የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አመታዊ ስብሰባውን እያከናወነ በሚገኝበት ሰዓት በተለያዩ አነጋጋሪ ክስተቶች መታጀቡን የፍኖተ ነጻነት ምንጮች ገልጸዋል፡፡ የሲኖዶሱ ስብሰባ ከመጀመሩ አስቀድሞ የፌደራል መንግስት ጉዳዩች ሚኒስትር ተወካዩች በተገኙበት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰዎች፣የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎችና ጳጳሳት በተገኙበት በተካሄደ ውይይት ጳጳሳቱ የመንግስት ተወካዩች ላቀረቡት ሐሳብ ያላቸውን ልዩነት በመግለጽ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ እጁን እንዲሰበስብና ለህገ መንግስቱ ተገዢ እንዲሆን […]

በደቡብ ኦሞ ጂንካ ከተማ በ2003 ዓ.ም የተሰራ ሁለገብ ስታዲየም መፍረሱ ተሰማ፡፡ ስታዲየሙ ለ13ኛው የአርብቶ አደር ጉባኤ ወደ ዞኑ ላቀኑት የቀድሞ ጠ/ሚ/ር አቶ መለስ ዜናዊ ጉብኝት እንዲደርስ ተብሎ የተወጠነ እንደ ነበር ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በዚህ ሁኔታ ጥር 13 ቀን 2003 ዓ.ም የዋለው የአርብቶ አደር ቀን በስታዲየሙ እንዲከበር ለማድረግ ስራው ሙሉ በሙሉ በ20 ቀናት ውስጥ እንደተጠናቀቀ ለማወቅ ተችሏል፡፡ […]

ጥቂት ቀደም ሲል “አጼ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ በደራሲ ተስፋዬ ገ/አብ አይን” በሚል ርእስ በለቀቅሁት ጽሁፍ ሳቢያ በርካታ አንባቢያን የተለያዬ አስተያየት ልከውልኛል። አንዳንዱ “ይህን እየወጣ ያለ ደራሲ ወደታች ባትጎትተው ምናለ?” ሲል ሌሎችም “አበጀህ” ብለውኛል። መጽሃፍትን አነባለሁ ብዬ አስባለሁ–በተለይ የአማርኛ ስራዎችን። አሁን አሁን የሚወጡትን ካልሆነ በቀር ብዙም ያመለጠኝ ስራ አልነበረም። አንድ መጽሃፍ አጀማመሩ ካላስደሰተኝ ለመጨረስ ራሴን […]

‹‹ሀገሬ ናይጄሪያ ኢትዮጵያን ለማሸነፍ ምትችልበት ብቸኛው መንገድ አንድም ጸሎት አሊያም ዕድል ነው፡፡›› የቀድሞው ዝነኛውና ኮከብ የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች የሆነው ካኑ ለአንድ ታዋቂ የስፖርት ድረ ገጽ በሰጠው አስተያየት ነበር እንዲህ ያለው፡፡ በጨዋታው ላይ የሆነው ሁሉ እንዳለ ሆኖ በእውነትም ካኑ እንደገመተው የናይጄሪያዎቹ ፈጣን ንስሮች ‹‹በጸሎትም ወይም በዕድል›› ሊባል በሚችል ሁኔታ የኢትዮጵያ አቻዎቻቸውን 2-1 በማሸነፍ ለ2014 የብራዚሉ […]

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ካለፈው ስህተታቸው በመማር ከአጉልና ማስረጃ አልባ ፍረጃ እንዲላቀቁ አሳሰበ። ፓርቲው ከትናንት በስትያ ባወጣው መግለጫ እንደገለፀው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ባለፈው ሳምንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በመሪ ደረጃ በማይጠበቅ መልኩ የአንድነትን እንቅስቃሴ ስም ለማጥፋት በመሞከራቸው ከዚህ ድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል ብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የራሳቸው አጀንዳ የላቸውም፣ የሻዕቢያ መልእክት አድራሾች […]

ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ በሀገራችን ላይ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲሰፍንና ፍትሃዊነት እንዲኖር በቁርጠኝነት እየታገለ ይገኛል፡፡ በትግሉ ውስጥም ፓርቲያችን የተጋረጡበትን ፈተናዎች እየተወጣና የሚከፈለውን ዋጋ እየከፈለ ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ በመቀጠል ለህዝቡ ያለውን ታማኝነት እያረጋገጠም ነው፡፡ ፓርቲያችን በመላ ኢትዮጵያ ያለውን አደረጃጀት በመጠቀምና ሕዝቡን በማሳተፍ ለሶስት ወራት የሚቆይ ህዝባዊ ንቅናቄ በማካሄድ የመጀመሪያ ዙር የሆነውን ሰላማዊ […]

