አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ‹‹የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነት››በሚል መሪ ቃል የጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ መስከረም 5/2006 በአዲስ አበባ በሚደረግ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠናቀቃል፡፡ፓርቲው በተለያዮ የአገሪቱ ክፍሎች ያደረጋቸውን ህዝባዊ ስብሰባዎችና ሰላማዊ ሰልፎች በአንክሮ ሲከታተሉ የቆዮት 33 ፓርቲዎች በአዲስ አበባ የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ በጋራ ለማድረግ ስምምነታቸውን በመግለጽ በዛሬው ዕለት በአንድነት ዋና ጽ/ቤት ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ 33 ፓርቲዎችን በመወከል ንግግር ያደረጉት […]

በሀገሬ ሰማይ ስር በሚደረገው የተቃውሞ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ከኢዴፓ እስከ አንድነት ፓርቲ ድረስ በመሳተፍ ለአስራ ሶስት ዓመታት ያህል የምችለውን አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ፡፡ ይህ ኩነትም የፓርቲዎችን ጓዳ ፈትሼ ግንዛቤ እንዳገኝ ስላመቻቸልኝ፣ በቀጣይ ህዝባችን የፖለቲካና ሰብአዊ መብቶቹ ተከብረው ነፃነቱን እንዳያገኝ እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ የማስባቸውን ነጥቦች እንደሚከተለው ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡ 1. እንደ ገዥው ፓርቲ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችም ከኋላቀሩ የፖለቲካ ባህላ የተላቀቁ […]

በቅስቀሳ ስራ ላይ የነበሩ አራት የአንድነት ፓርቲ አባላት አዳማ ከተማ ውስጥ መታሰራቸው ታወቀ፡፡ ፖሊስ ከ5ሺ በላይ በራሪ ወረቀቶችን ቀምቷቸዋል፡፡ ፖሊስ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ እውቅና ተሰጣችሁ እንጂ በራሪ ወረቀት የመበተን ፍቃድ የላችሁም በሚል ዳንኤል ፈይሳ፣ደረጄ መኮንን፣አስናቀ ሸንገማና ደረጄ ክበበው የተባሉት አባላት ወረዳ አንድ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ታስረው ከሰዓታት በኋላ መለቀቃቸውን የቅስቀሳ ቡድኑ አባላት አስታውቀዋል፡፡ ከትራፊክ ፖሊስ፣ከፖሊስ፣ከደህንነት፣ከደንብ […]

ሰልፈኞቹ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የማያባራ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመቃወም በደቡብ ኮርያ ፕሬዚደንት ጽ/ ቤት ፊት ለፊት ፕሬስ ኮንፈረንስ በማድረግ የኮርያ መንግስት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እንዲፈጥር ተማጽነዋል። ለ ደቡብ ኮርያ ፕሬዚደንት ፓርክ ግን-ሄ ደብዳቤም ኣስገብተዋል። ሰልፈኞቹ ለደቡብ ኮርያ UNHCR ተወካይና የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ደብዳቤዎችን ያስገቡ ሲሆን በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እንዲፈጥሩ ተማጽነዋል። ከሰልፈኞቹ መሃል ኣብዛኛዎቹ […]

ስፖርት በጣም እወዳለሁ፤ ወቅታዊ ዜናና ጥናታዊ ፊልምም አዘወትራለሁ። ከሁለቱ ዉጭ ግን ኢትዮጵያ እያለሁም ሆነ ዛሬ በስደት ኑሮዬ ከቴሌቪዥን ጋር ብዙም አልዋደድም . . . ግን አንዳንዴ እበድ ሲለኝ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ቴሌቪዥን ሆኖ ከመተኛቴ በፊት ኢቲቪ እየከፈትኩ አብዳለሁ። አዎ . . . አብዳለሁ። ሆዴ ያመቀዉ ቁጣና ልቤ የተሸከመዉ የ22 አመት በደል ቀለል የሚለኝ ሳብድ ነዉና ኢቲቪ […]

