በነሶሊያና ሺመልስ የክሥ መዝገብ ብይን ሲጠብቁ የነበሩት አራቱ የኢንተርኔት አምደኞች ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ክሣቸው ተቋርጦ በነፃ የተሰናበቱትም በኤግዚቢትነት ተይዘው የነበሩ ንብረቶቻቸው እንደተመለሱላቸው ተናግረዋል፡፡

በኮምፕዩተሮቻቸው ውስጥ የነበሩ ልዩ ልዩ ሠነዶች ግን በመጥፋታቸው ማዘናቸውን ገልፀዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ድንበር አቋርጣችኋል የተባሉ ኢትዮጵያዊያን ማላዊ ውስጥ በእሥር ላይ ይገኛሉ። እነዚህ 232 ኢትዮጵያዊያን የሚገኙበት ሁኔታም እጅግ አስከፊና ጤንነትንም የሚጎዳ መሆኑን እዚያው ኗሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል። ከእነዚህም አንዷ ዋና ከተማይቱ ሊሎንግዌ ውስጥ ከሃያ ዓመታት በላይ የኖሩት ወ/ሮ …

ማላዊ ውስጥ 232 ኢትዮጵያዊያን ታስረዋል Read more »

በሚሌ ወረዳ የሀርሲስ ቀበሌ ነዋሪዎች በድርቅ መጎዳታቸውን የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ግርማይ ጋብሩ በአፋር ክልል ታዘዋውሮ ዘግቧል። Listen

በአገሪቱ የዝናም እጥረት ከተከሰተ ጀምሮ በተለይ በቆላማ አካባቢዎች የእንሰስሳት መኖ አቅርቦት ሥራ እየተካሄደ መሆኑን የግብርና ሚንስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች የዝናብ ስርጭቱ በእጅጉ ዘግይቶ በመጀመሩ፤ በከብት እርባታ የሚተዳደሩ የአፋርና ኢሳ አካባቢዎች መጎዳታቸውን የማህበረሰቦቹ ተወካዮች ገለጹ። በድርቁ የተነሳ በአንዳንድ አካባቢዎች የሰዎች ህይወት መጥፋቱንና በርካታ እንስሳት መሞታቸውን፤ የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ከአፋርና ኢሳ ማህበረሰቦች መሪዎች ካገኘው መረጃ ለመረዳት ተችሏል። የፌዴራልና …

የክረምት ዝናብ ዘግይቶ መጀመሩ አሳሳቢ ሆኗል፤ በአፋርና ኢሳ አካባቢዎች ለ5 ወራት የዝናብ እጥረት ተከስቷል Read more »

ዓለምአቀፍ ጉዞ ላይ ሳሉ ከየመን ዋና ከተማ ሰንዓ አይሮፕላን ጣቢያ ተጠልፈው ወደ ኢትዮጵያ የተወሰዱትና አሁን እሥር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲለቀቁ ለማድረግ እየጣረ መሆኑን ሪፕሪቭ የሚባለው ድርጅት ዳይሬክተር አስታውቀዋል፡፡ የሞት ፍርደኞችን ለማገዝና ለመደገፍ የሚሠራው …

አንዳርጋቸውን ለማስለቀቅ ሪፕሪቭ የሚባለው ድርጅት እየጣረ ነው – VOA Read more »

በቦረና ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በኖኖ-አሎ ቀበሌ በሚኖሩ ዜጎች ላይ ባካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናትና ጥቂት ተባባሪዎቻቸው ብሄር-ተኮር ጥቃት ደርሶባቸዋል ሲል ሰ መ ጉ የተሰኘው የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ገለጸ። ጥቃቱ ብሄር-ተኮር ይሁን እንጂ የብሄር ግጭት አይደለም ሲሉ የ ሰመጉ ጽሕፈት ቤት …

በቦረና ክልል በኖኖ-አሎ ቀበሌ በሚኖሩ ዜጎች ላይ ጥቃት ተፈጸመ ሲሉ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድን ሀላፊ ተናገሩ Read more »

ሳዑዲ አረቢያ ሁለት ኢትዮጵያዊያንን ሰሞኑን በሞት ቀጥታለች፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ ታስረው የነበሩት ጂዛን በሚገኘው እሥር ቤት ውስጥ እንደነበረ ታውቋል፡፡ አረጋዊ ኃይለማርያም እና ሃዲሽ ዘላለም በሚባሉት ኢትዮጵያዊያን ላይ የሞት ቅጣቱ የተፈፀመባቸው አንገት በመቅላት መሆኑ ታውቋል፡፡ እዚያው ጂዛን እሥር ቤት ውስጥ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እሥረኞች …

ሳዑዲ አረቢያ ሁለት ኢትዮጵያዊያንን አንገት በመቅላት ገደለች – ነሐሴ 10, 2015 Read more »

ኢሕአዴግ በአባሎቹ፤ በየጋፊዎቹና የፓርቲው ደጋፊ ናቸው ተብለው በሚታሰቡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ የበቀል እርምጃ እያደረሰ መሆኑን በመግለፅ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መድረክ ክሥ አሰማ፡፡

በሽብር ወንጀል ተከሰዉ ትላንት ቅጣት የተጣለባቸዉ የሙስልም ማህበረሰብ ችግሮች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ጠበቃ፣ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሰጡት ቃለምልልስ የፍርድ ቤቱ ዉሳኔ ግራ አጋብቶናል ይላሉ። Listen

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት በነ አቡበከር አሕመድ የክስ መዝገብ የጥፋተኛነት ውሳኔ በሰጠባቸው 18 ተከሳሾች ላይ ከሰባት እስከ 22 አመታት የሚደረስ የጽኑ እስራት ቅጣት ፈረደባቸው። Listen

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ስለ ኢትዮጵያ ምርጫ የሰጡት አስተያየት “በጎውን ንግግራቸውን ሁሉ የሻረ ነው” ሲሉ የመድረክ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ተናገሩ። LISTEN

በኢትዮጵያ እስር ቤት የሚገኙት የግንቦት ሰባት ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ በተሻለ ሁኔታ መያዛቸዉን የአገሪቱ ዉጭ ግዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገለጹ። ሚኒስትሩ ትላንት ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዩ የአማርኛዉ ቋንቋ ስርጭት ስለ ፕሬዚደንት ኦባማ ኢትዮጵያ ጉብኚት በሰጡት ቃለ ምልልስ ስለ አቶ …

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አዲስ መጽሃፍ እንደጻፉና የልማት ቦታዎችን እንደሚጎበኙ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ተናገሩ – (VOA – ሐምሌ 29, 2015) Read more »

ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በአፍሪቃ ሕብረት ባደረጉት ንግግርና ከጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር ባደረጉት ጋዜጣዊ ላይ በተነሱት ነጥቦች ከኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎች የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል። Listen

ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ከትላንት በስቲያ ከኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር ባደረጉት አዲስ አበባ ዉስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ ጉባኤ ለጋዜጠኛ ጥያቄ በሰጡት መልስ የዚያችን አገር መንግስት በዴሞክራሲያዊ መንገድ እንደተመረጠ አድርጎ መግለጻቸዉ ከብዙ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች ትችት አስከትሏል። Freedom House የተባለዉ …

የኦባማ ንግግር የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ትችት ገጠመው – VOA Read more »