Tag: News in Amharic
Amharic News 1800 UTC – ዲሴምበር 13, 2013
News, Community Heroes or Call-in, Crossfire and African Topics
በእሥራኤል ደም ልገሳ ያስከተለዉ ዉዝግብ፣
በኢትዮጵያ ተወልደው፣ በ 3 ዓመታቸው እሥራኤል በመግባት ፤ በዚያ ያደጉ የተማሩና የፓርላማ (ክኔሰት) አባል የሆኑት ፔኒና ታማኖ-ሻታ የተባሉት የ 32 ዓመት ወ/ሮ ፣ ከትናንት በስቲያ ደም ለመለገሥ ተዘጋጅተው ፤ በጤና ጥበቃ ሚንስቴር መመሪያ
13.12.2013 ዜና 16:00 UTC
የዓለም ዜና
የሶማሊያ ፕሬዝደንትና አዲሱ ጠ/ሚኒስትራቸው
የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ ትላንት አዲስ ጠ/ሚ መሰየማቸው ተዘገበ። ፕሬዝደንት መሐሙድ የቀድሞውን ጠ/ሚ ካባረሩ ሳምንታት ቢቆጠሩም ጠ/ሚ ሺርዶን ግን ኣሻፈረኝ ብለው ቆይተው ነበር። የሶማሊያው ም/ቤት የመተማመኛ ድምጽ ከነፈጋቸው በኃላ ግን ሺርዶን ስልጣን መልቀቃቸው ታውቐል።
የፌስቡክ ጎልማሳ መሆን
በፌስቡክ ላይ የተደረገ አንድ አዲስ ጥናት እንደሚያመላክተው አሁን አሁን ከወጣቱ የፌስ ቡክ ተጠቃሚ ቁጥር የጎልማሳው እየበለጠ መጥቷል።
ማንዴላና የስፖርት ውርሳቸው
የስፖርት አዋቂዎች እንደሚሉት ማንዴላ ከዓለማችን ፖለቲከኞችና የመብት ተሟጋቾች በተለየ ስፖርትን በሰላም መሣሪያነት ተጠቅመዋል ። ለስፖርት ትልቅ ቦታ ይሰጡ የነበሩት ማንዴላ በተለያዩ ዓለም ዓቀፍ የስፖርት ተቋማትና በስፖርት ዓዋቂዎች ዘንድ ትልቅ ከበሬታ አላቸው ።
የመድረክ ማስጠንቀቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሰላማዊ ትግል መንገድ እየተዘጋ ነዉ አለ፦ ህዝቡን ወደ ትጥቅ ትግል እንዳይወስድ እንደሚሰጋ አስጠነቀቀም።
የተከበሩ አፍሪካዊ ኔልሰን ማንዴላ ስንብት
ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሀገሬ) 
ኔልሰን ሮሺስላሽላ ማንዴላ ለነጻነት የሚያደርጉትን ረዥሙን ጉዞ እ.ኤ.አ በ2013 መገባደጃ ወር ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ደመደሙ።
የፕሪቶሪያው ስብሰባና የኢትዮጵያ ቦታ – ዲሴምበር 13, 2013
Pritoria, Ethiopia, Mandela
ESAT Radio: Dec 12
ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen
የሽብር ክሥ የተመሠረተባቸው በነፃ ተለቀቁ – ዲሴምበር 13, 2013
Charged with terrorism released, Ethiopia
የድምጻችን ይሰማ ዋና መሪዎች እንዲከላከሉ ተበየነባቸው
ታህሳስ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብር ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የድምጻችን ይሰማ መሪዎች ተከላከሉ መባላቸውን ጠበቃ ተማም አባ ቡልጉ ተናግረዋል። 12 ሰዎች በነጻ የተለቀቁ ሲሆን፣ እነ አቶ አቡበከር አህመድና ሌሎች ደግሞ በተከሰሱበት ሽብር የማድረግ ወንጀል ሳይሆን ሽብር በማነሳሳት ጉዳይ ላይ እንዲካለከሉ ተበይኖአል። ሙራድ ሹኩር ጀማል፣ ኑሩ ቱርኪ ኑሩ፣ ሼህ ባህሩ ኡመር ሸኩር …
መድረክ በኢትዮጵያ ያለው አፈና መባባሱን ገለጸ
