰኞችን ግንኙነት አይቻለሁ፡፡ አንድ ሰው ሁለት አጥር ይኖረዋል፡፡ ጭሰኞች የውስጠኛውን አጥር ከመግባታቸው በፊት ማደግደግና፣ አጋሰሶቻቸውን ማራገፍ አለባቸው፣ እህሉን ተሸክመው ለመግባት፡፡
6ኛ ክፍል ሆኜ ትምህርት ቤት ስሄድ ትንሽ ልጅ የሚመራቸው አንድ መንገድ ዳር ላይ የሚለምኑ ሽማግሌ ነበሩ፡፡ እናም በዛች ትንሽ ጭንቅላቴ ብዙ አስብ ነበር፡፡ ጭሰኞቹ ሲያረጁ እንደዚህ ሰውዬ እንደሚሆኑ አስብ ነበር፡፡ ምክንያቱም ያፈሩትን እየሰጡ ነው፤ ሲያረጁ ደግሞ ከመሬታቸው ይነሳሉ፡፡ እናም ግን ለምን? ግን ለምን? ግን ለምን? የሚል ጥያቄ በብዛት በአዕምሮዬ ይመላለስ ነበር፡፡ ፍቅር እስከ መቃብርን እንዳገኝና እንዳነብ ያደረገኝ ወንድሜ ስለ ችግሮቹ እንድጽፍ ያደርገኝ ነበር፡፡ የተሰማኝን መጻፍ ጀመርኩ፡፡
እስከ 9ኛ ክፍል እስክደርስ ድረስ ሶስትና አራት ባለ 50 ገጽ ደብተር ጻፍኩ፡፡ በ1966 የጻፍኳቸውን ደብተሮች ብቻ ይዤ አዲስ አበባ በመምጣት ንግድ ስራ ትምህርት ቤት ገባሁ፡፡ በ1967 ዘመቻ መሄድ ነበረብኝ፡፡ ዘመቻ እንደሄድኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ያነበብኩት የማኦን ስለ ጭሰኞች የሚያወራ ‹‹The peasant uprising›› የሚለውን መጽሃፍ ነበር፡፡ ውስጤ ያለውን የሚነካ ነገር ተፈጠረ፡፡ ይህ ነገር (አብዮት) ያስፈልገናል ብዬ አመንኩ፡፡ የቄስ ልጅ፣ አክራሪ ኦርቶዶክስ ነበርኩ፡፡ ሆኖም በዘመቻው ወቅት በመጾምና ባለመጾም ተፈትኛለሁ፡፡ ወጣት ስትሆኑ ደግሞ አዲስ ነገር መቀበልና መሆን አለባችሁ፡፡ በሶሻሊዝም መጾም የለም፣ እንዲያውም በሶሻሊዝም ስም ማረድ (መባረክ) አለብን ሁሉ ይባል ነበር፡፡ በዚህ ጉዳይ ለ6 ወር ያህል ተፈትኛለሁ፡፡ በኋላ ተሸነፍኩና ተቀላቀልኩ፡፡ ስለ ኮምኒዝም የሰማሁት 7ኛ ክፍል ሆኜ ነው፡፡ ስለቻይና ሶቬት አብዮት ነው፡፡ ኮሚኒስት ከሆንን መኪና የለም፣ ቤት የለም፣ ሱፐር ማርኬት ሄዶ መግዛት የለም፣ በካርድ ብቻ መግዛት ነው የሚል ነው፡፡ ይህ ለእኔ በውስጤ የነበር ነው፡፡ የማኦ መጽኃፍና ሌሎች መጽሃፎች ሲጨመሩ ሶሻሊዝም ለኢትዮጵያ እንደሚያስፈልጋት አመንኩ፡፡ ይህ መነሻ ሆኖ ዘመቻ ጣቢያ እያለሁ ዴሞክራሲያን ሳነባት ደግሞ ይበልጡን አመንኩበት፡፡ እንዲያውም ዴሞክራሲያን የሚጽፉት ሰዎች መላዕክት ይመስሉኝ ነበር፡፡ እስከዚያ ድረስ የሚመስጥ ጽሁፍ ነበር፡፡ ያ መመሰጥ ውስጤ ከነበረው መመሳሰል ጋር በመመሳሰሉ ነው ኢህአፓ ውስጥ ያስገባኝ፡፡ ማንም ቀስቅሶኝ አይደለም፡፡ እኩል ተቀስቅሰን እኩል መሄድ አልቻልንም፡፡ እኩል እንደ እኔ ቢቀሰቀሱም ከዘመቻ ተመልሰው ትምህርታቸውን የቀጠሉና ሌላ አቅጣጫን የመረጡ ነበሩ፡፡ ስለዚህ ውስጤ ያለውን ነገር ስለነካ ነው ገብቼ የቀረሁት፡፡ ባላምንበት ኖሮ ከተቀሰቀስኩ በኋላ ቤት ስመለስ በተውኩት ነበር፡፡
1966 አብዮት በእኔ ምሳሉ ሳየው ድንገተኛ አልነበረም፡፡ የካቲት ወር በአንድ ሰልፍ ዩኒፎርም ለብሰን መንገድ ላይ ስንወጣ ‹‹እንኳን ደስ አላችሁ!››፣ ‹‹እንኳን ጀግና ሆናችሁ!›› እንባል ነበር፡፡ ነባራዊ ሁኔታው፣ የኑሮ ውድነት (ከዛሬው ጋር የሚወዳደር አልነበረም) አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ አባቴ በርካታ ቤተሰብን በ80 ብር ማስተዳደር ይችል ነበር፡፡ የዛን ጊዜና የአሁኑን ማመሳሰል አይቻልም፡፡ የተወደደው ቅቤ ሳንቲም ጨምሮ 3 ብር፣ ዘይት ሁለት ብር፣ ጤፍ 50 ብር ይሸጥ ነበር፡፡ የ1966ቱ የኑሮ ውድነት ከዛ በፊት ከነበረው ርካሽ ኑሮ ጋር የሚነጻጸር ነው፡፡ ከድሮው ጋር ሲነጻጸር የኑሮ ውድነቱ እሳት እንደነደደ ይቆጠራል፡፡ ያ የምርት ግንኙነት፣ ማህበራዊና ስነ ልቦናዊ ችግር ጋር ሲደማመር እንጅ ወታደሩና ተማሪው ስለተሰለፈ ብቻ የመጣ አይደለም፡፡ ያን ሁኔታ ወደ አንድ ሁኔታ (አብዮት) ለመቀየር፣ የታክሲ ሾፌሮች፣ የወታደሩ የደሞዝ ጭማሬ፣ የሴክተር ሪቪው ተጨምሮበት 1966ን የኢትዮጵያ አንድ ምዕራፍ አደረገው፡፡ ስርዓቱ ጠንቃቃ ባለመሆኑና ብዙ ስላልተሰራ ነው አብዮቱ የፈነዳው፡፡ አሁን እኮ እየተመለስን ያለነው ወደ ካፒታሊዝም ነው፡፡ ስርዓቱ ጠንቃቃ ቢሆን ያለምንም ውጣ ውረድ የተሳካ ስርዓት በገነባን ነበር፡፡ የከፈልነው መስዕዋትነት የማይገባ ነበር፡፡
