ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ! – ታደለ መኩሪያ
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
አንባገነኖች ስልጣን ላይ የሚቆዩበት ጊዜ እየረዘመ በሄደ ቁጥር አሰራራቸውን እየገመገሙና ራሳቸውን እያረሙ፤ ስልጣን ላይ ለመዝለቅ ያበቋቸውን ስልቶች የበለጠ ማጠናክራቸው እንዳለ ሆኖ፤ ቆይታቸው አዳዲስ ስልቶችን ለመፍጠርና ለመሞከርም እድል ይሰጣቸዋል ። ለምሳሌ መለስ ዜናዊ አባይን እንገነባለን ብሎ ድንገት እየተጯጯኽ ህዝብን ማሯሯጥ እንደጀመረው አይነት። ይህ አባይን የመሰለ ብሄራዊ ጉዳይ ባልታሰብ ሁኔታና ጊዜ ድንገት ያነሳው ቡድን፤ ኢትዮጵያን እንደሀገር ሊያቆዩአት […]
አንድነት በመብራት ሃይል አዳራሽ በአጭር ጊዜ የጠራው ስብሰባ በድምቀት እና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ታውቋል፡፡ በመብራት ሐይል በተካሄደው በዚሁ ስብሰባ ላይ የፓርቲው አመራር አባሎች እና ከአንድ ሺህ አምስት መቶ በላይ የሚሆን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን፤ በተለይ ዛሬ ለስብሰባው ቅስቀሳ ሲያደርጉ በህገወጥ መንገድ የታሰሩት የአንድነት ፓርቲ አባላት ተለቀው ወደስብሰባ አዳራሹ በማመራት ስበሰባውን መሳተፍ ችለዋል፡፡ ከነሱ መሀል […]
አንድነት ፓርቲ ነገ ነሃሴ 5, 2005 ዓ.ም ሜክሲኮ በሚገኘው የመብራት ሃይል አዳራሽ ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ 12 የፓርቲው አባላትና ሁለት መኪኖች መስቀል አደባባይና ሳሪስ አካባቢ ህገወጥ እስር ተፈፅሞባቸዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችም አባሎቹ ወደ ታሰሩባቸው ፖሊስ ጣቢያዎች አምርተዋል፡፡ ቀደም ሲል አዲሱ ገበያ አካባቢ 3 አባላት ተይዘው የነበረ ሲሆን እስከ አሁኗ ሰአት ድረስም 15 […]
አንድነት ፓርቲ ነገ በመብራት ሃይል ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ ባልቀ ከመንግስት የአዳራሽ ፍቃድ ዛሬ ከቀኑ 6 ሰዓት ቢሰጥም ገና የመከና ላይ ቅስቀሳ በጀመሩ በፖሊሶች ክልከላ ማድረግ ጀምረዋል፡፡ በአዲሱ ገበያ አካባቢ ሲቀሰቅስ የነበረው መኪና ላይ የነበሩት ሶስት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አባላት ማዕከላዊ (3ኛ ፖሊስ ጣቢያ) ታስረዋል፡፡ የታሰሩት አባላት ሰፊው መኮንን፣ አቶ ኃይሉ ግዛው እና ወርቁ ፡፡ […]
አረም ማለት ያልተዘራበት የሚበቅል ገበሬ የዘራውን ሰብል የሚሻማ፣ ውሀውን የሚጠጣበት፣ ለበሽታና ተባይ መጠለያ በመሆን ለሰብል ጉዳት ምክንያት የሚሆን እጽዋት ማለት ነው። አረም በስሮቹ አማካይነት የሰብሉን ስር አንቆ የሚገድል፣ አንዳንዱም እንደ ፓራሳይት ሰብል ላይ ተጣብቆ የሚበቅል እንደ አቀንጭራ ያለ ማለት ነው። አረሞች በፈጣን አስተዳደጋቸው ሳቢያ አልሚ ንጥረ ነገሮችን ከመሬት የፀሀይ ብርሃን ከሰማይ በመሻማት የሚያቀጭጩና የሚገድሉ ናቸው። […]
