Tag: Ethiopia
ቴሌፎኑ ‘ለግዜው’ ጥሪ አይቀበልም
ክንፉ አሰፋ
“የደወሉላቸው ደንበኛ ለግዜው ጥሪ አይቀበሉም። …” የምትለዋ አሰልቺ የቴሌ መልዕክት ያላጋጠመው ቢኖር ወደ ኢትዮጵያ ስልክ ደውሎ የማያውቅ ሰው ብቻ መሆን አለበት። ኮ/ል መንግሥቱ ኃይለማርያም ወደ ቀድሞ ወዳጆቻቸው መደዋወል ጀመሩና በመሃል ተስፋ ቆረጡ አሉ።
ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በእንተ ትንሣኤኹ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያየ አህጉር የምትኖሩ፣ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችኹ፣ በሕመም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችኹ፣ እንዲኹም የሕግ ታራሚዎች ኾናችኁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ፤ እርሱ ሕያው ኾኖ ሕያዋን መኾናችንን በትንሣኤው ላበሠረን ለጌታችን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ እንኳን በሰላም …![]()
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ኤፕረል 20, 2014
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
ዩክሬይን፤ የመፍቀሬ ሩሲያ የሠዓት ዕላፊ ገደብ
በምሥራቅ ዩክሬይን መፍቀሬ ሩሲያውያን ኃይላት በስሎቭያንስክ የሠዓት ዕላፊ ገደብ አወጁ። በአዋጁ መሰረት ማንኛውም ሰው የሠዓት ዕላፊው ገደብ ሳይጠናቀቅ ወደ ውጭ ወጥቶ መንቀሳቀስ አይፈቀድለትም።
በዩክሬይን መፍቀሬ ሩሲያ የሠዓት ዕላፊ ገደብ
በምሥራቅ ዩክሬይን መፍቀሬ ሩሲያውያን ኃይላት በስሎቭያንስክ የሠዓት ዕላፊ ገደብ አወጁ። በአዋጁ መሰረት ማንኛውም ሰው የሠዓት ዕላፊው ገደብ ሳይጠናቀቅ ወደ ውጭ ወጥቶ መንቀሳቀስ አይፈቀድለትም።
ማኅበረ ቅዱሳንን የማፍረስ አደገኛው ተልእኮ
በመኾኑም ታጋዮቹ የመንግሥትነት ሥልጣንን ሲቆናጠጡ ቤተ ክርስቲያንን የማጥቃት የቀደመ ሕልማቸውን አሐዱ አሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከዚህ ቀደም ይዛ የነበረውን መሬት መንጠቅ፣ በግፍ የተነጠቀቻቸውን ቤቶችና ሕንፃዎች አሟልቶ አለመመለስ፣ ቤተ ክርስቲያኗ በማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በተለይም የማስታረቅና ግጭቶችን በሰላም የመፍታት ተልእኮዋን በመንጠቅ አዲስ ለተመሠረቱት ፖሊቲካዊ ማኅበራት መስጠት፤ ከዚኽም ባሻገር ከትጥቅ ትግል አንሥቶ በስለላና በሌሎች ተግባራት ህወሓትን ሲያገለግሉ የነበሩ ‹‹ታጋይ …![]()
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ኤፕረል 19, 2014
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
አሳሳቢው የደቡብ ሱዳን ውጊያ
በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች በቦር፣ ጆንግሌይ የሚገኘውን የተመድ ሰፈር አጥቅተው ቢያንስ 50 ሰዎች ገደሉ። በዚሁ ቢያንስ 5000 ሰዎች ከለላ ባገኙበት ሰፈር በተጣለው ጥቃት ከቆሰሉት መካከልም ሁለት የተመድ ሰላም አስከባሪዎች ይገኙባቸዋል።
ፑቲን የዩክሬይን ውጥረትን ለማለዘብ ዝግጁ ነኝ አሉ
የሩስያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የዩክሬይን ቀውስን ተከትሎ ሀገራቸው ከምዕራባውያን ጋ የገጠማትን አለመግባባት ለማረቅ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጡ።
አክራሪነትና የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር – የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የአክራሪነት ትርጉም የተሳሳተ ነው! የፈራጁን ማንነትም መጠራጠር ይኖርብናል!
