ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓ.ም የጎንደር ከተማ የገዢዉ ፓርቲ ካድሬዎችን ታላቅ አሳፋሪ አፈና ጥሶ በመሄድ ድምጹ በታላቅ ጀግንነት አሳምቷል። የአንድነት ድህረ ገጽ ላይ የወጣ በኦዶዮ የታጀበ ዝርዝር ሸገባ እንደ እንደሚከተለዉ አቅርበናል። እዚህ ይጫኑ !

የነገው አበባ ለምን ለፌደራል ፖሊስ ይሰጣል? ዳዊት ሰለሞን (ፍኖት ዘጋቢ) ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ.ም አበባ የሰው ልጆች በአንድ ድምጽ «ፍቅራችንን ወክልልን» በማለት የመረጡት ይመስል የፍቅርን አደራ ተሸክሟል፡፡ከሶስተኛው አለም እስከ አንደኛው የሚገኙ የአዳም ልጆች «አበባን» የፍቅር ስጦታ በማድረግ ለሚወዱት ይቸሩታል፡፡የሚወዱት ሲሞትባቸውም ፍቅራቸውን ለሟቹ ለመግለጽ አስከሬኑ ላይ አበባ ያኖሩለታል፡፡ ወደ ደሴና ጎንደር እንምጣ፣ ነገ ከሌላው ጊዜ […]

ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ.ም “ህገ መንግስት ተጥሷል !” ካልክ ድምጽህን በሰላማዊ ተቃውሞ አሰማ ! ይድረስ ትናንተም ሆነ ዛሬ ግፍ በነገሰባት ምድር፣ ኑሮን በመከራ ለምትገፋው ወገኔ ! ይድረስ መልካም አስተዳደር ጠፍቶ በደል ለተጫነብህ ፣ ፍትህ ርትዕ ተዛብቶ የአስተዳደር ሚዛኑ ኑሮህን ላጨለመው ወገኔ ! ይድረስ ከዲስኩር ባላለፈ “የእድገት ስላጣኔ መንገድ እየተጓዝክ ነው ” ለሚሉህ ፣ ይድረስ […]

ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ.ም በደሴ አካባቢ ከሚገኙ ከተሞች(ከወረባቡና ሐይቅ)፣ በነገው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ለመገኘት ወደ ከተማይቱ ለመምጣት ትራንስፖርት ያስፈልጋቸው የነበሩ ዜጎች፣ በከተማው አስተዳደር ስውር ትዕዛዝ መሰረት፣ ከዛሬ ምሽት ጀምሮ የትራንስፖርት መኪኖቹ ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆኑ መታዘዛቸውን የየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ለሰልፉ አዘጋጆች በመደወል እየገለጹ ነው፡፡ ሁኔታው ያሳዘናቸው ሰዎች በቻሉት መንገድ ሁሉ ወደ ሰልፉ […]

ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ.ም “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” የሚል መሪ ቃል በማንገብ ዕሁድ በሚካሄደዉ ህዝባዊ የተቃዉሞ ሰልፍ ላይ ሁሉም ተሳታፊ የሚከተሉትን ተግባራት ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ 1. ሰልፉን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማካሄድ፡፡ የተለያዩ ትንኮሳዎች ቢፈታተኑንም እንኳን ሰልፉ ስነ-ስርዓቱን በጠበቀ እና ጨዋነት በተሞላበት መልኩ ማካሄድ ይገባል፡፡ አንድ ጠጠር እንኳን ፍፁም መወርወር የለበትም፡፡ 2. የተመረጡ መፈክሮችን ብቻ […]

ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ.ም የአገዛዙ ካድሬዎች ላለፉት በርካታ ሳምንታት የአንድነት ፓርቲ እያደረገ ያለዉን ሰላማዊና ሕዝባዊ ቅስቃሳ ከግቡ እንዳይደርስ ለማድረግ፣ በአለቆቻቸው ታዘው የተለያዩ የአፈና እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ እንደነበረ በሰፊት ተዘግቧል። በርካታ ታሰረዋል፤ ወከባና እንግልትም ደርሶባቸዋል። ነገር ግን የአንድነት አባላትን ደጋፊዎች እንደዉም ሕዝቡ እግዚአብሄር የሰጣቸውን የዜግነት መብት ለማረጋገጥ ቀርተዉ የተነሱ ይመስላል። አፈናዉ የበለጠ እየጨመረ በመጣ ቁጥር የሕዝቡን […]

ሐምሌ 7 በጎንደርና በደሴ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተሳተፉ!! ድምፃችሁንም በአደባባይ አሰሙ!! ————————————————————– ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ ————————————————————– ፓርቲያችን አንድነት ህጋዊና ሰላማዊ መንገድ የሚታገል ፓርቲ በመሆኑ የሚያደርጋቸውን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ኃላፊነት በተሞላበት ህጋዊ አግባብ ሲተገብር ቆይቷል፡፡ ፓርቲያችን “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት/Millions of voices for freedom” በሚል መሪ ቃል የጀመረውም ህዝባዊ ንቅናቄ የህዝባችንን መሰረታዊ ጥያቄዎችን ያነገበ […]

ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ.ም ነገ እሁድ ጠዋት ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓ.ም. በጎንደር እና ደሴ ከተሞች ለሚደረገው ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተፈቅዶ ከፖስተር መለጠፍ፣ በራሪ ወረቀት ከመበተን በተጨማሪ በድምፅ ማጉያ ሰልፉን ያዘጋጀው አንድነት ፓርቲ ቅስቀሳውን እያደረገ ይገኛል፡፡ ይንንም ተከትሎ በተመሳሳይ ጊዜ በደሴ ከተማ አራዳ ገበያ ህንፃ አንድነት ፓርቲ ተከራይቶ ያለውን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አከራዩ እንዲያስለቅቁ […]

በአምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት የሐሰት ዉንጀላ ለእስር የተዳረገዉ ታዋቂዉና ተወዳጁ ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር ነጋ ዲያስፖራዉ በሀገር ዉስጥ እየተካሄደ ባለዉ ሠላማዊ ትግል ላይ በአካል ተገኝቶ እንዲሳተፍ መልዕክት አስተላለፈ፡፡ የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን በአካል ለመጠየቅ ቃሊቲ ለተገኙ ጋዜጠኞች እና የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሕዝባዊ ንቅናቄ የግብር ሃይል አባላት አደራ ሲል ባስተላለፈዉ መልዕክቱ ከአገር ዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ቀጣይ በሚካሄዱ […]

ጎንደሮች በሰልፉ ለመገኘት የትኛውንም ዋጋ እንከፍላለን እያሉ ነው! ሐምሌ 5 ቀን 2005 ዓ.ም በጎንደር የአንድነት አመራሮች ፖሊስ ካሜራ እየነጠቀ ነዉ ! ‹‹እኛ ሰላማዊ ታጋዮች ነን። የያዝነው ጥያቄ እንጂ መሳሪያ አይደለም» አቶ ዘካሪያስ የማነአብ ፣ የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ ———————————————————– በ30/10/2005 በጎንደር ሰላማዊ ሰልፍ ለማከናወን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ያቀረበውን ጥያቄ የከተማው አስተዳደር ባቀረቡት ጥያቄ […]

ሐምሌ 5 ቀን 2005 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ዞን ዋና ከተማ፣ ጎንደር፣ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓ.ም ለጠራው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ፣ ህዝቡ እንዳይገኝ ለማድረግ የከተማውና የዞኑ አስተዳዳሪዎች ከፍተኛ ውጥረትና ጭንቅ ላይ ናቸው፡፡ ይህንንም ተከትሎ ከፍተኛ አመራሮቹ የብአዴን/ኢህአዴግ አባላትንና የዞኑ የየወረዳው አመራሮችን በከተማው መምህራን ማኀበር አዳራሽ ትናንት ሐምሌ 4 ቀን 2005 […]

