በጦር ኃይሎች፣ ቤትል ጎጃም በረንዳና መሳለሚያ ከመስጊድ የወጡ ሙስሊሞች ታፍሰዋል፡፡ በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች በርከት ያሉ ፌደራል ፖሊሶች ይታያሉ፤ ከሌሊቱ 5 ፡00 ሰዓት ጀምሮ መኪናዎች ላይ ከባድ ፍተሻ እየተደረገባቸው ነው፡፡ የሙስሊሙን የመብት እንቅስቃሴ የሚመራው ድምፃችን ይሰማ የተባለው የሶሻል ሚዲያ ግሩፕ ከቤተመንግስት በቅርብ ርቀት በሚገኘው ተውፊቅ መስጊድ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ብሶቱን እንዲያሰማ ጥሪ ማስተላለፉ አይዘነጋም፡፡

ሐምሌ ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው በመጪው እሁድ በመቀሌ፣ ባህርዳር፣ ጅንካ እና አርባ ምንጭ የሚያደርገውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ የገዢው ፓርቲ ሰዎች ሰልፎችን ለማደናቀፍ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው። በመቀሌ የአንድነት አመራሮች መጉላላት የደረሰባቸው ሲሆን፣ በጅንካ ደግሞ አካባቢው የሽብርተኞች ጥቃት ኢላማ በመሆኑ ሰልፉን ማድረግ አይቻልም የሚል መመሪያ እስከ ማስተላለፍ ተደርሶ ነበር። የአንድነት አመራሮች ባሳዩት የአቋም …

ሐምሌ ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዚህ ሕግ መሠረት የሕዝብ ገንዘብ ዘርፈው ወደውጪ አገር ፈርጥጠዋል የሚባሉ ሰዎች ተጠያቂ ይሆናሉ ተብሎ ይገመታል ፡፡ የሚሻሻሉት ሕጎች የተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የስነስርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅ እንደገና ለማሻሻል የወጣውን ረቂቅ አዋጅ፣ የተሻሻለውን የስነምግባርና የጸረ ሙስና ኮምሽን ማቋቋሚያ አዋጅ እንደገና ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅ እና የሙስና ወንጀሎችን እንደገና ለመደንገግ …

ሐምሌ ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አሶሺየትድ ፕሬስ እንደዘገበው የተመድ ሠራተኞችን ጭኖ ወደ ደቡብ ሱዳን ሲጓዝ የነበረው ሄሊኮፕተር በመከስከሱ በርካታ የተመድ ወራተኞች ጉዳት ደርሶባቸዋል። የ ኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በበኩላቸው አደጋው መድረሱን በማረጋገጥ የጉዳቱ ዝርዝር መጠን እንዳልደረሳቸው ተናግረዋል። የመንግስታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ ፈረሀን ሀቅ-ሄሊኮፕተሩ  የተባበሩት መንግስታት የምግብ ፕሮግራም በጆንገሊ …

ሐምሌ ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2005 የክዋኔ ኦዲት ግኝቶች ሪፖርት የህዝብና የመንግስት ሃብት አጠቃቀም አሳሳቢ የሆነ ክፍተት እንዳለባቸው ተጠቅሷል፡፡ መስሪያ ቤቱ  በመጠናቀቅ ላይ ባለው አመት በኢንዱስትሪ ከተማ ልማት ቢሮ ፤ በገጠር መንገዶች ባለስልጣን ፤ በጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጅንሲ ፤በባህል እና ቱሪዝም ና ፓርኮች ልማት ቢሮ …

የግብፅ ጦር የሰየመዉ ጊዚያ መንግሥት ግን ጥሪ ማሳሰቢያዉን የተቀበለዉ አይመስልም።የጊዚያዊ መንግሥቱ ካቢኔ መፈንቅለ መንግሥቱን በመቃወም በሁለት አደባባዮች የከተመዉን ሕዝብ «ለሐገሪቱ ፀጥታ አስጊ» እና «አሸባሪ» በማለት ወንጅሎታል።ፖሊስ ሕዝቡን ከሁለቱም አደባባዮች እንዲያባርርም አዟል።

ኢትዮጵያ የኤርትራን መንግስት ወደሰላማዊ የድርድር መድረክ ለማቅረብ 250 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል በነጻ ለመስጠት አስባለች መባሉንየሚጠቁም ዜና በድረገጾች እየተነበበ ነዉ።

የዛኑ ፒኤፍ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ምርጫውን አሸንፈናል ፣ ተቀናቃኛችን የዲሞክራሲያዊ ለውጦች ንቅናቄ MDC አልቋለታል ተቀብሯል እያሉ ነው ። ስማቸውን ያልጠቀሱ አንድ ነፃ የዚምባብዌ የምርጫ ታዛቢም የድምፅ ቆጠራ የመጀመሪያው ውጤት ለቻንጋራይ ታላቅ ውድቀት እንደሚመስል ለሮይተርስ አታውቀዋል ።

