ሰበር ዜና፤ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ የታሰሩት የአንድነት ፓርቲ አባላት ቁጥር 15 ደረሰ – ፍኖተ ነጻነት
አንድነት ፓርቲ ነገ ነሃሴ 5, 2005 ዓ.ም ሜክሲኮ በሚገኘው የመብራት ሃይል አዳራሽ ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ 12 የፓርቲው አባላትና ሁለት መኪኖች መስቀል አደባባይና ሳሪስ አካባቢ ህገወጥ እስር ተፈፅሞባቸዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችም አባሎቹ ወደ ታሰሩባቸው ፖሊስ ጣቢያዎች አምርተዋል፡፡ ቀደም ሲል አዲሱ ገበያ አካባቢ 3 አባላት ተይዘው የነበረ ሲሆን እስከ አሁኗ ሰአት ድረስም 15 የአንድነት ፓርቲ አባላት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ፡፡
#Millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ #ADDISABABA