ሙስሊም ወገኖቻችንን መግደል፣ ማሰርና መደብደብ ሕገ-ወጥነት እንጅ መፍትሔ አይደለም!! ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ሁለት ዓመት ለመሙላት ጥቂት ወራት የቀረውን የሙስሊም ወገኖቻችንን ሠላማዊ የመብት ጥያቄ እንዲያከብር፣ መንግሥት በእምነት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆምና ያነሷቸውን ጥያቄዎች በአስተውሎት በማየት እንዲሁም ወደ ውይይት በመምጣት ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መንገድ ምላሽ እንዲሰጥ ሲያሳስብ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ የመንግስት ሚዲያዎችና አንዳንድ የገዢው […]
በወላይታ የአንድነት ሰብሳቢ ታሰሩ በደቡብ ክልላዊ መስተዳደር ወላይታ ዞን የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሰብሳቢ ታሰሩ፡፡ ሰብሳቢው አቶ ወኖ መንዓሳ ትናንት ነሐሴ 1 ቀን 2005 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ የዞኑ የፓርቲው ከፍተኛ አመራር የሆኑትንና ባለፈው ሳምንት ሐምሌ27 የታሰሩትን ወ/ሮ ሀዲያ መሐመድን ለመጠየቅ ከሚኖሩበት በዴሳ ወረዳ ወላይታ ሶዶ ከተማ ደርሰው ሊመለሱ ሲሉ ከአውቶቡስ ተራ ተይዘው መታሰራቸውን የዞኑ […]
ወያኔ እንደ ቆሰለ አውሬ. . . ከተስፋዬ ዘነበ(ኖርዌይ በርገን) ዘመንኑ ያለቀበት ስርዓት፣ መዋቅሩ የፈረሰ ስርዓት፣ ሁለመናው እኩይ በሆነ በሕዝብና ሃገር ጥላቻ የተተበተበ ስርዓት፣ የእድሜ ዘመኑ እያለቀና የማስተዳደርና የመምራት አቅም ማጣት ሲጀምር ለስልጣኑና በስልጣን ዘመኑ የመዘበረውን የሕዝብና የሃገር ሃብት ለማስጠበቅ የውር ድንብሩን ዪዳክራል፡፡ ይህው በመቃብር አፋፍ ላይ ያለው የወያኔ ዘረኛ ቡድን ላለፉት ሁለት አስርተ አመታት በሕዝብና […]
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
መንግስት ከ4 ዓመት በኋላ በፀረሽብርተኝነት ህጉ ላይ የውይይት መድረክ አዘጋጀ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የፀረ ሽብርተኝነት ህጉን ለማሻር የጀመረው የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ በሀገር ውስጥና በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ማግኘቱንና የመዋያያ አጀንዳ መሆኑን ተከትሎ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ድርጅት ህጉ ከፀደቀ ከ4 ዓመት በኋላ ፓርቲዎች በህጉ ላይ ያላቸውን አቋም የሚያስረዱበት መድረክ አዘጋጀ፡፡ ኢቲቪ አንድነት ፓርቲን ጨምሮ ለተለያዩ ፓርቲዎች […]
ደራሲ፣ ካሕሳይ አብርሃ ብስራት ብዛት፣ 446 ገጾች በተስፋዬ ወልደዮሃንስ አዲስ አበባ ታትሞ የተሰራጨ * ከስር በስእሉ እንደሚታየው ኢሲምባ 3250 ሜትር ከፍታ ላይ በትግራይ ውስጥ ያለ ተራራ ነው። አሲምባ በዚህ ከፍታው ሳቢያ ሌሊት ላይ በጉም ይሸፈናል። አሲምባ “ቀይ አንባ” ማለት ነው። እንደ መንደርደርያ ይሀ መጽሃፍ በዋሽንግተን ዲሲ – ሳንኮፋ ቢሮ ውስጥ ሲመረቅ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝቼ […]
