Tag: ethiopian news in amharic
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ሐምሌ 06, 2015
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና
ፍርድ ቤት እነአቡበከርን ጥፋተኛ አለ
የፊደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት በነአቡበክር አህመድ መዝገብ በፀረ-ሽብር ሕግ የተከሰሱት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጠ።
ፍርድ ቤቱ በእነ አቡበከር የክስ መዝገብ አስራ ስምንቱንም ተከሳሾች ጥፋተኛ አለ
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት በእነ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ የአቃቤ ህግን እና የመከላከያ ምስክሮችን ቃል በንባብ አሰምቶ ማጠናቀቁን ተከትሎ ዛሬ በ18 ተከሳሾች ላይ ፍርድ ሰጥቷል። በዚህም መሰረት አቡበከር አህመድ፣ አህመዲን ጀበል፣ ያሲን ኑሩ፣ ካሚል ሸምሱ፣ በድሩ ሁሴን፣ ሼህ መከተ ሙሄ መኮንን፣ ሳቢር ይርጉ፣ መሀመድ አባተ፣ አህመድ ሙስጠፋ፣ አቡበከር አለሙ፣ ሙኒር ሁሴን፣ ሼህ […]![]()
በሽብርተኝነት የተከሰሱት እነ አቡበከር መሐመድ ጥፋተኛ ተባሉ
የሽብረተኝነት ክስ የተመሠረተባቸው እነ አቡበከር መሐመድ ከሁለት ዓመት በላይ ጊዜ ከወሰደ ክርክር በኋላ በዛሬው ዕለት ጥፋተኛ ተባሉ፡፡
በፌዴራል ዓቃቢ ሕግ ክስ ተመሥርቶባቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ከጥቅምት 15 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ በተካሄደ ክርክር፣ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበባቸውን የሰውም ሆነ የሰነድ ማስረጃዎች ማስተካከል አልቻሉም የተባሉት
አቡበከር መሐመድ፣ አህመዲን ጀበል፣ ያሲን ኑሩ፣ ከሚል ሸምሱ፣ በድሩ ሁሴን፣ ሼክ መከተ ሙሔ፣ ሳቢር ይርጉ፣ መሐመድ አባተ፣ አህመድ ሙስጠፋ፣ ካሊድ ሽኩር፣ አቡበከር ዓለሙ፣ ጉሩ ቱርኪ፣ ሼክ ባህሩ ኡመር፣ ሙኒር ሁሴን፣ ሼክ ሰኢድ፣ ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው፣ ሙባረክ አደም፣ እንዲሁም ካሊድ አብርሃም በዛሬው ዕለት ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡
ተከሳሾቹ የተሰጠባቸውን የፍርድ ውሳኔ ከመቀመጫቸው በመነሳት በተደጋጋሚ ተቃውመዋል፡፡ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ለሐምሌ 27 ቀን 2007 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን፣ ዓቃቤ ሕግ የቅጣት ማክበጃውን ተከሳሾች ደግሞ የቅጣት ማቅለያቸውን እስከ ሐምሌ 10 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ በጽሕፈት ቤት በኩል እንዲያስገቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት ይናገራል
«ወደ ዝዋይ ማረሚያ ቤት እንደተዘዋወርኩ ከጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እና አበበ ቀስቶ ጋር ነበርን፡፡ ከጥቂት ጊዜያቶች በኋላ አበበ ቀስቶ ለህክምና ወደ አዲስ አበባ ሲዘዋወር ውብሸት ታዬ ወደ ሌላ ዞን ተቀየሯል፡፡ ዛሬ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በማንም እንዳይጎበኝ ተከልክሏል፡፡ እኔም ለተወሰኑ ወራት በማንም እንዳልጎበኝ እግድ ተጥሎብኝ እንደነበር ታውቃላችሁ፡፡ በኋላ ላይ ቤተሰቦቼ እና ወዳጆቼ እንዲጠይቁኝ ተፈቅዶ ነበር፡፡ ሰሞኑን ግን […]![]()
ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ስለላ ለማድረግ አንድ ሚሊዮን ዶላር ከፍላለች።
አፕሪል 18፣ 2012 ከሚላን የ”ሐኪንግ ቲም” ቢሮ የወጣው የክፍያ መጠየቂያ የተላከው ለኢንሳ (የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ)ነው። ክፍያው የተፈጸመለት ሐኪንግ ቲም መቀመጫውን ጣልያን ያደረገ የኢንተርኔት ስለላ መሣሪያዎችና አግልግልቶችን የሚሰጥ ድርጅት ነው። ዜናው አክሎ እንደሚያተተው፣ ከመለስ ዜናዊ ሞት ከስምንት ወራት በኋላ ቢንያም ተወልደ የተባለ ግለሰብ ከመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ጋራ ግንኙነት ያላቸው ስምንት ዶሜኖችን (የድረ ገጽ ስያሜና […]![]()
አርበኞች ግንቦት ጥቃት መሰንዘሩን እንደቀጠለ ነው// የሳምንቱን አበይት ዜናዎችን ከDCESON ራዲዮ ይከታተሉ
አርበኞች ግንቦት 7 ጥቃት መሰንዘር መጀመሩን ዛሬ አስታወቀ። የአርባ ምንጭና አካባቢው ነዋሪዎች በወያኔ የፀጥታ ኃይሎችና ደህንነቶች ያልተቋረጠ እስር፣እና አፈና እየተፈፀመባቸው መሆኑ ተገለፀ፡፡ ኢትዮጵያዊው ወታደር አልሸባብን መቀላቀሉ ተሰማ ብሀዴን መቢያስተዳድረው የአማራ ክልል የተለያዩ ተቋማት ውጤት አልባ በመሆናቸው እየፈረሱ መሆኑ ተነገረ በላይቤሪያ አዲስ በኢቮላ ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ለሁለተኛ ጊዜ ተገኙ። አሰግድ ታመነ Filed under: NEWS, political […]![]()
የኢትዬጵያ ቡና የተጫዋቾች ሰርቪስ የመጋጨት አደጋ ገጠመው ፡፡
የኢትዬጵያ ቡና የተጫዋቾች ሰርቪስ የመጋጨት አደጋ ገጠመው ፡፡ የኢትዬጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ከ17 አመት በታች ቡድን ለጥሎ ማለፍ ዋንጫ ለዋንጫ ለማለፍ ሰኔ 28/2007 ዓ.ም ከደደቢት ጋር ወሳኝ ግጥሚያ ነበረባቸው ፡፡ ይህን ተከትሎ ዛሬ ልምምዳቸውን በሱሉልታ ሜዳ አድርገው በሰርቪሱ ሲመለሱ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት አካባቢ ወደ 18 ማዞሪያ የመኪና አደጋ አጋጥሟቸዋል ፡፡ በአደጋው ሶስት ተጫዋቾች ላይ […]![]()
ከቻይና በኮንቴይነር ታሽጎ ወደ ኢትዮጵያ የተላከው ዘይት የድንጋይ ንጣፍ ሆኖ ተገኘ
ከ1.9 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል -የጋላፊንና የሚሌን ፍተሻ ጣቢያዎች ማለፉ ግርምት ፈጥሯል -ተጠያቂዎቹ ንግድ መርከብና የቻይና ድርጅት መሆናቸው ተጠቁሟል በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የሚገኘው አሚድአብ ጄኔራል ቢዝነስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ከቻይናው ዌይፋንግ ሹኦፌንግ ኢምፖርትና ኤክስፖርት ኩባንያ ገዝቶ ወደ ኢትዮጵያ ያስመጣው በአራት ኮንቴይነሮች የአኩሪ አተር ዘይት፣ ሰኔ 23 ቀን 2007 ዓ.ም. መቐለ ደረቅ ወደብ […]![]()
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ሐምሌ 05, 2015
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡
የፕሬዝደንት ኦባማ የኢትዮጵያ የጉብኝት ዕቅድና ትችቱ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በሐምሌ ወር ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ተነግሯል። ፕሬዝደንቱ በአፍሪቃ በሚያደርጉት ጉብኝት የአባታቸዉ ሀገር ኬንያን እንደሚጎበኙ ቀደም ብሎ ነበር የተሰማዉ። ቆየት ብሎ ደግሞ ኢትዮጵያንም እንደሚሄዱ ተነገረ።
