አንድነት ፓርቲ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለሆኑት Jhon Kerry በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ጉዳይ ደብዳቤ ፃፈ፡፡

የአንድነት ፓርቲ የፊታችን ሚያዚያ 26 ቀን በአዲስ አበባ ሰልፍ እንደሚያደርግ ማሳወቁ ይታወቃል። መጋቢት 28፣ ሚያዚያ 5፣ ሚያዚያ 19 ሰልፍ ለማድረግ ጠይቆ ፣ አስተዳደሩ በተለያዩ ምክንያቶች እውቅና ለመስጠት ፍቃደኛ ባለመሆኑ ነበር አንድነት የሰልፉን ቀን ለሚያዚያ 26 ያስተላለፈው።

ጽዮን ግርማ – አዲስ አበባ

ዘወትር እንደምታደርገው ሁሉ በምታዝበት ሬዲዮ ጣቢያ ጓደኞቿን ሰብስባ ወደ ስቱዲዮ የገባችው ሚሚ ስብሃቱ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ስለታሠሩት ሁለት ጋዜጠኞችና ሰባት ጦማሪዎች ከፖሊስ አገኘኹት ያለችውን መረጃ ጠቅሳ ስታወራ ነበር። ኢትዮጵያን ለማተራመስ ከሚሠራው አርቲክል ዐሥራ ዘጠኝ ከሚባል ድርጅት ጋር ሲሠሩ ነበር፣ትልልቅ ሆቴል እየተገናኙ ይወያዩ ነበር፣ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎችን ያደራጁ ነበር፣ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅትና ከአምነስቲ እንዲሁም ከግብጽና ከኤርትራ ገንዘብ ይቀበሉ ነበር፤ የሚሉ ውርጅብኞችን በማውረድ እነርሱን የኢትዮጵያ ጠላት እራሷን ደግሞ የኢትዮጵያ ወዳጅ አድርጋ በመሳል ውንጀላዋን ስታዥጎደጉደው ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጽዮን ግርማ (አዲስ አበባ)

Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 21 ቀን 2006 ዓ.ም. April 28, 2014)፦ ባለፈው ሳምንት ወደ ማእከላዊ እስር ቤት የተጣሉት ስድስት  የ’ዞን ዘጠኝ’ አባላትና ሶስት ጋዜጠኞች ሁኔታ አነጋጋሪ ሆኖ መሰንበቱ ይታወቃል። በአሁኑ ሰአት እስረኞቹ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ሲሆን ክስም እንደተመሰረተባቸው ለማወቅ ተችሏል። ሁኔታውን ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ በፌስ ቡክ ገጿ እንደሚከተለው ዘግባዋለች።

የማዕከላዊ ወንጅል ምርመራ ፖሊስ በትናንትናው (እሁድ) ዕለት ጠዋት አራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት አቅርቦ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል፡፡ በሦስት መዝገብ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ዘጠኝ ጸሐፊዎች አገሪቷን በሶሻል ሚዲያ ለማተራመስ ራሱን የመብት ተሟጋች ነኝ ብሎ ከሚጠራ የውጭ ኃይል ጋር በሐሳብም በገንዘብም ተረዳድተውና ተስማተው በአገሪቷ ላይ የብጥብጥ ቅስቀሳ ለማነሳሳት አቅደው ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸው በቁጥጥር ውለዋል ይህንንም በሚመለከት መረጃ እስክናሰባስብ ጊዜ ይሰጠን በሚል የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተመስገን ደሳለኝ – አዲስ አበባ

…ከ97ቱ በእጅጉ የተቀዛቀዘው የ2002ቱ ምርጫ የቀናት ዕድሜ ብቻ ቀርተውታል፤ ከመቼውም በላይ የፖለቲካ ምህዳሩን ያጠበበው ገዢው ግንባር፣ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር የሚያደርገውን የምረጡኝ ክርክር እንደ 97ቱ በቀጥታ ስርጭት እንዲተላለፍም ሆነ በአዳራሹ ታዳሚዎችና ታዛቢዎች እንዲገኙ አልፈቀደም፤ በዚህ ክርክር ላይ ኢህአዴግ እንደተለመደው ለመጀመሪያ ጊዜ ካቀረባቸው ጥቂት አፈ-ቀላጤዎቹ መካከል የተመልካችን ትኩረት በመሳብ ጎልማሳው የወራቤ ፍሬ ሬድዋን ሁሴንን የሚተካከል አልነበረም፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