የረመዳን የጾም ወር ተጋምሶ ፍችዉ የኢድ አልፈጥር በዓል እየተቃረበ ነዉ። በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች በቀን ወደ 18 ሰዓት ያህል ይጾማሉ። በዕለቱ ዝግጅታችን በቦን ከተማ አቅራብያ በምትገኘዉ በብሩል ከተማ የሚኖሩ አንድ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ቤተሰብ ቤት ጎራ ብለን የእፈጠር ምሽትን አብረን አሰልፈን ልናካፍላችሁ ይዘናል፤

ሰበር ዜና ከመቀሌ – የአንድነት ከፍተኛ አመራር እና የፓርቲው አባል ታሰሩ መቀሌ ውስጥ አንድ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ እንግዳ ተክለፃዲቅ እና በዚህ ሳምንት “መቀሌን በ24 ሰዓት ለቀህ ውጣ” ተብሎ የነበረው የአንድነት ፓርቲ አባል አቶ የማነህ አበራ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በፖሊስ በህገወጥ መንገድ ታስረዋል፡፡ ‪#‎millionsofvoicesforfreedom‬ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎UDJ‬

ከሁሉ አስቀድመን ፣ በየመልኩ በዉጭ ለምንኖር ኢትዮጵያዉያን፣ ባህላችንን፣ ታሪካችንን ችግሮቻችንና የአገራችንን እሴቶ፣ በየወቅቱ በመከታተል፣ ግንዛቤ እንድናገኝ ለምታደርጉት ጥረት፣ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን። ዛሬ አገራችን አጣብቂኝ ሁኔታ ዉስጥ እንዳለች፣ የሁላችንም ግንዛቤ ነዉ። ከሁሉም በላይ፣ እንደ ማንኛዉም አገር ሕዝብ፣ የሃይማኖት የብሄረሰብ የቋንቋ ልዩነቶች ቢኖሩም፣ የእኛ የኢትዮጵያዉያን ልዩ እሴት፣ ልዩነቶቻችንን አቻችለን፣ በፍቅርና በሰላም መኖራችንና መቻቻላችን ቀዳሚነቱን ስፍራ የሚይዝ […]

መግቢያ፡- (ከ18 ዓመት ዕድሜ በታች የሆነ ሰው እንዲያነብ የማይመከር) የሰው ልጆች በሃይማኖት መከፋፈላቸውን አምርሬ ብቃወምም፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሃይማኖቶች የውሸትና ለብዝበዛም የተፈጠሩ መሆናቸውን ባምንም፣ እጅግ ብዙዎቹ ሃይማኖቶች ሰይጣን የተጣባቸው ወይም የሰይጣናዊነት መንፈስና አሠራር በጉልህ የሚታይባቸው መሆናቸውን ብረዳም በትውልድና በገዛ ፈቃዴ ይዤው ያለሁት ሃይማኖት ክርስትና ነው፡፡ ክርስትና በራሱ በመቶዎችና ከዚያም በላይ የተከፋፈለ መሆኑንም አውቃለሁ – አንዳቸው ለአንዳቸው […]

የጅንካ ወጣቶች ታሪክ እየሰሩ ነው፡፡ አንድነት ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ በንቃት ለመሳተፍ ከመንቀሳቀሳቸውም በላይ በጅንካና በአካባቢዋ በራሳቸው ተነሳሽነት ቅስቀሳ እያከናወኑ ነው፡፡ በተያያዘ ዜና የደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሞሎካ ውብነህ በ22/11/2005 ዓ.ም በቁጥር 417/107/05 በፃፉት ደብዳቤ ለአንድነት አመራሮች የእንወያይ ጥሪ አድርገው ከ14 የሀገር ሽማግሌዎችና ከጅንካ ከተማ ከንቲባና የተለያዩ የከተማው ባለስልጣናት ጋር በመሆን አንድነት ሰላማዊ ሰልፉን […]

የኢህአዴግ መንግስት በኢቲቪ በኩል ስለ ‘ሽብር’ና የ‘ፀረሽብር ሕግ’ አስፈላጊነት ያወራል። አንዳንድ ተቃዋሚዎች ደግሞ ስለ ‘ፀረሽብር’ ሕጉ ኢ-ሕጋዊነት ይሰብካሉ። እኔም የፀረሽብር ሕጉ ከማይደግፉ ሰዎች ጋር እንደምሰለፍ ካሳወቅኩ ከጥቂት ግዜ በኋላ አንድ የምወደው የህወሓት አባል የሆነ ጓደኛዬ እንዲህ ሲል በውስጥ መልእክት ላከብኝ፣ “ፀረሽብር ሕግ መቃወም ኮ ሽብርን መደገፍ ነው። አንዳንድ አክራሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ ስም ሽብርተኝነትን ማስፋፋት ይፈልጋሉ። […]

ከምሽቱ አራት ሰዓት ተኩል ላይ ወደ አውሮፕላኑ እንድንገባ ተጋበዝን፡፡ በቀኜም በግራዬም ከፊቴም ከኋላዬም የተቀመጡት የእስያ ዝርያ ያላቸው ተጓዦች ናቸው፡፡ እንዲህ ኤስያውያን በሞሉበት አውሮፕላን ስሄድ የመጀመሪያዬ ነው፡፡ አስተናጋጆቹ ከዚህ በኋላ ወደ ቀጣዩ መዳረሻችን ለመድረስ የስምንት ሰዓት ከሩብ ጎዳና ይቀረናል አሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ ሌላ አውሮፕላን እንይዛለን፡፡ ድሮ ሦስተኛ ክፍል ስንማር ‹ንብ አበባ ለመቅሰም የምታደርገውን ጉዞ በአንድ መሥመር ብታደርገው ኖሮ፣ ዓለምን ትዞር ነበር› የሚል ነገር ተምሬ ነበር፡፡ አሁንም የኔ ነገር እንደዚያ ሳይሆን አይቀርም፡፡

