ክቡራትና ክቡራን ጤና ይስጥልኝ በዛሬው ስብሰባ ከአቶ መለስ ሕልፈት በተያያዙ ጉዳዮች ላይ በማተኮር አንዳንዳ ሃሳቦችን ለማንሳት እፈልጋለሁ፡፡ የአቶ መለስ ህልፈተ ህይወት ይፋ ሆኖ አስከሬኑ ቦሌ ደረሰ ሲባል የአዲስ አበባ ሕዝብ በድንጋጤና በሓዘን፤ የክረምቱ ዶፍ እየወረደበት አሰከሬኑን ቤተ መንግስቱ ድረስ አድርሶታል፡፡ አስከሬኑ ከገባ ከአስራ ሁለት ቀን በኋላ ስርዓተ ቀብሩ ተፈጽሟል፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዝብም እርሙን አውጥቷል፡፡ በአቶ […]

ውድ እስክንድር፦ በቅድሚያ እንኳን ለዘመነ ማቴዎስ አደረሰኽ። በመቀጠልም ስለኑሮኽ ልጠይቅኽ፦ (ኑሮ ካሉት ቃሊቲም… ነውና) እንዴት አለኽ? ውድ ባለቤትኽስ? ልጅኽስ? እኔ አምላከ-ኢትዮጵያ ይመስገን ከመላ ቤተሰቤ ጋራ ደኅና ነኝ። ከዚህ የሚቀጥለውን እንዳንድ ታናሽ ወንድም ማስታወሻ ውሰድልኝ። ስላንተ ላንተ ማውሳት ከንቱ ድካም ይኾናል። ስለዚህ አልሞክረውም። ይልቅ የማውቅኽ በዝና ብቻ ሳይኾን አንድ ቀን ተያይተን እንደነበረ ልጠቁምኽ እወዳለኹ። ሥድስት ኪሎ […]

ቀበርኩ ብዬ ነበር መለስ ብሎ መጣ ምነዉ አላልቅ አለኝ የመለስ ቀለስ ጣጣ በቃኝ ያንተ ነገር ሂድ ከፊቴ ዉጣ ዛሬስ የቁርጥ ነዉ የፈለገዉ ይምጣ! ዋግሹም ጎበዜና አፄ ዮሐንስ ከአፄ ቴዎድሮስ ህልፈት በኋላ እኔ ልንገስ እኔ ልንገስ በሚል ለጦርነት ሲዘጋጁ ዋግሹም ጎበዜ ስልቻ ሙሉ ጤፍ ለአፄዉ ይልኩላቸዋል። መልዕክቱ . . . ዋ! ብዙ ሠራዊት አለኝ የሚል ነበር። […]

የኢትዮጵያን ታሪክ፣ጥንታዊ ሥልጣኔ፣ውብና ድንቅየ ባህል፣ቅርስና የአገሪቱ ነፃነት ተጠብቆ መዝለቅ ሲነሳ፣በማንኛውም ንፁሕ ኅሊና ባለው ሰው አዕምሮ ውስጥ ቀድሞ ድቅን የሚለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ነወ፡፡ ይህ ያለምክንያት አይደለም፡፡ የሃማኖቱ አባቶች፣ሕግ አውጥተው፣ሥርዓት ዘርግተው፣ሕዝቡ መንፈሳዊና ዓለማዊ ሕይዎቱን እንዲመራበት ያስቻሉ፤ክፉና ደጉን፣ጥሩውንና መጥፎውን፣ለይቶ እንዲያውቅ ያደረጉ ከመሆናቸውም በላይ፣ የግዕዝና የአማርኛ ቋንቋዎችን ድምፆች ወካይ የሆኑ ፊደሎችን ቀርጸው ትውልድን በተከታታይ ያስተማሩ ከመሆናቸው የተነሳ […]