33 ፓርቲዎች እየተባሉ የሚጠሩት በ15/02/ 05 የአዳማ ፔቲሽን ተብሎ የሚጠራውን የፈረሙ ናቸው፡፡ የጋራ ስምምነት ሰነድ የፈረሙት 24 ፓርቲዎች ሲሆኑ ጥቅምት 10 ቀን በዋለው ስብሰባቸው ወደ ቅንጅት አድገዋል፡፡ እሁድ በተደረገው ስብሰባቸው የመተዳደሪያ ደንብ፣ የመመስረቻ ፅሁፍና መለስተኛ የድርጊት ፕሮግራም በመፈረም “ትብብር ለዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ/ ትብብር/ በሚል ተሰይመዋል፡፡ በዚህ ውስጥ የተካተቱት 10 ፓርቲዎች ብቻ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ያልተካተቱበት ምክንያት ተብራርቷል፡፡ […]

አብረሃ ጅራ እና አብደራጊ የተባሉ ሁለት ወረዳዎች ከዚህ በፊት በአማራ ክልል ስር ነበሩ፡፡ ነገር ግን መሬቱ ባብዛኛው በቅርብ ጊዜ ከትግራይ ክልል በመጡ ገበሬዎች ተይዟል፡፡ ገበሬዎቹም አስተዳደራዊ የበላይነትን በመጠቀም ወረዳዎቹን ወደ ትግራይ ለማካለል እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተጠቁሟል፡፡ ጥቅምት 5 ቀን 2005 ዓ.ም በዋለው ስብሰባ የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ የጀመሩ ሲሆን ከ500 ሺህ ብር በላይም ለጉዳዩ ማስፈፀሚያ ማዋጣታቸው ተጠቁሟል፡፡ […]

እንደ መንደርደሪያ የሁለት ሺህ ስድስት ዓመተ-ምህረት የመጀመሪያ ወር ተጠናቅቋል፤ አዳዲስ ክስተቶችም ታይተዋል፤ ያለፉት አስራ ሁለት ዓመታትንበጃንሆይ ቤተ-መንግስት ያሳለፉት ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ፣ በኦህዴዱ ሙላቱ ተሾመ መተካታቸው አንዱ ነው፡፡ አባይ ፀሀዬና ዶ/ር ካሱ ኢላላም ከበረከት ስምዖንና ኩማ ደመቅሳ በተጨማሪ በሚኒስትር ማዕረግ የኃ/ማሪያም ደሳለኝ ‹‹የፖሊሲና ጥናት ምርምር›› አማካሪ ሆነው መሾማቸው ሌላው ነው (በነገራችን ላይ ሹመቱን እንደተለመደው አይቶ ችላ […]

ባለፈው ሣምንት የሆነ ነገር ጽፌ በአንዳንድ የዘመኑ የዴሞክራሲ ነፋስ በገባቸው ድረ-ገፆች ማስነበቤ ይታወሳል፡፡ ያ ጦማሬ በተቃውሞው ጎራ ተሰልፈው እየታገሉ ለሚገኙ የተወሰኑ አካላትና ለላንቲካውና ለመናጆነትም ቢሆን ለአንድ አካሄዱ ‹ያስፈራኝ› ግለሰብ የተላከ ነበር፡፡ መልስ ስጠብቅ አንድ ሣምንት ሆነኝ፡፡ ነገር ግን በድጋፍም በነቀፌታም በስድብም ጭምር ጥቂት ከማይባሉ ግለሰቦች በኢሜል ከተላከልኝ መልእክት በስተቀር ከጠየቅኋቸው አካላት ጭንቀቴን ተረድተው በተዛዋሪም ቢሆን […]