ሐምሌ 5 ቀን 2005 ዓ.ም – የደሴ ከንቲባ «ሰልፉ ይተላለፍ አሉ»። በጽሁፍ እስካልቀረበ ድረስ አንድነት ጥያቄዉን ዉድቅ አደረገው! – በጎንደርና በደሴ ለፌደራልና ለክልል ፖሊሶች አበባ ይበረከታል! የደሴ ከንቲባ ሰልፉ ለሳምንት እንዲራዘም ጠየቁ። ነገር ግን የአንድነት አመራር አባላት ሕጉ እንደሚፈቅደው በጽሁፍ እስካልቀረበላቸው ድረስ ከንቲባዉ በቃል የጠየቁትን እንደማይቀበሉ አረጋግጠዉላቸዋል። በጎንደር የከተማዋ አስተዳዳሪዎች «ሕዝቡ እናንተን አይሰማም። አምሳ ሰው […]

ሐምሌ 4 ቀን 2005 ዓ.ም ደሴ በፖለቲካ ቅስቀሳ ተናውጣላች። በአንድ በኩል፣ አንድነት ሕዝቡ ሕገ መንግስታዊ መብቱን የመጠቀም ፣ ሃሳቡን በነጻነት የመግልጽ፣ መሪዎቹን በፈለገ ጊዜ የመሾምና የመሻር መብት እንዳለው እያስተማረ፣ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለዉን የግፍ ቀንበር በመቃወም፣ እግዚአብሄር የሰጠዉን፣ የአለም አቀፍ ሕግ ሆነ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት የፈቀደለትን መብት በመጠቀም ደሴዎች ድምጻቸውን እንዲያሰሙ በላወድ ስፒከር እየቀሰቀሰ ነዉ። […]

ሐምሌ 4 ቀን 2005 ዓ.ም አንድነት ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ የከተማው መስተዳደሮችና የፀጥታ ኃይሎች ፓርቲው ህጋዊ የማሳወቅ ስራውን መስራቱን ገልፀው ሰልፉን መከልከል እንደማይችሉ ካረጋገጡ በኋላ፣ በከተማው ያሉ የቀበሌ ሰራተኞች መደበኛ ስራቸውን ጥለው በሰላማዊ ሰልፉ ዙሪያ በየቤቱ እየዞሩ ማስፈራራትና ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ማንም እንዳይገኝ፣ ሰልፉ ህገወጥ ነው በሚል ቅስቀሳ እየሰሩ መሆናቸውን ከስፍራዉ የደረሱ ዜገባዎች ይጠቁማሉ።፡ «ነዋሪው […]

ሐምሌ 3 ቀን 2005 ዓ.ም የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላት፣ በጎንደርና በደሴ የሚያደርጉትን ቅስቀሳ ቀጥለዉበታል። በደሴ ወረቀቶች እየተበተኑ፣ ፔትሽኖችም እየተሞሉ ሲሆን፣ በመኪና ላይ በመሆንና በየሰፈሩ በመዘዋወር በላውድ ስፒከር የትግል ጥሪ እየተላለፈ ነዉ። እንደዚያም ሆኖ ግን ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ፣ ባህሪዉ ነዉና፣ አፍራሽ እርምጃዎችን ከመዉሰድ አልተቆጠበም። ላለፉት ሃያ አመታት እንዳደረገዉ፣ የሕዝብን መሰረታዊ የዴሞክራሲ ጥያቄዎችንና ሕገ መንግስታዊ መብቶች ለማፈን […]

በደቡብ ክልላዊ መንግስት ጋሞጎፋ ዞን የምትገኘው ቁጫ ወረዳ ሰላም በር ከተማና አካባቢዋ ላለፉት ሁለት ቀናት በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ስትታመስ መቆየቷን የፍኖተ ነጻነት ምንጮች ከስፋራው አጋልጠዋል፡፡ እንደ ምንጮቻችን ዘገባ በቁጫ ወረዳ የሚገኙ ከ200.000የሚልቁ ነዋሪዎች ያለ ፍላጎታቸው በጋሞጎፋ እንዲጠቃለሉ መደረጋቸውን ሲቃወሙ ቆይተዋል፡፡‹‹እኛ ጋሞ ወይም ወላይታ አይደለንም››በማለት የማንነት ጥያቄ ያነሱት ቁጫዎች የራሳችን ቋንቋና ከጋሞም ሆነ ከወላይታ የሚለየን ባህል […]

