በርሊን፤ ዓለም ዓቀፉ የቱሪዝም ትርዒት
ባለፈው ሳምንት የተከፈተዉ በርሊን ላይ የተካሄደዉ ትልቁ የዓለም ዓቀፍ የቱሪዝም ድርጅቶች ትርኢት ለተሳታፊዎቹ ጥሩ ዉጤት አስገኝቶ መጠናቀቁን የበርሊኑ ወኪላችን በላከዉ ዘገባ ጠቅሷል።
ባለፈው ሳምንት የተከፈተዉ በርሊን ላይ የተካሄደዉ ትልቁ የዓለም ዓቀፍ የቱሪዝም ድርጅቶች ትርኢት ለተሳታፊዎቹ ጥሩ ዉጤት አስገኝቶ መጠናቀቁን የበርሊኑ ወኪላችን በላከዉ ዘገባ ጠቅሷል።
የሶማልያ መንግሥት ጦር እና የአፍሪቃ ህብረት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች፣ አሚሶም በደቡባዊ እና ደቡብ ማዕከላይ የሀገሪቱ ከፊል በሚገኙት የአሸባብ ተዋጊዎች አንፃር ካለፉት ሰባት ቀናት ወዲህ ሰፊ የጥቃት ዘመቻ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።
በአፋር ክልል የሚገኙ ጨዉ አምራቾች መንግስት የሚያስፈልገንን አዮዲን በወቅቱ ስለማያቀርብልን ምርቶቻችን በዝናብና አቧራ እየባከ ለኪሳራ እየተዳረግን ነዉ አሉ።
መላዋ ኢትዮጵያ እንደ አንድ የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሀገረ ስብከት ትቆጠር የነበረችበት የ1600 ዓመታት የሞግዚትነት ታሪክ ከብዙ ተጋድሎና እልክ አስጨራሽ ጥረት በኋላ አክትሞ የመንበረ ፕትርክናውን ነጻነት መቀዳጀቷ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን የተበሠረበት ዘመን ነው – በዓለ ሢመተ ፓትርያርክ፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በመንበረ ተክለ ሃይማኖት የመጨረሻውን የክህነት ማዕርግ መብቷን (የኤጲስ ቆጶስነት፣ የሊቀ ኤጲስ ቆጶስነትና የፓትርያርክነት ጸጋን) ለማረጋገጥ …![]()
አፈንዲ ሙተቂ
———-
ኤርትራ ዛሬ ራሷን የቻለች ሀገር ናት፡፡ ትናንት ግን የኛው አካል ነበረች፡፡ አጼ ኃይለ ሥላሤ ብልጥ የሆኑ መስሎአቸው ለሁላችንም አስፈላጊ የነበረውን የፌዴሬሽን ፎርሙላ ሰረዙትና ህዝቡን አስቀየሙት፡፡ ደርግ ደግሞ የራሳችንን ህዝብ እንደ ባዕድ እየቆጠረ በመትረየስ አጨደው፡፡ በታንክ ደመሰሰው፡፡ በዚህም የተነሳ ወጣቱ “አደይ ኤሪቲሪያ”ን እየዘመረ ወደ ባርካና ሳህል ነጎደ፡፡ ራሱን አደራጅቶ ጀብሃና ሻዕቢያ ሆኖ መጣ፡፡ ውጤቱም 1983 ላይ ታየ፡፡
የደርግና የኃይለ ሥላሤ መንግስታት ያደረጓቸው ነገሮች ሲገርሙን በጣም ግራ የሚያጋባው ሶስተኛው መንግሥታችን መጣ፡፡ ይህ የኛ መንግሥት “የተበላሸውን ሁሉ አስተካክለን አብረን መኖር እንችላለን” ብሎ መከራከር ሲገባው ጭራሹኑ “ኤርትራ ካልተገነጠለች ኢትዮጵያ ሰላም አታገኝም” ባይ ሆኖ ተገኘ፡፡ ክፍለ ሀገሩ ወደዚያ ከሄደ በኋላም መንግሥቱ ከሚከተለው ግልጽነት የጎደለው አሰራር የተነሳ በ1990 ዓ.ል. ሺዎችን ያረገፈ ግዙፍ ጦርነት ተቀሰቀሰ፡፡ ከአንድ ምንጭ የተቀዱ ህዝቦች ተጋደሉ፡፡ እነሆ ዛሬም ድረስ ነገሩ ሳይለይለት በጨለማ ውስጥ ነው ያለነው፡፡
እኛ ግን ተስፋ አንቆርጥም! በአያያዝ ጉድለት የተለየንን ወገናችንን መመለስ እንፈልጋለን፡፡ ህዝቡ ለጊዜው ሪፈረንደም አድርጎ ነጻነቱን ማወጁን ብንደግፍለትም አንድ ቀን ተቀራርበን በጋራ ስለመስራት እንወያይ ይሆናል ብለን እናልማለን፡፡ የኛ ልጆች ደግሞ በኮንፌዴሬሽን ስለመስራት ያስቡ ይሆናል፡፡ የልጅ ልጆቻችን በፈቃደኝነት ስለመዋሃድ ያስቡ ይሆናል፡፡ በዚያን ጊዜም አሁን የምንመኘው በአንድነት ውብ የመሆን ሚስጢራችን ይመለስልናል ብለን እናልማለን፡፡ ምን ይታወቃል?
ወገኖቼ ደጉን ነው የተመኘሁት፡፡ በቅን ልቦና በርትተን ከጸለይንና ከኛ የሚጠበቀውን ካደረግን ሁሉንም የሚችለው ፈጣሪ ህልማችንን እውነት ያደርግልናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡
——-
ምን እንደጣለብኝ እንጃ! ያንን ምድር እጅግ ሲበዛ እወደዋለሁ፡፡ እኔ ለተወለድኩበትና አብዛኛውን ዘመኔን ለጨረስኩበት የምስራቅ ኢትዮጵያ ክልል ጎረቤት ከሆነችው ሶማሊያ ይልቅ በ1600 ኪ.ሜ. የምትርቀው አስመራ ናት የምትናፍቀኝ፡፡ ስለሶማሊያ የተጻፈ መጽሐፍ ማንበብ ብዙም አይማርከኝም፡፡ ስለ ኤርትራ የተጻፈ መጽሐፍ ካጋጠመኝ ግን ሳላየው አላልፍም (ይህ ግን ሶማሊያን ከመጥላት እንደማይቆጠርብኝ ተስፋ አደርጋለሁ)፡፡
ታዲያ በርካቶቻችሁም እንደኔው ትመስሉኛላችሁ፡፡ ለምሳሌ ከ1970ዎቹ ጀምሮ ሲታተም የቆየው የቤኒ አምሩን ወጣት የሚያሳየው ፖስተር ዛሬም ድረስ ከኛ ጋር ተሳስሮ ነው ያለው፡፡ አሁንም ድረስ በበርካታ ስፍራዎች ተለጥፎ አይቼዋለሁ፡፡ በፌስቡክም እርሱን እንደ ፕሮፋይል ፒክቸር የሚጠቀም ኢትዮጵያዊ ሞልቷል፡፡ በሌላ በኩል የኤርትራን ሙዚቃ የሚያዳምጡ ሰዎች በሽ ናቸው፡፡ ደራሲ መሐመድ ሳልማን መቐለ ሄዶ ያየው ነገር ቢያስገርመው “በኤርትራ ሙዚቃ የምትጨፍር ከተማ” የሚል አስደናቂ ወግ ጽፎ እውነቱን አስረድቶናል፡፡ መንግሥታት ቢጣሉ እንኳ ህዝቦች ምንጊዜም እንደሚነፋፈቁ ከዚህ በላይ የሚያስረዳ ዋቢ ያለ አይመስለኝም፡፡
——–
ማርታ ሀይሉን አስታወሳችኋት? አዎን! ማርታን “ብራ… ነው… ብራ ነው”፤ “አዘዞ”፤ “ሎጋ ..ና እናውጋ” በተሰኙት ዘፈኖቿ እናውቃታለን፡፡ ከማርታ ዘፈኖች ዘወትር ቀልቤን ይገዛ የነበረው ግን የትግርኛ ዜማዋ ነው፡፡ አዝማቹ እንዲህ ይመስለኛል፡፡
ካብ አስመራ ድንገት ርእዮ
ምጽዋ ገባሁ ልበይ ሕብዮ
እንተርጉመው እንዴ?… ግድ የለም ማርታ ራሷ እንዲህ እያለች በአማርኛ ተርጉማዋለች፡፡
“ከአስመራ ድንገት አይቼው
ምጽዋ ገባሁ ልቤን ሰጥቼው”፡፡
አዎን! ትናንት የኛ ናት ስንላት ለነበረችው ኤርትራ ነው እንዲህ የዘመርንላት፡፡ ዛሬም ብንዘምርላት እንከበራለን እንጂ አንወቀስም፡፡ ምክንያቱም በመንግሥት ደረጃ ነው የተለያየነው፡፡ ሁለት ፓስፖርት እንዲኖረን ነው የተደረግነው፡፡ ሁለታችንም ግን አንድ ህዝቦች ነን፡፡ በደምም ሆነ በባህል በጣም የተዋሃድን የአንድ መሬት ብቃዮች ነን፡፡ ሁለታችንም የተዋብን የሴምና የኩሽ ህዝቦች ውቅር ነን፡፡ እንደኛ የሚያምር ህዝብ በትኛውም ዓለም የለም፡፡ የጀበና ቡና፣ ዶሮ ወጥ፣ ድፎ ዳቦ፣ የስጋ ፍትፍት፣ አምባሻ፣ ወዘተ…. ሁለታችን ዘንድ ብቻ ነው ያለው፡፡
—–
በርግጥ እላችኋለሁ፡፡ በምንባብና በወሬ እንጂ በአካል የማላውቃት ኤርትራ ትናፍቀኛለች! ያ በታሪክ ምዕራፎች “ምድሪ ባህረ ነጋሽ” እየተባለ ሲጠራ የኖረው ጀግና መሬትና ህዝብ ይናፍቀኛል፡፡ ያ የሰሜኑ በረኛ እያልን እንመካበት የነበረው ህዝባችን ይናፍቃል፡፡
እውነትም ኤርትራ ! የዳማት ታሪክ ውቅር! የመጠራ አብያተ መንግሥታት ከርስ! የሀውልቲ ፍርስራሾች ቀብር! የአዱሊስና የዙላ ወደቦች መዘክር! የሱዋኪምና የዳህላክ ሱልጣኖች ደብር!
ኤርትራ የአብረሃ ደቦጭ ሀገር! የሞገሥ አስገዶም ሀገር! የዘርዓይ ደረስ ሀገር! የሎሬንዞ ታዕዛዝ ሀገር! የደጃች ሀረጎት ሀገር! በአይበገሬ ጀግንነታቸው ድፍን አፍሪቃን ያኮሩ አርበኞች የበቀሉበት ምድር!
ኤርትራ የበረከት መንግሥተ አብ ሀገር! የአብረሃም አፈወርቂ ሀገር! የአሕመድ ሼኽ ሀገር! የሄለን መለስ ሀገር! የየማነ ባሪያው ሀገር! የሄለን ጳውሎስ ሀገር! በስርቅርቅ ድምጻቸው የሰውን ልብ እየሰረሰሩ የመግባት ሀይል ያላቸው የጥበብ ከዋክብት የወጡበት መንደር!
ኤርትራ የፊያሜታ ጊላይ ሀገር! የስዕላይ በራኺ ሀገር! የኦቦይ ተኽሌ ሀገር! የተክላይ ዘድንግል ሀገር! የሆቴል ፓራዲዞ ሀገር! የዕቁባይ ሲላ ሀገር! የምንወደው ደራሲያችን በዓሉ ግርማ በ“ኦሮማይ” መጽሐፉ እንደ ፊልም ግልጥልጥ አድርጎ እየተረከልን ዝንተ-ዓለም እንድንወዳት ያደረገን የቀይ ኮከብ ትዝታ ወመዘክር!
ኤርትራ የፊዮሪ ሀገር! የሳባ ሀገር! የማርቲና ሀገር! የብርኽቲ ሀገር! ፊያሜታ ጊላይን የመሳሰሉ “ሽኮሪናዎች”ን ያበቀለች ውብ የውቦች እመቤት!
—–
ኤርትራን ስንጠራ በቅድሚያ ወደ አዕምሮአችን የምትመጣው አስመራ ናት፡፡ የአስመራ ናፍቆት ይገድላል፡፡ አስመሪና፣ አስመሪቲ፣ አቲ ጽብቕቲ!…
ውይ ስታምር! “ቀሽቲ” እኮ ናት፡፡ ያኔ በልጅ አዕምሮአችን በዘምባባ ጥላዋ ተሸክፋ በፖስትካርድ ስትቀርብልን “የኛ ውቢት” እያልን እንመጻደቅባት ነበር፡፡ እንቆቅልሽ ስንጫወትና መልሱ ጠፍቶን “ሀገር ስጠኝ” ስንባል እርሷን ለመስጠት እንሰስት ነበር፡፡ ጠያቂውም የዋዘ ስላልሆነ “አስመራ” ካላልነው ለጠየቀን ጥያቄ ትክክለኛውን መልስ አይነግረንም ነበር፡፡ ከማናውቃቸው “ዋሽንግተንና” ሮማ አስመራ ነበር የምትበልጥብን፡፡ በትምህርት ቤት መዝሙራችንም እንዲህ እንል ነበር፡፡
ኦኬ ኦኬ ኦኬ ስራ
ሰላም ሰላም ወደ አስመራ
አዲስ አስተማሪ ከጃፓን የመጣ
ማስተማሩን ትቶ በቦክስ የሚማታ
አናግረኝና አናግርሃለሁ
በአሜሪካ ሽጉጥ አዳፍንሃለሁ፡፡
ግጥሙ “አንታራም” የሚሉት የህጻናት ጨዋታ ዓይነት ነው፡፡ ነገር ግን አስመራ ከልባችን እንዳትጠፋ አድርጓል፡፡ ዛሬም በልባችን ነግሳለች አስመሪና!
—-
አስመሪና! እንተይ ሽኮሪና! ሰሜናይት ጽብቕቲ! በዓሉ ግርማ ላንቺ ክብር የጻፈው ትዝ ይልሻል? እስቲ እናስታውሰው!
አስመሪና አስመራዬ
ካብ ሐንቲ ንግሥቲ ይበልፅ መልክእኪ
አማአድዬ ክርእየኪ ከሎኹ ኽአ
አብ ኢደይ ዘሎ ነገር ይወድቕ፡፡
——
ጸጸራት፤ ፎርቶ፣ ሐዝሐዝ፣ አርበእተ አስመራ፣ እምባጋሊያኖ፣ ኮምቢሽታቶ፣ አዲጓእዳድ፣ ቃኘው፣ ማይተመናይ፣ ሰምበላይ፣ ጎዳይፍ፣ ገጀረት፣ ወዘተ…በጽሑፍ የማውቃቸው የአስመራ ሰፈሮች ናቸው፡፡ አንድ ቀን በሆነልኝና ባየኋቸው እያልኩ አልማሁ፡፡ እነዚህ አስገራሚ የአስመሪና ሰፈሮች ብዙ ባለታሪኮችን አብቅለዋል፡፡ ብዙዎች ገድላቸው እየተደጋገመ ሲነገርላቸው እሰማለሁ፤ አነባለሁ፡፡ ለኛ ቅርብ የነበረ አንድ ውድ ልጅ እየተረሳ በመሆኑ ግን አዝኛለሁ፡፡
አማኑኤል እያሱ ይባላል! አስታወሳችሁት አይደል? አዎን! አማኑኤል በኛ ዕድሜ ዘመን ኢትዮጵያ ዋንጫ መብላት እንደምትችል ያስመሰከረው የታላቁ የ1980 የእግር ኳስ ቡድናችን ቋሚ ተሰላፊ ነበረ፡፡ የማሊያ ቁጥሩ 2 ይመስለኛል፡፡ አማኑኤል የያኔው ቡድናችን ባደረጋቸው ሁሉም ጨዋታዎች ተሰልፏል፡፡ ቡድኑ ዋንጫውን ሲበላም ከጓደኞቹ ጋር ቤተመንግሥት ድረስ ተጋብዞ ተሸልሟል፡፡ አማኑኤልን ያስገኘው ከዚያ ዘመን ዝነኛ ቡድኖቻችን መካከል አንዱ የነበረው የኤርትራ ጫማ ቡድን ነው፡፡ ይህ ቡድን የኤርትራ አንደኛ ዲቪዚዮን ዋንጫን በተደጋጋሚ ያሸነፈ ነው፡፡
አማኑኤል እያሱ በኢትዮጵያ ትቅደም አንደኛ ደረጃ ዋንጫም ለኤርትራ ክፍለ ሀገር ምርጥ ቡድንም ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡ ባልሳሳት የ1981 የኢትዮጵያ ዋንጫን ያሸነፈው እነ አማኑኤል የነበሩበት የኤርትራ ክፍለ ሀገር ቡድን ነው፡፡ የአማኑኤል እያሱን ወሬ ለመጨረሻ ጊዜ ያነበብኩት በ1988 ለወዳጅነት ጨዋታ አዲስ አበባ መምጣቱን በማስመልከት በርካታ የግል ጋዜጦች ቃለ-መጠይቅ ባደረጉለት ጊዜ ነው፡፡ ከዚያ ወዲህ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ መረጃው የለኝም፡፡ እስቲ የአስመራ ልጆች ወሬው ካላችሁ ስለአማኑኤል እያሱ አንድ ነገር በሉን፡፡
—–
ወደ ምዕራብ ኤርትራ ተሻግረናል! ባርካና ጋሽ የሚባሉት የኤርትራ ቆላዎች እዚህ ነው ያሉት፡፡ አቆርዳት፣ ተሰነይ፣ አሊጊደር፣ ባሬንቱ የተሰኙት ከተሞችም በቆላው ውስጥ ተዘርግተዋል፡፡ ኩናማ፣ ናራ እና ቤጃ የተሰኙት ብሄረሰቦች እዚህ ነው የሚኖሩት፡፡ የአካባቢው ዋነኛው ህዝብ ግን ለኛ በጣም ቅርብ ሆኖ ዓመታትን ያስቆጠረውን ሳቂታውን የቤኒ አምር ወጣት ያስገኘው የትግረ ህዝብ ነው፡፡
የትግረ ህዝብ በውስጡ በርካታ ጎሳዎች አሉት፡፡ ከሁሉም የሚበረክተው ግን የቤኒአምር ጎሳ ነው፡፡ ህዝቡ የሚነጋገርበት የትግረ ቋንቋ ከሴማዊ ቤተሰብ ነው የሚመደበው፡፡ ለዚህ ቋንቋ በጣም የሚቀርበው በደጋው ኤርትራና በኛዋ የትግራይ ክልል የሚነገረው ትግርኛ ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ቋንቋዎች ከጥንታዊው የግዕዝ ቋንቋ ነው የተወለዱት፡፡ የትግረ ቋንቋ ከኤርትራ ሌላ በሱዳንም (ከሰላ አካባቢ) በስፋት ይነገራል፡፡
ትግረና ትግርኛ በጣም ከመመሳሰላቸው የተነሳ እንግዳ ለሆነ ሰው አንድ ዓይነት ቋንቋዎች ሊመስሉት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ለትግርኛ ተናጋሪዎች የትግረ ቋንቋን መልመድ በጣም ቀላል ነው ይባላል፡፡ የትግረ ተናጋሪም ትግርኛን በቶሎ መልመድ ይቀለዋል፡፡ በመሆኑም በዛሬዋ ኤርትራ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ህዝብ ሁለቱንም ቋንቋዎች መናገር ይችላል፡፡
ምዕራባዊው ቆላ ኤርትራዊያን በጣም የሚያደንቋቸውን እንደ ሃሚድ ኢድሪስ አዋቴ፣ ሙሐመድ ኢድሪስ እና ኢድሪስ ገላውዴዎስን ያፈራ መሬት ነው፡፡ በዚህ ሰሞኑን ልቤን ያሸፈተው የትግረ ልጅ ግን “አሕመድ ሼክ” ነው፡፡ አሕመድ ሼክን አወቃችሁት አይደል? አዎን! “ባቡሬይ”፣ “ኢላ ሰርጎ” ወዘተ.. እያለ በማይጠገበው የትግረ ምት የሚያዜመው ተወዳጅ ድምጻዊ ነው፡፡ አንድ ኤርትራዊ ወዳጃችን “ኤላ ሰርጎ”ን ሲፈታልን `ከጀርባው ፌሎሶፊ አለው” ነው ያለኝ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡
የትግረ ሴት ለምትወደው አንድ ሰው (ለባሏ) እንጂ ለማንም ጸጉሯን አትገልጠውም፡፡ ስለዚህ ጉብሊቷን ልጅ የወደደው አሕመድ ሼክ በተዋቡ ግጥሞች እያወደሳት ዘፈነላትና ፍቅሩ ልቧ ውስጥ ዘልቆ መግባቱን ለማረጋገጥ ጸጉሯን ማየት ጀመረ፡፡ እርሷም ግጥሞቹን ከሰማችለት በኋላ ጸጉሯን ገልጣ አሳየችው፡፡ ድል አድራጊው ወዲ ሼክም ይዟት በረረ፡፡ ኤላ ሰርጎ! ኤላ ሰርጎ” እያለ ነጎደ!
——
ሰሜን ኤርትራ!