በዘመቻው ወቅት ከአዲስ አበባ ወጥተን ገጠር በመግባታችን ለማንበብም ሆነ ለህዝብ ቅርብ መሆን ችለናል፡፡ ውስጣችን የነበረውን እምነት የቀየረው ይህ ነው፡፡ ወጣቱም አንዴ ከተነሳ መመለስ ያቃተው ለዚህ ነው፡፡ ኢህአፓ ውስጥ ስገባ ያጋጠመኝ ነገር ደግሞ በፊት ከማስበው የተለየና እምነቴን ያሳደገልኝ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች እንደ ሰው አይደሉም የሚለውን እምነቴን አጠናክሮልኛል፡፡ በወጣት ማህበራት እንገናኝ ነበር፡፡ የፓርቲው ሳይሆን ኢህአወሊ (የወጣት ማህበሩ) አባል ነበር፡፡ ኢህአወሊ ራሱን የቻለ ፓርቲ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ከወጣት ሊጉ ከገባሁ በኋላ ሀይለኛ ስብዕና አግኝቻሁ፡፡ ከዛ በፊት የነበረኝ አላማ ዩኒቨርሲቲ መግባት የዩኒቨርሲቲ መምህር፣ ፕሮፌሰር ሆኜ የምሁር ህይወት መኖር ነበር፡፡ ያ ሁሉ ህልሜ ቀርቶ ከዘመቻ ስንመለስ ‹‹ከትግል በኋላ ትምህርት›› የሚለው የወጣት ሊጉን መፈክር ይዘን ትግል ገባን፡፡ ትግሉ እየከረረ መጣ፡፡ ደም በደም ሆነ፡፡ የመጀመሪያው ደም በሚኒስትሮቹ ጀመረ፡፡ በእነሱ የተጀመረው ግድያ ወደ ሌላ ግድያ ተቀየረ፡፡
ኢህአፓ ውስጥ ከገባን በኋላ የሰዎቹ መልካምነት፣ እድገት በህብረት ሄጄ የዩኒቨርሲቲ ካየሁ በኋላ ባገኘኋቸው ተማሪዎች ስብዕና በማየቴ ከውስጤ ነው ያመንኩት፡፡ ምክንያቱም ኢህአፓ የውስጣችን ስሜት ነው የነካው፡፡ ፓርቲ ውስጥ ያየሁት ደግሞ ይበልጡን ልቤን የሚሞላ ነበር፡፡፡ ለራሳችን መኖርና ስብዕናችንን መጠበቅ እንዳለብን፣ ነገር ግን ቅድሚያ ለህዝብ እድንኖር በተግባር አስተምረውናል፡፡ ኢህአወሊ እያለሁ አንድ ሰልፍ ነበር፡፡ ለማምለጥ ስንሮጥ አንድ ሰፈር ውስጥ የተደረመሰ ሽንት ቤትና ውጭ ደግሞ የሚመጥ የቆመ መኪና ላይ ደረስን፡፡ በዚህም ምክንያት አስም ተቀሰቀሰብኝ፡፡ ትንሽ እንደሄድን መራመድ አቃተኝና ተቀመጥኩ፡፡ ሌላው እየሮጠ አንድ በእድሜ የሚበልጠኝ ሰው ቆሞ ይጠብቀኛል፡፡ ‹‹ለምንድን ነው የቆምከው? አምልጥ!›› ስለው ‹‹ለምን ጥየሽ እሮጣለሁ? ይልቁን ጥቂት እርጅኝና ጥግ አስይዤሽ እሄዳለሁ›› አለኝ፡፡ ጥይት እየተተኮሰ እኔን ይጠብቃል፡፡ ይህ ድርጅቱ ለእኔ እንደሚቆም ማወቅ ስላስቻለኝ ብርታት ሰጥቶኛል፡፡ አስሙ እየባሰብኝ ሲሄድ ባልጠበኩት ሁኔታ የአስም መድሃኒት ተላከልኝ፡፡ ይህኛውም ሌላ ጉልበት ነበር፡፡
ሌላ ጊዜ ደግሞ አዲስ አበባ ላይ መኖር ከባድ ሆነ፡፡ ወደ አሲምባ ለመሄድም አይቻልም ነበር፡፡ ናዝሬት ላይ አንድ ቤዝ ሊቋቋም ነበር፡፡ ያኔ ከእኛ ሰፈር ሶስት ወጣቶች ወደ ቤዙ ሊሄዱ ነበር፡፡ ግን መድረስ ባለመቻላቸው ተመልሰው መጡ፡፡ ከተመለሱ በኋላ ታሰሩ፡፡ ልጆቹ በመታሰራቸው ለእኔ ሂስ መጣልኝ፡፡ ቁጭ ብየ አነበብኩት፡፡ ሂሱም ልጆቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በሚተዋወቁት ሰዎች መካከል ሊሆን እንደሚችልና፤ መረጃ ከእኔ በኩል አፈትልኮ እንደሆነ የሚያሳይ ጠንከር ያለ ሂስ ነው፡፡ እኔ የት እንደሄዱ ስላላወቅሁ በጣም አዘንኩ፡፡ መልስ መጻፍ እንዳለብኝ አሰብኩ፡፡ እኔም ለእንዲህ አይነት ድርጅት ከሆነ አባል የሆንኩት መሳሳቴንና ከድርጅቱ እንደምወጣ ጻፍኩ፡፡ በሳምንቱ ግን የሚገርም መልስ ጻፉልኝ፡፡ መልሱ ለእኔ ለትንሹዋ ልጅ የሚሰጥ አልነበረም፡፡ ‹‹ተንበርክከን ይቅርታ እንጠይቃለን›› የሚል ከጸኃፊው ማብራሪያ ጋር ተዳምሮ ይቅርታ ተጻፈልኝ፡፡ ‹‹እንደ አንቺ ያለ ጠንካራ አባል ስላለን እንኮራለን›› አሉኝ፡፡ ይህም ሌላ ጉልበት ነበር፡፡ ይህን የጻፉልኝ ለአባላት ትልቅ ክብር እንዳላቸው መሆኑን አምኛለሁ፡፡ ሂስና ግለሂስን የተማርኩት ያኔ ነው፡፡