የኢህአዴግ ካድሬዎች የበተኑት ህገወጥ ወረቀት በቁጥጥር ስር ዋለ በባህርዳር አንድነት የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በሰላም ተጠነቋል፡፡ ነገር ግን አንድነት ፓርቲ ያዘጋጀው በራሪ ወረቀት ቢጫ እና ቀይ ሲሆን ጭንቅላታቸውን ባዶ ያደረጉ የኢህአዴግ ካድሬዎች አረንጓዴ ሽብር በሚል በነጭ ወረቀረት የተፃፈ ነጭ ወረቀት የፓርቲው በራሪ ወረቀት ላይ የተፃፈውን የስልክ ቁጥር በመፃፍ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡትንና ፓርቲውን ለመወንጀል ቢዘጋጁም ነቄዎቹ የአንድነት […]
በምእራብ አሩሲ ዞን በኮፈሌና ዋቢ የፌድራል ፕሊሶች በንፁሀን ሙሰሊም ኢትዮጵያውያን ላይ በወሰዱት እርምጃ ከ20 በላይ ሰዎች ተገደሉ :: አካባቢው አሁንም የጦር ቀጠና መሰልዋል ፤ ፍተሻው ተጠናክሯል :: ወደ አካባቢው የሚደረግ ጉዞ ተቋርጧል:: በኮፈሌና ዋቢ ብቻ ከ400 በላይ ሙሰሊሞች ታሰረዋል :: በመላው አገሪቱ የታሰሩ ሙሰሊሞች በሺዋች ይቆጠራሉ መንግሰት ባለፈው ሐሙሰ ያወጣው መግለጫ ተከትሎ የተወሰደ እርምጃ ነው […]
አንድነት ፓርቲ “የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት” በሚል መርሃ ግብር በሃገሪቱ በተላያዩ ከትሞች እይካሄደ ያለው ሕዝባዊ ሰብሰባ እና ሰላማዊ ሰልፎች የተለያየ ማፈራራት፤ ማዋከብ፤ ዛቻ፤ እስራት እና እንግልት ቢበዛብትም ሕበርተስቡ ፍርሃትን በማስወገድ በንቃት በመሳተፍ በተሳካ ሁነታ በሰላም ተጠንቋል። ወላይታ፤ በወላይታ ህዝባዊ ስብሰባውን ሞቅ ባለ ሁኔታ አካሂዷል። ስብሰባውን የከፈቱት የአንድነት አመራር ይህን ሁሉ አፈና እና ማስፈራራት ተቋቁሞ በአዳራሹ የተገኘውን […]
አቶ ደምሴ መንግስቱ የአንድነት ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የሕግና ሰባአዊ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፣ አቶ እንግዳ ገብረጻድቅ የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት አባል፣ እንዲሁም አቶ የማነ የድርጅት ጉዳይ ኮሚቴ አባል ፣ የአንድነት ፓርቲ በመቀሌ ሊያደርግ የነበረዉን ሰልፍ ለመምራትና ሕዝቡን ለመቀስቀስ፣ ደፋ ቀና በሚሉበት ወቅት፣ በፖሊሲ ታግተዉ፣ ከመቀሌ አሮፕላን ማረፊያ አጠገብ በምትገኘዉ የኩያ ከተማ፣ ቀኑን ሙሉ እንዳይንቀሳቀሱ […]
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ያዘጋጀው ሕዝባዊ ስብሰባ እንይካሄድ ከፍተኛ ወከባ ፣ ጫና እና ውንብድና ቢደረግም የዞኑ አመራሮች የደረሰባቸውን ተደጋጋሚ እስርና አፈና በመቋቋም በአሁኑ ሠአት ጫናውን ጥሶ ከመጣው ሕዝብ ጋር ስብሰባው እየተደረገ ይገኛል፡፡ አንድነት ፓርቲ በወላይታ ህዝባዊ ስብሰባውን ሞቅ ባለ ሁኔታ ጀምሯል። ስብሰባውን የከፈቱት የአንድነት አመራር ይህን ሁሉ አፈና እና ማስፈራራት ተቋቁሞ […]