ተወዳጇ የከረን ከተማ እዚህ ነው ያለችው! የሀረርጌዋ የድሬ ዳዋ ከተማ መንትያ እህት የምትመስለው ውቢቷ የሰሜን ፈርጥ! በቪዲዮ አይቻት ውበቷን አደነቅኩላት! አበቦቹ! ቤቶቹ! መንገዶቹ ሁሉም ውብ ናቸው፡፡ ከትግራይ የተገኘው ዝነኛው ብርሃነ ሃይለ አንድ ላይ በነበርነት ዘመን ለከረኗ ጉብል እንዲህ ብሎላታል፡፡
ሸው በሊ ብለነይ ብለነይ
ዝለሊ ብለነይ ብለነይ
አሊሊ ብለነይ ብለነይ
አቲ ጓል ከረነይ ብለነይ
አዎን! ቢለን ከከረን ከተማ ጋር ስሙ የሚጠቀስ ብሄረሰብ ነው፡፡ ቋንቋው ከኛው የአገው ቋንቋ ጋር አንድ ዐይነት ነው፡፡ እንግዲህ እዚህ ላይ ነው አንባቢ ሊመራመር የሚገባው፡፡ በወሎና በጎጃም የሚኖረው አገው ምን ሊያደርግ እዚያ ሄደ?… መቼ ነው እዚያ የሄደው?… መላምት ከመዘብዘብ በስተቀር ማንም ሰው ይህንን እንቆቅልሽ በሚያመረቃ ሁኔታ ሊፈታው አልቻለም፡፡ ኤርትራና እኛ አንድ ነን የሚያሰኘኝ እንዲህ ዓይነት ተጨባጭ ማስረጃ ስላለን ነው፡፡
ቢለን ውብ ባህል ያለው ህዝብ ነው፡፡ በዚህ ህዝብ ባህል መሰረት ሴቶቹ ካገቡ በኋላ ጸጉራቸውን መሰተር ግድ ነው፡፡ ህዝቡ የቢለን ቋንቋ ተናጋሪ ቢሆንም የትግረ ቋንቋንም ይጠቀማል፡፡ ትግርኛም በስፋት ይነገራል፡፡ እጅግ ታዋቂ የሆነው የቢለን ተወላጅ “ዑመር እዛዝ” ነው፡፡ የጀብሃ ጦር ከመፍረክረኩ በፊት የሁለተኛው ዞን አዛዥ እንደነበረ ከዚህ በፊት ጽፌ ነበር፡፡
ከከረን ሽቅብ ወደ ሰሜን ስናመራ ታሪካዊቷ አፋቤት አለች፡፡ ጄኔራል ታሪኩ አይኔ የሚመራው ናደው እዝ እዚህ ነበር የሰፈረው፡፡ የቀይ ኮከብ ዘመቻ ዋና አምባም ይህ ነበር፡፡ ከአፋቤት ወደ ሰሜን ስንበር ንዳዳማውና አስቸጋሪው የሳህል መሬት አለ፡፡ በዓሉ ግርማ እንደተረከልን ከሆነ ሳህል ማለት እሳት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ይኖሩበታል፡፡ ከብቶች ይሰማሩበታል፡፡ ተክልም ይበቅልበታል፡፡ እዚህ አካባቢ በብዛት የሚኖረው ህዝብ “ረሺዳ” ይባላል (አንዳንዶች “ራሻይዳ” ይሉታል፤ ስህተት ነው፤ ትክክለኛው አጠራር “ረሺዳ” ነው)፡፡
የ“ረሺዳ” ህዝብ ከሌላው የኤርትራ ህዝብ የሚለይበት በርካታ ነገሮች አሉት፡፡ ለምሳሌ ይህ ህዝብ ከሳዑዲ ዐረቢያ ተነስቶ ወደ ኤርትራ የገባው በቅርብ ዘመን (በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ) ነው፡፡ በዚያ ወቅት የአሁኗ ሳዑዲ ዐረቢያ አልነበረችም፡፡ ሀገሩ ሁሉ በጎሳዎች የተከፋፈለ በረሃማ ምድር ነበር፡፡ ከነዚህ ጎሳዎች አንዱ አል-ረሺድ ይባላል፡፡ ይህ የአል-ረሺድ ህዝብ የአካባቢው የበላይ እንዲሆን በኦቶማን ቱርክ ተወሰነ፡፡ አብዛኛው ህዝብም ለነርሱ አደረ፡፡ “አል-ሱዑድ” የሚባለው ቤተሰብ ግን “አሻፈረኝ” አለ፡፡ “ራሴ በረሃውን ጠቅልዬ መግዛት ስችል ለምን በአል-ረሺድ ጎሳ የበላይነት አድራለሁ” በማለት አንገራገረ፡፡ በሁለቱ መካከል ጠብ ተነሳ፡፡ በመጀመሪያው ላይ የአል-ረሺድ ጎሳ አሸነፈ፡፡ አል-ሱዑዲዎች ወደ ኢራቅ ሸሹ፡፡
ከጥቂት ዓመታት በኋላ ግን የአል-ሱዑድ ቤተሰብ በእንግሊዞች ደጋፊነት ራሱን አጠናክሮ መጣ፡፡ በአል-ረሺድ ጎሳ ላይም ድልን ተቀዳጀ፡፡ በዚህም የተነሳ የዐረቢያ በረሃ ለአል-ረሺድ ጎሳ አባላት ሲኦል ሆነ፡፡ ረሺዳዎች እየተያዙ በጅምላ ታረዱ፡፡ ንብረታቸው ተዘረፈ፡፡ በፊት ይረዳቸው የነበረው የቱርኮች መንግሥት በራሱ ችግር በመወጠሩ ምንም ሊያደርግላቸው አልቻለም፡፡ በመሆኑም ከእልቂቱ ለመዳን ሲሉ ባህር እያቋረጡ ወደ አፍሪቃ ምድር ተሰደዱ፡፡ በሱዳንና በኤርትራ መኖሪያቸውን ቀለሱ፡፡
እንግዲህ ረሺዳዎች ከዘር ማጥፋት ወንጀል ለመሸሽ ወደ ኤርትራ የመጡ ተፈናቃዮች ናቸው ማለት ነው፡፡ በኤርትራ ውስጥ ንጹህ የዐረብ ዝሪያ የሚባሉት እነርሱ ናቸው፡፡ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውም ዐረብኛ ነው፡፡ በረሺዳ ባህል መሰረት ለአካለ መጠን የደረሰች ማንኛዋም ሴት ፊቷንም ሆነ ጸጉሯን መሸፈን ግዴታዋ ነው፡፡ በዓሉ ግርማ በኦሮማይ ውስጥ ሲተርክልን “ማንኛውም የረሺዳ ባል የሚስቱን ፊት ገልጦ የሚያይበትን ሰው አይፈልግም” በማለት የተናገረውም የባህላቸው አንድ አካል ነው፡፡
—————–
ታላላቅ ግድቦችን በመሥራት ላይ የሚገኙ ታዳጊ አገራት ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸው ተነገረ፡፡ በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረገው የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ባወጣው ዘገባ መሠረት አገራቱ ለከፍተኛ ዕዳ እና ከዚያ ጋር ተዛማጅ ለሆኑ ችግሮች የሚጋለጡ መሆናቸውን ፋይናንሺያል ታይምስ ጥናቱን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ “ለሕዝባችሁ የምታስቡ ከሆነ ገንዘቡን ለሌላ ተግባር አውሉት” በማለት ምክርም ሰጥቶዋል፡፡
እኤአ ከ1934ዓም ጀምሮ በ65 አገራት የተገነቡ 245 ግድቦችን በማካተት የተደረገው በዓይነቱ ለየት ያለው አጠቃላይ ጥናት በቅርቡ እየተገነቡ ያሉትን ታላቅ ግድቦችንም ያካተተ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ካለው የግልገል ጊቤ ሦስት ግድብ ጀምሮ እስከ ብራዚሉ የአማዞን ቤሎ ሞንቴ የግድብ ፕሮጀክቶችን የሚገነቡት ታዳሽ ኃይልን አጠቃቀም ለማጎልበት እና የኤሌክትሪክ አቅርቦትን ለመጨመር በሚል እንደሆነ የጠቀሰው ጥናታዊ ዘገባ ግንባታው በርካታዎችን ከመኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ የሚያደርግና ለብዝሃ ህይወት አደጋ እንዲጋለጡ የሚያደርግ መሆኑን ጠቁሟል፡፡
እንደነዚህ ዓይነቱን የግድብ ሥራ የሚቃወሙ ቡድኖች እንደሚሉት የታላላቅ ግድቦች የኮንስትራክሽን ወጪ ሲጀመር ከታሰበው በጀት በአማካይ ከ90 በመቶ በላይ ተጨማሪ ወጪ የሚያስከትል እንዲሁም ከአስር ግድቦች ስምንቱ ከተወሰነላቸው የመጠናቀቂያ ጊዜ እንደሚያልፉ ይናገራሉ፡፡ በመሆኑን በኢትዮጵያና በብራዚል የሚገነቡት ግድቦች የፓኪስታንንና የምያንማርን (በርማ) ጨምሮ “ከፍተኛ ወጪ እንዲሁም ከመመጠናቀቂያ ጊዜያቸው በማለፍ የአገራቱን የኢኮኖሚ ገጽታ ችግር ውስጥ” እንደሚከቱ ዘገባው ያስረዳል፡፡
ጥናቱን ያቀረቡት ምሁራን እንደሚሉት ግድብ መሥራት አስፈላጊና እነርሱም በዚህ ጉዳይ ላይ ተቃዋሚ አለመሆናቸውን በአጽዕኖት ተናግረዋል፡፡ ችግሩ ያለው ታዳጊ አገራቱ ካላቸው የኢኮኖሚ ሁኔታ አኳያ በእንደዚህ ዓይነት የታላላቅ ግድብ ሥራ ላይ መጠመዳቸው ወደፊት ግድቦቹ በሥራ ላይ ሲውሉ ከሚጠይቁት ከፍተኛ ወጪና አገራቱ ግድቦቹን ለማንቀሳቀስ ከሚጠፈለግባቸው ከፍተኛ የፋይናንስ ጥያቄና ብቃት ማነስ አኳያ ሁኔታው እጅግ አሳሳቢ መሆኑን በመዘርዘር አስረድተዋል፡፡ “በመሆኑም” ይላሉ ከምሁራኖቹ አንዱ “በመሆኑም ይህንን ሁሉ ሁኔታ አንድ ላይ ስንወስደው ግድቦቹን መገንባት ስሜት የሚሰጥ አይደለም፡፡”
እንዲህ ያለው መረጃና ማስጠንቀቂያ ይፋ ቢሆንም የግድቦቹን መሠራት የሚደግፉ ወገኖች ቀድሞ የተሠሩ ስህተቶች እንዳይደገሙ አድርገን ነው የምንገነባው በማለት ለሚቀርበው ማስረጃ መከላከያ ይሰጣሉ፡፡ ሆኖም የኦክስፎር ዩኒቨርሲቲ ዘገባ የበርካታ ዓመታት መረጃ በመውሰድ ያወጣው ዘገባ ላይ እንዳመለከተው የግድቦቹን ሥራ ለማጠናቀቅ፣ ከተሰሩም በኋላ ለጥገናና ግድቦቹ በሥራ ላይ እንዲቆዩ ለማካሄድ የሚወጣው ወጪ ባለፉት በርካታ ዓመታት እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ እንዳልመጣ ያስረዳል፡፡ በጥናቱ ላይ የተሳተፉ ሌላው ምሁር ሲናገሩ “እነዚህ ኢኮኖሚያችን እያደገ ነው የሚሉ አገራት በእርግጥ ለዜጎቻቸው ዋስትና ግድ የሚላቸው ከሆነ ገንዘባቸውን ከታላላቅ ግድብ ሥራ ይልቅ በሌላ (ሰብዓዊ) ተግባር ላይ ቢያውሉት ይሻላል” ብለዋል፡፡
ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት የኦሞ ወንዝን ተከትሎ በሚገነባው ግድብ ላይ ስለተፈናቀሉት ዜጎች በቅርቡ ባወጣው በሳተላይት ፎቶ በተደገፈ ማስረጃ መሠረት በኢትዮጵያና በኬኒያ የኦሞን ወንዝ ተከትለው የሚኖሩ እስከ ግማሽ ሚሊዮን የሚደርሱ የአካባቢው ነዋሪዎች በግድቡ ሥራ ምክንያት የመኖር ኅልውናቸው ያከተመ መሆኑን ዘግቦ ነበር፡፡ ሰሞኑን የኢህአዴግ ባለሥልጣናት (ከግብርና ሚ/ር) በኢህአዴግ ፓርላማ ሲጠየቁ በሰጡት ቃል አንዳችም የተፈናቀለ ሰው የለም በማለት የመለሱ ሲሆን በተደጋጋሚ ማስረጃ ተደግፎ የሚወጣውን መረጃ አጣጥለውታል፡፡
(ፎቶ: AP)
goolgul
ዘወትር ቅዳሜ ማታ ከደሳለኝ መኮንን ጋር፣ምርጥና አዳዲስ የካንትሪ ማለትም የአሜሪካ አገር ሰብእ፣ የሮክ፣ተሶል፣የፖፕ፣የአር-ኤን-ቢ፣ብሉዝ፣የሬጌና የሂፕ-ሃፕ ዜማዎችን እንዲያደምጡ ተጋብዘዋል።
የትላንት በስቲያውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን መታሰቢያ ተንተርሶ በተሠናዳው ታላቁ ሩጫ “ሃሳባቸውን ለመግለጥ” የወጡ ያላቸው አባሎቹ ለእስር ተዳረጉ ሲል፤ ሰማያዊ ፓርቲ ወነጀለ።
ይበልጡን የፓርቲው አባልና የአመራር አባል የሆኑ ወጣት ሴቶች የሚገኙባቸው በርካቶች አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኙ ነው፤ ሰማያዊ ፓርቲ ያስታወቀው።
በእንቅስቃሴው በመሳተፋቸው ብቻ የደምብ ልብስ በለበሱ ፖሊሶችና እንዲሁም የሲቪል ልብስ በለበሱ የደህንነት ሠራተኞች ለአጭር ጊዜ ተይዘው ከቆዩ በኋላ፥“ሁከትና ሽብር እያነሳሳችሁ፤” የሚል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው መለቀቃቸውን የፓርቲው የሴቶች ጉዳይ ምክትል ኃላፊ ወ/ሪት ኢየሩሳሌም ተሥፋው።
በኢትዮጵያ የአዉሮፓ ሕብረት ልኡካን ቡድን መሪ አምባሳደር ቻንታል ሔበሬሽ፣ በአዉሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ እና የሕንድ ዉቂያኖስ አካባቢ ዴስክ ኦፌሴር ቪክቶሪያ ጋርሲያ ጉሌን እንዲሁም ቶማስ ሁይገባርቴስ የተሰኙ ፣ የአዉሮፓ ሕብረት ሃላፊ ፣ በነርሱ አነሳሽነት፣ ከአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት ጋር ሰፊ ዉይይት አደረጉ። ከአንድ ሳምንት በፊት በኢትዮጵያ ስላለው የዲሞክራሲ ግንባታ ዙሪያ ከጠ/ሚኒስተር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር እንደተነጋገሩ […]
መግቢያ ይህ ጽሑፍ በኢትዮጵያ ላለፉት አስርት አመታት ጎሣና ኃይማኖትን መሰረት አድርገው በተደጋጋሚ ጊዜያት በተከሰቱት ግጭቶች ዙሪያ እና ግጭቶቹ ባስከተሉት ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት ላይ የሚያተኩር ነው። በተለይም ከ1983 ዓ.ም. ወዲህ ጎሣን መሰረት ያደረገውን የኢሕአዴግ ፌዴራላዊ የመንግስት አወቃቀር ተከትሎ በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች ውስጥ የተከሰቱ ዋና ዋና ግጭቶችን ይዳስሣል። ለግጭቶቹ መንስዔ ተደርገው የሚጠቀሱትን ጉዳዮች፣ በግጭቶቹ ሳቢያ በሰው ሕይወትና […]
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
ያቺ ትንሽ ግን ሥልታዊ ምድር ሐያል ዓለም ለጦርነት እንዳሰለፈች ሁሉ-ሐያላንን ለሠላም ሰብስባም ነበር።የሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት አሸናፊዎች የሶቬት ሕብረቱ መሪ ጆሴፍ ስታሊን፥የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳት ፍራክሊን ሩዘቬልት እና የብሪታንያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ዊንስተን ቸርችር ዓለም የሸነሸኑት-ክሬሚያ ላይ ነበር
ትናንት ምሽትም 45 አፍሪቃውያን ስደተኞች በየመን የባህር ዳርቻ መስጠማቸውን የሃገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል ። የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ድረ ገፅ እንዳስነበበው በባህር ዳርቻዋ ከተማ በቢር አሊ ከተማ ከደረሰው ከዚሁ አደጋ 30 ሰዎችን በህይወት ማትረፍ ተችሏል ።
ከአደጋው በኋላ ህዝብና ፖሊስ መጋጨታቸውን በግርግሩም ሶስት ሰዎች በጥይት መቁሰላቸውን የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘግቧል ።

በሴቶች የነጻነት ቀን በሴት አባላቶቻችን ላይ የተወሰደውን ህገ ወጥ እርምጃ እናወግዛለን !
ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
*********************
‹‹ማርች-8›› የሴቶችን ነጻነትና እኩልት እንዲሁም ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ የሚከበር የሴቶች ቀን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህን በዓል አስመልክቶ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ባለፈው ዕሁድ የካቲት 30/2006 ዓ.ም ሴቶች ብቻ የሚሳተፉበት የጎዳና ላይ ሩጫ ማዘጋጀቱ ይታወቃል፡፡ በዚህ የሐገራችንም ሆነ የዓለም ሴቶች የነጻነት ቀናቸውን በሚያከብሩበት ዕለት እንደሌሎች ሴቶች ሁሉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትም አላማውን ደግፈው በዕለቱ ቀኑን አስመልክቶ በተዘጋጀው ሩጫ ላይ ተሳትፈዋል፡፡
እንደሚታወቀው ታላቁ ሩጫ በተለያየ ጊዜ በሚካሄድበት ወቅት ተሳታፊዎች በሐገራቸው የሰፈነውን ጭቆና በመቃወም ሀሳብን የመግለጽ ህገ መንግስታዊ መብታቸውን በመጠቀም ድምጻቸውን የሚያሰሙበት በመሆኑ ‹‹የብሶት መግለጫ›› መድረክ እስከመባል ደርሷል፡፡ ልክ እንዳለፉት ጊዜያት ሁሉ በእሁዱ የጎዳና ሩጫም በርካታ የሩጫው ተሳታፊዎች ይህን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ የመጣውን ጭቆና በመቃወም ድምጻቸውን ሊያሰሙበት ችለዋል፡፡
በዚህ በሴቶች የነጻነት ቀን በስርዓቱ ላይ የሚነሱ ብሶቶችን ካሰሙት ተሳታፊዎች ውስጥ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሚገኙበት ሲሆን፣ በተለየ መልኩ በእነዚህ አባላቶቻችን ላይ ያነጣጠረ የአፈሳ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እንደዚህ አይነት ህዝባዊ መድረኮችን ላይ ብቻ ሳይሆን ሁሌም ህዝብ ላይ የሚደርሰውን በደል በማጋለጥ ለህዝብ መብት እና ለአገራችን ብሄራዊ ጥቅም በመቆሙ በገዥው ፓርቲ ተደጋጋሚ ህገ ወጥ እርምጃ ሲወሰድበት ቆይቷል፡፡ በትናንትናው ዕለት የተደረገውም ከዚሁ ፓርቲው ለህዝብና ለአገር መቆሙን ተከትሎ እየደረሰበት ያለው የከፋ የጭቆና አካል ነው፡፡
ምንም እንኳ ይህ የህወሓት/ኢህአዴግ ህገ ወጥ እርምጃ አዲስ ባይሆንም በሴቶች ነጻነት ቀን በአባላቶቻችን ላይ የተወሰደው ህገ ወጥ እርምጃ አገዛዙ በህገ መንግስቱም ሆነ በሌሎች ህጎች ለሴቶች መብት መከበር የደነገጋቸው አንቀጾች ከወረቀት ያለፉ እንዳልሆኑ በተጨባጭ ያሳየ ምሳሌ ነው፡፡ ከምንም በላይ አባላቶቻችን የታሰሩበት ምክንያት ‹‹የጣይቱ ልጅ ነን፣ የምኒልክ ልጅ ነን›› ማለታቸው እንደሆነ በመርማሪ ፖሊስ የተገለጸላቸው መሆኑ ነው፡፡
ይህም ህወሓት/ኢህአዴግ ምን ያህል ከታሪክ ጋር የተጣላ መሆኑን ከማሳየቱም በተጨማሪ አባላቶቻችን ለማሰር አሳፋሪ የሆኑ ምክንያቶች እየፈለገ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ይህኛውን እርምጃ የተለየ የሚያደርገው ሰማያዊ ፓርቲ በመላው አገሪቱ መዋቅሩን እያደራጀና ህዝብን ከጎኑ እያሰለፈ ባለበት ወቅት መሆኑ፤ የህዝብ ድጋፍ የሌለው ገዥው ፓርቲ በሰበብ አስባቡ ሰማያዊ ፓርቲን ከወዲሁ ለማዳከም የወሰደው ነው፡፡
በተለይ የምርጫ ወቅት እየቀረበ መሆኑን ተከትሎ ይህን ህገ ወጥ እርምጃ መውሰዱ አሁንም ቢሆን የአገራችን የፖለቲካ ምህዳር ምን ያህል እየጠበበ እንደሄደ ያሳያል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ መቼም ቢሆን ይህንና መሰል የአገዛዙን አፈናዎች አጥብቆ የሚያወግዛቸውና የሚታገላቸው መሆኑን እየገለጸ በሴቶች የነጻነት ቀን ያላአግባብ የታሰሩ አባላቶቻችን በአስቸኳይ እንዲፈቱ ይጠይቃል፡፡ ኢትዮጵያውያንና መላው የዓለም ማህበረሰብ ይህን ህገ ወጥ እርምጃ ተመልክቶ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን እንዲቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
መጋቢት 1 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ዛሬ ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ ፍርድ ቤት የቀረቡት የሰማያዊ ፓርቲ ሁለት ከፍተኛ አመራሮችና አባሎች ለመጋቢት 5 ተቀጠሩ
እሁድ ለት በተካሄደው የሴቶች 5000 ሜትር ሩጫ ላይ ለነፃነት እንሩጥ በሚል መርህ በሩጫው ላይ በመሳተፍ በርካታ ፖለቲካዊና መሀበራዊ ጥያቄዎችን ያነሱ የሰማያዊ ፓርቲ የሴቶች ጉዳይ ሀላፊዎችና አባላት እንዲሁም ሰፍራው ንበረቶ ነን ቻቸውን ይዘው የነበሩ ሁለት የፓረቲው ከፍተኛ አመራሮች እና አንድ አባል ታፍሰው ወደ ሾላ የካ ፖሊሰ መምሪያ መወሰዳቸው ይታወቃል ፡፡
በዛሬው እለትም ፍርድቤት ቀርበው የተከሰሱበትን ምክንያት መርማሪ ፖሊሱ /ኮማንደር የማታ/አብራርቷል፡፡ የተከሰሱበት ምክንያት እሁድ በተካሄደው የሴቶች ሩጫ ላይ ተመሳስሎ በመግባት የጣይቱ ልጆች ነን ፣ የምኒልክ ልጆች ነን ፣ ኑሮ መረረን ፣ የህሊና እስረኞች ይፈቱ በሚል ሁከትን ለማነሳሳት ቀስቅሳችኋል የሚልኘ ሲሆን መርማሪው መረጃ አሰባስቤ ስላልጨረስኩና መረጃዎቼን ያጠፋሉ ሰዎችንም እንዳይመሰክሩ ያስፈራሩብኛል በተጨማሪም ብዙዎቹ ቋሚ አድራሻ የሌላቸው ስለሆነ መረጃ እስካሰባስብ የ15 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ብሏል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮችም እድል እየጠየቁ ለማስረዳት ጥረት ያደረጉ ሲሆን የተከሰሱበት ምክንያት ሀሳባቸውን በአጋጣሚው በነፃነት በመግለፃቸውና በተባለው መልኩ ሳይሆን አስበው እና ሩጫውንም እንደማንኛውም ሴት ኢትዮጵያዊ ቲሸርት ገዝተውና ተመዝግበው ሲሆን አሉ የተባለውን እንዳሉ አስረግጠው ነገር ግን ሁከት አለማስነሳታቸውንም እንዲሁም ሩጫው ሲጠናቀቅ አፍሰው እስርቤት እንደወሰዷቸው ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡ አብረው የታሰሩት ወንዶችም በወቅቱ በቦታው የጓደኞቻቸውን እቃዎች ተሸክመው ሩጫውን እስኪፈፅሙ እየጠበቁ በነበረበት ሰዓት ሴቶቹን እየለቀሙ ሲወስዱ ለምንድነው የምትወስዷቸው በማለታቸው ብቻ አብረው እንደታሰሩ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡ አክለውም እኛ ህጋዊ ሰውነት ያለን የፓርቲ አመራሮችና አባላት ነን ስራችንም በዚሁ በአዲስ አበባ ሆኖ ሳለና በተፈለግን ጊዜ የምንገኝበት ግልፅ አድራሻ በምርመራ ወቅት ተመዝግቦ እያለ ዋስትና አይሰጣቸው የተባለው ተቀባይነት የለውም እንዲሁም መረጃ ላሰባስብ የሚለውም ምክንያት ሁሉም ንብረቶቻችን በወቅቱ ተወስደው በፖሊሶች እጅ የሚገኝ ስለሆነ ተገቢ አይደለም በሚል ፍርድ ቤቱን ሞግተዋል፡፡
ክሱን የሚመራው ኮማንደር ይህን በማስተባበል የዋስትና መብታችን ይከበር ማለታቸውን “ፍርድ ቤቱ እንደሚያውቀው በሀገሪቱ ያለው ነገር የታወቀ ነው የአሸባሪዎች ስጋት አለ እና ከዛ ጋር የሚተባበሩ ተልዕኮ ያላቸው ስለሆኑ ለማጣራት ጊዜ ያስፈልገኛል” በማለት የዋስትና መብታቸው እንዲነሳ ጠይቋል፡፡
በመጨረሻ ዳኛው ኮማንደሩ ይህን ለማጣራት የጠየቀው ጊዜ የተንዛዛ ስለሆነ በአምስት ቀን ውስጥ አጣርቶ ለአርድ መጋቢት 5 እነዲቀረቡ አዞአል ለታሰሪዎቹም ፓርቲው አሰፈለጊውን ሁሉ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
በሀገር ወሰጥ ሆነ ከሀገር ውጭ ሆናችሁ ደጋፍ ላደረጋችሁልን ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን፡፡
የኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች በዶ/ር ደብረጺሆን ፍቃድ ካልሆነ ምንም አይነት ውሳኔ መስጠት አይችሉም::
የደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋና ባለስልጣኖቻቸው በሙስና እና በዘረፋ ላይ ተሰማርተዋል::
የፍርድ ቤቶች እና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴ ማኮላሸት ለአለቃ ጸጋዬ በርሄ ተሰቷቸዋል::
የጦር ሰራዊቱን በተጠንቀቅ የሚከታተሉ ወታደራዊ ደህንነቶች ተደራጅተው በየእዙ ተበትነዋል::
ምንሊክ ሳልሳዊ በመከላከያ ሰራዊት የሕወሓት መኮንኖች ስር የሰደደው የሙስና እና የዘረፋ አድራጎት በደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥም ከሹሙ ከአቶ ጌታቸው እና ከባለስልጣኖቻቸው ጀምሮ እስከ ገራፊዎች ድረስ መንሰራፋቱን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል:: እንደውስጥ አዋቂ ምንጮቹ መረጃ ከሆነ የደህንነት ባለስልጣኖቹ የተዘፈቁበት የሙስና ተግባር በተጨማሪ ዘረፋን እና ሴት መድፈርን እንዲሁም የቡድን ወንጀሎችን ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል::በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ባለሃብቶችን በማስፈራራት ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ውጪ በማሰር እንዲሁም የሙስና ወንጀል ተገኝቶብሃል ይህን ያህል ገንዘብ አምጣ ካላመጣህ እንገድልሃለን እስከማለት በከመድረሳቸውም በተጨማሪ ይህንን ጉዳይ ለፖሊስ የጠቆመ ባለሃብት በማፈን ንብረቱ ባማገድ እና በተለያዩ ስልቶች የተጠየቀውን ገንዘብ እንዲሰጥ በማስገደድ ላይ መሆናቸውን ምንጮቹ ጠቁመዋል::
ከዚህ ቀደም በሙስና የተከሰሱ የስርኣቱ ባለስልጣናትን ተገን በማደርግ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ባለሃብቶችን በመከታተል እና ደህንነት ቢሮ ድረስ በመውሰድ በሙስና ከታሰረው ስም እየተጠቀሰ … ከሚባል ባለስልጣን ጋር ግንኙነት አለህ ማስረጃ ተገኝቶብሃል በማለት በፈጠራ ወንጀል ባለሃብቱን በመዝረፍ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበረ እና እንዲሁም የአዲስ አበባን ቆነጃጅት ቢሯቸው ድረስ በግብረአበሮቻቸው አፋኝነት እና አስገዳጅነት በመውሰድ ካለፍላጎታቸው አስገድደው በመድፈር ላይ ናቸው ያሉት ምንጮቹ ተራ የደህንነት አባላት ለዚሁ ተልእኮ ተሰማርተው የሚሰሩት ምንም አይነት ወንጀል በቡድን ሲፈጽሙ የሚጠይቃቸው አለመኖሩን የሕዝቡን በደል የከፋ አድርጎታል::ምንሊክ ሳልሳዊ
ኢትዮጵያውያን በሕወሓቱ የደህንነት መዋቅር የሚመራ የሽብር ተግባራትን አጥብቆ ስለሚፈራ እና በየጊዜው በሕወሓት ደህንነቶች መሪነት የሚወሰዱ እርምጃዎች በሃገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ስጋትን በመፍጠራቸው በየእስር ቤቱ የሚካሄዱ ሕገወጥ ጸረ ፍትህ ተግባራት እና የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች የኢትዮጵያውያን የቀን ተቀን አጀንዳ ሆነው መምጣታቸው ገዢው ፓርቲ ሕዝቡን ምን ያህል እንዳሸበረ ይጠቁማል ሲሉ ምንጮሹ አክለው ገልጸዋል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሕወሓትን ሳይጨምር ብኣዴን ኦሕዴድ ደኢሕዴግ እና አጋል የክልል ጎሳ ፓርቲዎች ከአቶ ደብረጺሆን በሚወርድ ትእዛዝ ካልሆነ በስተቀር ምንም አይነት እርምጃ በፍቃዳቸው መፈጸም እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል:: በቅርቡ የአቶ አለማየሁ አቶምሳን ሞት ተከትሎ አፈጻጸሙ በዶ/ር ደብረጺሆን መልካም ፍቃድ እንደሆነ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የተባለው የኦሕዴድ ሙክታር ከድር አቶ አለማየሁ ደክመው እያየ እና እያወቀ ሆስፒታል እንዲሄዱ አስቸኳይ ትብብር እንዲደረግ ወይዘሮ አስቴር ማሞ ስትጠይቀው ለዶ/ር ደብረጺሆን ነግረሽ አስፈቅጂ በማለት ሕወሓት በኦሕዴድ አናት ላይ ምን ያህል እየሸና እንዳለ እንዲሁም በሞራላቸው አመራሮቹ እንዳይራመዱ እያደረገ እንዳለ ፍንትው አድርጎ ያሳየ ነው:: ማንኛውም የኢሕኣዴግ አባል እና አጋር ድርጅት በድርጅቱ ሊቀመንበር ወይንም ምክትል አማካኝነት በቅድሚያ ለዶ/ር ደብረጺሆን ሪፖርት ማድረግ እና ሁኔታው ታይቶ ፈቃድ እና ውሳነ ካልተሰጠው በስተቀር መፈጸም እንደማይችል ትእዛ መተላለፉ ሲታወቅ በአዲስ አበባ እና በክልል ያለው የፍርድ ቤቶች እና የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ በአለቃ ጸጋይ በርኸ ስር ክትትል እየተደረገ እርምጃ የሚወሰድበት መሆኑ ሲታውቅ የጦር ሰራዊቱን በተመለከት በተዋረድ የሚያስተዳድሩ የወታደራዊ ደህንነት የሕወሓት መኮንኖች ተደራጅተው በየእዙ መመደባቸው ታውቋል:: ምንሊክ ሳልሳዊ
![]()

ከዚህ ቀደም በተለያየ ጊዜ በተዘጋጁ ሁለት ፅሁፎች፣ የድህረ መለስን ኢህአዴግ የኃይል አሰላለፍ ለማመልከት መሞከሬ የሚታወስ ቢሆንም፤ ዛሬም ያልተጠበቁ ክስተቶችን ማስተዋላችን አልቀረም፡፡ በርግጥ «አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ ፪» በሚል ርዕስ ቀርቦ በነበረው ተጠየቅ ከሞላ ጎደል ሀገሪቷን እንደንጉስ ሚካኤል ከጀርባ ሆነው የሚያሽከረክሯት ህወሓት እና ብአዴን መሆናቸው የተጠቀሰበት አውድ ብዙም አልተቀየረም፡፡ ይሁንና በኦህዴድ እና ደኢህዴን ውስጥ እየታየ ያለው የእርስ በእርስ መተጋገል መደምደሚያ ምናልባት ወቅታዊውን መልከአ ኢህአዴግ ሊለውጠው የሚችልበት አጋጣሚ እንዳለ እገምታለሁ፤ ማን ያውቃል? …እነዚህን ኩነቶች ታሳቢ አድርገን የገዢው ፓርቲ አክራሞትን በአዲስ መስመር ጨርፎ ወደመመልከቱ እንለፍ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ «ብላቴኖች»
ክልሉን የሚያስተዳድረው የደኢህዴን የአመራር አባላት በስርዓቱ ልሂቃን የፖለቲካ ግምገማ ገና «ብላቴና» ተደርገው የሚወሰዱበት የትምክህት ዘመን አላከተመም፡፡ በርግጥ ድርጅቱ ደርግን ለመጣል በተደረገው የትጥቅ ትግል ላይ የተሳተፈ ባለመሆኑ፣ ዛሬም ፖለቲካን (ሀገር ማስተዳደርን) በበረሃው ትግል ተፈትኖ ከማለፍ ጋር ከሚያጋምዱት የግንባሩ ጉምቱ መሪዎች ዘንድ፣ ይህን መሰል ማጣጣያ የሚጠበቅ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለደኢህዴን ደካማነት በምክንያትነት የሚነሳው ጉዳይ ከአወቃቀሩ ጋር የሚያያዝ ነው፤ ይኸውም በክልሉ የሚገኙ 56 የተለያዩ ዘውጎችን ማቀፉ ለመከፋፈል አደጋ በቀላሉ የሚጋለጥበትን ዕድል የማስፋቱ እውነታ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ከክልሉ ነዋሪዎች በቁጥር የሚልቁት የወላይታና የሲዳማ ተወላጆች፣ በደኢህዴን ውስጥ ያላቸው ተሰሚነት (ተፅዕኖ) የገዘፈ መሆኑን ለመረዳት፣ ሕገ-መንግስቱ ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ የፓርቲውን ሊቀ-መንበርነትም ሆነ የክልሉ ፕሬዚዳንትነት ከሁለቱ ብሔሮች በቀር፣ ለሌሎቹ የሰማይ ያህል የራቀ ያደረገውን «ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት» መጥቀሱ በቂ ነው፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የፓርቲው ሊቀ-መንበር ኃይለማርያም ደሳለኝ የያዘውን መንግስታዊ ስልጣን የሚመጥን ተሰሚነት ለማግኘት ድርጅታዊ ድጋፍ ማሰባሰብ ላይ ያተኮሩ የሚመስሉ ክስተቶችን ሲከውን ታዘብናል፡፡ ኩነቱን በስነ-አመክንዮ ለማጠናከር ጥቂት ማሳያዎችን ላቅርብ፡- በጠቅላይ ሚኒስትርነት መንበር ላይ ከተቀመጠ በኋላ፣ በደኢህዴን ውስጥ ያሉ የተወሰኑ ተገዳዳሪዎቹን ከኃላፊነታቸው ከማንሳትም አልፎ፣ ደጋፊዎቹ (ታማኞቹ) እንደሆኑ የሚነገርላቸውን በከፍተኛ ሥልጣን ላይ አስቀምጧል የሚያስብለው፣ ከወራት በፊት በፓርቲውም ሆነ በደቡብ ክልል ከእርሱም የበለጠ ተሰሚነት የነበረውን ሽፈራው ሽጉጤን አንስቶ፤ ትጉህ አገልጋዩ እንደሆነ የሚነገርለትን ደሴ ዳልጌን ተክቶታል፤ በቅርቡ ደግሞ ሌላኛው ‹የደኢህዴን ቁልፍ ሰው› የሚባለው የፖለቲካ (የድርጅት) ጉዳይ ኃላፊ እና የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አለማየሁ አሰፋን ያለአንዳች ኮሽታ «በትምህርት ስም» ከቦታው አንስቶታል (ይህ ጉዳይ እስከአሁን ድረስ መንግስታዊው ሚዲያ የዜና ሽፋን አላገኘም)፡፡ በግልባጩ ታማኝነታቸውን ያስመሰከሩ፣ ከሲዳማ ብሔር ውጪ ያሉ ጓዶቹን በፌደራል መንግስቱ ወሳኝ የስልጣን እርከኖች ላይ አስቀምጧል፡፡ ለማሳያ ያህልም አሰፋ አብዩ /ሀድያ/፣ ወርቅነህ ገበየውን ተክቶ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር፤ ደበበ አበራ /ከፋ/፣ የኢህአዴግ ዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ፤ ውዱ ሀቶ /ሸካ/፣ የፀረ ሙስና ምክትል ኮሚሽነር፤ አማኒኤል አብርሃም /ወላይታ/፣ በሚኒስቴር ዴኤታ ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕዝብ አደረጃጀት አማካሪ፤ ሰለሞን ተስፋዬ /ጉራጌ/፣ በተመሳሳይ ማዕረግ የፕሬስ አማካሪ፤ ካይዛ ኬ (ጂንካ) በገቢዎች ባለስልጣን የገብረሀዋድን ቦታ ተክቶ የገባ እና የፌደራል ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት ምክትል ኃላፊ ተደርጋ የተሾመችውን የወላይታዋ ተወላጅን መጥቀስ ይቻላል (ከደኢህዴን የሥራ-አስፈፃሚ አባላት መካከል የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትሩ ሬድዋን ሁሴን እና መከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈጌሳም የሲዳማ ተወላጅ አለመሆናቸውን ልብ ይሏል) ይህንን ጉዳይ እንዲህ በብሔር ደረጃ ቁልቁል አውርደን እንድንመለከተው የሚያስገድደን ስርዓቱ ከሚያራምደው የፖለቲካ ፍልስፍና እና በክልሉ እየተነሱ ካሉ የማንነት ጥያቄዎች ጋር የመቆራኘቱ አንድምታ ነው፡፡ በተለይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሲዳማዎች ራሳቸውን ችለው
በክልል ደረጃ ለመዋቀር ተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበው አያሌ መስዋዕትነትን መክፈላቸው ይታወሳል (በኢህአዴጋዊ የክልል አሰያየም ቀመር ሕገ-መንግስታዊ ድጋፍ ያላቸው መሆኑ ሳይዘነጋ)፡፡ ይሁንና ጥያቄው ተቀባይነት ቢያገኝ የክልሉ አስተዳደር መቀመጫ የሆነችውን አዋሳን ከመውሰዳቸውም በላይ፣ ሊያስከትል የሚችለው አለመረጋጋት ሲታከልበት፣ ህዳጣን ልሂቃኑን የኢኮኖሚ ጥቅመኝነት ያሳጣቸዋል፡፡ ይህ ስጋትም በደኢህዴን ውስጥ ከሲዳማ ተወላጆች ውጪ ካሉ የአመራር አባላት ድርጅታዊ ድጋፍ ለማግኘት ብርቱ ትግል ከሚያደርገው ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር በወሳኝ ሰዓት፣ መሀል መንገድ ላይ ቢያስተቃቅፋቸው የማይታመን አይሆንም፡፡
የእነዚህ አዳዲስ ኩነቶች (ሹም ሽሮች) መግፍኤ፣ በሁለት የቢሆን ሃሳቦች ተነጣጥለው ሊታዩ ይችላሉ፡፡ የመጀመሪያው ኃይለማሪያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚንስትርነት ሹመቱን ተከትሎ ‹በዚህ ላይ ፈርም›፣ ‹ይህንን ተናገር›፣ ‹እንዲህ አይነት አስተያየት ስጥ!!› ወዘተ የሚሉ ከጀርባ ሆነው የሚሾፍሩት የአለቆቹ ቀጭን ትዕዛዛትን የሚገዳደርበት ፖለቲካዊ ጉልበት ለማሰባሰብ እና በቁርጥራጭ ጨርቅ በተጣጣፈው እናት ድርጅቱ ውስጥ ያሉ ችግሮችን ስልታዊ በሆነ መልኩ አስወግዶ ቅቡልነቱን ለማጠናከር እንቅስቃሴ ጀምሯል የሚል ሊሆን ይችላል፡፡
ሌላኛው ደግሞ ከኢትዮጵያውያንም አልፎ በውጪ ዜጎች ሳይቀር ‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሻንጉሊት ነው› የሚለውን እምነት ለማስቀየር በህወሓትና ብአዴን እየተደረገ ያለ ፖለቲካዊ ጨዋታ ሊሆን የመቻሉ ጉዳይ ነው፡፡
ኦህዴድ
ባለፉት የህወሓትም ሆነ የአቶ መለስ ዜናዊ የበላይነት በገነኑባቸው ዘመናት፣ ኦህዴድ ምንም እንኳን ስርዓቱን ካነበሩ የግንባሩ አባል ድርጅቶች አንዱ መሆኑ ባይካድም፣ በስጋት መታየቱ የአደባባይ እውነታ ነው፡፡ እንዲያውም በአንድ ወቅት አቶ መለስ ራሱ «ኦህዴድ ሲፋቅ ኦነግ ነው» ማለቱ አይዘነጋም፡፡ ከሶስት ያላነሱ የስራ አስፈጻሚ አባላቱ፣ ድርጅቱን ከድተው ኦነግን መቀላቀላቸውም የውንጀላው ማሳያ ተደርጎ እስከመወሰድ ደርሶ ነበር፡፡ ይህ ሁኔታም ኦህዴድን የተረጋጋ አመራር እንዳይኖረው ከማደናቀፉም ባሻገር፣ በተቀነባበረ ማኪያቬሊያዊ ሴራ እርስ በርስ በማይተማመኑና በተከፋፈሉ ሰዎች ስር እንዲቆይ አስገድዶታል፡፡ ግና፣ ኩነቱን ምፀት የሚያደርገው ህወሓት በረሃ እያለ ያሳትመው በነበረው ልሳኑ «የኦሮሞ ጥያቄና የኢትዮጵያ አብዮት» በሚል ርዕስ ባሰራጨው ፅሁፍ ኢህአፓን «የኦሮሞ ሕዝብ በነፍጠኛው ላይ የነበረውን ተገቢ ጥላቻ በማራገብ ፋንታ ለማብረድ በተጨባጭ ተንቀሳቅሷል» («የትግል ጥሪ» 3ኛ ዓመት ቁጥር 10፣ 1979 ዓ.ም) ሲል ይከስሰው እንደነበረ ማስተዋላችን ነው፡፡
በአናቱም አቶ መለስ እስከ ህልፈቱ ድረስ በኦህዴድ ደስተኛ እንዳልነበረ ይነገራል፡፡ ይህ ግን ‹የኦሮሞን ሕዝብ በአግባቡ አላገለገለም› ከሚል ቁርቆራ የተነሳ አይደለም፤ እንዲህ አይነቱ ስሜት ሌላውን ክልል ቀርቶ ትግራይንም የሚመለከት ቢሆን አሳስቦት አያውቅምና፡፡ የእርሱ ቅሬታ ‹ህዝቡን አሳምነውም ሆነ ጠርንፈው ከድርጅቱ ጎን አላሰለፉትም›፣ ‹ሁላችንንም በሚያሳጣ መልኩ ዘረፋ ውስጥ ገብተዋል›፣ ‹ዲሲፕሊን የላቸውም…› የሚሉና ሌሎች መሰል መነሾዎች ናቸው፡፡ እንዲህ ያለ የድርጅቱ «እንዝህላልነት» ደግሞ የህዝቡ ልብ ይበልጥ ኦነግን እንዲናፍቅ ማስገደዱን መለስ ዜናዊ ጠንቅቆ ያውቅ ነበር፡፡ ለዚህም ይመስለኛል የክልሉን ባለስልጣናት ሁሉ ወደ ጎን ብሎ እታች ድረስ በመውረድ የወረዳ አመራሮችን ቀጥታ ያለ ሥልጣን ተዋረድ በስልክ እስከማናገር የተገደደባቸው ቀናት የበዙት፡፡ በርግጥ በድርጅቱ ስብሰባዎች ላይ መተላለፍ ያለባቸውን ውሳኔዎች በፅሁፍ መስጠት እና ለአመራርነት የሚመረጡ ሰዎችን መመደብ ድረስ ባሉ ጉዳዮች ጣልቃ የመግባቱ ነገር ማንም አሌ የማይለው በግልፅ ይታይ የነበረ ክስተት ነው፡፡
የሆነው ሆኖ ከምንጮቼ እንዳረጋገጥኩት አባዱላ ገመዳ ዕድሜውን ሙሉ ሲፈራ የኖረው መለስ ዜናዊን ብቻ ነበር፤ መለስ ደግሞ ይህችን ምድር ለመጨረሻ ጊዜ ከተሰናበታት አንስቶ የተቆጠሩት በርካታ ወራት ፍርሃቱን ጥሎ ነፃነቱን እንዲጎናፀፍ ለመርዳት ያስችሉታል ብዬ አስባለሁ፡፡ እናም በዚህ መልኩ ተፈጥሮ ያመቻቸለትን ታሪካዊ አጋጣሚ ተጠቅሞ ይደቆስ የነበረውን ኦህዴድ ከወደቀበት ለማንሳት ሙከራዎችን እያደረገ ይመስለኛል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኦህዴድ በሚያደርጋቸው ስብሰባዎች ላይ የሚቀርቡ አንዳንድ አጀንዳዎችና አቋሞችን የአባዱላ ግፊት እንዳለባቸው ስናስተውል፣ «ጄነራሉ» ወሳኝ ሰው ለመሆን እያደረገ ያለው የጥንጣን ጉዞ ምን ያህል እየሰመረለት እንደሆነ ለመረዳት ያስችላል፡፡ ይህንን መከራከሪያ ከለጠጥነው ደግሞ፣ ከህወሓት/ብአዴን ጋር ትከሻ መገፋፋት ጀምሯል ወደሚል ጠርዝ ይገፋናል፡፡ ይህም ባይሆን እንኳ ከኃይለማርያም ደሳለኝ የተሻለ ተሰሚነት እንዳለው ለመናገር የሚያስደፍሩ ማስረገጫዎች አሉ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቀን የከዳ ዕለት በተናጠል በኃላፊነት ሊያስጠይቁት የሚችሉ ጉዳዮችን ሳይቀር፣ በያዘው ሕገ-መንግስታዊ ሥልጣን ከመወሰን ይልቅ በቡድን እንዲያልቅ ሲስማማ፤ በግልባጩ አፈ-ጉባኤው ከዚህ ቀደም በምክር ቤቱ ውስጥ ተነስተው ለአቶ መለስ ይቀርቡ የነበሩ ጉዳዮችን ወዲያውኑ መፍትሔ እንዲያገኙ በማድረግ ሲቋጫቸው ተደጋግሞ ተስተውሏል፡፡ ኦህዴድንም በሚመለከት ‹በድርጅታዊ መደጋገፍ› ስም ማንም ጣልቃ መግባት እንደማይችል በይፋ እስከ መናገር መድረሱን ምንጮች ጠቅሰውልኛል፡፡ በቀጣይ አመት የሚደረገውን አምስተኛ ዙር አገር አቀፍ ምርጫን አስመልክቶም እየተደረገ ባለው ዝግጅት በሃሳብ አመንጭነት እየተሳተፈ ነው፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት ለምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ ከሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤት ለተወከሉ እና ምርጫ ቦርድ ሀላፊዎች /ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እና ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሔር በተገኙበት/ «የአውራ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ባህሪያት» በሚል ርዕስ ጥናታዊ ፅሁፍ ማቅረቡ አስረጅ ሆኖ ሊወሰድ ይችላል (በነገራችን ላይ ስርዓቱ በምርጫ ስም የሚፈፅመውን ደባ ፍንትው አድርጎ የሚያሳየው፣ ሁለቱ የቦርዱ ኃላፊዎች የዚህ አይነቱ ውይይት ላይ ተሳታፊ መሆናቸው ነው)፡፡ እንዲሁም ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ በአዳማ ለክልል አፈ-ጉባኤዎች ሰፊ ትንተና ሰጥቷል፡፡
የአባዱላ ገመዳንና የበረከት ስምኦንን መገፋፋት በጨረፍታም ቢሆን ሊያሳይ የሚችለው ሌላኛው ሁነት ደግሞ ወ/ሮ አና ጎሜዝን አስመልክቶ ሊነሳ የሚችለው ነው፡፡ በረከት «የሁለት ምርጫዎች ወግ» በሚለው መጽሐፉ «የቅኝ-ገዥነት መንፈስ ያልለቀቃት» ብሎ የገለፃትን አና ጎሜዝ (የመለስ በስድብ የተሞላ የኢትዮጵያን ሄራልድ ጋዜጣ መጣጥፍ ሳይዘነጋ)፣ ከሁለት ወራት በፊት አዲስ አበባ
በመጣችበት ወቅት አባዱላ በጓዳዊ ስሜት እንዳስተናገዳት ራሷ ከመመስከሯም በዘለለ፣ እነርሱም በአዲስ ዘመን ጋዜጣቸው «እየተመካከርን ነው» የሚል የወዳጅነት መንፈስ የረበበበት የፎቶ ዘገባ ማቅረባቸውን እናስታውሳለን፡፡ ይህች ተራ የምትመስል ሁነት ለበረከት የምታስተላልፈው መልዕክት ቢኖር ‹እናንተ እንደሰይጣን የረገማችሁትን ሁሉ እየተከተልን አንረግምም» የምትል እኩዮች ነን አይነት ትከሻ መጋፋት ትመስለኛለች፡፡
በአናቱም አባዱላ አብዛኛው የኦህዴድ አመራርን በዙሪያው ማሰባሰብ ስለመቻሉ ይነገራል፡፡ ከዚህ ቀደም በአደባባይ እስከመዘላለፍ የተደራረሱትን አቶ ሙክታር ከድርንም ከጎኑ ማሰለፍ ችሏል፡፡ በአንድ ወቅት የግል ጠባቂው የነበረውና አሁን የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆነው አብይ አህመድ በእንዲህ አይነቱ ጊዜ ውለታ ለመመለስ የሚያደርገው ተጋድሎ የማይናቅ ጠቀሜታ አስገኝቶለታል፡፡ የሰሞኑ ሹም ሽርም የራሱ የሆነ አንድምታ አለው፡፡ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ በማዕከላዊ ኮሚቴ ድምጽ ከስልጣኑ የተሻረው የክልሉ ፕሬዚዳንት አለማየሁ አቱምሳ (እርሱን ማንሳት የሚችለው ጠቅላላ ጉባኤው ብቻ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ በርግጥ ሰውየው አሁን አልፏልና በባህላዊ ልማዳችን መሰረት ነፍስ ይማር ብለን እናልፋለን) በ2002ቱ ምርጫ ማግስት አቶ መለስ ከካድሬዎቹ ይሁንታ ውጪ አባዱላን ለመተካት ያመጣው እንደነበር ይታወሳል፡፡ (በነገራችን ላይ በወራት እድሜ ውስጥ በመለስ የተሾሙ የክልል ፕሬዚዳንቶች ከኃላፊነታቸው ሲነሱ ከሽፈራው ሽጉጤ እና አያሌው ጎበዜ ቀጥሎ አለማየሁ አቱምሳ ሶስተኛው ሰው መሆኑ ነው) የድርጅቱ ሊቀ-መንበር እና ምክትል ሆነው የተመረጡት ሙክታር ከድርና አስቴር ማሞም የአባዱላን የበላይነት ለመቀበል ግለ- ሂሳቸውን ውጠዋል፡፡ ይህም ሆኖ የክልሉ አስተዳዳሪ ማን ይሆናል? የሚለው ጥያቄ ገና መልስ አላገኘም፡፡ ምናልባት (ከስራ አስፈፃሚዎችም መካከል መምረጥ እንደሚቻል ታሳቢ ተደርጎ) በሌሎች አካባቢዎች እንደታየው ከድርጅቱ ሊቀ-መናብርት (ሙክታርና አስቴር) አንዳቸውን መሾም ቢፈልጉ እንኳ ዕውን የሚሆንበት ዕድል የለም፡፡ ምክንያቱም እነርሱ የህዝብ ተወካዮች እንጂ የጨፌ ኦሮሚያ ም/ቤት አባል አይደሉምና፡፡ በእኔ ግምት እስከሚቀጥለው የምርጫ ዘመን ድረስ ቦታው አዲስ ሰው ሳይሰየምበት በምክትል ፕሬዚዳንቱ አብዱል አዚዝ ስር እንዳለ የሚቆይ ይመስለኛል፡፡
ከምርጫው በኋላስ? ….አፈ-ጉባኤው በኦህዴድ ውስጥ ለማስፈን እየሞከረ ካለው «አምልኮ አባዱላ» ተነስተን «ተገፈተርኩበት!» የሚለውን ያደረ ቁጭቱን ስንደምርበት ወንበሩን ራሱ ይይዘው ይሆናል ከሚል ጠርዝ ያደርሰናል፤ አሊያም ከሽርኮቹ ሙክታር ከድር እና ወርቅነህ ገበየው አንዳቸውን አሾሞበት በጨፌ ኦሮሚያም የሚካኤል ስሁልን መንፈስ ማንበሩ አይቀርም ብሎ ቅድመ ግምት ማስቀመጥ ይቻላል (ይህ መላምት የህወሓት-ብአዴን ጥንካሬ በዚሁ ከቀጠለ እና የእነርሱ ፍላጎት ደግሞ የተለየ ከሆነ ከህልም ሊዘል አለመቻሉን በማመን ላይ የተመሰረተ ነው)
ኦህዴድን ካነሳን የሌንጮ ለታን ኦዴግን መፃኢ እድልም መመልከት ግድ ይለናል፤ ምክንያቱም ኦዴግ አገር ውስጥ ገብቶ በሰላማዊ መንገድ መታገል ወስኖ ጨርሷልና፤ ሂደቱንም ለማመቻቸት ከግንባሩ መሪዎች አቦ ሌንጮ ለታ፣ ዶ/ር ሌንጮ ባቲ፣ ዶ/ር ዲማ ነጎዎ፣ ዶ/ር ታደሰ ኤባ እና ዶ/ር በየነ አሰቦ ጋር ከስምምነት ለመድረስ፣ ኢህአዴግ በውጪ ሀገር ከሚገኙት የጄኔራል ታደሰ ብሩ ልጆች በተጨማሪ፣ ፕ/ር እንድሪያስ እሸቴ፣ ፕ/ር ኤፍሬም ይስሃቅ፣ ፓስተር ዳንኤል፣ ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ፣ ሻለቃ ደራርቱ ቱሉ፣ አባቢያ አባጆቢር፣ አቶ በቀለ ነዲ (የአዋሽ ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩ)፣ ወ/ሮ ሙሉ ሰለሞንን የመሳሰሉ አደራዳሪዎችን ማሳተፉ ይነገራል፡፡
ይህም ሆኖ ድርድሩ በስኬት ተቋጭቶ ኦዴግ ሀገር ቤት መግባት ቢችል እንኳ፣ ኦህዴዶች ‹አያሰጋንም› የሚል እምነት እንዳላቸው ሰምቻለሁ፡፡ ግና፣ ያለፉት ሁለት አስርታት ዘግናኝ ክስተቶች አሻራ ዛሬም በረዣዥሞቹ የባሌ ተራሮች በጉልህ ተቸክችኮ የመታየቱ እውነታ፣ በስርዓቱ ላኮረፈው የኦሮሚያ ህዝብ፣ ኦዴግን አማራጭ የሚያደርግበት «አኪር» ሸሽጎ ይዞ እንደሆነ ማን ያውቃል? ይህ እንግዲህ እነ ሌንጮ «ካዳሚ» ለመሆን አይመጡም በሚል ስሌት ከተቃኘ ነው፡፡ ይሁንና ከድርድሩ ጀርባ ያለውን እንቆቅልሽ ለመፍታት
ጊዜ የሚጠይቅ ቢሆንም፣ ጉዳዩን ውስብስብ የሚያደርጉ ክስተቶችን ግን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ይኸውም በአፈ-ጉባኤ አባዱላ ፊት አውራሪነት ስር ለመጠናከር እየሞከረ ያለው ኦህዴድ፣ ከሰዎቹ ሀገር ቤት መግባት ምን ያተርፋል? ምንስ ያጣል? ከሚለው ጋር ይያያዛል፡፡
መቼም የኦዴግን መምጣት፣ ኦቦ ሌንጮ «እንጮቴ» (ተወዳጅ ባሕላዊ ምግብ ነው) በአይኑ ላይ እየተመላለሰ እንደሆነ ከሰነዘረው ቀልድም ሆነ «ከሌሎች የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ዘመናዊ ፌደራሊዝምን እመሰርታለሁ» ብሎ በደምሳሳው ከገለፀው ዓላማው ጋር አያይዞ ማለፍ አይቻልም፡፡ አሊያም ያኔ እርሱ ሸገርን ተሰናብቶ ሲወጣ ገና ያልፀደቀውን አንቀፅ 39ን «አስፈፅማለሁ» በሚል ቀቢፀ-ተስፋ ተገፍቶ ነው ማለትም አይቻልም፡፡ በግልባጩ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ‹የኦዴግ መሪዎች በኦነግ ዘመን ለእስር የዳረጓቸውን በሺ የሚቆጠሩ የኦሮሚያ ተወላጆችን ለማስፈታት ሲሉ፣ በታማኝ ተቃዋሚነት ለመታገል ወስነው ነው የሚመጡት› የሚለውን መከራከሪያቸውን ለመቀበል የሚቸግረው ደግሞ፣ እስረኞቹን መፍታት ለሃያ አመታት ያህል በክልሉ ላይ ሰላማዊ ዜጎችን በማሰር የሚታወቀውን ኦህዴድን ሊያሳጣ የመቻሉ ነገር ነው፡፡ ያም ተባለ ያ፣ «ለሁሉም ጊዜ አለው» እንዲል ጠቢቡ
ሰለሞን ሁሉም ቋጠሮ ጊዜ የሚፈታው ይሆናል፡፡ አሁን ላይ እርግጠኛ መሆን የሚቻለው በኦህዴድ ውስጥ አባዱላ ገመዳ ወሳኝ እየሆነ የመምጣቱ እውነታ ብቻ ነው፡፡
ህወሓት-ብአዴን
በዋናነት ሀገሪቷን እንደሚያሽከረክሯት የሚነገርላቸው ህወሓት እና ብአዴን፣ በመጪዎቹ ጊዜያት ‹ኢህአዴግ ለዳግም ክፍፍል ሊዳረግ ይችላል› በሚል ፍርሃት ድርና ማግ ሆነው እየሰሩ ስለመሆኑ እየሰማን ነው፡፡ በርግጥ ‹መለስ ህወሓትን አዳክሞ ነው ያለፈው› የሚል የትግርኛ ተናጋሪዎች ድምፅ መሰማት ከጀመረ ሰነባብቷል (በነገራችን ላይ ከ2000 ዓ.ም ወዲህ የህወሓትን የምስረታ በዓል የካቲት 11ን በብሔራዊ ደረጃ ማክበር መቅረቱን በይፋ ከማወጃቸውም በላይ፣ መለስ ራሱ ለመጨረሻ ጊዜ በመቀሌው የሰማዕታት አዳራሽ የተገኘው 35ኛው ዓመት በተከበረበት ወቅት ነበር፡፡ ይሁንና ከህልፈቱ በኋላ ድርጅቱ የደረሰበትን ድክመት ለመሸፋፈን በደመቀ መልኩ እያከበረው ይገኛል፤ ለዚህም ይመስለኛል በአምናውም ሆነ በዘንድሮው በዓል ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ መቀሌ የሞቀ ተገኝቶ ንግግር ከማድረግም አልፎ ከሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኡመር ሀሰን አልበሽር ጋር በትግሉ ዘመን በተቀነቀኑ ዜማዎች ሲደንስ በቴሌቪዥን መስኮት ተመልክተን ሦስተኛው ሚሊንየም ገባ እንዴ? ብለን ግራ የተጋባነው፡፡ አልበሽርስ አንድ ቻርተር አውሮፕላን ለክልሉ በስጦታ ያበረከተው ዕውን በዓሉን አስመልክቶ ነው? ወይስ በምትኩ የተሰጠው ነገር ኖሮ? መቼም የህወሓት የምስረታ በዓል እንዲህ ሊያስፈነጥዘው እይችልም)