ብዙዎቹ ጓደኞቻችን ሞቱ፣ የተረፍነው ዳንን፣ ከእስር ተፈታን፣ መኖር የግድ ነውና መኖር ጀመርን፡፡ ያ ውስጤ የነበረን አላማ የነካውን ኢህአፓና ኢህአወሊ ውለታ ተሸክሜ መኖር አቃተኝ፡፡ በእርግጥ 20ና 30 አመት አልፎታል፡፡ ያ ትውልድ የሞተው፣ እኔ ያን ሁሉ የሆንኩት ኢትዮጵያን ለማጥፋት ባይሆንም በርካቶች ግን መኖር እንዳንወድ አድርገው ይወቅሱናል፡፡ በእርግጥ ስለማያውቁን ነው የሚል ጥያቄ ይመላለስብኝ ነበር፡፡ አንድ ወቅት ይህን መልስ እንዳገኝ አደረገኝ፡፡ አንድ ዓለም አቀፍ ድርጅት በምሰራበት ወቅት አንድ ቡድን ይዤ ለልምድ ልውውጥ ወደ ኬንያ ሄድኩ፡፡ በእረፍት ሰዓት ሰብሰብ ብለን ስናወራ ስለ ‹‹ያ ትውልድ›› መወራት ጀመረ፡፡ አጥፍተውት አለፉ እያሉ ይወቅሱታል፡፡ የአንድን ነገር ውጤቱን ብቻ አይቶ መገምገምና መውቀስ ተገቢ አይደለም፡፡ ‹‹ለምን እንዲህ ትወቅሷቸዋላችሁ?›› ስለቻው፤ ‹‹አታውቂያቸውም!›› አሉኝ፡፡ ‹‹እኔን አታውቁኝም? እንዴት ነው እኔ የማላውቃቸው? ያ ትውልድ ማለት እኔ ነኝ!›› አልኳቸው፡፡ ‹‹አንቺ ምንድን ነሽ?›› አሉኝ፡፡ ‹‹ኢህአፓ ነበርኩ!››፡፡ አላመኑም፡፡ ‹‹እኔ አላማ የለኝም? ጭራቅ ነኝ? እኔ ክፉ ነኝ? እኔ ኢትዮጵያን አልወድም?›› የሚል ጥያቄ አነሳሁላቸው፡፡ ‹‹አትቀልጅ! ያ ትውልድማ እንዲህ ሊሆን አይችልም›› አሉኝ፡፡ በእርግጥ በደርግ ጊዜ ሲማሩ ኢህአፓን እንደ ጭራቅ አድርገው ይስሉላቸው ስለነበር ነው፡፡ ‹‹እንግዲያውስ የጠፋው ጠፍቷል ነገር ግን አውቀን አላጠፋነውም አልኳቸው፡፡›› አንድ ነገር መለካት ያለበት በውጤቱ ብቻ አይደለም፡፡ የእኛ አጀንዳ ኢትዮጵያን ማጥፋት አልነበረም፡፡
ልጆቹን ‹‹ስለዛ ትውልድ፣ ስለ ኢህአፓ ማወቅ ትፈልጋላችሁ ልጻፍ?›› አልኳቸው፡፡
‹‹አዎ ጻፊ!››
‹‹ምን አይነት ልጻፍ?››
‹‹ትንሽ እንጨት እንጨት እንዳይል እንጅ ጻፊ!››
‹‹ምንድን ነው እንጨት እንጨት እንዳይል ማለት?
‹‹ትንሽ ፍቅር ቢጤ ጣል አድርጊበት?
‹‹እንዴ! እኛም እኮ ፍቅር እናውቅ ነበር ከየት አምጥቼ ነው ጣል የማደርገው?››
ከዛም ‹‹ምርኮኛ››ን መጻፍ ጀመርኩ፡፡ ከ30 አመት በኋላ ይህን መጽኃፍ የጻፍኩት የዛ ዘመን ፖለቲካ ስላሳመነኝ ነው፡፡ ከአንድ ነገር ጋር ለመዝለቅ ውስጣችን መነካት አለበት፡፡ ሌላ አጀንዳ ካለን፣ ሌላ የምናስበው ነገር ካለን፣ ያንን አጀንዳ ብለን የምንገባ ከሆነ በጊዜ መውጣት ነው የሚያዋጣው፡፡ እኔ የምችለውን ያህል ሄጃለሁ ብዬ አስባለሁ፡፡ ተሂዶ ተሂዶ መዝለል የማይቻል ጎርጅ ላይ ሲደረስ የግዱን ይቆማል፡፡ ከዛ በኋላ ያ ትውልድ ለምንድን ነው ያልቀጠለው የሚለው ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ በደርግ ዘመን የደረሰውን ስነ ልቦናዊ ችግር ሲታሰብ ከባድ ቢሆንም ከዛም በኋላ ግላዊ ህይወት ባሻገር ለአገር መስራት አይቻልም ነበር ወይ? የሚለው የእኔም ጥያቄ ነው፡፡ የትውልዱ አለመቀጠል ግን በርካታ ምክንያቶች ይኖሩታል፡፡
የ1966 አብዮት ሲፈነዳ ከላይ የጠቀስኳቸው እርሾዎች ሆነው አብላልተውታል፡፡ ተማሪውም ጥያቄ የጀመረው ቀደም ብሎ ስለነበረ ነው፡፡ የዓለም የፖለቲካ ሁኔታም ስላገዘው ነው፡፡ ይህ ጉዳይ የ1966ን አብዮት አዲስ ምዕራፍ ቢያስከፍተውም ያ ምዕራፍ ግን መዝለቅ አልቻለም፡፡ ምክንያቱም አንዳንዴ ያልታሰበ ውጤትና ስኬት ሰውን ወደ ሰማይ እንዲመጥቅ ያደርጋል፡፡ በዚህም ምክንያት መነሻን አለማሰብ ነገር ተከስቷል፡፡ ብዙ ፖለቲካ ብስለት ሳይኖር ብዙ ነገሮች ተከሰቱ፡፡ ስለዚህ የ1966 አብዮት ለውጥ አምጥቶ ነበር፡፡ ሆኖም የመከነ ለውጥ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ በሌላ በኩል ለብዙዎቻችን ዛሬ ድረስ የተሻገረ የአገር ፍቅር ሰጥቶን አልፏል፡፡ ስብዕናችንን እንድንሞርድና እንድንሻሻል አድርጎናል፡፡ እኔ ስለ እራሴ ብቻ ነው መናገር የምፈልገው፡፡ ቢያንስ እኔ አጭበርብሬ አላውቅም፡፡ እንዳላጭበረብር ያደረገኝ ግን እኔ ልዩ ሰው ሆኜ ሳይሆን ያኔ የተፈተሸው ማንነቴ ይመስለኛል፡፡ እኔ ለራሴ ጥቅም ብዬ በማንም ላይ ተራምጄ አላውቅም፡፡ ዛሬ 55 አመት ያለፈኝ ትልቅ ሰው ነኝ፡፡ ግን አጭበርብሬ አላውቅም፡፡ ይህን ያላደረኩት ግን የሚፈትነኝ ነገር ጠፍቶ አይደለም፡፡ ህይወትን ለማሸነፍ ይህኛውን መንገድን (ማጭበርበሩን) ብመርጥ እንደሚያዋጣኝ አጥቸው አይደለም፡፡ ግን በዛን ወቅት የተሞረደው ስብዕናዬ ዛሬም ድረስ አብሮኝ ስላለ ነው፡፡ ብዙዎቹ ይህ ስብዕና አላቸው፡፡ እናም 1966 ብዙ ሰው ፈጥሯል፣ ብዙ ሰው ገድሏል፡፡ የገደለው ግን ያመዝናል፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ኢትዮጵያ አሁን ለምትገኝበት ሁኔታ የደረሰችው፡፡ የትም አልደረስንም፤ መዋሻሸት አያስፈልግም፡፡ ዛሬም የትም አይደለንም፡፡ የኢትዮጵያን ህዝብ ወደ ውስጥ ገብተን ካየነው