አንድነት ፓርቲ በባህር ዳር የጠራው ሰላማዊ የተዋውሞ ሰልፍ በድምቀት ተጠናቋል። በመጨረሻም የምዕራብ ጎጃም የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ማሩ እና ሌሎችም አመራሮች በሰልፉ ላይ ንግግር እድርገዋል፡፡ በዕለቱ ከ 50 ሺህ በላይ የሚሆን ሰልፈኛ መሳተፉ ተገልጿል። ቨሌላ በኩል በሰ፤ፉ መካክል አንድ የቀበሌ አመራር ሰዎችን ለማስፈራራት ሲሞክሩ በሕዝብ ትብብር ከሰልፉ እንዲገለሉ የተደርገ ሲሆን ሕብረተስቡም የግለሰቡን ማስፈራራት አጣጥሎታል። ዛሬ […]
ለአርባምንጭ ሰላማዊ ሰልፍ በቅስቀሳ ላይ መሰማራቷ ያልተወደደላት መኪና እንቅስቃሴዋን ለመግታት ከ6 የቱሪስት መኪናዎች ተለይታ 4ቱም ጎማዎቿ ተንፍሰው ተገኙ ለሴቻ ወረዳ ፖሊሶች ሪፖርት ቢደርሳቸውም የበላይ አካል ካላዘዘን መጥተን ልንመለከት አንችልም የሚል ምላሽ በመስጠት የአለቆቻቸውን ትዕዛዝ እየተጠባበቁ ነው፡፡ (3 photos)
የአርባ ምንጭ ቅስቀሳ በከፊል ለመመልከት እዚህ ይጫኑ
ኢህአዴጋውያን ወደ ተራ ውንብድና እየገቡ ነው ዛሬ ለሊት በአርባምንጭ አንድነት ፓርቲ ለቅስቀሳ የሚጠቀምበትን መኪና አራቱንም ጎማ አስተንፍሰዋል፡፡ ነገ በአርባምንጭ ደማቅ ሰላማዊሰልፍ እንደሚደረግ ያወቁት የኢህአዴግ ደህንነቶች የአንድነት ፓርቲ የቅስቀሳ ቡድን ያረፈበትን ሆቴልና መኝታ ክፍሎችን ከበዋል፡፡ #millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ) ህገ-መንግስታዊ መብታችንን ሳንገል እየሞትን እናስከብራለን!!! አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ሰኔ 13 ቀን 2005 ዓ.ም በጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቆ ወደ ንቅናቄው ከገባ ጊዜ ጀምሮ በርካታ ህዝባዊ ድጋፍና በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ መነቃቃት እና የነፃነት ጥያቄ ድምፅ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች በመደመጥ ላይ […]
የመቀሌው ሰላማዊ ሰልፍ እንዲተላለፍ ተወሰነ መንግስት አንድነት ፓርቲ በመቀሌ የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በኃይል አደናቀፈ፡፡ የመቀሌ ከተማ አስተዳደር በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የአንድነት አመራሮችን በህገወጥ ሁኔታ በማሰር፣ከመቀሌ ለቅቀው እንዲወጡ በማስጠንቀቅ እንዲሁም ቅስቀሳ ሲደረግባቸው የነበሩ ቁሳቁሶችን በአደባባይ በመንጠቅ በመቀሌ በቂ ቅስቀሳ እንዳይደረግ በማድረግ ሰላማዊ ሰልፉን በኃይል አደናቅፏል፡፡ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ግብረኃይል ኮማንድ ፖስት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ መንግስት በመቀሌ […]