‹ህወሓት ተዳክሟል› የሚለውን ቅሬታ የሚያሰሙ የቅርብ ሰዎች፣ ድርጅቱ አቅምና ልምድ በሌላቸው መሪዎች ስር ማደሩን ይጠቅሳሉ፡፡ ተስፋ የጣሉበት ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤልም ቢሆን ከአምባገነንነቱም በላይ ሀሳቡን አፍታቶ የማስረዳት ችሎታው ደካማ መሆን መፍትሄውን አርቆ ሰቅሎታል፡፡ እንደ ድርጅቱ የቅርብ ሰዎች አገላለፅ የ«ጠንካራ ተተኪ» አልቦነትን ለመረዳት፣ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ኃላፊነቱ በተነሳው አቶ ዘርዓይ አስገዶም ቦታ ላይ የዋልታ ስራ አስኪያጅ መመደቡ እና ራሱ ዘርዓይም በጓሮ በር የብሮድካስት ባለስልጣን ሆኖ መሾሙን (አዲስ ፊት አለመታየቱን) መመልከቱ በቂ ነው፡፡ በቅርቡ የዶክትሬት ዲግሪውን ያገኘው አርከበ እቁባይም ለአመራርነት ለቀረበለት ጥያቄ እያንገራገረ እንደሆነ ተሰምቷል፤ አቦይ ስብሃት ነጋም ኢ-መደበኛ በሆነ የጠረጴዛ ወግ ህወሓት «በግብር በላ» መሪዎች እጅ መውደቁን በቁጭት መናገራቸው ይጠቀሳል፡፡ ይሁንና በዚህ ቀውጢ ወቅት ሁለት ተቋማት ድርጅቱን ለጊዜውም ቢሆን ፖለቲካዊ ጉልበቱን እንዳይነጠቅ ታድገውታል፡፡ ደህንነቱ እና ሰራዊቱ፡፡
የሆነው ሆኖ ህወሓት ዛሬም ከብአዴን ጋር በማበር (በአባይ ፀሐዬ እና በበረከት ስምኦን የፊት መሪነት) የፖለቲካው አሽከርካሪነቱን እንዳስከበረ ይገኛል፡፡ ሁለቱ ሰዎች የስርዓቱን ርዕዮተ-ዓለምንም (በተለይም አብዮታዊ ዲሞክራሲን) ከሌሎች ጓዶቻቸው በበለጠ ማብራራት እንደሚችሉ ይነገራል፡፡ በጅጅጋ ከተማ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በተከበረበት ወቅትም ሆነ ከሳምንታት በፊት በመቀሌ ከተማ በተዘጋጀ መድረክ አባይ ፀሐዬ የርዕዮተ-አለሙ «ተንታኝ» ሆኖ የቀረበው ከዚህ አኳያ ነበር፡፡ በአናቱም አባይ እና በረከትን ጨምሮ ከኦህዴድ ኩማ ደመቅሳ፤ ከደኢህዴን ዶ/ር ካሱ ኢላላ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር አማካሪ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡ በዋናነት ለኢህአዴግ የስልጣኑ መሰረት (ከታጠቀው ኃይል እና ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬው በተጨማሪ) ‹በልማታዊ መንግስት፣ በጥርነፋ፣ ሳር-ቅጠሉን በማደራጀት፣ የብሔር ጉዳይን በማጎን እና መሰል ጭብጦችን በማስጮኽ የሚያምታታበት ርዕዮተ-ዓለሙ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የእነ በረከት የተሰሚነት ምስጢርም ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በርግጥም የካቲት 14 ቀን 2006 ዓ.ም. የተሰበሰበው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከልን ለማቋቋም የሚያስችል ደንብ ማፅደቁን እና የአራቱም ድርጅት የአመ

ከዚህ ቀደም የብርሃኑ አባነጋን መንሸራተት አስመልክቶ የፖለቲካ ሽርሙጥና እንደሆነና ግለሰቡም የፖለቲካ ዝሙት በመፈጸም ላይ እንደሆነ ቢገለጽም ሰሚ ጆሮ ለማግኘት አልታደልንም :: አዎ እንደ ግንቦት ሰባት እና እንደኢሳት ያሉ የዲያስፖራው መስታዎቶች ሊያዳምጡን ፍቃደኛ ካለመሆናቸውም በላይ እነሱ የሚያዳምጡት የወያኔን ዝሙተኛ ፖለቲከኞችን ስለሆነ መለማመጥን አንፈልግም:; ደስ ካላቸው ደስ ይበላቸው ደስ ካላላቸው ገደል ይግቡ ….. እኛ ግን ኢትዮጵያዊነታችንን የሚነጥቀን በነጻነት የምንተነፍሰውን ሃሳብ የሚገድብ ምንም ነገር አይመጣም…. እኛም አናቆምም …
በመጀመርያ ደረጃ ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር በሻእቢያ እና በወያኔ መካከል ከፍተኛ የሆነ የመረጃ ልውውጥ በፓርቲ ደረጃ እንደሚካሔድ እና ሁለቱ ጸረ ኢትዮጵያ አቋማቸው ያንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ መሆኑ ልንቀበለው የሚገባ ጉዳይ ነው:: አለም ሰልጥኖ ወደ አንድነት በማምራት በሰው ልጆች መካከል ያለ የቀለም እና የዘር ልዩነትን ለማጥፋት እና በቴክኖሎጂ እውቀት ተመንጥቆ ለመሄድ በሚሰራበት ዘመን በኢትዮጵያ ውስጥ ባረጀ እና ባፈጀ የጎሳ ፖለቲካ ጥያቄ ህዝብም ውስብስብ መንገድ ላይ በመጠላለፍ ለመከፋፈል እና ጠንካራ ሃገራዊነትን ለማዳከም የሚሰሩ ስራዎችን ልብ ብለን ማጤን እንዳለብን ለማስታወስ እገደዳለሁ:;
ብርሃኑ ዳምጤ አሊያም አባመላ በመባል የሚታወቀው የፖለቲካ ግልሙተኛ እና ሴሰኛ ግለሰብ ማረፊያ ያጣበትን ተሌኮ ለማስፈጸም በሚያደርገው መራወጥ ውስጥ ራሱን ግንቦት ሰባት ብሎ ከሚጠራው ድርጅት ጋር የፖለቲካ ዝሙት ሲፈጽም ቆይቶ በሁለት ስለት ቢላዋ በማረድ የራሱን እና የሌሎችን ደም በአደባባይ ለማፍሰስ ቆርጦ የተነሳ እና ያልተሳካለት ግለሰብ ነው::
ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር ይህ ግለሰብ ትክክል ነው ይህ ግለሰብ ትክክል አይደለም የሚለው ነገር እንደተጠበቀ ሆኖ የደፈረሰው መጥራት እንዳለበት በግልጽ ለመናገር እፈልጋለሁ::
ብርሃኑ ዳምጤ አባመላ በሚለው የፓልቶክ ፕሮግራሙ አጀማመሩ የወያኔን በልማታዊነት ሽፋን የሚሴረውን የጎሳ ፖለቲካ እና የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በዲያስፖራው ውስጥ ለማስረጽ የፕሮፓጋንዳ ስራ ሲሰራ ቢቆይም ሊሳካለት አለመቻሉ ጸረ ወያኔ አቋም እንደያዘ ተደርጎ በሰርጎ ገብነት ከወያኔ በወረደለት ትእዛዝ አባካኝነት እና ከሻእቢያ ጋር በተደረገ የመረጃ ልውውጥ በሻእቢያ የነገር አባትነት ከግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጋር የፖለቲካ ዝሙት እንዲፈጽም ተደረገ:: የፖለቲካ ዝሙቱ በእርካታ ታጅቦ በኢሳት የሳምንቱ እንግዳ ሆኖ ወያኔ በማሳጣት እና በመዝለፍ በሰርጎ ገብ የቆረጣ ታክቲክ የኢሳት ጋዜጠኞችን በማወዳደስ ግንቦት ሰባትን በማንቆለጳጰስ ራሱን ከተቃዋሚዎች ጎራ አሰልፎ የነበር ሲሆን እንዲሆን አክራሪዎች አሸባሪዎች ሲላቸው የነበረውን የኢትዮጵያውያንን ሙስሊሞች ትግል ለመጠጋት በመሞከር ቢያሞጋግስም አናቱን በፍልጥ ስላልነው ሳይሳካለት ቀርቶ አፉን ይዞ ተቀመጠ:: ዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሲኖር ከነበረው ከጃዋር መሃመድ ጋር ማታ ማታ ሻይ ቡና እያለው የኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎችን ፖለቲካ በማጥላላት እና በወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ሲያጠምቀው የነበረው አባመላ ዞር ብሎ አዛኝ በመምሰል በጃዋር መሃመድ ላይም ጸር የሆኑ ቃላቶችን ሲተፋ እንደነበር ሲታወቅ አባመላ ራሱ ጃዋርን በጥላቻ ሲያሰለጥነው እንደነበር የማይዘነጋ እውነት ነው::
ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ብሎ ራሱን የሚጠራው ድርጅት ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንን እንደማይወድ እና ከጀርባው በሻእቢያ እየተጠመዘዘ የጸረ ኢትዮጵያ አቋም ማራመጃ መሆኑ የማይካድ ሃቅ ነው:: እንደ ኢሳት ባሉ በዲያፖራው ሃብት በሚተዳደሩ ሚዲያዎች የፖለቲካ ትግል እና የለውጥ አማራጭ ሃሳብ ያላቸው ኢትዮጵያውይና እንዳይቀርቡ እና እንዳይጠቀሙ በማገድ የወያኔ ትርፍራፊ የፖለቲካ ጋለሞታዎች እንዲዘፍኑበት መደረጉ አሌ የማይባልበት ጉዳይ ሲሆን በዚህ ጉዳይ ላይን ራሱ የሚዲያ ነጻነቶችን በመጋፋት ለውጥ ከማምጣት ይልቅ ነጻነቶች በሻእቢያና ወያኔ ተላላኪዎች በተዘዋዋሪ ሲቀበሩ እያየን ነው::
እንደ ግንቦት ሰባት ያሉ ድርጅቶች በፖለቲካ አማራጭ ሃሳብ የያዙ እና ለውጥ በማምጣት ረገድ ሚና መጫወት የሚችሉ ኢትዮጵያውያንን በመግፋት የወያኔ ሰርጎ ገብ ወንበዴዎችን በአመራር እና በድርጅታቸው የደህንነት መዋቅር ውስጥ በማስገባት ራሳቸውን ከትግሉ ውጪ ለመጠለዝ እየተወራጩ ይገኛሉ:; ኢሳት የሚዲያ ተቋም ተብሎ እስከተቋቋመ ድረስ ማድረግ የሚገባውን የማያውቅ እና ባልበሰሩ ሰዎች እና የጋዜጠኝነት ልምድ ባሌላቸው እንዲሁም በሳል እና ሚዛናዊ መረጃዎችን ባልያዙ ደረቅ ተንታኞች ታጅቦ የሞት ጉዞውን እያፋጠነ ነው::
ወያኔ በብርሃኑ ዳምጤ በኩል በአባቱ ሻእቢያ አዝማችነት የመጀመሪያ ዙር ስራውን አጠናቆ ብርሃኑ ዳምጤን ወደ ልማታዊ ጋዜጠኝነት መልሶታል:; በሃገር ወዳድነት ሽፋን በማስመሰል የተካነው ብርሃኑ ዳምጤ ድራማውን አጠናቆ ዲያስፖራ ተቃዋሚዎችን በመዝለፍ ስራ ላይ ተመልሶ ተሰማርቷል:: ካሁን በኋላ የአባመላ ፓልቶክ እንግዶች እንደ ጃዋር እና ዘርኣይ ያሉ የጥላቻ ፖለቲካ ስልጥኡኖች ናቸው:;ከሃገር ቤት የተሰራውን የወያኔን ድራማ እና የሚሚ ስብሃቱን ጸረ ግንቦት ሰባት እና ኢሳት ውንጀላ እና ትችት ተከትሎ የብርሃኑ ዳምጤ ትፋት ምን እየተሰራ እናዳለ እና የዲያስፖራውን የለውጥ ፖለቲካ ገደል ለመክተት በህዝብ የመኖር ህልውና ላይ ፍርሃት እና ሽብር ነዝቶ ወያኔን በስልጣን ለማቆየት የተሸረበውን ሴራ በገሃድ ያሳያል::
ከዳዊት ከበደ እና ከጃዋር የሰርጎ ገብ ፖለቲካ ያልተማሩት ግንቦት ሰባት እና ኢሳት ሃገር ወዳድ እና ብዙ ስራዎችን ሊሰሩ የሚችሉ ኢትዮጵያውያንን ወደ ጎን በማግለል በዙሪያቸው እንደብርሃኑ ዳምጤ ያሉትን ሰርጎ ገቦች በመኮልኮል ያላዋቂ ሳሚ … ሆነው ህዝቡን … በመለቅለቅ ላይ ይገኛሉ::ኢሳት አንድ ሃገር ወዳድ የሆነ ኢትዮጵያዊ በፕሮግራሞቹ ላይ ከማቅረብ ይልቅ የወያኔ ኮልኮሌ የመረጃ ሰዎች እና ሰርጎ ገቦችን ቢያቀርብ ያተረፈ እየመሰለው በፖለቲካ ኪሳራ ውስጥ ገብቶ ከሕዝብ ልሳንነት ይልቅ የግንቦት ሰባት ልሳን እንደሆነ እያንጸባረቀ ነው:: ኢህኣፓ በተፋቻቸው እንደ ብርሃኑ ነጋ ባሉ የፖለቲካ ሰልባጆች ትእዛዝ የሚመራ አስመስሎበታል:: እንደ ነእመን ዘለቀ ባሉ በሻእቢያ እና ወያኔ ትራፊዎች የሚመራው ኢሳት አጀማመሩ መልካም ቢመስልም ግን በጀት አይለቀቅልህም ከወያኔ ከዳሁ የሚሉ ግለሰቦችን እያባዛህ ካላቀረብክ የተባለ ይመስል ነጋ ጠባ የምናያቸው የወያኔ ሰዎችን መሆኑ አሳሳቢ አድርጎታል::ስለዚህ ግንቦት ሰባት እና ኢሳት ከወያኔ ሰርጎ ገቦች ጋር የፖለቲካ ዝሙት እየፈጸሙ የህዝብን ትግል እየገደሉት ነው ቢባል ድፍረት አይሆንም:: ለዛሬ በዚህ ይብቃ ጹሁፉ ቀጣይ ነው ይጠብቁት::
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

today’s 5000 meter running event ended dramatically.
In a major show of force, dozens of Addis Ababa police officers in riot gear arrested the Blue Party Women Groups who were shouting that political prisoners must be released. These young women were demanding for the release of journalists and political prisoners.
The women were shouting “Release Reeyot Alemu!!” .. “Release the Journalists!!”… “Release all political prisoners!!”
The police arrested dozens of these women who all are members of the Blue Party. Some of these are members of the Executive Committee of the Blue Party. They have been interrogated and assaulted for they supported the peaceful struggle of the women form the Blue Party in the rally!
Here are names of the ladies and executives of the party still arrested:-
Woyinshet Molla
Woyni Niguse
Nigest Wondifraw
Meron Alemayehu
Emebet Girma
Metasebiya Tekle
Getaneh Balcha (Head of Organizational affairs)
Brhanu Tekleyared (Head of Public Relations)
Abel Ephrem (member of Public Relations committee)
The other two women who were leading the protest namely Eyerus Tesfaw and Elsabeth Wessna are still not found and no one knows where they are taken.
ዘወትር ቅዳሜ ማታ ከደሳለኝ መኮንን ጋር፣ምርጥና አዳዲስ የካንትሪ ማለትም የአሜሪካ አገር ሰብእ፣ የሮክ፣ተሶል፣የፖፕ፣የአር-ኤን-ቢ፣ብሉዝ፣የሬጌና የሂፕ-ሃፕ ዜማዎችን እንዲያደምጡ ተጋብዘዋል።
የ ‘11% እድገታችን’ ከሚታየው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ሲነጻጸር
Sebhat Amare( Norway)
March 9,2014
እንደሚታወቀው በአንድ ሃገር የኤኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማህበራዊ ክንውኖች የቀን ተቀን ለውጥ ውስጥ የህብረተሰብ ተሳትፎ(አስተዋጽኦ) ጉልህ ሚና አለው፡፡ እንዲሁም በሂደቱ ውስጥ የሚያጋጥሙ አገራዊ ጠቀሜታ ያላቸው ጉዳዮችም ይሁኑ ወይም በተቃራኒው የሚከሰት ተፈጥሯዊም ሆነ በመልካም አስተዳድር ችግር ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮች ዞሮ ዞሮ ከህብረተሰብ ጫንቃ ላይ አይወርድም፡፡ ይህ ስለሚታወቅ ሃላፊነት የሚሰማቸው፣ ለሃገርና ለሕዝብ ታማኝ የሆኑ፣ በሕዝብ ይሁንታ ስልጣን የያዙ መንግስታት ያላቸው ሃገሮች በየትኛውም ሃገራዊ እንቅስቃሴ ላይ ሕዝባቸውን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳታፊ በማድረግ በብሔራዊ ስሜት የታነፀና በሃገሩ ጉዳይ ላይ ቅንጣት ታህል የማያመነታ ብርቱ ህብረተሰብን ይገነባሉ፡፡ የእንደኛ አይነቶቹ የሃገርና የሕዝብ ፍቅር የሌላቸው አምባገነን የወያኔ መሪዎች ግን እንኳን ‘የሃገርህ ጉዳይ ያገባሀል’ ብለው ሊያሳትፉት ቀርቶ የአንድን ሕዝብ የዴሞክራሲ መሰረት የሆነውን የመናገርና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ተፈጥሮዊ የሆነውን መብቱን እንኳ ገፍፈው ሃገሪቱን የቁም እስር ቤት አድርገዋታል፡፡
የወያኔ ጁንታ ‘11% እድገት አሳይተናል’ እያለ በሌለ ተስፋ ላይ ተቀምጦ በሚኮፈስበት እና ሳተላይት ልናመጥቅ ነው፤ አውሮፕላን ፈበረክን፤ ልማታዊ መንግስት ……. እያለ ትምክህቱን በሚያሳይበት በአሁን ወቅን በሃገራችን መኖር ያልቻልን ኢትዮጵያውያን ድንበር አቋርጠን በተፈጥሮ የበለጸገች ሀገራችንን ጥለን ወደ ተለያዩ ሀገራት በስደት ተበትነን እንገኛለን፡፡ በአንጻራዊ የተሻለ የመኖርያ ቦታ ፍለጋ ለስደት የወጣው ወገናችን ያሰበበት ቦታ ሳይደርስ በበረሃ አሸዋ የተበላውና በባህር ሰጥሞ የቀረውን ቤቱ ይቁጠረው፡፡ እንደ ሰው አንድ የያደርገን ባሕርይ፤ እንደ ኢትዮጵያዊነትም ሁላችንንም የሚመለከተንና የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት ልዩነት ያልታየበት በደል ባለፈው ሰሞን በሳዑዲ ዐረብያ ግዛት እንደተፈጸመን መጥቀስ በቂ ነው። የጥቃት ዒላማዎቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው። የጥቃቱ ልክ የለሽነትና አሰቃቂነት ደግሞ ይበልጥ የጎላው በሴት እህቶቻችን ላይ ነው። የዱር አውሬ እንኳን ከዚህ የተሻለ ክብር አለው። እነዚህ እጅግ ኋላ ቀር የሆኑ አረመኔዎች ከእንስሳ እንኳን አንሰው አንዲት በፍርሃት ነብሷን የሳተችን ሴት የሚደፍሩትን እያየን የተደፈሩት ‘ህጋዊ’ ናቸው ‘ህገወጥ’ የሚል የሕግ አንቀጽ መረጣ ውስጥ ልንገባስ እንዴት ይቻለናል? ህዝባችን እረኛ እንደሌለው መንጋ ተበትኖ፤ ተዋርዶና ክብሩን ጥሎ መኖር ከጀመረ እነሆ 23 አመታትን አስቆጠሯል፡፡ ዜጎቻችን በቄያቸዉ በሰላም ሰርተዉ እንዳይኖሩ በወያኔ አረመኔያዊ አገዛዝ መሬታቸውን ተቀምተውና ተማርረው በስደት የበረሀና የባህር ሲሳይ እየሆኑ ከዛም የተረፉት ይኸዉ አሁን እንደምናየዉ በጨካኝ መንግስታት ፖሊሶች ለእንግልት እና ለአሰቃቂ ሞት ተዳርገዋል፡፡ በሰለጠነ ዘመን ወደኋላ እንደ ጋርዮሽ የጨለማ ዘመን በወገኖቻችን ላይ በአረብ ሀገራት መንግስታት የሚደርሰዉን እንግልት የአለም አይን እና ጆሮ እንዲያይ እና እንዲሰማዉ በየቦታው ባሉ የሳዑዲ ኤምባሲዎች የተደረጉት ሰላማዊ ሰልፎች በመጠኑም ቢሆን የአለም ህዝብ ችግሩን እንዲረዳ ለማድረግ አስችሏል፡፡
”ነፃነት፣ አንድነት፣ ፍትህ እና እኩልነት በወሬና በዲስኩር አይመጣም” እንደተባለው የመስዋዕቱ አይነት ይለያይ እንጂ አነሰም በዛም ለነፃነት የሚደረግ ትግል ወይ ሃብትን ወይም የህይወት መስዋዕትነትን ይፈልጋል፡፡ ይህንን ሁሉ በህዝብና በሃገር ላይ የሚደርሰውን ለከት ያጣ ጭቆና የምናይ እና የምንሰማ በተለይ በሰለጠነው አለም የምንኖር ወገኖች እኛ በሰው ሃገር የምናገኘውን እንዲህ ያለውን የመፃፍ፣ የመናገር፣ የመሰብሰብና ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት ወገናችን በገዛ ሃገሩ ሲያጣ፣ ይህ ነው የማይባል ችግር ሲወርድበት በተግባር መልካም ውጤት የሚያመጣ ስራ ለመስራት ቆርጠን ልንነሳ ይገባል፡፡ በአንድነትና በቁጭት ለሃገራችን ህዝብ ነጻነት ካልተነሳን በስተቀር የወያኔን ተንኮል ችላ ማለት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የወገኖቻችንንና የውዲቱ ሃገራችንን የመከራ ጊዜ ማራዘም ማለት ነው፡፡ ዘረኛው ወያኔ በነፃ አውጪ ስም ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ እንዲሁም ከዛም በፊት የሚከተለው የተሳሳተ የኢትዮጵያን ሉዐላዊነት የማፍረስና የመበተን የመገነጣጠሉንና ብሔራዊ ጥቅምን አሳልፎ ለባዕዳን የመስጠቱን እኩይ ተግባር መመልከት የተለመደና የቀን ከሌት ክንውናቸው መሆኑ በሃይል ስልጣን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬዋ ዕለት የሚታይ እውነታ ነው፤ ለዚህም ለማስረጃ ያህል ሰሞኑን በስፋት እንደሚወራው የ’ድንበር ማካለል’ ስም ተሰጥቶት የምዕራቡን የሃገራችንን ክፍል ለሱዳን አሳልፈው መስጠታቸውን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በኢትዮጵያችን መልካም አስተዳደር ጠፍቷል፤ ሙስና እንደ ሸረሪት ድር በየቦታው አድርቷል፤ ‘የሕግ የበላይነት አለ’ በሚባልበት አገር ፍትህ ርቋል፤ ዘረኝነትና ጎጠኝነት ከመቼውም በላይ ተንሰራፍቷል፤ በሕገ መንግሥት የተረጋገጡ መብቶች ተጨፍልቀዋል፡፡
በነፃነት በመኖር የምንቀድማቸው ሃገራት ሰልጥነው በዴሞክራሲያዊ ስርዓትና መልካም አሰተዳደር የህዝቦቻቸውን ሰብዓዊ መብት ለማስጠበቅ ደፋ ቀና በሚሉበት በዚህ ዘመን የኋሊት የሚጓዘው ከዘመኑ ጋር መዘመን ያቃተው ወያኔ ከብዙ ዘመናት በፊት በነበረው ኢትዮጵያዊነትን የማፍረስ አስተሳሰብና የሃይል አምባገነናዊ አገዛዝ ተሸብቦ ያላስነባው ህዝብ፤ ያልጣሰው ህግና ስርዓት፤ ያላፈረሰው አንድነት፤ ያላዋረደው የህዝብ ስብዕና፤ ያልገባበት የእምነት ተቋም፤ ያልበተነው የሞያ ማህበራት፤ ያልገደለው፣ ያላሰረውና ያላስለቀሰው የህብረተሰብ ክፍል የለም::
ባለፉት አመታት በወያኔ አገዛዝ በግልጽ እንዳየነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እኩልነቱን፤ መብቱንና ነጻነቱን ለማስከበር የሚያደርገውን ትግል ለማኮላሸት እርስ በርሱ የሚቃረኑ ህጎችና መመርያዎችን አርቅቆ አያጸደቀ ሠላማዊ ዜጎችን አስሯል፤ አንገላቷል፤ ገድሏል፤ ከአገር በግፍ እንዲሰደዱም አድርጓል። ይሄንኑ የወያኔን ግፍ የአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት እ.ኤ.አ በ2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ተፈፀሙ ያላቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሪፖርት ሰሞኑን አውጥቷል፡፡ በሪፖርቱ የተካተቱት የመብት ጥሰቶች በህዝባችን ላይ በተደጋጋሚ እና በከፍተኛ ሁኔታ ወያኔ እያደረሰ ያለውን ግፍ በእማኝነት ያሳየ ሪፖርት ነው፡፡ የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በሪፖርቱ ያካተታቸው እንደተጠበቁ ሆኖ፤ በወያኔ የተፈጸሙ እና እየተፈጸሙ ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ከዚያም የላቁ እንደሆኑና ሃገራችንና ህዝቧ ምን ያህል ውጥንቅጥ ውስጥ እንዳለን ያሳየ ሪፖርት ነበር፡፡
ኢትዮጵያ ሃገራችን ሀሳብን በነፃነት ያለፍርሀት መግለፅ የማይቻልባት፤ የዜጎች የኑሮ ደረጃ ከዕለት ዕለት እየተባባስ የሚሄድባት፤ ዘመናዊ የመረጃ መገናኛዎች ሆን ተብለው የታገዱባት፤ የህዝቦቿን ጥንታዊና ብርቅዬ የሆነውን መከባበርና አንድነት በዘር ጥላቻና በሀይማኖት ለመከፋፈል አገዛዙ የሚጥርበት፤ ዜጎች አለአግባብ የሚታሰሩባት፣ የሚገደሉባት፤ ዜጎች በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰደዱባት፤ ነፃ፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያልተካሄድባት፤ ዜጎች ከመኖሪያቸውና ከቀዬአቸው የሚፈናቀሉባት፤ ለሕግ ተገዢ ያልሆነ መንግሥት ያለባት፤ ዜጎች የገዢው ፓርቲ አባል ካልሆኑ በስተቀር በነፃነት ሠርተው መኖር የማይችሉባት፤ ነፃ ሚዲያ የሌለባት፤ ዜጎች ለሀብት ንብረታቸው ዋስትና የማያገኙባት፤ ህዝባዊ መንግሥት የሚናፍቅ ህዝብ ያለባት፤ በሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ተቋማት የገዢው ፓርቲ ፖለቲካዊ መጠቀሚያ የሆኑባት፤ ቤቶች በቁመታቸው ማደጋቸው እንደዕድገት የሚቆጠርባት ሀገር ሆናለች። ስለሆነም ኢትዮጵያንና ህዝቧን ለመታደግ በየትኛውም የትግል መስክ ተሳትፎ በማድረግ ለነፃነት፣ ለፍትህ እና ለእኩልነት በሚደረገው ትግል ውስጥ የየራሳችንን አሻራ ለማሳረፍ ለተግባራዊ ትግል እንትጋ፡፡
ለዚህ ሁሉ በሃገርና በህዝብ ላይ ለሚደርሰው እንግልትና መዋከብ ምንም እንኳን የመንግስትን እርካብ የተቆናጠጡት ’ገዢዎቻችን’ ከተፈጥሮ ባህሪያቸውና የኢትዮጵያን ሉዐላዊነት ከማፍረስ አንፃር የፈለጉትንና ያሻቸውን ቢያደርጉም በየግዜው በህዝብና በሃገር ላይ የሚያደረሱትን ሰቆቃ የየሰሞኑ መነጋገሪያ ከማደረግ በዘለለ በአንድነት በማበር በደል በቃኝ፣ ግፍ በቃኝ፣ መሰደድ በቃኝ፣ መታሰርና መገረፍ በቃኝ፣ ከሃብትና ከቀዬ መፈናቀል በቃኝ ብለን ለለውጥ እንድንነሳ በህብረት በመስራት ውዲቱ ሃገራችንን ከውድቀትና ከጥፋት ለማዳን የኢትዮጵያዊነት ሃላፊነታችንንና ድርሻችንን እንወጣ፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
ኢትዮጵያ ሀገራችን ለዘለዓለም በክብር ትኑር !!
