ሳዑዲ አረቢያ ሁለት ኢትዮጵያዊያንን አንገት በመቅላት ገደለች – ነሐሴ 10, 2015


ሳዑዲ አረቢያ ሁለት ኢትዮጵያዊያንን ሰሞኑን በሞት ቀጥታለች፡፡

ኢትዮጵያዊያኑ ታስረው የነበሩት ጂዛን በሚገኘው እሥር ቤት ውስጥ እንደነበረ ታውቋል፡፡

አረጋዊ ኃይለማርያም እና ሃዲሽ ዘላለም በሚባሉት ኢትዮጵያዊያን ላይ የሞት ቅጣቱ የተፈፀመባቸው አንገት በመቅላት መሆኑ ታውቋል፡፡

እዚያው ጂዛን እሥር ቤት ውስጥ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እሥረኞች መካከል አንዱ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል የተገደሉትን ሰዎች እንደሚያውቋቸውና ለአራት ዓመታት አብረው ታስረው መቆየታቸውን ገልፀው ሐምሌ 29/2007 ዓ.ም ከመካከላቸው ወስደው ቆራርጠውና አንገታቸውን ቀልተው እንደገደሏቸው ተናግረዋል፡፡ Listen