ወያኔ አርበኞች ግንቦት 7 የከፈተበትን ጦርነት ከህዝብ ለመደበቅ እየሞከረ ነው
ባለፉት ሦስት ቀናት የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ትግራይ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የወያኔን ሃይል ገጥመው የወያኔ መኮንኖችን ጨምሮ በርካታ የወያኔ ሰራዊት አባላትን እንደገደሉ በቃል-አቀባያቸው አማካኝነት ለኢሳት ቴሌቪዥን ገልጸዋል። ለጥቀውም እስከ ትላንት ድረስ ውጊያው ቀጥሎ እንደሚገኝ በድጋሜ ዜናውን አብስረዋል። በወያኔ ዘረኛና ግፈኛ አገዛዝ የተንገፈገፈው የኢትዮጵያ ህዝብም ጆሮውን አቅንቶ ሁኔታውን በመከታተል ላይ ነው። ቀድሞውንም የወያኔ ሥርዓት ያለ ሃይል […]![]()
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያምና ፕሬዚዳንት ኦባማ በነዳጅ ማስተላለፊያ ግንባታ ላይ እንደሚወያዩ ታወቀ

ግዙፉ የአሜሪካ ኩባንያ ብላክ ስቶን ከጂቡቲ ኢትዮጵያ ድረስ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ለመገንባት በያዘው ዕቅድ ላይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እንደሚወያዩ ምንጮች ገለጹ፡፡
በሐምሌ አጋማሽ ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ ተብለው የሚጠበቁት ፕሬዚዳንት ኦባማ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያምና ከኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ከሚወያዩባቸው በርካታ ጉዳዮች መካከል፣ የአሜሪካ ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ለማካሄድ ያቀዷቸው ፕሮጀክቶች እንደሚገኙበት ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ከእነዚህ ፕሮጀክቶች መካከል ብላክ ስቶን ከጂቡቲ አዋሽ ድረስ ለመገንባት ያቀደው፣ 550 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር አንዱ እንደሆነ ታውቋል፡፡
ኩባንያው ይህንን ፕሮጀክት ለማካሄድ ቀደም ብሎ ምክረ ሐሳብ (ፕሮፖዛል) ለኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ኢንተርፕራይዝ አቅርቧል፡፡ ኢንተርፕራይዙ ከኩባንያው ጋር ሲደራደር ቢቆይም፣ መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ አቅጣጫ መስጠት አለበት ተብሎ ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር አቅርቧል፡፡
ገንዘብ ሚኒስቴር ጉዳዩ ነዳጅ የማጓጓዝ በመሆኑ ከአዲስ አበባ ጂቡቲ ድረስ እየተገነባ ያለው የባቡር መስመር ከሚያጓጉዛቸው ሸቀጦች አንዱና ዋነኛው ነዳጅ ማመላለስ በመሆኑ፣ በዚህ ላይ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ አስተያየት እንዲሰጥ ምክረ ሐሳቡን ልኮታል፡፡
የኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ የነዳጅ ማመላለሻ መስመሩ አዋጭ ስለመሆኑ እያጤነ መሆኑን፣ እስካሁን ቦርዱ ውሳኔውን እንዳላሳወቀ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ከጂቡቲ አዲስ አበባ ድረስ ናፍጣ፣ ቤንዚንና የአውሮፕላን ነዳጅ ለማጓጓዝ በተያዘው ፕሮጀክት 1.4 ቢሊዮን ዶላር ይፈልጋል ተብሎ ተገምቷል፡፡ ይህንን ገንዘብ ኩባንያው ከራሱና ከፋይናንስ ምንጮች የሚሸፍን ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ እንዲሰጠው የሚፈልገውም በኮንሴሽን ነው፡፡
ኩባንያው እዚህ ሥራ ውስጥ ለመግባት የፈለገው በማደግ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ፣ የነዳጅ ፍላጐቷ በየዓመቱ 15 በመቶ ዕድገት የሚያሳይ በመሆኑ ነው ተብሏል፡፡ ይህንንም ነዳጅ በየቀኑ 500 የነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች በጠባብ መንገድ ላይ 800 ኪሎ ሜትር እየተጓጓዙ የሚያመላልሱ በመሆናቸው አዋጭነቱን በመገንዘብ ነው፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን ፕሮጀክት ቢፈልገውም፣ የባቡር መስመሩ በከፍተኛ ብድር በመገንባቱና ብድሩን ለመመለስ የግድ የአገሪቱ ነዳጅ በባቡር መመላለስ ይኖርበታል በሚል ምክንያት በጥልቀት መመርመር አስፈላጊ በመሆኑ እንዳዘገየው ምንጮች ይናገራሉ፡፡
ነገር ግን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ባለሙያዎች ግን፣ መንግሥት የአገሪቱ ነዳጅ በባቡርም፣ በነዳጅ ማስተላለፊያ መስመርም ቢጓጓዝ ጠቀሜታ ይኖረዋል ይላሉ፡፡
ምክንያቱን ሲያስረዱም በሁለቱም ማስተላለፊያ መስመሮች ነዳጅ ቢጓጓዝ የትራንስፖርት ዋጋ ላይ ውድድር ስለሚኖር ቅናሽ ይኖራል የሚል ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አንዱ ማጓጓዣ መስመር እንከን ቢገጥመው፣ በአንደኛው መጓጓዣ ዘዴ መጠቀም ስለሚቻል የፕሮጀክቶቹ መደራረብ ጥቅም እንጂ ጉዳት እንደሌለውም ያስረዳሉ፡፡
ብላክ ስቶን ይህንን ፕሮጀክት ለማከናወን ያቀደው በእህት ኩባንያው ብላክ ሬይ አማካይነት ሲሆን፣ ከዓመት በፊት በአጠቃላይ ጉዳዮች ላይ ከጂቡቲና ከኢትዮጵያ መንግሥታት ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡
የአሜካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለጉብኝት አዲስ አበባ በሚመጡበት ወቅት፣ በዚህ ጉዳይ ላይ መንግሥታቸው የሚሰጠውን ድጋፍ በማስረዳት ድርድሩ ተቋጭቶ ወደ ሥራ ለመግባት ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያምና ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር እንደሚነጋገሩ ፕሮግራም መያዙን፣ ምንጮች ለሪፖርተር አረጋግጠዋል፡፡
ከቻይና በኮንቴይነር ታሽጎ ወደ ኢትዮጵያ የተላከው ዘይት የድንጋይ ንጣፍ ሆኖ ተገኘ

–ከ1.9 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል
-የጋላፊንና የሚሌን ፍተሻ ጣቢያዎች ማለፉ ግርምት ፈጥሯል
-ተጠያቂዎቹ ንግድ መርከብና የቻይና ድርጅት መሆናቸው ተጠቁሟል
በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የሚገኘው አሚድአብ ጄኔራል ቢዝነስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ከቻይናው ዌይፋንግ ሹኦፌንግ ኢምፖርትና ኤክስፖርት ኩባንያ ገዝቶ ወደ ኢትዮጵያ ያስመጣው በአራት ኮንቴይነሮች የአኩሪ አተር ዘይት፣
ሰኔ 23 ቀን 2007 ዓ.ም. መቐለ ደረቅ ወደብ ደርሶ ሲከፈት ኮንክሪት የድንጋይ ንጣፍ ሆኖ ተገኘ፡፡
የሪፖርተር ምንጮች ከደረቅ ወደብ አስተዳደር የመቐለ ቅርንጫፍ እንደገለጹት፣ አሚድአብ ጄኔራል ቢዝነስ ከቻይናው ኩባንያ የገዛውን አራት ኮንቴይነሮች አኩሪ አተር ዘይት አጓጉዞ ወደ አገር ውስጥ እንዲያስገባለት፣ ከኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ጋር ተስማምቷል፡፡ ድርጅቱም በገባው ውል መሠረት ሲአይኪው የተባለው የቻይና ድርጅት አረጋግጦና ሠርተፊኬት አሳይቶት ዕቃው መጫኑን ሰነዶች እንደሚያስረዱም ምንጮች ተናግረዋል፡፡