በዚህች ኣጭር ጽሁፍ ውስጥ ኤርትራን ለነጻነት ትግሉ በመጠቀሙ ዙሪያ በሚነሱ ክርክሮች ላይ የግል ኣስተያየት ለማከል እፈልጋለሁ። እንደሚታወቀው ኣመጸኛው ህወሃት ያስመረራቸው እና ለለውጥ የሚታገሉ ሃይሎች በሰላማዊ መንገድ በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ማምጣት ዘበት ነው ብለው ኣምርረው በማመናቸው ነፍጥ ማንገባቸው ከታወቀ ውሎ ኣድሯል። እነዚህ ሃይሎች ኤርትራን እንጠቀማለን ኤርትራ የኢትዮጵያን ህዝብ ትግል ለማገዝ ከፍተኛ ፍላጎት ኣሳይታለች እያሉ ነው። ታዲያ […]

በአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት የተዘጋጀው የ5 ሳምንት ስልጠና ዛሬ ተጀመረ፤ ስልጠናው በሰላማዊ ትግል ላይ ጥልቅ ጥናት ባደረጉት በአቶ ግርማ ካሳ ነው፡፡ አቶ ግርማ ሞገስ ኢትዮጵያ ረዥም የነፃነት ታሪክ ቢኖራትም በስልጣኔ ለምን እንዳልገፋች? እስከዛሬ ሰላማዊ ትግል ተደርጓል ወይ? የሚሉ ጭብጦች ላይ አተኩረዋል፡፡ በተለይ የሀገሪቷ ባህል ቀራፂ በነበሩ አካላት ዘመናዊ ስልጣኔ ሲያጥላሉ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ በመቀጠልም ሀገሪቷ የጦርነት […]

ኢትዮጵያን ለረጅም ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩትና ሰፊ ስልጣን የነበራቸው መለስ ዜናዊ በነሃሴ ወር በድንገት መሞት በሃገር ውስጥም ሆነ በኢትዮጵያ ዓለማቀፍ አጋሮች ዘንድ የሀገሪቱን ፖለቲካዊ ሽግግር የሚመለከቱ ጥያቄዎችንና አጠራጣሪ ሁኔታዎችን አስነስቶ ነበር።በኢትዮጵያ ያለው የሰብአዊ መብቶች አያያዝ በተለይ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ እየከፋ ሄዷል።አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በመስከረም ወር ስልጣኑን የተረከቡ ቢሆንም መንግስት በርሳቸው አመራር ሰብአዊ […]

ሃገር ውስጥ የተገኙ ዝሆኖች ሁሉ ይታሰሩ የሚል አዋጅ ይወጣል። አንድ አይጥ ከላይ ወደ ታች ትራወጣለች። ምን ሆነሽ ነው ብለው ይጠይቋታል። በሃገር ውስጥ ያሉ ዝሆኖች ሁሉ ይታሰሩ ተብሎ የወጣውን አዋጅ አልሰማችሁም እንዴ? ብላ ትነግራቸዋለች። ታዲያ አንቺ አይጥ እንጂ ዝሆን አይደለሽ ብለው ሲጠይቋት ። እሲኪጣራስ ብላ መለስች አሉ። እሲኪጣራ በዝሆንና በአይጥ መካከል ያለውን ልዩነት ጊዜ ይወስዳል። የተስፋዬ […]

በሀገራችን የስም አወጣጥ ወግና ልማድ እልም ያለችዋ ጥሩራ ባሪያ “አልማዝ” ወይም “ፀሐይ”፣ በነጭናጫነቷና በምግባረ ብልሹነቷ መንደርተኛው ሁሉ የሚያውቃት ሴት ወይዘሮ “ዐመለወርቅ” ወይም “አበቅየለሽ”፣ እልም ያለው ቦቅቧቃ “ደም መላሽ” ወይም “ሺመክት”፣ ቤሣቤስቲን የሌለው የኔቢጤው መናጢ ድሃ “ሀብታሙ” ወይም “አዱኛ”፣ እንዴት ያለው ንፉግና ክፉ ሰው “ቸሩ” ወይም “ደጉ”፣ … ተብሎ ሲጠራ እናውቃለን፡፡ መቼም ‹ስም አይገዛም› ይባላልና በዚህ […]

ክፍል ስድስት በስምምነት ላይ የተመሰረተ የባህል አንድነት (CCU) የእድገት አቅጣጫዎች በዚህ ንድፈ ሃሳብ መሰረት ባህል አዳጊ ነው፡፡ ባህል በተፈጥሮው ዳይናሚክ በመሆኑ በኣንድ ቡድን ህይወት ውስጥ ትውልዶች በራሳቸው ዘመን የየራሳቸውን ፈጠራ እየጨመሩበት ወደላይ ያድጋል:: በሌላ በኩል ደሞ ባህል ወደ ጎን ካለው ሌላ ቡድን ጋር ሲነካካ(interact ሲያደርግ) እሴት እየተጋባ ወደ ጎንም ያድጋል።ወደ ጎን ሲያድግ ብዙ ያጋራ እሴቶችን […]

