በአየር ሃይል አውሮፕላን ጥቃት ተሰዘነረ -አርአያ ተስፋማሪያም
90 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላትን የጫነ የአየር ሃይል አንቶኖቭ አውሮፕላን ከመጋየት መትረፉን የቅርብ ምንጮች ያደረሱኝ መረጃ ያመለክታል። ዛሬ ጠዋት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት አቆጣጠር 90 የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪዎችን አሳፍሮ ደቡብ ሱዳን – ሃዲጉሊ የተባለች ግዛት የደረሰው አንቶንቭ አውሮላን ወደ መሬት እየወረደ ባለበት ወቅት ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በዲሽቃ በተተኮሰ ሁለት ጥይት በጎን በኩል እንደተመታ ምንጮቹ ጠቁመዋል። በአብራሪዎቹና ወታደሮቹ ድንጋጤ ተፈጥሮ እንደነበረ ያመለከቱት ምንጮቹ የተተኮሰው ጥይት ሞተሩ አካባቢ ቢያርፍ ኖሮ አውሮፕላኑ ሊነድ ይችል እንደነበረ አስታውቀዋል። አንቶኖቭ አውሮፕላኑ ባላፈው ሳምንት በአንዱ የሞተር ክፍል ብልሽት ገጥሞት ለሰባት ቀናት በጥገና ላይ እንደሰነበተ ምንጮቹ አስታውቀዋል። በደቡብ ሱዳን በየጊዜው ከሚሰማራው የመከላከያ ሰራዊትና ሰላም አስከባሪ ሃይል የመከላከያ ጄኔራሎች በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ከሰራዊቱ እየዘረፉ ኪሳቸው እንደሚያስገቡ የሚታወቅ ሲሆን ዝርዝር መረጃውን በቅርቡ የምንመለስበት ይሆናል።
The post በአየር ሃይል አውሮፕላን ጥቃት ተሰዘነረ -አርአያ ተስፋማሪያም appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.