በተንጣለለ ቪላ ውስጥ ከበድ ያሉ እንግዶች “ጸዳ” ባሉ ምግብና መጠጦች እየተስተናገዱ ነው። ታዋቂ ግለሰቦች፤ ባለስልጣናት እና አርቲስቶች የቀረበላቸውን ብፌ በልማታዊ ወጋቸው እያወራረዱ ሳሉ አንድ እንግዳ ነገር በመሃላቸው ተከሰተ። ሞቅ ባለው የአይቴ ነጋ ገብረእግዚአብሄር ድግስ ላይ ያልተጋበዙ ሁለት ሰዎች ዘው ብለው ከግብዣው ክፍል ገቡ። የፌዴራል ፖሊስ አባላት ነበሩ። በዚህ ያልተለመደ ክስተት የአቶ ነጋ እንግዶች አልተደናገጡም ነበር። […]

ሰሞኑን ከፀረ አሸባሪነት ህግ በማስቀጠል የአዲስ አበባን ከተማ ነዋሪን በተለ ሲያምስ ከርሞ አሁንም በማመስ ላይ ያለው የመኖሪያ ቤት ጉዳይ ነው፡፡ በእዲስ አባባ የመኖሪያ ቤት ችግር እንዳለ አሌ የሚባል አይደለም፡፡ ይህ ችግር እዚህ እንዲደርስ ደግሞ ዋናው ተዋናይ መንግሰት እንደሆነ መዘንጋት የለበትም፡፡ ምክንያቱም ለቤት መስሪያ የሚሆነውን ቦታ በቁጥጥሩ ስር አድርጎ ለዜጎች እንዳይደርስ በማድረጉ ነው፡፡ አንደኛው በቁጥ-ቁጥ ቦታ […]

ለረጅም ጊዜ የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ አዘጋጅ ሆኖ ያገለገለዉና የጋዜጣዉ ህትመት ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ የኢቦኒ መፅሔት ዋና አዘጋጅ ሆኖ በመስራት ላይ የሚገኘዉ ጋዜጠኛና ብሎገር ብስራት ወልደ ሚካኤል ሰሞኑን በ4 የደህንነት ኃይሎች ታግቶ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እንደተፈፀመበት ተናገረ ፡፡ ድርጊቱ የተፈፀመዉ ባሳለፍነዉ ሰኞ (ነሐሴ 20 – 2005ዓ.ም) ከምሽቱ 2፡35 ላይ ከስራ ወደ ቤቱ በጉዞ ላይ እያለ ነበር፡፡ […]

1-ይህ ጽሁፍ ዓላማው አድናቆት፡ ትችትና ግብዣ ነው። የአንድነት ምሽት በቶሮንቶ ግብዣ። ከአድናቆትና ከግብዣው በፊት ስለፖለቲካ መሪዎችና ስለፖለቲካ ተንታኞች አትቶ፤ የብርሀኑ ነጋን (ዲባቶ) አቀራረብ ይተቻል። የሰማያዊ ፓርቲን ርምጃ ያደንቃል። የአንድነት ዘመቻን ስለማገዝ ያሳስባል። እንደው ተገጣጥሞ ነው እንጂ፤ አንዱን ለማሞገስ ሌላው መኮሰስም መከሰስም የለበትም። ግን አንዳንዴ ደግሞ፤ በጊዜ ያልተተቸ፤ ይለመዳል። አጉል ልማድ ይሆናል። ሁሉንም ለያይቶ ለመጻፍ ደግሞ፤ […]

የኢትዮጵያ ጀግኖች ታሪክ ሲነሳ፤ በግንባር ቀደም ከሚጠቀሱት መካከል ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ በዋናነት ይጠቀሳሉ። – በአባታቸው ኦሮሞ፣ በናታቸው የጉራጌ ተወላጅ የሆኑት ባልቻ ሳፎ (ባልቻ አባ ነፍሶ) በተለይ በ1888 ዓ.ም. በአድዋ ጦርነት ወቅት በአጼ ምኒልክ ስር ሆነው በመድፍ አስተኳሽነት በሰሩት ጀግንነት ይታወሳሉ። እኚህ ታላቅ ኢትዮጵያ ለአገራቸው እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ያደረጉት ታላቅ ጀብዱ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ ይኖራል። […]

