የኢትዮጵያ አትሌቶች በሞስኮ እየተካሄደ ባለው በ14ኛው የዓለም አትሌክቲክስ ሻምፒዮን ውድድር ላይ ዛሬ አስደናቂ ውጤት አስመዘገበ 1 ወርቅ፣ 2 ብር፤ እና 1 ነሃስ አገኙ፤ እውነትም አረንጓዴው ጎርፍ!!
የኢትዮጵያ አትሌቶች በሞስኮ እየተካሄደ ባለው በ14ኛው የዓለም አትሌክቲክስ ሻምፒዮን ውድድር ላይ ዛሬ አስደናቂ ውጤት አስመዘገበ፤ 1 ወርቅ፣ 2 ብር፤ እና 1 ነሃስ ያገኙ ሲሆን እውነትም አረንጓዴው ጎርፍ የሚለውን ስማቸውን አድሰዋል። በውጤቱም በወንዶች ማራቶን ኢትዮጵያውያን፤ 2ኛ ለሌሳ ደሲሳ, 3ኛ ታደሰ ቶላ, 4ኛ ጸጋዬ ከበደ እና 8ኛ የማነ ጸጋዬ የወጡ ሲሆን፤ በሴቶች 5000 ሜትር ሩጫ ደግሞ፤ 1ኛ መሰረት ደፋር፣ 3ኛ አልማዝ አያና 5ኛ ብዙ ድሪባ አሸናፊ ሆነዋል፡፡ በአጠቃላይ በዛሬው እለት ብቻ 1 ወርቅ ፣ 2 ብር እና 1 ነሀስ በድምሩ 4 ሜዳሊያዎችን በመጨመር ኢትዮጵያ ከራሺያ፤ ከአሜሪካ፤ ከጃማይካ እና ከኬንያ በመቀጠል በ6ኛነት በ3 ወርቅ፣ 3 ብር እና 4 ነሀስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በማግኝት የኢትዮጵያ ባንዲራ በሞስኮ ስታዲዮም ከፍ ብሎ እንዲወለበለብ ላደርጉት ብርቅዬ አትሌቶቻችን ከፍተኛ ምስጋና እያቀረብን፤ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እና አትሌቶቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!! እንኳን ደስ አለን። አቡጊዳ
የአትሌቶቻችን ውጤት፤
ማራቶን፤ ወንዶች
2 417 ለሌሳ ደሲሳ 2:10:12
3 430 ታደሰ ቶላ 2:10:23
4 425 ጸጋዬ ከበደ 2:10:47
8 431 የማነ ጸጋዬ 2:11:43 SB
5000 ሜትር ውጤት፤ ሴቶች
1 329 መሰረት ደፋር 14:50.19
3 327 አልማዝ አያና 14:51.33
5 332 ብዙ ድሪባ 15:05.38