(አዲስ ጉዳይ፤ ቅጽ ፰ ቁጥር ፪፻፲፪፤ ሚያዝያ ፳፻፮ ዓ.ም.) ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እስከ አሁን በታተሙ ቅዱሳት መጻሕፍትም ኾነ ለጥምቀት በታተሙ ካኔቴራዎች ላይ በኤፌሶን ፬÷፬ ላይ ያለው ጥቅስ ከነመገኛው ተጠቅሶ ከመታተሙ በቀር አንድ ሀገር የሚል የለውም፡፡ ከእውነታ አንጻር ይህን ጥቅስ መጥቀስ በራሱ ስሕተት ነው፤ የሌለን ነገር እንዳለ አድርጎ ማቅረብ ነውና፡፡ ‹‹ጥቁር ድመትን በጨለማ ውስጥ መፈለግ አስቸጋሪ …![]()
የአቡነ ማትያስ ቃለ-ቡራኬ
የፋሲካ በዓል መከበር ያለበት ሌሎችንም በማሰብ መሆኑን ብዑዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አሳሰቡ፡፡
በክርስቶስ ሞት ቤዛነት እግዚአብሄር የሰውን ልጅ የታረቀበት ነው ብለዋል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ።
ለዝርዝሩ ፓትርያርኩ በዓሉን አስመልክቶ የሰጡትን ቡራኬና ያስተላለፉትን መልእክት የተከታተለን እስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡
ኬንያ ውስጥ የስደተኞች ጉዳይ ጋብ ቢልም አሳሳቢ መሆኑ ተገለፀ፡፡
ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ላይ የሚታየው ስደተኞችን እያፈሱ የማሰር እንቅስቃሴ ዛሬ ጋብ ያለ ቢመስልም ሶማሊያዊያን ስደተኞች ወደ ዳዳብ፣ ኢትዮጵያዊያን ወደ ካኩማ እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
ኪቱዪ ሻሪአ የሚባል ለስደተኞቹ ጥብቅና የሚቆም እና የሚሟገት ድርጅት ባልደረባና ጠበቃ የሆኑት አቶ ኡጁሉ ኦቻላ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
ኬንያ ውስጥ የስደተኞች ጉዳይ ጋብ ቢልም አሳሳቢ መሆኑ ተገለፀ፡፡ – ኤፕረል 18, 2014
kenya, refugees
የአቡነ ማትያስ ቃለ-ቡራኬ – ኤፕረል 18, 2014
Abba Mathias Easter Benediction – 04/18/14
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ኤፕረል 18, 2014
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ
የኢየሱስ ክርስቶስ ዕለተ ስቅለት መታሰቢያ በዛሬዉ ዕለት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመላዉ ዓለም ሲከበር ዉሏል።
የስቅለት በዓል አከባበር
የእየሱስ ክርስቶስ ስቅለት የሚታስበበት የስቅለት በዓል ዛሬ በመላው አለም በሚገኙ ክርስቲያኖች በሙሉ ተከብሮ ዋለ ። በዓሉ በተለይም በሺህዎች የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች በተገኙበት በእየሩሳሌም ክርስቶስ መስቀል ተሸክሞ እንደተጓዘበትና ስቃይና መከራ እንደተቀበለበት በሚታመንበት መንገድ መስቀል ተሸክሞ በመጓዝ ተከብሯል ።
የስቅለት በዓል በመላዉ ዓለም
የኢየሱስ ክርስቶስ ዕለተ ስቅለት መታሰቢያ በዛሬዉ ዕለት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመላዉ ዓለም ሲከበር ዉሏል።
የዩክሬን ቀዉስ የአሜሪካ ምላሽ