ኑር ከሰው ኑር ከሃገር ይል ነበር፡ የሃገሬ ሰው፤ ሰው ለሰው መፈጠሩን የሚገልጽ አባባል ነው። በአጠገብህ ካለው መሰልህ ሰው አብረህ መኖር ከቻልክ በመላው ሃገርህ ካለው ሰው መኖር አያቅትህም ለማለት ነው። የሰው ልጅ ለራሱ መልካሙን እንደሚያስብና እንደሚሰራ ሁሉ ራሱን ለማጥፋትም የዛኑ ያህል ይሠራል። ጥያቄው ባብላጫው ለየትኛው ይሠራል ነው? ሕዝብ እንደ አንድ የሃገር ዜጋ ተሰባስቦ ሲኖር ማሟላት ያለበት […]

በአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ህዝባዊ ንቅናቄ ንቁ ተሳትፎ ያደርጉ ከነበሩ ወጣቶች መካከል ሁለት ደህንነቶች ዘላለም ደበበን ወደ ሚሰራበት የአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ግቢ በመዝለቅ በህገ ወጥ መንገድ ከወሰዱት በኋላ በማስፈራራትና ተራ የስድብ ቃላትን በማዝነብ በመጨረሻ ያለ ምንም ክስ መልቀቃቸው ታውቋል፡፡ እንደሁልግዜው ማልዶ በስራ ገበታው የተገኘው ዘላለም በሚሰራበት የአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ቤተ መጻህፍት ለአዳዲስ […]

ታዋቂው የፖለቲካ ተንታኝና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በሚገኝበት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር በተላለፈ ትዕዛዝ መሰረት የጎብኚዎቹ ቅጥር መወሰኑን የማረሚያ ቤቱ ምንጮች ለፍኖተ ነጻነት ገለጹ፡፡ የመስከረም 19/2006 ሰላማዊ ሰልፍ ብስጭት ከፈጠረባቸው አካላት መካከል አንዱ የሆነው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ብስጭቱን አደባባይ ያወጡበትን እርምጃዎች መውሰድ መጀመሩ እያነጋገረ ነው፡፡ለአንዷለም አራጌ የጎብኚዎቹን ስም እንዲሰጥ ካልሆነ ግን በማንም እንደማይጎበኝ የነገረው አስተዳደሩ የእስክንድርን […]

ላለፉት ሶስት ወራት ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ፣ ሕዝባችን በአራቱም ማእዘናት ለነጻነትና ለዲሞክራሲ ያለዉን ጥማት ለመግለጽና በሚታዩት የዜጎች የሰብአዊ መብት ረገጣ ላይ ያለዉን ተቃዉሞ ለማስተጋባት፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መርህ ስር ሲንቀሳቀስ እንደነበረ በስፋት ተዘግቧል። በጂንካ፣ በአርባ ምንጭ፣ በወላይታ/ሶዶ፣ በባሌ/ሮቢ፣ በፍቼ፣ በአዳማ/ናዝሬት፣ በመቀሌ (በሙሉ ባይሳካም) ፣ በደሴም በባህር ዳርና ፣ በጎንደር የተደረገው የመጀመሪአዉ ዙር የሚሊየነሞች […]

በዚህች ቅጽበት በጣም ተናድጃለሁ፡፡ አንዳንዴና መጻፍ ስፈልግ በጣም መናደዴን ብዙም አልከፋበትም፡፡ ካልተናደድኩ የምጽፈው ነገር አለ በቂ ምክንያት ሰዎችን እንዳያስቀይም ወይም ለማስደሰት ብቻ አለ በቂ ምክንያት እንዳያስደስት በማደርገው ሀበሻዊ ይሉኝታ አዘል ጥንቃቄ ወረቀት ላይ የሚቀመጠው ነገር አንዳንዴ ለራሴም ስሜት አልባ የሚሆንብኝ አጋጣሚ አለ – ይህንን ስል ግን ተናድጄ የምጽፈው ሁሉ ቱሪናፋ ነው ማለቴ እንዳልሆነ ግንዛቤ እንድትወስዱ […]