በወላይታ የአንድነት አመራር ልጅ ታፍኖ ተወሰደ አቶ ማሞ ዳሞ በወላይታ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራር አባል ናቸው፡፡ለህዝባዊ ስብሰባው ስኬት በማሰብም ሙሉ ጊዜያቸውን በመሰዋት ጠንካራ ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ማሞ ከዚህ ቀደም በህገ ወጥ መንገድ ሲታሰሩና ሲፈቱ ሁሉንም በጸጋ በመቀበል በሰላማዊ ትግል ሃሳባቸውን ከመግለጽ መንግስት መብቴን ሊያከብር ይገባዋል በሚሉት ሁሉ ያለምንም ፍርሃት ድምጻቸውን በማሰማት በወላይታ ነዋሪዎች ዘንድ አክብሮትን […]
ሰበር ዜና ከባህርዳር በአሁን ሰዓት የአንድነት ፓርቲ ለነገው ሰለማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ እያደረገ ሳለ ከየት እንደመጡ የማይታወቁ የደህንነት ኃይሎች የቅስቀሳ ስራ የሚሰሩ ሰዎችን ለማደናቀፍ ቢሞክሩም የባጃጅ ሾፌሮቹ ቀስቀሳውን በጋራ ቀጥለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ፓርቲው ቅስቀሳውን እንዲያደርግ የማስታወቂያ ፈቃድ ከከተማው ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የወሰደ ቢሆንም አሁን ኮድ -3- የታርጋ ቁጥር 62399 በሆነ ነጭ ፒክ አፕ መኪና የመጡ […]
ሰበር ዜና፤ ከአርባምንጭ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ከከተማው የመንግስት ኃላፊዎች ጋር የተሳካ ውይይት ተደረገ!! አቶ አበበ አርባ የአርባምንጭ ከንቲባ፣ ኮረኔል ዳንኤል አረጋ የአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ ኃላፊ እና ዳንኤል አጀቤ የፍትህና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ከ አንድነት የሰልፉ አስተባባሪዎች ከአቶ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺ ፣ ሻለቃ አርጋው እና አቶ ክፍሌ ትንቧለል የጋሞ ጎፋ ዞን የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ እልህ […]
በባህርዳር ከተማ የባጃጅ ተሸከርካሪ ባለንብረቶችና ሾፌሮች የአንድነት ፓርቲ የሚሰራበትን ተሸከርካሪ መኪና በማጀብ ለሰላማዊ ሰልፉ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው፡፡
ሰበር ዜና ከወላይታ – በወላይታ የአንድነት ሹፌር ተደበደበ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በወላይታ ከተማ በሚያከናውነው ህዝባዊ ስብሰባ የሚሳተፉ አመራሮችን ከአዲስ አበባ በመጫን የተንቀሳቀሰው ሹፌር ዛሬ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ወላይታ ማርያም ሰፈር አካባቢ ሞንታርቦና በግዢ የተገኘ ጀነሬተር ለመጫን ሲሞክር በተከለከለ መንገድ ቆመሃል ያለ የትራፊክ ፖሊስ የሹፌሩን መንጃ ፈቃድ በመንጠቅ ይሰወራል፡፡ሹፌሩ የተወሰደበትን መንጃ ፈቃድ ለማስመለስ ትራፊኩ ወዳመራበት […]