በአንድ ወቅት በደቡብ አፍሪካዊቷ ከተማ በኬፕታውን የሚኖር አንድ በንግድ ሥራ የሚተዳደር ኢትዮጵያዊ ጎልማሳ አንድ አሳዛኝ ገጠመኙን እንዲህ አጫውቶኝ ነበር፡፡ ይህን ታሪኩን ያካፈለኝ ኢትዮጵያዊ ጎልማሳ የሥራ ቦታው ላይ ከአንድ ከኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ጋር በተነሳ ጠብ በተፈጠረ ግጭት የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ የሆነው ጓደኛውን አንድ የፊቱን ጥርሱን በቦክስ ያወልቀዋል፡፡ የጥርሱን መውለቅ የሰሙ የዚህ ሰው ጓደኞችም ተሰባስበው ይህን ሰው […]

በአባይ ወልዱ የሚመራውና ሰባት ከፍተኛ የሕወሐት ባለስልጣናት የተካተቱበት ቡድን በአሜሪካ አራት ከተሞች ባካሄደው ስብሰባ በተለይ በላስቬጋስ ጠንካራ ተቃውሞ እንደገጠመው በስፍራው የተገኙ ምንጮች አስታወቁ። ቡድኑ በዋሽንግተን ኢትዮጲያ ኤምባሲ በጀመረውና በመቀጠል በላስቬጋስ፣ ሲያትልና ካሊፎርኒያ ከተሞች ባካሄደው ስብሰባ “አላማ” አድርጎ የያዛቸው ጉዳዮች እንደነበሩ የጠቆሙት ምንጮች፣ እነሱም፥ “የመለስ ፋውንዴሽን፣ የአባይ ግድብና የ40/60 የቤቶች ግንባታ.” ሲሆኑ፣ ለነዚህ ማስፈፀሚያ “ገንዘብ አዋጡ” […]

ለአንድ ህዝብ ሃገር ማለት የመኖር ዋስትናው ተጠብቆ ሳይሸማቀቅ፣ ሳይበደል፣ ፍትህ ሳዩጓደል፣ የዜግነት መብቱ ተጠብቆ የህግ ከለላ አግኝቶ በነፃነት የሚኖርብት ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን ሃገር መሆን ከተሳናት እንሆ ሃያ ሁለት አመት ተቆጠረ፡፡ የደርግ ስርዓትን ተክቶ በትጥቅ ትግል መንበሩን የተቆናጠጠው የወያኔ ዘረኛ ቡድን ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ የፖለቲካ ስልጣኑንም ሆነ የኤኮኖሚ አውታሩን በአንድ ብሄር ብቻ አደራጅቶ የተቀረውን ኢትዮጵያዊ እንደ […]

ተጋባዥ፥ ኢትዮጵያውያን ሚዲያዎች በሙሉ በስብሰባው ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች፥ 1) የፓርላማ አባል የተከበሩት አቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ እና 2) የአንድነት ፓርቲ ፍኖተ ነፃነት ቦርድ ሰብሳቢ አቶ በላይ ፈቃዱ በረዳ – በኢትዮጵያችን በአቀፍ ደረጃ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ እእንዲሁም በቀጣዩ የነፃነት እና የዴሞክራሲ ትግላችን ላይ እነዚኽ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ባልደረቦች […]

ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ ማብራሪያ የሚሊየኖች ድምፅ ለነፃነት ንቅናቄ በአራቱም የኢትዮጵያ ማዕዘናት የነፃነት ድምፅ ማስተጋባት ከጀመረ እንሆ ዛሬ ስልሳ ሰባተኛ(67) ቀኑን ይዟል፡፡ ፓርቲያችን በእዚህ ታላቅ ሕዝባዊ የነፃነት ንቅናቄ መሪር የሆነ ውድ ዋጋ እየከፈለ ድምፅ አልባ ለሆኑት ሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ድምፅ በመሆኑ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡ ላለፋት ስምንት ዓመታት ሰቆቃ እና ግፍ በገዢዎቻችን ሲፈፀምበት የኖረው የገጠሩም […]