ታህሳስ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መድረክ ዓርብ ታህሳስ 4 ቀን 2006 ዓ.ም በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ ሲሆን፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና ለኢሳት እንደገለጹት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው አፈና እየተባባሰ መሄዱ መግለጫውን ለመስጠት አስገድዷቸዋል። የሳውድ አረቢያ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደውን እርምጃ ለመቃወም መድረክ ቢጠይቅም በገዢው ፓርቲ መከልከሉን ዶ/ር መረራ አውስተዋል …
የሕገመንግስት የትርጉም ጥያቄ ያስነሳው የአቶ መላኩ ጉዳይ ዛሬም አልተቋጨም
ታህሳስ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ ክሳቸው በየትኛው ፍርድ ቤት ይታይ በሚለው ጉዳይ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የመጨረሻ ውሳኔውን እንዲያሳውቅ ሲል የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ትእዛዝ በመስጠት ለታህሳስ 22 ቀን 2006 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። ፍ/ቤቱ ቀደም ሲል በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ጉዳዩን …
በኔልሰን ማንዴላ የመታሰቢያ ዝግጅት ላይ መስማት ለተሳናቸው ትርጉም ያቀርብ የነበረው ግለሰብ የተሳሳተ መልእክት ሲያስተላልፍ ነበር ተባለ
ታህሳስ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ማክሰኞ በደቡብ አፍሪካ ስዌቶ በተደረገው የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት የኔልሰን ማንዴላ መታሰቢያ ከመድረክ ይተላለፍ የነበረውን ዝግጅት በምልክት ቋንቋ መስማት ለተሳናቸው ዜጎች እንዲያስተላልፍ ተመድቦ የነበረው ሰው፤ ያሳይ የነበረው አካላዊ እንቅስቃሴና ምልክት የውሸት እንደነበር መጋለጡን ዓለማቀፍ ብዙሀን መገናኛ እየዘገቡ ነው። ድርጊቱ የደቡብ አፍሪካን መንግስትና በ ዓለማቀፍ ደረጃም መስማት የተሳናቸውን የህብረተሰብ …
አዲስ አበባና ዋሽንግተን ዲሲ የእህትማማችነት ስምምነት ፈርሙ
አዲስ አባባና ዋሽንግተን ዲሲ በእህትማማች ከተማነት ለመተሳሰር ትላንት እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ በከንቲባዎቻቸው በኩል ፊርማቸውን አኑረዋል።
የሽብር ክሥ የተመሠረተባቸው በነፃ ተለቀቁ
እንዲከራከሩ ብይን የተሰጣቸው የሕግ ድንጋጌ እንዲለወጥ ታዘዘ፤ በሙስና የተከሰሱ ጉዳይም ታይቷል፡፡
ከሳውዲ አረቢያ የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን
የሳውዲ አረቢያ መንግስት ህገወጥ ስደተኞች ያላቸውን የውጪ ዜጎች ከኣገሩ ለማስወጣት በጀመረው መጠነ ሰፊ ዘመቻ አኩዋያ የኢትዮጵያ መንግስትም 30 000 ያህል ዜጎችን ወደ ኣገራቸው ለመመለስ መገደዱን ባለፈው ወር ማስታወቁ ይታወሳል።
UTC 16:00 የዓለም ዜና 121213
የዕለቱ ዜና
የኢትዮጵያ ሙስሊም መሪዎች የፍርድ ሒደት
የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት ጥርጣሬ ካሰራቸዉ የኢትዮጵያ የሙስሊሞች ጉዳይ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎች፥ አባላትና ተባባሪዎች መካካል አስራ-ሁለቱ በነፃ እንዲለቀቁ ተወሰነ።
ሻምበል ጉታ ዲንቃ የማንዴላ ልዩ ጠባቂ