ዛሬም የምንበላው የለንም፣ ዛሬም ድሃ ነን፣ እኔ በዙሪያዬ ብዙ በልተው የማያድሩ ሰዎች አሉኝ፡፡ በዙሪያየ የሚኖረው ህብረተሰብ በታክሲ መሄድ የማይችልና ድሃ ነው፡፡ ጤፍ መግዛት የማይችል ማህበረሰብ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ምክንያት ከ1966 በኋላ በተከሰተው ችግር ነው፡፡ እሴቶቻችንን አጥተናል፡፡ እምነታችንን አጥተናል፡፡ ድሮኮ የእኛ ቤተሰቦች የሆነ ቦታ መሄድ ፈልገው የተሸከሙትን ነገር ቁጥቋጦ ውስጥ ደብቀው ተመልሰው ያገኙት ነበር፡፡ ይህን መጣል ነበረብን? በምን ተክተነው? መጣል አልነበረብንም፡፡ ነገር ግን እምነትን ጣልን፣ መታመንን ጣልን፡፡ አገር ባላደገበት ግን ለራሳችን ለማደግ ብንፍጨረጨርም ከመውደቅ አንድንም፡፡ አንድን ነገር ይዞ ለመዝለቅና ለመነሳሳት ከውስጥ እርሾ ታስፈልጋለች፡፡ 1966ንም የወለደው ያ እርሾ ነበር፡፡ ነገር ግን መነሻው ጥሩ አልነበረምና የተጋገረው ዳቦ ሊጥ ሆነብን፡፡ እናም እዚህ ደረስን፡፡
(ከአዘጋጁ:- ይህን ጽሑፍ ያሰናዳነው ቆንጅት ብርሃኑ ባለፈው ቅዳሜ በሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ተገኝተው ለወጣት የፓርቲው አባላት የትግል ልምዳቸውን ባካፈሉበት ወቅት ከተናገሩት ውስጥ ነው፡፡)
ክንፉ አሰፋ ብርሃኑ ዳምጤ እንደገና ሲገለበጥ የአስር አመት ልጅ ሳለሁ ያጋጠመኝን አንድ ክስተት አስታወሰኝ። በሰፈራችን ውስጥ ልጆችን ሁሉ የሚጠሉ አንድ ሰውየ ነበሩ። አንድ ቀን በድንገት ተነሱና የሰፈሩን ሰው ሁሉ መሰናበት ጀመሩ። በእጃቸው 3 ሜትር የሚያህል ርዝመት ያለው ገመድ ይዘዋል። “የሰፈሩ ልጆች ስላስቸገሩኝ ራሴን ልስቅል ነው። ደህና ሁኑ…” እያሉ ሁሉንም ተሰናብተው ሲያበቁ ለመሰቀል መንገዳቸውን ጀመሩ። የእኝህ […]
ማጋቢት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ለሦስት ወራት በሚካሄደው ክፍል ሁለት “የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ሪፎርም” በሚለው ዘመቻ፣ በዋነኛነት በተመረጡ 14 ከተሞች እና በሦስት ተጓዳኝ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍና ህዝባዊ ስብሰባ ይካሄዳል። የመሬትን አጀንዳ የሁለተኛው ዙር የመታገያ አጀንዳ ለምን እንዳደረገ ፓርቲው ሲያብራራ፣ “በባለሃብት ስም ገበሬው ከይዞታው መፈናቀሉ፤ በከተሞች በልማት ስም ዜጎች እየተፈናቀሉ […]
ዘወትር ቅዳሜ ማታ ከደሳለኝ መኮንን ጋር፣ምርጥና አዳዲስ የካንትሪ ማለትም የአሜሪካ አገር ሰብእ፣ የሮክ፣ተሶል፣የፖፕ፣የአር-ኤን-ቢ፣ብሉዝ፣የሬጌና የሂፕ-ሃፕ ዜማዎችን እንዲያደምጡ ተጋብዘዋል።
ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ህዝብ በኢኮኖሚ ሲጐሳቆል፣ በፖለቲካ በደል ሲሰማውና በማህበራዊ ህይወቱ ያልተረጋጋ ከሆነ ደግ አደለም፡፡ በጥንቱ ማርክሳዊ አካሄድ ፖለቲካ ማለት የተጠራቀመው የኢኮኖሚ ይዘት ነፀብራቅ/መገለጫ እንደማለት ነው፡፡ በግድ አራምደዋለሁ ካሉ አንገት መቀጨት፣ መሰበር፣ መውደቅ፣ አልጋ ላይ መቅረት ይከተላል ማለት ነው፡፡ ለማደግ አቅጣጫ ያስፈልጋል፡፡ ከመዓቱ ለማምለጥ መፍጠንም ያስፈልጋል፡፡ አቅጣጫ ማወቅ ብቻ ሳይሆን መሮጥና መፍጠን ያስፈልጋል ስንል ግን፣ ከምን አቅም? በምን ነፃነት? በምን ፍትሐዊ እርምጃ? በምን ዓይነት ቢሮክራሲያዊ ተቋም? በምን ዓይነት እርስበርስ መተማመን? በምን ዓይነት የገዢ ተገዢ ግንኙነት? ብሎ መጠየቅ ያባት ነው፡፡
የአስተዳደር ነገር መቼም ዋና ጉዳይ ነው፡፡ ኢኮኖሚያችን በኑሮ ውድነቱ መነጽር ሲታይ ዛሬ አሳሳቢ ነው፡፡ የሁሉም ነገር ዘዴው ተገኝቷል እንዴት እንደምንኖር መላው ከመጥፋቱ በስተቀር ፡፡ለፍቶ ለፍቶ፣ ዳክሮ ዳክሮ ኑሮ ጠብ አልል ያለው ሰው ከምሬት ሊወጣ አይችልም፡፡“እምዬ ኢትዮጵያ ሥራሽ ብዙ ፍራንክሽ ትንሽ” አለ አሉ አንድ ሠራተኛ! በእርግጥ በሊቀ – ሊቃውንት አስተሳሰብና ስሌት “ከአምስት አመት በኋላ ሠንጠረዡ ከፍ ይላል”፤ “በ2017 ዓ.ም አያሌ ፕሮጄክቶች ስለሚጠናቀቁ የተለየ ዓለም ይታያል” ወዘተ ይባላል፡፡ ምንሊክ ሳልሳዊ ችግሩ ህዝባችን “ሰብል በጥር ይታፈሳል” ቢሉት “ሆዴን እስከዚያ ለማን ላበድረው” አለ፤ የሚባለው ዓይነት ችግር ውስጥ ይገባል፡፡ አጣብቂኙ ከባድ ነው፡፡ ያለፈው ዘመን መሪ “የወረቀቱ ገብቶኛል፡፡ የገበያውን፣ የመሬት ያለውን ጉዳይ አስረዱኝ” አሉ አሉ፡፡ በግራፍ (ሠንጠረዡ ላይ) ሰብሉ ሰማይ ነክቶ፣ ከገበያው ግን ጠፍቶ ሲያዩት ቢጨንቃቸው ነው፡፡
