ከሚሊዮኖች አንዱ ነን – ሶሊዳሪቲ ንቅናቄ

በታዋቂዉ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ አቶ ኦባንግ ሜቶ የሚመራዉ የሶሊዳሪቲ ንቅናቄ፣ የሚሊዮኖች ድምድ ለመሬታ ባለቤትነት እና ለፍትህ እንቅስቅሴን እንደሚደገፍና የእንቅስቃሴዉም አካል እንደሚሆን ባወጣዉ መግለጫ ገለጸ። ሶሊዳሪቲ «እኛም ከሚሊዮኖች አንዱ ነን» በሚል ባወጣዉ መግለጫ፣ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንቅስቃሴዉን እንዲቀላቀሉና የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስቧል። በግለሰብ ደረጃ ተራ ሰዎች ብንሆንም፣ ከተባበረንና ሚሊዮኖች ከሆነን ፣ ሊቋቋመን የሚችል ምንም ኃይል እንደሌለ የገለጸው የሶሊዳሪቲ መግለጫ፣ ኢትዮጵያዉን በዘር፣ በሃይማኖት ፣ በፖለቲካ ዝንባሌ ሳይለያዩ በአንድነት ከቆሙ ያኔ የኢትዮጵያ ትንሳኤ እንደሚሆን በመገለጫዉ አስምሮበታል።

መነበብ ያለበት የሶሊዳሪቲን ልብ የሚነካና አስተማሪ መግለጫ ለማንበብ ከታች ይመለከቱ

እንደ ሶሊዳሪቲ ንቅናቄም ሸንጎ የተሰኘው አንጋፋው የብዙ ድርጅቶች ስብስብ፣ ከሁለት ቀናት በኋላ በዋሺንገትን ዲሲ ትልቅ ስብሰባ የሚያደርገው የብሄራዊ ሽግግር ምክር ቤት፣ እኛም የሚሊዮኖች አንዱ ነን በሚል፣ በዳያስፖራ እየተንቀሳቀስ ካለው የሚሊዮኖች ድምጽ ግብረ ኃይል ጋር ለመስራት ልዑካን ቡድን እንደላኩ እና፣ ከግብረ ኃይሉ ጋር በቅርብ እየሰሩ መሆኑ ከግብረ ሀይሉ ለመረዳት ችለናል።SNME-1