የዛሬው ‘ የጽናት’ ሬድዮ ጋዜጠኛ የቀድሞው አቀንቃኝ ሰለሞን ተካልኝ ‘ቅንድባሙ መሪ’ የሚለውን ዘፈኑን ወደ ሸገር ዘልቆ ካስባረካና ከስርዐቱም ጋር እርቅ ካደረገ በሁዋላ የመጀመሪያ ልምጩን ያሳረፈው የሙያ ወዳጁ አቀንቃኝ ነዋይ ደበበ ላይ ነበር። ( አቀንቃኝ ሲያረጅ ኮሚቴ ይሆናል መሰል ነዋይ ደበበ የልቅሶ ኮሜቴ አመራር ውስጥ ይህን ጽሁፍ ሳዘጋጅ ሰማሁ ሹመት ያዳብር ብለናል ነዋይ ) የሰለሞንን እርቅና […]

1. ብሔራዊ ዉርደታችንን እንቓቓም 2.የ ወገኖቻችንን የተገደደ እንባ እንገድብ 3. የሞተዉን የአምባገነኑን አገዛዝ በተጎጂዉ ሕዝብ ለቅሶ አይመለስም 4. የ ዓመታት የገዳይና የአስገዳይ ሥርዓት አብቅትዋል. ዳግም ባርነት እንዲቀጥል አንፈቅድም ይድረስ ለወገኖቻችን በሙሉ። ይህን ብሔራዊ ዉርደት ለመቓቓም ጥሬ ከአገር ወዳድ ኢቲዩዺያዉያን ቀርቦልሃል ቀንና ቦታው ዓርብ ከቀኑ ፱ ሰዓት በ State Departement, 2201 C Street Northwest Washington, DC […]

‹‹አቡነ መርቆርዎስ ወደ መንበራቸው ሊመለሱ ይገባል›› ኢህአዴግን ለመገዳደር የሚያስችሉ ስልቶች 2 መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ገብረሚካኤል ገ/ኪዳን በአሜሪካ የሚኔሶታ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ ወደ ክፍፍል እያመራ እንደሆነ ተገለፀ ኢህአዴግን ለመገዳደር የሚያስችሉ ስልቶች ቤተመንግስት የደረሰው የሙስሊሞች ተቃውሞ የኤርትራ መንግስትና ኤርትራውያን ስለምን የጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ህመም አስጨነቃቸው? መንግስት ከመቼውም ጊዜ በላይmከሃይማኖት ጉዳይ […]

ይሄ የአቶ መለስ ሞት ግዴላችሁም ገና ብዙ ጉድ ሳያሳየንና ሳያሰማን አይቀርም፡፡ ነገሩ ደግሞ ከ2005ዓ.ም መስከረም ጋር በመግጠሙ የተለመደውን ‹ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም› ብንል ወቅታዊነት አለው፡፡ ለካንም ለዚህ ኖሯል የቀብሩን ጊዜ ለሁለት ሣምንታት አራዝመው ዓለምን በሚያስደምምና ከዓለምም በተለዬ ሁኔታ አዲስና የሰሜን ኮሪያን የሚመስል የሀዘን ሥነ ሥርዓት ያወጁት፡፡ አራት ኪሎ ድንጋይ መጣያ ቦታ የለም – ሰው በሰው […]

ከፈጣሪያቸው ይልቅ ቀጣሪያቸው መለስን ይፈራሉ የሚባሉት የአቡነ ጳውሎስን ሞት ስሰማ ሁለት ነገር ትዝ አለኝ፡፡ ቀጣሪያቸውን ያልኩት በአንድ ወቅት ጳጳሱ የሲኖዶሱን ህግ ሊቀይሩ ፈልገው በተነሳው ውዝግብ ዙሪያ አለቃ አያሌውን ቃለ-ምልልስ ስሰራ ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቀኖና ውጭ ጳጳስ በህይወት እያለ በመንግስት የተቀጠሩ ቀኖና የሻሩ ናቸው ስላሉኝ ነው፡፡ የአቡነ ጳውሎስም ሞት ስሰማ ትዝ ያሉኝ ሶስት ነገሮች…አንደኛ ተወልጄ ያደኩበት ሰፈር […]