የአመራራችንን ጉዳይ ችላ ብለን፣ የቢሮክራሲውን አካሄድ ወደጐን ትተን፣ ወደየትም የተሻለ ህይወት መዝለቅ አንችልም፡፡ በአካላችን እያወደስን በሆዳችን እየሰደብን የቱንም ወንዝ አንሻገርም፡፡ የምርጫችንን የዲሞክራሲያችንን ነገርም አደራ መባባል ያለብን ጊዜ ነው፡፡ መጽሐፍ ከመፃፍ፣ አዋጅ ከማወጅ፣ መመሪያ ከማውጣትና ጋዜጣዊ ጉባዔ ከማካሄድ አልፈን በቀናነት ለህዝባችን የሚበጀው ማንኛው መንገድ ነው? ማለት በጐ ነገር ነው፡፡
በኢኮኖሚያዊ ገቢያችን፣ በፖለቲካዊ መልካም አስተዳደራችን፣ በማህበራዊና ባህላዊ ማንነታችን የሚደርስብንን ጉስቁልና አሸንፈንና ድህነታችንን ታግለን በሁሉም አቅጣጫ ለውጥ እናመጣ ዘንድ፤ የህዝብ መነሳሳትን የሚያህል ካፒታል የለም፤ መነሳሳት ተገቢ ነው! አለበለዚያ ትላንት የነበርንበት ቦታ እንደተመቸን ቆጥረን መቀበል “ያደሩበት ጭቃ ከጭድ ይሞቃል” የሚለውን ተረት ከማረጋገጥ በቀር ፋይዳው በድን ነው፡፡
በትዕዛዝ እንግዳ ከመቀበል ይሰውረን፡፡ ባህላዊ እንግዳ – ተቀባይነታችንን ይባርክልን፡፡ ከጐረቤት ጋር ከመጣላት ይሰውረን፡፡ ተጣልተን ከታረቅንም ዕውነቱን የሚነግረን አያሳጣን፡፡ ስንጣላ መፈክር ከማስነገርና ከመራገም፤ ስንታረቅ ከማጨብጨብ ይሰውረን፡፡ የመንግስታችንን ልብና ልቦና እናውቅ ዘንድ የመረጃ ደሀ አያድርገን! የምንሰማውን በሌላ እንዳንተረጉም ንቃተ – ህሊናውን ያድለን ዘንድ፤ የሰላምና የማስተዋል ያድርግልን፡፡ ብሶት ሁሉ የፈጠራ፣ ጩኸት ሁሉ የሁከት፣ ሥጋት ሁሉ የትርምስ፤ እንዳያስመስልብን አስተዋይ ተመልካች ይሰጠን፡፡ ማየት – የተሳነው ተመሪ እንዳይሸበር ነገሩን ግልጥልጥ የሚያደርግ መሪ ይባርክልን፡፡ምንሊክ ሳልሳዊ
በጅጅጋ 300 እስረኞች መንገድ ላይ ተጣሉ
በጅጅጋ እስር ቤት ውስጥ ታስረው ከነበሩ ቁጥራቸው በውል ከማይታወቅ እስረኞች መካከል 300 ያክሉ ከአራት ቀናት በፊት በጅጅጋ መንገድ ላይ መጣላቸው ታውቀ።
የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ያላከውን መረጃ በመንተራስ ኢሳት ባደረገው ማጣራት፣ ባለፈው ሃሙስ ለአርብ አጥቢያ አካላቸው በምግብ እጦት የከሳ፣ አይናቸው የታወረ፣ እግሮቻቸው ሽባ የሆኑ፣ የአእምሮ መታወክ የደረሰባቸውና አሰቃቂ የእስር ቤት ህይወት እንዳሳለፉ የሚናገሩ እስረኞች በጅጅጋ ጎዳናዎች ላይ ተጥለዋል።
ከተጣሉት መካከል ወላጅ አልባ የሆኑ ምናልባትም በእስር ቤት ውስጥ የተወለዱ ህጻናት፣ ወጣቶችና አዋቂዎች ይገኙበታል።
አብዛኞቹ እስረኞች ከሰውነት ተራ የወጡና በበሽታ የተጠቁ እንዲሁም ለረጅም ጊዜ በእስር ቤት ውስጥ የቆዩ ናቸው። ኢሳት ለማረጋገጥ ባይችልም፣ የኦብነግ መረጃ እንደሚያሳየው ከተፈቱት እስረኞች መካከል 20ዎቹ በሶስት ቀናት ውስጥ በበሽታ ሞተዋል።
ከአንድ ወር በፊት ኢሳት ከጅጅጋ ከተማ 25 ኪሜትር ርቆ በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ በኮሌራ በሽታ ከ40 በላይ ሰዎች ሞተው በእስር ቤቱ አካባቢ አግባብ ባልሆነ መንገድ በመቀበራቸው አስከሬናቸውን ጅቦች እያወጡ በመብላታቸውና እና አካባቢው በበሽታ በመበከሉ በድጋሜ እንዲቀበሩ መደረጉን ዘግቧል።
የክልሉ መንግስት አሁን የወሰደው እርምጃ በእስር ቤቶች ውስጥ የተነሳውን የኮሌራ በሽታ ለመከላከል እንደሆነ እየተነገረ ነው።
በሶማሊ ክልል የተካሄደውን የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን አስመልክቶ የክልሉን ገጽታ ያበላሻሉ የተባሉ ከ700 በላይ የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎችና መታወቂያ የሌላቸው ሰዎች እንዲታሰሩ መደረጉ ይታወቃል።በጉዳዩ ዙሪያ የክልሉን የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። ማጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና

እንደልቡ/ዳግም (ከቫንኮቨር፣ ካናዳ)
አባ መላ ማን ነው?