ከግማሽ ም/ዓመት በፊት አንጋፋው የደቡብ ኣፍሪካ የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ኢትዮጵያ ውስጥ ስልጠና ላይ በነበሩበት ወቅት የተቃጣባቸውን የግድያ ሙከራ ያከሸፉት ኢትዮጵያዊ ወታደር በቀብራቸው ለመገኘት እያሰቡ ነው።
የኬንያ 50ኛ ዓመት የነጻነት ክብረ-በዓል
ኬንያ የምሥራቅ አፍሪቃ የዕድገትና መረጋጋት ሞተር መሆኗ ነው የሚነገርላት።ፕሬዚዳንት ዑሑሩ ኬንያታና ምክትላቸው ዊልያም ሩቶ በሄግ ፤ ኔዘርላንድስ ዓለም አቀፍ የጦር ወንጀለኞች መርማሪ ፍርድ ቤት፤ ቢከሰሱም፤ አገራቸው፤ እ ጎ አ በ 2010 አዲስ
መስቀል ክብረ በዓል- በዓለም የቅርስ መዝገብ
የኢትዮጵያዉ የመስቀል በዓል አከባበር በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ የትምህርትና ባህል ማዕከል /UNESCO/መዝገብ በዓለም ቅርስነት ተመዝግቦአል። የዚህ ክብረ በዓል በዓለም መዝገብ መፃፉ ለኢትዮጵያ የሚያመጣዉ ፋይዳ ምን ይሆን? ኢትዮጵያ እስከ ዛሪ ዘጠኝ ታሪካዊ ቅርሶችን በ UNESCO መዝገብ በማፃፍ ከአፍሪቃ ቀዳሚዋ ሀገር መሆንዋ ያዉቃሉ?
የአ/አበባ እና የዋሽንግተን ዲሲ እህትማማች ከተሞችነት
አዲስ አበባ እና ዋሽንግተን ዲሲ እህትማማች ከተሞች ሆኑ። ሁለቱ ከተሞች ይህን የሚ,ለከተውን ስምምነት ትናንት በዩ ኤስ አሜሪካ የዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ተፈራርመዋል። ስምምነቱ የኤኮኖሚ፣ የትምህርት እና የልማቱን ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክር ፣ የልምድ ልውውጥ እንዲኖር የሚያደርግ መሆኑ ተገልጾዋል።
በኢትዬጲያ ሙስሊሞች ታሳሪዎች ላይ መንግስት የጥፋተኛነት ውሳኔ አስተላለፈ
መንግስት በኢትዬጲያ ሙስሊሞች ላይ የጥፋተኘነት ውሳኔ ማስተላለፉን ምንጮች አስታወቁ፡፡ ለታህሳስ 3 በተቀጠረው የብይን ቀነ ቀጠሮ መሰረት 10 ተከሳሾችን ነፃ ናቸው ሲል ፍርድ ቤቱ ያሰናበተ ሲሆን የተቀሩት ላይ ግን በሽብር ድርጊት ፈፃሚነት ወንጀል ጥፋተኛ ናችሁ ሲል ብይን አስተላልፏል፡፡ በዚህም መሰረት ሁሉም በዕድሜ የገፉት አባቶች ዶ/ር ከማል ገለቱ፣ሼህ አብዱረህማን፣ሼህ ሃጂ ኢብራሂም፣ ሼህ ጣሂር፣.ሼህ ሱልጣን አማን፣ ኡስታዝ ጀማል […]
በራሳሽን ላይ የምንሰለፍበት ቀን ናፈቀኝ? ኤርሚያስ ሽፈራው
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
A New Journalists Association is Under-formation in Ethiopia
![]() |
| The Press Release (Amharic) |
- for the respect of Freedom of Expression granted in the FDRE constitution article 30;
- for the benefit of journalists;
- for promoting professional excellence of journalists through trainings;
- for strengthening the relationship/communication among journalists;
- for facilitation of financial, material and legal support whenever needed;
- for recognizing journalists who are contributing positively to the sector;
- The term ‘Forum’ might be confusing with a political coalition that is referred by the same term – Forum;