አሚድአብ ጄኔራል ቢዝነስ ዘይቱን ለሚልከው የቻይናው ኩባንያ እስከ ወደብ ማድረሻና የዘይቱን ዋጋ 67,860 ዶላር ከፍሏል፡፡ ለመርከብ ማጓጓዣ ደግሞ ከቻይና እስከ ጂቡቲ 7,684 ዶላር ከፍሏል፡፡ ከጂቡቲ እስከ መቐለ ደግሞ የማጓጓዣ 6,433.75 ዶላር ከፍሏል፡፡ በድምሩ 81,977.75 ዶላር ወይም 1,861,550.87 ብር መክፈሉን ምንጮች ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡
አራት ኮንቴይነር አኩሪ አተር ዘይት በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ አገልግሎት ድርጅት የደረቅ ጭነት ማጓጓዣ ተሽከርካሪ ተጭኖ መቐለ ደርሶ ሲከፈት፣ በኮንቴይነሮቹ ውስጥ የተጫነው ንፁህነቱ የተረጋገጠና የተመሰከረለት የአኩሪ አተር የምግብ ዘይት ሳይሆን፣ መንገድ ላይ የሚነጠፍ (በተለይ ለውኃ ማስተላለፊያ ቱቦዎች ከላይ ሽፋን የሚውል ጠፍጣፋና ረዘም ያለ መዝጊያ ድንጋይ) ኮንክሪት ንጣፍ ድንጋይ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
በሥፍራው የነበሩ የደረቅ ወደቡ ሠራተኞችም ሆኑ ስማቸው ያልተገለጸው የድርጅቱ ባለቤት ከመደንገጣቸው የተነሳ፣ ለደቂቃዎች በፀጥታ ውስጥ ሆነው እርስ በርስ ሲተያዩ መቆየታቸውን ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡
ኤክስፖርት የሚያደርገው የቻይናው ኩባንያ ኮንቴይነሮቹን ሲወስድ ባዶ መሆናቸው ተረጋግጦና ማሸጊያ (ሲል) አብሮ እንደሚሰጠው የጠቆሙት ምንጮች፣ ኩባንያው ምርቶቹን በገባው ውል መሠረት ጥራታቸውን የጠበቁና ጉድለት እንዳይኖርም ሲአይኪው የሚባለው የጥራት ተቆጣጣሪ የቻይናው ድርጅት መከታተል እንደነበረበት፣ የመጫን ኃላፊነቱን የወሰደው የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ አገልግሎት ድርጅትም ቁጥጥር ማድረግ ይገባው እንደነበር ተናግረዋል፡፡ የመጫኛው ትዕዛዙ (ቢል ኦፍ ሎዲንግ) ዘይት ቢልም፣ ሲከፈት ግን ድንጋይ መሆኑን አክለዋል፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ መንግሥት የተወከለው የቻይናው ሲአይኪው ድርጅት ተከታትሎ ማሳሸግና ማስጫን ሲገባው፣ የማይታወቅ ዕቃ እንዲላክ ማድረጉ ግራ እንዳጋባቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ጊዜው አስፈሪ ከመሆኑ አንፃር፣ ማለትም አሸባሪ መላ ዓለምን እያሰጋ ባለበት ‹‹የተጫነው ዕቃ ፈንጂ ቢሆንስ?›› በማለት የሚጠይቁት ምንጮች፣ የድንጋዩ ጉዳይ ሕጉን ተከትሎ መፍትሔ የሚያገኝ ቢሆንም፣ መንግሥት ግን ችግሩን ሊፈትሽ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ሌላው ምንጮችን ያስገረመው ኮንቴይነሮቹ የባህር ላይ ጉዞአቸውን ጨርሰው መቐለ ደረቅ ወደብ ከመድረሳቸው በፊት፣ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ቅርንጫፍ መፈተሻ ጣቢያዎች የጋላፊንና የሚሌን የፍተሻ ጣቢያዎች የመፈተሻ እስክሪን ውስጥ ሲያልፉ፣ የታየውን የዕቃ ዓይነት ሪፖርት አለማድረጋቸው ወይም እዚያው አለማስቆማቸው ነው፡፡ በስክሪን ውስጥ ስለሚታይ ጥብቅ ቁጥጥር አድርገው ቢሆን ኖሮ እዚያው ሊይዙት ይችሉ እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ዕቃውን ያስጫኑትን የአሚድአብ ጄኔራል ቢዝነስ ድርጅት ባለቤትን ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ ችግሩን የፈጠረው ወይም ቁጥጥሩን በአግባቡ ያልተከታተለው ማን እንደሆነ፣ በአስጫኙ ላይ ለደረሰው ኪሳራ ተጠያቂው ማን እንደሆነ፣ በተለይ ጥብቅ ቁጥጥር መደረግ ያለበት የባህር ላይ ትራንስፖርትን በሚመለከት ምን መደረግ እንዳለበት ማብራሪያ እንዲሰጥ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅትን ለማነጋገር የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ በጋላፊና በሚሌ የፍተሻ ጣቢያዎች እንዴት ኮንቴይነሮቹ ሊያልፉ እንደቻለም ማብራሪያ ለመጠየቅ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣንን የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊዎችን ለማግኘት የተደረገው ጥረትም እንዲሁ አልተሳካም፡፡
ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት ልዩ የምርመራ ቴክኒኮችን የሚፈቅድ አዋጅ ቀረበ
–ለመርማሪዎች የይምሰል ጋብቻ ከመፈጸም እስከ ወንጀል ድርጊት መሳተፍ ይፈቅድላቸዋል
-የውጭ ሥራ ስምሪት አዋጅም ለፓርላማው ቀርቧል
ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት ልዩ የምርመራ ቴክኒኮችን የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ሰኔ 23 ቀን 2007 ዓ.ም. ለፓርላማ ቀረበ፡፡
ረቂቅ አዋጁ ‹‹ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርና ስደተኞችን በሕገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ›› የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
ረቂቅ አዋጁ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ፣ ምክር ቤቱ ለሕግ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና ለማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ መርቶታል፡፡ የረቂቅ አዋጁ መፅደቅ በአስቸኳይ የሚፈለግ መሆኑ በአፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ የተገለጸ ሲሆን፣ ረቂቁ ፓርላማው ማክሰኞ ሰኔ 30 ቀን 2007 ዓ.ም. የሥልጣን ዘመኑን ከማብቃቱ በፊት ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ረቂቅ አዋጁ በሃምሳ አንቀፆችና በሰባት ምዕራፎችም የተከፋፈለ ነው፡፡ ምዕራፎቹም ጠቅላላ ድንጋጌዎችን፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርና ስደተኞችን በሕገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀሎችን፣ የመከላከል፣ የምርመራ፣ የክስና የማስረጃ ሥነ ሥርዓት ድንጋጌዎችን፣ የተጎጂዎችን ጥበቃ፣ መልሶ ማቋቋምና ካሳ፣ ስለፈንድ መቋቋም፣ የባለድርሻ አካላት ትብብርና ልዩ ልዩ ድንጋጌዎችን የያዘ ነው፡፡
ረቂቅ አዋጁ በኢትዮጵያ በጥብቅነቱና አወዛጋቢነቱ ከሚታወቀው የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ ሁሉ እጅግ የጠበቀ የሚያደርጉ አንቀጾችን ይዟል፡፡ ከዚህ ውስጥ አንዱና በዋነኝነት የሚጠቀሰው ልዩ የምርመራ ዘዴዎችን ስለመጠቀም የሚፈቅደው አንቀጽ 18 ይገኝበታል፡፡
ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርና ስደተኞችን በሕገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀሎች በባህሪያቸው በቡድን የሚፈጸሙ በመሆናቸው፣ የወንጀል ድርጊቱ ከአንድ አገር በላይ በተደራጀ የወንጀል ቡድን የሚፈጸም በመሆኑ፣ በተለይም ከምልመላ ጀመሮ እስከ መጨረሻው ሒደት ያለው የወንጀሉ አፈጻጸም በቅብብሎሽና በቅንጅት የሚሠራ በመሆኑ፣ በዚህ ወንጀል ውስጥ የሚሳተፉ ተጠርጣሪዎችን በተሟላ ሁኔታ ለመያዝ መደበኛውን የምርመራ ሒደት መጠቀም አዋጭ እንዳልሆነ የረቂቅ አዋጁ ማብራሪያ ያስረዳል፡፡
እነዚህን ወንጀሎች ከሥር ከመሠረታቸው ለመረዳትና በወንጀል ድርጊት አፈጻጸሙ የሚሳተፉ ሰዎችን ማንነት፣ የወንጀሉን ማስረጃ፣ የአፈጻጸም ሥልት፣ የሚፈጸምበትን ሁኔታና ጥቅም ላይ የዋሉ የጉዞ አቅጣጫዎች በአግባቡ ለማወቅና በመረጃ ላይ የተመሠረተ የምርመራ ሒደትን ለማከናወን ልዩ የምርመራ ዘዴዎች መጠቀም እንደሚያስፈልግ ማብራሪያው ያስረዳል፡፡
ከእነዚህም ቴክኒኮች መካከል ሰርጎ የመግባት ማለትም በአንድ የተደራጀ የዚህ ወንጀል ቡድን ውስጥ ራሱን የዚያ ድርጊት ደጋፊ በማድረግ፣ በወንጀል ቡድኑ ውስጥ አባል በመሆን መረጃዎችንና ማስረጃዎችን ማሰባሰብ ይገኝበታል፡፡
ሌላኛው ደግሞ በድብቅ ክትትል ማድረግ ወይም ወንጀል የሚፈጽሙ ሰዎችን ቢያንስ በሁለት ዓይነት መንገድ ክትትል ማድረግን እንደሚመለከት ማብራሪያው ይገልጻል፡፡ አንደኛው ዘዴ ተጠርጣሪው ላይ በአካል የሚደረግ ክትትልና መረጃ የመሰብሰብ ሒደት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ እንደ አመቺነቱ የሚኖርበትን አካባቢ፣ ቤት፣ የሥራ ቦታ፣ ወዘተ በድብቅ የስለላ ካሜራዎች በመጠቀም እንቅስቃሴውን የመከታተል ሒደት ነው፡፡ ሌላኛው የምርመራና መረጃ የመሰብሰብ ዘዴ ደግሞ የይምሰል ግንኙነት መፍጠርን የሚመለከት ነው፡፡ ‹‹የይምሰል ግንኙነት ማለት በሕግ ውጤት የሌለው ነገር ግን በወንጀል ድርጊቱ የሚሳተፉ አካላት ላይ ማስረጃ ለማሰባሰብ የሚረዳ ግንኙነት ሲሆን፣ ለምሳሌ የወንጀል ቡድኑ ወንጀሉን ለመፈጸም ገንዘብ የሚያስፈልገው መሆኑ ከታወቀ ቀድሞ ከጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በሚገኝ ፈቃድ አንድ ሰው የወንጀል ድርጊቱን በገንዘብ እንዲረዳ በማድረግ ማስረጃ ማሰባሰብ›› መሆኑን የረቂቁ አባሪ ማብራሪያ ይገልጻል፡፡
ሌሎች ዓይነቶችን የይምሰል ግንኙነቶችን መፍጠር እንደሚቻልም ማብራሪያው ያትታል፡፡ ከእነዚህም መካከል ‹‹ከተጠርጣሪዎች ጋር ጋብቻ መፈጸም››፣ ‹‹የንግድ ተቋም በጋራ መመሥረት››፣ ወዘተ ሊያጠቃልል የሚችል ሲሆን፣ ዋነኛ ዓላማው ከሌሎች ወገን ወንጀሉን አስመልክቶ መረጃ ለማግኘት ታሳቢ ተደርጎ የሚፈጠር ግንኙነት እንደሆነና በሕግ ፊት ተጠያቂነትን እንደማያስከትል ይገልጻል፡፡
አንድ መርማሪ ሠርጎ በገባበት የወንጀል ቡድን ውስጥ አባልነቱን እንዲቀበሉት፣ የወንጀል ቡድኑ አባላት ይህንን ሠርጎ ገብ መርማሪ በግልጽ ወንጀል እንዲፈጽም ሊያደርጉት እንደሚችሉ የሚያትተው የረቂቅ አዋጁ ማብራሪያ፣ መርማሪው በተግባር ወንጀል እየፈጸመ ቢሆንም ዓላማው ማስረጃ ለማሰባሰብ በመሆኑ በወንጀል እንደማይጠየቅ ያስረዳል፡፡
ለዚህም ሲባል መርማሪው አስቀድሞም የወንጀል ነፃ ስምምነት መፈራረም እንደሚኖርበትና ይህን የወንጀል ነፃ መብት አለ በሚል ግን ግድያ ከመፈጸም፣ አስገድዶ መድፈር የመሳሰሉት ከባድ ወንጀሎች መፈጸም እንደሌለበት ያብራራል፡፡
ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርና ስደተኞችን በሕገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል ማለት፣ በአገር ውስጥ ሥራና ሠራተኛን ለማገናኘት ወይም ለሥራ፣ ለሥራ ልምምድ ወደ ውጭ አገር መላክ በሚል ሽፋን የሚፈጸም፣ በጉዲፈቻ ስምምነት በማድረግ ወይም በጉዲፈቻ ሽፋን፣ ወይም በሌላ ማንኛውም መንገድ ለምሳሌ ዛቻን፣ ኃይልን፣ ጠለፋን፣ ማታለልን፣ የተስፋ ቃልን፣ ስለሌላው ኃላፊነት ያለበትን ሰው ፈቃድ ለማግኘት በመደለል፣ ጥቅም በመስጠት ሰዎችን የመመልመል፣ የማጓጓዝ፣ የማዘዋወር፣ የማስጠለል፣ የመቀበል ወንጀል መሆኑን ረቂቅ አዋጁ ይገልጻል፡፡
ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው የራሱንም ሆነ በይዞታው ሥር ያለውን ቤት፣ ሕንፃ ለሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ዓላማ ያከራየ፣ እንዲጠቀሙ የፈቀደ ወንጀሉን በመደገፍና በማመቻቸት ተጠያቂ እንደሚሆን ይገልጻል፡፡
በተፈጸመ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ድርጊት በተጎጂው ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ወይም ሞት ያስከተለ እንደሆነ ወንጀል አድራጊው ድርጊቱን የፈጸመው በተደራጀ የወንጀል ቡድን አባል በመሆን፣ ቡድኑን በመምራት ወይም በማስተባበር እንደሆነ ወይም ወንጀሉ የተፈጸመው በብዛትና በስፋት ከሆነ ቅጣቱ የዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ወይም ሞት እንደሚሆን በረቂቁ ተካቷል፡፡
በዚህ ወንጀል ዓይነት ላይ ይርጋ እንደማይኖር የተቀመጠ ሲሆን፣ ማንኛውም ሰው ወንጀል መፈጸሙን ወይም ሊፈጽም መሆኑን የሚያውቅ ማንኛውም ሰው ለሕግ አካል የማሳወቅ ግዴታ ተጥሎበታል፡፡ በተመሳሳይም ለዚህ የወንጀል ድርጊት ዓላማ የቤተሰቡ አባል የሆነ ሰው ከመደበኛ የመኖሪያ አካባቢው የጠፋ መሆኑን ያወቀ ከሆነ፣ ወዲያውኑ ለሕግ አካል እንዲያሳውቅ ረቂቁ ያስገድዳል፡፡ በዚህ ረቂቅ አዋጅ መሠረት የተከሰሰ ሰው ወንጀሉን ስላለመፈጸሙ ለፍርድ ቤት የማስረዳት ሸክም እንደሚወድቅበትም ይደነግጋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በተመሳሳይ እጅግ በጣም ጥብቅ የሆነ የኢትዮጵያ የውጭ አገር ሥራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅም ለፓርላማው ሰኔ 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀርቧል፡፡ በዚህ ረቂቅ አዋጅ መሠረት ወደ ውጭ አገር በቤት ሠራተኝነት ለመሄድ ቢያንስ የስምንተኛ ክፍል ደረጃ ሊኖር እንደሚገባና ይህንኑም በማስረጃ ማስደገፍን ይጠይቃል፡፡ በተጨማሪም የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መያዝ የሚያስፈልግ ሲሆን፣ በሠራተኝነት መሄድ የሚቻለው ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ስምምነት ያደረገችባቸው አገሮች ብቻ ነው፡፡
በዚህ የሥራና ሠራተኛ የማገናኘት ሥራ ላይ ለመሰማራት የሚፈልጉ ኤጀንሲዎች በግለሰብ ደረጃ ከሆነ አንድ ሚሊዮን ብር ካፒታል እንደሚያስፈልግ፣ በአክሲዮን ደረጃ ከሆነ ደግሞ አምስት ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ረቂቁ ያስረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ማንኛውም ኤጀንሲ ለሠራተኛው መብትና ደኅንነት ዋስትና ማስከበሪያ የሚውል 100,000 ዶላር ወይም ተመጣጣኙን የኢትዮጵያ ብር በዝግ ሒሳብ በባንክ እንዲያስቀምጥ ይገደዳል፡፡
እንዲሁም ሠራተኛን የሚቀጥር አካል ሠራተኞች በሥራ ውል መጣስ ምክንያት የሚያነሱትን የገንዘብ ክፍያ ጥያቄዎች መሸፈን እንዲቻል፣ የውጭ አሠሪዎች የዋስትና ፈንድ እንደሚቋቋምና ለዚሁ ይረዳ ዘንድ እያንዳንዱ ቀጣሪ ለአንድ ሠራተኛ 50 ዶላር ወደ ፈንዱ እንዲያስገባ ይገደዳል፡፡