ሰበር ዜና፤ ከመቀሌ የአንድነት አመራሮች ከነ መቀስቀሻ ሞንታረቮአቸው በቀዳማይ ወያኔ ፖሊስ ጣቢያ ታሰሩ የአንድነት ፓርቲ አመራር የሆኑት አቶ አርአያ፣ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ እንግዳ ወ/ፃዲቅ እና የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ፀሀፊ አቶ ክብሮም ብርሀነ በመቀሌ ከነ መቀስቀሺያ ሞንታረቮአቸው ቀዳማይ ወያነ ክፍለከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታስሩ፡፡ አቶ እንግዳ ወ/ፃዲቅ እና አቶ ክብሮም ብርሀነ ለሁለተኛ ጊዜ […]
ታርጋ አልባዎቹ ሞተር ሳይክሎችና ዳንኤል ሺበሺ August 2, 2013 at 6:14pm በወላይታ ሶዶ ከተማ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በ28/11/05 ለሚያደርገው የህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ ለማካሄድ በስፋራው የተገኙት የፓርቲው አመራሮችና በወላይታ የፓርቲው አባላት የተለያዮ ህገ ወጥ ድርጊቶች እየተፈጸመባቸው ይገኛል፡፡በአመራሩና በአባለቱ ላይ እየደረሰ የሚገኘው ህገ ወጥ ድርጊት የተለያየ መልክ የተላበሰ ሲሆን በዋናነትም ታርጋ አልባ በሆኑ ሞተር ሳይክሎች የተፈናጠጡ […]
በወላይታ በመንግስት ተደራጅተው ዝርፊያ የሚፈፅሙት ታርጋ አለልባ ሞተር ሳይክለኞች፡፡ #millionsofvoicesforfree #Ethiopia #UDJ
ዜና ከወላይታ መንግስት አንድነት ፓርቲ ላይ የክስ ድራማ እያዘጋጀ መሆኑ ተደረሰበት መንግስት በወላይታ ሶዶ በአንድነት ፓርቲ ላይ የሀሰት ድራማ በመስራት ላይ ነው፡፡ መንግስት በመስጊድ ውስጥ በድብቅ ያሰራጨው ሙስሊሙን ህብረተሰብ ለአመፅ የሚቀሰቅስ በራሪ ወረቀት የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን አመራር የሆኑት ወ/ሮ ሀድያ መሀመድ እንዳሰራጩት በማስመሰልና የሀሰት ምስክሮችን በማጋጀት ስራ ተጠምዷል፡፡ ወ/ሮ ሀድያ መሀመድንም “በራሪ ወረቀቱን እንድበትን […]
ወያኔዎች በጣም እየከፉ ነው፡፡ ክፋታቸው ጠርዝ እየለቀቀ መጥቷል፡፡ ይሉኝታና ሀፍረት ወትሮውንም ወያኔዎች ጋ እንደሌለ የታወቀ ቢሆንም አሁን አሁን ግን በጣም የለየላቸው ጋጠ ወጦችና ኅሊናቢሶች እየሆኑ ነው፡፡ እነሱን በሰው ልጅነት ለመፈረጅ እንኳን በጭራሽ የማይሞከር የሚገርሙ ፍጡራን ናቸው፡፡ ይቅርታችሁንና ወያኔዎች ዞሮ የሚያይ አንገት ያልፈጠረባቸው ባልጩት ራስ መሆን አለባቸው፡፡ የሚሠሯቸውን የሕጻን አይሏቸው የዐዋቂ ሞኛሞኝ ሥራዎች ስታዩ ከዚህም በላይ […]
በባህርዳር ከተማ እሁድ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም. የሚደረገው የተቃውሞ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል በመላ ሀገሪቱ የጀመረውን ህዝባዊ ተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አባላቱ በከተማዋ በተሸከርካሪ መኪና እና ድምፅ ማጉያ በመታገዝ አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ ከድምፅ ቅስቀሳው ጎን ለጎን በከተማዋ ፖስተሮች የመለጠፍና በራሪ ወረቀቶችንም የመበተን […]