ለተከበሩ ኢንጂነር ይልቃል፣ ለክቡራን ከፍተኛ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት፣ በቅድሚያ ሰላምታዬ ባላችሁበት ቦታ ይድረሳችሁ! ጤና ይስጥልኝ። ለሰማያዊ ፓርቲ አድናቆት አለኝ። የግራዚያኒ ሃዉልትን በመቃወም ያደረጋችሁት ሰልፍን ተከታትያለሁ። በብዛት ግን ሰው ያወቃችሁ፣ በአዲስ አበባ በጠራችሁት ሰላማዊ ሰልፍ ነዉ። ያኔ ትልቅ ሥራ ነው የሰራችሁት። አኩርታችሁኛል። ብዙ ደጋፊዎችም በአጭር ጊዜ ዉስጥ አግኝታቹሃል። ያኔ የጠራችሁትን ሰልፍ አብዛኞቻችን ብንደግፈውም፣ ሌሎች ድርጅቶችን […]

የአገሬ ሰው “ነገሩ ነው እንጂ ጩቤ ሰው አይጎዳም”የምትል አባባል ነበረችው።ግፍ በተለያየ ምክንያት ሊውልብህ ቢችልም የግፉ ደራሲ ግፉን ሲፈጽምብህ ወይም እየፈጸመብህ መርዘኛ በሆነ ፀያፍ አነጋገር በሕሊናህም ላይ ጠባሳ ካልተወ በጊዜ ብዛት የደረሰብህን ግፍ ችላ ልትል፤ ከቶውንም ግፈኛውንም ይቅር ልትል እንደምትችል ለማመላከት ይመስለኛል። “ስልጣን ያባልጋል፤ፍፁም ስልጣን ደግሞ ፍፁም ያባልጋል” የሚለው አባባል ደጋግሞ በታሪክ እንዳሳየን አምባገነኖችና ጀሌዎቻቸው ግፍ […]

ለስድስት አመት ኤፈርትን ሲመሩ የቆዩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከሃላፊነት መነሳት ተከትሎ በሕወሐት ውስጥ ውጥረት መንገሱን ምንጮች አመለከቱ። የኤፈርት ቦርድ ሰብሳቢ በነበሩት ባለቤታቸው አቶ መለስ አማካይነት ዳይሬክተር ተደርገው አዜብ መሾማቸውን ያስታወሱት ምንጮች፣ ከመለስ ሕልፈት በኋላ ቦታውን የተረከቡት ኤርትራዊው ቴዎድሮስ ሃጎስ መሆናቸውን፣ እንዲሁም ዳይሬክተር የመሾምና የመሻር ስልጣኑ የቦርዱ መሆኑን ያስረዳሉ። አዜብ ከኤፈርት እንዲወገዱ የተደረገው ግን በነቴዎድሮስ ሃጎስ […]

አንድነት ታርቲ ዛሬ በባሌ ሮቤ የሚያደርገውን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በኦህዴድ ባለስልጣናትና በደህንነት ሀይሎች አፈና ተፈፀመበት፡፡ ሰልፉን ለማደናቀፍ የአካባቢው ባለስልጣናት ትላንት ምሽት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ካረፉበት ታይታኒክ ሆቴል ንብረታቸውን ሳይዙ በግዳጅ እንዲወጡ ከመደረጉም በላይ አብዛኞቹ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና የቅስቀሳ ቡድን አባላት ታግተዋል፡፡ በስፍራው የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና የቅስቀሳ ቡድን አባላት ደህንነት አደጋ ላይ እንደሆነም ከስፍራው […]