በድሮ ጊዜ ሰው ሲሞት ጥይት መተኮስ ልምድ ነበር። ታዲያ ጠራ ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ አንድ ትልቅ ሰዉ ሞቶ ብዙ ጥይት ወደ ሰማይ ሲተኮስ የተመለከቱ አንድ ሽማግሌ ወደ ደብረብርሃን ሲጓዙ አንድ ሰው መንገድ ላይ ያገኝና ስለ ጠራ ይጠይቃቸዋል። ሽማግሌው ሃገሩ ሰላም ነው ግን እግዜርና ሰው ተጣልተው ብዙ እየተታኮሱ ነበር። እስከ አሁን እግዜር አንድ ጥሏል ። የሰዎቹን ግን […]

በያዝነው ሀምሌ ወር በዩኬ ታላቁ ያኦሎምቢክ ውድድር ተደርጎ ነበር። የበአሉ ሙቀት በያለንበት ሁላችንንም ሲሰማን ቆይቷል። የኛ ጀግኖችም መዳሊያ አግኝተዋል። በዚህ አመት የተለመደውን አቀባበል ህዘብ እንዲያደርግላቸው አልተደረገም። “Citius,Altius, Fortius” Latin for “faster, Higher, stronger. የላቲን ቃላት ሲሆኑ በፍጥነት፤ በከፍታኛና ፤ በጥንካሬ ለማለት ነው። ወደ ኦሎንቢኩ እንመለስና በፍጥነት በከፍተኛ፤ በጥንካሬ የሚሉት ቃላት አትሌቶች ያሸናፊነትን መንፈስ ለማላበስና ለማበረታት […]

ላለፉት ሁለት ወራት በዚህ በውጭ ለምንኖር ኢትዮጵያውያን መነጋገሪያ ሆኖ የቆየው የመለስ መኖር አለመኖር ነበር። ኢትዮጵያውያን እንኳን ለሟች ቋሚን አክባሪ፣ የየትኛውም ሀይማኖት አማኝ እንሁን ፈርሀ እግዚያብሔር ያለን ነን። እንደሌሎች አገር ባህሎች ከዚህ ጥፋትም ይሁን ልማት ለኔ ምን ይደርሰኛል የምንል ሳንሆን። ያለንን አመስግነን የምንኖር ነን። በእርግጥም ነጻነታችንን ጠብቀን የኖርን በመሆናችን የማንንም ባህል አልቀላቀልንም። እናም ለመጀመሪያ ለሚያየንም ሆነ […]

*******ወቅታዊ እና እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሊመራበት የሚገባ የግል ውሳኔ።********* የአስተሳሰብ ለውጥን ለማስረፅ አስቀድመን ራሳችንን ወደውስጥ ስንመለከት ኅሊና ቅድሚያ ሥፍራውን ይይዛል።በተለይም ኅሊና ከዳኝነት ጋር ተቆራኝቶ ሲገለፅ ኃይለ-ቃሉ ምን ያህል ጥልቅና ረቂቅ እንደሆነ እንረዳለን።ኅሊና ኅለየ ከሚል የግዕዝ ቃል የወጣ ሲሆን ዐሰበ ማለት ነው።በእርባታውም ኅልዮ ማሰብ ሲሆን ኅሊና፦ዐሳብ፡ልባዊ፡ረቂቅ ሥራ፦ እያለ ይገልጸዋል።ዳኝነት ደግሞ የሰውን ልጅ ያስተሳሰብ ሚዛን የሚፈትን ከእዚአብሔር የሚሰጥ […]