‹ይህ ነው ምኞቴ እኔ ለሕይወቴ› የሚል የቆየ የማርሽ መዝሙር  ትዝ አለኝ፡፡ እዚያ መዝሙር ውስጥ ደግሞ

ረዥሙን ጉዞ ትግሉን ዐውቄ

ተነሥቻለሁ ትጥቄን አጥብቄ

የሚል ነገር ነበረው፡፡ ምን ይደረግ ሰው ከሀገሩ ሲወጣ ትዝታ ነው የሚተርፈው፡፡ ከወሎ መቄት ወደ አዲስ አበባ መጥተው የኖሩት አለቃ ለማ ኃይሉ አይደሉ እንዴ ቢቸግራቸው ‹‹እግር አዲስ አበባ ልቡና መቄት›› ያሉት፡፡ አንዳንድ ጊዜ ‹ሀገር ማለት ምንድን ናት?›› ያሰኛል፡፡ በሀገራችን ተሰቃየን፣ ታሠርን፣ ተንገላታን፣ ግፍ ተፈጸመብን ብለው ከሀገር የሚወጡ ወገኖቻችን እንኳን መልሰው ‹ሀገሬ› ሲሉ ሳያቸው ይህቺ ሀገር የምትባል ‹መንፈስ› ምንድን ናት? እላለሁ፡፡ አንድ ጊዜ ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ አዲስ አበባ ስመጣ ከጎኔ አንድ በጎልማሳነት እድሜ ላይ የደረሰ ኢትዮጵያዊ ወገን ተቀምጦ ነበር፡፡ አውሮፕላኑ ሲነሣ እጁ ይንቀጠቀጣል፡፡ ያመመው መሰለኝና ዘወር ብዬ ‹‹አመመህ›› ስል ጠየቅኩት፡፡ ግንባሩን በመሐረብ እየጠረገ ‹‹ደኅና ነኝ፣ ምንም አልል›› አለኝ በእንግልጣር፡፡ አሁንም እጁ ይንቀጠቀጣልና ዘወር አልኩ፡፡

‹‹ይገርምሃል ከሀገሬ ከወጣሁ ሠላሳ ዓመቴ ነው፡፡ ወደ ሀገር ለመሄድ ሳስብ ሁልጊዜ ሰውነቴ ይንቀጠቀጣል፡፡ አንዳች ነገር መጥቶ ይወርረኛል፡፡ ልቤ ምቱ ይጨምራል፡፡ አሁንማ አውሮፕላን ውስጥ ስገባ ባሰብኝ፡፡ ውስጤ ብርድ ብርድ ይለኛል፤ እንደገና ይሞቀኛል፡፡ ምን እንደሆነ ማወቅ አልቻልኩም›› አለኝ፡፡ እያየሁት እገረም ነበር፡፡ ከሕይወቱ አብዛኛውን፤ ያውም ነፍስ ያወቀበትን ዘመን ያሳለፈው አሜሪካ ነው፡፡ ግን ‹ኢትዮጵያ› የሚለውን ሲያስበው አንዳች ስሜት፣ እርሱም የማይገባው ስሜት ይወርረዋል፡፡ ‹‹ሀገር ምንድን ነው?››

ደግነቱ አንድ ወዳጄ ‹‹ዜጋን ከሀገሩ ማስውጣት ቀላል ነው፤ ሀገርን ከዜጋው ልብ ማስውጣት ግን አይቻልም›› ብሎኝ ነበር፡፡ እኛ ልብ ውስጥ ልዩ የሆነች ሀገር አለች፡፡ ማንም የማይነካት፣ ማንም የማይወስዳት፣ ማንም የማያጠፋት፡፡ አለቃ ለማ ‹ልቡና መቄት› ያሉትኮ መቄት ከልባቸው አልወጣ ብላቸው ነው፡፡

ይህንን ሁሉ እያሰብኩ አውሮፕላኑ ተነሥቶ ወደ ሕንድ ውቅያኖስ አቅጣጫ ማምራት ጀመረ፡፡ እኔም የሕይወት ተፈራን Tower In The Sky አውጥቼ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ ያ ትውልድ አሁንም አብሮኝ ሕንድ ውቅያኖስን ሰንጥቆ ሊጓዝ ነው፡፡ ዓላማ፣ ትጋት፣ ቆራጥነት፣ መሥዋዕትነት፣ ጽንዓት የነበረው አንድ ትውልድ ጠፍቷል፡፡