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
አነሰም በዛም ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሃገር ውስጥ የተቃውሞ ድምጻቸውን ማሰማታቸውን የሚደግፉ ቢኖሩም መንግሥት ለመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ቆሜያለሁ ለማለት እንዲመቸው የማስመሰያ መጠቀሚያ ሆነዋል የሚሏቸውም አልጠፉም ።
የአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ህልውና የሚወሰነው ወጣቶች ባላቸው ሚና ላይ ሲሆን በብዙ ሀገራት እንዳየነው እና እንደተመለከትነው ወጣቶች ስለ ነፃነታቸው ፊት ለፊት መንግስታትን በመጋፈጥ ለመብታቸው ታግለዋል መስዋህትነትም በመክፈል የፈለጉትን አለማና ግብ አሳክተዋል::ለዚህም የሰሜን አፍሪካ አገሮችንና የመካከለኛው ምሥራቅን የለውጥ አብዮት ያቀጣጠሉትን ወጣቶች ዞር ብሎ መመልከት ያሻል:: የአንባ ገነኖች የስልጣን አገዛዝ አልዋጥላቸው ያላቸው እነዚህ የሰሜን አፍሪካ አገሮች እንደነ ግብጽ […]
የአመራርና የውሳኔ ሰጭነት አቅማቸው አጠያያቂ ኾኗል (ፋክት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፴፮ የካቲት ፳፻፮ ዓ.ም.) ከዓመት በፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፮ኛው ፓትርያርክ ኾነው የተመረጡበት አንደኛ ዓመት በዓለ ሢመት፣ የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. የተከበረላቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያን ከሚታወቀው አስተዳደራዊ መዋቅር ውጭ ለአማካሪነት አቅርበዋቸዋል በተባሉ አካላትና ግለሰቦች ማንነት ሳቢያ በአንድ የቅዱስ …![]()
ዘወትር ቅዳሜ ማታ ከደሳለኝ መኮንን ጋር፣ምርጥና አዳዲስ የካንትሪ ማለትም የአሜሪካ አገር ሰብእ፣ የሮክ፣ተሶል፣የፖፕ፣የአር-ኤን-ቢ፣ብሉዝ፣የሬጌና የሂፕ-ሃፕ ዜማዎችን እንዲያደምጡ ተጋብዘዋል።
http://freedomfighterj.blogspot.no/2014 … ost_8.html
የፓትርያርኩ የለውጥ ተግዳሮትና ተስፋ – በአንደኛ ዓመት በዓለ ሢመት ዋዜማ
የብልሹ አሠራርና ሙስናን ችግር በዐደባባይ የተናገሩ የመጀመሪያው ፓትርያርክ ናቸው
ፓትርያርኩ ጽኑ አቋም ስለሌላቸው ለጣልቃ ገብነት የተመቹ ኾነዋል
ጣልቃ ገብነቶችን መቋቋምና የቅ/ሲኖዶሱን የውሳኔ ልዕልና ማስከበር ይጠበቅባቸዋል
ፓትርያርኩ ዙሪያቸውን መፈተሽ አለባቸውብቃት ያለው የአማካሪ መዋቅር ያስፈልጋቸዋል

የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም ፤ ለስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ምርጫ ከቀረቡት አምስት ዕጩዎች መካከል በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማትያስ በከፍተኛ ድምፅ መመረጣቸው ተነገረ። ሊቀ ጳጳሱ በቤተ ክርስቲያኒቱ የፓትርያርኮች ምርጫ ታሪክ ከፍተኛውን የመራጮች ድምፅ በማግኘት አሸናፊ መኾናቸው በተገለጸበት ወቅት የብዙዎችን ትኩረት በሳበ ኹኔታ በመስቀላቸው ሲያማትቡ ታዩ።
የወቅቱን ስሜታቸውን አስመልክቶ ‹‹ዜና ቤተ ክርስቲያን›› በተሰኘው መጽሔት ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ÷ ‹‹ፓትርያርክ እኾናለሁ የሚል መንፈስ በውስጤ ስላልነበረ ውጤቱ ሲገለጽ እንዴት ነው ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ምንድን ነው ከሚል ደነገጥኩኝ፤ በዚያው ቅጽበት የተሰማኝ፣ እግዚአብሔር ይህን ታላቅ ሓላፊነት እንዴት እችለዋለሁ? በል አንተ ታውቃለህ፤›› የሚል እንደነበር አስረድተዋል፡፡
ከምርጫው ሦስት ቀናት በኋላ የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተከናወነው ሥርዐተ ሢመት÷ ለፓትርያርክነት መመረጣቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ጥሪ እንደኾነና ጥሪውን የተቀበሉት መኾኑን፣ መቀበላቸውም ለክብርና ለልዕልና ሳይኾን ለመሥዋዕት በመታዘዝ በመኾኑ የቅዱስ ሲኖዶሱን አባላት በመያዝ በጋራ እንደሚወጡት ያላቸውን እምነት ተናግረው ነበር፡፡
ፓትርያርኩ በዚያ ንግግራቸው ‹‹ቅዱስ ሲኖዶሱ በራሱ መተማመን አለበት›› ሲሉ በአጽንዖት የተናገሩ ሲኾን እንደ አንድ ልብ አሳቢ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾኖ በሥምረት ከሠራ፣ ችግር ይኖራል ብለው እንደማያምኑ ገልጸዋል፡፡ በቅዱስ ሲኖዶሱ ሊሠሩ ይገባል በሚል ካሳወቋቸው ተግባራት መካከልም ቤተ ክርስቲያኒቱ ፍትሕ ርትዕ እኩልነት የሞላባት፣ መልካም አስተዳደር የሰፈነባት፣ የእውነትና የሐቅ መገኛ እንድትኾን በመንፈሳዊነት፣ ታማኝነትና ተጠያቂነት የተደገፈ መጠነ ሰፊ የሥራ እንቅስቃሴ ማድረግን ይጨምራል፡፡ ‹‹እምነትና ሐቅ በቤተ ክርስቲያን ካልተገኙ ከየት ይገኛሉ?›› ሲሉ የጠየቁት ፓትርያርኩ፤ ካህናትና ቤተ ክርስቲያኒቱን በሞያቸውና በልግሥናቸው አቅፈው ደግፈው የያዙ ምእመናንም የድርሻቸውን ለመወጣት ብርቱ ጥረት ማድረግ አለባቸው ማለታቸውም ይታወሳል፡፡
ከፕትርክና ሢመቱም በኋላ ለብዙኃን መገናኛዎች በሰጧቸው ቃለ ምልልሶች÷ ሰው ሊመሰገንም ሊሾምም፣ ሊሻርም፣ ሊወቀስም የሚገባው በጠባዩ፣ በግብረ ገብነቱ፣ በትምህርቱ ብቻ እየተመዘነ እንጂ በዘሩ አንወደውም አንጠላውም በማለት በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ውስጥ ሥር የሰደደ የመጠቃቀሚያ መንገድ ነው የሚባለውን በጎሰኝነት መሳሳብን ተቃውመዋል፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቷ ታላቅ መኾኗንና ለታላቅነቷ የሚመጥኑ ሰዎች መገኘት እንዳለባቸው በአጽንዖት የተናገሩት ፓትርያርኩ፣ ‹‹የተሟላና የተቃና ሥራ ለመሥራት ከኹሉ አስቀድሞ ብቃትና ጥራት ያለው ሥራ መሥራት ያስፈልጋል፡፡ ለዚኽ ደግሞ ሰው በሰው ላይ መደራረብ ሳይኾን ትምህርትና ችሎታ ያለው፣ ለተመደበበት የሥራ ደረጃ የሚመጥን ሰው መቀመጥ አለበት፤›› ብለዋል፡፡
የቤተ ክህነቱ አስተዳደር ከላይ እስከ ታች ተስተካክሎ የመልካም ሥራ አብነት ይኾን ዘንድ ‹‹ሙስና ይጥፋ፤ ተጠያቂነትና ሐቀኝነት ይስፋፋ›› የሚለውን ዐዋጅ ደጋግመው በማሰማት እየታወቁ የመጡት ፓትርያርኩ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያኒቱን ስም ለመጠበቅና ክብርዋን ለመመለስ ሊወስዳቸው ይገባል ያሏቸውን የለውጥ ርምጃዎች በመዘርዝር በምልዓተ ጉባኤው አጀንዳነት አስይዘው ለማስወሰን አስችለዋል፡፡
ፓትርያርኩ ሥር ነቀል ለውጥን የሚያመጡና ቆራጥ አቋምን የሚሹ ናቸው ያሏቸው እኒህ ርምጃዎች÷ ብልሹ አሠራር በፀረ-ሙስና እንቅስቃሴ የሚታረምበትና የሚወገድበት፣ የአስተዳደር መዋቅሩና የሚሠራባቸው ደንቦች ሕጎች፣ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲኖረው ተደርጎ የሚሻሻልበት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ራእይና ተልእኮ በግልጽ የሚታይበት ስትራተጅያዊ የአመራር ሥርዐት የሚነደፍበት፣ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ ላለው የገንዘብ አያያዝ አንድ ወጥ የኾነ ሥርዐት የሚዘረጋበት እንደኾነ አመልክተዋል፡፡
አቡነ ማትያስ አሳፋሪና አሳዛኝ ነው ያሉት የአሠራር ብልሽት ሳይታረም ቢቀጥል ቤተ ክርስቲያኒቱ ለሚገጥማት አስከፊ ችግር ፓትርያርኩ ራሳቸውን ከተወቃሾች ተርታ በመቁጠር ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚታደግና ችግሮቿን የሚቀርፍ አጀንዳ በመያዝ ‹‹በእግዚአብሔር፣ በታሪክና በመጪው ትውልድ ፊት›› የሚመዘን፣ ችግር ፈቺ ውሳኔ እንዲወሰን የቅዱስ ሲኖዶሱን አባላት አነሣስተዋል፡፡
ፓትርያርኩ ከሹመታቸው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በርእሰ መንበርነት የመሩትና በግንቦት ወር 2005 ዓ.ም. የተካሔደው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በይፋ ባስታወቁት በዚህ መግለጫቸው ላይ በመወያየት፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ሥራዎቿን በመሪ ዕቅድ በመምራት፣ ሙስናንና የመልካም አስተዳደር ዕጦትን ከሥሩ ለመቅረፍ የሚያስችል ጥናት የሚያቀርብ ከሊቃነ ጳጳሳት፣ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከቤተ ክህነቱ የሥራ ሓላፊዎችና ከምሁራን ምእመናን የተውጣጣ ዐቢይ ኮሚቴ ሠይሟል፡፡
ይኸው የቅ/ሲኖዶሱ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ የአደረጃጀትና አሠራር ጥናት የሁሉም አህጉረ ስብከት ማእከልና የመንበረ ፓትርያርኩ መቀመጫ በኾነው በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት እንዲደረግ መመሪያ ሰጥቷል፡፡ ሀ/ስብከቱም በመዋቅርና አደረጃጀት፣ በሰው ሀብት አስተዳደር፣ በሒሳብ አሠራርና ቁጥጥር የሚታይበትን የገዘፈና የተመሰቃቀለ ችግሩን ለመፍታት የባለሞያ ቡድን አቋቁሞ በፍጥነት ወደ ተግባር ገብቷል፡፡
በመንበረ ፓትርያርክም በአዲስ አበባ ደረጃም የተቋቋሙት ሁለቱም አካላት የጥናት ውጤታቸውን በጥቅምት ወር 2006 ዓ.ም. ለተካሔደው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቅርበው በማስገምገም የወሳኝ አካሉን ይኹንታ ከማግኘታቸውም በላይ ቀጣይ የአፈጻጸም አቅጣጫ ተሰጥቷቸዋል፤ የመሪ ዕቅድ ማህቀፉን ያስገመገመው ዐቢይ ኮሚቴ በቀጣይ ዕቅዱን በሥራ መተርጎም በሚያስችል ኹኔታ በዝርዝር አዘጋጅቶ እንዲያቀርብ መመሪያም ተሰጥቶታል፡፡
የአዲስ አበባውን የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ የሠራው የባለሞያ ቡድንም ጥናቱን ወደ ታች አውርዶ በካህናት፣ በምእመናንና በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በውይይት ካዳበረ በኋላ፣ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርብና በቋሚ ሲኖዶሱ እንዲጸድቅ በምልዓተ ጉባኤው በተሰጠው የአፈጻጸም አቅጣጫ መሠረት ተግባሩን አከናውኖ የብዙኃን ካህናትና ምእመናን ተቀባይነት ያረጋገጠውን የጥናት ሰነድ በሀ/ስብከቱ አማካይነት ለቅ/ሲኖዶሱ አስረክቧል፡፡
ከነገ በስቲያ ሰኞ፣ የካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. በሚከበረው አንደኛ ዓመት የበዓለ ሢመት ዋዜማቸው ላይ የሚገኙት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ በቀጣዩ የሥራ ዘመናቸው የተናገሯቸውንና ተጠንቶ የቀረበላቸውን በተግባር ለመተርጎም የሚንቀሳቀሱበት እንደሚኾን አዲስ አድማስ ያነጋገራቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ሓላፊዎች፣ አገልጋይ ካህናትና ምእመናን ተስፋቸውን ገልፀዋል።
ቤተ ክህነቱ ያለበትን መሠረታዊ ተልእኮውን የማያገለግል የተንዛዛ ቢሮክራሲ፣ ወገንተኝነትና ሙስና በፓትርያርክ ደረጃ አምነውና ተቀብለው በዐደባባይ ገልጠው ለመናገር አቡነ ማትያስ የመጀመሪያው እንደኾኑ የሚናገሩት አንድ አገልጋይ፤ የፓትርያርኩ መግለጫዎች በየአጥቢያቸው ችግሩን የሚጋፈጡ ወገኖችን በልዩ ልዩ መንገድ እንዳነሣሣ ይህም ቢያንስ ብልሹ አሠራሩን ለሕገ ወጥ ጥቅም ያዋሉ አማሳኞችን እንዳሸማቀቀ ይገልጻሉ፡፡
ለዓመታት የተከማቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ዘርፈ ብዙ ችግር በአንድ ዓመት ተጠንቶ ሊታወቅ ይችል እንደኾነ እንጂ መፍትሔ ያገኛል ተብሎ እንደማይጠበቅ የጠቀሱት አገልጋዩ፤ አንድ ዓመት የፓትርያርኩን ስኬት ለመገምገም በቂ አይደለም ይላሉ፡፡ ፓትርያርኩ በጵጵስና ከተሾሙበት ጊዜ ጀምሮ በውጭ የነበሩ እንደመኾናቸው ቤተ ክህነቱን የመምራት ልምድ ሊያንሳቸው እንደሚችል ጠቁመው ይህን ክፍተት የሚጠቀሙ ከቀድሞም የነበሩና ዛሬም ያልታጠፉ የጥፋት እጆችን ተጽዕኖ በፓትርያርኩ ዙሪያ እንደሚያስተውሉ ገልጸዋል፡፡ ለዚህም ፓትርያርኩ የሚያስጠጓቸውን አማካሪዎች ማንነት በጥንቃቄ መለየት እንደሚኖርባቸው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ስለ ፓትርያርኩ የአንድ ዓመት ጉዞ የተጠየቁትና ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ከፍተኛ የሥራ ሓላፊ፣ ፓትርያርኩ ከተሾሙበት ዕለት አንሥቶ ያስተጋቧቸውን የተቋማዊ ለውጥ ዕሴቶችና መርሖዎች ተግባራዊ ለማድረግ ዙሪያቸውን መፈተሽ አለባቸው የሚለውን አስተያየት ይጋራሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያለው ኹኔታም ብቃት ያላቸውን እውነተኛ ባለሞያዎች ከፓትርያርኩ የሚያሸሽ እንጂ የሚያቀርብ አይደለም ብለዋል፡፡
የአስተዳደራዊ መዋቅር ማሻሻያ ሒደት የራሱ ተግዳሮቶች እንዳሉት የሚናገሩት የሥራ ሓላፊው፣ የአመራር ብቃትና ብስለት ተግዳሮቶቹን ለበጎ ለውጦ በመጠቀም እንደሚረጋገጥ ያስረዳሉ፡፡ ፓትርያርኩ ሥር ነቀልና ቆራጥ ተግባራዊ ርምጃ እወስዳለኹ ብለው በጀመሩት እንቅስቃሴ ተቃውሞ ሲገጥማቸው፣ ተቃውሞውን የማዳመጥ አባታዊ ሓላፊነት ቢኖርባቸውም ዋናውን የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ ሳይቀር እስከማመቻመች መድረሳቸው የፀረ ሙስና አቋማቸው ከሚዲያ ፍጆታና ከንግግር ያላለፈ፣ የሚናገሩትንም ያህል ጠንካራና ጽኑ አቋም የሚይዙና ውሳኔ ሰጭ ናቸው ብለው እንዳያምኑ እንዳደረጋቸው አስረድተዋል፡፡ ይህም በውጤቱ የለውጥ ተቃዋሚዎቹን በማፈርጠምና የለውጥ ተስፋውን በማመንመን ሒደቱን አደጋ ውስጥ ሊከተውና የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር የበለጠ ሊያወሳስበው እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡
ለፓትርያርኩ የአቋም ጽናት፣የሊቃነ ጳጳሳቱ የአቋም አንድነት አስፈላጊ ነው የሚሉት ሌላው አስተያየት ሰጪ፤ ከምንጊዜውም በላይ በቤተ ክህነቱ ላይ ተባብሶ የሚታየውን የተቋማዊ ለውጡን ሒደት የሚያደናቀፉ አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነቶችን መቋቋምና የቅ/ሲኖዶሱን የውሳኔ ልዕልና ማስከበር እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡
ፓትርያርኩ በተመረጡበት ቀን “እግዚአብሔር ይህን ታላቅ ሓላፊነት እንዴት እችለዋለሁ? በል አንተ ታውቃለህ›› ማለታቸው በርግጥም የሚገባ ነው ያሉት እኚሁ አስተያየት ሰጪ፤ ታላቋንና ጥንታዊቷን ቤተ ክርስትያን በአባትነት ለመምራት ተግዳሮቱ የበዛ ቢሆንም ወደ ዕድገትና ሥልጣኔ የሚያደርሰው ጎዳና በአቡነ ማትያስ ዘመነ ፕትርክና መጠረግና መደልደል ይገባዋል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
![]()
(አፈንዲ ሙተቂ)
———-
ኤርትራን በኢትኖግራፊ መነጽር በዳሰስኩበት የክፍል አንድ ጽሑፌ ላይ የተሰነዘሩ አንዳንድ አስተያየቶች የኤርትራን ችግር ከመሰረቱ እንዳስሰው አነሳስተውኛል፡፡ በተለይም ብዙዎች የሚሳሳቱባቸውን ነጥቦች ማብራራት ተገቢ ሆኖ ታይቶኛል፡፡ ስለዚህ በራሴ ጥናት በደረስኩበት መደምደሚያ መሰረት የግል እምነቴን የሚያንጸባርቀውን ይህንን መጣጥፍ አሰናድቻለሁ፡፡
====የኤርትራ ጥያቄ አነሳስ===
አንዳንዶች “የኤርትራ ጥያቄ በኢጣሊያ ቅኝ ገዥዎች የተፈጠረ የስነ-ልቦና መቃወስ ነው” የሚል እይታ አላቸው፡፡ ይሁንና ይህ አነጋገር ከመሰረታዊ የታሪክ ሐቅ ጋር ይጋጫል፡፡ የኢጣሊያ ቅኝ ገዥዎች ኤርትራን ለ60 ዓመታት ይዘዋታል፡፡ ይሁን እንጂ ህዝቡን የተለየ ስነ-ልቦና ያለው ህዝብ አድርገው ለመቅረጽ ብዙም አልሞከሩም፡፡ በሌላው የአፍሪቃ ሀገር እንደሚታየው ኤርትራዊያን ከጥንታዊ ማንነታቸው ብዙም አልተለወጡም፡፡ ባህላቸውንና ቋንቋቸውን በሚገባ አስጠብቀዋል፡፡ ለምሳሌ በኢጣሊያዊት ኤርትራ ጣሊያንኛ መናገር የሚችለው ህዝብ ከመቶ አስር እጅ ብቻ ነበር፡፡
የኤርትራ ጥያቄ መንቀልቀል የጀመረው በእንግሊዞች አስተዳደር ዘመን ነው፡፡ በዚያ ዘመን ፓርቲ፣ የሙያ ማህበራት፤ ነጻ ፕሬስ፣ ወዘተ በተግባር ላይ በመዋላቸው ህዝቡ በግዛቲቱ የወደፊት እጣ ላይ እንዲነጋገር መንገድ ከፍተዋል፡፡ ይህ ውይይት ተጧጡፎ ሁለት ተጻራራ ጎሳዎች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኗል፤- የአንድነትና የነጻነት ጎራ፡፡ ታዲያ የአንድነት ጎራው ዛሬ እንደሚባለው መላውን የኤርትራ ህዝብ የሚወክል አልነበረም፡፡ የነጻነት ደጋፊም ዛሬ እንደሚባለው በጣም አናሳ አይደለም፡፡ ከተባበሩት መንግሥታትና ከልዩ ልዩ ምንጮች የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት 40% የሚሆነው የራቢጣ ኢስላሚያ ፓርቲ ደጋፊ እና 6 % የሚሆነው የሊበራል ፕሮግሬሲቭ ፓርቲ (የወልደአብ ወልደማሪያም ፓርቲ) ደጋፊ “ነጻነት”ን ይፈልጉ ነበር፡፡ የአንድነት ደጋፊዎች (የሀገር ፍቅር ማህበር አባላትና ሌሎቹም) ብዙሃን የነበሩ መሆናቸው ትክክል ቢሆንም ከኤርትራ ህዝብ 48 % የሚሆነውን ብቻ ነበር የሚወክሉት፡፡ የተቀረው አነስተኛ ቡድን ፕሮኢታሊያ (የጣሊያንን ሞግዚትነት የሚፈልግ ፓርቲ) ደጋፊዎች ነበሩ (እነዚህኛዎቹ ከኢጣሊያ ቅኝ ገዥዎች የተወለዱ ክልሶቸ ነበሩ)፡፡
የኤርትራን ጥያቄ ከዐረቦች ተንኮልም ከእስልምና ተስፋፊነት ጋር ማያያዝም አግባብ አይደለም፡፡ ጥያቄው በኤርትራ ምድር ነው የተነሳው እንጂ በዐረቦች ዘንድ አይደለም፡፡ ዐረቦች ከጥንት ጀምሮ ሁለታችንንም “ሐበሻ” ነው የሚሉን፡፡ በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ኤርትራን ለመያዝ የዘመተችው ግብጽ ፍላጎቷ ሁሉንም የሰሜን ምስራቅ አፍሪቃ ሀገራት ጠቅላላ በመያዝ የአባይን ምንጭና የቀይ ባህር ንግድን መቆጣጠር እንጂ ኤርትራን ለብቻ ገንጥላ የተለየ ቀጣና ማድረግ አልነበረም፡፡ ለዚህም ነበር ግማሽ ጦሯን ይዛ ከዘይላ እስከ ሀረር ድረስ የተዘረጋ ግዛት የመሰረተችው፡፡ በኤርትራ በኩል ግን ከምጽዋ በስተቀር ሊሳካላት አልቻለም፡፡ በራስ አሉላ የሚመራው ጦር ድባቅ እየመታት መልሶአታል፡፡ በታጁራና ጅቡቲ በኩል የመጣውን ጦሯን (በኮሎኔል ሙዚንገር የሚመራውን) ደግሞ የአፋር ጀግኖች ደምስሰውታል፡፡
በእንግሊዞቹ ዘመን የነጻነቱን ጥያቄ በስፋት ይደግፉ የነበሩት ሙስሊሞች እንደነበሩ መካድ አይቻልም፡፡ ሙስሊሞቹ ይህንን ሃሳብ ሲያቀነቅኑ የነበሩት በዘመኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ይታይ ከነበረው ተጨባጭ እውነታ በመነሳት እንጂ “ኢትዮጵያ የምትባለውን ሀገር ስለሚጠሉት አይደለም፡፡ የኤርትራዊያኑ ሙስሊሞች ስጋት “በኃይለ ሥላሤዋ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተቀላቀልን በሀይማኖታችን ምክንያት ከፍተኛ ጭቆና ይፈጸምብናል፤ ስለዚህ ኤርትራ ነጻ ሀገር ብትሆን ነው መብታችን የሚከበረው” የሚል ነው፡፡ የአጼ ኃይለ ሥላሤ መንግሥት የሙስሊሞቹን ስጋት ለመቅረፍ የሚያስችሉ እርምጃዎችን ቢወስድ ኖሮ የኤርትራ ጥያቄ ባልተከሰተ ነበር፡፡
ከላይ እንደተጠቀሰው ሁለቱ ጎራዎች ተቀራራቢ ሚዛን ነው የነበራቸው፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ኤርትራ በፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ጋር እንድትተሳሰር ያደረገበት አንዱ ምክንያትም የሁለቱ ጎራ ደጋፊዎች የተቀራረበ የሀይል ሚዛን (46ለ48) ያላቸው መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡ በሌላ በኩል በእንግሊዞች አስተዳደር የመጨረሻ ዓመታት በሁለቱ ጎራዎች መካከል ከፍተኛ የሆነ ሽኩቻና መጠፋፋት ይካሄድ ስለነበር የተባበሩት መንግሥታት የትኛውንም ጎራ ደግፎ ጥያቄውን ቢፈታው የከረረ የርስ በርስ ጦርነት ይከሰታል የሚል ፍርሃት አድሮበት ነበር፡፡ በመሆኑም “ኤርትራ በፌዴሬሽኑ ከኢትዮጵያ ጋር ብትዋሃድ በሁለቱም ጎራ መካከል ፍጅት እንዳይቀሰቀስ ለማገዝ ይችላል” የሚል እምነት ነበረው፡፡