የአንድነት ፓርቲ የህዝባዊ ንቅናቄ ግብረሀይል፣ የሶሻል ሚዲያ ኮሚቴ አባላት የነፃነት ታጋዮቹን አንዱአለም አራጌንና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጎበኙ፡፡ የሶሻል ሚዲያ አባላቱ ትላንት በቃሊቲ እስር ቤት ባደረጉት ቆይታ የአንዱአለም እና የእስክንድር መንፈሳዊ ጥንካሬ እንዳስደሰታቸው ለፍኖተ ነፃነት ተናግረዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት የነፃነት ታጋዮቹ አንዱአለም አራጌና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አንድነት ፓርቲ የጀመረውን ህዝባዊ ንቅናቄ አበረታች መሆኑን አስምረው ሁሉም ኢትዮጵያዊ በንቅናቄው […]

ባለፈው ጊዜ ኣንድ ወንድማችን በኣልጃዚራ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ “እኔ በመጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ…” በማለታቸው ኣንዳንድ ነቀፌታዎችን እየሰማንና እያነበበን ነው። ነገሩ ግን ኣዲስ ኣይደለም። በኢትዮያ ውስጥ የባህል ቡድን ፖለቲካ ከተጀመረ ጀምሮ ኣንዳንድ ወገኖች በስሜትና በእልህ ይህን ሲግልጹት ይታያል። እንዴውም ኣሁን ትንሽ ረገብ ያለ ይመስላል።የሆነ ጊዜ በጣም ጦፎ ነበር። የዚህች ጽሁፍ መነሻ ታዲያ በፍጹም ግለሰቡን በመንቀፍ […]

የመጽሐፉ ርዕስ፦ የብርሃን ልክፍት(ስብስብ ግጥሞች) ደራሲ፦ ዮሐንስ ሞላ የሽፋን ምስል ዳዊት አናጋው ገጽ፦108 የተካተቱት ግጥሞች፦72 ዋጋ፦ 28 ብር (18 ዶላር) ብዙ ጸሀፍያን (ገጣምያን) የራሳቸው የአፃጻፍ ዘይቤ እንዳላቸው ሁሉ ፤ ዮሐንስ ሞላም የራሱን ዘይቤና ስልት ይዞ በኢትዮጵያ ሥነ-ጽሁፍ መድረክ ብቅ ያለ ወጣት ገጣሚ ነው። ከሚያነሳቸው ጭብጦች፣ በአጭር ግጥሞች ጥልቅ መልዕክቶችን ከመግለጹ እና ዘለግ ባሉ ስንኞች ቃላትን […]

በአዲስ አበባ የፀረ ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ የሚጠይቅ በራሪ ወረቀት የበተነ የአንድነት አባል በአደራ ታሰረ፡፡ አንድነት ፓርቲ ‹‹የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት›› በሚል መሪ ቃል የጀመረውን ህዝባዊ ንቅናቄ አጠናክሮ መቀጠሉን ተከትሎ መንግስት የማደናቀፍ ተግባሩን በአዲስ አበባም ጀምሯል፡፡ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፁት ሙሉጌታ ተፈሪ የተባለውን የአንድነት ፓርቲ የወረዳ 15 አባል ካዛንችስ አካባቢ በህገወጥ መንገድ በፖሊስ ታስሯል፡፡ ሙሉጌታ […]