የሩሲያን ጨምሮ የዩክሬን የዩናይትድ ስቴትስና የአዉሮጳ ኅብረት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ጄኔቭ ላይ ትናንት ባካሄዱት ዉይይት አማካኝነት የደረሱበት መግባባት በቀዉስ በተወጠረችዉ ሀገር የተባባሰዉን ሁኔታ ለማርገብ ያስችላል እየተባለ ነዉ።
UTC 16:00 የዓለም ዜና 180414
የዕለቱ ዜና
የስቅለቱ እና የትንሣኤው አብነት
ከሆሳዕና እስከ ማዕዶት
በየዓመቱ የትንሣኤ በዓል ተከብሮ የሚውለው፣ በዕለተ እሑድ ነው። ጌታችንና መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳው በዕለተ እሑድ-መጋቢት 29 ቀን ነው። የግዕዝ ቋንቋ ሊቃውንት እንደሚተረጉሙት ከሆነ፣ “ትንሣኤ ማለት-መነሳት ማለት ነው።” ሞትን ድል አድርጎ፣ ከሙታን ተለይቶ መነሳት ማለት ነው። “ሕይወት ማግኘት፣ ነፍስ መዝራት፣ ሕልው መሆን” ማለት ነው።
የኢትዮጵያ ስዊድን ዲፕሎማሲ
የኢትዮጵያ መንግስት ላለፉት ጥቂት ዓመታት በስዊድን ስቶክሆልም የነበረዉን ኤምባሲ ወደቆንሳ ደረጃ ዝቅ አርጎ ቆይቷል።
አዲስ አድማስ – በሱሉልታ ከተማ የአማራ ተወላጆች ናችሁ የተባሉ ተደበደቡ(ናፍቆት ዮሴፍ)
ሶስት ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው በአዲስ አበባ የተለያዩ ሆስፒታሎች ገብተዋል “ረብሻውን ያነሱት ህዝብን የማይወክሉ ወሮበሎች ናቸው” የከተማው ኮሙዩኒኬሽን “ባህርዳር በተካሄደው የስፖርት ውድድር ላይ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ አድልዎ ተፈጽሟል” በማለት የተቧደኑ ወጣቶች፣ ባለፈው ሐሙስ የሱሉልታ ከተማ ነዋሪ የሆኑ በርካታ የአማራ ተወላጆች ላይ ድብደባ ፈፀሙ፡፡ በድብደባ በርካታ ሰዎች ከመጐዳታቸውም በተጨማሪ፤ ቤት ንብረት ላይም ጥፋት እንደደረሰ የተናገሩት ጉዳት […]
ሰማያዊ ፓርቲ የሚያዚያ 19ኙን ሰልፍ ለሌላ ቀን እንዲቀይር የአ.አ አስተዳደር ጠየቀ
የሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን ሰልፍ ለማድረግ ላሰገባዉ የማሳወቂያ ደብዳቤ ፣ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ምላሽ እንዳገኝ ሰማያዊ ፓርቲ ገለጸ። የአስተዳደሩ ደብዳቤ፣ ሰልፉን በታሰበው ሚያዚያ 19 ቀን፣ ማድረግ እንደማይቻልና ለሌላ ቀን እንዲያስተላልፈው የሚጠይቅ ሲሆን፣ የሰማያዊ ፓርቲ ግን፣ ለሰልፉ መራዘም የቀረቡት ምክንያቶች በቂ አይደሉም በሚል፣ ቀኑን እንደማይለወጥ፣ ባስገባው ሁለተኛ ደብዳቤ ለአስተዳደሩ አሳዉቋል። የሰማያዊ ፓርቲ በላከው ሁለተኛ ደብዳቤ፣ […]
የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ረዥም ጥቁር ጥላውን በ(መካከለኛው) አፍሪካ ጥሎአል
ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)
የ1994 የሩዋንዳ የጭፍጨፋ እና የእልቂት ጸጸት በ2014 የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ሰማይ ላይ እያንዣበበ ነው!
ባለፈው ሳምንት የሩዋንዳ ህዝብ እርስ በእርስ የተራረደበትን 20ኛውን ዓመት የሩዋንዳ የዘር ፍጅት መጥፎ ገጽታ ለማስታወስ የሀዘን ሳምንት አውጆ ድርጊቱን በመራር ሀዘን ዘክሮታል።
ኪርይያ ላይሶን (krie lyson)
ሰማያዊ ፓርቲ የሚታገለው ማንን ነው?