አንድነት ሰላማዊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነዉ። አገዛዙ ግን ሕገ መንግስቱን በመርገጥ የሰለጠነን ሳይሆን፣ የዛቻን ፖለቲካ እያራገበ ነዉ። «በሮቢ ደም ሊፈስ ይችላል» በማለት ማስፈራሪያዊች እየቀረቡ ሲሆን፣ ፖሊሲስ ሰልፍን የምታደርጉ ከሆነ እርምጃ እንደሚወስድ አሳዉቀዋል። የሮቢ የአገዛዙ አስተዳዳሪዎች፣ 20 ሰዎች የሚገኙበት የ«ሽማግሌዎች» ቡድን አቋቁመዋል። ይሀ ቡድን ከጥቂት ሰዓት በኋላ ከሚሊየነም ድምጽ ለነጻነት ግብረ ኃይል ጋር ዉይይት ያደርጋል። ኮምቴዉ፣ ስብሰባው […]

የአንድነት ፓርቲ የቅስቀሳ ቡድን አባላት የሚደርስባቸውን ጫና ተቋቁመው በባሌ ሮቤ የተሳካ ቅስቀሳ በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ የቅስቀሳ ቡድኑ አባላት “የህዝቡ አቀባበል መንግስት የሚያደርስብንን ጫና ተቋቁመን ስራችንን እንድናከናውን ረድቶናል” ብለዋል፡፡ በባሌ ሮቤ ከንቲባ ጽ/ቤት አራት የአንድነት ፓርቲ ተወካዮች ለውይይት ተጠርተው ታግተው የነበሩ ሲሆን እነዚሁ የአንድነት ፓርቲ ተወካዮችና የቅስቀሳ ብድን አባላት አሁን የተለቀቁ ቢሆንም በሁለት መኪኖች የተጀመረውን ቅስቀሳ […]

የአንድነት ፓርቲ የቅስቀሳ ቡድን መኪናና በባጃጆችን በመጠቀም የተቀናጀ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የፍቼ ከተማ የኢህአዴግ ካድሬዎችና የመንግስት ሹመኞች ህዝቡ ለነገው ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይወጣ ቤት ለቤት በመሄድ በማስፈራራት ላይ ቢገኙም ህዝቡ በነገው የተቃውሞ ሰልፍ ብሶቱን ለመግለፅ ተዘጋጅቷል፡፡ ዘግይቶ በደረሰን ዜና በፍቼ ከተማ የሚገኘውን የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት የመንግስት የደህንነት ሀይሎች ሰብረው በመግባት በቢሮው ውስት ያሉትን አባላት ቢያባርሩም […]

በመጪው እሁድ ነሃሴ 19 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚገኘው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መ.ኢ.አ.ድ/ ዋና ጽ/ቤት 33ቱ ፓርቲዎች ለጠሩት ህዝባዊ ውይይት የመኪና ላይ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ የፓርቲዎቹ አባላት በህገወጥ መንገድ ታስረዋል፡፡ አቶ ደመላሽ፣ አቶ አብርሃም ፣ አቶ አታላይ በለው፣ አቶ እዮብዘርና አቶ መላኩ መሰለ የተባሉት አባላት የቅስቀሳ መከናውን ከያዘው ሹፌርና ረዳት ጋር ታስረዋል፡፡ የፓርቲዎቹ አመራሮች […]

በመጪው እሁድ ነሃሴ 19 ቀን 2005 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ሊያደርግ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ወደ ጷጉሜ 3 መዘዋወሩን የአንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ግብረ ኃይል ማምሻውን አስታወቀ፡፡ ግብረኃይሉ እንዳስታወቀው የአዳማ ከተማ አስተዳደር ለአንድነት ፓርቲ በፃፈው ደብዳቤ ነሃሴ 19 በከተማው ስብሰባ በመኖሩና የሀይል እጥረትም ስላለበት አንድነት ሰላማዊ ሰልፉን እንዲያስተላልፍ ጠይቋል፡፡ አንድነት ፓርቲም የቀረበለትን ጥያቄ ከግምት በማስገባት ሰልፉን […]