አንድነት ፓርቲ የሶስት ወራት ህዝባዊ ንቅናቄ የትግል ስልት በመንደፍ የመጀመሪያውን የአደባባይ ላይ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ሰኔ 30/10/2005 በጎንደር ከተማ እንደሚያደርግ ማሳወቁ የሚታወስ ነው፡፡ ሁልጊዜም የሀገሪቱን ህግ ጠብቆ በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሰው ፓርቲያችን የአገሪቱ ህገ መንግስት አንቀፅ 30ና የሰላማዊ ሰልፍ አዋጅ 50ኛ ዓመት ቁጥር 4 በሚደነግገው መሰረትም ከህዝቡ ጋር የሚያደርገውን ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር ከተማ ማወቅ ለሚገባው አካልና […]

የሰሜን ጎንደር የአንደነት አመራሮችን ማሰር ቀጥሏል ዛሬ ዞኑ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ አለላቸው አታለለ ህገወጥ እስር ተፈፅሞባቸዋል፡፡ የክልሉ መንግስት በሚፈፅመው ህገወጥ እስርና እንግልት አንድነት ሰላማዊ ሰልፉን እንደማያስሰርዘው ገልጧል፡፡ አንድነት በጎንደር የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማደናቀፍ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው የክልሉ መንግስት የሰሜን ጎንደር አንድነት የፓርቲውን አመራሮች የማሰር ዘመቻ ጀምሯል፡፡ በዚህም መሰረት ዛሬ አቶ አለላቸው አታለለ በህገወጥ መንገድ ታስረዋል፡፡ […]

ትናንትና ማታ ከአስራ ስድስት ሰዓት ስራ በሗላ ለደከመው ሰውነቴ እረፍት ለመስጠት በጥድፊያ ነው ወደ አልጋዬ የሄድኩት። በርግጥም ጅርባዬ አላጋዬ ላይ እንዳረፈ ነው ጭልጥ አድርጎ እንቅልፍ የወሰደኝ። መጥፎነቱ ስልኬን ማጥፋት ረስቼ ኖሮ ስልኬ ሊረብሸኝ የጀመረው ብዙም ሳይቆይ ነበር። ጭህቱን ለመርሳት ሞክሬ ስላልተቻለኝ ልጠረቅመው ስልኩን ማንሳት ነበረብኝ። ቁጥሩን ሳየው ያገር ቤት ስልክ ስለነበር ደስ ሳይለኝ አንስቼ ማውራት […]

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ‹‹የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነት››በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ ንቅናቄ ይፋ ማድረጉና የንቅናቄው የመጀመሪያ የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር ከተማ ሰኔ 30 ቀን 2005 ዓ.ም ለማድረግ በህገ መንግስቱ መሰረት ለሚመለከተው አካል የማሳወቂያ ደብዳቤ በማስገባት የቅስቀሳ ስራውን በጎንደርና አካባቢው መስራት ቢጀምርም መንግስት ህገወጥ እስር እያካሄደ ይገኛል፡፡ ለቅስቀሳ ስራ ወደ ምዕራብ አርማጭሆ ተንቀሳቅሰው የነበሩ አራት የፓርቲው […]

ያለ መታደል ጎንደርን በአካል አላውቃትም። ነገር ግን እንደ ማንም ኢትዮጵያዊ በልቤ ዉስጥ ልዩ ቦታ አላት። ያለ ጎንደር ኢትዮጵያ የምትባል አገር ትኖር ነበር ለማለት ያስቸግራል። ግራኝ መሃመድ በቱርኮች እየተረዱ፣ አብዛኛዉ የኢትዮጵያን ክፍል ተቆጣጥረዉ በነበረ ጊዜ፣ ስመ ጥሩ ያልነበሩ፣ ብልሹዉ የሸዋ ንጉስ፣ አጼ ልብነህ ድንግል ይሞታሉ። አጼ ገላዉዲዮስ ይተኳቸዋል። የግራኝ ጦር በመጠንከሩ ሽሽት ወደ ሰሜን፣ ወደ ጎንደር […]