=====የፌደሬሽኑ ፎርሙላ====
ይህኛውም ብዙ ሰዎች የሚሳሳቱበት ነጥብ ነው፡፡ የኃይለ ሥላሤ መንግሥትም ሆኑ የደርግ መንግሥት ደጋፊዎች ለኤርትራ የተፈቀደው ፌዴሬሽን ምን ዓይነት እንደሆነ ግንዛቤው ያላቸው አይመስለኝም፡፡ “ፌዴሬሽኑ መነካት አልነበረበትም” የሚል ሐሳብ ሲሰነዘር ለተቃውሞ የሚነሱትም በዚሁ ምክንያት ይመስለኛል፡፡ በሌላ በኩል የነጻነት ጎራ ደጋፊዎች በተባበሩት መንግሥታት የተፈቀደውን የፌዴሬሽኑን ፎርሙላ ከከፍተኛ ቅሬታ ጋር የተቀበሉት መሆናቸውም ይረሳል፡፡
ለኤርትራ የተፈቀደው ፌዴሬሽን ዛሬ ላይ ተሁኖ ሲታይ እጅግ በጣም “ሊበራል” የሚባል ነበር፡፡ ሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶችም በዚያ ሞዴል ቢቀረጹ ኖሮ ዛሬ የሚታየው ምስቅልቅል ሁኔታ ተለውጦ ሀገራችን ሌላ መልክ በያዘች ነበር፡፡ በዚያ ዘመን ነጻ ያልወጡት ሶማሊላንድና ጅቡቲም የኛ አካላት ሊሆኑ ይችሉ ነበር ለማለትም ያስደፍራል፡፡ ነገር ግን ንጉሡና ባለሟሎቻቸው በግዴለሽነት ሰረዙት፡፡
——
ኤርትራ በወቅቱ ከኢትዮጵያ ጋር የተዋሃደችበት ፌዴሬሽን በትክክለኛው አገላለጽ ሲታይ “ሙሉ ራስ ገዝ አስተዳደር” የሚባል ነው፡፡ ኤርትራ የራሷ ፓርላማ፣ ህግ አስፈጻሚና ህግ ተርጓሚ አካላት አሏት፡፡ መንግሥቱን የሚመራው “ዋና ስራ አስፈጻሚ” (Chief Executive officer) በፈረቃ ከክርስቲያን ደገኞቹና ከሙስሊም ቆለኞቹ እንዲመረጥ ተወስኗል፡፡ ዋና ስራ አስፈጻሚው ክርስቲያን ከሆነ የፓርላማው ፕሬዚዳንት ከሙስሊም ቆለኞች ነው፡፡ ስራ አስፈጻሚው ከቆለኞቹ ሲመረጥ ደግሞ የፓርላማው ፕሬዚዳንት ከደገኞች ይሆናል፡፡
የኤርትራው ራስ ገዝ አስተዳደር ከውጭ ጉዳዮች፣ ከገንዘብ ነክ ጉዳዮች፣ ከንግድና ከመገናኛ በስተቀር በሁሉም ነገሮች ላይ መወሰን ይችላል፡፡ እነዚህ አራት ዘርፎች የሚመሩት የፌዴራሉ መንግሥት ሆኖ በሚሰራው የአጼ ኃይለ ሥላሤ መንግሥት ነው፡፡ የምጽዋና የአሰብ ወደቦችም በፌዴራሉ መንግሥት ስር ነበር የሚተዳደሩት፡፡
—-
ታዲያ ይህ ፌዴሬሽን ምን በደለ?. ምን አጠፋ?… ይህንን ፌዴሬሽን ለማፍረስ መቸኮል አግባብ ነው?…. ዛሬ እኮ ለኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነት ያልተማከለ አስተዳደር ያስፈልጋታል ነው እያልን ያለነው፡፡ የአጼ ኃይለ ሥላሤ መንግሥት ግን በማን አለብኝነት አጠፋውና ረዥሙን ጦርነት ቀሰቀሰ፡፡ የሀገራችንም ታሪክ ሌላ መልክ ያዘ፡፡
===ፌዴሬሽኑ እንዴት ፈረሰ?====
ሌላው በብዙ ሰዎች የሚሰነዘረው አባባል “ፌዴሬሽኑ የፈረሰው በአንድነት ኃይሎች ሙሉ ፈቃደኝነትና ግፊት ነው” ይላሉ፡፡ ይህኛውም አባባል ምንም ማስረጃ የለውም፡፡ እንዲያውም በፌዴሬሽኑ ዘመን የፌዴሬሽኑ አስተዳዳሪዎች ይከተሉት ከነበረው አድሎአዊነት የተነሳ ከአንድነት ጎራ ደጋፊዎች መካከል እጅግ የሚበዙት የፌደሬሽኑ ተቃዋሚ በመሆን የነጻነቱን ጎራ ተቀላቅለዋል፡፡ በተጨማሪም የቢትወደድ አስፋሓ መንግሥት በኤርትራ ሰራተኞችና የሙያ ማህበራት ላይ በሚያካሄዳቸው የእመቃ ተግባራት ብዙዎችን አስቀይሟል፡፡ ስለዚህ የአንድነት ሀይሎች ጉልበት ኖሯቸው በመንግሥቱ ላይ ግፊት የሚፈጥሩበት ሁኔታ በጭራሽ አልነበረም፡፡ አብዛኛው የኤርትራ ህዝብ “አደይ ኤሪትሪያ”ን መዘመር የጀመረው በነዚያ አመታት ነው፡፡
ፈዴሬሽኑን በግልጽ ያፈረሱት የቢትወደድ አስፋሓ ደጋፊችና ጄኔራል አቢይ አበበን የመሳሰሉ የአጼ ኃይለ ሥላሤ መንግሥት ሹማምንት ናቸው፡፡ ቢትወደድ አስፋሓ ከመጀመሪያኑ በኤርትራ የተሾሙት ለዚሁ ነበር፡፡ እኝህ ሰው በኤርትራ ተወለዱ እንጂ አልኖሩባትም፡፡ ዕድሜአቸውን ያሳለፉት እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ በትርጉም ስራ ላይ ነበር፡፡ በጣሊያን ወረራ ዘመን በአዲስ አበባ ሀገረ ገዥነት ተሹመው በአዲስ አበባ ገነተ-ልዑል ቤተ መንግሥት የሚቀመጡት የዱክ ኦፍ አኦስታ እና የጄኔራል ናዚ አስተርጓሚ ነበሩ፡፡ በኋላም በሲቪል ሰርቪሱ ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡ ለጣሊያን መንግሥት በአስተዳዳሪነት ተሹመው ለሰጡት አገልግሎት ቤኒቶ ሙሶሎኒ ፊት ቀርበው የፈረሰኛ ኒሻን ተሸልመዋል (አምባሳደር ዘውዴ ረታ፣ የኤርትራ ጉዳይ፣ ገጽ 461-462 ተመልከቱ)፡፡
ቢትወደድ አስፋሓ ለሶስት ዓመታት በኤርትራ ፌዴሬሽን የንጉሠ ነገሥቱ ምክትል እንደራሴ ነበሩ፡፡ በዚያ ዘመን በደጃች ተድላ ባይሩ የሚመራው የኤርትራ አስተዳደር በሁለት እግሩ ቆሞ እንዳይሰራ በማድረግ ተግባር ላይ ነው የተጠመዱት፡፡ በዚህ ረገድ ከዋናው እንደራሴ ራስ አንዳርጋቸው መሳይ (ሁለተኛው የልዕልት ተናኘወርቅ ባለቤት) ጋርም ዘወትር ይወዛገቡ ነበር፡፡ የሚገርመው ነገር አጼ ኃይለ ሥላሤ አማቻቸው በቢትወደድ አስፋሓ ላይ የሚያቀርቡትን ክስ በስራ ከመበለጥ የመጣ የዝቅተኝነት ስሜት (inferiority complex) አድርገው መቁጠራቸው ነው፡፡
ቢትወደድ አስፋሓ ከ1955 ጀምሮ ፌደሬሽኑ እስከፈረሰበት ድረስ (1962) ቺፍ ኤክስኩቲቭ ኦፊሰር ወይንም የራስ ገዙ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ሰርተዋል፡፡ እዚህ ላይ አንድ ነገር ልብ በሉ፡፡ የኤርትራን ዋና አስፈጻሚ የሚመርጠው የኤርትራ ፓርላማ ነው፡፡ ተመራጩ የፓርላማው አባል መሆን አለበት፡፡ ይሁንና የአጼ ኃይለ ሥላሤ “የኤርትራ ስራ አስፈጻሚ የግዴታ የፓርላማው አባል መሆን የለበትም” በሚል የጉልበተኝነት ስሜት ቢትወደድ አስፋሓ ለፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚነት እንዲመረጡ አድርገዋል፡፡
ቢትወደድ አስፋሓ የኤርትራ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ሲሾሙ መጀመሪያ ያደረጉት ነገር ለሚወስዷቸው እርምጃዎች ህጋዊ ሽፋን ለማሰጠት የኤርትራ ፓርላማ የኃይለ ሥላሤ መንግሥት እንደሚፈልገው አድርጎ ማዋቀር ነው፡፡ በዚህም መሰረት ቀደም ሲል በተባበሩት መንግሥታት ታዛቢነት የሚካሄደውን የምርጫ ዘይቤ ለወጥ በማድረግ አሁን በአፍሪካ የሚካሄደውን የምርጫ ቲያትር አመጡ፡፡ ለምሳሌ ከምዕራብ ቆላ በሚመረጡ ሙስሊሞች ወንበሮች ላይ ለርሳቸው ታማኝ የሆኑትን የደጋ ሙስሊሞችን አስመርጠዋል፡፡
ከዚህ በኋላ ነበር ፌዴሬሽኑን የማፈራረሱ ስራ የተጀመረው፡፡ ፓርቲዎች ታገዱ፡፡ ነጻ ፕሬስም ታገደ፡፡ የሰራተኛ ማህበራትም ታገዱ፡፡ “ዐረብኛ የባዕድ ቋንቋ ነው” በሚል ከህገ-መንግሥቱ ተፍቆ ወጣ፡፡ ከዚያም የኤርትራ ባንዲራ እንዳይውለበለብ ተደረገ፡፡ በማስከተልም ትግርኛ ከስራ ቋንቋነት ተሰረዘ፡፡ በምትኩ አማርኛ የስራ ቋንቋ ሆነ፡፡ “ዋና ስራ አስፈጻሚ” የሚለው የፌዴሬሽኑ ገዥ መጠሪያም “ዋና አስተዳዳሪ” በሚል ተተካ፡፡ ፡ በመጨረሻ ላይ “የኤርትራ ፓርላማ ወስኗል” በሚል ፌዴሬሽኑ ፈረሰ፡፡
ፌዴሬሽኑ እንዲህ እየተገዘገዘ ነበር ቀስበቀስ የፈረሰው፡፡ የፈዴሬሽኑ አፍራሾችም ድሮ ለአንድነት የታገሉ የአንድነት ሀይሎች ሳይሆኑ ቢትወደድ አስፋሓ በሚፈልጉት መንገድ የተመረጡ አድር ባዮች ነበሩ፡፡
ይህንን የቢትወደድ አስፋሓን ታሪክና የማምታት ዘዴ ብዙዎች ጽፈውታል፡፡ በአማርኛ ታሪኩን በሰፊው የጻፉት ግን አምባሳደር ዘውዴ ረታ ናቸው፡፡ አምባሳደር ዘውዴ መጽሐፉን ሲጽፉ ቢትወደድ አስፋሓን የአንድነትና የነፃነት ጠበቃ በማድረግ ነው የሚያንቆለጳጵሱት፡፡ ቢትወደድ አስፋሓ የወሰዱትን እርምጃ አንድ በአንድ እየተረኩልን እንኳ ህገ-ወጥነታቸውን ያደንቁላቸዋል፡፡ ታዲያ በጣም የሚያሳዝነው ነገር በዚሁ መጽሐፍ ውስጥ ጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ኤርትራን በፌዴሬሽን ለማስመለስ ያደረጉት እልህ አስጨራሽ ትግልና ፌዴሬሽኑ እንዳይፈርስ ያደረጉት ጥረት ሰፋ ብሎ የቀረበ መሆኑ ነው፡፡ ጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ለአጼ ኃይለ ሥላሤ “በህግ ፈርመን የተቀበልነውን አደራ ማክበር አለብን” የሚል ተደጋጋሚ ምክር ቢሰጧቸውም ንጉሡ በጭራሽ ሊሰሟቸው አልፈቀዱም፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያና ኤርትራ ሁለት ሀገር የመሆናቸው እርሾ ተጠነሰሰ፡፡
===የኤርትራ ነጻነት ትግል እና የኤርትራዊነት ስነ-ልቦና===
የኤርትራ ነጻነት ትግል የተለኮሰው ፌዴሬሽኑ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ታዛቢዎች በወጣለት ህገ-መንግሥት መሰረት ስራዎቹን በአግባቡ ማከናወን ስላቃተው ነው፡፡ ከላይ እንደተገለጸው በ1950ዎቹ አጋማሽ አብዛኛው ህዝብ ከአንድነት አቀንቃኝነት ወጥቶ ወደ ነጻነት ፈላጊው ጎራ መቀላቀል ጀምሯል፡፡ ትግሉን በተደራጀ መንገድ የመጠንሰሱን ሃሳብ የወጠነው ግን ሰባት ሰዎች የመሰረቱት “ማህበር ሸውአተ” የሚባለው እድር መሳይ ማህበር ነው፡፡ ይህ ማህበር ከጥቂት ጊዜ በኋላ “ምንቕስቓስ ሓርነት ኤርትራ” (“ሐረካት ታሕሪረል ኤሪትሪያ”/Eritrean Liberation Movement) የሚባል ድርጅት ወለደ (ድርጅቱ በታሪክ ምዕራፎች “ሐረካ” እየተባለ ነው የሚጠራው)፡፡
“ሐረካ” ወደ ትግሉ የገባው ፌዴሬሽኑ ከመፍረሱ ከሶስት ዓመታት አስቀድሞ ነው፡፡ የትግሉ ዋነኛ ዓላማም “የኤርትራ ፌዴሬሽን በህገ-መንግሥቱ መሰረት ስራውን እንዲያከናውን መጠየቅ” ነበር፡፡ ይሁንና አብዛኛው ኤርትራዊ ኤሊት ለአስር ዓመታት ባየው የፌዴሬሽኑ አሰራር ተስፋ የቆረጠ በመሆኑ “የፌዴሬሽን አሰራርን በጭራሽ አንቀበልም” ባይ ሆነ፡፡ በተለይም የቀድሞ የኤርትራ ፓርላማ አባላት በዚህ ላይ ግትር አቋም ያዙ፡፡ በመሆኑም ከነጻነት በመለስ ሌላ አማራጭ ለመቀበል ዝግጁ ያልሆነው “ተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ” ወይንም “ጀብሃት ታሕሪረል ኤሪቲሪያ” (ጀብሃ) እ.ኤ.አ መስከረም ወር 1961 በካይሮ ከተማ ብዙ ህዝብ በተሰበሰበት ተመሰረተ፡፡ ጀብሃ ትግሉን ለሃያ ዓመታት ከቀጠለበት በኋላ በውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች ተዳክሞ ሲወድቅ ከርሱ የተገነጠለው “ህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ” ወይንም “ጀብሃት አሽ-ሻዕቢያ ሊ-ተሕሪረል ኤሪቲሪያ” (ሻዕቢያ) እርሱን ተክቶ መዋጋቱን ተያያዘው፡፡ በ1983 (1991) ኤርትራ ነጻ ሀገር ሆነች ፡፡ የኤርትራ የነጻነት ትግል የተጓዘበት መንገድ ከብዙ በጥቂቱ ይህንን ይመስላል፡፡ ይህ መሆኑ እየታወቀ “የቅኝ ገዥዎች ተንኮል”፣ “የዐረቦች ሸር” ወዘተ.. የሚሉ ሰበቦችን መደርደር ራስን መደለል ነው፡፡
ኤርትራዊነት “የቅኝ ተገዥነት ስሜት የፈጠረው የተቃወሰ ስነ-ልቦና ነው” የሚለውም ክስ ከዚሁ ጋር ነው የሚታየው፡፡ ኤርትራዊያንን እስከምናውቃቸው ድረስ ለፈረንጅ ገዥ ያላቸው ስሜት ከኛ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ለዚህም ነበር በ1929-1933 የኢጣሊያ ወረራ ዘመን በርካታ የኤርትራ ጀግኖች ድንበር አቋርጠው ከኢትዮጵያ አርበኞች ጋር የተቀላቀሉት፡፡ የኢትዮጵያ ባንዲራ በኢጣሊያ ወታደሮች መረገጡ አንገብግቦት የጠላቶቹን አንገት በሰይፍ የቀላው ጀግናው ዘርዓይ ደረስ ከተወለደበት ኤርትራ ውጪ የተቀረውን የኢትዮጵያ ክልል ለአንድም ቀን ረግጦ አያውቅም፡፡ ጀግኖቹ አብረሃ ደቦችና ሞገስ አስገዶምም በቅኝ ገዥዋ ኮሎኒያል ኤሪትሪያ ነበር የተወለዱት፡፡ የህዝቡ ስነ-ልቦና በቅዥ ተገዥነት ስሜት የተቃወሰ ቢሆን ኖሮ እንደዚህ የበረከቱ ጀግኖች በሀገሩ ላይ ባልበቀሉ ነበር፡፡
——
ለኤርትራ ጥያቄ መፈጠር እርሾ የሆነው የቅኝ ተገዥነት ስሜት ሳይሆን የኛ መንግሥታት ሲያካሄዱት የነበረው ኢ-ፍትሐዊነትና ብሄራዊ ጭቆና ነበር፡፡ ያለፉት መንግሥታት ቤታችንን በማስተካከል ለሁላችንም እንዲመች ቢያደርጉት ኖሮ ጥያቄው ባልተፈጠረ ነበር፡፡ ለዚህ ፋና ወጊ የነበረውን የልጅ እያሱ ፖሊሲ መጥቀስ ይቻላል፡፡
ይልቅ ከኤርትራዊያን ጋር የማንግባባው “ኢትዮጵያ ቅኝ ገዥ ነበረች” በሚለው አገላለጽ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ቀርቶ ረጅም ሀገር አቋርጠው ምጽዋን ለአራት መቶ ዓመታት የያዙት ኦቶማን ቱርኮች እንኳ ቅኝ ገዥ ተብለው አልተጠሩም፡፡ መንግሥታቶቻችን የኤርትራን ጥያቄ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ለመስማት ባይፈለጉትም አውሮጳዊያን እንዳደረጉት አዲስ ሀገር በወረራ አልያዙም፡፡ መሬቱ ከጣሊያኖች መምጣት በፊት በራስ አሉላ ስር “መረብ ምላሽ” ተብሎ ይተዳደር ነበር፡፡ በጥንቱ ታሪክ ውስጥ ደግሞ ኤርትራ “ባህረ ነጋሽ” የሚል ስያሜ የነበራት ዋነኛዋ የኢትዮጵያ አስኳል እንደነበረች ነው የምናውቀው፡፡ የጥንቱ “አቢሲኒያ” (ሐበሻ) የሚለው አጠራር መጀመሪያ የተፈጠረው በኤርትራና በትግራይ ውስጥ ነው፡፡ እዚህ ላይ ፕሮፌሰር መስፍን በግንቦት ወር 1983 የለንደን ኮንፈረንስ ሲካሄድ ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ “እኛ ኢትዮጵያዊያን አይደለንም ማለታችሁ ትልቁ ስህተታችሁ ነው፤ ኢትዮጵያዊያን እኛ እንጂ ሌሎች አይደሉም ብትሉ ኖሮ ትንሽ እውነት ይኖርበት ነበር” ያሉትን መጥቀስ ተገቢ ነው፡፡ የፕሮፌሰር መስፍን አገላለጽ ለዘመናችን ሰው ባይስማማም የታሪክ ሐቅ አለበት፡፡
====የመንግሥታቱ የቅራኔ አፈታት እንከኖች====
የኤርትራን ጥያቄ ያወሳሰበው አንዱ ምክንያት መንግሥታቱ ቅራኔዎችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አለመከጀላቸው ነው፡፡ ሁሉም ሀገረ ገዥ እና አስተዳዳሪ ጦርኝነትን እንጂ ተስፈኝነትን ሲዘምር አልታየም፡፡ እስቲ ነገሮችን በምሳሌ ላስረዳ፡፡
ጀብሃ በአንድ ጊዜ ብዙ ተከታዮችን ለማፍራት የቻለው ራስ አስራተ ካሣ በሚያካሄዱት የጭካኔ ዘመቻ የኤርትራ ቆላ ህዝብ በብዛት ወደ ግንባሩ በመጉረፉ ነው፡፡ ራስ አስራተ ከሚወስዱት እርምጃ ሳይታረሙ ተከታታይ ዘመቻዎችን ሲያካሄዱ ደግም ህዝቡ በብዛት ወደ ሱዳን ተሰደደ፡፡ የተቀረው ጀብሃን ተቀላቀለ፡፡ ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርስ “ሬድ ቲርስ” በተሰኘው መጽሓፋቸው ራስ አስራተ ያዘመቱት ጦር በወሰደው እርምጃ በአንድ ጀንበር ብቻ ከአምስት ሺሕ የማያንስ ህዝብ ማለቁን ያስረዳሉ፡፡
የደርግ መንግሥት ሲመጣም ችግሩ ተባባሰ እንጂ አልተቃለለም፡፡ በተለይም ሻዕቢያ ተከታታይ ድል በሚቀዳጅባቸው የመጨረሻዎቹ ዓመታት ሺዎች በታንክና በመድፍ አልቀዋል፡፡ ለምሳሌም በዓለም የመገናኛ ብዙሃን ሰፊ የመነጋገሪያ አጀንዳ ለመሆን የበቃውንና በ1980 በቀይ ባህር ዳርቻ ባለችው የሸዒብ ከተማ ህዝብ ላይ የደረሰውን ፍጅት መጥቀስ ይቻላል፡፡
እነዚህ መንግሥታት የኤርትራን ችግር በሰላም ለመፍታት የወሰዷቸው እርምጃዎች ኢሚንት ናቸው፡፡ ራስ አስራተና የአሜሪካ ሚሊታሪ አዛዦች በአጼ ኃይለ ሥላሤ ጠያቂነት የተቋቋመውን የሰላም ኮሚቴ በመጥለፍ ጀብሃና ሻዕቢያ እንዲጨራረሱ ለማድረግ ሞከሩ፡፡ የደርግ መንግሥት ደግሞ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የክፍለ ሀገሩን ችግር በሰላም ለመፍታት ያግዛሉ በማለት ተስፋ ያሳደረባቸውን ጄኔራል አማን አንዶምን አስገደለ፡፡ እንዲህ ማድረጋቸው ሳያንስ በጄኔራል አማን ላይ ተከታታይ የቅጥፈት ወሬ ማስወራት! ያሳዝናል፡፡
ደርጎች እስከዛሬ ድረስ “ጀኔራል አማን የተገደሉት ወንበዴዎቹ ኤርትራን እንዲገነጥሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸታቸው ስለተደረሰበት በዚህ አኩርፈው ቤታቸው ውስጥ ስለመሸጉ ነው” ይላሉ፡፡ በደርግ ወገን ሆነው የጻፈ የትኛውም ሰው ይህችን ቃል ይደጋግማል፡፡ ይሁንና ለህሊናቸው ታማኝ የሆኑት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም “በጄኔራል አማን ላይ የተደረገው ቅጥፈት እጅግ በጣማ ያሳዝናል፤ ጄኔራል አማን ኤርትራ ከኢትዮጵያ እንዳትገነጠል ተገቢውን ጥረት ያደረጉ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ናቸው” በማለት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል (የክህደት ቁልቁለት የተሰኘውን መጽሐፍ አንብቡ)፡፡ ጄኔራል ጃጋማ ኬሎም በሰጡት የምስክርነት ቃል ይህንኑ አረጋግጠዋል፡፡
የደርግ መንግሥት የሚወስዳቸው እርምጃዎች የኤርትራ ጥያቄ እጅግ በጣም የተወሳሰበ እንዲሆን ነው ያደረጉት፡፡ ደርግ በመውደቂያው ሰሞን ከሻዕቢያ ጋር ንግግር ለማድረግ መሞከሩ ሚዛን የሚደፋ ዜና ለመሆን ያልቻለው ወርቃማው እድል ካመለጠ በኋላ የተመዘዘ ካርድ ስለሆነ ነው፡፡
ከደርግ ቀጥሎ የመጣው ህወሐት ለኤርትራ ጥያቄ እውቅና መስጠቱ የሚያስወድሰው ነው፡፡ ነገር ግን ከኤርትራዊው አጋር ድርጅቱ (ሻዕቢያ) ጋር ወደፊት አብሮ መኖር ስለሚቻልበት ሁኔታ በመነጋገር የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያሰፋበትን ሁኔታ መቀየስ ሲገባው “የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው” የሚል ግትር አቋም የሚያራምድ ሆኖ ተገኘና ህዝቡን አስቀየመ፡፡ በተጨማሪም የኤርትራ ሪፈረንደም በተካሄደበት ወቅት ውሳኔውን የሚያጸድቅበት “ማንዴት” ከህዝብ ያልተሰጠው የሽግግር ጊዜ መንግሥት ይዞ ውሳኔውን በማጽደቁ የህዝቡን ልብ ሰበረው፡፡ ለዚህችው ብቻ ሲታገል የኖረ አስመሰለበት፡፡
——–
ከላይ እንደለገጽኩት የኤርትራ ጥያቄ አግባብነት የነበረው ጥያቄ ነው፡፡ መንግሥታቱ ግን በተገቢው መንገድ አላስተናገዱትም፡፡ ኃይለ ሥላሤና ደርግ በጀብደኝነት ጥያቄውን ረገጡት፡፡ ይህኛው መንግሥት ደግሞ ከህዝብ ስል&
239 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲበር የነበረ ንብረትነቱ የማሌዢያ የሆነ ቦይንግ 777 የመንገደኞች አውሮፕላን ደብዛው ከጠፋ ከ20 ሠዓታት በኋላም ሊገኝ አልቻለም።
የዓለም ዜና
ዘ ሄግ ፣ ኔዘርላንድስ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት የጦር ባላባት ጀርሜን ካታንጋን እአአ የካቲት 24፣ በ2003 ዓም በአንድ መንደር 200 ሰዎች አንድም በስለት ተጨፍጭፈው ወይም በጥይት
በሳህል አካባቢ የተከሰተው ድርቅ፣ የሰብል መበላሸት፣ የዋጋ መወደድ፣ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች የረሀብ አደጋ አሰጋቸው። በተመድ የምግብ ይዞታ ተመልካች መስሪያ ቤት ያወጣው ዘገባ እንደሚያሳየው፣ በሞሪታንያ ብቻ ከየአምስቱ ነዋሪዎች መካከል አንዱ በምግብ እጥረት ተጎድቶዋል።
ስለ ማኅበራት የሰጡትን አስተያየት መልሰው እንዲያጤኑት ተጠየቀ ‹‹ማኅበራት በትኩረት ሊመሩና ጉዟቸውም እየተፈተሸ ሊስተካከል ይገባል›› መንግሥት (አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፫ ቁጥር ፯፻፴፰፤ የካቲት ፳፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ‹‹ከዩኒቨርስቲ ተመርቀው ቤተ ክርስቲያንን እንምራ እያሉ ነው፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ ትውፊትና ሥርዓት አላት፤ እንዲህ ማለት አይችሉም›› በማለት የሰጡትን አስተያየት መልሰው …![]()
By Addis Admass Newspaper , Written by Administrator

ኪሳራው በጊዜ ሲሰላ፣ የአገሪቱን የስልጣኔ ጭላንጭል ያዳፈነ፣ የ30 ዓመት የኋሊት ጉዞ ነው።
30 ዓመት ቀላል አይደለም፤ እነ ደቡብ ኮሪያ ከድህነት ወደ ብልፅግና የተሸጋገሩበት ጊዜ ነው።
“የአብዮተኛው ትውልድ”ን ኪሳራዎችን ለመደበቅ ተብሎ ብዙ ታሪክ ተድበስብሷል
ትምህርት የተስፋፋው፣ የሴት ተማሪዎች ቁጥር ያደገው ከአብዮቱ በፊት ነው ወይስ በኋላ?
የኤሌክትሪክ፣ የስልክ፣ የመንገድና የአየር ትራንስፖርት በፍጥነት የተሻሻለውስ መቼ ነው?
በእህል ምርት፣ በኢንዱስትሪ፣ በኤክስፖርት መስኮች የብልፅግና ምልክት የታየውና የጠፋውስ?
የሙያ ፍቅር ያበበው፤ ስነፅሁፍ፣ ትያትርና ሙዚቃ ያደገው፤ ስፖርት የተሻሻለው መቼ ይሆን?
በ1950 ዓ.ም በአዲስ አበባ፣ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍል የመጡ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ላይ የዳሰሳ ጥናት ያካሄዱት ዊሊያም ሻክ፤ በአገሪቱ እያቆጠቆጠ ከመጣው የትምህርትና የስልጣኔ ጅምር ጋር መልካም የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ እንደነበር ይገልፃሉ። አንደኛ፤ የዘመኑ ወጣቶች እንደ ጥንቱ የመንግስት ስልጣንንና ተቀጣሪነትን አልያም የሃይማኖት መሪነትንና ሰባኪነትን የሚመኙ አይደሉም። ሁለተኛ፤ “ይሄኛው ሙያና ይሄኛው የሕይወት ዘይቤ፣ ለአማራ፣ ለኦሮሞ ወይም ለሶማሌ ተወላጅ ነው። ያኛው ሙያና ያኛው የኑሮ ዘይቤ ደግሞ ለትግራይ፣ ለወላይታ ወይም ለጉራጌ ተወላጅ ነው” የሚሉ የዘልማድ አዝማሚያዎችን አይቀበሉም። የ1950ዎቹ ወጣቶች የሙያና የግል ሕይወታቸውን በራሳቸው መንገድ መምራት እንደሚችሉ የሚያምኑ ሆነዋል።
ተማሪዎቹ ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የመጡ ቢሆኑም፤ የሙያ ምርጫቸው ይመሳሰላል። ከመንግስት ስልጣንና ተቀጣሪነት ወይም ከሃይማኖት ሰባኪነት ይልቅ፤ ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሚሰጡት ለምህንድስና ወይም ለህክምና ሙያ፣ ለሜካኒክነት ወይም ለአስተማሪነት ሙያ እንደሆነ ጥናቱ ገልጿል። በአጭሩ፤ በያኔው የስልጣኔ ጭላንጭል፤ ለእውቀትና ለሳይንስ፤ ለሙያዊና ለምርታማ ስራ ክብር የሚሰጥ ትውልድ እየተፈጠረ ነበር። በአገሪቱ እየታየ የነበረውንም የትምህርትና የኢኮኖሚ ብሩህ አቅጣጫ ያመላክታል። Occupational Prestige, Status, and Social Change in Modern Ethiopia: William A. ShackSource: Africa: Journal of the International African Institute, Vol. 46, No. 2 (1976), pp. 166-181
በ1950ዎቹ ዓ.ም ኢትዮጵያ በሁሉም መስኮች ከእንቅልፏ እየነቃች እንደነበረ የሚያሳዩ የጥበብ ስራዎችንም መጥቀስ ይቻላል። የሃዲስ አለማየሁና የፀጋዬ ገብረመድህን ድርሰቶች፣ የነጥላሁን ገሠሠና የነምኒልክ ወስናቸው የሙዚቃ ስራዎች፣ ዛሬ ከአርባ እና ሃምሳ አመታት በኋላም፣ ወደር አልተገኘላቸውም። በእግር ኳስ እና በሩጫ ስፖርቶችም እንዲሁ።
በመንግስት አስተዳደር በኩልም፤ ትልቅ “የስልጣኔ አብዮት” የተካሄደው፣ ከ1960ዎቹ “አብዮተኛ ትውልድ” በፊት ነው። ለሺ አመታት በሃይማኖታዊ ሰነዶች (በክብረ ነገስትንና በፍትሃ ነገስት) ላይ ተመስርቶ የቆየውን የአገሪቱ ሥርዓትና ሕግ፣ ከኋላቀርነት ለማላቀቅና የስልጣኔ እድል ለመፍጠር ያስችላሉ የተባሉ የሕገመንግስት እና የምርጫ ህጎች ከ1923 እስከ 1948 ዓ.ም ፀድቀዋል። የተለያዩ የፍትሐ ብሄርና የወንጀል ሕጎች ከ1935 እስከ 1960ዎቹ መግቢያ ድረስ ታውጀዋል። የወንጀልና የፍትሐ ብሄር ህጎቹ እስከ ዛሬ ድረስ ይሰራሉ – (በ2000 ዓ.ም የተወሰነ ማሻሻያ ቢታከልባቸውም)።
ነገር ግን ሕጎችን በማወጅ ብቻ ሳይሆን፤ በግል አርአያነትና ጥረትም አገሬውን ወደ ስልጣኔ ለማራመድ ሙከራዎች ተደርገዋል። “በለውጥ ላይ የምትገኝ ኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ በ1948 ዓ.ም ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሞን ሜሲን፤ በ1925 ገደማ ዓ.ም የንጉሡ ሴት ልጅ መሞቷን ጠቅሰው፤ ለሟቿ ልዕልት የተዝካር ድግስ እንደማይዘጋጅ በአዋጅ መነገሩን ይገልፃሉ። ኢትዮጵያውያን ገበሬዎች ያለ አቅማቸው በሚደግሱት ተዝካር ኑሯቸው መናጋቱ ብቻ አይደለም ችግሩ። የየአካባቢው የመንግስት ባለስልጣናት በየፊናቸው ተዝካር ሲደግሱ፤ የአካባቢው ነዋሪና ገበሬ፤ ወደደም ጠላም፤ እህል፣ ከብት እና ገንዘብ እንዲያዋጣ ይገደዳል። ገበሬዎችን ከዚህ ልማዳዊ ሸክም ለመገላገል ነበር የንጉሡ ሙከራ – ይላሉ ፀሐፊው።
ይህም ብቻ አይደለም። የድሮ ለቅሶ እንደዛሬ አይደለም። በእርግጥ ዛሬም ቢሆን፤ የአገራችን ለቅሶ ለታይታ የሚቀርብ ቅጥ ያጣ ልማድ ነው። ግን የድሮው ይብሳል። ሰው ሲሞት፣ ልብስ መቅደድና ፀጉር መንጨት፤ ፊት መቧጨርና ደረት መደለቅ፤ መሬት ላይ መንከባለልና አፈር መልበስ የተለመደ ነበር። ነውጠኛ ለቅሶ ይሉሃል ይሄ ነው። ይህን ለማስቀረት ንጉሡ እንደጣሩ የሚገልፁት ሲሞን ሜሲን፤ ነጠላ አዘቅዝቆ መልበስ የተጀመረው ያኔ ነው ይላሉ። Changing Ethiopia፡ Simon D. MessingSource: Middle East Journal, Vol. 9, No. 4 (Autumn, 1955), pp. 413-432።
እንዲህ በየመስኩ የስልጣኔ ጭላንጭሎች ብቅ ብቅ ቢሉም፤ የ1960ዎቹ ተማሪዎችና ወጣት ምሁራን፤ በንጉሡ ደስተኛ አልነበሩም። እንዲያውም፤ ንጉሡን እንደ ዋነኛ ጠላት ፈርጀዋቸዋል። “ንጉሡ አገሪቱን በኋላቀርነት አስረው ይዘዋል። ህዝቡን ከትምህርት አራርቀውታል፤ በተለይ ሴቶች በመሃይምነት ጨለማ ተውጠዋል (ድርብ ጭቆና እንዲሉ)። ህዝቡ ከመሰረተ ልማትና ከኢኮኖሚ እድገት፣ ከኤሌክትሪክና ከስልክ፣ ከመንገድና ከትራንስፖርት አገልግሎቶች እንዳይተዋወቅ፤ የእርሻና የኢንዱስትሪ እድገት እንዳያይ ያደረጉት ንጉሡ ናቸው” የሚሉ ውግዘቶች፤ በያኔዎቹ “የአብዮታዊ ትውልድ” አባላት እንደተጀመሩ እስከዛሬ ዘልቀዋል።
እውነታው ግን፤ ሙሉ ለሙሉ የዚህ ተቃራኒ ነው። በእርግጥ፤ የንጉሡን ዘመን በብዙ ምክንያቶች መተቸት ይቻላል። “የአገሪቱ የስልጣኔ ጅምር ተንቀራፈፈ፤ መፍጠን ነበረበት” ብሎ መተቸት ስህተት አይሆንም። በአብዮቱ የመጣው ለውጥ ግን፤ ጭራሽ የስልጣኔ ጅምርን አዳፍኖ የሚደመስስ ሆነ። ከንጉሡ ድክመት ይልቅ “የአብዮታዊው ትውልድ” ጥፋት በብዙ እጥፍ ይልቃል። “የአብዮታዊው ትውልድ” በርካታ አባላት ታዲያ፣ ይህ ታሪካዊ ውድቀታቸውና ኪሳራቸው በግልፅ እንዲታወቅ አይፈልጉም። ለዚህም ነው፤ እንደያኔው አሁንም ጨምር፤ የንጉሡን አስተዳደር ከማውገዝና ከማጥላላት ያልቦዘኑት። ነገር ግን እውነታውን ለዘላለም መሸፈን አይችሉም። የንጉሡንና የአብዮቱን ዘመናት፤ የዛሬውንም ጭምር ለመመዘንና ለማነፃፀር የምንችልባቸው መረጃዎች ብዙ ናቸው። ዛሬ ጥቂቶቹን ብቻ እንመልከት።
ትምህርት ከጀማሪ እስከ ዩኒቨርስቲ
በ1938 ዓ.ም የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ቁጥር፣ 35ሺ እንደነበር የሚገልፁት ዶ/ር ተከስተ ነጋሽ፣ ከአስር አመት በኋላ 95ሺ እንደደረሰ ይገልፃሉ – ዘጠኛ ሺ ገደማ የአንደኛ ደረጃ፣ አራት ሺ ገደማ የሁለተኛ ደረጃ፣ አራት መቶ ገደማ የከፍተኛ ትምህረት ተማሪዎች። በ1955 ዓ.ም፣ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች አስር ሺ፣ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ደግሞ 305 ሺ መድረሱን ዶ/ር ተከስተ ጠቅሰዋል – በወቅቱ የስምንተኛ ክፍል ተማሪ እንደነበሩ በማስታወስ Education in Ethiopia Nordiska Afrikainstitutet, Uppsala። እንደገና ከአስር አመት በኋላ በአብዮቱ ዋዜማ፣ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ቁጥር 1.04 ሚሊዮን ደርሷል – በሃያ አመታት ውስጥ ከአስር እጥፍ በላይ በማደግ።
በደርግ ዘመን፣ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት የተመዘገበው የተማሪዎች ቁጥር ወደ 2.9 ሚሊዮን ገደማ ነው – በሶስት እጥፍ አድጓል ማለት ነው። በኢህአዴግ 20 አመታት ውስጥስ? የተማሪዎቹ ቁጥር ወደ 15 ሚሊዮን ገደማ ሆኗል። በደርግ ዘመን ከነበረው ቁጥር ጋር ሲነፃፀር በአምስት እጥፍ ይበልጣል።
በንጉሡ ዘመን በሃያ አመታት ውስጥ ከሃያ እጥፍ በላይ የጨመረው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ቁጥር በ1966 ዓ.ም 190ሺ ገደማ እንደደረሰ የሚገልፀው የአለም ባንክ መረጃ፣ በደርግ ዘመን ወደ 900ሺ እንደተጠጋ ይገልፃል። የደርግ ዘመን የተመዘገበው የአራት እጥፍ እድገት ከንጉሡ ዘመን ያነሰ ነው። በኢህአዴግ ጊዜም እንዲሁ። ኢህአዴግ ደግሞ በሃያ አመታት ውስጥ ወደ አምስት እጥፍ ገደማ በማሳደግ 4.5 ሚሊዮን አድርሶታል።
የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ቁጥር፣ በንጉሡ ዘመን በሃያ አመታት ውስጥ፣ ከአራት መቶ ገደማ ወደ 6500 አካባቢ ጨምሯል – በአስራ አምስት እጥፍ። በደርግ ዘመን ወደ ሶስት እጥፍ ገደማ አድጎ 18ሺ የደረሰ ሲሆን፣ በኢህአዴግ የሃያ አመታት ጊዜ፣ እንደ ንጉሡ ዘመን ከአስራ አምስት እጥፍ በማደግ ከ350ሺ በላይ ሆኗል።
ትምህርት በወንዶችና በሴቶች
የአብዮተኞቹ አንዱ መፈክር፣ የፆታ እኩልነት የሚል አልነበር? እስቲ የሴት ተማሪዎችን ድርሻ እንመልከት። አብዮተኞቹ የንጉሡን ዘመን ሲያወግዙ ስትሰሙ፤ በአብዮቱ ዋዜማ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት፣ የሴቶች ድርሻ ከዜሮ በታች የነበረ ነው የሚመስላችሁ። ነገር ግን፣ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በ66 ዓ.ም. ከአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች መካከል 32 በመቶ ያህሉ ሴቶች ነበሩ። በደርግ ዘመን የሴቶች ድርሻ ወደ 40 በመቶ ገደማ ደረሰ፣ በኢህአዴግ ደግሞ ወደ 47 በመቶ።
በከፍተኛ ትምህርት፣ እዚህ ግባ የማይባል ድርሻ የነበራቸው ሴቶች፣ በ1952 ዓ.ም ወደ 3 በመቶ ድርሻ ካገኙ በኋላ፣ በሶስት እጥፍ አድጎ በአብዮቱ ዋዜማ ወደ አስር በመቶ ገደማ ድርሻ ለመያዝ የበቁ ሲሆን፣ በደርግ ዘመን የሴቶች ድርሻ ወደ 18 በመቶ አድጓል። በኢህአዴግ ዘመን ደግሞ፣ ወደ 30 በመቶ ገደማ ደርሷል።
በሴቶች ትምህርት ዙሪያ ፈጣን እድገት የተመዘገበው መቼ እንደነበር፤ ይሄው መረጃው ራሱ ይናገራል።
የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ላይም አብዮተኞቹ ለውጥ አላመጡም። በንጉሡ ዘመን፣ በመጨረሻዎቹ ሃያ አመታት፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ከሰላሳ እጥፍ በላይ ስለጨመረ፣ የተማሪዎቹ ቁጥር በአብዮቱ ዋዜማ 8700 ገደማ ደርሶ ነበር። በደርግ ዘመን የታየው እድገት ኢምንት ነው። የተማሪዎች ቁጥር ከአስር ሺ ብዙም ፈቀቅ አላለም። በመጀመሪያዎቹ የኢህአዴግ አስር አመታትም እንዲሁ፣ የእድገት ፍንጭ አልታየም። ከዚያ በኋላ ነው በፍጥነት ማደግ የጀመረው። በኢህአዴግ ሃያኛ አመት ላይ፣ የቴክኒክና ሙያ ተማሪዎች ቁጥር፣ ከሰላሳ እጥፍ በላይ በማደግ ከ350ሺ በላይ ሆኗል።
የ“መሰረተ ልማት” አቅርቦት
በ1947 ዓ.ም፣ በአገሪቱ የነበረው አመታዊ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት፣ 33 ጊጋዋትሃወር እንደነበር የውሃ ሚኒስቴር ባለሙያ መረጃ ያሳያል። በአማካይ ለአንድ ሰው 1600 ዋትአወር… በጣም ትንሽ ነው። ለአንድ ቤተሰብ በቀን ለ25 ደቂቃ አንድ አምፖል ብቻ ያበራ ነበር እንደማለት ነው። እስከ አብዮቱ ዋዜማ ድረስ ሃያ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ግን፣ አቅርቦቱ በ18 እጥፍ ጨምሯል። 18 እጥፍ? ፈጣን እድገት ነው።
የአለም ባንክ መረጃ እንደሚያሳየው፣ በአብዮቱ ዋዜማ አመታዊው የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት 590 ጊጋዋትአወር ደርሶ ነበር። ግን በእነዚሁ አመታት ውስጥ የሕዝብ ቁጥርም ስለጨመረ፣ የኤሌክትሪክ ሃይል የማግኘት እድል በ18 እጥፍ ሳይሆን በ11 እጥፍ ነው የጨመረው። ይሄም ቀላል አይደለም። በቤተሰብ በየቀኑ 5 ሰዓት ያህል አምፖል እንደማብራት ቁጠሩት። ይሄ በንጉሡ ዘመን ነው።
በደርግ ዘመንስ? በ17 የደርግ አመታት ውስጥ፣ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት 1210 ጊጋዋትአወር ነው የደረሰው። በንጉሡ ዘመን ከነበረው ጋር ሲነፃፀር በአንድ እጥፍ ብቻ ነው የጨመረው። ግን ኢትዮጵያውያን የኤሌክትሪክ ሃይል የማግኘት እድላቸው ብዙም አልጨመረም። ለምን ቢባል፣ የሕዝብ ቁጥርም ጨምሯላ። እናም፣ በቤተሰብ ሲሰላ፣ በየቀኑ 6 ሰዓት ለማይሞላ ጊዜ አንድ አምፖል የማብራት ያህል ነው። በአጭሩ፣ በደርግ ዘመን ኤሌክትሪክ የመጠቀም እድል የተሻሻለው፣ ከሰባት በመቶ ባነሰ መጠን ነው።
በኢህአዴግ ዘመንስ? ከ1983 ዓ.ም እስከ 2003 ዓ.ም ድረስ ያለውን የሃያ አመታት እድገት እንመልከት። የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦቱ በምን ያህል ጨመረ? አሁንም የአለም ባንክ መረጃን ነው የምጠቅሰው። በጊጋዋትአወር፣ 1210 የነበረው ወደ 5000 ገደማ ጨምሯል። በአራት እጥፍ ገደማ ማለት ነው። ነገር ግን፣ በንጉሡ ዘመን እስከ አብዮቱ ዋዜማ ድረስ በነበሩ ሃያ ዓመታት፣ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ከ18 እጥፍ በላይ ማደጉን መዘንጋት የለብንም። በደርግ ዘመን ከነበረው ጋር ሲነፃፀር ግን፣ በኢህአዴግ ዘመን የታየው እድገት በእጅጉ የተሻለ ነው። ሰዎች በኤሌክትሪክ የመጠቀም እድላቸውስ ምን ያህል ተሻሻለ? በኢህአዴግ ሃያ አመታት ውስጥ፣ ከአንድ እጥፍ በላይ ተሻሽሏል። በቤተሰብ ሲሰላ፣ በየቀኑ ወደ 15 ሰዓታት ያህል አንድ አምፖል ለማብራት የሚችል የኤሌክትሪክ ሃይል ተገኝቷል እንደማለት ነው።
እንግዲህ አስቡት። በ1947 ዓ.ም አንድ የኢትዮጵያ ቤተሰብ በአማካይ በየቀኑ ለ25 ደቂቃ ብቻ አንዲት አምፑል ማብራት ይችል ነበር። በ1966 ዓ.ም፣ በየቀኑ ለ5 ሰዓታት ያህል ማብራት ቻለ። በ1983 ዓ.ም ወደ 6 ሰዓት ያህል ፎቀቅ አለ። በ2003 ዓ.ም፣ ወደ 15 ሰዓት ገደማ አደገ። የትኛው ዘመን እድገት ይሻላል?