- The committee should not be called ‘founding’ but ‘coordinating’ as it is working to coordinate;
- Working for the respect of ‘Freedom of Expression’ should not be the role of the ‘Forum’ rather practicing it;
#HRDay2013፤ ከሰው በታች የሆኑ ሰዎች አሉ ብለው የሚያምኑ ኢትዮጵያውያን አሁንም አሉ
ሰውዬው ያወራልን ሌሊት ወደጅብነት ስለሚለወጡ ሰዎች ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ሁላችንም አፍረን ስናፈገፍግ ከመሐላችን አንዱ “እንዲህ ዓይነት ነገር እውነት ነው ብለህ ታምናለህ?” ብሎ ጠየቀው፡፡ እሱ ሆዬ በሙሉ መተማመን እኛን እንዳላዋቂ በመቁጠር ሌሊት ወደጅብነት የሚለወጡ ሰዎች እንዳሉ ያስረዳን ጀመር፡፡
ይህንን ትዝታዬን የቀሰቀሰው ትላንት ጋዜጠኛ Masresha Mammo የጻፈው ማስታወሻ ነው፡፡ ርዕሰ ጉዳዩ የተለየ ስለነበር እኔ ግን ለዚህች ጽሑፌ የሚጠቅመኝን ገንጥዬ አጣቅሳለሁ፡፡ ማስረሻ እንዲህ ይላል፤
‹‹…ተወልጄ ያደግኹት ከእንጦጦ ተራራ ስር ቀጨኔ በምትባል ሰፈር ውስጥ ነው፡፡ […] ቀጨኔ ላይ ያለው ማኅበረሰብ ወደአዲስ አበባ የተሰደደው የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ሲል አልነበረም፡፡ ቡዳ ነው የሚል ስም ስለተለጠፈበት ‹ልጆቻችንን በልተው ጨረሷቸው› በሚል ግድያው ስለበዛበት ነበር፡፡ አንድ ቀጥቃጭ አባቱ፣ ወይም ሸማኔ ወንድሙ፣ አሊያም ሸክለኛ እናቱ በዚሁ ሰበብ ሲገደሉበት፤ በምላሹ እሱም ደሙን ተወጥቶ ይሸሻል፡፡ ይሰደዳል፡፡…
‹‹ይኼ ማኅበረሰብ ለሺሕ ዓመታት ለኢትዮጵያ ሕዝብ የጀርባ አጥንት ኾኖ ቆይቷል፡፡ በቴክኖሎጂ ላልሰለጠነችው ኢትዮጵያ ማረሻ እና ወገል ያቀርባል፣ እንዳይበርዳቸው ልብስ ይሠራላቸዋል፣ ለመመገቢያቸው የሚኾኑትን ሸክላዎች እና የዕደ ጥበብ ውጤቶች ሁሉ ይሰጣቸዋል፡፡ ያለዚህ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያን ወደኋላ ዞር ብላችኹ አስቧት፡፡ [ማኅበረሰቡ] በሚኖርባት በየትኛውም የአገሪቱ ክልል ግን ስሙ ቡዳ ነው፡፡
‹‹ቡዳ ማለት ደግሞ፤ ቀን ቀን ጋቢ ለብሶ የሚኖር፣ ማታ ማታ ወደ ጅብነት የሚቀየር ማለት ነው፡፡ ይህ አስተሳሰብ እና አመለካከት የሚመራው በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ውስጥ ነበር፡፡…››
ማስረሻ ‹‹ነበር›› ይበል እንጂ ዛሬም ድረስ ከዚህ ባልተለየ መንገድ የሚያምኑ ‹‹ምሁራን›› ሳይቀሩ አሉ፡፡ ልዩነቱ በዚህ ዘመን በተለይ በከተማ እንዳይገዳደሉ ሕግ ያግዳቸዋል፤ በገጠር ግን አሁንም በግልጽ አለ፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት የሄድኩበት የገጠር አካባቢ ውስጥ ካሉ ‹‹ቡዳ›› ወይም ‹‹ባለእጅ›› ከሚባሉ ሰዎች/ቤተሰብ አባላት ጋር እንዳልገናኝ እና ‹‹ዓይናቸው እንዳልገባ›› አብረውኝ ያሉ ሰዎች ሲጠብቁኝ እና ሲያከላክሉኝ ነበር፡፡ ዛሬም እናቴን ብቻ ሳይሆን ወጣት ጓደኞቼን ሳይቀር ቡዳ የሚባል ነገር የለም ብዬ ማሳመን ይከብደኛል፡፡
ይህ ሰዎችን የማግለያ ሰበብ ነው፡፡ ሰዎችን ንዑስ-ሰው አድርጎ የመቁጠር አባዜ ነው፡፡ የሰብኣዊ መብት ዋና ፅንሰ ሐሳቡ ደግሞ ሰዎች ሁሉ ዕኩል ናቸው የሚለው ነው፡፡ ያንን የማያምኑ ሰዎች ባሉበት አገር በመንግሥት ጥረት ብቻ ሰብኣዊ መብት አይከበርም፡፡
—
እዚህ ጽሑፍ ላይ የተሰጡ ለማየት እዚህ ጠቅ ያድርጉ!