ማንኛውም ትግል በአይምሮ ውስጥ ይጀምራል ፥ በአይምሮ ውስጥ ያበቃል። በስፓርት ፡ በንግድ ፡ በፓለቲካ ፡ በጦርነት ፡ በመንፈሳዊ ትግሎች ሁሉ ፍልሚያው ሚጀምረው በስነልቦና ውስጥ ነው። የስነልቦናን ድል ማግኘት የትግሉ ትልቁ ክፍል ነው። የስነልቦና ሽንፈት የተከናነበ ፡ የትግል ሽንፈቱ የጊዜ ጉዳይ ነው። የስነልቦና ሽንፈት ገጥሟቸው የሚያሸንፉ አጋጣሚያዊ እንጂ ተደጋጋሚ ክስተት አይደለም። ከኢህአዴግ አምባገነናዊ አገዛዝ ጋር የሚካሄደው […]

ቀራፊ ማለት፡ በቤተ ክርስቲያናችን ቋንቋና ሥርአት ለሰሞንና ለሰንበት እንጨት እየለቀሙ፡ እየቆርጡና እየፈለጡ፤ ማይ (ው ) ከወንዝ እየቀዱ፡ በደ  ሰላም ለወደቁና ለቤተ ልሄም ለሚያቀርቡ ሰወች የተሰጠ ያገልግሎት ድርሻና መታወቂያ ስም ነው። በንባብ፡ በዜማና በቅኔ ትምህርት ቤት ያሉ ተማሪዎችም አገልግሎቱን ከቀራፊዎች ጋራ በቅጣት መልክ ይጋሩታል። ሰሞኑን በመገናኛ መስመሮች ሲናገሩ የሰነበቱት የነ አቶ ስብ ት ነጋ ንግር ይህን ትዝታ ጭሮብኛል። […]

ሀገራችን የጉድ መንተክተኪያ ጎላ ድስት ከሆነች ቆየች፡፡ ባለሥልጣን ከናካቴው የለንም ወይም ሁሉም በየፊናው ባለሥልጣን ሆኗል፡፡ ተጠያቂነት የሚባል ነገር ድራሹ ጠፍቷል፡፡ ነገረ ሥራችን ሁሉ የአባትህ አገር ሲወረር አብረህ ውረር ዓይነት ነው፡፡ ሁሉም ባመቸው አጋጣሚ የቻለውን መቦጨቅና ኢንቬስተር መሆን በተለይ ለወያኔያውያን በጣም የተንቦረቀቀ መስክ ከሆነ ሰነበተ፡፡ እስኪ ስለ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ትንሽ እናውራ፡፡ ከመሪያችን ሁኔታ በተጓዳኝ ይህም ነገር […]

በአሁኑ ሰአት ስልጣን ላይ ያለውን ዘረኛና አንበገነናዊ ስረአት ለማስወግድ እየተደረገ ባለው ትግል ጠንካራ የለውጥ ሀይል ሊሆኑ የሚችሉ የተለያዩ ክፍሎችን ሁለንተናዊ አቅም ደረጃ እንስጥ ቢባል ከተቃዋሚ ድርጅቶች ቀጥሎ የመምሀራን ሁለንተናዊ ጥንካሬ በአምስተኛ ደረጃ የሚመጣ ይመስለኛል። መምህሩ የሰራተኛው መደብ አካል ነው። በአንድ ደምረን ከወሰድነው ደረጃችን ወደ አራትተኛ ከፊ ሊልም ይችላል። በእሰካሁኑ ታሪካችን እንዳየነው ለነጻነት፤ ለእኩልነት፤ ለፈትህ በተደርጉ […]

በአክሱማውያን ታሪክ «አልነጃሺ» የተባለ የሰለመ ንጉሥ ነበርን፡- ስለ ነቢዩ መሀመድ፣ የእስልምና ሃይማኖት እና ኢትዮጵያ ግንኙነት ዙሪያ ታሪክ የሚነግረን ሀቅ ምንድን ነው? በፍቅር ለይኩን፡፡ [[email protected]/[email protected]] ከጥቂት ወራት በፊት የመንግሥታቸውን የሥራ ሂደት ሪፖርት ለማሰማትና ከክቡራን የምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት በፓርላማ የተገኙት ክቡር ጠቅላይ ሚ/ር መለስ ዜናዊ በሀገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ መስመሩን እየሳተ እየሄደ ስላለውና […]