ይህ አዋጅ በተጠናቀቀው የፓርላማው የሥልጣን ዘመን ይፀድቃል ተብሎ የማይጠበቅ ቢሆንም፣ የፓርላማው የማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና የሕግ፣ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በጋራ እንዲያዩት ተመርቶላቸዋል፡፡
በቀናት ውስጥ አንድ ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ከውጭ ሊገባ ነው
የኢትዮጵያ ስኳር ልማት ኮርፖሬሽን ባለፈው ዓመት ክረምት ተከስቶ የነበረው ዓይነት የስኳር ዕጥረት እንዳያጋጥም፣ በቀናት ውስጥ ከውጭ የገዛውን አንድ ሚሊዮን ኩንታል ወደ አገር ውስጥ እንደሚያስገባ አስታወቀ፡፡
ከውጭ እንደሚገባ ከሚጠበቀው ስኳር በተጨማሪ፣ በሙከራ ምርት ላይ የሚገኙት የተንዳሆና የከሰም ስኳር ፋብሪካዎችም ምርታቸው እንደሚያቀርቡ፣ የኮርፖሬሽኑ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ዘመድኩን ተክሌ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
አቶ ዘመድኩን እንደሚሉት፣ በጥቂት ቀናት ውስጥ የሚገባው የስኳር ምርት በአገር ውስጥ ያሉ ፋብሪካዎች በክረምቱ ምክንያት ምርት ቢያቆሙ እንኳ፣ ቅድመ መጠባበቂያ እንዲሆን ከዱባይ የተገዛ ነው፡፡
በተለይ የመተሐራና የወንጂ ስኳር ፋብሪካዎች እስካሁን እያመረቱ ቢሆንም፣ በክረምቱ ምክንያት የሸንኮራ አገዳ አቅርቦት ዕጥረት እንደሚያጋጥም ይጠበቃል፡፡
ይሁን እንጂ በመኩራ ምርት ላይ ያሉት የተንዳሆና የከሰም ፋብሪካዎች የክረምቱ ዝናብ ብዙም ተፅዕኖ ስለማያደርግባቸው፣ በመጠኑም ቢሆን እንደሚያመርቱ ኃላፊው አስረድተዋል፡፡
የወንጂ ስኳር ፋብሪካ የማምረት አቅሙን ወደ 2.2 ሚሊዮን ቶን ለማድረስ ማቀዱን በቅርቡ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ የፋብሪካው ኃላፊዎች እንደገለጹት፣ በተለይ የሸንኮራ ምርት አሁን ካለው ከአምስት ሺሕ ሔክታር ወደ 12,500 ሔክታር ለማሳደግ ታቅዷል፡፡
በከፊል የሙከራ ምርት ከጀመሩት ውስጥ የተንዳንሆና የኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎችም ከሦስት እስከ ስድስት ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚጀምሩ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ የከሰም ስኳር ፋብሪካ በቀን እስከ 10,000 ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም እንዳለው የገለጹት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ አብተው፣ ሆኖም በአሁኑ ወቅት 6,000 ቶን አገዳ በቀን በመፍጨት ሙከራ እንደሚጀምር አስታውቀዋል፡፡
እንደ ስኳር ኮርፖሬሽን መረጃ ከሆነ፣ የከሰም ስኳር ፋብሪካ በ20,000 ሔክታር መሬት ላይ የተንጣለለና በመስኖ ውኃ የሚለማ የአገዳ እርሻ አለው፡፡ ሥራ በሚጀምርበት ወቅት 153 ሺሕ ቶን ስኳር፣ 12,500 ሜትር ኩብ ኤታኖል በዓመት እንደሚያመርት የሚጠበቅ ፕሮጀክት ነው፡፡ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር 260 ሺሕ ቶን ስኳርና 30,000 ሜትር ኩብ ኢታኖል፣ እንዲሁም 15 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል ተብሎም ይጠበቃል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ የዞን አመራር ገድሏል የተባለው ግለሰብ በጽኑ እሥራት ተቀጣ

‹‹ይህ ራስን ማታለልና አገርን ማዋረድ ነው›› የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር
‹‹ቅጣቱ የተሰጠው በፖሊስ ከተጣራና ፍርድ ቤቱም በምስክሮች ካረጋገጠ በኋላ ነው›› የአማራ ክልል መንግሥት
በአማራ ክልል በምሥራቅ ጎጃም ደብረ ማርቆስ ከተማ ውስጥ ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም. የተገደለው የሰማያዊ ፓርቲ የዞን አመራርና የሕግ ባለሙያው የአቶ ሳሙኤል አወቀ ገዳይ ነው የተባለ ግለሰብ፣ በ19 ዓመታት ጽኑ እሥራት እንዲቀጣ ሰኔ 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ፍርድ ተሰጠ፡፡
ፍርዱን የሰጠው የምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ማርቆስ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን፣ ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም. ከምሽቱ 1፡30 ሰዓት አካባቢ ግድያውን መፈጸሙ በምስክሮች ተረጋግጧል የተባለው ፍርደኛ ተቀበል ገዱ ይባላል፡፡
የፓርቲው የዞን አመራር አቶ ሳሙኤል በተገደለበት ወቅት የክልሉ መንግሥት በሰጠው መግለጫ፣ አቶ ሳሙኤል የተገደለው ጥብቅና ቆሞለት ከነበረ አርሶ አደር ጋር በፈጠሩት አለመግባባት እንደነበር ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ ገዳዩ የቅጣት ማቅለያ እንዲያቀርብ ሲጠይቀው፣ በደብረ ማርቆስ ከተማ ቤት ተከራይቶ የቀን ሥራ እየሠራ ቤተሰቦቹን የሚያስተዳድር መሆኑን በመግለጽ ቅጣቱ እንዲቀልለት ማመልከቱ ተነግሯል፡፡ በመሆኑም ገዳይ መሆኑ የተረጋገጠበት ፍርደኛ፣ ከአርሶ አደርነት እንዴት የቀን ሠራተኛ ሊሆን እንደቻለ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ግራ መጋባታቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በዕለቱ በችሎት ከተገኙት ቤተሰቦቹና የችሎቱ ታዳሚዎች እንደተረዱት፣ የወንጀሉ አፈጻጸም አልተገለጸም፡፡ ገደለ የተባለው ግለሰብ ሟችን አያውቀውም ብለው፣ በወቅቱ ወንጀሉን አብረው የፈጸሙ ተባባሪዎች እንዳልተያዙ የተገለጸ ቢሆንም፣ ክትትል ተደርጎ የእነሱ መያዝና አለመያዝ ሳይረጋገጥ፣ በጥድፊያ የቅጣት ውሳኔ መስጠቱ በራሱ የሚያሳየው ነገር እንዳለ አስረድተዋል፡፡
የፓርቲያቸው አባል የተገደለበት ሁኔታ የተቀነባበረና ሊድበሰበስ የማይችል መሆኑን የሚገልጹት ሊቀመንበሩ፣ የወንጀል ሒደቱ በትክክል እንዳልተጣራ ፍርድ ቤቱ እንኳን ከሰጠው ፍርድ መረዳት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡
ሟች አቶ ሳሙኤል አወቀ እነማን እየተከታተሉት እንደሆነ፣ ሊገደል እንደሚችል፣ እሱ ቢሞትም ትግሉ እንደሚቀጥል ጽፎና አሳውቆ መሞቱን የጠቆሙት ኢንጂነር ይልቃል፣ አንድ ሰው የማያውቀውን ሰው ሊገድል እንደማይችል ገልጸዋል፡፡ ‹‹የተፈጸመው ድርጊት ራስን ማታለልና አገርን ማዋረድ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ቤተሰቦቹና ሕዝቡ በጣም ማዘናቸውንም አክለዋል፡፡
ገዳይ ተቀበል ገዱ ወንጀሉን ሲፈጽም የአካባቢው ነዋሪዎች ጮኸው እጅ ከፍንጅ እንደያዙት የገለጹት ደግሞ፣ የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው፡፡
በፖሊስ ተጣርቶና ፍርድ ቤቱ በምስክሮች አረጋግጦ ተገቢ ነው ያለውን ቅጣት መወሰኑን የገለጹት ኃላፊው፣ አንዳንድ ወገኖችና የፓርቲው አመራሮች ግድያውን ከፖለቲካ ጋር ለማገናኘት የሚያደርጉት ጥረት ተገቢነት እንደሌለው አስታውቀዋል፡፡