በዚህች ቅጽበት በጣም ተናድጃለሁ፡፡ አንዳንዴና መጻፍ ስፈልግ በጣም መናደዴን ብዙም አልጠላውም፡፡ ካልተናደድኩ የምጽፈው ነገር አመዛዛኝ ይሆንና ሁሉንም አለ በቂ ምክንያት ላለማስቀየም ወይም አለ በቂ ምክንያት ላለማስደሰት በማደርገው ጥረት ወይም ጥንቃቄ የምጽፈው ነገር ለራሴም ስሜት ያጣብኛል፡፡ ተናድጄ ስጽፍ ግን ስሜቴን እንደወረደ ወረቀት ላይ አየዋለሁ፡፡ እርግጥ ነው – ተናድዶ መጻፍ ‹ሪስክ› አለው፡፡ ሰዎችን ልታስቆጣ ትችላለህ፡፡ በሌላም በኩል […]

ትላንት ምሽት። እለተ እሁድ፤ ኦክቶበር 6፣ 2013። ታማኝ በየነ እና ቴዲ አፍሮ በስልክ ያወራሉ። ንግግራቸው ከወትሮው የተለየ አልነበረም። እንደቀድሞው እየተቀላለዱ ይሳሳቃሉ። ታማኝ ከዴንቨር-ኮሎራዶ፣ ቴዲ ደግሞ ከሲድኒ-አውስትራሊያ በስራ ላይ ነበሩ። በዚህ የሶስትዮሽ የስልክ ጨዋታ ላይ እኔና ጴጥሮስ አሸናፊም ገብተናል። ያን ሰሞን በኢትዮጵያ ድረ-ገጾች፣ በተለይ ደግሞ በፌስቡክ እና ሌሎች ማህበራዊ መድረኮች ላይ የውይይት ርእስ ሆኖ ሰነበተ። የታማኝ […]

አምስተርዳም ጉባዔ ላይ ለጥናት የቀረበ ጽሁፍ! 1.0 መግቢያ የታሪክ ግዴታ ሆኖ የሰው ልጅ እንደማህበረሰብ ከተደራጀና፣ ስልጣንና ሀብት በጥቂት ሰዎች ቁጥጥር ስር መውደቅ ከጀመረ ወዲህ የአንድ ህዝብ ዕድልና የወደፊት ጉዞው፣ ታሪክ የመስራትና ያለመስራት ችሎታው በመጀመሪያ ደረጃ ሊወሰን የሚችለው ስልጣንን በቁጥጥራቸው ውስጥ ባስቀመጡ ጥቂት ሰዎች አማካይነት ነው። በታሪክ ውስጥ አንድ ህዝብ ከአንድ አገዛዝ ቁጥጥር ውጭ በሆነ መንገድ […]

መግቢያ የዛሬው የመወያያ ሃሳብ ኢትዮጵያን እንደገና ለማነጽ ኣዲስ የማህበራዊ ፖለቲካ መዋቅር በማስተዋወቅ ላይ ያተኮረ ነው። ይህ መዋቅር ኢትዮጵያን ወደ ኣዲስ ኪዳን የሚጋብዝ ነው። ኢትዮጵያ የገጠማት የከፋ ችግር በኣብዛኛው ከታችኛው የማህበራዊ ፖለቲካ (socio politics) መዋቅር ጋር የተገናኘ በመሆኑ በዚህ ላይ ኣማራጭ ሃሳብ ማምጣት በተለይ ይህ የኣሁኑ ትውልድ የሚጠበቅበት ይመስላል። ያለፉትን ችግሮች ኣስር ጊዜ እያወጣን ብናወርዳቸው ድካም […]

ከሶስት ቀናት በፊት ቀትር ላይ አንድ የስልክ ጥሪ ደረሰኝ ። አንድ እዚህ ጅዳ የሚገኝ ወዳጀ ነበር ። ይህ ወዳጀ በስደተኛ ዜጎቻችንና በኮንትራት ሰራተኞች ላይ የከፋ ግፍ ሲፈጸም ፣ ዜጎች በራሳችን መንግስት ተወካዮች በጅዳና ሪያድ መጠለያዎች ፍዳቸውን ሲያዩ ፣ ኢትዮጵያውያን ሲያመን ህመሙ ዘልቆ ሲያመው እና የአረቡ መገናኛ ብዙሃን ስማችን አጉድፈው ክብራችን ቀንሰው መረጃ ሲያሰራጩ በስጨት ብለው […]