የኢህአዴግ ፖለቲካ ዜጎችን የማሰር፣ ዜጎችን የማሸበር ፖለቲክ ነው። በቅርቡ በዞን ዘጠኞችና ጋዜጠኖች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ የሚያሳየው፣ አገዛዙ ሃሳብን በሃሳብ መመከት ሲሳነው የሃይል እርምጃ ለመዉሰድ ወደ ኋላ የማይል መሆኑን ነው። ኢሕአዴግ ሽብርተኝነትን ለመከላከል ሳይሆን፣ ሰላማዊ ዜጎችን ለማሸበር ሲል ያወጣዉ የጸረ-ሽብርተኝነት ሕግ እንዲሰረዝ በመጠየቅ፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ ማድረጉ ይታወሳል። በአገሪቷ ክፍሎች ያሉ ሚሊዮኖች፣ አገዛዙ ዜጎችን በማሸበር […]

“ሕገወጥ ቅስቀሣ ሲያደርጉ ይዣቸዋለሁ” ያላቸውን 22 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በአንድ አንድ ሺህ ብር ዋስትና እንዲፈቱ ወስኗል፡፡

ይሁን እንጂ “ይህ ተደጋጋሚ ውሣኔ ሊለወጥ ይገባል” በማለት ፖሊስ እስከአሁን እንዳልለቀቃቸው ተነገረ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በርካታ አባላቱና መሪዎቹ በፖሊስ ቢያዙም ፓርቲው ዕሁድ፤ ሚያዝያ 19/2006 ዓ.ም “የተሣካ ሰልፍ አድርጌአለሁ” ብሏል፡፡

ለዝርዝሩ የያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ሦስት ጋዜጠኞችን ጨምሮ “አሸባሪ ውዥብር ነዝተዋል” በሚል ጥርጣሬ ፖሊስ ሰሞኑን በቁጥጥር ሥር ያዋላቸውን ዘጠኝ የኢንተርኔት አምደኞች (ብሎገሮች) ፍርድ ቤት አቅርቧል።

ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መፈቀዱም ተገልጿል።

በሌላ በኩል ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች፣ እንዲሁም ለጋዜጠኞች ደኅንነት ተቆርቋሪ ድርጅቶች ታሣሪዎቹ እንዲፈቱ የጠየቁባቸውን መግለጫዎች አውጥተዋል።

ታሣሪዎቹ ቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶቻቸውም ሆኑ የሕግ አማካሪዎቻቸው እስካሁን እንዳላዩዋቸውም ተገልጿል።

በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ጣቢያ አርብና ቅዳሜ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ያሉት የዞን-9 ዌብሳትይ አምደኞች ለመሆኑ እነማን ናቸው? ሦስቱ ጋዜጠኞችስ?

ለዝርዝሩ የያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በቃሊቲ እሥር ቤት የሚገኙት አቶ በቀለ ገርባና አቶ ኦልባና ሌሊሳ “የሕክምና እርዳታ እንዳያገኙ ተደርገዋል” ሲል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አሳስቧል፡፡

በተለይ የአቶ ኦልባና ሌሊሣ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን የድርጅቱ የኢትዮጵያና የኤርትራ መርማሪ ክሌር ቤስተን ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል፡፡

ድርጅቱ ባለፈው ዓርብ ባወጣው የአፋጣኝ እርምጃ ጥሪው መልዕክቱን የሚያዩ ሁሉ ለኢትዮጵያ መንግሥት ተመሣሣይ ጥሪ እንዲያስተላልፉ አሳስቧል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞችን በአዲስ አበባ ማስተር ችላንውስጥ አካትቶ ለማልማት በሚል የተያዘውን ዕቅድ የኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች በተለያዩ ከተሞች ተቃውሞዎቻቸውን እያሰሙ ነው፡፡