ጉዳዩን ከምርጫ ጋር ለማያያዝ ቢሞከርም ሁሉም ነገር ከተጠናቀቀ በኋላ የተፈጸመ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ንጉሡ፣ ሰማያዊ ፓርቲ በምርጫው ያጣውን የኅብረተሰቡን ውሳኔ (ድምፅ) ወደጎን በመተው ሰበብ እየፈለገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ሰላማዊውን ሕዝብ ሰላም ለመንሳትና የእርስ በርስ ቅራኔ ለመፍጠር ካልሆነ በስተቀር፣ ወንጀሉን የፈጸመው አካል በምስክር ተረጋግጦበት ቅጣቱን ማግኘቱን አስረድተዋል፡፡ ገዳይ በደብረ ማርቆስ ከተማ ቤት ተከራይቶ የቀን ሥራ በመሥራት ወንድሞቹን እንደሚያስተዳድር አቶ ንጉሡም አረጋግጠዋል፡፡
የደብረ ማርቆስ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው የጽኑ እሥራት ቅጣት ላይ አስተያየት የሰጡ ደግሞ፣ ድርጊቱ በተፈጸመ በ17 ቀናት ውስጥ የቅጣት ውሳኔ መሰጠቱ ጥሩ ቢሆንም፣ ተመሳሳይ ወንጀል ፈጽመው ለዓመታት ውሳኔ ሳይሰጥባቸው በየማረሚያ ቤቱ ያሉትን ተጠርጣሪዎች ሲያስቡ ግን፣ ጥርጣሬ እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል፡፡ አንድ ሰው በወንጀል ተጠርጥሮ ሲታሰር፣ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ ዝቅተኛ የሚጠይቀው የምርመራ ጊዜ 14 ቀናት በተለመደበት ሁኔታ፣ ይኼኛው የክስ ሒደት በ17 ቀናት ውስጥ መፈጸሙ ግራ እንዳጋባቸው ተናግረዋል፡፡ አቶ ንጉሡ ግን ወንጀለኛው እጅ ከፍንጅ የተያዘና ሁሉም ማስረጃ በአንድ ጊዜ በአጭር ቀናት በመሟላቱ፣ ተገቢ ውሳኔ መሰጠቱን ገልጸው አስተያየት ሰጪዎቹን ተቃውመዋል፡፡
ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለመልካም አስተዳደር ዕጦትና ለሙስና ትኩረት እንዲሰጥ ተጠየቀ

ሰሞኑን ለውይይት የቀረበው ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ቢያቅፍም፣ ሙስናና የመልካም አስተዳደር እጦት ሥጋት እንደሆነበት ተገለጸ፡፡
ከአብዛኛዎቹ ተሰብሳቢዎች ጐልተው የተነሱ ነጥቦች ይህንን ግዙፍ ብሔራዊ ዕቅድ ለመተግበር፣ ቅድሚያ የመልካም አስተዳደርና የሙስና ጉዳዮች መፍትሔ ሊያገኙ እንደሚገባ የሚገልጹ ናቸው፡፡
አስተያየት ሰጪዎቹ እንደሚሉት፣ በአዲስ አበባና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች የመልካም አስተዳደር እጦት ተባብሷል፡፡ ሙስና የዕለት ተዕለት ክስተት እየሆነ መምጣቱ በምሬት ተገልጿል፡፡
መንግሥት የቀረፀው የዚህ ግዙፍ ፕሮጀክት ስኬት በቀጥታ ከመልካም አስተዳደር ጋር የሚገናኝ በመሆኑ፣ አገርን በማዳን አስተሳሰብ ላይ የተመሠረተ ዕርምጃ ሊወሰድ ይገባል በማለት አስተያየት የሰጡ በርካታ ናቸው፡፡
ከጥቂት ቀናት በኋላ የሚጠናቀቀው የመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ይዞ መቅረቡ ይታወሳል፡፡
ከእነዚህ መካከል አሥር የስኳር ፕሮጀክቶች፣ ከሁለት ሺሕ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍን አዲስ የባቡር መስመር ግንባታ፣ ታላቁ የህዳሴ ግድብና የማዳበሪያ ፋብሪካዎች ተጠቃሾች ናቸው፡፡
በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እነዚህ ፕሮጀክቶች ተስፋፍተው እንደሚቀጥሉ፣ ቀደም ባለው ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ ያልነበሩ የፔትሮሊየምና የኬሚካል ፋብሪካዎች ይገነባሉ ቢባልም፣ ከመጀመሪያው ዕቅድ ተነጥሎ ሊታሰብ የሚያስችለው ዓይነተኛ መለያ የለውም ተብሏል፡፡
ይህ ሐሳብ ባለፈው ረቡዕና ሐሙስ በአዲስ አበባ ባህልና ቴአትር አዳራሽ በተካሄደው የዕቅድ ሰነድ ውይይት፣ የኢሕአዴግ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት የአንድ ክፍል ኃላፊ የሆኑት አቶ ሴኮቱሬ ጌታቸው በሰጡት አስተያየት፣ የመጀመሪያው ዕቅድ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ይዞ በመቅረቡ ብሔራዊ መነሳሳት ፈጥሯል ብለው፣ የአሁኑ ዕቅድ ፕሮጀክቶችን ቢይዝም ከመጀመሪያው ዕቅድ ጋር በግልጽ የተቀመጠ ልዩነት የለውም በማለት አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
‹‹እኛ የምንከተላቸው ልማታዊ መንግሥታት አንድ ዕቅድ አጠናቀው ሌላ ሲያቅዱ ልዩነቱ በግልጽ ይታያል፤›› በማለት የተናገሩት አቶ ሴኮቱሬ፣ ‹‹እኛም ብሔራዊ መነሳሳት ለመፍጠር ልዩነቱን በግልጽ በማውጣት ብሔራዊ ግብ ልናስቀምጥ ይገባል፤›› ብለዋል፡፡
አቶ ሴኮቱሬ ቢካተቱ ያሏቸውን ሐሳቦችም ሰንዝረዋል፡፡ ከሰነዘሯው ሐሳቦች ብሔራዊ አገልግሎት አንዱ ነው፡፡ ‹‹በወታደራዊው መንግሥት የሥልጣን ዘመን ብሔራዊ ውትድርና መጥፎ ጠባሳ ጥሎ ቢያልፍም፣ በአሁኑ ወቅት በሩቁ ከምንሸሸው በበጐ ጐኑ ልንጠቀምበት ይገባል፤›› ካሉ በኋላ፣ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ለተወሰኑ ጊዜያት ወደመጡበት ኅብረተሰብ ተመልሰው እንዲያገለግሉ ቢደረግ ጥቅሙ የጐላ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ ‹‹ይህ ሁኔታ ኅብረተሰቡን ከመጥቀሙ ባሻገር ተማሪዎቹ ከፍተኛ ዕውቀት የሚያገኙበት ይሆናል፡፡ በአገራቸው እንዲኮሩም ያደርጋል፤›› ብለዋል፡፡
ስብሰባውን ይመሩ የነበሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ለአቶ ሴኮቱሬ አስተያየት ምላሽ ሲሰጡ፣ የብሔራዊ አገልግሎት ጉዳይ እንደ ስትራቴጂ ሊወሰድ ይችላል ብለዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ ይበልጥ በመነጋገር የሚያዋጣውን ማየት ይቻላል ካሉ በኋላ፣ በኢትዮጵያ ይህንን ጉዳይ መተግበር አዋጭ ስለመሆኑ ከባህልና ከታሪክ አንፃር መርመር ያስፈልጋል በማለት አክለዋል፡፡ አቶ ድሪባ ጉዳዩ ከኢሕአዴግ መስመር ጋር ያለውን ልዩነትም አስረድተዋል፡፡
‹‹ኢትዮጵያ የምትከተላቸው ሌሎች አገሮች ልማታዊ መንግሥት ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ግን ልማታዊ ዴሞክራሲን የምትከተል በመሆኑ ጉዳዩን በጥልቀት ማየት ያስፈልጋል፤›› በማለት አቶ ድሪባ ተናግረዋል፡፡
በዕለቱ በተካሄደው ስብሰባ አብዛኛዎቹ ተሰብሳቢዎች በትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ጥልቅ ሐሳቦች ላይ አስተያየት ከመሰንዘር ይልቅ፣ ብዙም ግንኙነት በሌላቸው የዕለት ተዕለት ጉዳዮች ላይ አስተያየት ሲሰጡ ተስተውለዋል፡፡
በዚህ ጉባዔ የአምስት ዓመቱን ዕቅድ ያቀረቡት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ጌታቸው አዳም ሲሆኑ፣ ከአቶ ድሪባ ጋር መድረኩን የመሩት የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው ናቸው፡፡ የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ 192 ገጽ ያለው ሲሆን፣ ለውይይት የቀረበው በ65 ገጽ ተጨምቆ መሆኑን አቶ ጌታቸው ተናግረዋል፡፡
ሚድሮክ ጐልድ ምንም ዓይነት የመንግሥት ዕዳ የለብኝም አለ