የሥልጣኔ ሞት- ከድርሰት ሞት
የዛሬ 600 ዓመት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የተባለ ኢትዮጵያዊ ደራሲ ‹አርጋኖን› የተሰኘ መጽሐፍ ይደርሳል፡፡ ይህንን መጽሐፍ የተመለከቱ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትም እጅግ ያደንቁና ለንጉሡ ለዐፄ ዳዊት ያቀርባሉ፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም መጽሐፉን ተመልክተው በማድነቅ በወርቅ ቀለም እንዲጻፍ አዘዙ፡፡ አባ ጊዮርጊስንም ሸለሙ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላም አባ ጊዮርጊስ ‹መጽሐፈ ምሥጢር› የተባለ መጽሐፍ ደረሰ፡፡ ይህንን የተመለከቱ ሊቃውንትም አድናቆታቸውን ‹‹ቄርሎስና ዮሐንስ አፈወርቅ በሀገራችን ተገኙ፤ ኢትዮጵያም እንደ ሮምና ቁስጥንጥንያ፣ እንደ እስክንድርያም ሆነች› ብለው በማሸብሸብ ነበር የገለጡት፡፡
በዚህች ሀገር ጥንታዊ ታሪክ መጻሕፍትን መጻፍ ብቻ ሳይሆን፤ ማንበብ፣ ማስነበብ፣ ማስጻፍ፣ ሲነበቡ መስማት ጭምር እጅግ የተከበረ ነገር ነበር፡፡ የተከበረ ብቻም ሳይሆን የቅድስናም ምንጭ ነበር፡፡ በየገድላቱና ድርሳናቱም ‹የጻፈ ያስጻፈ፣ ያነበበ የተረጎመ፣ የሰማ ያሰማ› የሚሉት ቃል ኪዳኖች መጻፍን ብቻ ሳይሆን የተጻፈውን ማንበብ፣ ማንበብ ለማይችሉትም ድምጽን ከፍ አድርጎ እያነበቡ ማሰማት፣ ሲነበብም በጽሞና መስማት ጭምር ዋጋ እንዲኖራቸው ያደረጉ ነበሩ፡፡ የደራስያኑ መጻሕፍት እንዳሁኑ በማተሚያ ማሽን በብዛት አይባዙም ነበርና ለጸሐፊዎች ከፍሎ ማስጻፍ፣ ዋጋ ተቀብሎ በሚገባ መጻፍ የሚያስመሰግን የሚያጸድቅም ነገር መሆኑን ኢትዮጵያውያን ያምኑ ነበር፡፡
የደራስያኑ የድርሰት ሥራ የተወደደ፣ ባለቤትነቱም የተከበረ በመሆኑ በቃል የሚፈስሰው ቅኔ እንኳን ‹የእገሌ ቅኔ; እየተባለ ይጠቀስ ነበር እንጂ የባለቤትነት መብቱን የሚያስከብርለት ሕግና ሕግ አስከባሪ አካል የለም ተብሎ አይደፈርም ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ጎጃም ከመምህሩ የሰማውን ቅኔ ትግራይ ሄዶ እንደራሱ አድርጎ ሲቀኝ የተሰማ ተማሪ ቅኔውን ሲጨርስ ‹ቅኔያቸውስ ደረሰን፣ ለመሆኑ የኔታ ደኅና ናቸው?› የሚል ውርደት የገጠመው ለደራስያኑ የባለቤትነት መብት ጠበቃ የሆነ ማኅበረሰብ ስለነበረን ነው፡፡ የጎንደሩ ደብረ ብርሃን ሥላሴ ለሸዋው ደብረ ብርሃን ሥላሴ 2000 መክሊት ወርቅ ‹ደብረ ብርሃን› የሚለውን ስም ለመጠቀም የከፈለውኮ ለባለቤትነት መብት ክብር የነበረው ሕዝብ ስለነበረን ነው፡፡
እነዚህ የዕውቀት ምንጮች ዕውቀታቸውን እንደ ጉንፋን ማጋባት እንዲችሉ መጻፍ አለባቸው፡፡ ጊዜ ወስደው፣ ዐቅም ሰብስበው፣ መረጃ አስሰው፣ ሰርዘው ደልዘው፣ ቀምረው ሰድረው መጻፍ አለባቸው፡፡ የምንጠቅሰው፣ የምንመራበት፣ ብርሃን የምናይበት፣ ዓይነ ልቡናችንን የምናበራበት የዕውቀት ማዕድ ማዘጋጀት አለባቸው፡፡ ይኼ ደግሞ የደራሲው የጸሐፊው ድርሻ ብቻ አይደለም፡፡ የጥንት እናቶቻችንና አባቶቻችን ቀለም ገዝተው፣ ብራና አስፍቀው፣ ለጸሐፊው ድርጎ ሰጥተው፣ ርስት ከፍለው፣ ዋጋ ቆርጠው፣ ሲጨርስም ሸልመው ያስጽፉ እንደነበረው ሁሉ ደራስያኑን የሚያበረታታ፣ የድካማቸውን ዋጋ እንዲያገኙ የሚያደርግ፣ ለውጥ የሚያመጣ ዓይነተኛ ሥራ ሠርተው ሲገኙም የሚሸልም መንግሥትና ሕዝብ ያስፈልጋል፡፡ ከወረቀትና ከማተሚያ ዋጋ እስከ ሥራ ግብር፣ ከማከፋፈያ ችግር እስከ መብት ማስከበር፤ ከትምህርት ቤት የንባብ ባህል እስከ ሀገራዊ የጽሕፈትና የንባብ አብዮት፣ ከዓመታዊ ሽልማት እስከ የማዕረግ ስሞች፣ የሚሰጥ ተቋማዊ አሠራርና ባህል ያስፈልገናል፡፡ የሀገር ሥልጣኔ ከድርሰት ሥልጣኔ እንደሚጀምረው ሁሉ የሀገር ሞትም ከድርሰት ሞት ይጀምራልና፡፡
በጅዳ ቆንስል በር ውላ የምታድረው እህት ክራሞት … ከነቢዩ ሲራክ
ይህችን እህት በጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት በር ተቀምጣ ካየኋት ሳምንት አልፏል። አልፎ አልፎ ላነጋግራት ብሞክርም መልስ አትሰጥም። መጀመሪያ የየኋት ቀን አካባቢ ከስራ ለተፈናቀሉ እህቶች አነሰም በዛ መጠለያ እያለ ፣ ለምን በር ላይ ትሆናለች? ብየ የጠየቅኳቸው የቆንስሉ ጸጥታ አስከባሪ ” አንተየ የዚህች እህት ጉዳይ አስቸጋሪ ነው ። ከመጠለያው ብዙ ቆይታለች ፣ አሁን በር ላይ የሆነችው ሃገር […]
ዲፕሎማቶችና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ስለኔልሰን ማንዴላ – ዲሴምበር 12, 2013
Ethiopians and Diplomats on Mandela, Addis Ababa, Ethiopia
ESAT Radio: Dec 11
ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen
የኔልሰን ማንዴላ መታሰቢያ በዋሽንግተን ዲሲው ብሄራዊ ካቴድራል
ባለፈው ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የደቡብ አፍሪካው የጸረ-ዓፓርታይድ እንቅስቃሴ መሪና የነጻነት አባት ኔልሰን ማንዴላ እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በዛሬው እለት በተካሄደ የጸሎት ስነ ስርዓት ታስበዋል።
በብሄራዊ ካቴድራል በተካሄደው በዚህ ሥነ ሥርዓት የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፥ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፥ የኮንግረስ አባላትና ዲፕሎማቶች፤ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
40 በ 60 እና 10 በ 90 የቤት እቅዶች መንግስትን ፈተና ውስጥ ጥለውታል
ታህሳስ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት በውጭ አገር ለሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ሀቅሙ ላላቸው ዜጎች የ40 በ60 እንዲሁም በአዲስ አበባ በአነስተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ዜጎች ደግሞ የ10 በዘጠና እና የ20 በ80 የቤት ልማት እዶችን ዘርግቷል። በ10/90 850 ሺ በ 20/80 ደግሞ 350 ሺ የአዲስ አበባ ነዋሪ ተመዝግቦ እድሉን በመጠባበቅ ላይ ሲሆን ከ12 ሺ በላይ በውጭ አገር …
በኢትዮጵያ ለሚታየው መብራት መጥፋት መስሪያቤቶች እርስ በርስ እየተካሰሱ ነው
ታህሳስ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች እና በሰሜን የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ከተሞች መብራት በተደጋጋሚ እየተቋረጠ ሲሆን፣ መብራት ሀይል የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተናበው ለመስራት አልቻሉም በሚል ወቀሳ አሰምቷል። በጉዳዩ ዙሪያ ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው የኢትዩጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ 40 በመቶ የሚሆነው ኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥ የሚፈጠረው በሰው ሰራሺ አደጋ ነው ያሉ …
በአርባ ምንጭ ዙሪያ የሚገኙ መምህራን ደሞዛቸውን ለመቀበል ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ
ታህሳስ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መምህራኑ ለኢሳት እንደተናገሩት ያለፍላጎታቸው ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ከደሞዛቸው ላይ ገንዘብ መቆረጡን በመቃወም የተቆረጠው ገንዘብ ተመልሶ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ሙሉ ደሞዛችን እስካልተሰጠን ድረስ ምንም አይነት ክፍያ አንቀበለም ያሉት መምህራኑ፣ እስከ ፊታችን አርብ ሙሉ ደሞዛችን የማይሰጠን ከሆነ የስራ ማቆም አድማ እንዳርጋለን ሲሉ አስጠንቅቀዋል። በደቡብ ክልል መንግስት ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል …
የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ፪
ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)
ባለፈው ሳምንት የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካን ተጨባጭ እውነታዎችን ቃኝቼ ተከታዩን ክፍል በይደር አቆይቼው እንደነበረ ይታወሳል፤ እነሆም ዛሬ እንዲህ እቀጥላለሁ፡-
ሐረር እንደ ማሳያ
(መቼም ኢህአዴግ በብቸኝነት የሚኩራራበት የፖለቲካ ‹ስኬት›፣ ለዘመናት አንድ ሆኖ የኖረ ሕዝብን ‹ብሔር ብሔረሰቦች› በሚል ከፋፋይ የ‹ክርስትና ስም› እጥምቆ በአደባባይ ማስጨፈር ከሆነ ሰነባብቷል፡፡
ዲፕሎማቶችና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ስለኔልሰን ማንዴላ
ኔልሰን ማንዴላን ማሠልጠንን ጨምሮ በደቡብ አፍሪካ ፀረ-አፓርታይድ ትግል ውስጥ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሚና መጫወቷን አንጋፋ ዲፕሎማቶች ተናግረዋል፡፡
Amharic News 1800 UTC – ዲሴምበር 11, 2013
News, Ethiopians in America, Americana, Democracy and Women and Family
ኢትዮጵያዊው ምርጥ የዩኒቨርስቲ ምሁር
በርካታ የሂሳብ ጥናትና ምርምር ሥራዎችን አቅርበዋል ።በራሳቸው ስም የሚጠራ የሂሳብ ስሌት እሳቤም ፈጥረዋል ። እኚህ መምህር ከመላው አሜሪካን ለውድድር ከቀረቡ 360 ከፍተኛ መምህራን እጎአ የ2013 ምርጥ የዩኒቨርስቲ ምሁር በመባል ተመረጠዋል ።
በሳይንስ የኖቤል ተሸላሚዎችና ምርምራቸው
ትናንት ፤ በእስቶክሆልም ፤ ስዊድን ፣ በኔልሰን ማንዴላ የመጨረሻ የስንብት ሥነ ሥርዓት ሳቢያ ታላላቅ ዓለም አቀፍ እንግዶች ተመናምነው ፣ ሆኖም ከ 1,300 በላይ ታዳሚዎች በተገኙበት ስብሰባ ፣ በ3 ቱም የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፎች ውድድር ፣ የዘንድሮዎቹ አሸናፊዎች ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።
ዙማ የገጠማቸው ተቃውሞ
ለቀድሞው የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት እና ዋነኛው የፀረአፓርታይድ ታጋይ ለኔልሰን ማንዴላ ትናንት በጆሀንስበርግ በሶዌቶ በሚገኝ ስቴድዮም ይፋ ስንብት በተደረገበት ጊዜ ከመላው ደቡብ አፍሪቃ የመጣው ሕዝብ
ግርማ ካሣ ቀልድ ጨምሯል! ነጻነት ዘለቀ
የግርማ ካሣን ጽሑፎች አልፎ አልፎ አነባቸዋለሁ፡፡ ሀገር ወዳድ መሆኑን ይጠቁማሉ – ጽሑፎቹ፡፡ ታታሪ ሰው ይመስለኛል፤ በጥረቱና በሀገር ፍቅር ስሜቱ እወደዋለሁ፡፡ ሁልጊዜ ሳይታክት ይጽፋል፡፡ ሳይታክቱ የሚጽፉ ብፁዓንነት የሚበዛባቸው ቢሆን ዕድለኞች ግን ናቸው፡፡ ብዙዎቻችን እየደከመን መጻፍ ቀርቶ ማንበባችንንም እያቆምን በምንገኝበት ሰዓት አዘውትሮ መጻፍ መታደል ነው፡፡ አያ ግርማ ሰሞኑን የጻፋቸውን ሁለት ያህል መጣጥፎች አንብቤያለሁ፡፡ ሁለቱም ግንቦት ሰባትን ለመንቀፍ […]
ESAT Radio: Dec 10 New
ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen
በጋሻው ደሳለኝ በይቅርታ ሚዛን ተመዘነ÷ ቀልሎም ተገኘ – ምእመኑን አስቆጣ አባቶችን አሳዘነ! የ‹ፀጉራሙ በግ› ታሪክ በሐዋሳ ተደገመ
‹‹በነበረው ሒደት በተለያየ ምክንያት የበደላችኹንን ኹሉ ይቅር ብለናችኋል›› (በጋሻው ደሳለኝ፣ ኅዳር ፳፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.፤ ለሐዋሳ ደ/ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ምእመናን የተናገረው) ‹‹ይኼ ጉልበት ላይ መውደቅ፣ ይቅርታ መጠየቅ በፍጹም እንዳያደርገው፡፡ ጉልበት ላይ መውደቅ፣ ይቅርታ መጠየቅ ማለት ጥፋተኛ ነኝ፤ ተሸማቅቄ እኖራለኹኝ ማለት ነው፤›› (በጋሻው ደሳለኝ፣ በግንቦት ፳፻፬ ዓ.ም. የክብረ መንግሥት ግብረ አበሮቹን ሲመክር) ይቅርታ ጠያቂ ሳይኾን …![]()
የኔልሰን ማንዴላ አሠልጣኝ፣ ኮሎኔል ፈቃዱ ዋኬኔ – ዲሴምበር 11, 2013
Fekadu, Wakene, Colonel, Nelson Mandela, traniner in Ethiopia
ዓለም ማንዴላን ተሰናበተች – ዲሴምበር 11, 2013
Mandela, Johannesburg, funerals