በጂማ፣ በነቀምት፣ በሃሮማያ፣ በአምቦና በሌሎችም ከተሞች ያሉ የኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች የአዲስ አበባ ዙሪያ ከተሞችን በማስተር ፕላኑ ውስጥ መካተት እየተቃወሙ ያሉት በሰላማዊ ሰልፎች ነው፡፡

በጂማና በነቀምቴ የፀጥታ ኃይሎች የኃይል እርምጃ መውሰዳቸው የተሰማ ሲሆን በሌሎቹ ከተሞች ግን ከማስፈራራት ወይም ከሥጋት የዘለቀ እንቅስቃሴ እንዳልነበረ ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

የኦሮሚያን የአስተዳደርና የፀጥታ ዘርፍ፣ እንዲሁም የክልሉን የፖሊስ ኮሚሽን አግኝተን ለማነጋገር ጥረት እያደረግን ነው፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የወባ ወረርሽኝ በዓለም ዙሪያ በእጅጉ ቢቀንስም አሁንም ቢሆን በየዓመቱ ሁለት መቶ ሚሊየን ሰው እንደሚያዝ የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡

ዛሬም ቢሆን በዓመት ከስድስት መቶ ሺህ በላይ ሰው እንደሚሞትም ድርጅቱ የዘንድሮን የወባ ቀን አስታክኮ ባወጣው ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

በሌላ በኩል ግን ኢትዮጵያ ላለፉት አምስትና ስድስት ተከታታይ ዓመታት የወባ ወረርሽን ተከስቶባት እንደማያውቅ የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሃገርአቀፍ የወባ መከላከያ መርኃግብር አስተባባሪ ወ/ት ሕይወት ሰሎሞን ለቪኦኤ በሰጡት ማብራሪያ ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ በወባ የመያዝ አጋጣሚ በ67 ከመቶ መቀነሱን፣ የሞት መጠኑ በ48 ከመቶ መውረዱንና ዕድሜአቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት የወጣ ሞት መጠን…

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በአራት ዪኒቨርሲቲዎች የሚገኙ የኦሮሞ ተማሪዎች የአዲስ አበባ አዲሱን ማስተር ፓልን በመቃወም ተቃዉሞውውቸዉን አሰሙ። በዉጭ አገር የሚገኘውና በቅርቡ የተቋቋመው የኦሮሞ ሜዲያ ንቴዎርክ ማስተር ፓልኑን በመቃወም ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረገ የነበረና የሚገኝ ሲሆን፣ በዶር መራራ ጉዳናን የሚመራዉ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን ጨመሮ በርካታ የኦሮሞ ድርጅቶች በርካታ የኦሮሞ ድርጅቶች ፕላኑን አዉግዘዋል። የኦሮሞ ተማሪዎች ም በአምቦ፣ በወለጋ፣ በጂማና በሃረማያ ሰላማዊ በሆነመንገድ […]

ዩኤስ አሜሪካ እና የአውሮጳ ህብረት ሩስያ በዩክሬይን ቀውስ ላይ እያካሄደችው ነው ባሉት ሕገ ወጥ ጣልቃ ገብነት ሰበብ ካሁን ቀደም የጣሉትን ማዕቀብ አጠናከሩ።

ዩኤስ አሜሪካ እና የአውሮጳ ህብረት ሩስያ በዩክሬይን ቀውስ ላይ እያካሄደችው ነው ባሉት ሕገ ወጥ ጣልቃ ገብነት ሰበብ ካሁን ቀደም የጣሉትን ማዕቀብ አጠናከሩ።

በትናንትናዉ ዕለት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሁለት ርዕሳነ ሊቃነ ጳጳሳትን የቅድስና ሥርዓት አካሂዳለች። በቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱሳን የተባሉት ዮሐንስ 23ኛ እና ዮሐንስ ጳዉሎስ ዳግማዊ የተባሉት በርዕሳነ ሊቃነ ጳጳሳትነት ያገለገሉ አባቶች ናቸዉ።