ግርማ ካሳ
ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ እንደጠራ አነበብኩ። ገረመኝ። መጋቢት 28 ቀን በአንድነት ፓርቲ ሰልፍ ይደረጋል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። የአዲስ አበባ አስተዳደር ሕጉን ባፈረሰ መልኩ በመጋቢት 28 ቀን ሰልፍ ማድረግ እንደማይቻል ገለጸ።
አባ ማትያስ ወደ ግብፅ ሊሄዱ ነው
ከአንድ ሣምንት በኋላ ወደግብፅ የሚያደርጉት ጉዞ በህዳሴ ግድብ ላይ ከተፈጠረው ልዩነት ጋር የተያያዘ ያለመሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትረያርክ አቡነ ማትያስ አስታወቁ።
ግድቡን አስመልክቶ በኢትዮጵያ ያለው አስተሳሰብ ግልፅ እና አብረን እንጠቀም መሆኑን የተናገሩት አባ ማትያስ ርዕሱ ከተነሳ ምላሽ እንደሚሰጡ ከአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል።
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የኬንያ ስደተኞች ጉዳይ ብዙዎችን እያሳሰበ ነው
ኬንያ ውስጥ ሰሞኑን በስደተኞችና ፍልሰተኛ ነዋሪዎች ላይ እየካሄደ ያለው ፍተሻ፣ የቤት ለቤት አሰሳና የጅምላ እሥራት የፈጠረው የውጥረት ድባብ የሰብዓዊ መብቶች ጥያቄዎችን እያስነሣ ነው፡፡
ቪኦኤ ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተለና ዘገባዎችንም እያወጣ ነው፡፡
ከኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች መካከል እያነጋገርን ነው፡፡
የኬንያ ፖሊስ ያለህጋዊ ፈቃድ ሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የውጭ ሀገር ስደተኞችን ዒላማ ባደረገው ዘመቻችው ከአንድ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችን መርምረናል፥ ሁለት መቶ ሃያ አምስት ሰዎችን ልናስወጣ ነው ሲል አስታውቋል።
ለሰብዓዊ መብቶች የሚሟገቱ ቡድኖች እና ኬንያ ውስጥ ያሉ ሶማሌዎች ፖሊሶች ያዋክቡናል፥ ጉቦ ይጠይቁናል ፥ በጎሣችን ምክንያት የዘመቻው ዒላማ እየተደረግን ነው ሲሉ አማርረዋል።
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ኤፕረል 17, 2014
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
የትንሣኤ በዓል በመላው ዓለም በተመሣሣይ ቀን
ዘንድሮ የትንሣኤ በዓል በመላው ዓለም በሚገኙ ክርስቲያኖች ዘንድ በተመሳሳይ ቀን ይከበራል። የአይሁዳውያን ፋሲካም በትንሣኤ ቀን ይውላል። የትንሣኤ በዓል ከሐይማኖታዊ ዳራው ባሻገር እንደየሀገሩና የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ የተለያዩ ባህላዊ እሴቶችም አሉት። በተለይ የዶሮ እንቁላል ሀገር ቤትም ሆነ እዚህ ጀርመን በትንሣኤ በዓል ልዩ ስፍራ ይሰጠዋል።
የዩክሬን ቀውስና የጄኔቩ ስብሰባ