–ዋና ኦዲተር ማስተባበያውን አጣጥሎታል
የፌዴራል ዋና ኦዲተር በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ ለፓርላማ ባቀረበው ሪፖርት፣ የማዕድን ሚኒስቴር የሼክ መሐመድ አል አሙዲ የወርቅ ልማት ኩባንያ ከሆነው ሚድሮክ ጐልድ በሕግ የተወሰነውን ገቢ ባለመሰብሰቡ
፣ አገሪቱ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ አጥታለች ማለቱን የኩባንያው ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር አርጋ ይርዳው ‹‹ፍፁም ሀሰት›› ነው ሲሉ አስተባበሉ፡፡ ዋና ኦዲተር ገመቹ ዱቢሶ በበኩላቸው፣ የሚድሮክ ጐልድን ማስተባበያ በማጣጣል ማዕድን ሚኒስቴር ያልሰበሰበውን የመንግሥት ገንዘብ አሁንም ገቢ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል፡፡
በማዕድን አዋጁ 78/2002 መሠረት በከፍተኛ የማዕድን አምራቾች ላይ ስምንት በመቶ የሮያሊቲ ክፍያ፣ እንዲሁም በከፍተኛ የማዕድን አምራች ኩባንያዎች ላይ መንግሥት አምስት በመቶ ነፃ የአክሲዮን ድርሻ እንደሚኖረው ቢደነገግም፣ የማዕድን ሚኒስቴር ከ2004 እስከ 2006 ዓ.ም. ባሉት የበጀት ዓመታት ከሚድሮክ ጐልድ የሰበሰበው የሮያሊቲ ክፍያ አምስት በመቶ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ እንዲሁም ከመንግሥት ነፃ የአክሲዮን ድርሻ ሁለት በመቶ ብቻ መሆኑን በማዕድን ሚኒስቴር ላይ በተካሄደው የክዋኔ ኦዲት ቁጥጥር መረጋገጡን ዋና ኦዲተሩ ለፓርላማ ሪፖርት አድርገዋል፡፡ ፓርላማው ካፀደቀው የሮያሊቲና የመንግሥት ድርሻ ምጣኔ ውጪ ሚኒስቴሩ ሚድሮክ ጐልድን በዝቅተኛ ምጣኔ በማስከፈሉ፣ በድምሩ 429 ሚሊዮን ብር ገቢ መንግሥት ማጣቱን ሪፖርት በማድረግ ማዕድን ሚኒስቴር በአገሪቱ ሕግ መሠረት ገቢዎችን እንዳልሰበሰበ ገልጿል፡፡
ሪፖርተር ይህንን የዋና ኦዲተሩን የኦዲት ሪፖርት መሠረት በማድረግ በሰኔ 17 ቀን 2007 ዓ.ም. ዕትሙ ዘገባ ያቀረበ መሆኑ ይታወሳል፡፡ የሚድሮክ ጐልድ ዋና ሥራ አስኪያጅና የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አረጋ ይርዳው ለሪፖርተር በላኩት ደብዳቤ፣ ‹‹ኩባንያው ሕግን አክብሮ ኃላፊነቱን የሚወጣ ድርጅት ነው፡፡ አሥር ሳንቲም የመንግሥት ዕዳ የለበትም፤›› ብለዋል፡፡
ሚድሮክ ጐልድ የማዕድን አዋጅ ቁጥር 52/1985 መሠረት በማድረግ ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር የ20 ዓመታት የማዕድን ማውጣት ውል መግባቱን፣ በውሉ መሠረትም አምስት በመቶ የሮያሊቲ ክፍያና ሁለት በመቶ ነፃ የአክሲዮን ድርሻ በኩባንያው ላይ እንዲኖረው መደረጉን በደብዳቤያቸው አብራርተዋል፡፡
ውሉ መሠረት ያደረገበት የማዕድን አዋጅ በአዋጅ ቁጥር 678/2002 ተሻሽሎ በሐምሌ ወር 2002 ዓ.ም. ሥራ ላይ መዋሉን የሚያስታውሰው የዶ/ር አረጋ ደብዳቤ፣ በዚህ አዋጅ ላይ የሮያሊቲ ክፍያ ወደ ስምንት በመቶ እንዲያድግ፣ የመንግሥት ነፃ ድርሻ ሁለት በመቶ እንዲሆንና ለወርቅ ማምረት ሥራ የቀረጥ ነፃ መብት እንዳይፈቀድም መከልከሉን ገልጸዋል፡፡ ይህንን አዋጅ መሠረት በማድረግም የማዕድን ሚኒስቴር ለሚድሮክ ጐልድ እ.ኤ.አ. ጃንዋሪ 24 ቀን 2011 ክፍያዎች በአዲሱ አዋጅ መሠረት እንዲከናወኑ ማሳሰቡን ጠቅሰዋል፡፡
ይሁን እንጂ ቀደም ብሎ ለ20 ዓመታት የተገባን የውል ስምምነት አዲሱ አዋጅ ሊቀይር አይገባም በማለት፣ ሚድሮክ ጐልድ ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር ለሦስት ዓመታት የተከራከረ መሆኑንና በመጨረሻም ሚኒስቴሩ በሚድሮክ ጐልድ አቋም መስማማቱን የሚገልጽ ደብዳቤ ጥር 28 ቀን 2005 ዓ.ም. መላኩን ገልጸዋል፡፡ በደብዳቤው መሠረትም ሚድሮክ ጐልድ በገባው ውል መሠረት እንዲቀጥል መደረጉን አስረድተዋል፡፡
ዋናው ኦዲተር ሪፖርቱን ለፓርላማ ከማቅረቡ በፊት ሙያው በሚጠይቀው መሠረት ከማዕድን ሚኒስቴር ወይም ከሚድሮክ ጐልድ ማግኘት የሚችለውን ሰነድ ሳይመረምር የሰጠው መግለጫ፣ በኩባንያው ላይ ተገቢ ያልሆነ ገጽታ እንዲያጠላበት በማድረጉ ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ፣ ‹‹በሚድሮክ ጐልድ ላይ የኦዲት ቁጥጥር አናደርግም፡፡ ቁጥጥር ያደረግነው በማዕድን ሚኒስቴር ላይ ነው፤›› ብለዋል፡፡
ይህ ቢሆንም በኦዲት መርህ መሠረት ተገቢው ምርመራ በሚኒስቴሩ ላይ መደረጉንና ለ20 ዓመታት የተደረገውን ውል መሠረት በማድረግ ተደርጐ የነበረውን ክርክርና የተሰጠውንም እልባት መመርመራቸውን ጠቁመዋል፡፡ ‹‹ነገር ግን ፓርላማው ያወጣውን ሕግ ማዕድን ሚኒስቴር በደብዳቤ ሊቀይረው አይችልም፡፡ ፓርላማው ራሱ በአዋጁ ላይ ማሻሻያ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ኃላፊነት ደግሞ የመንግሥት ተቋማት ሕግን አክብረው መሥራታቸውን ተቆጣጥሮ ለፓርላማው መረጃ ማቅረብ ነው፤›› ብለዋል፡፡ በመሆኑም ማዕድን ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር 678/2002 አንቀጽ 81 ላይ፣ ‹‹ይህ አዋጅ በሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት የተሰጠ ፈቃድ ወይም የተደረገ የማዕድን ስምምነት ከዚህ አዋጅ ጋር እስካልተቃረነ ድረስ ፀንቶ ለሚቆይበት ቀሪ ዘመን ተፈጻሚነቱ ይቀጥላል፤›› የሚለውን አንቀጽ ተላልፏል ብለዋል፡፡
በኦዲቱ ወቅት የሚድሮክን ጥያቄም ሆነ ሚኒስቴሩ የሰጠውን ምላሽ የኦዲት ቡድኑ ማየቱን የገለጹት ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹ፣ ‹‹ተቀባይነት ያለው አሠራር አይደለም፤›› ብለዋል፡፡ በመሆኑም ማዕድን ሚኒስቴር ይህንንና ሌሎች በኦዲት የተለዩ የአሠራር ችግሮቹን ለማስተካከል የድርጊት መርሐ ግብር አውጥቶ ለዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት መላክ የሚኖርበት መሆኑንና መንግሥት ከሚድሮክ ጐልድ ያጣውን ገንዘብ ማስከፈል አለበት በማለት አስታውቀዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፓርላማው በ2006 ዓ.ም. በማዕድን አዋጁ ላይ ባደረገው ማሻሻያ፣ በኢትዮጵያ በከፍተኛ የማዕድን ልማት ብቸኛ የሆነውን ሚድሮክ ጐልድ የመከራከሪያ ነጥብ የተገነዘበ ማስተካከያ አድርጓል፡፡
የማሻሻያ አዋጁ 816/2006 በአንቀጽ 9 ‹‹ይህ አዋጅ በሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት የተሰጠ ወይም የተደረገ ማንኛውም የማዕድን ማምረት ፈቃድ ወይም የማዕድን ማምረት ስምምነት ፀንቶ ለሚቆይበት ቀሪ ዘመን፣ ፈቃዱ በተሰጠበት ወይም ስምምነቱ በተደረገበት ወቅት ተፈጻሚ በነበረው ሕግ መሠረት ባለበት ይቀጥላል፡፡ ሆኖም በፈቃዱ ወይም የስምምነቱ ዘመን አብቅቶ ሲታደስ በዚህ አዋጁ ድንጋጌዎች መሠረት ይፈጸማል፤›› የሚል ማስተካከያ አድርጓል፡፡
የኢትዮጵያ የበካይ ጋዞች ልቀት ወደ 147 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን እንዲቀንስ ይደረጋል ተባለ
