ዜና ከአርባ ምንጭ፤ ከጂንካ እና ከወላይታ – ሕበረተሰቡ ፍርሃትን በማስወገድ ድምጹን አሰማ!!
አንድነት ፓርቲ “የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት” በሚል መርሃ ግብር በሃገሪቱ በተላያዩ ከትሞች እይካሄደ ያለው ሕዝባዊ ሰብሰባ እና ሰላማዊ ሰልፎች የተለያየ ማፈራራት፤ ማዋከብ፤ ዛቻ፤ እስራት እና እንግልት ቢበዛብትም ሕበርተስቡ ፍርሃትን በማስወገድ በንቃት በመሳተፍ በተሳካ ሁነታ በሰላም ተጠንቋል።
ወላይታ፤
በወላይታ ህዝባዊ ስብሰባውን ሞቅ ባለ ሁኔታ አካሂዷል። ስብሰባውን የከፈቱት የአንድነት አመራር ይህን ሁሉ አፈና እና ማስፈራራት ተቋቁሞ በአዳራሹ የተገኘውን ህዝብ “ጀግኖች ናችሁ” ሲሉ አወድሰዋል። ወ/ሮ ሀድያ የሚባሉ የአንድነት አመራር አባል በቅስቀሳ ወቅት ተይዘው እንደታሰሩና አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኙ ስብሰባውን የሚመሩት የአንድነት አመራሮች ለህዝቡ ይፋ አድርገዋል።
ጅንካ፤
በጅንካ ከተማ አንድነት ፓርቲ አባላት በጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሕዝቡን እንዳይወጣ ለማስፈራራት የአድማ በታኝ ፖሊሶች በብዛት ቢወጡም ሕበረተሰቡ ፍርሃትን በማስወገድ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ፍጹም ጨዋ እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተቃውሞን እና የተገፈፈው መብቱ እንዲከበር በመጠይቅ በሰላም ተጠናቋል፡፡
አርባ ምንጭ፤
በአርባምንጭ የቅስቀሳ መኪና 4ቱንም ጎማ በማስተንፈስ እና ከአገልግሎት ውጭ እንዲሆን ከማድረግ አንስቶ የተለያየ ጫና እና እንገልት ተቋቁመው በተሳካ ሁኔታ የሰላማዊ ሰልፉ የተጠናቀቀ ሲሆን በአርባ ምንጭ እየተስተጋቡ ያሉ መፈክሮች በከፊል
• የታሰሩ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ይፈቱ
• መንግስት ህገ-መንግስቱን ያክብር
• መንግስት በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን ያቁም!
• መንግስት ለብሄራዊ መግባባት ባስቸኳይ መልስ ይስጥ!
• ውሸት ሰልችቶናል! ይቁም!!!
• የጸረ – ሽብር ህጉ ባስቸኳይ ይሰረዝ!
• ዘርን መሰረት ያደረገ ማፈናቀል ባስቸኳይ ይቁም!!
• ሙወስና የስርአቱ መገለጫ ነው!!