ይህ የአራትዮሹ ንግግር ለዩክሬን ቀውስ ምን ዓይነት መፍትሄ እንደሚያስገኝ ከወዲሁ መገመት ቢያዳግትም ቢያንስ ዩክሬንና ሩስያን የዩክሬን ቀውስ ከተባባሰ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ላይ እንዲወያዩ በማድረጉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል ።
የሩዋንዳው እልቂትና አስተምህሮቱ
የጀርመን መንግሥት የሰብዓዊ ጉዳዮች ተጠሪ ክርስቶፍ ሽትሬሰር ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ በተለይ ግጭቶች እየተባባሱ በሚሄዱባቸው አካባቢዎች ህዝቡን በሰብዓዊ እርዳታ መደገፍ ከዚያም አልፎ ተፋላሚ ወገኖችን ቢቻል በሰላማዊ መንገድ አለያም በኋይል ማስቆም እንደሚገባ አሳስበዋል ።
የዩኔስኮ የቻይና አደራ ፈንድ
ቻይና 8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ያደረገችበት የዚሁ የዩኔስኮ የቻይና አደራ ፈንድ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ከሆኑት ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት ።
17.04.2014 ዜና 16:00 UTC
የዓለም ዜና
አቡጉዳ – በጋራ እንሰራለን ካሉ (ሰማያዊች) ጥሩ ነው – የአንድነት አመራር(ሰንደቅ)
የአንድነት ፓርቲ፣ ለሚያዚያ 26 ቀን በአዲስ አበባ ሰልፍ እንደጠራ፣ ከአዲስ አበባ አስተዳደሩ አስፈላጊዉን እውቅና እንዳገኘ መዘገቡ ይታወቃል። አንድነት ሰልፉን መጋቢት 28 ቀን ጠርቶ የነበረ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር በተባለው ቀን እውቅና ባለመስጠቱ፣ የተለያዩ ዝግጅቶ በመኖራቸውና የአመት በዓላትም ጊዜ በመሆኑ፣ ወደ ሚያዚይ 26 መሸጋገሩን የአመራር አባልቱ ይገልጻሉ። በዚህ ሂደት ከአስተዳደሩ ጋር በርካታ የደብዳቤ ልዉዉጦች የተደረጉ ሲሆን፣ […]
አቡጊዳ – “ውድድር ጤናማ ጉዳይ ነው። መወዳደር አለብን (አንድነት እና ሰማያዊ) – የሰማይዊ አመራር አባል (ሰንድቅ)
የአንድነት ፓርቲ፣ ለሚያዚያ 26 ቀን በአዲስ አበባ ሰልፍ እንደጠራ፣ ከአዲስ አበባ አስተዳደሩ አስፈላጊዉን እውቅና እንደገኘ መዘገቡ ይታወቃል። በተመሳሳይ ሁኔተ የሰማይዊ ፓርቲ ደግሞ ከአንድ ሳምንት በፊት ሚያዚያ 19 ቀን በጃን ሜዳ ሰልፍ መጥራቱን ገልጿል። አስፈላጊዉን የማሳወቂያ ደብዳቤ ለአስተዳደሩ እንዳሰገቡ ሰማያዊቾ ቢገልጹም፣ በተባለው ቀን ከአስተዳደሩ እውቅና ይሰጣቸው አይሰጣቸው እስከ አሁን የተወቀ ነገር የለም። ሰልፉን በጋራ መጥራት ለምን […]
በጥቂት ገንዘብ ኤሌክትሪክ ለአፍሪቃ
በአፍሪቃ እስካሁን 3000 ቤቶች ሌት ብርኃን እንዲያገኙ አስችሏል። ኤሌክትሪክ ፈፅሞ ባልነበረበት ቦታ የኤሌክትሪክ ኃይል ይዘን እንመጣለን ይላል። ሞቢሶል የተሰኘው ከፀሀይ ብርሃን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ መሣሪያ የሚፈበርከው ድርጅት።
ሚሊዮኖች ድምጽ – የእሪታ ቀን ሰልፍ በሚያዚያ 26 ቀን እንደሚደረግ አስተዳደሩ እውቅና ሰጠ !