በቅጽል ስሙ “አባ መላ” በእውነተኛ ስሙ ደግሞ ብርሃኑ ዳምጤ ተብሎ ይጠራል፣ በ60ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ አዛውንት ነው (ምንም እንኳ ስራው እንደ እድሜው ባይሆንም)። ፓልቶክ የሚባለውን የማህበራዊ መገናኛ መድረክ በመጠቀም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዲስኩር በማሰማት ይታወቃል። በወጣትነቱ ኢህአፓ ውስጥ ነበር የሚባለው ብርሃኑ ዳምጤ ወዲያውም የኢህአፓን መዳከም አይቶ ወደ ደርግ ቡድን መቀላቀሉን የሚያውቁት ይናገራሉ። በወቅቱ አብረውት በኢህአፓ ውስጥ ይሳተፉ የነበሩ ወጣቶችን ለደርግ በእጅ መንሻ መልክ አሳልፎ ሳይሰጥ እንዳልቀረ በደርግ ካድሬነት ቆይታው የሚያውቁት ይጠረጥራሉ አንዳንዶች ደግሞ አፋቸውን ሞልተው ይናገሩታል።
ብርሃኑ ዳምጤ ከደርግ መውደቅ በኋላ በስደቱ ዓለም (ዳያስፖራ) ፖለቲካ መድረክ ብቅ ያለው በምርጫ 97 ወቅት የዝነኛውን ቅንጅት ማልያ ለብሶ ነበር። ይሁንና በስልጣን ላይ ያለው የህወሃት/ወያኔ መንግስት ምርጫውን አጭበርብሮ፣ የምርጫውን መጭበርበር የተቃወሙትን በገፍ በአደባባይ በጥይት ደብድቦ፣ ህዝቡ የመረጣቸውን የቅንጅት አመራሮች፣ ጋዜጠኞችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ጨመሮ ከ50 ሺህ በላይ ባብዛኛው ወጣቶችን አስሮና በየጦር ካምፖቹ አጉሮ በአምባገነንነቱ ለመቀጠል ሲወስን ብርሃኑ ዳምጤም ባፋጣኝ የቅንጅትን ማልያ አውልቆ የህወሃት/ኢህአዴግን ማልያ ለብሶ ቁጭ አለ።
ሰሞኑን ደግሞ ብርሃኑ ዳምጤ አስደናቂ መገለባበጥን ፈጽሞ የህዝብን አይን አስበልጥጧል። እነዚህ ብርሃኑ ዳምጤ (አባ መላ) ሰሞኑን የሚፈጽማቸው መገለባበጦች በ1960ዎቹ እና 70ዎቹ ከነበሩት የመገለባበጥ ትሪኢቶቹ ለየት የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር አሁን መገለባበጡን የሚፈጽመው በቀጥታ ስርጭት ወቅት (በፓልቶክ) መሆኑና ጉዳዮን በመሪ ዜና መልክ የሚዘግብለት የቴሌቪዥን ጣብያ “ኢሳትን” ማግኘቱ ነው።
ብርሃኑ ዳምጤ ከጥቂት ወራቶች በፊት ነበር የተሰለፈበት የህወሃት/ኢህአዴግ ጎራ በተለይም ከወያኔው ቁንጮ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ እየተዳከመ መምጣትን አይቶና ገምቶ ወያኔዎችን “አፍንጫችሁን ላሱ፣ እኔ ከአሁን ብኋላ የድሮው አባ መላ አይደለሁም፣ እንዲያውም ጉዳችሁን አዝረጠርጣለሁ…” በማለት ፉከራ ቢጤ አሰምቶ የዲሞክራሲና የነጻነት ታጋዮችን ጎራ መቀላቀሉን ያበሰረው።
መንፈቅ እንኳ ሳይሞላ አባ መላ በመጣበት አይነት መንገድ ተመልሶ ህወሃት/ኢህአዴግን ለማገልገል መወሰኑን ይፋ አደርጓል። ለሱ እምብዛም አዲስ ያልሆነውን የክህደት ቁልቁለትም ዳግም ተያይዞታል።
አባ መላ፣ ኢሳትና ዳያስፖራው
የኢሳት ጋዜጠኞች፣ አንዳንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና የተቃዋሚ ፖለቲከኞችም ጭምር ይህ አባ መላ የሚባለውን ቦታ እየቀያየረ ይሚጫወት ዝቅተኛ ካድሬ ከሚገባው በላይ ቦታ ሰጥተውት እንደነበር እገምታለሁ፣ በውጤቱም ተከታዮቻቸውን ያሳሳቱና ያዘናጉ ይመስለኛል። ይህንን ጉዳይ ማንሳቴ “ብዬ ነበር” ለማለት ሳይሆን ይልቁኑም ይህ ክስተት እንደ መማሪያ ሆኖ እንዲያልፍ በመፈልጌ መሆኑን አባብያን እንዲረዱልኝ እፈልጋለሁ።
እንደ አባ መላ አይነቱ ቀደም ሲል በተደጋጋሚ የመገለባበጥ ብቃቱን ያሳየ ወለፈንዴ ተቃዋሚ ጎራ ገብቻለሁ ሲል አያያዛችን ጥንቃቄ የተሞላበት፣ ሊሆን ይገባል። በቅርቡ ተገልብጦ ሊያሳፍረን ይችላል ብሎ መስጋት፣ ለጉዳዩ መጠነኛ የአየር ሰዓት መስጠትና ውሎ አድሮ ደግሞ መርጋቱን እያዩ ወደሌላው መተላለፍ ተገቢ ነው። እንደው በአንድ ጊዜ ይህን ከምላስ በስተቀር ቁም ነገር የሌለው ተራ ካድሬ ወደላይ ቆልሎ አንድ ጊዜ “አክቲቪስት” ሌላ ጊዜ ደግሞ “የፖለቲካ ተንታኝ” እያሉ በኢትዮጵያውያን ስም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቋቋመ ግብረ ሰናይ ድርጅትን እንዲመራ ማጨት ድረስ መጓዙና አሉ ከሚባሉ ፖለቲከኞች ጋር መድረክ እንዲጋራ ሁኔታዎችን ማመቻቸቱ አገባብ አልነበረም።