ኢትዮጵያን ለማጥፋት ከተሾመ የወንበዴ መንግሥት ፍትህንና ወገንተኝነትን መጠበቅ ቂልነት መሆኑን በ22 ዓመታት ያልተረዳ ዜጋ፣ የማይሆን ጥያቄ ጠይቆ የማይሆን መልስ ቢሰጠው ሊገረም አይገባውም፡፡ ከነተረቱ “ራሷ ሄዳ ጣፊያ የከለከሏት ‹ምላስ ሰምበር ላኩልኝ› አለች” ይባላል፡፡ ወያኔ ከመነሻው ሀገርንና ዜጋን ድራሹን ለማጥፋት መነሳቱንና ይሄ ሁሉ ሕዝብ በዓለም ዙሪያ እንዲበተን ያስገደደው ራሱ ወያኔ መሆኑን እየተገነዘብን በራሱ አምሳል የተቀረጹ ድፍን ቅል […]

ክቡር ፕሬዚደንት ግርማ ሆይ፣ ኢትዮጵያንና “ሕዝቦቿ”ን የሚወዱ ከሆነ ቀጥዬ የምነግርዎትን ከልብ እንዲሰሙኝ በሚያምኑት እለምነዎታለሁ፡፡ ሰሞኑን በጡረታ ሊሰናበቱ እንደሆነ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዜና ዘገባ ሰማሁ፡፡ በመጀመሪያ ሥራዎን ጨርሰው ለዚህ በመብቃትዎ እንኳን ደስ ያለዎ፡፡ ቀጥዬም በሥራ ዘመንዎ ምን እንደሠሩና እኛ በምናውቅልዎም ሆነ እርስዎ በሚያውቋቸው ምክንያቶች የተነሣ ምን ምን መሥራት ፈልገው ሊሠሩ እንዳልቻሉ “ፕሬዚደንታዊ የሥልጣን ዘመን”ዎን የኋሊዮሽ በማሰብ […]

ይድረስ ለተከበራችሁ የአንድነት ደጋፊወቻችን እና ለኢትዮጵያውያን ሚዲያዎች በሙሉ በቅድሚያ ሰላምታችን ባላችሁበት ይድረሳችሁ። ላለፉት ሶስት ወራት የተደረገዉ የመጀመሪያዉ ዙር የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት እንቅስቃሴ፣ በኛ ግምት በጣም በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋልብለን እናምናለን። በዚህ ሂደት ብዙዎች ኢትዮጵያውያን ሚዲያዎች እና ደጋፊወቻችን በሙሉላደረጉልን ድጋፍና ትብብር ምስጋናችን ከፍተኛ ነው:: የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ የሰሜን አሜሪካ አንድነት ፓርቲ ደጋፊ ግብረ ኃይል ያዘጋጀውን ቴሌ […]

ኢህአዴግ ከቀድሞ ሊቀ-መንበሩ አቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ በተከሰተበት ውስጣዊ ልዩነት በተለዋዋጭ የኃይል ሚዛን ሥር ለማደር በመገደዱ የስልጣኑን መዘውር የሚያሽከረክረውን አካል ለመለየት አዳጋች ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ይህ ሽኩቻ መፍትሄ ማግኘቱን የሚያመላክቱ ሁናቴዎች መፈጠራቸውን የውስጥ አወቅ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ እንደ መግቢያ ድንገቴው የመለስ ህልፈት ህወሓትን ቢከፍለውም፣ ብአዴን ራሱን እንዲያጠናክር መደላድል ፈጥሮለታል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት መለስ […]

የዛሬውን ሰልፍ ለመታደም ስወስን ብዙ ሰው እንደሚገኝ ገምቼ ነበር። አልተሳሳትኩም፣ የዞን ዘጠኝ ጓደኞቼን ጨምሮ ሌሎችም በፌስቡክና ከፌስቡክ ውጪ የማውቃቸው አራማጅ/ተራማጆች ሁሉ በጠዋቱ ተሰባስበዋል — ተያይዘን ስንሄድ፤ ቀበና ያለወትሮዋ በእሁድ ምድር ደምቃለች። ሰልፉ ገና ከመነሻው መድመቁ መንገዱን ካልዘጉት በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠር ሰው እንደሚታደም እርግጠኛ ሆንኩ። ሰልፈኛው ቁጥሩ እየገፋ ቢመጣም የትራፊክ ፖሊሶቹ መኪና ማገድ የፈለጉ አይመስልም። ፖሊስ […]