በማርክሲስት ሌኒኒስት ቀንበር ተቀይዶ፣ የሁሉንም ነገር መፍትሔ ከመጻሕፍት ውስጥ ሲያስስ፣ እርስ በርስ ተከራክሮና ተወያይቶ በመተማመን ወይም ባለመተማመን መፍታት ሲቻል፤ ተምሮ እንዳልተማረ፣ ዐውቆ እንዳላወቀ ሲጨራረስ ማየት አሳዛኝ ነው፡፡ ሁሉንም ነገር በሳጥን ውስጥ ብቻ ለመመልከት የሚተጋ ትውልድ የ‹ኢስት› ብዛት፡- ማርክሲስት፣ ማኦኢስት፣ ቾቭኒስት፣ ፌሚኒስት፣ ካፒታሊስት፣ አናርኪስት፣ ፋሺስት፣ ትሮትስኪስት፣ ኮሙኒስት፣›› የ‹ኢዝም› መዓት፡፡ ሁሉንም ሃሳቦች፣ ሁሉንም አመለካከቶች በሳጥኖች ብቻ አድርጎ የመመልከት አባዜ፡፡ ማርክስ፣ ሌኒንና ኤንግልስ የሚባሉ ሐዋርያት ያመጡት አዲስ ሃይማኖት፤ ቦልሼቪስት፣ ማኦኢስት፣ ማርክሲስት የሚባሉ ምእመናን፤ አናርኪስት፣ ትሮትስኪስት፣ የሚባሉ መናፍቃን፤ ኢምፔሪያሊስት፣ ፊውዳልና ቡርዧ የሚባሉ አጋንንት፣ ተፈጥረው አማኝና ከሃዲ ሲወጋገዙና ሲጫረሱ የኖሩባቸው ዘመናት፡፡

መጽሐፉ እያሳዘናችሁ እያስገረማችሁ፣ እያበሳጫችሁም ይጓዛል፡፡ የአንድ ፓርቲ ሰዎች ትናንትም ይከፋፈላሉ፤ ዛሬም እንዲሁ፤ ተከፋፍለውም ይወጋገዛሉ፤ ዛሬም እንዲሁ፤ ተወጋግዘውም ይገዳደላሉ፤ ዛሬም እንዲሁ፤ ለአብዮቱ ሲባል፤ ለትግሉ ሲባል፤ አድኅሮት ኃይላትን ለማስወገድ ሲባል በጓዶች ላይ ርምጃ ይወሰዳል፡፡ ድመት ይመስል አብዮት ልጆቿን ትበላለች፡፡ እስካን አይጥ ለማጥመጃ ስንት መሣሪያ ሲሠራ፤ ምነው ይህቺን ልጆቿን የምትፈጅ ‹የአብዮት ድመት› ማጥፊያ መድኃኒት ጠፋ?

የዚያ ዘመን ሰዎቹ ዐልፈዋል፤ ሥርዓቱ ዐልፏል፤ ታሪኩ ዐልፏል፤ መንፈሱ ግን አለ፡፡ ‹‹ግደል ተጋደል በርታ ወገኔ›› የሚለው ዛር ግን አለ፡፡ ፖለቲካዊ ጽንፈኛነት፤ ደጋፊነትና ጠላትነት፤ ሥር ነቀልነትና ደምሳሽነት አሁንም አሉ፡፡ ይህንን መንፈስ የሚያጠፋ ትምህርት፤ የሚደመስስ ጸሎት፤ የሚያስቀር ሥርየት አልተገኘም፡፡

መጽሐፉን እንዲህ እያነበብኩ እያለ አስተናጋጆቹ ምግብ ይዘው በጎናችን መጡ፡፡ ከጎኔ ላለው ሰውዬ የሰጠችው ምግብ ስሙን የጠራችው በቻይንኛ ሳይሆን አይቀርም፡፡ የነዚህ የእስያውያን ነገርኮ ምን እንደሚበሉና ምን እንደማይበሉ አይታወቅም፡፡ ቢጨንቀኝ ዓሣ አዘዝኩ፡፡ የመጣውን ነገር አልነግራችሁም፡፡ ምናልባት ምግብ ላይ ትሆናላችሁና ይቅር፡፡ አንድ ወዳጄ ‹‹እነዚህ ሰዎችኮ ሰውን ባሕር ውስጥ ቢያገኙት ዓሣ ነው የሚሉት›› ያለኝ ትዝ አለኝ፡፡ እንኳን ልበላው ኢትዮጵያ የበላሁትም ምግብ ሆዴ ውስጥ ሆኖ እንደ ኤርታሌ ይተራመስ ጀመር፡፡

ከድኜ ተውኩትና መጽሐፉን ቀጠልኩ፡፡ አይ ሕይወት እግዜር ይይልሽ፡፡ ልደታ ብስኩት ቤት፣ ፒያሳ ጮርናቄ ቤት፣ ሐረር ምግብ ቤት፣ ምናምን ክትፎ ቤት እያለች የአዲስ አበባን ምግብ ቤቶችና ሻሂ ቤቶች ትዘረዝራለች፡፡ ይህም አልበቃ ብሏት በመቀሌ መንገድ ላይ ‹‹ምን የመሰለ ዱለት በላሁ›› ትላለች፡፡ እኔ እዚህ በአንድ በኩል የሚዘጋ ምግብ ከፊቴ ተቀምጦ ይተናነቀኛል፤ በሌላ በኩል ደግሞ የሀገሬን ምግብ ቤትና ምግብ እያነበብኩ ረሃቤ ይቀሰቀስብኛል፡፡ ተርቦ ስለ ረሃብ ማንበብን የመሰለ ቅጣት መቼም የለም፡፡