በአሜሪካ ዴንቨር ከተማ ከቤተሰባቸው ጋር የሚኖሩት አቶ ታምራት ላይኔ የጋዝ እስቴሽን በመክፈት በንግድ ስራ መሰማራታቸውን ምንጮች ገለፁ። በሙስና ወንጀል ተከሰው ለአስራ ሁለት አመት ታስረው የወጡት አቶ ታምራት ከተፈቱ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ፥ አማኝ ሆነው እንደሚቀጥሉና ነገር ግን በማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከማንም ፖለቲካ ድርጅት ጋር ሳይወግኑ ለአገር ይጠቅማል የሚሉትን ሃሳብ እንደሚያካፍሉ፣ መፅሃፍ እንደሚያዘጋጁ…ገልፀው […]

አቶ ስዬ አብርሃ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አሰከባሪ ተቋም ውስጥ በወታደራዊ አማካሪነት በጥሩ ደመወዝ መቀጠራቸውን ምንጮች ጠቆሙ። በሙስና ወንጀል ተከሰው ከወንድሞቻቸው ጋር ለስድስት አመት ታስረው የተፈቱት ስዬ በተፈቱ ማግስት የአሜሪካን ድምፅ ራዲዬን ጨምሮ ለተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ « ፖለቲካ ከልጅነቴ ጥርሴን የነቀልኩበትና አብዛኛው እድሜዬን ያሳለፍኩበት በመሆኑ ከትግሉ መድረክ ልርቅ ጨርሶ አልችልም» በማለት አስረግጠው መናገራቸውን […]

አንድነት በየትኛውም የመንግስት ህገወጥ ጫና ሰልፉን እንደማይሰርዝ ይፋ አድርጓል በጎንደር ቅስቀሳ ላይ የነበሩ 4 የአንድነት አባላት በፖሊስ መታሰራቸው በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ቁጣን ቀሰቀሰ፡፡ አንድነት ምንም አይነት ህገወጥ እስር በጎንደር የተዘጋጀውን የተቃውሞ ሰልፍ እንደማያስቆመው አሳውቋል፡፡ ዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2005 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ምዕራብ አርማጨሆ በጎንደር ሰኔ 30 የሚደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ የሚመለከት በራሪ ወረቀት በማሰራጨት ላይ […]

አንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበር በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን 30ኛው አመት የስፖርትና የበዓል ዝግጅት ወቅት July 5 2013 ከ 11:30 AM ጀምሮ -እስከ 2:00 PM በDoubleTree Hotel Silver Spring ሜሪላንድ ሕዝባዊ ስብሰባ ያደርጋል፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ አቶ ብርሃነ መዋ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳዮች፤ በፖለቲካ ሃይሎች አሰላለፍ ዙሪያ ፤ እንዲሁም በአገራዊና ወቅታዊ አሳሳቢ ክስተቶች ላይ […]

ሽማግሌው ስብሃት ነጋ ከጥቂት ቀናት በፊት በሰጡት ቃለ-ምልልስ አስበውት ይሁን ሳያስቡት “እውነት” አምልጧቸዋል። አጥብቀው ያነሷቸው የሙስና ጉዳዮች ራሱን የቻለ « አላማና ግብ » አላቸው። የመጀመሪያው በፓርቲያቸው ውስጥ ያለው ክፍፍል (የጥቅም) እንደተዳፈነ እሳት ውስጥ ለውስጥ እየተብላላ መሆኑን በግልፅ ያሳያል። ከተናገሩት የሚከተለውን እንመልከት፤ « .በጤናማ ሁኔታ የሚገኙ ሰዎችን እንቆርጣለን፣ እናስራለን ወዘተ እያሉ ሲያስፈራሩ የነበሩ የፖለቲካ፣ የመንግስት ሰዎች […]