ሀሙስ ነሃሴ 16 ቀን 2005 ዓ.ም የአንድነት ፓርቲ ተወካዮች ከሮቤ ከተማ ከንቲባ፣ ምክትል ከንቲባ፣ የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊና ከከተማው ካቢኔዎች ጋር 3 ሰዓት የፈጀ ውይይት አድርገዋል፡፡ ባለስልጣናቱ “አንድነት ሰላማዊ ሰልፉን ማድረግ አይችልም፤ እኛ ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ ስጋት አለብን፡፡ የቀድሞው ጠ/ሚር መለስ በፓርላማ እንደተናገሩት በአካባቢያችን የአልቃይዳ ክንፍ አለ” ብለዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ተወካዮች በበኩላቸው “በባሌ አካባቢ ያለውን የፀጥታ […]

በጥንቱ ስርዓት፣ አንድ ሰው ከአራቱ በአንዱ መንገድ ባሪያ ይሆናል። የመጀመሪያው በጦርነት ተሸንፎ ከተማረከ ፣ ሌላው እዳውን መክፈል አልችል ብሎ በእዳ ከተያዘ ፣ ሶስተኛው ከባሪያ ቤተሰብ የተወለደ ከሆነ በውርስ፣ አራተኛው ደግሞ ባሪያ ፈንጋዮች ይዘው ከሸጡት ነው። በዚህ ዘመን የባሪያ ንግድ ቢጠፋም፣ ባርነት ግን አልጠፋም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንዲያውም አምስተኛውን የባርነት መንገድ እያየን ነው፤ ይሄ ባርነት በባህሪው […]

በትናንትናው እለት ሁለት የአንድነት ፓርቲ የእስቀሳ ቡድን አባላት ፍቼ ከተማውስጥ ከፍተኛ ድብደባ እንደተተፈፀመባቸው መግለጻችን ይታወሳል፡፡ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል ሶስት ከተሞች “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ ለቅስቀሳ ወደ ፍቼ ካቀኑት የፓርቲው አመራሮችና አባላት መካከል ትላንት ነሃሴ 15 ቀን 2005 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ በከተማው የፀጥታ ዘርፍ ምክትል ሀላፊ […]

የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መርህ የአንድነት ፓርቲ የሚያደርጋቸዉን፣ አገረ ሰፊ ሰላማዊ እንቅስቃሴዎቹን በስፋት ገፍቶበታል። በኦሮሚያ በሚገኙ ሶስት ታላላቅ ከተሞች፣ አዳማ/ናዝሬት፣ ባሌ ሮቢና ፍቼ ሰላማዊ ሰልፎች እንደሚያደርግ፣ ለከተሞቹ ባለስልጣናት ያሳወቀ ሲሆን ፣ ቅስቀሳዎችንም በስፋት አያደረገ ነዉ። ከጥቂት ሰዓታት በፊት ፣ ሰላማዊ ሰልፉን ለማስተባበር ወደ ፍቼ ያቀኑ ሁለት የአንድነት ፓርቲ አሰተባባሪዎች በአገዛዙ ካድሬዎች ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው ሲሆን፣ […]

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ እሁድ ነሃሴ 19 ቀን 2005 ዓ.ም በአዳማ(ናዝሬት)፣ በባሌ ሮቤ እንዲሁም በፍቼ ለሚያደርጋቸው ሰላማዊ ሰልፎች ለሚመለከታቸው የመንግስት አካናት የማሳወቂያ ደብዳቤ አስገብቶ መጨረሱን የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ግብረኃይል አስታወቀ ፡፡ አንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል የጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ ህዝባዊ ተቀባይነቱና የተፅዕናኖ አድማሱ እየጨመረ መጥቷል፡፡ #Millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia

ወቅቱ በኦርቶዶክሳውያንና በኢትዮጵያውያን ካቶሊኮች ዘንድ የፍልሰታ ለማርያም የፆምና የሱባኤ ጊዜ ነው፡፡ በዚህ ለየት ባለ የሱባኤ ወቅት ለምንገኝ ወገኖች ፈጣሪ የልባችንን መሻት ተረድቶ የዘመናት ህልማችንን በቅርብ እውን ያድርግልን፤ የሚሳነው ነገር የለምና፡፡ ጸሎት ምህላችንን ሰምቶ ከነዚህ ሽል መንጣሪዎች፣ ከነዚህ የሰው ግርድ እና አመሳሶ አውጪዎች ይገላግለን፡፡ የእስላም የክርስቲያኑን ዕንባ ተመልክቶ ከነዚህ ሰው በላዎች ነጻ የምንወጣበትን መንገድ ያሳየን፡፡ በመካከላችን […]