እንደ ኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ሁሉ፤ የመንገድ ግንባታ፣ የአውሮፕላን ትራንስፖርትና የስልክ መስመር አገልግሎትም እንዲሁ፤ ከአብዮቱ ዘመናት ይልቅ በንጉሡ ጊዜ የተሻለ እድገት ተመዝግቧል። ለምሳሌ በቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ፤ ከ1950 ዓ.ም እስከ 1966 ዓ.ም ድረስ ወደ ስድስት እጥፍ ገደማ በመስፋፋት፣ 45ሺ ገደማ የስልክ መስመሮች አገልግሎት ላይ ውለዋል።
በደርግ ዘመንስ? በሁለት እጥፍ ገደማ ነው ያደገው – ወደ 135ሺ ገደማ የስልክ መስመሮች። እንደ ንጉሡ ዘመን ከስድስት እጥፍ በላይ እድገት የታየው በኢህአዴግ ዘመን ነው። የስልክ መስመሮች ቁጥር በሃያ አመታት ውስጥ 900ሺ ደርሰዋል።
ይህም ብቻ አይደለም። እስከ አብዮቱ ዋዜማ ድረስ፣ የኤክስፖርት ገበያ አራት እጥፍ ገደማ አድጓል – ከ70 ሚሊዮን ዶላር ወደ 270 ሚሊዮን ዶላር። በደርግ ዘመን፣ በእነዚያ ሁሉ አመታት፣ የኤክስፖርት ገበያ በአንድ እጥፍ እንኳ ማደግ አልቻለም። ከ470 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ አላለፈም። በኢህአዴግ ዘመንም በመጀመሪያዎቹ አስር አመታት፣ ከኤስፖርት ገበያ የተገኘው ገቢ እዚያው ገደማ ተገድቦ ቆይቷል። ከዚያ በኋላ ነው ከቀድሞው የተሻለ ፈጣን እድገት መታየት የጀመረው። በጥቅሉ፣ በሃያ የኢህአዴግ አመታት ውስጥ እስከ 2003 ዓ.ም ድረስ የኤክስፖርት ገቢ፣ ከአራት እጥፍ በላይ በማደግ፣ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሆኗል – በንጉሡ ዘመን ከተመዘገበው እድገት ጋር ተቀራራቢ ነው።
የእህል ምርትና እጦት
የእህል ምርትን ደግሞ እንመልከት። ከአብዮቱ በፊት በነበሩ 20 ዓመታት፣ ለአንድ ሰው በአማካይ በየአመቱ 175 ኪሎ ገደማ እህል ይመረት ነበር። በአብዮቱ ዘመናት በደርግ ጊዜስ? ለአንድ ሰው በአማካይ 135 ኪሎ ገደማ እህል ነው በየዓመቱ ሲመረት የነበረው። በሌላ አነጋገር፤ የሕዝብ ብዛትን ከግምት አስገብተን ስናሰላው የእህል ምርት፣ በንጉሡ ዘመን የ30 በመቶ ብልጫ ነበረው።
በኢህአዴግ ዘመንስ? በመጀመሪያዎቹ የኢህአዴግ አስር አመታት፣ የአገሪቱ የእህል ምርት፣ ከደርግ ዘመንም የባሰ ነበር – በየአመቱ በአማካይ ለአንድ ሰው 125 ኪሎ እህል ነበር የሚመረተው። ቀጥለው ባሉት አስር አመታትስ? ምርቱ በአማካይ ወደ 165 ኪሎ ግራም ገደማ ደርሷል። በእርግጥ ያለፉትን ስምንት አመታት ብቻ ካየን፣ የአገሪቱ የእህል ምርት እየተሻሻለ፣ በአማካይ 175 ኪሎ ገደማ እንደደረሰ እናያለን። በአጠቃላይ ሲታይ፤ ከአብዮቱ ዋዜማ ጀምሮ ወደ ታች ሲያሽቆለቁል የነበረው አብዮታዊ የውድቀት ጉዞ ቀስ በቀስ የተገታው፤ የሶሻሊዝም አብዮት ከተገታ በኋላ ነው። ቀስ በቀስም እያገገመ፣ የአገሪቱ ኢኮኖሚ በንጉሱ ዘመን ወደ ነበረበት ደረጃ ለማደግ ችሏል። በሌላ አነጋገር፤ ኢትዮጵና ኢትዮጵያዊያን በአብዮቱ ሳቢያ ለድህነትና ለረሃብ ከመዳረጋቸው በተጨማሪ፤ ለ30 አመታት ያህል የኋሊት ተጉዘዋል። አዲሳድማስ ጋዘጣ ነጻ አስተያየት
ብሄር ብሄረሰብ፤ የዘር ፓለቲካ… ደስታው አንዳርጌ (ዶ/ር)
እውቀት ይስፋ፣ ድንቁርና ይጥfa
ይህ ነው የኢትዮጵያ ተስፋ።
ተስፋ ገብረሥላሴ
ፊደል የቆጠርሁት በአገራችን የህትመት ፋናወጊ (እና አርበኛ) የሆኑት ተስፋ ገብረሥላሴ ያሳትሟት በነበረው የባለ ፲ ሣንቲም ፊደል ነበር። ከፊደሏ ሽፋን ላይ ታዲያ ‘ተስፋገብረሥላሴ ዘብሄረ ቡልጋ’ ይላል። መጠየቅ እወድ ነበርና መርጌታን ‘የንታ ብሄረ ቡልጋ ምን ማለት ነው?’ ብየ ጠየኳቸው። የንታም ልጄ ብሄር ማለት በግእዝ አገር ማለት ነው። ቡልጋ ደሞ ሽዋ ክፍላገር ውስጥ የሚገኝ አውራጃ ነው። የተስፋ ገብረሥላሴ አገር እዚያ ነው፤ አሉኝ።
ከዚያ አስኮላ ትምርት ገብቸ ፬ኛ ክፍል ህብረተሰብ መጽሀፍ ውስጥ የኢትዮጵያ ‘ብሄረሰቦችን’ የሚያሳይ ስዕል ተደርድሮ አየሁ። በተለይ ሲዳማን የዎከሉት ቆንጃጅት ሙገጫ ሲዎግጡ የሚያሳየው ስእል አይረሳኝም። ይሁን እንጅ ብሄረሰብ የሚለው ቃል አልገባኝም ነበርና አስተማሪየን ጠየኳት። እሷ ግን ጎሳ፣ ነገድ ቅብጥርሴ ብላ የባሰ ግራ አጋባችኝ። ደግነቱ ማታ ማታ የንታ ዘንድ ወንጌል እማር ነበርና ወንበር ከመጀመሩ በፊት ቀደም ብዬ ሄጄ የንታን ‘ብሄረሰብ ምን ማለት ነው?’ ብዬ ጠየኳችው። የንታም ብሄር ማለት አገር ነው፣ ሰብ ደሞ ሰው ማለት ነው። እንግዲህ ብሄረሰብ ያው የሰው አገር መሆኑ ነዋ አሉኝ። የበለጠ ግራ ተጋባሁ። ህብረተሰብ መጽሀፌ ውስጥ ያዬሁት የሚያማምሩ ቆንጃጅትን ምስል እንጅ ወንዝ ወይ ጋራና ሸንተረር አልነበረማ።Ethiopia and Eritrea map
ሁሉ ሆነና ደርግም በኢሕአዴግ ተተካ። አሁን ግራ ያጋባኝ የነበረው ‘ብሄረሰብ’ የሚለው ቃል ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ ተብሎ ተራብቶ መጣ። የግዕዙን ቀጥተኛ ትርጉም ካየን እንግዲህ አገራት፣ የሰው አገራትና ህዝቦች እያልን መሆኑ ነው። ይሁንና ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ተብለው ይጠሩ የነበሩት የሁሉም ቋንቋ ተናጋሪዎች አሁን ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ ሆነው የተባዙት አንዳንዶቹ ብሄረሰቦች ወደ ብሄርነት ሌሎቹ ደግሞ ወደ ህዝብነት ተለውጠው ይሁን በሌላ ምክንያት በውል አይታዎቅም። በአንጻሩ አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ ብሎ ነገር የለም። በኢትዮጵያ ሕገ፡መንግስት ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚል ቃል አይገኝም። ፖለቲከኞችም ‘የኢትዮጵያ ህዝቦች’ እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ ሲሉ አትሰሙም። ይህ አጋጣሚ የሚመስለው ካለ እሱ የዋህ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ማለት (ልክ በኢህአዴግ የመጀመሪያዎቹ ሰባት የስልጣን አመታት ኢትዮጵያ አገሬ የሚል ዘፈን እንደማዳመጥ ያለ) በትምክህተኝነት ሊያስከስስ የሚችል የፖለቲካ ፋውል መሆኑን እያንዳንዱ ካድሬ ስለሚረዳ ነው።
የኢትዮጵያ ሕገ፡መንግስት በአገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ ስልጣኑም ሆነ ምድሩ አንዲሁም በላዩና በውስጡ ያለው ሀብት ሁሉ ‘የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ የጋራ ሀብት ነው ይላል። ይህ ደግሞ ከሌሎች ኣገሮች ሕገ፡መንግስታት ሁሉ ልዩ ያደርገዋል (ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሚለው ሀረግ እንደ ዋሊያ ኢትዮጵያ ብቻ ነው የሚታወቀው)። ይህ ይገርመኝ ነበርና ከአስር ኣመታት በፊት ከህገ፡መንግስት ጋር በተገናኘ የመመረቂያ ጽሁፍ ሳዘጋጅ ለመሆኑ አነዚህ የኣገሪቱን የፖለቲካ ስልጣንና ሀብት ኣንድም ሳያስቀሩ ጠቅልለው የያዙ ፍጡራን በትክክል አነማን ናቸው? ኣንዳቸው ከሌላቸው የሚለዩት በምን ነው? በአገሪቱ ውስጥስ ስንት ብሄሮች፣ ስንት ብሄረሰቦችና ስንት ህዝቦች አሉ? ለምሳሌ የቀበሌ መታወቂያ ስትወስድ ብሄርህን ተጠይቀህ ጉራጌ ብለህ ከሞላህ በኋላ ማታ በኢቲቪ የጉራጌ ብሄረሰብ ስላስመዘገበው ልማት ትሰማለህ። ታዲያ ብሄርና ብሄረሰብ አንድም ሁለትም ናቸው? ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎችን ይዠ መልስ ፍለጋ ሰነዶች ማገላበጥ ነበረብኝ። የህገ፡መንግስቱን ረቂቅ (ፕሪፓራቶሪ ዎርክስ) ሳይቀር አገላብጨ የሚረባ ነገር ላገኝ አልቻልሁም። ሕገ፡መንግስቱን በማርቀቅ የጎላ ድርሻ ነበራቸው የሚባሉትን ሰዎችም ጠይቄ ያገኘሁት ውጤት ኣልነበረም። በጣም ተገረምሁ። በአገራችን ላይ ከፈጣሪ ቀጥሎ ሁሉን ሀብትና ስልጣን ‘የተቆጣጠሩት’ ግኡዛን ማንነት እንዴት አይታዎቅም? ይህ እኮ እጅግ መሰረታዊ ጥያቄ ነው።
በተለይ ህዝቦች የሚለው ቃል ግራ አጋቢ ነው። በአለም ላይ አንድ ቋንቋ ተናጋሪ ወይም እንድ አይነት ማንነት ያላቸው ሰዎች ብቻ የሚኖሩባቸው አገራት ከአምስት አይበልጡም፤ ይህም ቢሆን በጣም የሚያከራክር ነው። ይሁን እንጅ የብራዚል ህዝቦች ወይንም የኬንያ ህዝቦች ቢባል እንግዳ ነው የሚሆነው። ምክንያቱም ህዝብ በትርጉሙ ያልተወሰነ ቁጥርና ማንነት ያላቸው ሰዎችን ያካተተ የጥቅል (የወል) ስም ስለሆነ ነው። ለዚህም ነው የአለም ህዝብ ቁጥር እንጅ የአለም ህዝቦች ቁጥር የማንለው። በርግጥ ፈረንጆቹም ከቅኝ በፊት ይኖሩ የነበሩ ቀደምት ጎሳዎችን (ትራይብስ) ለማመልከት ኢንዲጅነስ ህዝቦች ወይም አማዞን ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦች ይላሉ። ይህ ግን ቀደምት ጎሳዎችን (ነገዶችን)የሚተካ ተለዋጭ ቃል እንጂ ተደራቢ ስያሜ አይደለም። ስለሆነም ቀደምት ጎሳዎችና ኢንዲጅነስ ህዝቦች አይሉም። እንዲያውም ኢንዲጅነስ ህዝቦች የየአገራቸው (ሰፊ)ህዝብ አካል ናቸው። ለምሳሌ የካናዳ ህዝብ በአገሩ የሚኖሩ ኢንዲጅነስ ህዝቦችን ያጠቃልላል። በዚህ አግባብ ከመደበኛ ሰዋሰው ርባታ ተቃራኒ ቢመስልም በአንድ አገር ውስጥ ህዝብ የሚለው ቃል ህዝቦች ከሚለው ቃል ይሰፋል ማለት ነው። ከላይ በጠቀሁት ምሳሌ የካናዳ ህዝብ ካናዳዊያንን በሙሉ ሲያመለክት የካናዳ ኢንዲጅነስ ህዝቦች ግን የካናዳ ህዝብ አካል የሆኑ (ከአጠቃላዩ ህዝብ ፭ ፕርሰንት እንኳን የማይሞሉ) ግን ደግሞ የየራሳቸው የተለየ ማንነት ያላቸውን ነገዶችን ብቻ የሚያመለክት ነው። በሁሉም አገሮች የሚኖሩ የተለያዬ ቋንቋና ማንነት ያላቸው ሁሉ በአንድ ላይ የዚያ አገር ህዝብ ተብለው ነው የሚታዎቁት።
ወደ አገራችን ስንመጣ ግን ሁለት አደናጋሪ ነገሮችን እናገኛለን። የመጀመሪያው ህዝቦች የሚለው ቃል አግባብ በሌላው አለም እንደሚታወቀው ሁሉ ቀደምት ነዋሪወችን (ኢንዲጅነስ ትራይብስ) ለማመልከት ነው እንዳይባል ኢትዮጵያ ውስጥ ቀደምት ያልሆነው ማን እንደሆነና ማን ከማን እንደሚቀድም አይታወቅም። እንዲያውም ሁሉም ‘ብሄር ብሄረሰቦች’ ቀደምት ነዋሪወች ናቸው ማለት ይቻላል። ቢያንስ ይህ ላለመሆኑ ተቃራኒ ማስርጃ የለም (እንዲያውም እኮ እንደ ሳይንሱ ከሆነ የአለም ህዝብ ሁሉ የተገኘው ከኢትዮጵያ ነው)። ‘ህዝቦች’ የሚለው ቃል አንዳንዶች እንደሚሉት አናሳ ቁጥርና አገራዊ የፖለቲካ ተሳትፎ ያላቸውን የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ለማመልከት ነው እንዳንል እነሱው መልሰው ታዳጊ ብሄረሰቦች (አንዳንዴ አናሳ ብሄረሰቦች) ሲሏቸው እንሰማለን። ያ ከሆነ ደግሞ ብሄር ብሄረሰቦች በሚለው አገላለጽ ብንስማማ እንኳን ‘ህዝቦች’ የሚለው ቃል አላስፈላጊ ድግግሞሽ ከመሆንና ከማደናገር ኣልፎ የሚጨምረው ነገር የለም ማለት ነው። ሁለተኛውና በጣም የሚገርመው በአለም ላይ ባልተለመደ ሁኔታ በአገሪቱ የሚኖሩት ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ በአንድላይ የኢትዮጵያ ህዝብ አይሆኑም። ይህ የሆነው አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት ሕገ፡ መንግስታዊ ቃልኪዳን ገብተናል ያሉት ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ የሚጋሩት ማንነት ሳይኖራቸው ቀርቶ ይሁን በሌላ ምክንያት አይታወቅም። ለነገሩ የአንድ አገር ህዝብ አካል ለመሆን የዚያ አገር ዜጋ ከመሆን ሌላ ምን የተለየ የጋራ ማንነት ያስፈልጋል?
ግድየለም፤ ያ ሁሉ ፖለቲካ ነው ብለን እንለፈው። እኛስ ቢሆን ቃላትን (አንደኣብዛኛዉ ነገራችን) እንደልባችን የምንጠቀመው ለምን ይሆን? ኢትዮጵያ በዘር ተከፋፈለች፣ የዘር ፖለቲካ ያጠፋናል፣ የጦር ሰራዊቱ ከኣንድ ዘር በወጡ አዛዦች ቁጥጥር ስር ነው፣ አቶ እከሌ በተቋሙ ውስጥ የነገሰውን ዘረኝነት በመቃዎም ስልጣናቸውን ለቀቁ፣ ወዘተ…በየቀኑ የምንሰማው ሮሮ ነው። ለመሆኑ ዘር ምንድን ነው? ኢትዮጵያ ውስጥ ስንት ዘር አለ? ለምሳሌ አማራ አንድ ዘር ትግሬ ደግሞ ሌላ ዘር ናቸው? ከሆነስ ከየት ነው የመጡት? እንደሚታወቀው ያን ያህል ሩቅ ከማይባል ጊዜ በፊት ግእዝ እንጂ ትግርኛም አማርኛም ኣልነበሩም። ታዲያ ያኔ ትግሬ ነበር? ኣማራስ? ሌላው ቀርቶ ሴሜቲክ፣ ኩሽቲክ የሚባለውስ ምናልባት ቋንቋን ከመግለጽ (ይህም አከራካሪ ይመስለኛል) የዘለለ ያለው አንድምታ ምንድን ነው? ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ችሎታየም አላማየም አይደለም፤ ነገር ግን በጥንቃቄ መታየት የሚገባቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ይመስሉኛል። እንዲያውም ስለማንነታችን ሳይንሳዊ ብንሆን ብዙ ችግራችን የሚቃለል ይመስለኛል። ኢሕአዴግ ኢትዮጵያ ውስጥ ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ እንጅ እናንተ ቦታ የላችሁም፤ መሬቱ በሙሉ የእነሱ በመሆኑ እናንተ የመሬት ባለቤት መሆን አትችሉም ሲለን ቢያንስ እነዚያ ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ በትክክል እነማን እንደሆኑ እንዲነግረን እንጠይቃለን። በአንጻሩ ደግሞ እኛ የዘር ፖለቲካ ወዘተ…ስንል ምን ማለታችን እንደሆነ መረዳትና ማስረዳት ያለብን ይመስለኛል።
[email protected]
በዚሁ ላብቃ።
ሰላም
ባለፉት አራትና አምስት አመታት በግልጽ እንዳየነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እኩልነቱን፤ መብቱንና ነጻነቱን ለማስከበር የሚያደርገዉ ትግል ጫና በፈጠረበት ቁጥር ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ የራሱን ህገመንግስት የሚደፈጥጡ ህጎች አርቅቆ አያጸደቀ ሠላማዊ ዜጎችን አስሯል፤ ገድሏል ከአገር እንዲሰደዱም አድርጓል። ለምሳሌ በ2003 ዓም የኢትዮጵያ ፓርላማ ከቤተመንግሰት የተላለፈለትን ትዕዛዝ አክብሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ መብትና ነፃነት መከበር የሚታገለዉን የግንቦት 7 ንቅናቄ ሽብርተኛ አድርጎ ፈርጇል። ይህ ፈር የለቀቀ ፍረጃ ደግሞ ወያኔ የሱን ዘረኛ ስርዐት የሚቃወሙ ግለሰቦችን፤ ሀሳባቸዉን በነፃነት የሚገልጹ ዜጎችን፤ ጋዜጠኞችን፤ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና ከወያኔ ጋር አናብርም ያሉ ወጣት ኢትዮጵያዉያንን “ግንቦት ሰባቶች” ናችሁ እያለ በጅምላ እያሰረ እንዲያሰቃይ ህጋዊ ሽፋን ሰጥቶታል። ለምሳሌ ከፍትህና ከነጻነት ጥማት ዉጭ ከግንቦት 7 ንቅናቄ ጋር ምንም አይነት ግኑኝነት የሌለዉን የፖለቲካ ፓርቲ መሪዉን አንዱአለም አራጌን፤ ታዋቂዉን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና መምህርት ርኢዮት አለሙን የግንቦት 7 አባላት ናቸዉ የሚል ሰንካላና መሠረተ ቢስ ክስ መስርቶ ለረጂም ዘመን እስራት ዳርጓቸዋል።
ወያኔ እንደ ዛሬዉ ከተማ ዉስጥ ሆኖ ሥልጣን ሳይቆጣጠር ገና ጫካ ዉስጥ እያለ ጥርሱን ከነከሰባቸዉና ከተቻለ አጠፋቸዋለሁ ካለዚያም አሽመደምዳቸዋለሁ ብሎ አስራ ሰባት አመት ሙሉ ከተዘጋጀላቸዉ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ የአማራ ብሄረሰብ ነዉ። በለስ ቀንቶት ሥልጣን ከጨበጠ ማግስት ጀምሮም በወሎና በጎንደር በኩል ከትግራይ ጋር የሚያዋሰኑ ሰፊ የሆነ ለም መሬቱን ጠቅልሎ በመውሰድ ዘረኛ ሥርዓቱን ዕድሜ ሊያራዝሙልኛል ይችላሉ ብሎ የሚተማመንባቸውን የቀድሞ የትግል አጋሮቹንና ካድሬዎቹን አስፍሮበታል:: ይህ በደልና ግፍ አልበቃ ብሎትም ቀደምቶቹ የኢትዮጵያ ገዥዎች ለፈጸሙት ግፍና የአስተዳደር በደሎች ሁሉ አማራዉን በጅምላ ተጠያቂ የሚያደርግ ፕሮፖጋንዳ እነሆ እስከዛሬ በመርጨት ለዘመናት በሠላም ከኖረው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር በጠላትነት እንዲተያይ አድርጎታል:: በወያኔ አጋፋሪነት በበደኖ ፡በአርሲ በአረካና ሌሎች አካባቢዎች አማራው ላይ በግፍ የተፈጸመው ጭፍጨፋና ከ2004 እስከ 2005 ዓም አማራዉን ከጉራፈርዳና ከቤንሻንጉል ለማፈናቀል የተወሰደው እርምጃ የዚህ የወያኔ የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ውጤት መሆኑን የምስት የለም::
ሟቹ መለስ ዜናዊና በህይወት የሚገኙ ቀንደኛ የወያኔ መሪዎች የተጠናወታቸው የአማራ ጥላቻ በጸረ ፋሽስት ዘመቻ ወቅት ባንዳ ከነበሩ አባቶቻቸዉና አያቶቻቸዉ የተወረሰ ፋሽስት ጣሊያን ለደረሰባት ሽንፈት በዘርና በሃይማኖት ተከፋፍለን እርስ በርሳችን እንድንጠፋፋ ተክላብን የሄደቺው ተንኮል አካል ነው ::
የዚህ የጥፋት አጀንዳ አስፈጻሚ የሆነው ወያኔ የጀመረውን አገር የማፍረስና ህዝብ የመከፋፈል አጀንዳ ለማሳካት በየክልሉ የተኮለኮሉ ምስሌኔዎች እንወክለዋለን በሚሉት ህዝብና ክልል ላይ እየፈጸሙት ያለው በደልና ሰቆቃ አዲስ ምዕራፍ በያዘበት በአሁኑ ወቅት እራሳቸዏን ለባርነት አዋርደው ህዝባቸውን በማዋረድ ላይ የሚገኙት የብአዴኑ አለምነህ መኮንንን የመሳሰሉ ሆድ አደሮች ውርደት በቃን ዘረኝነት በቃን ብለው በተነሱ ዜጎች ላይ እየወሰዱ ያለው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ እጅግ አሳሳቢ ሆኖአል::
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና ሞክራሲ ንቅናቄ ከሰሞኑ በደረሰው መረጃ ወያኔ ከአማራው ቀምቶ በትግራይ ክልል ባስገባቸው ወረዳዎች ላይ የሚኖሩ ንጽሃን ዜጎች ለምን በወያኔ የግፍ አገዛዝ ትማረራላችሁ እየተባሉ በወያኔ ታማኝ ሚሊሻዎች
እስር እንግልትና ድብደባ እየተፈጸመባቸው መሆኑን አረጋግጦአል:: በዚህ በአዲስ መልክ በተጀመረዉ የወያኔ የጥቃት ዘመቻ መሳሪያ ያነገቡ የህወሃት ሚሊሻዎች ከክልላቸዉ ዉጭ ወደ ተለያዩ የአማራ ከተማዎችና ወረዳዎች ሰርገዉ እየገቡ የእነሱን ቋንቋ የማይናገረዉን ሁሉ የግንቦት 7 ተላላኪዎች ናችሁ በሚል እያሰሩ በመደብደብ ላይ ናቸዉ።
ይህ በመሆኑ ዛሬ አትዮጵያን ከሱዳንና ትግራይን ከጎንደር ጋር በሚያዋስኑ የአማራ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ገበሬዎች እጃቸዉ እርፍ ከሚጨብጥበት ግዜ በወያኔ ሰንሰለት የሚታሽበት ግዜ ይበልጣል፤ የመንግስት ሰራተኛዉና የከተማ ነዋሪዉም ቢሆን አብዛኛዉን ግዜ የሚያጠፋዉ ከወያኔ ካድሬዎች ጋር ግምገማ በመቀመጥ ሲሆን ተማሪዉና ወጣቱ ህብረተሰብ ደግሞ “መጡ አልመጡም” እያለ ሌሊቱን የሚያሳልፈዉ በየጫካዉ እየተሸሸገ ነዉ።
የዚህ አይነት አስከፊ ግፍና መከራ በአፋር ፡ በጋምቤላ በኦጋዴንና በኦሮሚያ በሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ ሲፈጸም ቆይቶአል:: ? ወያኔ እራሱ አርቅቆ ባጸደቀውና በሐምሌ ወር 1987 ዓም በስራ ላይ የዋለዉ የወያኔ ህገ መንግስት ኢትዮጵያ በዘጠኝ የፌዴራል ክልሎች መከፈሏንና እያንዳንዱ ክልል እራሱን በእራሱ የማስተዳደር መብቱ የተረጋገጠ እንደሆነ ይደነግጋል። በዚህ ህገ መንግስት መሠረት እያንዳንዱ ክልል የራሱ ቋንቋ፤ የአስተዳደር ማዕከልና እንዲሁም የክልሉን ሠላምና ጸጥታ የሚያስከብር የፖሊስ ኃይል ይኖረዋል ይላል። ታድያ ለምንድነዉ እያንዳንዱ ክልል የራሱ ፖሊስ ኃይል አያለዉ ከትግርኛ ቋንቋ ዉጭ ሌላ ቋንቋ የማይናገሩ የህወሃት ታማኝ ሚሊሻዎች አማራ ክልል ዉስጥ እየገቡ አማራዉን የሚያሰቃዩት?
መልሱ ቀላል ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ ህዝባዊ አምቢተኝነቱ እያየለ በመጣና የነጻነት ኃይሎች ጡንቻ በፈረጠመ ቁጥር ወያኔ አንገቷ ላይ ቀጭል እንደታሰረባት በቅሎ ይደነብራል። የደነበረ ደግሞ መራገጡ አይቀርምና መሳሪያ ያነገቡ ኃይሎችን እንቅስቃሴ እገታለሁ በሚል ከንቱ ጥረት ደንባራዉ ወያኔ የፈሪ በትሩን በድንበር አካባቢ በሚኖሩ የአማራ ክልል አርሶ አደሮች፤ ወጣቶችና ሠራተኞች ላይ ማሳረፍ ጀምሯል።
ወያኔ እንደ ግንቦት ሰባት የኮነነዉና የህዝብና የአገር ጠላት አድርጎ የሳለዉ ድርጅት የለም፤ የወያኔ የዜና ማሰራጫዎችም ይህንን የአገዛዙን አቋም በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ህዝብ አሰምተዋል።የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ማን ለመብቱና ለነጻነቱ እንደቆመና ማን መብቱና ነጻነቱ ላይ እንደቆመበት ለይቶ የሚያዉቅ ህዝብ ነዉ። ስለዚህም ግንቦት ሰባት ወያኔዎች አላፊዉንና አግዳሚዉን “ግንቦት ሰባት” ነህ እያሉ ከሚያሰቃዩ፤ ህዝብንና ግንቦት ሰባትን ያስተሳሰረዉ ነጻነት፤ ፍትህና ዲሞክራሲ ነዉና የኢትዮጵያን ህዝብ ጥያቄ ቢመልሱ ለእነሱም፤ ለእኛም ለአገርም ይበጃል የሚል የጸና እምነት አለዉ። ወያኔ በኢህአዴግ ስም ያሰጠጋቸዉን ምሰለኔዎች ጨምሮ ከራሱ ዉጭ ሌላ ማንንም አያምንም፤ ስለዚህም ነዉ የአገሪቱን የመከላከያ፤ የደህንነትና የፖሊስ ተቋሞች በራሱ ሰዎች ቁጥጥር ስር ያደረገዉ። ዛሬ በግልጽ እንደምንመለከተዉ ወያኔ በጉልበት ለያዘዉ ስልጣን ያሰገኛል ብሎ በሚጠረጥረዉ ቦታ ሁሉ የራሱን ልዩ ሚሊሺያ እየለላከ የኢትዮጵያን ህዝብ መኖሪያ ቤቱ ድረስ አየሄደ እያጠቃ ነዉ። ግንቦት ሰባት ወያኔና የፈጠረዉ ዘረኛ ስርዐቱ የቆሙት በፍጹም ማንሰራራት የማይችሉበትት የመጨረሻ መቀበሪያ ጉድጓዳቸዉ ጫፍ ላይ ነዉ የሚል ጽኑ እምነት አለዉ። ሆኖም ጉድጓድ ጫፍ ላይ የቆመ ጠላት በራሱ ተወርዉሮ ጉድጓዱ ዉስጥ አይገባምና ይህንን የተዳከመ ጠላት እተፈራገጠ ጉዳት ከማብዛቱ በፊት ለመደምሰስ ክንዳችንን አጠናክረን በህብረት እንደ አንድ ሰዉ እንነሳ ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
እየደጋገምን የምናጠፋው ጥፋት እኛን ራሳችንን ይዞ እንዳይጠፋ መጠንቀቅ ያባት ነው!
ያለ ለውጥ፣ ያለ ዋስትና መራመድ አይቻልም፡፡
በማንኛውም ረገድ ራስን መቻል እንደሚኖርብን ልብ እንበል፡፡ በምግብ ራሳችንን ችለን ረሀብተኛ ዲሞክራሲ ይዘን እንጓዝ ብንል የማያዋጣንን ያህል፤ በባዶ ሆድም ዲሞክራሲን አንግቦ መጓዝ ወንዝ አያሻግረንም፡፡ ጥቂት የናጠጡ ሀብታሞችና አያሌ የኔ-ብጤዎች ያሏት ሀገርም ሆነ ሰላሟን አጥታ ብዙ ሀብታሞችን ያፈራች ሀገር እንድትኖረን አይደለም ደፋ-ቀና የምንለው፡፡
እንደጥንቱ መፈክር “ጉዟችን ረጅም ትግላችን መራራ” ነው ማለትም አያዛልቀንም፡፡ ሁሌም ረጅም፣ ሁሌም መራራ መሆን የለበትምና! ያለ ለውጥ፣ ያለ ዋስትና መራመድ አይቻልም፡፡ የለውጥ አንቀሳቃሹ በአብዛኛው ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡ በዕውቀት የተገነባ፣ ለውጥ የገባው፣ ዛሬ ላይ የተደረሰው ብዙ ለውጥና መስዋዕትነት ታይቶ መሆኑን የተረዳ ወጣት እንጂ “ፋስት” በሚል ታርጋ የታሸገ የቢዝነስ ተሯሯጭ ለብ-ለብ ትውልድ ብቻ እንዳይሆን አገርና ነገር የገባው ወጣት መገንባት ያስፈልጋል፡፡ባለራዕይ-ለማኝ ዐባይ ሲገደብ የምሰጥህ ሁለት ብር አበድረኝ ይላል::
ያልፈጠርነውን፣ ያላስተማርነውን፣ በአግባቡ ያላነፅነውን ልጅ የሌለ ቅፅል ሰጥተን ብናሞካሸው ረብነት የለውም፡፡ በአናቱ ቅቤ ጣል ያለበት ሹሮ ዓይነት ካፒታሊዝም ኑሮአችን ቅቤ በቅቤ ነው እንደማያሰኝ ሁሉ፤ በእንዲህ ያለ ሥርዓት ውስጥ የሚያድግም ልጅ በአርቲፊሻል የተኳኳለ ከመሆን በቀር ኦርጅናሌ እንደማይሆን እናስተውል፡፡
ከመጠላለፍ ይሰውረን፡፡አደቡን ይስጠን፡፡ በተጠራጠርነው ሁሉ ፍርድ ከመስጠት ያድነን፡፡ እየደጋገምን የምናጠፋው ጥፋት እኛን ራሳችንን ይዞ እንዳይጠፋ መጠንቀቅ ያባት ነው! የምንገባው ቃል መፈፀሙን የሚያረጋግጥልን አንድም ታሪካችን፣ ሁለትም ለራስ መታመናችን ነው! በተግባር የምንሠራው በቃል የምናወራውን ካልመሰለ ዕቅዳችን፣ ስትራቴጂያችን ሁሉ፤ ውሃ የበላው ቤት እንደሚሆን አንርሳ! በታሪክ ያየነው ስህተት እንዳይደገም መጣጣር አዲስ ታሪክ መሥራት ነው!
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
የዓለም ዜና
ህዝባዊ ንቅናቄው የሚካሄድባቸው 17 ከተሞችም ተለይተው ታውቀዋል፤ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዛሬ ይፋ ያደረገው የህዝባዊ ንቅናቄ መርሃ ግብር በተከታታይ ሊካሂዳባቸው ካቀዳቸው ህዝባዊ ንቅናቄዎች መካከል አንዱ የሆነውን “የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባቤትነት”(Millions of voices for land ownership) የሚል ስያሜ የሰጠውን የህዝባዊ ንቅናቄ ነው፡፡ መረሃ ግብሩ በዛሬው እለት ይፋ የተደረገው ቀበና መድኃኔዓለም ቤ/ክ ፊት ለፊት በሚገኘው የፓርቲው ጽ/ቤት […]