ፀሀዮ መንግስታችንም የኢትዮጵያውያን በነፃነት የመኖር ህልም ማጨናገፉን ስራዮ ብሎ ተያዞታል – ሰሚር አሊ

ከአዲስነገር ጋዜጣ አባላቶች መሰደድ እንዲሁም ከውብሸት እስክንድር እና ርእዮት አለሙ መታሰር በሁዋላ ለእኔ መንግስት በሚዲያ ሰዎች ላድ በጅምላ የወሰደው ትልቅ ክስረት ነው። ፅሀዮ መንግስታችንም የኢትዮጵያውያን በነፃነት የመኖር ህልም ማጨናገፉን ስራዮ ብሎ ተያዞታል ምን ያህል እንዳዘንኩኝ አላውቅም ብዙ ሰው ስለሀገሬ አያገባኝም ባሉበት ሰአት ስለሚያገባን እንጦምራለን( እንፅፋለን) በማለት ለሀገራቸው ያላቸውን ቀና ነገር በበሳል ብእራቸው ሲፅፉ ነው የማውቀው። 1zone9

የ ዞን፱ አክቲቪስቶች እንደ አብዛኛው የ ሳይበር ፓለቲከኛ ሆይ ሆይታ ነገር የማይስባቸው እና በሳል እና core የሆኑ ህሳቦች በሚያነሱት ሀሳቦች፣ በምክንያት ላይ የተመሰረተ መንግስትን የሚሞግቱበት አውድ ከፍተው የማይታሰብ የሚመስለውን አሳይተውናል።

ለኔ ሁሌም የሚገርመኝ የቡድኑ ስብስብ ብዙ ሰው እንደሚያስበው ተመሳሳይ እምነት እና አቁዋም ያላቸው አድርጎ አለመሆኑ ነው።ለዞን፰ ዋንኛው መሰባሰቢያቸው እና አንድነታቸው ስለሀገራችን ያገባል ነው። በተረፈ ከአጥባቂ ህይማኖተኛ እስክ ኢ-አማኝ ኤቲስት ድረስ ስብስብ እና በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይም የተለያዮ የፖለቲካ አተያይ ያላቸው የወጣት ምሁራን ስብስብ ነው።

በነገራችን ላይ የዞን ፱ የሚለው ስያሜ የመጣው ጋዜጠኛ ርእዮት አለሙን ቃሊቲ እስር ቤት ሊጠይቁ በሄዱበት ሰአት ርእዮት አለሙ ዞን 9 ደህና ነው ? ብላ ስትጠይቃቸው ነበር።
ቃሊቲ እስር ቤት ያለው እስከ ዞን 8 ድረስ ነው ከየት አመጣሽው ? አይ ዞን 9 ማለት ከእስር ቤት ውጪ ያለው የኢትዮጵያ ትልቁ እስር ቤትን ነው ብላ መለሰችላቸው።

ከተወሰኑ ወራቶች ጀምሮ የዞን ፱ እንቅስቃሴ እየተዳከመ እና ጭርሱኑ ቆምዋል በሚባልበት ደረጃ ባለበት ሰአት ብዙ የብሎጉ ተከታታዮች እነሱ ያሉባቸውን ችግሮች ካለመረዳት በመነጨ ሲወቅሱዋቸው ነበር። እነሱም አላሳፈሩንም እንደ ገና እንቅስቃሴያቸውን ጀምረው ነበር ነገር ግን መፃፍ መጀመራቸውን ተከትሎ ለመታሰር ብቅተዋል በኔ በኩል አሁን ችግራቸው ግልፅ የሆነልን ይመስለኛል።

የኢህአዲግ እንቅልፍ የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነው እንዳሉት ዶ/ር መረራ መንግስት ስጋ እንዳየ አሞራ እያንዣንበባቸው እንደነበረ ፍንጭ የሚሆነው ከዞን፱ አባላት አንዱ አቤል ዋበላ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ባልታወቁ ሰዎች ተባለና ተደብድቦ ላፕቶፑን የተቀማ ጊዜ ነው ይሄ የነገሩ መጀመሪያ መሆኑን አይተን ትንሽም ሳንቆይ። ኢትዮጵያውያንን ሆይ ስለሀገራችሁ የሚያገባኝ እና የምንወስንላችሁ እኔ እንጂ ማንም አይደለም እኔ ባልኩዋችሁ እና በሰፈርንላችሁ ነፃነት ልክ ብቻ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር የምትችሉት በሚል ምክንያት ድርሰት እና ድራማ መስራት በማይደክመው መንግስታችን ተይዘው ታስረዋል።

ለኔ ዞን 9 የአዲሱ ትውልድ ጀግኖች ናቸው በፌስቡክ ላይ እና በብሎጋቸው መንግስትን የሚሞግቱ ምሁራዊ አስገራሚ ፅሁፎችን ፅፈውም አስገርመውናል። እንደ ሳይበሩ አለም ጀግኖች ማንነታቸውን ሳይደብቁ ወይም ውጪ ሀገር ሳይሆኑ ለሀገራችን ይጠቅማል የሚሉትን ሀሳብ እራሳቸውን ከጨካኙ ስርአት ጋር አጋፍጠው ለሀገራችን ይበጃል የሚሉትን ነገር ሲሰነዝሩ ነው የከረሙት። እናም መንግስት ድንጋይ ቢደረድር ህንፃ እና መንግስት ቢሰራ ሀገሩ ሰው ሰው ካልሸተተ ምን ሊረባን ነው።

ፈራን ፈራን ዙበርክ የሰጠንን መብት መጠቀም ፈራን
የምናስበውን እና የምናምነውን ላይ ኮሜንት ማድረግ ፈራን
ለሀገራችን በጎ መመኘት እና መጠየቅ ፈራን
ኢትዮጵያ የኛ ሳትሆን የጥቂቶች መሆንዋን ማየት ፈራን አስፈራን

በመጨረሻም ስለ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ የረዥም ግዜ የስራ አጋሩ የነበረው ዳኝነት መኮንን ያለውን እዚህ ጋር ብዮ ላጠቃልል
Tesfalem Waldyes ሁሌም ስለ ጋዜጠኝነት አለባዉያን፣ መሠረታውያን፣ ቀመር፣ እና ሥነ ምግባር አብዝቶ የሚጨነቅ ምናልባትም ብቸኛው ጓደኛችን ነው። ጋዜጠኝነት ማለት accuracy, balance, clarity, and neutrality ከኾነ የማውቀው አንድ ጋዜጠኛ ተሥፋዓለም ወልደየስ ነው። የዜና ዘለላ መቁጠር፣ የፊቸር አለላ ማሰባጠር ማን እንዳንተ ተስፍሽ! ዜናና ታሪክ ሲሠራ ቀዳሚ እና ፊተኛው፤ እስረኞችን ቃሊቲ ሄዶ በመጠየቅ ታታሪው ወንድሜ ጠያቂ እና ስንቅ አሳሪ ያብዛልህ። የእስር ቤት ማስታወሻህን ወይም ደብዳቤህን በናፍቆት እጠብቃለሁ።

አበበ ቶላ እንዳለው “በጠቅሉ ኢህአዴግዬ ጠቅላላ ኢትዮጵያን ቆልፎ ”ዴሞክራሲያዊ ፌደራሊያዊ ቃሊቲ እና ቂሊጦ” የምትባል ሃገር ሳይመሰርትልን አትቀርም! ” አበቃሁ