የቁጫ ሕዝብ ጥያቄ ሕጋዊ ምላሽ እንዲያገኝ ጥሪ እናቀርባለን!!! ከአንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ (አንድት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ፓርቲያችን አንድነት ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆኑ ከሚታገልላቸውና ገዥው ፓርቲ ከወረቀት በዘለለ ያልተገበራቸው ሀገራዊ ቁምነገሮች ውስጥ ዜጎች ሳይሸማቀቁ በነፃነት ሃሳባቸውን የመግለፅ፣ በነጻነት የመደራጀት፣ በገዛ ሀገራቸው በነጻነት የመንቀሳቀስ፣ በፈለጉበት አከባቢ የመኖር፣ ሀሳባቸውንና አመለካከታቸውን በነጻነት የመግለጽ፣ የመደገፍ፣ የመቃወም፣ ስለመብታቸው ሳይሸማቀቁ የመጠየቅ […]

የአቶ አማረ አረጋዊ ጋዜጣ ብቻ እንዲዘግበው በተፈቀደው መሰረት በቀደም ሶማሊያ ላይ ተከስክሶ የሰዎች ሕይወት የጠፋበት አንቶኖቭ 12 የተባለው ሩሲያ ሰራሽ አውሮፕላን አደጋ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁለተኛው አደጋ መሆኑን እ.ኤ አ በኦገስት 11,2013 ባሰፈረው ዘገባው ይነግረናል።ሌሎች ይህን ቢዘግቡት ምስጢር በማባከን የ”ብሔራዊ ደህንነትን”ሆነ ብሎ አደጋ ላይ በመጣል ወይም በዚያ በፈረደበት የሽብርተኛ ፍርደ ገምድል ሕግ ዘብጢያ ይወርዱ ነበር።ያም […]

ሙስሊም ወንድሞቻችን ሁለት አመት ለሚጠጋ ጊዜ እየተገደሉ ነው። በጽናት፤ በጀግንነትና በብልሀት እናም በመስዋእትነት የመብት ትግላቸውን ቀጥለዋል። በለተ – አውዳመት ኢድ አልፈጥርም የመስዋእትነት ደማቸውን፤ …ኢትዮያን የተቆጣጠራት የትግራይ ዱር አራዊት መንጋ አፍሷል። የሞቱትን ሁሉ አላህ በጀነት ነፍሳቸውን ያኑር ከማለት በቀር ምን ይባላል ? ለሁሉም ወገኖቻችን ለቤተሰቦቻቸው፤ ለዘመዶቻቸው አላህ ጥናቱን ይስጥ እላለሁ። በከንቱ ለፈሰሰ ደማቸውም እሱ በማያልቅበት ስልጣኑ […]

የኢትዮጵያ አትሌቶች በሞስኮ እየተካሄደ ባለው በ14ኛው የዓለም አትሌክቲክስ ሻምፒዮን ውድድር ላይ ዛሬ አስደናቂ ውጤት አስመዘገበ፤ 1 ወርቅ፣ 2 ብር፤ እና 1 ነሃስ ያገኙ ሲሆን እውነትም አረንጓዴው ጎርፍ የሚለውን ስማቸውን አድሰዋል። በውጤቱም በወንዶች ማራቶን ኢትዮጵያውያን፤ 2ኛ ለሌሳ ደሲሳ, 3ኛ ታደሰ ቶላ, 4ኛ ጸጋዬ ከበደ እና 8ኛ የማነ ጸጋዬ የወጡ ሲሆን፤ በሴቶች 5000 ሜትር ሩጫ ደግሞ፤ 1ኛ […]

