ዜና ከአዳማ – ፖሊስ 4 የአንድነት አባለትን በማሰር የሚበትኑትን ወረቀት ነጠቀ

በቅስቀሳ ስራ ላይ የነበሩ አራት የአንድነት ፓርቲ አባላት አዳማ ከተማ ውስጥ መታሰራቸው ታወቀ፡፡ ፖሊስ ከ5ሺ በላይ በራሪ ወረቀቶችን ቀምቷቸዋል፡፡ ፖሊስ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ እውቅና ተሰጣችሁ እንጂ በራሪ ወረቀት የመበተን ፍቃድ የላችሁም በሚል ዳንኤል ፈይሳ፣ደረጄ መኮንን፣አስናቀ ሸንገማና ደረጄ ክበበው የተባሉት አባላት ወረዳ አንድ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ታስረው ከሰዓታት በኋላ መለቀቃቸውን የቅስቀሳ ቡድኑ አባላት አስታውቀዋል፡፡ ከትራፊክ ፖሊስ፣ከፖሊስ፣ከደህንነት፣ከደንብ አስከባሪና ከሚሊሻ የተውጣጡ ስምንት ግለሰቦች የአንድነት አባላትን በማሰሩ ተግባር እንደተሳተፉና የተወሰኑት ደህንነቶችና ፖሊስ የድብደባ ሙከራ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡
የአንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ በአዳማ ከተማ ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ ስኬታማ የቅስቀሳ ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡ #Millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ934939_487240494685925_524628143_n