ዘሚካኤል ትዝ አለኝ፡፡ ዘሚካኤል ኤርትራዊ ነው፡፡ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ከዐሥራ ሁለት ዓመታት በፊት ባዘጋጀው አንድ ሴሚናር ላይ ለመሳተፍ ተጋብዘን ኡጋንዳ ኢንሴንዜ የምትባል መንደር ተገናኝተን ነበር፡፡ እዚያ ከአሥራ ስድስት የአፍሪካ ሀገሮች የመጡ ወጣቶች ነበሩ፡፡ ከሁሉም የእኔና የዘሚካኤል የምግብ ምርጫ ነበር የሚገርማቸው፡፡ ከምንበላው የማንበላው ይበልጣል፡፡ አንደ ቀን ሴሚናር ላይ ውለን አምሽተን ተመለስን፡፡ እኔ ቀደም ብዬ ጨለም ወዳለው የማምሻችን ቦታ መጣሁ፡፡ እሳት ነድዶ ጨዋታው ቀልጧል፡፡ ዘሚካኤል መታጠቢያ ቤት ገብቶ ዘገየ፡፡ ስደርስ የሆነ ነገር ሸተተኝ፡፡ አሻግሬ ሳይ ጠረጲዛው ላይ ያለውን ነገር ይሻሙበታል፡፡ በጨለማው ውስጥ ያለው የእሳት ብርሃን ብቻ ስለነበር ልለየው አልቻልኩም፡፡ ራቅ ብዬ ተቀመጥኩ፡፡

ዘሚካኤል መጣና ጠረጲዛ ላይ ያለውን ነገር አየው፡፤ ‹‹ዘቢብ ሳይሆን አይቀርም›› አለኝ፡፡

‹‹አይ እኔ ይቅርብኝ አንተ ሞክረው›› አልኩት፡፡

‹‹ዘቢብ መሆን አለበት፤ መልኩ እንደዚያ ነው›› አለና ሊያመጣ ሄደ፡፡ ልክ ጠረጲዛው ጋ ሲደርስ ‹‹ቧ፣ አተ›› አለና ፈጠን ፈጠን ብሎ ወደ ማደሪያው ገባ፡፡ ምን ሆነ ብዬ ደነገጥኩና ተከተልኩት፡፡ ባንኳኳ ባንኳኳ አልከፍትም አለ፤ በስንት መከራ ሳስከፍተው ፊቱ በውኃ ርሷል፡፡

‹‹ምን ሆነህ ነው?›› አልኩት

‹‹ጉድ ሠሩኝኮ›› አለኝ

‹‹ምን አደረጉህ››

‹‹ምን እንደሆነ ዐውቀሃል››

‹‹ምንድን ነው?››

‹‹የተጠበሰ ክረምት አግባ›› በሳቅ ፈረስኩ፡፡ ለካስ እንደ ዘቢብ አምሮ የታየው እኛ ክረምት አግባ የምንለውን ሰብስበው ቆልተውት ነው››

ዛሬ የደረሰብኝ በዘሚካኤል በሳቅኩት ግፍ ነው፡፡

ከዱባይ ወደ ብሩናይ መንገድ፣ ሕንድ ውቅያኖስ ላይ

ሐምሌ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዞኑ ነዋሪዎች ከመንግስት ጋር ምንም አይነት ትብብር እንደማያደርጉ መግለጻቸውን ተከትሎ፣ ከጠቅላይ ሚ/ሩ ጀምሮ ያሉ ባለስልጣናት ከቦረና ሽማግሌዎች ጋር ውይይት ቢያደርጉም ችግሩ አልተፈታም። ውዝግቡ የተጀመረው መንግስት ገሪ እየተባሉ የሚጠሩትን የሶማሊ ጎሳ አባላት በቦረና ዞን ለማስፈር እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ ነው። በቅርቡ የ50 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው ግጭት ከመከሰቱ በፊት መንግስት …

ሐምሌ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመቃብር ቦታ ጥያቄያችን አልተመለሰም ፤ ለመስጊዶቻችንን  የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር ተከልክለናል፡፣ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ፍትህ አጥቷል” በማለት ሙስሊሞች ተናግረዋል። የጎንደር ከተማ ኗሪ የሆኑት ሐጅ ሙርፉቅ ሙስሊሙ ከመንግስት ጋር ሆድና ጀርባ መሆኑን ገልጸዋል። በየቀኑ ደብዛቸው እየጠፋ በአፋልጉኝ የሚጠሩት ህዝበ ሙስሊሞች የመንግስት የአፈና ውጤት መሆናቸውን የተናገሩት የጎንደር ህዝበ ሙስሊሞች፤ያለምንም ፍትህ የሚያስረውና …