የደቡብ ሱዳን ግጭት እስካሁን በሺህዎች የሚቆጠሩ የሀገሪቱ ነዋሪዎችንለሞት ዳርጓል። ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎችም ቀዬያቸውን ጥለው እንዲሰደዱ አስገድዷል። ከወራት በፊት በሁለቱ የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ኃይላት መካከል አዲስ አበባ ውስጥ የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተፋላሚዎችን ደም ከመፋሰስ አልታደገም።

ዩናይትድ ስቴትስ በሲና በረሃ አካባቢ ለገጠማት የሽብር ስጋት እንዲዉሉ በሚል አስር አፓቼ ሄሊኮፕተሮችን ለግብፅ ልትሰጥ መሆኗን ሰሞኑን አስታዉቃለች። ይህንኑ ድጋፍ ተከትሎ የግብፅ መንግስት ወታደራዊ አቅሙን እያጠናከረ የሚገኘዉ

ማዕከላዊን በከፊል አውቀዋለሁ፡፡ ትናንት ሰባት የሚሆኑ ጋዜጠኞች፣ ብሎገሮችና አክቲቪስቶች መታሰራቸውን ተከትሎ ወደ ማእከላዊ መወሰዳቸውን ሰምተናል፡፡ በቀጣዮቹ ቀናት ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ ጨለምተኛ ልመስል እችል ይሆናል፤ እውነታው ግን ይኸው ነው፡፡ መጀመሪያ ክሱ ምን ሊሆን ይችላል የሚለው አጓጊ ጥያቄ ነው፡፡ ይህን ለማወቅ ወሳኝ ፍንጭ የሚሰጠው የቤት ፍተሻው ነው፡፡ የታሰሩትን ሰዎች ቤት የሚፈትሹት ፖሊሶችና መርማሪዎች ቤቱን […]

ሰማያዊ በመባል የሚታወቀውና የወጣቶች ፓርቲ እንደሆነ አዘወትሮ የሚናገረው ሰማያዊ ፓርቲ ባለፈው ሳምንት በወጣ ልሳኑ ‹‹ነገረ ኢትዮጵያ›› ላይ ታዋቂውን ኢትዮጵያዊ ምሁርና በተቃውሞ ጎራ እድሜ ሳይገድባቸው ትግል እያደረጉ ያሉትን ምሁር ዶ/ር ኃይሉ አርአያን አሰደበ፡፡ የፓርቲው ልሳን ዶ/ር ሃይሉን ለመሳደብ የተገደደው የሚል ጠንካራ አቋም ስላላቸው ሲሆን ሳሙኤል አወቀ በተባለ ጎረምሳ ፀኃፊ በኩል ተብለው መገለፃቸው ብዙዎችን ያሳዘነ ሲሆን ከኢትዮጵያዊ […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም የመንግስታቸውን የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ለፓርቲያቸው የፓርላማ አባላት ባቀረቡበት ወቅት(ሁለት ወንበር ከማጣታቸው ውጪ) ‹‹ዴሞክራሲያዊነት ለመንግስታቸው የህልውና ጉዳይ ››እንደሆነ አውስተው ነበር፡፡ልማታዊ በመሆናችን ዴሞክራሲን እንደ ትርፍ ነገር የምንቆጥር የሚመስላቸው ተሳስተዋል ለማለት አስረግጠው ሲናገሩ አድምጬ ነበር፡፡ ኢህአዴግ በየጊዜው የፖለቲካ አክሮባት እየሰራ ንፋሱ እንደወሰደው ከአንዱ ርዕዩተ ዓለም ወደ አንዱ እንደፌንጣ እየዘለለ ‹ልማታዊ ወ ዴሞክራሲያዊ ነኝ› እያለን ነው፡፡ድርጅቱ […]

በማዕከላዊ የሚገኙ የዞን ዘጠኝ አባላትን ከተፈቀደልን ለመጠየቅ ካልሆነም የታሰሩበትንና ፍርድ ቤት የሚቀርቡበትን ቀን ለማወቅ ወደ ስፍራው ዛሬ ማለዳ አምርተን ነበር፡፡የጦማርያኑ ቤተሰቦች ያመጡትን ምግብ ከማቀበል ውጪ ማንንም ሊያናግሩ እንደማይችሉ ተነግሯቸው በሐዘን እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡ መቼ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ለሚለው ጥያቄም ኃላፊነት ወስዶ የሚናገር አካል በመጥፋቱ ማወቅ አልተቻለም፡፡ለምን ታሰሩ ለሚለው ጥያቄ ግን መልስ ከተባለ‹‹ ተረጋጉ መስማታችሁ መቼ ይቀራል››ተብሏል፡፡ […]