የኢሳት ባልደረባ ደረጀ ሃብተወልድ የአባ መላን መገልበጥ አስመልክቶ በፌስቡክ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው ከሆነ ግን ኢሳቶች ከስህተቶቻቸው ሊማሩ የተሰናዱ አይመስልም ይልቁኑም አባ መላን አስመልክቶ ሊቀርቡ የሚችሉ ትችቶችን ቀድሞ ለመከላከል ነው ሙከራ የሚያደርጉ ያሉት። ደረጀ ሃብተወልድ እንዲህ ነበር ያለው፣
“ነገሩ ወዲህ ነው። አባ መላ ኢህአዴጎችን እየሰደበ ወደ ተቃዋሚው ጎራ ሲቀላቀል “አገኛለሁ” ብሎ ያሰላው ጥቅም ነበር። ሆኖም ሀሳብን በነፃነት ለመግለጽ ከሚያስችል ነፃ መድረክ ውጪ ሌላ ነገር ሊያገኝ አልቻለም። ባገኘው ነፃ መድረክም ማንም ሳይቆነጥጠው ከትንሽ እስከ ትልቅ የቀድሞ አለቆቹን እስከ ዶቃ ማሰሪያቸው ነግሯቸዋል። እኛንም አስቆናል። ስንስቅለት ጨምሮ ጨማምሮ አቅምሷቸዋል። እኛም፦“የአገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ” እያልን ተዝናንተናል። ከዚያ ባለፈ ግን ለቁም ነገር ያሰበው ሰው ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ።”
የደረጀን አባባል ሁሉም ሰው የተቀበለው አይመስልም ይህን ለማሳየት ከተቃውሞ ሃሳቦች መካከል አንዱን ከዚያው ከደረጀ ሃብተወልድ የፌስቡክ ገጽ ልበደር፣
“የአባ መላን መገልበጥ ተከትሎ ኢሳቶች ከተወቃሽነት ለመዳን የዘየዳችሁት ይሄው ነው? ደረጀ “አባ መላን ለቁም ነገር ያሰበው ያለ አይመስለኝም” ያልከው ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው፣ በሳውዲ ወገኖቻችንን ለመታደግ በተቋቋመው አለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ ከታማኝ እና አበበ ገላው ቀጥሎ ሶስተኛ ሰው ተደርጎ አልነበረም? በጣም ብዙ ማለት ይቻላል… “እጄን በጄ” ሆኖብን እንጂ። ለማንኛውም ከስህተቶቻችሁ ተማሩ፣ በጣምም አንፍጠጥ ያስተዛዝባል።” ethiopian unity
ለማጠቃለል ያህል የሚሰራ ጋዜጠኛ፣ ለውጥ ለማምጣት የሚተጋ ፖለቲከኛና የዲሞክራሲ ታጋይ በሂደት ውስጥ ስህተት ሊሰራ ይችላል፣ ከስህተቶች ትምህርት ወስዶ ለሁለተኛ ጊዜ ተመሳሳይ ስህተትን ላለመድገም ጥረት ማድረግ ግን ሊለመድ ይገባል። ነገሮቻችን ሁሉ “ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ” እንዳይሆኑ ሃላፊነት ወስደን ከስህተቶቻችን ለመማር ዝግጁ እንሁን።

(ሁኔ አቢሲኒያዊ ከፒተርቦሮው ዩ.ኬ) :-አቶ ስብሃትን ጠጋ ብለው የሚያውቁት ሰዎች “አቦይ ብላችሁ አትጥሩት። አባታዊ አንደበትና ምግባር የለውም እርሱን አቦይ ማለት ትግራይ የሽማግሌ መሀን እንደሆነች መቁጠር ነው” ይሉታል፡፡
ሰውዬው ስብሐት ነጋ የህወሓትን አመሰራረት ቅድመ ታሪክ ለሚያውቅ ሰው ምን ያህል ተንኮለኛ እና በዘር ልክፍት የተለከፈ እንደሆነ ግልጽ ይሆንለታል፡፡ በ1963 ዓ.ም እንደተመሰረተ የሚነገርለት ማገብት (ማህበር ገስገስቲ ብሔረ ትግራይ) የተመሰረተው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የትግራይ ተወላጅ ተማሪዎች ነበር፡፡ የማህበሩ ተልእኮም የተለያዩ የበጐ አድራጐት ስራዎችን በክረምት ወደ ትግራይ በመሄድ ማከናወን የሚል ነበር፡፡ በሂደት ሙሉ በሙሉ ወደ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በመቀየር ለተሐህት/ህወሓት መመስረት መሰረት ሆነ ለዚህ ዓላማ የማስቀየር ስራ ትልቁን አስተዋፅኦ ካደረጉት መካከል ደግሞ ዛሬ ታሞ የሚማቅቀው ስብሐት ነጋ አንዱ ነው፡፡
ስብሐት ነጋ የህወሀትን መስመር እና ዓላማ መሀንዲስ ከመሆንም አልፎ እስከዛሬ ለብዙ ሰዎች ምስጢር በሆነ መልኩ መለስ ዜናዊንም ወደ ህወሀት ሊቀመንበርነት ብሎም የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስተር ያደረገ እና በህወሀት ክፍፍል ወቅትም ትልቅ ሚና ከነበራቸው ቀደምት የህወሀት ታጋዮች አንዱ ነው፡፡
ለባለፉት 23 ዓመታት የኢትዮጵያን ህዝብ ከጀርባ ሆነው ሲያንቀጠቅጥ የነበረው አይተ ስብሐት ነጋ እርሱም ተራው ደርሶ ቤልጅየም ብራሰልስ በሚገኘው ሴንት ሚካኤል ሆስፒታል Hôpital Saint Michel – (Brussels) መመላስ ከጀመረ 11 ዓመታት እንደሞላው የውስጥ አዋቂዎች ቢገልፁም የበሽታው አይነትና የሰውዬው የጤንነት ሁኔታ እስካሁን ድረስ ከቅርብ ሰዎች ውጪ ሳይወጣ ቀርቷል ሆኖም የህወሀት የውስጥ ሹኩቻን ተከትሎ ሚስጥሮ እያፈተለኩ መውጣታቸውን ቀጥለው ዛሬ ስለ ስብሀት ነጋ ጤንነት በተመለከተ ለዚህ ጽሁፍ ፀሀፊ አፈትላኪ መልዕክት ደርሷል፡፡