ሐምሌ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ዞንና ወረዳዎች በበጎ አድራጊዎች ድጋፍና በህብረተሰቡ የተገነቡ ከ110 በላይ  የውሃ ተቌማት ላይ የእጅ ፓምፕ ዝርፊያ በመፈጸሙ በውሀ አቅርቦቱ ላይ ችግር ተፈጥሯል። ዝርፊያውን ተከትሎ የወረዳ አመራሮች ለህዝቡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ናቸው እያሉ ፤ ፓርቲዎችን የማሰጠላት ዘመቻ እያከናወኑ ነው፡፡ በተለያዩ  አካባቢዎች እየተከሰተ ባለው የውሃ ተቋማት ዝርፊያ …

የዝምባብዌው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ በዛሬው ምርጫ የሚሸነፉ ከሆነ ሥልጣናቸውን እንደሚለቁ አስታወቁ። አያሌ ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆዩት ሙጋቤ፣ ተፎካካሪአቸውን ጠ/ሚንስትር ሞርጋን ቻንጊራይን ለማሸነፍ ሙሉ በሙሉ እንደሚተማመኑም ገልጸዋል። በሃራሬ

«ጨው ሲበዛ ያቅራል ፤ በርበሬ ሲበዛ ይመራል» ይባላል፣

ለሰውና እንስሳ ጠቀሚ ከሆኑ ማዕድናት መካከል አንዱ ጨው ነው፤ የዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት(WHO) እንደሚመክረው ከሆነ እያንዳንዱ ሰው በየቀኑ መጠኑ ፣ከ 5 ግራም የማይበልጥ ጨው መመገብ

ማሕበሩ በተለይ ብሪታንያ፥ ፈረንሳይና ዳች (ወይም ኔዘርላንድን) ካሳ እንዲከፍሉ በሕግ ሊሞግታቸዉ ተዘጋጅቷል።ጠበቆች፥ አንዳድ ሙሑራንና የመብት ተሟጋቾችም የማሕበሩን አቋም እንደሚጋሩ እየተናገሩ ነዉ

እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር በ1701 ፈረንሳዊዉ የቅኝ ገዢ ጦር መኮንን አንቶኒዮ ደ ላ ሞንቴ ካዲላክ የቆረቆራት ከተማ ከሰሜን አሜሪካ ትላልቅ ከተሞች አንዷ ለመሆን ብዙ ጊዜ አልወሰደባትም።ዲትሮዮት።

በማሊዉ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ኢብራሂም ቡባከር ኬይታ የሚሳካላቸዉ ይመስላል። የእሁዱ ምርጫ መነሻ ዉጤት የሚያመለክተዉም ይህንን ነዉ። የሆነ ሆኖ ኬይታ በምርጫዉ ያገኙት የድምጽ መጠን ገና አልተረጋገጠም። የዶቼ ቬለዋ ካትሪን ጌንዝለር እንደዘገበችዉ ግን የማሊ የፖለቲካ ተቃዋሚ ወገን በዚህ አልተደሰተም።

በሻሸመኔ ጩሉሌ ሀበራ ቀበሌ በሚገኘው በመስጊዱራህማ መስጊድ ም/ኢማምና የመስጊዱ ኮሚቴዎች በህገወጥ መንገድ ታስረቸዋል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአንድነት ፓርቲ አቤቱታቸውን አቀረቡ፡፡ በሻሸመኔ ጩሉሌ ሀበራ ቀበሌ በሚገኘው በመስጊዱራህማ መስጊድ ም/ኢማም ሼህ አማን ተሺተን ጨምሮ 15 የመስጂዱ ኮሚቴ አባላት የታሰሩት ባለፈው እሁድ ሐምሌ 14 ቀን 2005ዓ.ም የመስጂዱ ንብረት የሆነን ከአንድ ሄክታር ላይ የታጨደ በግምት ከ10 ኩንታል በላይ የሚመዝን […]

አንድነት በወላይታ በ28/11/2005 ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ የጥሪ ወረቀት በመበተን ላይ የነበሩ የወላይታ የአንድነት አመራርና አባላት በህገ ወጥ መንገድ በመያዝ ለእስራት የዳረገው የከተማው ፖሊስ ለአመራሮቹ‹‹በዕለቱ በምታደርጉት ስብሰባ የሚነሱ አጀንዳዎችን መነጋገር አለብን››ማለቱ ተሰምቷል፡፡ በየትኛውም መመዘኛ ስብሰባው ላይ ስለሚቀርቡ አጀንዳዎች ከፖሊስ ጋር የመወያየት ግዴታ ስለሌለብን ይህንን ለማድረግ እንቸገራለን፡፡ፖሊስ ወይም አቃቤ ህግ ህግን የጣሰ አጀንዳ ለውይይት ቀርቧል የሚል ድምዳሜ […]

የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ አመራር አባል የሆነው ወጣት ብርሃኑ ገረፋ ትናንት ሐምሌ 22 ቀን 2005 ዓ.ም. ሳሪስ አካባቢ የፓርቲውን በራሪ ወረቀት ሲበትን በደህንነትና በ6 ፖሊሶች በህገወጥ መንገድ መታሰሩን ፓርቲው በተለይ ለፍኖተ ነፃነት አስታውቋል፡፡ ወጣት ብርሃኑ በደህንነት አባሉ በመሳሪያ ሰደፍ ጀርባውንና ጭንቅላቱን ከመመታቱ በተጨማሪ ፖሊሶችም እጁን ጠምዝዘው በቦክስ ግራ ጉንጩን መመታቱ ተጠቁሟል፡፡ በእስር ቤት ውስጥ አንድ […]