ከሁለት ሣምንት በፊት ኢትዮ- ሲቪሊቲ ፓልቶክ ባዘጋጀው የጋዜጠኞችና የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች ውይይት ላይ ኢሣትን በመወከል ተሳትፌ ነበር። በክፍሉ ታዳሚ ከነበሩት ከ 500 በላይ ተሳታፊዎች መካከል በጣም የሚበዙት የኢሳት ደጋፊዎች መሆናቸውን ሳይ ደስታ ሳይሰማኝ አልቀረም። ከደስታው ባሻገር የተሰማኝ ሌላ ስሜት ግን፦” ሰው እንደዚህ ሲደግፋችሁ፤ የበለጠ በርትቻችሁና ጠንክራችሁ መሥራት አለባችሁ” የሚል አደራዊ ሸክም ነው። ደጋፊዎቻችን የመብዛታቸውን ያህል […]

የግርጌ ማስታዎሻ : ከዘጠኝ አመት በፊት ያጣሁት አንድ ወንደም ነበረኝ ፣ ጋዜጠኛና ደራሲ መጽሐፈ ሲራክ የሚባል። መጽሐፈ የሃገር ፍቅር ልክፍቱን ብቻ አልነበረም ጥሎብኝ እስከ ወዲያኛው ያሸለበው ፣ የዘመናቸን ታላቅ የጥቁር ህዝብ የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላን አበክሬ እንዳውቀው የረዳኝ ፣ ለነጻነት ክብር ለዲሞክራ ከቆሙት ጎን እንድቆም ፣ ሰብአዊ መብት ሲዳጥ ዝም እንዳልል፣ የግፉአንን ድምጽ እንዳሰማ የህይወትን […]

1.ብዜ ግዜ የአቶ አያልሰው ደሴ ጽሁፎች ረዣዥሞች ስለሆኑ፤ እንዲሁም ክፍል ስለሚበዛቸው (1፣ 2፣ 3፣ 4፣ … )፤ ርእሳቸውን ብቻ እያየሁ አልፋቸው ነበር። በዚህ በአባይ ጉዳይ ግን የጻፉት አነበብኩት። ጽሁፉ በርስ በርስ ቅራኔ የሚንተከተክና በኢህአዴግ የአባይ ግድብ ማጭበርበሪያ ዘመቻ ዙሪያ ያለውን ተቃውሞ በቅጡ ያልዳሰሰ፡ ይልቅስ ሌሎችን ተቺዎች በሚከስበት ደዌ ክፉኛ የታመመ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። በተጨማሪም ጽሁፉ የአካባቢውን […]

(ሰኔ 13/2005) በጽ/ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሳወቀው ለ3 ወራት የሚዘልቅ “ሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” የተሰኘ ሕዝባዊ ንቅናቄ አውጇል። ሕዝባዊ ንቅናቄው የአዳራሽ ስብሰባ፣ የተቃውሞ ሰልፍ እና የፀረሽብር ሕጉ እንዲሰረዝ የሚጠይቅ ፊርማ (ፒቲሽን) ይሰበሰባል። በዚህም በአዲስ አበባ 6 እና በክልል ደግሞ ለመጀመሪያ ዙር ዐሥር ስብሰባዎች ይካሄዳሉ። የንቅናቄው ዓላማ የፀረሽብር ሕጉ እንዲሰረዝ፣ የዜጎች መፈናቀል እና የመሬት መቀራመት እንዲቆም፣ የሥራ […]

የሕወሐት አባልና የአገር ውስጥ ደህንነት ዋና ሃላፊ አቶ ወልደስላሴ ከስልጣናቸው እንዲነሱ መደረጉን የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። ወ/ስላሴ ከስልጣን እንዲነሱ ያደረጉት የደህንነት ዋና ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ መሆናቸውን ምንጮቹ ጠቁመዋል። የሁለቱ ሹማምንት ፀብ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ ቆይቶ መጨረሻ መፈንዳቱ ታውቋል። በመቀሌ በተካሄደው የፓርቲው ጉባኤ አቶ ጌታቸው የፓርቲው ማ/ኮሚቴ አባል ሆነው እንዳይመረጡ ሰፊ ቅስቀሳ ሲካሂድ የቆየው ወ/ስላሴ በመጨረሻም […]