ሕዝብ፤ ሙስና እየነዳ ላመጣው ግፍ ለዋጋ ንረት፣ ለኑሮ ውድነት፣ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ተዳርጓል፡፡
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) :- የመንግስት ሹመኞችና ባለሟሎቹ የሙስናን በሽታውን ወደ ሕዝብ ነዝተውታል፡፡ ነጋዴው ማህበረሰብ እንደወትሮው ወጭ ገቢውን የሚያሰላው ከቀጥተኛ ወጭው ጋር ያተያያዘውን ግዢና ግብር ብቻ አይደለም፡፡ የቀን ጅብ ለሆኑ ሙሰኞች የሚሰጠውን ኮሚሽንና ውጣ ወረዱን ጭምር ነው። ………… ሕዝቡ የኑሮ ውድነት ከበደኝ! የእቃ ዋጋ ንረት አስመረረኝ! ግፍ በዛብኝ! ሸምቶ መቃመስ አቃኝ የሚል ምሬት ሲያሰማ.. ሹመኞች አፍ ለማስያዝንና ለማሸማቀቅ ይሽቀዳደማሉ፡፡ “በገበያ ስርዓት ነው የምንመራው የሚችል ይገዛል፡፡ ያልቻለ አይገዛም” ይባላል፡፡ ገፋ ሲልም “አጭበርባሪ ነጋዴ ስናሳድድ አንገኝም!” የሚል ማበረታቻ አከል መልስ ለሕዝቡ ይሰጣል፡፡
የተረጋጋ የነበረውን የግብይይት ስርዓት ያለበቂ መነሻና ጥናት የዋጋ ጣራ በማወጅ፣ ውቅያኖሱን ደብድቦ አሳውን የሚረብሽ ፖሊሲ ይዘረጋል፡፡ አለመረጋጋቱን ታኮ ነጋዴው እጥረትን፣ የጥራት ችግርን፣ ቅሸባን፣ ሚዛን ማጓደልን አይነተኛ የስራውና የትርፉ መሰረት ያደርገዋል፡፡ ሕዝብ፤ ሙስና እየነዳ ላመጣው ግፍ ለዋጋ ንረት፣ ለኑሮ ውድነት፣ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ተዳርጓል፡፡
http://minilik-salsawi.blogspot.com/201 … -post.html