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ እንደተለመደው የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በመረጃና ደህንነት አገልግሎት ተሰናዳ ያለውን ‹‹ሸህ ኑሩን ማን ገደላቸው?›› በሚል ርዕስ ዶክመንተሪ አዘጋጅቶ አስተላልፏል፡፡ ይህ ዶክመንተሪ የገዥውን ፓርቲ ብፅእና ከመተረክም በላይ ጉልበተኝነትንና ፍረጃን ማእከል አድርጎ ከአኬልዳማ እና ከጃሀዳዊ ሀረካት የቀጠለ በፓርቲያችን እና በዜጎች ላይ የተቃጣ ህገ ወጥ የፕሮፓጋንዳ ስራ ነው፡፡ የመንግስትነት ስልጣን የያዘ አካል […]

አንድነት ፓርቲ የጀመረውን ህዝባዊ ንቅናቄ ለማስተጓጎል ከፍተኛ አበል በመክፈል ለአባላቱ ስልጠና ማዘጋጀቱን ለኢህአዴግ ቅርበት ያላቸው የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቆሙ፡፡ አንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል የጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ ህዝባዊ ተቀባይነት ማግኘቱንና በስኬት መቀጠሉን ተከትሎ ኢህአዴግ “አንድነት ፓርቲንና ንቅናቄውን እንዴት ማስቆም ይቻላል” በሚል በከፍተኛ አመራሮቹ ውይይት ካደረገ በኋላ በመላ ሀገሪቱ ፀረ አንድነት ፓርቲ ስልጠና […]

ትብብራችን የሙስሊሙ ማኅበረሰብ በህገ መንግሥቱ የተረጋገጠውን የእምነት ነጻነት መብቱን ተከትሎ ጣልቃ አትግብቡኝ ሲል ያቀረባቸውን ሦስት ጥያቄዎች በሚመለከት መንግሥት ከሰለጠነ የመፍትሄ ውይይት ፋንታ ከሚወስዳቸው ህገወጥ እርምጃዎችና ፍረጃ እንዲቆጠብ፣ በፈጠራ የሽብር ወንጀል ያሰራቸውን የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈታና ለጥያቄዎቹም ፍትሀዊ ምላሽ እንዲሰጥ የካቲት 05/2005 ባወጣነውና ሌሎች መግለጫዎች በተደጋጋሚ መጠየቁ ይታወሳል፡፡ ገዢው ፓርቲና መንግሥት ግን በሙስሊሙ ማኅበረሰብ፣ በሙስሊሙ […]

አገርን የሚመሩና የሚያስተዳድሩ ሰዎች የሚወስኗቸው ዉሳኔዎች፣ አገርን በማልማትም ሆነ በማጥፋት ረገድ ትልቅ አስተዋጾ አላቸው። ብዙዎች በአፋቸው «ፖለቲካን አንፈልግም። ፖለቲካ ውስጥ የለንበትም» ቢሉም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግን፣ የፖለቲካዉ አካል ናቸው። ፖለቲካዉ የማይነካዉ ማንም ዜጋ የለም። የፖለቲካ ስልጣን የያዙ በሙስና ከተጨማለቁ፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንደ ዜጋ ሊያገኝ የሚገባዉን አገልግሎት በሚገባ አያገኝም። ፖለቲካዉ ዜጎችን በዘር ከፋፍሎ ፣ «የዚህ […]

አገርን የሚመሩና የሚያስተዳድሩ ሰዎች የሚወስኗቸው ዉሳኔዎች፣ አገርን በማልማትም ሆነ በማጥፋት ረገድ ትልቅ አስተዋጾ አላቸው። ብዙዎች በአፋቸው «ፖለቲካን አንፈልግም። ፖለቲካ ውስጥ የለንበትም» ቢሉም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግን፣ የፖለቲካዉ አካል ናቸው። ፖለቲካዉ የማይነካዉ ማንም ዜጋ የለም። የፖለቲካ ስልጣን የያዙ በሙስና ከተጨማለቁ፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንደ ዜጋ ሊያገኝ የሚገባዉን አገልግሎት በሚገባ አያገኝም። ፖለቲካዉ ዜጎችን በዘር ከፋፍሎ ፣ «የዚህ […]