«ህግን አክብረን ለድርድር የማናቀርበውን ህገመንግስታዊ መብታችንን አሳልፈን አንሰጥም። ታላቁ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ‹‹የእሪታ ቀን ›› በሚል መሪ ቃል ሚያዚያ 26፣2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ይደረጋል፡፡» ሲሉ የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው ገለጹ። ፓርቲዉ ከአዲስ አበባ አስተዳደር አስፈላጊዉን እውቅና ያገኘ ሲሆን ፣ ከትንሳኤ በዓል በኋላ በሃያ ሶስቱም የአዲስ አበባ ወረዳዎችና በአዲስ አበባ […]
የኬንያ ስደተኞች ጉዳይ ብዙዎችን እያሳሰበ ነው – ኤፕረል 17, 2014
Kenya, refugees, 04/17/14
አባ ማትያስ ወደ ግብፅ ሊሄዱ ነው – ኤፕረል 17, 2014
Ethiopian Patriarch is heading to Egypt, 04/17/14
ቤኒሻንጉል ውስጥ ታጣቂዎች አደጋ ጣሉ
ማክሰኞ፤ ሚያዝያ 7/2006 ዓ.ም ጠዋት ላይ ያልታወቁ ታጣቂዎች፣ በቤኒሻንጉል-ጉምዝ ክልል 28 ሰዎች አሣፍሮ ይጓዝ በነበረ ከፍተኛ ተሽከርካሪ ላይ ተኩስ ከፍተው 9 ተሣፋሪዎችን ሲገድሉ በሰባቱ ላይ ደግሞ ከቀላል እስከ ከባድ የማቁሰል አደጋ አድርሰዋል።
ፖሊስ የጥቃቱን ምክንያት እያጠና መሆኑን ገልጿል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡
ኦፌኮ በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ላይ ድምፁን አሰማ
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ – ኦፌኮ ባለፈው ዕሁድ አዲስ አበባ ላይ በጠራው ህዝባዊ ስብስባ ኦሮሚያ ውስጥ የሚገኙ ከተሞችን ከአዲስ አበባ አስተዳደር ጋር ለማስተሳሰር በወጣው ማስተር ፕላን ላይ ተቃውሞውን ገልጿል፡፡
ኦፌኮ ይህንን ያሳወቀው ያካሄደውን ምክክር ተከትሎ ባወጣው የአቋም መግለጫ የከተሞቹን ነዋሪዎች የሚጎዳ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ በመድረሱ መሆኑ ታውቋል፡፡
“የኦሮሞ ገበሬዎች እየተነቀሉ ቦታቸው በሊዝ የሚሰጠው ለመሬት ቅርምት እንጂ ለልማት አይደለም” በማለት ኦፌኮ ተቃውሞውን አሰምቷል።
ዋና ፀሐፊው አቶ በቀለ ነጋ ለቪኦኤ የሰጡትን መግለጫ የያዘውን የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
ቤንቲዩ ወደቀች
የደቡብ ሱዳን ፀረ-መንግሥት ኃይሎች የዩኒቲ ግዛት ዋና ከተማይቱን ቤንቲዩን መቆጣጠራቸውን የመንግሥቱ ኃይል የሆነው የሱዳን ሕዝብ አርነት ሠራዊት – ኤስፒኤልኤ ዛሬ አረጋግጧል፡፡
መንግሥቱ አክሎም ተቃዋሚዎቹ ምናልባት ድጋፍ ከኻርቱም አግኝተው ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁም መልዕክት ቢያስተላልፉም አማፂያኑ ግን ይህንን የጁባን ውንጀላ ፈጥነው ሙሉ በሙሉ አስተባብለዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ቤንቲዩ ላይ ሁለቱም ወገኖች ገና እየተፋለሙ መሆናቸውን የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር ተናግረዋል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያደምጡ፡፡
የእናቶች ጤናና የሕፃናት ሞት እና የልማት ግቦቹ
ኢትዮጵያ ከአምስት ዓመት ዕድሜ በታች ያሉ ህፃናትን ሞት ቁጥር በሁለት ሦስተኛ መቀነስ ብትችልም በሚሌኒየሙ የልማት ግቦች የሠፈረው ግብ ላይ እንዳልደረሰች ተገለፀ።
የእናቶችን ሞት ለመቀነስ አሁንም ብዙ እንደሚቀር ተገልጧል።
የአውሮፓ ኅብረት እነዚህን ግቦች ለመምታት ያግዝ ዘንድ አርባ ሚሊዮን ዶላር ለግሷል።
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካችው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ ልኮልናል።
(2007-2008 ዓ.ም)
የሚሌኒየሙ የልማት ግቦች
ሥር የሰደደ ድኅነትና ረሃብን ማጥፋት፤
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትን ለሁሉም ማዳረስ፤
የፆታዎች እኩል መሆንን ማስተማር እና የሴቶችን ውሣኔ ሰጭነት ማስፋት፤
የሕፃናት ሞትን መቀነስ፤
የእናቶች ጤናን ማሻሻል፤
ኤችአይቪ/ኤድስን፣ ወባንና ሌሎችም በሽታዎችን…