ሰበር ዜና፤ ከባህር ዳር፤ ከወላይታ፤ ከጅንካ እና ከመቀሌ ከተሞች‬ – ፍኖተ ነጻነት

ሰበር ዜና፤ ከባህር ዳር፤ ከወላይታ፤ ከጅንካ እና ከመቀሌ ከተሞች‬ – ፍኖተ ነጻነት

ባሕር ዳር፤

አንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ በባህር ዳር ከተማ ለሚያደርገው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ የመኪና ላይ ቅስቀሳ እንዳያካሂድ እየተከለከለ ነው፡፡ የኢህአዴግ ካድሬዎችም ለቅስቀሳ የወጣውን መኪና በመክበብ ሁከት ለመፍጠር እየሞከሩ ነው፡፡ ለቅስቀሳ የወጣውን መኪና በማገትም የሹፌሩን መንጃፍቃድ ነጥቀዋል፡፡ የከተማዋ ነዋሪዎች የካድሬዎቹን ክልከላ በመቃውም ከፀጥታ ሀይሎቹ ጋር በመከራከር ላይ ናቸው፡

ወላይታ፤

በወላይታ አንድነት ፓርቲ የጠራውን ህዝባዊ ስብሰባ ለማኮላሸት የዞኑ አስተዳደር ተጨማሪ ታርጋ የሌላቸው ሞተር ሳይክሎችን አሰማራ፡፡ የወላይታ ዞን የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ኢህአዴግ ያሰማራቸውን ዘራፊ ሞተረኞች ተቋቁመው በራሪ ወረቀት በማሰራጨት ላይ ናቸው፡፡ ዝርፊያውን የሚያሳይ የቪዲዮ ምስል ዛሬ በፍኖተ ነፃነት ይፋ ይደረጋል፡፡

ጅንካ፤

በጅንካ ከተማ አንድነት ፓርቲ አባላት የመኪና ላይ ቅስቀሳ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ ነው፡፡ የከተማው ወጣቶች በፍቃደኝነት የቤት ለቤት ቅስቀሳ እያደረጉ ነው፡፡

መቀሌ

የአንድነት ስራ አስፈፃሚና ከፍተኛ አመራር ታሰሩ!!!
የአንድነት ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ደምሴ መንግስቱ፣ የአንድነት ከፍተኛ አቶ እንግዳ ወ/ፃዲቅ እና የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ፀሀፊ አቶ ክብሮም ብርሀነ በመቀሌ አቅራቢያ ኩያ ከተማ ውስጥ ታስረዋል፡፡

‪#‎millionsofvoicesforfree‬ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎UDJ‬