ከጋዳፊ ውድቀት መለስ ይማር!
ሊቢያን ለአርባ ሁለት ዓመታት ቀጥቅጠው የገዙት ኮሎኔል ጋዳፊ በትውልድ መንደራቸው ስርት ውስጥ እጎርፍ ማስወገጃ ቱቦ ውስጥ ተገኙ። እንደተባለው ከሆነ ከወርቅ የተሠራ ሽጉጣቸውን የመጠጣት እድል እንኳን ሳያገኙ በአልባሌ ጥይት ቆሰሉ። “አይጦች፣ በረሮዎች፣ ሃሽሻሞች፣ ዱርየዎች” እያሉ በሰደቧቸው እና የመድፍ ናዳ ሲያወርዱባቸው በነበሩ ወጣት አብዮተኞች ጫማ ተረገጡ፣ ተጎሸሙ። በጥፊ ተመቱ፤ ተዋረዱ። በመኪናም ታስረው ተጎተቱ:: እየጮሁ በአሳዛኝና በአዋራጅ ሁኔታ […]