ከአዲስነገር ጋዜጣ አባላቶች መሰደድ እንዲሁም ከውብሸት እስክንድር እና ርእዮት አለሙ መታሰር በሁዋላ ለእኔ መንግስት በሚዲያ ሰዎች ላድ በጅምላ የወሰደው ትልቅ ክስረት ነው። ፅሀዮ መንግስታችንም የኢትዮጵያውያን በነፃነት የመኖር ህልም ማጨናገፉን ስራዮ ብሎ ተያዞታል ምን ያህል እንዳዘንኩኝ አላውቅም ብዙ ሰው ስለሀገሬ አያገባኝም ባሉበት ሰአት ስለሚያገባን እንጦምራለን( እንፅፋለን) በማለት ለሀገራቸው ያላቸውን ቀና ነገር በበሳል ብእራቸው ሲፅፉ ነው የማውቀው። […]

ከአርብ ሚያዚያ 17 ቀን ጀምሮ ኢሕአዴግ ዞን ዘጠኝ ተብለው በሶማል ሜዲያ ምህበረሰቡ የሚታወቁ ወጣት ጦማሪያንን ( ብሎገርስ) እንዲሆም ሌሎች ጋዜጠኞችን አይሰረ ሲሆን፣ እስረኞቹ ትልናት እሁድ ሚያዚያ 19 ቀን ፍርድ ቤት እንደቀረቡ ታወቀ። የታሰሩ የዞን9 አባላትና ጋዜጠኞች ትላንትና እሁድ ሚያዝያ 19 አራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት ቤተሰብ ሳይወቅ እና የሕጝ ባለሞያ በሌለበት ሁኔታ ሲሆን፣ […]

ትላንት ሚያዝያ 17 2006 አመሻሽ ላይ ዞን 9 በተሰኘ ድረ ገጽ (ብሎግ) ላይ በሳል ፖለቲካዊና ማህበራዊ ትችቶችን በማቅረብ ከሚታወቁት ፀኀፍት መሀከል 6ቱ ማለትም ማህሌት ፋንታሁን፣ በፍቃዱ ሀይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ዘላለም ክብረት፣ አጥናፍ ብርሀን፣ አቤል ዋበላ እንዲሁም ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ፣ ጋዜጠኛ አስማመው ኃ/ጊዎርጊስ እና ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል፡፡ ግለሰቦቹ በተለያየ […]

በመድረክ እና በአንድነት መካከል ስላለው ግንኙነት ሁለት ኢትዮጵያዊያን የጻፉትን አነበብኩ። ዶር መሳይ ከበደ፣ መድረክ ዉስጥ ባሉ የዘዉግ ደርጅቶች እና በአንድነት ፓርቲ መካከል ያሉት የፖለቲካ ፕሮግራም ልዩነቶች የማይታረቁ መሆናቸውን በመገልጽ፣ አንድነት ጊዜዉን እና ጉልበቱን እነዚህ የዘዉግ ድርጅቶችን በማባበል ላይ ከማጥፋት፣ ከሌሎች አገር አቀፍ ድርጅቶች ጋር አብሮ እንዲሰራና እንዲዋሃድ ይመክራሉ። አቶ ዳዊት ተሾመ በበኩላቸው፣ ለዶር መሳይ መልስ […]

መፍቀሬ-ሩስያ ታጣቂዎች ይዘው ያቆዩዋቸውን የተወሰኑ የ«ኦኢሲዲ» ታዛቢ ቡድን አባላት ለመገናኛ ብዙኃን እይታ አቀረቡ። ከተያዙት ታዛቢዎች መካከል አንድ ስዊድናዊ የስኳር ህመም ስላለበት መለቀቁን ታጣቂዎቹ አስታውቀዋል።

የታሰሩ የዞን9 አባላትና ጋዜጠኞች ትላንትና እሁድ ሚያዝያ 19 አራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው እነደነበር ታወቀ