ከታማኝ ምንጮች የተገኙት መረጃዎች እንደሚያሳዩት ሰውዬው ማለትም ስብሐት ነጋ brainstem glioma በተባለ የካንሰር አይነት መጠቃቱን ገልፀዋል፡፡ ይህ የካንሰር አይነት በብዛት በህፃናት ላይ የሚታይ ሲሆን በአዋቂዎች ዘንድ ግን በዚህ የካንሰር ዓይነት የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ100,000 አንድ እንደሆነ የሳይንስ ማስረጃዎች ያሳያሉ፡፡
Brainstem glioma ስለተባለው የካንሰር አይነት መንስዔ እስካሁን የህክምና ባለሙያዎች ምንም ያሉት ነገር ባይኖርም በካንሰሩ የተጠቃ ሰው ግን ከፍተኛ የሆነ የራስ ህመም፣ ራስን የመቆጣጠር እና የማስመለስ ችግር እንደሚያጋጥመው ያስረዳሉ፡፡
በዚህ ካንሰር ተጠቅተው ወደ ህክምና ከሄዱ ሰዎች መካከል 37% የመኖሪያ እድሜያቸው ቢበዛ ዓንድ ዓመት 20% ያህሉ ሁለት ዓመት 13% ቢበዛ ቢበዛ ከሶስት አመት በላይ በህይወት የመኖር እድላቸው አነስተኛ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ከህወሀት አፈትልኮ የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ስብሐት ነጋ ባለፉት 11 ዓመታት ቤልጂየም ሲመላለስ የነበረው በዚሁ የካንሰር ምክንያት እንዳልነበረ እና የዚህ አይነት የካንሰር ተጠቂ እንደሆነ የተነገረው ፌብራዋሪ 9 እለተ እሁድ ቀን እንደነበር ጨምረው ገልፀዋል፡፡
የአቶ ስብሐት ነጋን መታመም ተከትሎ በሰውዬው ላይ በየዕለቱ የተለያየ ባህሪ እንደሚመለከቱ ገልፀው በተደጋጋሚ ከተለያዩ ስብሰባዎች ላይ አቋርጠው እየሄዱ እንደሚገኙ አክለው ገልፀዋል፡፡
በጦርነቱ ዘመን የትግራይ ህዝብ እጅግ የከፋ ድርቅና ረሀብ ሲፈራረቅበት፤ ከመሀል አገር የእርዳታ እህል እንዳይደርሰው መንገድ በመዝጋት፤ እነሱ በተቆጣጠሩት አካባቢና ባልተቆጣጠሩትም አካባቢ “እኛ ነን ለህዝባችን ረድኤት ድርጅቶች የሚያቀርቡትን እርዳታ ማደል ያለብን” ብለው የተባበሩት መንግስታትን ግራ አጋብተው ለረሀብተኛው እንዲያከፋፍሉ መድሀኒትና ምግብ ይሰጣቸው የነበሩ ሲሆን ያንን በብዙ ሚሊዮን የሚገመት የእርዳታ እህልና ቁሳቁስ ከአረብ ነጋዴዎች ጋር በመመሳጠር በቀጥታ ባህር እያሻገሩ በመሸጥ፤ በኩንታሎች አሸዋ እየሞሉ ለጋሾችን በማታለል እንዲገዙአቸው በማድረግ፤ በሚሊዮን ዶላር ሲንበሸበሹ፤ የጦር መሳሪያ ሲሸምቱ፤ የትግራይ ህዝብ እንደቅጠል ይረግፍ ነበር። እነሱ በየጫካው ከሰራዊቱ እየተሸሸጉ አረቄ ጠግበው ከውሽሞቻቸው ጋር ከበሮ እየደለቁ እየጨፈሩ ይዳሩ እንደነበር ህወሀትን ጥለው የኮበለሉ የቀድሞ አባላቶች የሚገልፁ ሲሆን ለእነዚህ ሁሉ ግፍ እና በደል መፈፀም ከፍተኛ ሚና የነበራቸው እኚሁ የካንሰር ተጠቂ ነበሩ፡፡
ሞት ፍትሃዊ ነው በቅርቡ እንኳን አፈ ቀላጤ መለስ ዜናዊን ከህወሀት አለማየው አቶምሳን ከኦህዴድ ( ኦህዴድ ብዬ ስጠራው የዋሸው ይመስለኛል) የወሰደ ሲሆን አሁን አፉን ከፍቶ ከስብሐት ነጋ ደጃፍ ደርሷል ስብሀት ነጋም ሞትን ወደ ቤቱ ላለማስገባት ከአዲስ አበባ ወደ ብራሰልስ በየዕለቱ እየተመላለሰ ይገኛል ግና ሞትን ሸሽቶ እስከመቼ ሊደበቅ እስከ አንድ ወር ወይስ?
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
ጀርመን ውስጥ በሚገኙ የስደተኞች መጠለያዎች ላይ በቀኝ አክራሪዎች የሚደርሱ ጥቃቶች መባባሳቸውን የጀርመን መንግሥት አስታውቋል ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችም የችግሩን አሳሳቢነት አጉልተው በማሳየት ላይ ናቸው ።
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ዓለም ዓቀፉ ሕብረተሰብ በተለይ ከሰሃራ በስተደቡብ ከሚገኙ ሃገራት የወባ ስርጭትን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ገንዘብ መድቧል። በዚህ አማካኝነት የተከናወኑ የተቀናጁ ጥረቶችም ለዉጥ ማሳየታቸዉ እየተነገረ ነዉ።