በባህርዳሩ የሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ የቀጠለ ሲሆን በወላይታ ዞን የአንድነት አመራር ታስረዋል – ፍኖተ ነጻነት
በባህርዳር ከተማ እሁድ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም. የሚደረገው የተቃውሞ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል በመላ ሀገሪቱ የጀመረውን ህዝባዊ ተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አባላቱ በከተማዋ በተሸከርካሪ መኪና እና ድምፅ ማጉያ በመታገዝ አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ ከድምፅ ቅስቀሳው ጎን ለጎን በከተማዋ ፖስተሮች የመለጠፍና በራሪ ወረቀቶችንም የመበተን ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ እሁድ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ የሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ መነሻውን የፓርቲው ጽህፈት ቤት ከሚገኝበት ግሽ አባይ ቀበሌ ፊትለፊት በማድረግ በጊዮርጊስ ቤተክርስቲን ፣ ጊዮን ሆቴል፣ ሙሉዓለም አዳራሽ በማድረግ መዳረሻው መስቀል አደባባይ እንደሆነ ፓርቲው አስታውቋል፡፡የባህርዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ቀጥሏል በባህርዳር ከተማ እሁድ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም. የሚደረገው የተቃውሞ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል በመላ ሀገሪቱ የጀመረውን ህዝባዊ ተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አባላቱ በከተማዋ በተሸከርካሪ መኪና እና ድምፅ ማጉያ በመታገዝ አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ ከድምፅ ቅስቀሳው ጎን ለጎን በከተማዋ ፖስተሮች የመለጠፍና በራሪ ወረቀቶችንም የመበተን ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ እሁድ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ የሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ መነሻውን የፓርቲው ጽህፈት ቤት ከሚገኝበት ግሽ አባይ ቀበሌ ፊትለፊት በማድረግ በጊዮርጊስ ቤተክርስቲን ፣ ጊዮን ሆቴል፣ ሙሉዓለም አዳራሽ በማድረግ መዳረሻው መስቀል አደባባይ እንደሆነ ፓርቲው አስታውቋል፡፡
በተያያዘ ዜና ደግሞ የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን አመራር የሆኑት ወ/ሮ ሀድያ መሀመድ የቅስቀሳ ወረቀት ሲበትኑ በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል፡፡ በወላይታ ሶዶ አፈናው በርትቷል፡፡#millionsofvoicesforfree #Ethiopia #UDJ