ከተደበደቡት ዘጠኝ ሰዎች መካከል ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሶስት ተጎጅዎች ወደ አማራ ክልል ቻግኒ ከተማ መጥተው በግል ክሊኒኮች እየታከሙ መሆናቸውን አስታማሚዎች የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ከስፍራው ዘግበዋል፡፡ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸው ቻግኒ ከተማ እየታከሙት የሚገኙት ግለሰቦች አቶ በለጠ መንግስቴ፣ አቶ ጥላሁን ገበየሁ፣ አቶ አቸነፍ ወንዴ የተባሉ ተፈናቃዮች ናቸው፡፡ በወረዳው ከ5200 በላይ ግለሰቦች መፈናቀላቸው የሚታወስ ሲሆን እስከአሁን ሁሉም ሙሉ […]

በአሰበ ተፈሪ በዓላማ የሚመስሏቸውንና በጥቅም የገዟቸውን የሀ/ስብከቱን ሥራ አስኪያጅና ጸሐፊ በመያዝ የደ/ጽዮን ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት እና በወረዳው የማኅበረ ቅዱሳን ጽ/ቤቶች እንዲታሸጉ አድርገዋል፡፡ ራሱን ‹‹ማኅበረ ናታኒም›› እያለ የሚጠራው በቅ/ሲኖዶስ የተወገዘው ሃይማኖተ አበው ርዝራዥ፣ የደ/ጽዮን ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤን ምርጫ በአባላቱ ብቻ ባቋቋመው አስመራጭ ኮሚቴ በኩል ለመቆጣጠርና አባላቱን በማስመረጥ በደብሩ ተጽዕኖውን ለማጠናከር …

Normal
0

false
false
false

MicrosoftInternetExplorer4

/* Style Definitions */
table.MsoNormalTable
{mso-style-name:”Table Normal”;
mso-tstyle-rowband-size:0;
mso-tstyle-colband-size:0;
mso-style-noshow:yes;
mso-style-parent:””;
mso-padding-alt:0cm 5.4pt 0cm 5.4pt;
mso-para-margin:0cm;
mso-para-margin-bottom:.0001pt;
mso-pagination:widow-orphan;
font-size:10.0pt;
font-family:”Times New Roman”;
mso-fareast-font-family:”Times New Roman”;
mso-ansi-language:#0400;
mso-fareast-language:#0400;
mso-bidi-language:#0400;}

Normal
0

false
false
false

MicrosoftInternetExplorer4

/* Style Definitions */
table.MsoNormalTable
{mso-style-name:”Table Normal”;
mso-tstyle-rowband-size:0;
mso-tstyle-colband-size:0;
mso-style-noshow:yes;
mso-style-parent:””;
mso-padding-alt:0cm 5.4pt 0cm 5.4pt;
mso-para-margin:0cm;
mso-para-margin-bottom:.0001pt;
mso-pagination:widow-orphan;
font-size:10.0pt;
font-family:”Times New Roman”;
mso-fareast-font-family:”Times New Roman”;
mso-ansi-language:#0400;
mso-fareast-language:#0400;
mso-bidi-language:#0400;}

/መሰፍን/ማርያም

ቀደምሲል « እግዚአብሔርና እኛ» በሚለው ርዕስ ስር የተነገረውን አንዳንድ ሰዎች ሌላ ትርጉም በመስጠት ጸረሃይማኖት ሊያስመስሉት ይሞክሩ ይሆናል። አይደለምእንዲያውም ሃይማኖትንና ሃይማኖተኛነትን የሚያጸናነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም ዓይነት ሃይማኖት ቢኖረው ለእግዚአብሔር ያለው ፍቅርና በእግዚአብሔርም ላይ ያለው እምነት ብርቱ ነው።ይህንን ከመገንዘብ የተነሳና በዚያው ፍቅርና እምነት ላይ የተመሠረተ ስለሆነ በምንም መንገድ ጸረ ሃይማኖት መስሎ ሊታይ አይገባም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሐምሌ ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ቅዳሜ ከላሊበላ ሰቆጣ ይሰራል ተብሎ የነበረው መንገድ ባለመሰራቱ የተበሳጩት   የከተማዋ ነዋሪዎች በራሳቸው አነሳሽነት የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን፣ ወጣቶቹ አጋጣሚውን በመጠቀም ” ነጻነት እንፈልጋለን፣ እኛ ወታቶች ብዙ ችገሮች አሉብን፣  ሰቆጣ መብት የለም፣ ብልጭጭልታ የእድገት ምልክት አይደለም፣ እድገት የለም፣ መንገድ ላሳ ህዝብ መንገድ ሊከለከል አይገባውም፣ ልማት በተግባር እንጅ …