ሰበር ዜና፤ ከባህር ዳር፤ ከወላይታ፤ ከጅንካ እና ከመቀሌ ከተሞች – ፍኖተ ነጻነት ባሕር ዳር፤ አንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ በባህር ዳር ከተማ ለሚያደርገው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ የመኪና ላይ ቅስቀሳ እንዳያካሂድ እየተከለከለ ነው፡፡ የኢህአዴግ ካድሬዎችም ለቅስቀሳ የወጣውን መኪና በመክበብ ሁከት ለመፍጠር እየሞከሩ ነው፡፡ ለቅስቀሳ የወጣውን መኪና በማገትም የሹፌሩን መንጃፍቃድ ነጥቀዋል፡፡ የከተማዋ ነዋሪዎች የካድሬዎቹን ክልከላ በመቃውም ከፀጥታ ሀይሎቹ […]
የቃሊቲ እንግልት፤ – ከግርማ ሠይፉ ማሩ ጎበዝ እንግዲህ እዚህ ሀገራችን ኢትዮጵያ ጉድ ሳይሰማ አይታደርም አይደል፡፡ ዛሬ ከአቤል አለማየሁ ጋር አንዱዓለም አራጌን እና ርዕዮት ዓለሙን እንጠይቅ ተባብለን ወደ ቃሊት ወረድን፡፡ ለዛሬው የነበረን ዕቅድ ሁለቱን ብቻ የማየት ነበር፡፡ ለዚህም እንዲሆን በቂ የሚባል ሰዓት ይዘን ልክ ከቀኑ አምሰት ሰዓት ላይ ቃሊት በር ደረሰን፡፡ በቅርቡ ቃሊት የሚገኙትን ወዳጆቻችን ለመጠየቅ […]
ልዩነታችን ዉበታችን ነዉ ! የሚሊዮኖች ድምጽ በጂንካ – ግርማ ካሳ ሐምሌ 25 ቀን 2005 ዓ.ም የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መርህ ሥር፣ ታላቅ ሕዝባዊ ሰላማዊ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ መጀመሩ ይታወቃል። በደሴና በጎንደር በአሥር ሺሆች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን የሰላም፣ የመብት የእኩልነትና የነጻነት ጥያቄዎቻቸዉን አስምተዋል። በፊታችን እሁድ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም፣ የአንድነት ፓርቲ በአራት ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እየተዘጋጀ […]
በጦር ኃይሎች፣ ቤትል ጎጃም በረንዳና መሳለሚያ ከመስጊድ የወጡ ሙስሊሞች ታፍሰዋል፡፡ በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች በርከት ያሉ ፌደራል ፖሊሶች ይታያሉ፤ ከሌሊቱ 5 ፡00 ሰዓት ጀምሮ መኪናዎች ላይ ከባድ ፍተሻ እየተደረገባቸው ነው፡፡ የሙስሊሙን የመብት እንቅስቃሴ የሚመራው ድምፃችን ይሰማ የተባለው የሶሻል ሚዲያ ግሩፕ ከቤተመንግስት በቅርብ ርቀት በሚገኘው ተውፊቅ መስጊድ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ብሶቱን እንዲያሰማ ጥሪ ማስተላለፉ አይዘነጋም፡፡
ሰበር ዜና ከመቀሌ – የአንድነት ከፍተኛ አመራር እና የፓርቲው አባል ታሰሩ መቀሌ ውስጥ አንድ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ እንግዳ ተክለፃዲቅ እና በዚህ ሳምንት “መቀሌን በ24 ሰዓት ለቀህ ውጣ” ተብሎ የነበረው የአንድነት ፓርቲ አባል አቶ የማነህ አበራ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በፖሊስ በህገወጥ መንገድ ታስረዋል፡፡ #millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ
ከሁሉ አስቀድመን ፣ በየመልኩ በዉጭ ለምንኖር ኢትዮጵያዉያን፣ ባህላችንን፣ ታሪካችንን ችግሮቻችንና የአገራችንን እሴቶ፣ በየወቅቱ በመከታተል፣ ግንዛቤ እንድናገኝ ለምታደርጉት ጥረት፣ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን። ዛሬ አገራችን አጣብቂኝ ሁኔታ ዉስጥ እንዳለች፣ የሁላችንም ግንዛቤ ነዉ። ከሁሉም በላይ፣ እንደ ማንኛዉም አገር ሕዝብ፣ የሃይማኖት የብሄረሰብ የቋንቋ ልዩነቶች ቢኖሩም፣ የእኛ የኢትዮጵያዉያን ልዩ እሴት፣ ልዩነቶቻችንን አቻችለን፣ በፍቅርና በሰላም መኖራችንና መቻቻላችን ቀዳሚነቱን ስፍራ የሚይዝ […]
መግቢያ፡- (ከ18 ዓመት ዕድሜ በታች የሆነ ሰው እንዲያነብ የማይመከር) የሰው ልጆች በሃይማኖት መከፋፈላቸውን አምርሬ ብቃወምም፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሃይማኖቶች የውሸትና ለብዝበዛም የተፈጠሩ መሆናቸውን ባምንም፣ እጅግ ብዙዎቹ ሃይማኖቶች ሰይጣን የተጣባቸው ወይም የሰይጣናዊነት መንፈስና አሠራር በጉልህ የሚታይባቸው መሆናቸውን ብረዳም በትውልድና በገዛ ፈቃዴ ይዤው ያለሁት ሃይማኖት ክርስትና ነው፡፡ ክርስትና በራሱ በመቶዎችና ከዚያም በላይ የተከፋፈለ መሆኑንም አውቃለሁ – አንዳቸው ለአንዳቸው […]
የጅንካ ወጣቶች ታሪክ እየሰሩ ነው፡፡ አንድነት ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ በንቃት ለመሳተፍ ከመንቀሳቀሳቸውም በላይ በጅንካና በአካባቢዋ በራሳቸው ተነሳሽነት ቅስቀሳ እያከናወኑ ነው፡፡ በተያያዘ ዜና የደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሞሎካ ውብነህ በ22/11/2005 ዓ.ም በቁጥር 417/107/05 በፃፉት ደብዳቤ ለአንድነት አመራሮች የእንወያይ ጥሪ አድርገው ከ14 የሀገር ሽማግሌዎችና ከጅንካ ከተማ ከንቲባና የተለያዩ የከተማው ባለስልጣናት ጋር በመሆን አንድነት ሰላማዊ ሰልፉን […]
የኢህአዴግ መንግስት በኢቲቪ በኩል ስለ ‘ሽብር’ና የ‘ፀረሽብር ሕግ’ አስፈላጊነት ያወራል። አንዳንድ ተቃዋሚዎች ደግሞ ስለ ‘ፀረሽብር’ ሕጉ ኢ-ሕጋዊነት ይሰብካሉ። እኔም የፀረሽብር ሕጉ ከማይደግፉ ሰዎች ጋር እንደምሰለፍ ካሳወቅኩ ከጥቂት ግዜ በኋላ አንድ የምወደው የህወሓት አባል የሆነ ጓደኛዬ እንዲህ ሲል በውስጥ መልእክት ላከብኝ፣ “ፀረሽብር ሕግ መቃወም ኮ ሽብርን መደገፍ ነው። አንዳንድ አክራሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ ስም ሽብርተኝነትን ማስፋፋት ይፈልጋሉ። […]
በሻሸመኔ ጩሉሌ ሀበራ ቀበሌ በሚገኘው በመስጊዱራህማ መስጊድ ም/ኢማምና የመስጊዱ ኮሚቴዎች በህገወጥ መንገድ ታስረቸዋል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአንድነት ፓርቲ አቤቱታቸውን አቀረቡ፡፡ በሻሸመኔ ጩሉሌ ሀበራ ቀበሌ በሚገኘው በመስጊዱራህማ መስጊድ ም/ኢማም ሼህ አማን ተሺተን ጨምሮ 15 የመስጂዱ ኮሚቴ አባላት የታሰሩት ባለፈው እሁድ ሐምሌ 14 ቀን 2005ዓ.ም የመስጂዱ ንብረት የሆነን ከአንድ ሄክታር ላይ የታጨደ በግምት ከ10 ኩንታል በላይ የሚመዝን […]