አርብ አመሻሹን እና ቅዳሜ ጠዋት የታሰሩት የዞን9 አባላትና ጋዜጠኞች ትላንትና (እሁድ ጠዋት) ፍርድ ቤት መቅረባቸው ታወቀ፡፡ ቤተሰብም ሆነ የህግ ባለሞያ ባላወቀበት ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ክስ ላይ 

“ውጨ ሃገር ከሚገኙ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ነን ከሚሉ ጋር በገንዘብና በሃሳብ በመተባበር በማህበረሰብ ሚዲያ ሃገርን ማሸበር” ወንጀል መጠርጠራቸው የተገለጸ ሲሆን 

1. ማህሌት ፋንታሁን አቤል ዋበላ እና በፍቃዱ ሃይሉ ለሚያዚያ 30
2. ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ጋዜጠኛ አስማማው ሃይለግዮርጊስ ዘላለም ክብረት ለሚያዝያ 29
3. አጥናፍ ብርሃኔ ኤዶም ካሳየ ናትናኤል ፈለቀ ሚያዝያ 30 ተቀጥረዋል፡፡

The journalists and bloggers are charged of “Working with foreign human right activist organizations agreeing with idea, finance and inciting violence through social media to create instability in the country” with three different files.

Hence;
1. Mahlet Fantahun
2. Abel Wabela
3. Befeqadu Hailu are appointed for May 8 2014 

1. Tesfalem Weldyes 
2. Asmamaw W/Giorigis
3. Zelalem Kebret are appointed for May 7 2014

1. Atenaf Berahene
2. Edom Kassaye
3. Natnael Feleke are appointed for May 8 2014

#FreeZone9bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem#FreeAsemamaw #Ethiopia

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ አመት የምህንድስና ተማሪ የሆነው ዮናስ ከድር ሰማያዊ ፓርቲ ለጠራው ሰልፍ ሲቀሰቅስ ተይዞ ጉለሌ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ ይገኛል፡፡ እስር ቤት ውስጥ ያለ ተማሪ በፖሊስ ታጅቦ ፈተናውን የመፈተን መብት ቢኖረውም ዮናስን ግን ‹‹አንተ የፖለቲካ እስረኛ ነህ፣ አንተን አጅበን ማስፈተን አንችልም፣ አንተን የሚያጅብ ፖሊስ የለንም!›› የሚሉ የተለያዩ ምክንያችን በመደርደር ለፈተና እንዳይቀርብ ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች (እደግመዋለው) የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ህገመንግስቱን ተመርኩዘው የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄዎችን በመያዝ ወኪሎቻቸውን በመምረጥ ህጋዊ ውክልን በመስጠት ወደ ገዢው መንግስታዊ ቡድን ህግን አንብበው ለይተው አውቀው መብታቸውን እና ግዴታቸውን ተረድተው አቤቱታቸውን ለማሰማት በሄዱበት የወይኔው ስርአት እንኳን ደህና መጣችሁ በሚል የህሰት ወንበዴያዊ ፈገግታ በአስመሳይ ሰላም እና ፍቅር አቅርቦ እውቅና የሰጠ በማስመሰል ደም በተለወሱ ጥርሶቹ ነክሶ ለመያዝ እና ለአገዛዙ […]

መብራት ውሃ የስልክና የኢንተርኔት ኔትወርክ አገልግሎቶች መብቶች የህዝብ ናቸው!!!!! -ምንሊክ ሳልሳዊ አቤቱታችን ከፖለቲካ ነጻነት እና ዲሞክራሲያዊነት ጎን ለጎን የመሰረታዊ አገልግሎቶች ጥያቄ ነው …ይህ ደሞ ለየት ባለ መልኩ አብዮታዊ ነው:: እኛ በሰው አገር የምንኖር ዲያስፖራዎች በወገናችን ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ ከማውራት እና መኖሪያ ፍቃዳችን ሲታደስ ከመቀዝቀዝ ዉጪ በወያኔ ላይ የምናሳድረው ጫና እምብዛም ጉልፍ ስፍራ የለውም:: እርስ በርሳቸው […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች