መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በማዕከላዊ ሶማሊያ ሂራን ግዛት ራሶ መንደር አቅራቢያ የ20 ና የ25 ዓመት ወጣት የሆኑት ወንድማማቾች ሶማልያዊያንና አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ በአልሸባብ ታጣቂዎች በግፍ ተገለው ተገኝተዋል። ሁለቱ ወንድማማቾች ባለፈው ሳምንት ነበር በቡቃበል ከተማ ውስጥ በድንገት የኢትዮጵያ ወታደሮችና የሶማሊያ መንግስት ሰራዊቶች አካባቢውን ለቀው ሲወጡ በአልሸባብ ሚሊሻዎች ታግተው የተያዙት። የአካባቢው …



አንድ ጆሮና ጊዜ የገጠሙለት ሰው ነበር አሉ፡፡ ሰውዬው የተማረው ትምህርት የለውም፡፡ ሁለት ችሎታ ግን ነበረው፡፡ ሲባል የሰማው እውነትም ይሁን ስሕተት ልቅም አድርጎ ይይዝና ሌላ ቦታ ሄዶ የተማረው ያህል ያንደቀድቀዋል፡፡ ሁለተኛው ችሎታው ደግሞ አፈ ጮሌ ስለሆነ ነገር በምላሱ ይቆላል፡፡ ያንንም ይኼንንም እያቆላመጠ ከተማሩትና ከተመራመሩት በላይ ከብሮና ታፍሮ ይኖራል፡፡ አንድ ቀን የማያውቀውን ቀለም ሲያዜም የሰሙት ሊቅ አፍረው አቀረቀሩ፡፡ እርሱ ግን ከዕውቀት የደነገለ ነበርና አልገባውም፡፡ በኋላ ቀረብ ብሎ ‹ደኅና ነዎት የኔታ› አላቸው፡፡ እርሳቸውም ‹ደኅና ነህ›› ብለው ዝም አሉት፡፡ እርሱም ያላወቁት ስለመሰለው ‹አላወቁኝም መሰል መሪጌታ እኮ ነኝ› አላቸው፡፡ሊቁም ‹ዐዉቄሃለሁ› አሉት፡፡ እንዳቀረቀሩ፡፡ ‹ታድያ ምነው ካወቁኝ ከነ ማዕረጌ ሳይጠሩኝ ቀሩሳ› አላቸው፡፡ ‹አንተን አከብራለሁ ብዬ ሞያውን እንዳልሰድበው ፈርቼ ነው›› አሉት ይባላል፡፡
 
እኔም ‹እርቲስቶቻችን› የሚለው ቃል በትእምርተ ጥቅስ ያደረግኩት ሊቁ የፈሩትን ፈርቼ ነው፡፡ እንዳልተውባቸው ደግሞ ምን ብዬ እንደምጠራቸው ግራ ገብቶኝ፡፡ የአዲስ ዓመት ዋዜማውን መርሐ ግብር በዕለቱ ለማየት ስላልቻልኩ ቪዲዮውን ነው የተመለከትኩት፡፡ ሊነግሩን የፈለጉት ስለ እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ፣ ስለ ሀገራችን ዕድገት፣ ስላለፈው ስኬታችን ቢሆንም እንኳን የቀረበው ዝግጅት ግን አደገች የምትባለውን ኢትዮጵያን የማይመጥን፣ ጥበብ ዞር ብላ ያላየቺው፣ ከንግግር ከፍ፣ ከፉከራ ዝቅ ያለ፤ ከፕሮፓጋንዳ ወረድ፣ ከዲስኩር ራቅ፣ ከድንፋታ ጠጋ ያለ ወለፈንዲ ሆኖ ነው የታየኝ፡፡ 
 
በሀገራችንኮ የልቅሶ ሥነ ሥርዓት እንኳን ወግ አለው፤ ጥበብ አለው፤ ትርዒት አለው፤ ፍሰት አለው፤ ድባብ አለው፤ ፈጠራ አለው፤ ርቀት አለው፣ ምጥቀት አለው፤ ደረጃ አለው፡፡ ይኼኮ ወግ የለው፣ ጥበብ የለው፣ ትርዒት የለው፣ ፍሰት የለው፣ ፈጠራ የለው፣ ደረጃ የለው፡፡ ድፍረት ብቻ፡፡ መሪዎቻችን ግን ለምንድን ነው የጥበብ አማካሪ የማይኖራቸው? ለምንድን ነው ጥበብን ከሚሰድቡ ሰዎች ጋር አብረው የሚቆሙት? ለምን ‹አርቲስቶቹን› እናከብራለን ብለው ሞያውን ይሰድቡታል? ይህቺ ሀገርኮ ሰማየ ሰማያት ደርሰው የመጡ፣ ድንጋዩን አቅልጠው ጥበብ የሚያፈልቁ፣ አራት ጸሐፊ አስቀምጠው አንድ አንድ ምዕራፍ እየነገሩ መጽሐፍ የሚያስጽፉ፤ መሰንቆ እንደ ሰው፣ ክራር እንደ ወፍ፣ በገና እንደ መልአክ የሚያናግሩ፤ ስንትና ስንት ጠቢባን ነበሩባት፡፡ ከሐይቅ ዳር የሸንበቆ ውዝዋዜ ተነሥተው ኅሊና የሚመስጥ አቋቋም የቀመሩ፣ እያዜሙ ሲሄዱ እንኳን ገበሬውን በሬዎቹን የሚያስደምሙ ጠቢባን ነበሩባት፡፡ እንዴት በጥበብ ሀገር በኢትዮጵያ ጠቢብ ነኝ የሚል ሰው ‹ከዕውቀት ርቆ፣ ንጽሕ ጠብቆ› በድፍረት ይኖራል? ይኼኮ ሀገርን መድፈር ነው?  
አገሪቱ አድግበታልሁ፣ እመነደግበታለሁ፣ እለወጥበታለሁ፣ አሰላለፌን አስተካክልበታለሁ ብላ የደከመችበት የአምስት ዓመት ዕቅድ እንዴት በስሕተትና በድፍረት በተሞላ መድረክ እንዲታወጅ ይፈቀዳል? ይህንን ዕቅድ ባስታወስን ቁጥር ያንን ትልቅ ስሕተት እንድናስታውስ ለምን ተፈረደብን? ጥበብ ሳይሆን ድፍረት ትዝ እንዲለን ለምን ተገደድን? 
 
ጥበብ ምንም ዓይነት ይዘት ይኑረው የጥበብን ደረጃ ማሟላት ግን አለበት፡፡ ልማታዊም ሆነ አብዮታዊ፣ ዲሞክራሲያዊም ሆነ አምባገነናዊ፣ ይዘቱ ይለያይ እንጂ የጥበብ ደረጃው ግን አንድ ነው፡፡ ጥበብም የሚያሰኘው የጥበቡ ደረጃ እንጂ የያዘው ይዘት አይደለም፡፡ እንዴት ምግብ ቤቶቻችን ለምግብ አሠራርና አቀራረብ የሚጨነቁትን ያህል ለሀገራዊ መድረክ የሚጨነቅ ይጥፋ? እንዴት የበያይነቱ ምግብ ያህል ጥበብ በሀገራዊ መድረክ ላይ እንጣ?
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹ሀገራችን የራስዋ የሆነ ልዩ የዘመን አቆጣጠር አላት› ብለው ነገሩን፡፡ እውነት ነው ጠቅላይ ሚኒስትራችን የሀገር ባህል ልብስ ለብሰው በነገሩን የሀገራችን ልዩ የዘመን ቆጠራ እንስማማለን፡፡ ‹አርቲስቶቹ›› ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሳስተዋል፤ ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የዘመን አቆጣጠር የላትም›› አሉን፡፡ ‹‹አዲስ ዘመንም የሚብተው እንደ አውሮፓውያን በእኩለ ሌሊት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን የዘመን አቆጣጠራችን የተለየ ነው ያሉት ተሳስተው ነው›› አሉን፡፡ ኧረ እባክዎን ይጠይቁልን? ለምን ‹‹አርቲስቶቹ›› ጠቅላይ ሚኒስትሩን መቃወም ከፈለጉ የፖለቲካ ድርጅት መሥርተው በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው ተቃዋሚ ፓርቲ አያቋቁሙም? ደግሞስ ለሌሎች ያልተፈቀደ እንዴት ለእነርሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የቀጥታ የዓመት በዓል ሥርጭት እንዲቃወሙ ተፈቀደላቸው? እንደ አሜሪካ የምርጫ ክርክር በቀጥታ ሥርጭት ተቃዋሚና መንግሥት በአንድ መድረክ የሚቀርቡ ከሆነማ እውነትም ሀገሬ ተለውጣለች?
 
የዛሬ ዓምስት ዓመት እንዲሁ ያለ ስሕተት ‹አርቲስቶቹ› ሲሠሩ ዐውቀው በድፍረት ሳይሆን ሳያውቁ በስሕተት ነው ተብሎ ታለፈ፡፡ ዘንድሮ እንዳይደገምም ብዙዎች በሚችሉት ሁሉ አስቀድመው አሳሰቡ፡፡ ሰሚም መስሚያም ጠፋና ስሕተቱ በባሰ ሁኔታ ተደገመ፡፡ ሰውና ሰይጣን የተለያዩትኮ ከስሕተት በመታረምና ባለመታረም ነው፡፡ ወደ ሥልጣኔው መሄድ ሲገባን ወደ ስ…   
ጠቅላይ ሚኒስትር ሆይ፤ አሁን ማንን እንመን? እርስዎን እንመን ወይስ ‹አርቲስቶቻችንን››?
  

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “ስለሚያገባን እንጦምራለን” በሚል መሪ ቃል ከዛሬ አራት ዓመት በፊት የተቋቋመው የዞን ፱ ዐምደ መረብ ጸሃፍት የሕገመንግስቱ የመጻፍ ነጻነት በሚፃረረው መልኩ እንደ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በአሸባሪነት ተከሰው ካለ ፍትሕ በእስር ቤት የሚገኙት ጦማሪያኑና የቡድኑ አባላት ለፕሬስ ነፃነት ላደረጉት አስተዋፆ ዓለማቀፉን የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ተሸላሚ አድርጓቸዋል። የጋዜጠኞች መብት …

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የታዋቂዋ አርቲስት የቀብር ስነስርዓት በ ቅድስ ስላሴ ካቴደራል ወዳጅ ዘመዶቿና አድናቂዎቿ በተገኙበት ተፈጽሟል። አርቲስት ሰብለ ተፈራ በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ወሎ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አይቤክስ ሆቴል አካባቢ በግንቦት ወር 1968 ዓም. የተወለደች ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በንፋስ ስልክ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቃለች። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷንም በዛው …

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታጋይ መኮንን ተስፋዬ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት ድርጅቱ ከሚያዚያ እስከ ነሃሴ በነበሩት ወራት ከታች እስከ ላይ የ7 ዓመታት ግምገማ አድርጓል። የሞላ አመራር “ትህዴንን ወደ ድል አላበቃውም ይቀየር” የሚል ጥያቄ በመላ ሰራዊት አባላት መነሳቱን የተነገሩት ምክትል አዛዡ፣ ሞላ አስጎደም አገርህን አድን ከሚለው አዲስ ጥምረት መመስረት ጋር …

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ትህዴን፣ የቀድሞው የድርጅቱ መሪ ሞላ አስገዶም የተወሰኑ ተከታዮቹን በመያዝ በሱዳን በኩል አድርጎ ኢትዮጵያ መግባቱን ተከትሎ በሰጠው መግለጫ ” የተወሰኑ በትግሉ የቆዩና ግላዊ ጥቅማቸው የተነካባቸው ግለሰቦች ትግሉን ባሻቸው መንገድ ሊጠመዝዙት ስላልቻሉና በአብዛናው ታጋይ በመድረክ ተይዘው መፈናፈና ስላጡ ተስፋ ቆርጠው ከትግሉ ጎራ ሸስተዋል” ብሎአል። ንቅናቄው …

የባለፈው ሣምንት በኤርትራ የጋራ ንቅናቄ ከመሠረቱት አራት በትጥቅ ትግል የተሠማሩ ንቅናቄዎች የአንደኛው የትግራይ ሕዝብ የጋራ ንቅናቄ መሪ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተገልጿል፡፡

የግብፅ ፖፕ ቴዎድሮስ ዳግማዊ ለመስቀል በዓል አዲስ አበባ ይገባሉ

የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፖፕና ፓትርያርክ ቴዎድሮስ ዳግማዊ በመስቀል በዓል አከባበር ላይ ለመታደምና የአራት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ፣ መስከረም 15 ቀን 2008 ዓ.ም. አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡

የኮፕቲክ ፓትርያርክ ቴዎድሮስ አራት ቀናት በሚወስደው ቆይታቸው መስከረም 16 ቀን 2008 ዓ.ም. የሚከበረውን የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ከመታደማቸው በተጨማሪ፣ ወደ አክሱምና ላሊበላ አቅንተው ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ሥፍራዎችን እንደሚጎበኙም ታውቋል፡፡ 

ከዚህ በተጨማሪም በሚኖራቸው ቆይታ በአዲስ አበባ የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላትን፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ከታዋቂ ግለሰቦች ጋር እንደሚነጋገሩ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ከፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመና ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ፣ እስካሁን ግን የተረጋገጠ ነገር አለመኖሩን አክለው አብራርተዋል፡፡  

ፓትሪያርኩ የአዲስ አበባ ጉዟቸውን አስመልክቶ ከሳምንት በፊት ከግብፅ የውኃ ሀብት ሚኒስትር ሆሳም አል ሞጋሃዚ ጋር መነጋገራቸው የተዘገበ ሲሆን፣ በውይይታቸውም ወቅት ግብፅ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ ያላትን ጥያቄዎች አንስተው ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናትና ከአቡነ ማትያስ ጋር ውይይት እንዲያደርጉ ሚኒስትሩ መጠየቃቸውና የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ተዘግቧል፡፡ 

ፖፕ ቴዎድሮስ በበኩላቸው ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ሁለቱ ቤተ ክርስቲያናት ባላቸው ታሪካዊ ግንኙነት የተነሳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በዚህ ረገድ እየተባበሯቸው እንደሆነና አስተዋጽአቸውም ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል በማለት ስታር አፍሪካ የተሰኘ ድረ ገጽ ላይ የወጣ ዘገባ ያትታል፡፡

የኢትዮጵያ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ባለፈው ጥር ወር ግብፅን ለስድስት ቀናት በይፋ በጎበኙበትና በካይሮ ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግሥት ከፕሬዚዳንት አልሲሲ ጋር በተወያዩበት ወቅት፣ ፕሬዚዳንቱ የዓባይ ወንዝ ለኢትዮጵያውያን የልማት ምንጭ ቢሆንም ለግብፅ ግን ልማት ብቻ ሳይሆን የደም ሥር መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል፡፡ 

አቡነ ማትያስም በበኩላቸው በጠንካራ ትስስር ላይ የተመሠረተው የሁለቱ አገሮች ግንኙነት፣ ከዓባይ የሚመነጭ ውኃ የማያቋርጥ የጋራ ሀብት በመሆኑ በፍትሐዊነትና በእኩልነት ተጠቃሚ የሚኮንበት ይሆናል ማለታቸውም አይዘነጋም፡፡ 

ፖፕ ቴዎድሮስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. በ1952 ማንሱራ በተሰኘ የግብፅ ከተማ የተወለዱ ሲሆን፣ በ1975 ከኤሌክሳንዳርያ ዩኒቨርሲቲ በፋርማሲ የመጀመሪያ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡ ለጥቂት ዓመታት በመንግሥት ቁጥጥር ሥር የሚገኝ መድኃኒት ፋብሪካን ከአስተዳደሩ በኋላ፣ ቅዱስ ፒስሆግ የተባለ ገዳም በመግባት የሥነ መለኮት ትምህርት በማጥናት እ.ኤ.አ. በ1989 ተመርቀዋል፡፡ 

የአቡነ ሺኖዳ ሕልፈተ ሕይወትን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት 118ኛው የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በመሆን ከሦስት ዓመት ወዲህ በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡   

 

 

    በአለማየሁ አንበሴ የፍቅር አዲስ – “ምስክር” ታዋቂዋ ድምፃዊት ፍቅር አዲስ ነቃጥበብ፤እንደ ብዙዎቹ ድምጻውያን ሁሉ ለብዙ ዓመታት ድምጽዋን ሳንሰማ ቆይተናል፡፡ 2007 ዓ.ም ሊሰናበት ጥቂት ቀናት ሲቀሩትና አዲሱ ዓመት ለመጥባት እየተሽኮረመመ ሲጠባበቅ እሷ በመሃል 8ኛ የዘፈን አልበሟን ይዛ ከተፍ አለች፡፡  …

ፍቅር አዲስ ነቃጥበብ ስምንተኛ አልበሟን አውጥታለች Read more »

ድርጅቱ ችግሩን ቀርፌያለሁ ይላል

የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የክፍያ ሥርዓት ችግር እንደገጠመው ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ድርጅት በበኩሉ ችግር ተፈጥሮ እንደነበር አምኖ በአሁኑ ወቅት መቀረፉን ገልጿል፡፡ 

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ድርጅቱ ማዕከላዊ የክፍያ ሥርዓት (ቢሊንግ ሲስተም) ከሁለት ወራት በፊት በገጠመው ችግር ሳቢያ፣ የደንበኞችን ወርኃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያ ለሁሉ ለተባለው የተቀናጀ የአገልግሎት መክፈያ ማዕከል መላክ እንዳልተቻለ ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ 

ደንበኞች ወደ ክፍያ ለሁሉ በሚሄዱበት ጊዜም ትክክለኛ መረጃ እንደማይነገራቸውና በሌላ ጊዜ እንዲመጡ ብቻ እንደሚገልጹላቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ 

ጉዳዩን በተመለከተ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የክፍያ ለሁሉ የሥራ ኃላፊዎች የተፈጠረው ችግር እነሱን እንደማይመለከት ይገልጻሉ፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሚሰጠን የደንበኞች ወርኃዊ ፍጆታ መረጃ መሠረት ደንበኞችን ማስከፈል ነው ሥራችን፡፡ መረጃ ካልደረሰን ማስከፈል አንችልም፤›› ብለዋል፡፡ 

በመሆኑም ጉዳዩ የበለጠ የሚመለከተው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በዚሁ መሠረት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ድርጅት የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ገብረ እግዚአብሔር ታፈረ ተጠይቀው ችግሩ ተፈጥሮ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ 

የማዕከላዊ የክፍያ ሥርዓት ሰርቨር የመረጃ ካርድ በመቃጠሉ ምክንያት ችግሩ እንደተፈጠረ የተናገሩት የውጭ ግንኙነት ኃላፊው፣ ካርዱ በአገር ውስጥ ስለማይገኝና ከውጭ ተገዝቶ እስኪገባ ድረስ የሐምሌ ወር የኤሌክትሪክ ፍጆታን ደንበኞች ማለትም ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚዎች ከሆኑ ድርጅቶች በስተቀር መክፈል አለመቻላቸውን አስረድተዋል፡፡ 

በአሁኑ ወቅት ግን ችግሩ የተቀረፈ በመሆኑ የሐምሌ ወር የክፍያ ቢል መውጣቱንና ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ ደንበኞች የነሐሴ ወር ፍጆታቸውን መክፈል እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡ 

የቀድሞው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽንን ለሁለት በመክፈል በ64.7 ቢሊዮን ብር የተፈቀደ ካፒታልና በ16.2 ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል የተቋቋመው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማኔጅመንት ፓወር ግሪድ ኮርፖሬሽን ለተባለ የህንድ ኩባንያ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ 

ኩባንያው ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎትን በመስጠት ደንበኞችን ማርካት ዋነኛ ኃላፊነቱ ሲሆን፣ መንግሥት ለሁለት ዓመት 16.7 ሚሊዮን ዶላር በመክፈል የሰጠው የማኔጅመንት ኮንትራት ነሐሴ 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ተጠናቋል፡፡ 

 

በያሬድ ቁምቢና ውብዓለም ተስፋዬ የአዲስ አመት ዋዜማ ጳጉሜ 5 ቱሉ ዲምቱ አቃቂ ደብረ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመገኘት ‹የመዳን ቀን ዛሬ ነው› እና‹ የጅራፍ ንቅሳት› የተሰኙ ሁለት የራሷን ግጥሞች አቅርባለች፡፡ ገና በስራዋ ስትታይ ድንቅ የትወና ብቃትና ፈጠራዋ የብዙዎችን ቀልብ መሳብ የቻለች ብርቅዬ ድንቅ አርቲስት ነበረች …ሰብለ ተፈራ፡፡ ፍጹም ባልተጠበቀ እና ድንገተኛ […]

አርቲስት እንድሪስ አህመድ ከ45 አመታት በፊት ነበር በብሄራዊ ቴዓትር ስራ የጀመሩት። ወሎ ክፍለ ሃገር ቢወለዱም ዳንስ የተማሩት በቅጽል ስሙ ውቤ በርሃ ተብሎ በሚታወቀው ደጃች ውቤ ሰፈር ነበር። አርቲስ እንድሪስ አህመድ ቡጊና ትዊስት ከደነሱበት ብሄራዊ ቴዓትር በጡረታ ቢሰናበቱም አሁን በፊልም ትወና ላይ ተሰማርተዋል።

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ዘረኝነትና ጥላቻ በመንግሥት ደረጃ በሚሰበክበት አገር፣ ድንቁርና እጅግ በተጫናቸው የወያኔ ቱባ ባለሥልጣናት ሕዝብ በሚዘለፍበት፣ ታሪክ ተጣሞ የአንድ ቋንቋ ተናጋሪን የሕብረተሰብ ክፍል በሌላው ላይ ለማነሳሳት ሌት ተቀን የሚደክሙና ጉርጓድ የሚምሱ ቡድኖችና ግለሰቦች ባሉበት አገር፣ ፍርሃትና ጥርጣሬ በነገሱበትና አፈና በበረታበት እንደ ኢትዮጵያ ባለ አገር እንደ ቴውድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ‹ ያሉ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በማሕበረሰቡ ውስጥ ያላቸው ሚና በዘፈን […]

አራት በትጥቅ ትግል የሚያምኑ ድርጅቶች፣ የአፋር ድርጅቶች ንቅናቄ፣ የአማራ ሕዝብ ንቅናቄ፣ የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደሚት) እና የግንቦት ሰባት አርበኞች ንቅናቄ ፣ በዚህ ሳምንት ዉስጥ አገር አድን ንቅናቄ በሚል ስያሜ መቀናጀታቸው በስፋት መዘገቡ ይታወሳል። ዶር ብርሃኑ ነጋ የቅንጁት ሊቀመንበር፣ አቶ ሞላ አስግዶም ደግሞ ም/ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል። የአራቱ ድርጅቶች መቀናጀት ይፋ በሆነ በጥቂት ቀናት ዉስጥ ጳጙሜን […]

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላንን የጠለፈው ረዳት ፓይለት መኪና ለጨረታ ቀረበች

በጥር 2006 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ወደ ሮም ጣሊያን ሲበር የነበረውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 767 አውሮፕላን ጠልፎ ጄኔቫ ስዊዘርላንድ ያሳረፈው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራ ንብረት የሆነች የቤት መኪና በሐራጅ ለጨረታ ቀረበች፡፡ 

የሰሌዳ ቁጥር አአ 2-A32521 መኪና ጨረታ ያቀረበው ዘመን ባንክ ነው፡፡ ረዳት አብራሪው ለመኪና ግዢ ከዘመን ባንክ የተበደረው ብድር ስላልተከፈለው ባንኩ ተሽከርካሪዋን በጨረታ ለመሸጥ መገደዱን አስታውቋል፡፡ 

ባንኩ ተሽከርካሪዋን ለጨረታ ያቀረበው በሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 261,503.37 ነው፡፡ ጨረታው የሚካሄደው በመስከረም ወር 2008 ዓ.ም. ነው፡፡ ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን መኪናዋን የገዛው ከአውሮፕላን መጥለፉ ጥቂት ወራት ቀደም ብሎ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

ኃይለ መድኅን ስዊዘርላንድ ውስጥ የፖለቲካ ጥገኝነት ቢጠይቅም የአገሪቱ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎት ፍርድ ቤት አንድ ጊዜ የቀረበ ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ ጉዳዩ በምን ደረጃ ላይ እንዳለ አይታወቅም፡፡ ለስዊዘርላንድ ኢሚግሬሽን ባለሥልጣን በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ 

ኢትዮጵያ ውስጥ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በግለሰቡ ላይ ክስ መሥርቶ፣ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሌለበት 19 ዓመት ፅኑ እስራት እንደተፈረደበት ይታወሳል፡፡ 

 

የአገሪቱ የነዳጅ ግዢ ጥያቄ ተነሳበት

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዓመታዊ የአገሪቱን የነዳጅ ፍጆታ ለመሸፈን የሚያካሂደውን ዓለም አቀፍ ጨረታ በመተው፣ በድርድር ከኩዌት መንግሥት ለመግዛት የተከተለውን አቅጣጫ ነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች ተቃወሙ፡፡ ድርጅቱ ተቃውሞውን አልተቀበለም፡፡

የአንዳንድ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ተወካዮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የነዳጅ ግዢ ጨረታ ማውጣት በመተው የተለያዩ የነዳጅ ውጤቶችን ከኩዌት በድርድር በመግዛት ላይ ይገኛል፡፡ ዕርምጃውን የተቃወሙት የኩባንያ ተወካዮች ውሳኔው አገሪቱን ዋጋ እንደሚያስከፍላት ይናገራሉ፡፡ 

‹‹አንደኛ ከኩዌት የሚገዛው ነዳጅ ውድ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከኩዌት ለሚገዛው ነዳጅ በበርሜል 0.30 ዶላር ጭማሪ ይከፍላል፡፡ ወይም በአንድ የነዳጅ ጫኝ መርከብ ላይ የ60 ሚሊዮን ብር ጭማሪ አለው፤›› ይላሉ፡፡ 

የኩባንያው ተወካዮች በሁለተኛ ደረጃ የሚያነሱት የነዳጅ ጥራት ጥያቄ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በአሁኑ ወቅት በመግዛት ላይ ያለው ነዳጅ የሊድ (እርሳስ) እና ሰልፈር መጠን ከፍተኛ በመሆኑ በአካባቢ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳድራል ብለዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በበኩሉ የቀረቡትን ወቀሳዎች አስተባብሏል፡፡ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ኃይለ ማርያም ለሪፖርተር በሰጡት ምላሽ፣ ከኩዌት መንግሥት ነዳጅ በቀጥታ መግዛቱ የተለያዩ ጠቀሜታዎች አሉት ብለዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ ዓመታዊ የነዳጅ ፍላጎት ከአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ጋር ተቀራራቢ በሆነ ቁጥር፣ በዓመት አሥር በመቶ በማደግ በአሁኑ ወቅት ሦስት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ደርሷል፡፡ አገሪቱ ለነዳጅ ግዢ የምታወጣው የውጭ ምንዛሪ 2.8 ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡ ከወጪ ንግድ የምታገኘው ደግሞ በዓመት ሦስት ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡ 

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት አገሪቱ ላላት የአውሮፕላን ነዳጅ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ከኩዌት የሚገዛ ሲሆን፣ 50 በመቶ የሚሆነውን የናፍጣ ፍላጎት የምታሟላው ከኩዌት በድርድር በሚገዛ ናፍጣ ነው፡፡ ሰባ አምስት በመቶ የሚሆነው የቤንዚን ፍጆታ ከሱዳን መንግሥት ይሸመታል፡፡ ሃያ አምስት በመቶ የሚሆነው የቤንዚን ፍጆታና 50 በመቶ የናፍጣ ፍጆታ የገዛው በግልጽ ጨረታ ከነዳጅ ነጋዴዎች ነው፡፡ የኩዌቱን ነዳጅ የሚያቀርበው የኩዌት መንግሥት ንብረት የሆነው ኩዌት ፔትሮሊየም ኮርፖሬሽን ሲሆን፣ 20 በመቶ ቤንዚንና 50 በመቶ የሚሆነው ናፍጣ የሚመጣው ሳዑዲ ዓረቢያ ከሚገኘው ያንቡ የድፍድፍ ነዳጅ ማጣሪያ ነው፡፡ 

የኢትዮጵያ የዕለት የቤንዚን ፍጆታ አንድ ሚሊዮን ሊትር፣ ናፍጣ 5.8 ሚሊዮን ሊትር፣ የአውሮፕላን ነዳጅ 1.8 ሚሊዮን ሊትር ነው፡፡ ዓመታዊ የነጭ ጋዝ ፍላጎት ደግሞ 260,000 ሜትሪክ ቶን ነው፡፡ ኅብረተሰቡ የኤሌክትሪክ ምድጃዎች በስፋት መጠቀም በመጀመሩ የነጭ ጋዝ ፍላጎት እየቀነሰ መጥቷል፡፡ በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች በ13 የመጠባበቂያ ነዳጅ ዴፖዎች የሚገኙ ሲሆን፣ 360,000 ሜትር ኪዩብ የማጠራቀም አቅም አላቸው፡፡ 

ኢትዮጵያ ከኩዌት ነዳጅ መግዛት የጀመረችው ከኩዌት መንግሥት ጋር ረዥም ጊዜ የፈጀ ውይይት ከተደረገ በኋላ እንደሆነ አቶ ታደሰ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ሚኒስትሮቻችን ሁለት ሦስት ጊዜ ወደ ኩዌት የተመላለሱ ሲሆን፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ከኩዌት የነዳጅ ሚኒስትር ጋር ተገናኝተው የኢትዮጵያን ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ከስምምነት ላይ በመድረሳቸው ነው፤›› ብለዋል፡፡ 

በተደረሰው ስምምነት መሠረት 70 በመቶ የአውሮፕላን ነዳጅ ፍጆታ፣ 50 በመቶ የናፍጣ ፍጆታ ከኩዌት ፔትሮሊየም ኮርፖሬሽን መገዛት መጀመሩን አቶ ታደሰ አስታውሰዋል፡፡ ባለፈው ዓመት የአውሮፕላን ነዳጅ አቅርቦት ኢትዮጵያ ለኩዌት ባቀረበችው ጥያቄ መሠረት ወደ 100 በመቶ አድጓል፡፡ 

ባለፈው ሳምንት በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ በአቶ አህመድ ሺዴ የሚመራ የኢትዮጵያ መንግሥት ልዑክ ወደ ኩዌት ተጉዞ፣ ከኩዌት የነዳጅ ሚኒስቴር ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ በወቅቱም አቶ አህመድ የኩዌት ፔትሮሊየም ኮርፖሬሽን ለኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የሚያቀርበውን የናፍጣ መጠን እንዲጨምር ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ከተቻለ የኢትዮጵያን 100 በመቶ የናፍጣ ፍላጎት እንዲያሟሉ ካልሆነ ግን 70 በመቶ እንዲሸፍኑ ጥያቅ አቅርበዋል፡፡ 

የኩዌት ባለሥልጣናት በበኩላቸው ቀደም ብለው የገቡዋቸው በርካታ ውሎች ስላሉ፣ 100 በመቶ መሸፈን እንደማይችሉ ገልጸው 70 በመቶ የሚለውን ጥያቄ (በ20 በመቶ ማሳደግ) ግን ገምግመው ምላሽ እንደሚሰጡ ለኢትዮጵያ ልዑክ አስረድተዋል፡፡ 

‹‹ከኩዌት ነዳጅ የመግዛት ዕድልን በብዙ ልምምጥ ያገኘነው ዕድል ነው፤›› የሚሉት አቶ ታደሰ፣ ከኩዌት ነዳጅ መገዛቱ ለኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ያስረዳሉ፡፡ 

‹‹ከኩዌት በምንገዛበት ወቅት 90 ቀናት የመክፈያ ጊዜ ይሰጡናል፡፡ ሱዳን የምትሰጠን 30 ቀናት ነው፡፡ ነዳጅ ነጋዴዎች ከ30 እስከ 45 ቀናት ብቻ ነው የሚሰጡን፡፡ የኩዌት ነዳጅ አቅርቦት አስተማማኝ ነው፡፡ ባሉት ቀነ ገደብ ያቀርባሉ፡፡ የዋጋ ክለሳ እንደ ነጋዴዎቹ በየጊዜው አያደርጉም፡፡ የሚጠቀሙት የራሳቸውን መርከቦች በመሆኑ ርካሽ መርከብ ሲፈልጉ ጊዜ አያቃጥሉም፤›› የሚሉት አቶ ታደሰ፣ የዋጋ ልዩነትን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ዝርዝር ጠቀሜታዎችን መመልከት እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል፡፡ 

‹‹ለምሳሌ እኛ ለኩዌት በበርሜል የምንከፍለው ፕሪሚየም ክፍያ (ትራንስፖርትና አገልግሎት) 4.50 ዶላር ነው፡፡ ለነዳጅ ነጋዴዎች በበርሜል 4.10 ዶላር ነው፡፡ ከነጋዴዎች ስንገዛ ኢንሹራንስ የምንከፍለው ራሳችን ነን፡፡ ነጋዴዎቹን ኢንሹራንስ ጨምሩበት ብንላቸው ዋጋቸው ሰባት ዶላር ይገባል፡፡ የኩዌት ግን ኢንሹራንስን ጨምሮ 4.50 ዶላር ብቻ ነው፤›› ብለዋል አቶ ታደሰ፡፡ 

የነዳጅ ጥራትን አስመልክቶ ለቀረበው ተቃውሞ በሰጡት ምላሽ የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት በአሁኑ ወቅት የሚገዛው ቤንዚን ከእርሳስ ነፃ የሆነ ነው ብለዋል፡፡ ‹‹ሊድ ያለው ቤንዚን መግዛት አቁመናል፡፡ ዓለም ሊድ ያለው ቤንዚን መግዛት አቁሟል፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡ 

‹‹ኢትዮጵያ ከኩዌት የምትገዛው ናፍጣ ውስጥ ያለው የሰልፈር መጠን 0.2 በመቶ ሲሆን፣ ከነጋዴዎች የሚገዛው ናፍጣ 0.05 በመቶ ሰልፈር ይዘት አለው፡፡ የናፍጣ ዋጋ ባለው የሰልፈር መጠን ይወሰናል፡፡ 0.2 በመቶ ሰልፈር ያለው ናፍጣ በበርሜል 57.76 ዶላር፣ 0.05 በመቶ ሰልፈር ያለው 58.76 ዶላር፣ 0.005 በመቶ 60.16 ዶላር፣ 0.001 በመቶ 61.16 ዶላር ዋጋ አለው፤›› ብለዋል፡፡ 

‹‹0.001 በመቶ ሰልፈር ያለውን ናፍጣ ገዝቶ ማምጣት ይቻላል፤›› የሚሉት አቶ ታደሰ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት መኪኖች ዕድሜ ጠገብ በመሆናቸው የሰልፈር ይዘቱ ዝቅተኛ የሆነ ናፍጣ ገዝቶ ማምጣቱ ጠቀሜታ እንደሌለው ይናገራሉ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት መኪኖች በአብዛኛው አሮጌ በመሆናቸው ከፍተኛ የካርቦን ልቀት አላቸው፡፡ 

‹‹በአገራችን ያሉት ብዙዎቹ መኪኖች ሦስት መንግሥታት ያገለገሉ ናቸው፡፡ ከፍተኛ ዋጋ ያለውን ናፍጣ ገዝተን ብናመጣ መኪኖቹ ነዳጁን በአግባቡ መጠቀም የሚችሉ ባለመሆናቸው አላስፈላጊ ዋጋ መክፈል ብቻ ይሆናል፤›› ያሉት አቶ ታደሰ፣ ሌሎች አገሮች ከፍተኛ ዋጋ ያለውን ነዳጅ ሲያስገቡ የመኪና ዕድሜ ገድበው እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ‹‹ኬንያ ከስምንት ዓመት በላይ ዕድሜ ያለውን መኪና ማስገባት አይቻልም፡፡ በናይጄሪያ ከአምስት ዓመት በላይ ያለውን መኪና ማስገባት አይቻልም፡፡ ወደ እኛ አገር ተጨባጭ ሁኔታ ስንመጣ ይህን ማድረግ አይቻልም፡፡ አንድ ኤንትሬ የጭነት መኪና አሥር ቤተሰብ ያስተዳድራል፡፡ ከፍተኛ ዋጋ ያለውን ናፍጣ ከማስመጣታችን በፊት ዕድሜ ጠገብ ተሽከርካሪዎችን ማስወገድ አለብን፡፡ በርካታ ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ አሮጌ መኪኖችን በአሁኑ ወቅት ማስወገድ አይቻልም፡፡ ምናልባት ያን ማድረግ የሚቻለው ወደ መካከለኛ ገቢ አገርነት ስንሸጋገር ይሆናል፤›› ብለዋል፡፡ 

የነዳጅ ኩባንያ ተወካዮች የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት እ.ኤ.አ. ለ2016 የሚውል ነዳጅ ለመግዛት ነሐሴ 17 ቀን ጨረታ ማውጣት የነበረበት ቢሆንም፣ እስካሁን ጨረታውን አለማውጣቱን ይህም የጨረታ ግዢ ሙሉ በሙሉ ቀርቷል የሚል ሥጋት እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል፡፡ 

አቶ ታደሰ ድርጅታቸው ጨረታ ማውጣቱን እንዳልተወ፣ የጨረታ ሒደቱ እንዲዘገይ የተደረገው ከኩዌት የሚገዛው የነዳጅ መጠን እስከሚታወቅ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ 

የኩዌት መንግሥት የሚያቀርበው የነዳጅ መጠን ከታወቀ በኋላ ጨረታው እንደሚወጣ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ተጨማሪ የአውሮፕላን ነዳጅ እንዲያቀርቡ ጠይቀናል፡፡ የሚያቀርቡትን የናፍጣ መጠን የፍጆታችንን 70 በመቶ እንዲሆንም ጠይቀናል፡፡ ምላሻቸውን አይተን ጨረታውን እናወጣለን፤›› ብለዋል፡፡ 

ከሱዳን እስከ 80 በመቶ ቤንዚን የሚገኝ በመሆኑ የተቀረው 20 በመቶ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን፣ ኩዌት ከናፍጣ ፍጆታ 70 በመቶ ልታቀርብ ትችላለች፡፡ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት 800,000 ሜትሪክ ቶን ናፍጣና 60,000 ሜትሪክ ቶን ቤንዚን ለመግዛት ጨረታ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ 

 

የገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ አጋር የሆነው የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ሥራ አስፈጻሚ አባላት መካከል አለመግባባት መፈጠሩ ተሰማ፡፡ በዚህ ምክንያት የክልሉን ቋሚ መስተዳድር መመሥረት እንዳልተቻለ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ 

አለመግባባቱ የተፈጠረው አብዴፓንና የአፋር ክልልን ላለፉት 20 ዓመታት ሲመሩ በቆዩት የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ እስማኤል ዓሊ ሴሮ ቡድንና እሳቸውን ተክተው በተመረጡት የአብዴፓ ሊቀመንበር አቶ ጠሃ መሐመድ ቡድን መካከል መሆኑን፣ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የአብዴፓ ሊቀመንበር አቶ ጠሃ መሐመድ የክልሉ መንግሥት የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ፣ በሌሎች ክልላዊ መንግሥቶች የሥልጣን አወቃቀር መሠረት የፓርቲው ሊቀመንበር እንደመሆናቸው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርም ሊሆኑ ይገባል የሚል ክርክር፣ በአቶ ጠሃ ቡድን አማካይነት መነሳቱን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ይህ ጥያቄ ግን አብላጫ ድምፅ ባለው የአቶ እስማኤል ዓሊ ሴሮ ቡድን በኩል ተቀባይነት ማግኘት አለመቻሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በዚህ ምክንያት አቶ ጠሃ መሐመድና አቶ እስማኤል ዓሊ ሴሮ የሌሉበት የፓርቲው የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ከአንድ ወር በፊት ተካሂዶ፣ አቶ እስማኤል ለተጨማሪ ሦስት ወራት በጊዜያዊ ፕሬዚዳንትነት እንዲቆዩ፣ ካልሆነ ደግሞ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ጊዜያዊ አስተዳደር ይመሥርት በሚለው ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ በስተመጨረሻም ከክልሉ ምክር ቤት ውጪ ሥራ አስፈጻሚው ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት መሾሙን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በዚሁ መሠረት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የውኃ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ አወል አርባ፣ በጊዜያዊ ፕሬዚዳንትነት ለሦስት ወራት መመረጣቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይሁን እንጂ በወደፊቱ ጉዳይ ላይ መግባባት ባለመቻሉ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰሞኑን በአዲስ አበባ እየመከረ እንደነበር፣ በዚህ ስብሰባ ላይም የኢሕአዴግ ተወካዮች ለታዛቢነትና ለማስታረቅ መገኘታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ 

በትጥቅ ትግሉ ወቅት አቶ እስማኤል ዓሊ ሴሮ የሕወሓት አባል የነበሩ ሲሆን፣ በትጥቅ ትግሉ የተሳተፉ የአፋር ክልል ተወላጅ ናቸው፡፡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የአብዴፓ ሊቀመንበር በመሆን ለ20 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ 

በግንቦት ወር 2007 ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ ክልሉን በመወከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት ተመርጠዋል፡፡    

በአብዴፓ ውስጥ የተፈጠረውን አለመግባባትና እየተካሄደ ስለነበረው ድርድርና ምክክር ለአብዴፓ ጽሕፈት ቤት፣ ለክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ፣ ለኢሕአዴግ የውጭ ግንኙነት ጽሕፈት ቤትና ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ጥያቄ ቢቀርብም ምላሽ ማግኘት አልተቻለም፡፡  

 

‹‹ምርመራ ዘመናት የሚያስቆጥር የአርኪዮሎጂ ቁፋሮ አይደለም›› የተጠርጣሪው አቶ ወንድሙ ቢራቱ ጠበቃ

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ነሐሴ 3 ቀን 2007 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ውለው በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣን አቶ ወንድሙ ቢራቱ፣ የአውሮፕላን ትኬት በመግዛት በግብዣ መልክ ለባለሥልጣናት ጉቦ መስጠታቸው ተገለጸ፡፡

አቶ ወንደሙ የተጠረጠሩባቸውን የሙስና ወንጀሎች እየመረመረ የሚገኘው የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት እንዳስረዳው፣ ተጠርጣሪው በሥልጣን ዘመናቸው ወደ ውጭ አገር በመሄድ ምን ያህል ገንዘብ እንዳወጡና ለባለሥልጣናት የአውሮፕላን ትኬት በመቁረጥ በግብዣ መልክ ጉቦ የሰጡበትን ሰነድ ከሚመለከተው ተቋም መጠየቁን አስረድቷል፡፡

መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው፣ ተጠርጣሪው የተጭበረበረ ሰነድ ሕጋዊ በማስመሰል መሬት የሸጡበትና ከባንክ ገንዘብ የተቀበሉበት ሰነድ ተሰብስቧል፡፡ ጉቦ በቼክ የተቀበሉበት ሰነድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተሰብስቧል፡፡ ከሁለት ሰዎች ሦስት ሚሊዮን ብር ጉቦ መቀበላቸውን ከሚያረጋግጡ ሰዎች የምስክርነት ቃል መቀበሉንም ቡድኑ ገልጿል፡፡ ከጉምሩክ ከጠየቀው የማስረጃ ሰነድ ከፊሉን መሰብሰቡን፣ በኦሮሚያ ልዩ ዞኖች ለሚደረገው ምርመራ ደጋፊ ሰነድ በማቅረብ እየተከታተለ እንደሆነና አንድ ተጨማሪ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር አውሎ ቃሉን መቀበሉን መርማሪ ቡድኑ አስረድቷል፡፡

የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት የጠየቀ ሲሆን፣ ምክንያቱንም አስረድቷል፡፡ ተጠርጣሪው ብዙ ቤቶችና ቦታዎች እንዳሏቸው ጥቆማዎች በመምጣታቸው ከአራት ከተሞች ማኅደሮችን መሰብሰብ እንደሚቀረው፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ ያልተሰበሰቡ ማስረጃዎችን መሰብሰብ፣ ተጨማሪ ሰነዶችን ለፎረንሲክ ምርመራ በመላከ ትክክለኛነቱን አረጋግጦ መሰብሰብ፣ ሌሎች ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን አድኖ መያዝና የምስክሮችን ቃል መቀበል ስለሚቀረው መሆኑን አስረድቷል፡፡

አቶ ወንድሙ ቀደም ባሉት ቀጠሮዎች እሳቸው የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባል ከመሆናቸውም በተጨማሪ፣ በእሳቸው ላይ የሚቀርብ ማንኛውንም ተጠያቂነት የመጠየቅ ሥልጣን ያለው የክልሉ መንግሥት መሆኑን በመናገር ሲከራከሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ተጠርጣሪው አሁንም በጠበቃቸው አማካይነት እንደገለጹት፣ የተጠረጠሩበትን የሙስና ወንጀል የማየት ሥልጣን ያለው የኦሮሚያ መንግሥት ብቻ ነው፡፡ የመመርመርና የመክሰስ ሥልጣን ያለው የኦሮሚያ የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ብቻ ነው፡፡ ይሄም በፌዴራል የፀረ ሙስና አዋጅ 433/97 አንቀጽ 7(4) እና በአዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 7(2/4) ተደንግጓል ብለዋል፡፡ ፌዴራል የክልሉን ሥልጣን ማክበር እንዳለበት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 50(8) መደንገጉንም አስረድተዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ የዳኝነት ሥልጣን ስለሌለውና ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መስጠት ስለማይችል፣ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 50(8) እና በወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ 110 መሠረት ክሱን ዘግቶ ተጠርጣሪው እንዲያሰናብታቸው ጠይቀዋል፡፡

የፖሊስ ምርመራ ተጠናቆ ቀዳሚ ምርመራ ውስጥ መግባቱን የጠቆሙት የአቶ ወንድሙ ጠበቃ፣ የምርመራ ሥራ ዘመናት የሚያስቆጥር የአርኪዬሎጂ ቁፋሮ አለመሆኑንና በፍጥነት መፈጸም ያለበት የሕግ ሥራ በመሆኑን በመጠቆም ተጨማሪ ቀጠሮ መሰጠት እንደሌለበት አመልክተዋል፡፡

የወንጀሉ መፈጸም አጠራጣሪ መሆኑንና ተጠርጣሪውን ዋስትና ሊያስከለክላቸው እንደማይችል የገለጹት ጠበቃው፣ ወንጀሎቹ መፈጸማቸውን የሚያስረዳ ምንም ዓይነት ማስረጃ ካለመገኘቱም በተጨማሪ ተጠርጣሪው ወንጀሉን መፈጸማቸውም አጠራጣሪ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አጠራጣሪ ወንጀል የቅጣት ጣሪያው ምንም ያህል ቢሆንም የዋስትና መብት እንደማያስከለክል ጠቁመው፣ መርማሪ ቡድኑ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ታልፎና መዝገቡ ተዘግቶ ከእስር እንዲፈቱ ወይም የመንቀሳቀስ መብታቸው ተገድቦ በዋስ እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡ 

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ በሰጠው ትዕዛዝ፣ የተጠርጣሪው ጠበቃ ቀደም ባለው ቀጠሮ መርማሪ ቡድኑ በጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ምንም እንዳልሠራ መግለጻቸውን በሚመለከት መዝገቡን ተመልክቶ፣ ጠበቃው እንዳሉት ሳይሆን ቡድኑ ምርመራ ማድረጉን ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡ የተጠርጣሪ ጠበቃ የደንበኛቸውን ጉዳይ የፌዴራል መንግሥት ወይም ፍርድ ቤቶች ማየት እንደማይችሉና ሥልጣኑ የክልሉ መሆኑን በመጥቀስ መዝገቡ ተዘግቶ አቶ ወንድሙ በነፃ እንዲሰናበቱ ያቀረቡትን አቤቱታ እንዳልተቀበለው አስረድቷል፡፡ ያልተቀበለበት ምክንያት ቀደም ባሉ ቀጠሮዎች ተመሳሳይ ጥያቄ ቀርቦ ችሎቱ ብይን የሰጠበት መሆኑን በመግለጽ፣ ለመርማሪ ቡድኑ ተጨማሪ ዘጠኝ ቀናትን በመፍቀድ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

አቶ ወንድሙ ሥልጣናቸውን በመጠቀምና ከፌዴራል ባለሥልጣናት ጋር በመመሳጠር አገራዊ ጠቀሜታ ላላቸው የተለየ ክህሎት ለሚጠይቁ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተፈቀደውን ከቀረጥ ነፃ መኪና ማስገባት መብት በመጠቀማቸው፣ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ሀብት በማከማቸት፣ በሕገወጥ መንገድ ያካበቱትን ሀብት ሕጋዊ በማስመሰል፣ በዘመዶቻቸው ስም ሀብት በማስቀመጥ፣ ለመንግሥት መግባት የነበረበትን ታክስና ቀረጥ ለግል መጠቀሚያ በማድረግ፣ ጉቦ በመቀበልና በማቀባበል ወንጀሎች መጠርጠራቸውን የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን ቀደም ባሉት ችሎቶች ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

 

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በመቀሌ ከተማ ባደረገው ስብሰባ ላይ በጥንቃቄ ተመርጠው የተጠሩ ታማኝ ካድሬዎችና አባላት የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰሙ፡፡ የትግራይ ፌስቡክ ተጠቃሚዎች አብዮታዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው መሆኑ በአባይ ወልዱ የሚመራው የህወሓት አንጃ አሳወቀ። አንጃው ይህንን አብዮታዊ እርምጃ እንደሚወስድ ያሳወቀው “12ተኛ ጉባኤ እንዴት አለፈ …?” በሚል አጀንዳ በየመንግሥት መስርያ ቤቶች፣ ከመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች፣ የክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች […]

የትግራይ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ሃላፊና የክልሉ ዳኞች ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማሪያም በሙስና ስለተገመገሙ ከሃላፊነታቸው መውረድ አለባቸው ሲሉ የህወሓት ጉባኤተኞች የወሰኑትን ውሳኔ እስከ አሁን ድረስ እንዳልተተገበረ ተገለፀ። እንደ ምንጮቻችን መረጃ መሰረት የአባይ ወልዱ ሚስት የሆኑት ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማሪያም ላለፉት አመታት የትግራይ ክልል የሲቪል ሰርቪስ ሃላፊ ሆነው በሰሩበት ጊዜ በመስሪያ ቤቱ አዳዲስ ለውጦች ባለማምጣታቸው የተነሳና ጊዜው […]

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድምጻችን ይሰማ የትግል ስትራቴጂውን በአዲስ መንገድ እንደሚቀይስ ማስታወቁን ተከትሎ፣ የመጀመሪያውን ትግል አንድ ቁጥር በመያዝ ትግሉን ጀምሯል። ሙስሊሙ ማህበረሰብ በቅርቡ ፍርድ ቤት በሙስሊም መሪዎች ላይ የሰጠውን ፍርድ ” የተቀበረች ፍትህ ቀባሪዋን ትቀብራለች፣ አምባገነናዊ ፍርድ አንቀበልም” የሚል መፈክር በማሰማት ተቃውሞ አሰምቷል። አሃዱን አሃድ፣ ትግላችን ይቀጥላል፣ ድምጻችን ይሰማ፣ ኮሚቴው ይፈታ፣ …

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አሳይቷል በዘንድሮ የአዲስ አመት ገበያ፣ የዶሮ ዋጋ ከበፊቱ በእጥፍ የጨመረ ሲሆን በአቃቂና በሳሪስ አካባቢ ዶሮ ከ200 ብር እስከ 400 ብር የሚሸጥ ሲሆን፤ በግ ከ1100 እስከ 3500 ብር፣ በሬ ከ4500 እስከ 25ሺ ብር፣ ፍየል ከ750 እስከ 4ሺ ብር እየተሸጡ ነው፡፡ በሾላ ገበያ በግ ከ900 ብር እስከ 4500 ብር፣ …

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል ባጠናው ጥናት ከአዋሳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ የሚወጣው ኬሚካል ሃይቁንና ወንዙን በመበከሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ህይወት አደጋ ላይ ወድቋል። ከፋብሪካው የሚወጣው ውሃ በቀጥታ ወደ ጥቁር ውሃ ወንዝ የሚፈስ ሲሆን፣ ወንዙም ወደ ሃይቁ የሚፈስ በመሆኑ ተጨማሪ ስጋት ፈጥሯል። የኬሚካሉ ወደ ውሃው መግባት የአሳዎችን ስደት እንደሚያስከትል የሚገልጸው …

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመጪው መስከረም ወር 2008 መቶ በመቶ በኢህአዴግና አጋሮቹ በተያዘው ፓርላማ ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ሁለተኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ይፋ ለማድረግ በሚል በእነሠራዊት ፍቅሬ እና ሽዋፈራው ደሳለኝ አጋፋሪነት ከምሽቱ 3 ሰዓት ጅምሮ በሚሌኒየም አዳራሽ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሚገኙበት ታላቅ የፌሽታ በዓል ተዘጋጅቷል፡፡ እነሠራዊት ፍቅሬ …

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከባህርዳር እስረኞችን ጭኖ አዲስ አበባ ወደሚገኘው ማእከላዊ እስር ቤት በመጓዝ ላይ ያለ ሚኒባስ ታክሲ ፣ ማለዳ 1 ሰአት ተኩል አካባቢ ሾላ ሰሜን ሆቴል ወይም መቀጠያ ሃበሻ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ሲደርስ ፣ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በመቆሙ በውስጡ ከነበሩት 13 እስረኞች መካከል 6ቱ ከመኪናው በመውረድ አምልጠዋል። የተቀሩት ከሚኒባስ ባለመውረዳቸው …

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በተጠለሉባቸው የስደተኞች መጠለያዎች ውስጥ የተቀሰቀሰው የኮሌራ ወረሽኝ በአጎራባች የደቡብ ሱዳንና የኢትዮጵያ ድንበሮች አካባቢ ስጋት እየፈጠረ ነው። ይህንን ተላላፊ ገዳይ በሽታ ለመግታት የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅትና ዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን በጥምረት ክትባትና የንጹህ ውሃ አገልግሎት አቅርቦት መስጠት ጀምረዋል።በአስር የስደተኞች መጠለያ …

ከትናንት ሐሙስ አንስቶ ለ 10 ቀናት የሚዘልቅ የፎቶ አውደ ርዕይ ዩናይትድ ስቴትስ- ኒው ዮርክ ከተማ ተከፍቷል። በዚህም አውደ ርዕይ ላይ የ11 ወጣት ኢትዮጵያውያን የፎቶ ስራዎች ለዕይታ ቀርበዋል።

ማስረጃዎች ለሕጋዊ ጥያቄ በሚያመቹበት ኹኔታ በአፋጣኝ ተዘጋጅተው እንዲቀርቡ ታዟል በጥምር እና በተናጠል ተጠያቂ የሚኾኑ የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች በስም ዝርዝር ይለያሉ የቤት እና የመኪና ሽልማት የተሰጣቸው አለቆች እና የስጦታው ምክንያት ተብራርቶ ይቀርባል   *          *          * የመሬት፣ የሕንጻ እና የልማት ይዞታዎች የኪራይ ውላቸው ለአንድ ዓመት ብቻ ይኾናል ከሦስተኛ ወገኖች ጋር ለመዋዋል እንዲቻል የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ በቋሚ …

የዞን 9 ጦማርያን ከታሰሩ አንድ አመት ከአምስት ወራት የተቆጠረ ሲሆን ወዳጅ ጋዜጠኞችን ጨምሮ ከጠቅላላው ዘጠኝ እስረኞች መካከል አራት ጦማርያን አሁንም በእስር ላይ በመሆናቸው ሁለተኛ እንቁጣጣሻቸውን በቅሊንጦ እስር ቤት ያከብራሉ ፡፡ ባለፉት አንድ አመት ከአምስት ወራት 36 ግዜ ፍርድ ቤት የተመላለሱ ሲሆን እስራቸው እና የፍርድ ሂደቱ በ2007 ዓ/ም ምን ይመስል እንደነበረ በመጠኑ እናያለን፡፡


የዞን 9 የእስር መስመር


መስከረም 2007  -የዓመቱ መጀመሪያ ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ በጻፈው  የቀድሞው አብዮተኛ ኑዛዜ  ተጀመረ፡፡ ጽሁፉ በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ የዞን9 ጦማር ላይ ታትሟል፡፡


ጥቅምት 2007 የህግ የበላይነት እና ጸረ ሽብርህጉ ሲገመገም የሚለው ‹‹የጸረ ሽብር ሕጉና›› የአሁኗ ኢትዮጲያ ያላቸውን ግንኙነት አንዲሁም ምን ተፅእኖ እንዳለው የሚያሳየው ልዬ ሪፓርተዥ ተዘጋጀ፡፡
ጥቅምት 11 2007 ዓ/ም በእስር ላይ ይገኙ የነበሩትን ጦማሪት ማህሌት ፋንታሁንን እና ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬን የእስር ቤት አያያዝ አስመልክቶ የቀረበውን አቤቱታ ለማየት ችሎቱ ተሰየመ፡፡ በእለቱም እስር ቤቱ የተለየ አያያዝ መኖሩን ክዶ የተከራከረ ሲሆን ፍርድ ቤቱም አንደተለመደው እንዳይደገም በሚል የማረሚያ ቃል ችሎቱን አጠናቀቀው፡፡

ከጥቅምት 12 ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ለዞን9 ጦማርያን 6 ወር የእስር ቆይታን አስመልክቶ ለቤተሰቦቻቸውን ድካም የማገዝ የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ በዞን9 ጦማርያን ወዳጆች አማካኝነት በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ፡፡

ጥቅምት 25 – የዞን9 ጦማርያን ለአስረኛ ፍርድ ቤት ቀረቡ ፡፡


ህዳር 2007  –

ህዳር 1 ቀን የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይማርያም ደሳለኝ በተለያዬ ሚዲያዎች ላይ ሲቀርቡ የሚሰጡትን አስተያየት ሕገ-መንግስታዊነትን የጣሰ መሆኑን አስመልክተው ደብዳቤ ጻፉ፡፡ ደብዳቤው የተከሳሾችን በህግ ፊት ንጹህ ሆኖ የመቆጠር መብት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየጣሱ እንደሆነ እና እንዲታረም የሚጠይቅ ነበር፡፡

ሕዳር 3  ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞቹ ለ11ኛ ፍርድ ቤት ቀረቡ ፡፡ በዚህ የፍርድ ቤት ውሎም አቃቤ ህግ በአምስት ጉዳዬች ላይ ክሱን አንዲያሻሽል ትእዛዝ ተሰጠው ፡፡ ( ሊፈጽሙ ነው የተባለውን የሽብር ወንጀል በግልጽ ማስቀመጥ፣ ቡድኑ እየተባለ የተቀመጠው ቡድን ማን እነደሆነ በግልጽ ማስቀመጥ፣ የሥራ ክፍፍልን አስመልክቶ የተጠቀሰውን በግልጽ መስቀመጥ ፣ ተላከ የተባለውን 48000 ብር አስልክቶ በግልጽ ከማን አንደተላከ ማስቀመጥ ፣ ስልጠና የተባሉት ምን እንደሆኑ በግልጽ ማስቀመጥ እና የሽብር ስልጠና ሰጪ ድርጅቱን በግልጽ ማስቀመጥ ይገኙበታል)

ሕዳር 17 – በጦማርያኑ የዋስትና መብትን አስመልክቶ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደርጎ በእስር መቆየታቸው እርግጥ ሆነ ፡፡

ሕዳር 24 – ተሻሻለ የተባለው ክስ በድጋሚ ለፍርድ ቤት ቀረበ ፡፡ ጠበቆች የተሻሻለው ክስ ላይ አስተያየታቸውን አንዲሰጡ ተነገራቸው፡፡ ተሻሻለ የተባለው ክስ ቡድኑ ግንቦት 7 ነው ከማለት ውጪ ምንም አይነት መሻሻል ሳይደረግበት ነበር ለፍርድ ቤት የቀረበው ፡፡


ታህሳስ 2007

ታህሳስ 7 – ጦማሪ ዘላለም ክብረት በእንግሊዘኛ የጻፈው የናፍቆት ደብዳቤ  ታተመ

ታህሳስ 9 – ጦማሪ አቤል ዋበላ ‹‹ሕልም እንደሆነ አይታሰርም›› የሚለው ተወዳጅ ጽሁፉ በዞን9 ጦማር ላይ ታተመ ፡፡

ታህሳስ 27 ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞቹ በድጋሚ ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ ፍርድ ቤቱ ክሱ አንዲሻሻል ታዞ ነገር ግን በተለያዩ አራት ጉዳዮች ላይ አሁንም ባለመሻሻሉ በድጋሚ አንዲሻሻል ሁለተኛ ትእዛዛ ሰጠ፡፡


ጥር 2007

ጥር 6 የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኛ ወዳጆች በድጋሚ ፍርድ ቤት ቀረቡ ፡፡ በእለቱ አቃቤ ህግ በድጋሚ አሻሻልኩት ያለውን ክስ ይዞ ቀረበ፡፡

ጥር 20 – ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ ያቀረበውን ያልተሻሻለ ክስ እንደተሻሻለ መቁጠሩን በመግለጽ ተከሳሾች የህብረተሰቡን ደህንነት ወይም ጤና በማወክ በጸረ ሽብር ህጉ አንቀጽ 4 መከሰሳቸውን አጸና፡፡ የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ የተጠቀሰበትን አንቀጽ በቀደመው ብይን ውድቅ በማድረጉም የተከሳሾች ጉዳይ ‹‹በጸረ ሽብር›› ሕግ ብቻ እንዲዳኝ ተወሰነ፡፡ የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ተቀጠረ፡፡

ጥር 26 – የዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች በድጋሚ ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ ፍርድ ቤቱ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ከመስጠታቸው በፊት መሃል ዳኛው አንዲነሱላቸው አቤቱታ አቀረቡ፡፡ ችሎቱም አቤቱታውን ሰምቶ ለመወሰን ሌላ ቀጠሮ ተሰጠ፡፡

ጥር 27 – በዚህም ቀጠሮ የተገኙት ተከሳሾች ሁለቱ ዳኞች ተሟልተው የዳኛው ይቀየርልን አቤቱታን መስማት ስላልቻሉ  በማግስቱ ለጥር 28 ተቀጠሩ ፡፡

ጥር 28 – በዚሁ እለት መሃል ዳኛው ባልተገኙበት ሁለቱ ዳኞች ጉዳዩን አይተው መሃል ዳኛው በፍርድ ሂደቱ ወቅት ጣልቃ አልገቡም አንዲሁም አፋጣኝ ፍትህን አላጓደሉም በማለት ውሳኔ መስጠታቸው ተገለጸ፡፡ ይህንን ተከትሎ የመሃል ዳኛው ምንም አንኳን በጉዳዩ ላይ ዳኞች ችሎቱ ላይ አንድቀጥል ቢፈልጉም ለእኔ ግን አንዲህ እየተባል ክሱ ላይ መቆየት አግባብ ስለማይሆን ራሴን ከችሎቱ አግልያለሁ በማለት አስተያየታቸው ሰጡ ፡፡ ( ነገር ግን ችሎቱን አሁንም የሚያስችሉት እኚሁ ዳኛ ናቸው) ፡፡

በተመሳሳይ እለት ጦማሪ አቤል ዋበላ ከማረሚያ ቤት የደረሰበትን የመብት ጥሰት ( በውሻ ሰንሰለት ታስሮ መቀመጥ እና በማዕከላዊ ሳለ በደረሰበት ድብደባ እንዲጠቀም የተገደደውን የጆሮ ማዳመጫ መሳሪያውን መቀማት) አስመልክቶ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቀረበ ፡፡ ይህን አቤቱታውን በጽሁፍ አንዲያቀርብ ከፍርድ ቤት ቢነገረውም በእለቱ የነበረው ሂደት ብዙዎን በፍርድ ቤት ውስጥ እንባ አራጨ፡፡ በእለቱ የነበሩት የእስር ቤት ተጠሪ የማውቀው ጉዳይ የለም በማለት የመብት ጥሰቱን ክደዋል፡፡


የካቲት 2007

የካቲት 11 – የዳኛው መቀየር አቤቱታን ፍርድ ቤቱ ውድቅ ካደረገው በኋላ የዞን 9 ጦማርያ እና ጋዜጠኞች የካቲት 11 ቀን ለ20ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት በመገኘት የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ በእለቱን ጦማሪ በፍቃዱ ‹‹የሽብር ተግባር አልፈጸምኩም ሽብር ተፈጽሞብኛል›› ሲል፣ ጦማሪ ናትናኤል በበኩሉ ‹‹እዚህ አገር ፍትህ ቢኖር ኖሮ እኔ የቆምኩበት ቦታ ላይ መቆም የሚገባቸው ከሳሾቼ ናቸው፤ ምንም አይነት ወንጀል አልፈጸምኩም›› የሚል ቃሉን ሰጥታል፡፡ ጦማሪ አጥናፍ ‹‹ምንም አይነት ወንጀል አልፈጸምኩም›› ያለ ሲሆን ጦማሪ አቤል በበኩሉ ‹‹የኅብረተሰቡን ደህንነት ለመጉዳት አላቀድኩም ለሽብር ተግባርም አላሴርኩም ብሏል፡፡››  የሴት እስረኞችን አያያዝ አስመልክቶ አጭር ቀጠሮ የሰጠን ሲሆን አጠቃላይ የማስረጃ ማሰማት ሂደቱን ግን ከአንድ ወር ከ10 ቀን በኋላ በተከታታይ ለሶስት ቀን ቀጥሮታል፡፡

የካቲት 18 – የሴት እስረኞችን አያያዝ አስመልክቶ ችሎቱ የተሰየመ  ጉዳዬን ለማየት በድጋሚ ቀጠሮ ሰጥታል፡፡  


መጋቢት 2007

መጋቢት 21 – የሰው ምስክር ናቸው ተብለው የቀረቡ ሰዎችን ምስክርነት መስማት ተጀመረ ፡፡ ሁሉም ምስክሮች እቃዎች ሲፈተሹ ያየን ነን በማለት የተያዙ እቃዎቸን ከማየታቸው በስተቀር ያቀረቡት የተለየ የወንጀል ምስክርነት አልነበረም ፡፡ ምስክሮቹ ተከሳሾን መለየት ሲያቅታቸው የተስተዋሉ ሲሆን በመጀመሪያው ቀን 6 ሰዎች ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ የተከሳሽ ጠበቆች ባልተካደ ነገር ላይ የፍርድ ቤቱም የተከሳሾችም ጊዜ መባከን አይገባውም እቃውም የእኛ አይደለም የሚል ቃል አልሰጠንም ስለዚህ የደረጃ ምስክሮች መስማት ይቁም ቢሉም ፍርድ ቤቱ ታዛቢዎቹን መስማት መቀጠል አለበት በማለቱ የተገኙ እቃዎችን ሲዘረዝሩ ከርመዋል ( መጽኃፍት ፣ መጽሄቶች፣ አርቲክሎች ላፕ ቶፕ ስልኮች እና ሲምካርዶች የመሳሰሉት ከፍተሻ ዝርዝሩ ውስጥ የተገኙ ናቸው)

መጋቢት 22 – ተጨማሪ 8 ምስክሮች በተመሳሳይ ሁኔታ ቃላቸውን ሲሰጡ ውለዋል፡፡ ከነዚህ በላይ ምስክሮችን ማቅረብ ያልቻለው አቃቤ ህግ ተጨማሪ ጊዜ በመጠየቁ ለመጋቢት 30 ቀጠሮ ተሰጥታል፡፡

መጋቢት 30 – አቃቤ ህግ ምስክሮቼ ጠፍተውብኛል፡፡ የሲዲ ማስረጃዎችንም የያዘው ሰው በአገር ውስጥ ስለማይገኝ ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ የሚል ጥያቄ አቅርቦ በመፈቀዱ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶ ችሎቱ ተበትናል ፡፡

መጋቢት 25 – ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ ይድረስ ለኢቢሲ ጋዜጠኞች የጻፈው ጽሁፍ ታትሞ ወጥቷል፡፡


ሚያዝያ 2007

ሚያዝያ 16-19  የ6ቱ ጦማርያንን እና የ3ቱን ጋዜጠኞች እስር አንደኛ አመት አስመልክቶ ለነጻነታቸው ዋጋ የሚከፍሉትን እናወድስ የሚል የሁለት ቀናት ማስታወሻ ተዘጋጀ፡፡ በማስታወሻው ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞቹ የደረሰባቸውን የመብት ጥሰት ዝርዝር እና የተያዙበትን እለት የነበረውን ድባብ ያሳየ ሲሆን ከ3 ሺህ በላይ ሰዎች በሁነቱ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል ፡፡  በዚሁ የማስታወሻ ዝግጅት ላይ የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች የላኩት የአንደኛ አመት ማስታወሻም ተስተናግዷል፡፡


ግንቦት 2007

ግንቦት 2

በዞን 9 ወዳጆች አማካኝነት የተዘጋጀው ሁለተኛው የቤተሰቦቻቸውን ሸክም መጋራት የሚለው የአንድ ሳምንት ዘመቻ ለሁለተኛ ጊዜ ተካሄዷል፡፡

ግንቦት19-21 በነዚህ ቀናት በዋለው ችሎት ላይ ከፍተኛ መወዛገብ ያሳየው አቃቤ ህግ ሲዲዎቹን እንደማስረጃ ማስመዝገብ ባለመቻሉ እና ምስክሮችንም ማቅረብ ስላልቻለ ሲዲዎቹ ከማስረጃ ላይ አንዲወገዱ እንዲሁም ተጨማሪ ምስክሮችን ለማቅረብም የተወሰነው ጊዜ በቂ ሆኖ አልተጠቀመበትም በሚል ምክንያት ተጨማሪ እድል እንዳይሰጠው ተወስኗል ፡፡

አቃቤ ህግ አንደኛ ተከሳሽ ሶልያና ሽመልስ ላይ አለኝ ያለውን የሲዲ ማስረጃ አስመልክቶ ሌሎች ተከሳሾች ማየት አለባቸው ወይስ ፍር ቤቱ በጽህፈት ቤት ማየት አለበት የሚለውን ለመወሰን ሰኔ 8 ተቀጥሯል፡፡

በተመሳሳይ ቀን ችሎት ውስጥ አቤል ዋበላ ከዳኞች ጋር በነበረው አለመስማማት የተነሳ የችሎት መድፈር ጥፋተኛ ተብሎ ለቅጣት ለግንቦት 25 ተቀጠረ፡፡

ግንቦት 23 – ሥነ-ስርዓት የሚለው የጦማሪ አቤል ዋበላ ጽሁፍ ታትሟል፡፡

ግንቦት 25 አቤል ዋበላ በችሎት መድፈር በገደብ 4 ወር ተፈርዶበታል ፡፡


ሰኔ 2007

ሰኔ 8 – ፍርድ ቤት የቀረቡት 9 ተከሳሾች  ከብይን ለሃምሌ 13 የተቀጠሩ ፡፡ በእለቱም አንደኛ ተከሳሽ ላይ የቀረበውን የሲዲ ማስረጃ በጽህፈት ቤት አይተን እንደማስረጃ ቆጥረነዋል፡፡ ለሌሎች ተከሳሾም መድረስ አይገባውም በማለት ችሎቱ ወሰነ


ሃምሌ 2007

ሃምሌ 1 ቀን 2007 ዓ/ም ባተጠበቀ ሁኔታ ሶስቱ ጋዜጠኞች እና ሁለት የዞን9 ጦማርያን ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር መፈታታቸው ዜና ተሰማ ፡፡ በእለቱ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ፣ ጋዜጠኛ አስማማው ሃይለጊዮርጊስ እና ጦማሪ ዘላለም ክብረት ሲፈቱ በማግስቱ ጠዋት ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ እና ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን ተፈቱ፡፡

በተመሳሳይ ቀን በቀሪዎቹ 5ቱ ተከሳሾች ላይ ክሱ አንደሚቀጥል የመንግስት ወዳጅ የሆነው ሬዲዬ ፋና በድረ ገጹ አሳወቀ ፡፡

ሃምሌ 9-11 ለሶስት ቀናት የሚቆይ እስቲ አንነጋገር የማስረጃን ነገር በሚል የተዘጋጀው ዘመቻ ተካሄደ ፡፡ ይህ ዘመቻ ሃሳቡ ተከሳሾች ላይ ማስረጃ ተብለው የቀረቡ ጉዳዬችን ለአደባባይ ማብቃትና ቀሪ አራት ታሳሪዎች የሚከላከሉት ምንም ነገር እንደሌለ ለማሳወቅ የታለመ ነበር ፡፡

ሃምሌ 10 – ጦማሪ በፍቃዱ ቁዘማ፣ ከአቃቤ ሕግ ማስረጃዎች በፊት እና ጦማሪ ናትናኤል የዕለት ተዕለት ጥያቄዎቻችን ብይናቸውን አስመልክቶ የጻፋቸው ጽሁፎች ታተሙ፡፡

ሃምሌ 13 – ፍርድ ቤቱ የአንድ ምስክር ቃል ተገልብጦ አልደረሰኝም በማለት ብይኑን መስራት አለመቻሉን ገልጾ ጽሁፉ መገልበጡን ለማረጋገጥ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ ፡፡

ሃምሌ 22 – የተከሳሾች ጽሁፍ ተገልብጦ ማለቁን አረጋግጫለሁ ያለው ፍርድ ቤቱ ከጽህፈት ቤት በማስቻል በድጋሚ ለጷጉሜ 2 ቀጠሮ ሰጠ

ሃምሌ 25 – ጥቂት ስለማእከላዊ የሚል ጽሁፍ ታተመ፡፡


ሜ 2007

በአመቱ የመጨረሻ ሳምንት የመጨረሻ የእስር ሳምንታቸው ይሆናል ተብሎ ተስፋ ቢደረግም ፍርድ ቤቱ ዳኞች አልተሟሉም በሚል ሌላ ሰበብ ሁለተኛ እንቁጣጣሻቸውን በእስር እንደሚያሳልፉ ያረጋገጠውን የ31 ቀን ቀጠሮ በመስጠት ለመስከረም 27 ለአራተኛ ጊዜ በአጠቃላይ ደሞ ለ37ተኛ ጊዜ ቀጠሮ ሰጠ ፡፡ 

 

በግዙፉ የአባይ ግድብ ላይ መካሄድ ያለበት የተጽእኖ ጥናት በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ያልቀጠለው በተመረጡት አማካሪ ድርጅቶች ችግር መሆኑን የኢትዮጵያ የቴክኒክ ኮሚቴ ሰበሳቢ አስታወቁ።

ጥናቱን ያዘገየችዉ ኢትዮጵያ እንደሆነች ተደርጎ በአንዳንድ የግብጽ ወገኖች የሚሰራጨው መረጃም የተሳሳተ ነው፤ ሲሉ አቶ ጌድዎን አስፋው ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

“እንደ ረዳት ጳጳስ ነኝ” የሚሉት ሥራ አስኪያጁ፣ ሕጋዊ ህልውናዋን ለአደጋ አጋልጠውታል ምደባቸው፣ ከመንግሥት ሕግ እና ከሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን አንጻር ጥያቄ ተነሥቶበታል ለስምንት ዓመታት የሒሳብ ሪፖርት ለሚመለከተው መንግሥታዊ አካል አልቀረበም በመላው ደቡብ አፍሪቃ ያለችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በደቡብ አፍሪቃ መንግሥት አትራፊ ባልኾኑ ሕዝባዊ ድርጅቶች ዐዋጅ(NPO) ሕግ መሠረት እ.አ.አ በ26/01/1999 ሕጋዊ ፈቃድ አግኝታ፣ በቁጥር 006-083 …

ጷግሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቫይስ ኒውስ የተባለው ድረገጽ የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ወቅታዊ ሁኔታ ይዞ በወጣው ዘገባ እንደገለጸው፣ የእንግሊዝ ባለስልጣናት አቶ አንዳርጋቸው ታስረው ከነበሩበት ስውር ቦታ ወደ ቃሊቲ መዛወራቸው በጎ ነገር ቢሆንም፣ በቃሊቲ በጥሩ ሁኔታ ተይዘዋል ብለው አያምኑም። የእንግሊዝ የውጭና የጋራ ብልጽግና አገራት ቃል አቀባይ ” ኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደም …

ጷግሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ የተለያዩ አገራት በፈረንጆች አቆጣጠር ከ2008 እስከ 2012 ለትምህርት የመደቡትን በጀትና ወደ ውጭ አገራት በህገወጥ መንገድ የወጣውን ገንዘብ በማነጻጸር ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ ላይ እንደጠቀሰው ፣ በኢትዮጵያ በህገወጥ መንገድ የወጣው ገንዘብ፣ ለትምህርት ከወጣው ገንዘብ በ245 በመቶ ይልቃል። ድርጅቱ ቀድም ሲል ባወጣው ሪፖርት ከ2008 እስከ 2012 ባሉት …

ጷግሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢሮው በጣና ሐይቅ ላይ በቱሪስት ማስጎበኘት ስራ በተሰማሩ ማህበራት አሰራር ጣልቃ በመግባቱ በተከሰሰበት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡ ባለስልጣን ቢሮው የቱሪስት ጀልባዎችን በተራ ለማሰራት ያደረገው የተራ ማስከበር ስራ ህግና ደንቡን ያልተከተለ ነው በማለት የተቃወመውን የጥዋት ብርሃን አነስተኛና መለስተኛ የግል ጀልባ ባለንብረቶች ማህበር ፣ …


የሰው ልጅ ምንጭ የተባለ ዝርያ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መገኘቱ ዛሬ፤ ጳጉሜ 05/2007 ዓ.ም ይፋ ሆኗል፡፡ የግኝታቸውንና የምርምራቸውን ሪፖርት ኢላይፍ መፅሔት ላይ ያወጡትና ጆሃንስበርግ ላይ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ሳይንቲስቶች የዝርያውን ስም “ኦሞ ናሌዲ – Homo Naledi” ሲሉ ጠርተውታል፡፡

ክሬድል ኦፍ ሂዩማንካይንድ እየተባለ በሚጠራው የዓለም ጥብቅ ውርስ አካባቢ ከደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ጆሃንስበርግ ወጣ ብሎ በሚገኙ የራይዚንግ ስታር አካባቢ ተያያዥ ዋሻዎች ውስጥ ነው ቅሪተ-አካሉ የተገኙት፡፡

የጋውተንግ ጠቅላይ ግዛት የአስተዳደር ምክር ቤቱ አባል ሌቦንግ ማይሌ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “ለሣይንስና ለግኝቶች፣ ለታሪክና ለዕውቀት፤ ታላቅ ቀን ነው” ብለውታል፡፡

ዝርያው ኢትዮጵያ ውስጥ ከተገኙት ከእነ ሉሲ ዓይነቱ ዝርያ የተለየ መሆኑ ቢገለፅም ዕድሜው ስንት እንደሆነ ግን ገና አልታወቀም፡፡

አምዶም ገብረስላሴ ኣንጃው ይህ ኣብዮታዊ እርምጃ እንደሚ ወስድ ያሳወቀው “12ተኛ ጉባኤ እንዴት ኣለፈ…?” የሚል ኣጀንዳ በየመንግስት መስርያ ቤቶች፣ ከመቐለ ከተማ ኑዋሪዎች፣ የክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ካድሬዎችና ኑዋሪዎች ውይይት እየተካሄደ ነው። በመቐለ ማዘጋጃ ቤት ማክሰኞ 3/ 13/ 2007 ዓ/ም በኣቶ ተስፋኣለም ተወልደብርሃን …

የትግራይ ፌስቡክ ተጠቃሚዎች ኣብዮታዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው መሆኑ በኣባይ ወልዱ የሚመራው የህወሓት ኣንጃ ኣሳወቀ Read more »

የታደለ አገልጋይ የበላዩን ከስሕተት ይጠብቃል፡፡ ‹አማካሪ የሌለው ንጉሥ ያለ አንድ ዓመት አይነግሥ› እንዲሉ፡፡ አክዓብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከክርስቶስ ልደት በፊት(871-852 ቅልክ) የነበረ ንጉሥ ነው፡፡ የሚስቱን የኤልዛቤልን ቃል ሰምቶ ነቢያተ እሥራኤልን ሊያጠፋ ተነሣ፡፡ ብዙዎች በሰይፉ ጠፉ፣ ብዙዎችም አገር ጥለው ተሰደዱ፡፡ በአክአብ ቤተ መንግሥት ውስጥ ግን አብድዩ የተባለ ልብ ያለው ባለሟል ነበር፡፡ ንጉሡን ከጥፋቱ ማዳን ቢያቅተው በንጉሡ ስሕተት ባለመስማማቱ 100 ነቢያትን በሁለት ዋሻ ውስጥ ደብቆ የቤተ መንግሥቱን ምግብ እየመገበ ከአክዓብ ጥፋት አድኗቸው ነበር፡፡ በዚያ ዘመን ነቢያት የእሥራኤል የዕውቀትና የእምነት መሪዎች ናቸው፡፡ የእሥራኤል ባህል፣ ታሪክ፣ ትውፊትና ዕውቀት የሚተላለፈው በነቢያት ትውፊት ነበርና፡፡ ነቢያቱን ማጥፋትም ሀገሪቱን ያለ ታሪክ፣ ዕውቀት፣ ባህል፣ ሥርዓትና ቅርስ ማስቀረት ነበር፡፡ ለዚህ ነው አብድዩ የንጉሡን ዐዋጅ ማስቀየር ቢያቅተው ነቢያቱን ደብቆ እየመገበ ሀገሪቱን ከከባድ ጥፋት የታደጋት፡፡ 

ይህንን ሥራውን ማንም እንዲያውቅለትም፣ እንዲያውቅበት አላደረገም፡፡ ዓላማው ዕውቅና ጥቅም ማግኘት ሳይሆን ሀገር ማትረፍ ነውና፡፡ የንጉሡን የጥፋት ዐዋጅ ማስቀረት አልችልም ብሎ ዝም አላለም፤ ነገር ግን በዐቅሙ የሚችለውን በማድረጉ በእውነትም እሥራኤል የዕውቀት፣ የታሪክና የባህል ጥፋት እንዳይገጥማት አደረገ፡፡ ያን ክፉ ዘመንም አሻገራት፡፡  
 
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የበላዮቻቸውን ጥፋት ከማስቀጠል ይልቅ በራሳቸው ዐቅም የሚችሉትን መልካምነት የፈጸሙትን ብቻ ሳይሆን፣ ‹ትእዛዝ ከበላይ እግር ወደ ላይ› ከማለት አልፈው አለቆቻቸውን ከጥፋት የታደጉ የበታች አገልጋዮችንም ታሪክ እናገኛለን፡፡ የሶርያው ንጉሥ የቤን ሐዳድ 2ኛ የጦር አዛዥ ንዕማን ወደ ሰማርያ መጥቶ ነቢዩ ኤልሳዕን ባገኘው ጊዜ ከለምጽ ሕመሙ ይድን ዘንድ በዮርዳኖስ ወንዝ እንዲጠመቅ መክሮት ነበር፡፡ ንዕማን በዚህ ደስተኛ አልሆነም፡፡ ተቆጥቶም ወደ ሀገሩ ሊጓዝ ተነሣ፡፡ አንደኛው ባለሟሉ ግን ለጦር አዛዥ የሚገባ ምክርን መከረው ‹‹ጌታዬ ምን ቸገረህ፣ ውረድና ተጠመቅ፤ ከተፈወስክ እሰዬው፤ ክልሆነ ግን ከሰማርያ ጋር የምንዋጋበት ምክንያት እናገኛለን››፡፡ የጦር አዛዡ ንዕማን በዚህ የወታደሩ ሐሳብ ተስማማ፡፡ ዮርዳኖስ ወርዶም ተጠመቀ፡፡ ዳነም፡፡ አገልጋዩም አዛዡን ከጥፋት አዳነው፡፡ ንዕማንም ሊፈጽመው በነበረው ስሕተት ተጸጸተ፡፡
 
በታሪክ ውስጥ ግን እንደ አብድዩና የንዕማን ወታደር የበላዮቻቸውን ስሕተት የማይደግሙ ወይም አለቆቻቸውን ከስሕተት የሚታደጉ የበታቾች ብቻ አይደሉም የነበሩት፡፡ ያሉትም፡፡ አለቆቻቸው ያላሰቡትን ጥፋት በመሥራት አለቆቻቸውን ያስደሰቱ መስሏቸው ሀገር ያጠፉም አሉ፡፡ ‹ከለማበት የተጋባበት› እንዲሉ፡፡ ‹ጌታዬ እንዲህ ባደርግለት ይደሰታል› ብለው በማሰብ ከልክ እያለፉ፣ የሌለ እየጻፉ፣ ያልታዘዘ እየፈጸሙ ግፍ ሲሠሩ የኖሩ፡፡ ያዘው ሲባሉ ጣለው፤ እሠረው ሲባሉ ግደለው፤ አምጣው ሲባሉ ስቀለው፤ ተቀበለው ሲባሉ ቀማው የተባሉ እየመሰላቸው ሕግ ሲያልፉ፣ ገደብ ሲጥሱ የኖሩ አሽከሮችም ነበሩ፡፡ አሉም፡፡   
 
በሀገራችን ከነነዌ ጾም በኋላ የሚመጣው ኀሙስ ‹የዕብድ ኀሙስ› ይባላል፡፡ ቀኑ አለቆቻቸውን ለማስደሰት ሲሉ በግፍ ላይ ግፍ፣ በክፋት ላይ ክፋት፣ በመከራ ላይ መከራ፣ በቅጣት ላይ ቅጣት፣ በእንግልት ላይ እንግልት በሕዝብ ላይ ለሚጨምሩ አሽከሮች መታሰቢያ ነው፡፡ እንደ አብድዩና የንዕማን ወታደር ‹እስኪ ነገሩን እንየው› ከማለት ይልቅ ጭካኔ፣ ግፍ፣ ቅጣትና በደል አለቆቻችንን ይበልጥ ያስደስትልናል ብለው ለሚያስቡ አሽከሮች መታሰቢያ፡፡
 
በሸዋው ንጉሥ አስፋ ወሰን ዘመን ንጉሡ ለዘመቻ እየተጓዙ በደብረ ብርሃን አልፈው አንጎለላ ደረሱ፡፡ ይህን ጊዜ ጎሜ ጎሹ የተባለ አሽከር አስፋ ወሰንን በምን ላስደስታቸው ይልና በራሱ ጊዜ ዐዋጅ ያውጃል (‹መቼም ንጉሡ ሥራ በዝቶባቸው ረስተውት ነው እንጂ ይህን ሳያውጁ አይቀሩም‹ ብሎም ይሆናል)፡፡ ‹‹በዚህ ሀገር ያለውን ሰው ሁሉ አንድ ሳታስተርፍ በለው ብለውሃል› የሚል ዐዋጅ፡፡ ሠራዊቱም የንጉሥ ዐዋጅ መሰለውና አእምሮው ትቶ ጉልበቱን በማሠራት ፈረሱን እየጋለበ ከበሬሳ እስከ አያብር፣ ካንድ ዐርብ እስከ መገዘዝ የነበረውን ሀገር ሁሉ በነነዌ ፋሲካ ዕለት ኀሙስ ዘምቶበት ዋለ፡፡ ሕዝብ አለቀ፣ ተሰደደ፣ በሀገርም ላይ መከራ ወረደ፡፡ ንጉሡም የሆነውን ሲሰሙ አዝነው ጎሜ ጎሹን ‹‹ማን አዞህ ዐወጅክ?› ቢሉት ‹‹ጌታዬ መቼም የዘመትነው ለዚህ ነው ብዬ ነው›› አለ ይባላል፡፡ ቃላዊ መረጃዎች እንደሚነግሩን አስፋ ወሰን ጎሜ ጎሹን ቀጥተውና አሥረው ከዘመቻ ወደ አንኮበር ላኩት፡፡
ሕዝቡም ‹‹ወይ ጎሜ ጎሹ ወይ ጎሜ ጎሹ
በድፍን ሀገር ዕዳ ነስናሹ› ብሎ ገጠመበት፡፡ ቀኑም ‹የዕብድ ኀሙስ ተባለ›› ይላሉ ጸሐፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ በጻፉት የዳግማዊ ምኒሊክ ታሪክ ላይ፡፡
 
የቻለ እንደ ንዕማን ወታደር አለቃውን ከስሕተት ይታደጋል፣ ከጥፋት ያድናል፤ ያልቻለም እንደ አብድዩ የበላዩን ስሕተት ማረም ቢያቅተው እርሱን ስሕተቱ ይዞት እንዳይጠፋ ራሱን ከስሕተቱ ያድናል፣ ከጥፋቱም ይጠብቃል፡፡ ለሌሎችም የመዳኛ ምክንያት ይሆናል፡፡ እንደ ጎሜ ጎሹ ‹አለቃየ ይህን ባጠፋለት ደስ ይለዋል› ብሎ የሚያስብ አሽከር ግን ‹በድፍን ሀገር ዕዳ ይነሰንሳል›፡፡ ጎሜ ጎሹዎች ትንሽ ቀዳዳ ካገኙ አስፍተው ስለሚጓዙባት አለቆቻችን ምንም አይሉንም ብለው ያስባሉ፤ እንዲያውም አብልጠው በማሰባቸው እንደሚሸለሙ ያምናሉ፡፡ ጎሜ ጎሹዎች የአለቆቻቸውን በር በመዝጋት፣ እንደ አለቆቻቸው ሆነው በመወሰን፣ ቁጣውን ወደ ጥፊ፣ ጥፊውን ወደ ግርፊያ፣ ግርፊያውን ወደ ግድያ በማሳደግ የተሻለ አፈጻጸም ለማሳየት ይተጋሉ፡፡ 
 
አብድዩና የንዕማን ወታደር የበዙላት ሀገር ዶፍ ዝናብን በጣራ፣ ካፊያን በጥላ እንደሚከለል ሰው፣ ከላይ የሚመጣውን ጥመት አቃንተው፣ የሚወርደውን ጥፋት አርመው፣ ቁጣውን በትዕግሥት፣ መዓቱን በምሕረት ስለሚለውጡት ድፍን ሀገር ዕዳ ሳይሆን ፋታ ያገኛል፡፡ ጎሜ ጎሹዎች ሲበዙ ግን በበሆር ላይ ቆረቆር፣ በዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ፣ በዕዝል ላይ እንጥልጥል፣ በራቁት ላይ ብርድ፣ በጥማት ላይ ንቃቃት ይሆናል፡፡ ሕዝቡ እንዳለው ጎሜ ጎሹዎች ‹በድፍን ሀገር ዕዳ ይነሰንሳሉ›፡፡ እነርሱ ለዕለቱ የሚያገኙትን ሹመት ሽልማት፣ ጉርሻና ድርሻ እንጂ አለፍ ዘለቅ አድርገው የችግሩን ውጤት አያስቡትምና ጎሜ ጎሹዎች የሚያመጡትን ዕዳ ሀገር ስትከፍለው ትኖራለች፡፡    
 
በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያችን ጎሜ ጎሹዎች ሳይሆን አብድዩዎችና የንዕማን ወታደሮች የሚበዙባት ሀገር ትሁን፡፡

Hailemaraim visits graduating troops
የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት መከላከያ ሰራዊት ለአባይ ግድብ መስሪያ ገንዘብ እንዲያዋጡ ለቀረበላቸው ጥሪ። እንዳልተቀበሉት ምንጮቻችን ከመከላከያ ውስጥ ገለፁ፣በምንጮቻችን መረጃ መሰረት።- የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንደ አዲስ ለአባይ ግድብ መስሪያ የሚሆን በሚል ገንዘብ እንዲያዋጡ በአመራሮቻቸው ለቀረበላቸው ጥሪ። አንቀበልም ማለታቸውን የገለፀው መረጃው። ለቀረበው ጥሪ ሳይቀበሉት የቀሩበት ምክንያትም “ ባለፉት ጊዚያት በተደጋጋሚ የከፈልነውን ገንዘብ ቦንድ ይሰጣቸኋል ተብለን እስከ አሁን ድረስ […]

ተሸራርፈው እና ተገልብጠው ጎልተው እንዳይወጡ መደረጋቸውን ዳይሬክቶሬቱ ገምግሟል “የመልካም አስተዳደር ድምፃችን አልተሰማም፤ ውክልናችንም አንሷል” (ሰንበት ት/ቤቶች) ምክክሩ፣ በሀገረ ስብከቱ የሰባቱ ክፍላተ ከተማ እና በሌሎችም አህጉረ ስብከት ይቀጥላል (ሰንደቅ፤ ፲፩ኛ ዓመት ፭፻፳፪፤ ረቡዕ፣ ጳጉሜን ፬ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት 170 አድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ሰባክያነ ወንጌል፣ ካህናት፣ የሰንበት …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ኤርትራ የኢትዮጵያ ወረራ ያሰጋኛል አለች

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ጳጉሜን 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ ኢትዮጵያ ኤርትራን ለመውረር እያስፈራራች መሆኗን አስታውቋል፡፡ ምንም እንኳ የመረጃው ምንጭ ማን እንደሆነ የኤርትራ መንግሥት ባይናገርም፣

ኢትዮጵያ ኤርትራን ለመውረር ከአሜሪካ ይሁንታ ማግኘቷንና ኢትዮጵያም በይፋ መግለጿን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ምንም እንኳ ከወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ኤርትራን በተመለከተ በፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ፣ የኤርትራ መንግሥት ኢትዮጵያንና ሌሎች የጎረቤት አገሮችን ለማተራመስ የያዘውን ስትራቴጂ የማይተው ከሆነ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ተገዶ ዕርምጃ እንደሚወስደና የኢትዮጵያን ሕዝብ እንደሚያሳውቅ መናገራቸው አይዘነጋም፡፡ በወቅቱ የኤርትራ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ምንም ሳይል አሁን የኢትዮጵያ ወረራ ያሰጋኛል ማለቱ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ በምሥሉ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ ዩኑስ በኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ቀን አከባበር ሥነ ሥርዓት በቅርቡ በተካሄደበት ወቅት የሚታዩ ሲሆን፣ ዝርዝር ዘገባው ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ ወይም በ ፖለትካ ገጽ ላይ ይመልከቱ፡፡ 

 

ጦማሪያኑ ለአራተኛ ጊዜ ለብይን መቀጠራቸውን ተቃወሙ

‹‹አንድ ዳኛ ምንም ማድረግ አይችልም›› ዳኛ ዘሪሁን ደሳለኝ

‹‹ከዳኞች ጋር ምንም ችግር የለብንም ከማን ጋር እንደተጣላን ገብቶናል›› በእስር ላይ ያሉ ጦማሪያን

በተጠረጠሩበት የሽብር ተግባር ወንጀል ክስ ከተመሠረተባቸው በኋላ የከሳሽ ዓቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ቀርቦባቸው ለብይን የተቀጠሩት አራት ጦማሪያን፣ ለአራተኛ ጊዜ ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱን ተቃወሙ፡፡ 

ተከሳሾቹ ጦማሪያን ናትናኤል ፈለቀ፣ አቤል ዋበላ፣ አጥናፍ ብርሃኔና በፍቃዱ ኃይሉ ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ብይን እንደሚሰጥ የጠበቁ ቢሆንም፣ ጉዳያቸው በሦስት ዳኞች የሚታይ ከመሆኑ አንፃር በዕለቱ አንድ ዳኛ አቶ ዘሪሁን ደሳለኝ ብቻ የተገኙ በመሆናቸው ብይኑ ሳይሰጥ ቀርቷል፡፡ ብይኑ ተሠርቶ የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ ዳኞች ባለመሟላታቸውና በመዝገቡ ላይ ባለመፈረማቸው ብይኑ ሊነገር እንደማይችል ዳኛ ዘሪሁን ገልጸዋል፡፡ 

በዳኞች አለመሟላት ለሁለተኛ ጊዜ መቀጠሩ ያበሳጫቸው ተከሳሾቹ፣ ‹‹እኛ ከዳኞች ጋር ምንም ችግር የለብንም፡፡ ከማን ጋር እንደተጣላን ገብቶናል፡፡ የምንፈልገው ቁርጥ ያለው እንዲነገረን ነው፡፡ ወይ በነፃ እንሰናበት ወይም ተከላከሉ እንባል፡፡ ብይን ለመስጠት በሚቀጠሩት ቀናት መካከል ያለው ጊዜ ለእኛ ሕመም ነው፤›› በማለት ቅሬታቸውን ተናግረዋል፡፡ 

የጦማሪያኑ ጠበቃ አቶ አመሀ መኰንን ‹‹ዳኞች እንዲሟሉ መተባበር ያለብን ነገር ካለ እንተባበር ወይም ለፍርድ ቤቱ አስተዳደር እናመልክት፤›› የሚል ሐሳብ ለዳኛ ዘሪሁን አቅርበዋል፡፡ ዳኛው በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹የሚቻል ከሆነ ሞክሩ፤›› ብለዋል፡፡ እሳቸውም ብይኑ ቢሰጥ እንደሚመርጡ፣ ተጠርጣሪዎቹን ዓይናቸውን ባያዩ ደስ እንደሚላቸውና (በተደጋጋሚ በመመላለሳቸው) በግላቸው እንደሚከብዳቸው ተናግረዋል፡፡ 

ያልተሟሉት ዳኞች በተለያዩ ምክንያቶች መቅረታቸውን በመጠቆም፣ እንደተሟሉ እስከ መስከረም 10 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ለማረሚያ ቤቱ ተነግሮ ብይኑ ሊሰጥ እንደሚችል በጽሕፈት ቤት አስታውቀዋል፡፡

 

በቁጥጥር ሥር የዋሉት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ነው

የጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ጋሕነን) ተብሎ በሚጠራው የሽብር ቡድን ውስጥ አባል ከሆኑትና በካናዳ፣ በእንግሊዝ፣ በኤርትራና በተለያዩ አገሮች ከሚገኙ አባላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ የጋምቤላን ክልልን ለመገንጠል ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል የተባሉ ሦስት ተጠርጣሪዎች ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ተከሰሱ፡፡

የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ተረኛ ችሎት ክስ የመሠረተባቸው ተጠርጣሪዎች ኦሞት አጉዋ ኦክዋይ፣ አሽኔ አስቲን ቲቶይክና ጀማል ዑመር ሆጃሌ የሚባሉ ናቸው፡፡ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ከስድስት ወራት በፊት የሽብር ቡድን የተባለው ጋሕነን ኬንያ ናይሮቢ በሚያካሂደው ስብሰባ ላይ ለመካፈል ሲሄዱ፣ መጋቢት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መሆኑን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

አንደኛው ተከሳሽ ኦሞት አጉዋ ኦክዋይ ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ ‹‹የጋምቤላን ክልል ከፌዴሬሽኑ መገንጠል›› የሚል ፖለቲካዊ ግብ በማስቀመጥ፣ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለማፈራረስ የአገር ውስጥ አስተባባሪ በመሆን ሲንቀሳቀስ እንደነበር በክሱ ተገልጿል፡፡ የሽብር ቡድኑ ከፍተኛ አመራር ከሆነውና በደቡብ ሱዳን ከሚገኘው ኡቺች ከሚባለው ግለሰብ ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ ኤርትራ ውስጥ ወታደራዊ ሥልጠና የወሰዱ አባላትን ወደ ጋምቤላ እንዲልክለት በማድረግ፣ የሽብር ቡድኑን ተልዕኮ እንዲያስፈጽሙ በጋምቤላ ልዩ የፖሊስ አባላት ውስጥ እንዲቀጠሩ ማድረጉንም አክሏል፡፡

ተከሳሹ በጋምቤላ ከተማ ውስጥም የቡድኑን አባላት በመሰብሰብና አመራር በመስጠት፣ እንግሊዝ ለንደን ውስጥ ከሚኖረውና ከፍተኛ አመራር ከሆነው ኝኬው አቡላ ከሚባል ግለሰብ ጋር በኢሜል በመገናኘት የአባላቱ ቁጥር እንዲጨምር መጠየቁን ክሱ ያስረዳል፡፡ ኝኬው አቦላ በውጭ አገር የሚገኙ ጋዜጠኞች አኝዋክ ዞን ሄደው መረጃ እንዳይሰበስቡ የኢትዮጵያ መንግሥት የከለከለ መሆኑን ለኦሞት ገልጾለት ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ አምስት ሰዎች፣ ከጋምቤላ አኝዋክ ዞን የቡድኑ አባላት፣ ከደቡብ ኦሞ አሥር ሰዎችን መልምሎ ኬንያ በሚደረገው የቡድኑ ስብሰባ ላይ እንዲሳተፉ እንዲያደረግ ባዘዘው መሠረት፣ መልዕክት በማስተላለፍና በማደራጀት ተግባር ላይ መሳተፉን ክሱ ያብራራል፡፡ ለሽብር ተግባር ማስፈጸሚያ 3,000 የእንግሊዝ ፓውንድ የተላከለት መሆኑንም አክሏል፡፡

ሁለተኛው ተከሳሽ አሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት ውስጥ በሚኖረው የሽብር ቡድኑ ከፍተኛ አመራር በሆነውና በቅጽል ስሙ ኡጆ በሚባለው ግለሰብ አማካይነት በ2006 ዓ.ም. የሽብር ቡድኑ አባል ሆኖ መመልመሉን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ ከዚያም እንግሊዝ አገር ከሚኖረው የሽብር ቡድኑ አባል ኝኬው አቡላ ጋር በኢሜል በመገናኘት፣ ‹‹የጋምቤላን ክልል ከሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች በመገንጠል ራሱን የቻለ ሉአላዊነት አገር መመሥረት›› በሚለው ሐሳቡ ተስማምቶ፣ በማጃንግ ዞን የሚኖሩ የማጃንግ ብሔርና ደገኞች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት፣ የማጃንግ ብሔሮች ተጐድተው እያለ፣ መንግሥት ዕርምጃ የወሰደው በማጃንግ ከፍተኛ አመራሮችና በጋምቤላ ክልል የልዩ ኃይል ፖሊስ ላይ ብቻ እንደሆነ በመግለጽ፣ ሐሰተኛ መረጃ ለሽብር ቡድኑ ያቀብል እንደነበር በክሱ ተብራርቷል፡፡ 

ተከሳሹ የአገር ውስጥ ከፍተኛ አመራር ከሆነው አንደኛ ተከሳሽ ኦሞት ጋር በስልክ ግንኙነት በማድረግ ቀኑ በትክክል ባልታወቀበት የካቲት ወር 2007 ዓ.ም. አራት ኪሎ አካባቢ በመገናኘት፣ ኑዌሮች ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመመሳጠር የሰብዓዊና የዴሞክራሲ መብት ጥሰት እያደረሱ መሆኑን፣ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ለማዳረስ የጋሕነን ከፍተኛ አመራሮች በኬንያ ናይሮቢ በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ እንዲገኝ መመካከራቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡ መንግሥት በጋምቤላ ነባር ብሔረሰቦች፣ በተለይም በማጃንግ ላይ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን እየፈጸመ መሆኑንና በክልሉ የመሬት ወረራ እያደረገ መሆኑን ለማስገንዘብ ‹‹Deforstation, Dis-Possission and Displacement of Gambella in General and Major People in Particular›› የሚል ጥናታዊ ጽሑፍ በስብሰባው ላይ እንዲያቀርብ ተሰጥቶት እንደነበር ክሱ ያብራራል፡፡ 

ሦስተኛው ተከሳሽ ደግሞ በጥቅምት ወር 2006 ዓ.ም. ‹‹የአካባቢ ግንኙነትና ጥበቃ›› በሚል ሽፋን በኬንያ ናይሮቢ የሽብር ቡድኑ በሚያደርገው ስብሰባ ላይ በመገኘት፣ መንግሥት የአካባቢው ተወላጆችን ከመሬታቸው በማፈናቀል ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ለቡድኑ አመራሮች መረጃ በመስጠት 8,800 ብር መቀበሉን የተመሠረተበት ክስ ይገልጻል፡፡ በስብሰባው ላይ እንደሚገኝ ለአንደኛ ተከሳሽ ማረጋገጫ በመስጠቱና በመገኘቱ 6,039 ብር መቀበሉንም አክሏል፡፡

በአጠቃላይ ሁሉም ተጠርጣሪ ተከሳሾች የሽብር ቡድኑ በኬንያ ናይሮቢ በሚያደርገው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ለመሄድ መጋቢት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውለው፣ ላለፉት ስድስት ወራት ምርመራ ሲደረግባቸው ሰንብተው ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ በአመራርነት፣ በማናቸውም መልኩ መሳተፍና ድጋፍ መስጠት ወንጀል እንደ ቅደም ተከተላቸው ክስ ተመሥርቶባቸዋል፡፡