ሐምሌ ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጣና ሞባይል የኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን ደንበኛ ከሆነው ከቻይናው ግዙፍ ቴሌኮም ኩባንያ ዜድ.ቲ.ኢ  ጋር በጋራ ለመስራት በደረሱት ስምምነት መሰረት በ2003 ዓ.ም በ50 ሚሊየን ብር ወጪ በባህርዳር ከተማ ዘመናዊ የሞባይል ቀፎዎችን ማምረቻ ፋብሪካ በመክፈት ምርቱን ለአገር ውስጥ ገበያ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ፋብሪካው ባልታወቀ ሁኔታ  ከቀጠራቸው ሠራተኞቹ መካከል ወደ 70 የሚጠጉትን …

ሐምሌ ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአራት ፓርቲዎች ግንባር የሆነው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በአደባባይ ላይ ሊያካሂድ ያቀደውን የአደባባይ ሰልፍ ተገዶ ወደ ሕዝባዊ ስብሰባ መቀየሩ ታውቋል፡፡ በዚሁ መሠረት ግንባሩ የፊታችን እሁድ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ/ም ሕዝባዊ ስብሰባ መጥራቱን የአዲስ አበባው ዘጋቢ ገልጿል፡፡ ከወቅታዊ የአገራችን ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ሐምሌ 7 ቀን 2005 …

ምሥራቅና በደቡባዊ አፍሪካ ሃገሮች ውስጥ በኤድስ ላይ ተጨብጧል የሚባለውን ግዙፍ ስኬት የተባበሩት መንግሥታት የኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ መርኃግብር ባለሥልጣናት አሞግሰውታል፡፡

ከኤድስ ጋር የተያያዘው የሞት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን እና ለኤችአይቪ እየተጋለጠ ያለው ሰው ቁጥርም በብዙ እየወረደ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያወጣው አዲስ ሪፖርት ጠቁሟል፡፡

ይህ ክስተት መድኃኒት በብዛት የመገኘቱ ውጤት ነው የሚለው ይህ ሪፖርት ፈተናዎቹ ግን እንዳሉ እንደሚቀጥሉ አሳስቧል፡፡

ሪፖርቱ ይፋ የተደረገው ዛሬ ጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪካ ላይ በተካሄደው የአህጉሪቱ የጤና ባለሥልጣናት ስብሰባ ላይ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ከጋምቤላ በስተቀር በብዙ የሃገሪቱ ክፍሎች የኤችአይቪ ሥርጭት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን በስብሰባው ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር …

የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ ንቅናቄ የጀመረው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በአዲስ አበባ የሚገኙ ዜጎች ህገ መንግስቱን በመጨፍለቅ በጸረ ሽብርተኝነት ሽፋን ፖለቲከኞችን፣አክቲቪስቶችን፣ጋዜጠኞችንና የመንግስትን በሃይማኖት ጣልቃ መግባት የሚቃወሙ ዜጎችን በሽብርተኝነት በመወንጀል ወህኒ እያወረደ ያለውን የጸረ ሽብር አዋጅ በመቃወም እንዲሰረዝ ፊርማቸውን በፓርቲው ጽ/ቤት በመገኘት በተዘጋጀው የፊርማ ሰነድ ላይ እንዲፈርሙ የሚጠይቅ በራሪ ወረቀት በማዘጋጀት ለህዝቡ ማሰራጨት […]

የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች ከሀገር እንዳይወጡ በቅርስ ጥበቃ ረገድ መስሪያ ቤታቸዉ ከሌሎች ድርጅቶችና የመንግስት ተቋማት ጋር እየሰራ መሆኑን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን የህዝብና ዓለማቀፍ ግንኙነት ረዳት ሃላፊ አቶ ፋንታ በየነ ለዶቼ ቬለ ገለጹ።

በግጥም ምሽት የኪነጥበብ አድናቂዎችን ሲያዝናኑ ወራት አስቆጥረዋል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ የካንሰር ታማሚ ህፃናትን መደገፍ ብቻ ሳይሆን ኅብረተሰቡ ስለበሽታዉ ያለዉን ግንዛቤ ለማስፋት እየጣሩ ነዉ።

በአሁኑ ጊዜ በስዊዘርላንድ የስደተኞች አቀባበል መርህ ከቀድሞው እየጠበቀ መምጣትና ፣ ሌሎችም ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ ተፅእኖዎች በበስዊዘርላንድ የተገን ጠያቂዎችን ህይወት አስቸጋሪ አድርጎታል እንደ አቶ ምስጢረ ።

የዛሬ ዓመት በቁልቢ በዓል ሲባርኩን የነበሩት የቀድሞ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ በአፀደ ስጋ ተለይተውን በሌሉበት አዲሱ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በተገኙበት የቁልቢን ባዕልን አክብረናል፡፡ በቁልቢ ገብርኤል ቅፅር ጊቢ ከአውደ ምዕረቱ ጀርባ ባለው መግቢያ ተሰቅለው ከነበሩት የቀድሞው ፓትርያርክ ምስሎች አንደኛው በፍፁም ደብዝዞ ሌላኛው በመስታውት ተሸፍኖም ቢሆን ግርማ ሞገስ ርቆት ቢታይም በሌላ በኩል ደግሞ በረጅም ተፅፎ የነበረውን የማዕረግ ስም […]