የአካባቢና የደን ሚኒስቴር ይፋ ያደረገው ጠቋሚ ዕቅድ የሙቀት አማቂ ወይም በካይ ጋዞች (ግሪን ሐውስ ጋዝ) ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቁበትን መጠን በመቀነስ፣ በመጪዎቹ አምስት ዓመታት ውስጥ 147 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ላይ እንዲገደቡ ለማድረግ ማቀዱን አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ ባለፈው ሐሙስ ሰኔ 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ለውይይት ባቀረበው የአምስት ዓመት ሰነድ ላይ በአገሪቱ ለበካይ ጋዞች ወይም ለሙቀት አማቂ ጋዞች መለቀቅ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ዘርፎች ላይ የሚሠሩ ሥራዎች፣ የልቀት መጠኑን ለመቀነስ እንደሚያስችሉ አመላክቷል፡፡ የአካባቢና ደን ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኑርመደድ ጀማል ባቀረቡት የአምስት ዓመት መነሻ ዕቅድ መሠረት፣ በአገሪቱ ለሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀት አስተዋጽኦ ከሚያደርጉት መካከል የደን መጨፍጨፍ፣ የአፈር መከላትና መሸርሸር፣ የጋማ ከብቶች ሲያመሰኩና እበት ሲጥሉ የሚመነጩ ጋዞች፣ የኢነርጂ ዘርፍና የመጓጓዣ ዘርፍ የሚያመነጩት፣ የኢንዱስትሪና የከተሞች መስፋፋት ከሚጠቀሱት መካከል ናቸው፡፡
በመሆኑም እንስሳት ያመነጩታል ተብሎ የሚጠበቀውን የ88 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ልቀት ወደ 44 ሚሊዮን መቀነስ ከታቀዱት መካከል ይገኝበታል፡፡ በአፈር መከላትና መሸርሸር ምክንያት 40 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ጋዝ ይለቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ በመሆኑ፣ ሚኒስቴሩ ይህንን መጠን ወደ 12 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ዝቅ የማድረግ ዕቅድ አስቀምጧል፡፡
መንግሥት ከአራት ዓመት በፊት በደቡብ አፍሪካ ይፋ ያደረገው የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት የተነሳው ስትራቴጂ አካል የሆነው የመጪዎቹ አምስት ዓመታት ዕቅድ፣ በጠቅላላው በ147 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የበካይ ጋዞችን ልቀት ለመቀነስ ተነስቷል፡፡ የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂው እንዳሰፈረው ከሆነ፣ እ.ኤ.አ. እስከ 2030 ባለው ጊዜ ውስጥ ሊመነጭ ይችላል ተብሎ የሚታሰበው ሙቀት አማቂ ጋዝ መጠን 400 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነው፡፡ ሆኖም ካለፉት አምስት ዓመታት ጀምሮ በየዓመቱ እየመነጨ የሚገኘው በካይ ጋዝ መጠን 150 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን እንደሚገመት አስፍሯል፡፡
አቶ ኑርመደድ እንዳስታወቁት፣ በኢትዮጵያ የሚመነጨው የሙቀት አማቂ ጋዝ መጠን 0.3 በመቶ በመሆኑ ከዓለም አኳያ ያለው ድርሻ ዝቅተኛ ነው፡፡ ይህም ቢባል ግን የአገሪቱን የልቀት መጠን በታቀደው ዝቅተኛ መጠን ለማቆየትና በመጨረሻም ወደ ዜሮ ለማውረድ መንግሥት ያለፉት አምስት ዓመታትን ጨምሮ፣ በሃያ ዓመት ውስጥ 150 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው በአረንጓዴ ስትራቴጂው ማስፈሩ አይዘነጋም፡፡
በሌላ በኩል መንግሥት ለመሠረተ ልማት ግንባታ ብቻ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ 50 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልገው እንደነበር በአረንጓዴ ስትራቴጂ ሰነድ ላይ ያሰፈረ ሲሆን፣ በተጠናቀቀው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱም ጠቅላላ ዕቅዱን ለማስፈጸም ከ75 እስከ 79 ቢሊዮን ዶላር በጅቶ እንደነበርም አይዘነጋም፡፡ በተጠናቀቀው የአምስት ዓመት ዕቅድ ዘመን ውስጥ ከዚህን ያህል ገንዘብ ውስጥ ምን ያህሉ እንደተገኘና ሥራ ላይ እንደዋለ መንግሥት ማብራሪያ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡
ቻይና ኢትዮጵያ ለምትነገባቸው ፕሮጀክቶች ተጨማሪ ፋይናንስ እንደምታቀርብ ይፋ አደረገች
ለሁለት ቀናት በሸራተን አዲስ ሲካሄድ ቆይቶ የተጠናቀቀውን ጉባዔ በማስመልከት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ተጨማሪ ፋይናንስ በማቅረብ ኢትዮጵያ የምትገነባቸውን ፕሮጀክቶች እንደምትደግፍ ቻይና ይፋ አደረገች፡፡
የቻይና ልማት ባንክ የዓለም አቀፍ ኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዳሬክተር ሺ ጂያንግ ከዓለም ባንክ ተጠሪ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ፣ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) ጋር በመሆን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት እንዳስታወቁት፣ ኢትዮጵያ ለምታካሂዳቸው የመሠረተ ልማትና የልማት ፕሮጀክቶች ባንካቸው ተጨማሪ ፈንድ ለመልቀቅ ዝግጁ ነው፡፡
በዚህም መሠረት ለኢንዱስትሪ ዞኖች ግንባታ፣ ለባቡር ትራንስፖርት፣ ለኤሌክትሪክ ኃይል ማሰራጫና ማስተላለፊያ የሚውል ፋይናንስ ለኢትዮጵያ እንደሚቀርብ ጂያንግ አስታውቀዋል፡፡ ጂያንግ ለጋዜጠኞች ሲያብራሩ፣ መንግሥታቸው በአፍሪካ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው አገሮች መካከል ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም በመሆኗ በተለይ ለኢንዱስትሪ ዞኖች ግንባታ የምታውለው ፋይናንስ ከቻይና ልማት ባንክ እንደሚቀርብ ገልጸዋል፡፡
ሊለቀቅ የሚችለው የገንዘብ መጠን ምን ያህል እንደሆነ ከመግለጽ የተቆጠቡት ጂያንግ፣ በተለይ በቅርቡ ፈንድ ሊያገኝ ይችላል ያሉት የኢንዱስትሪ ዞን የትኛው እንደሆነ መግለጽ አልፈለጉም፡፡ ሆኖም በድሬዳዋ የሚገነባው ኢንዱስትሪ ዞን ሊሆን እንደሚችል ፍንጮች ታይተዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በቅርቡ ይፋ የተደረጉ መረጃዎች እንደጠቆሙት፣ በሐዋሳ ለሚገነባው የኢንዱስትሪ ዞን የ250 ሚሊዮን ዶላር ፋይናንስ ከቻይና ተገኝቷል፡፡ በቦሌ ለሚ ለተገነባው የኢንዱስትሪ ዞን የዓለም ባንክ የ250 ሚሊዮን ዶላር ብድር መልቀቁ ይታወሳል፡፡
በርካታ የቻይና ኢንቨስተሮችና ባለሥልጣናት እንዲሁም ምሁራን የተሳተፉበት ጉባዔ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ሲካሄድ፣ ‹‹ኢንቨስት ኢን አፍሪካ ፎረም›› የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ነው፡፡ በየዓመቱ በቋሚነት እንዲካሄድ ስምምነት መደረጉን፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አህመድ ሺዴ አስታውቀዋል፡፡
በሌላ በኩል ቻይና ለአፍሪካ የምትሰጠውን የልማት ፋይናንስ በዚህ ዓመት ወደ አምስት ቢሊዮን ዶላር ማሳደጓን አስታውቃለች፡፡ እስካሁን ለአፍሪካ አገሮች የልማት ድጋፍ በብድር ሲሰጥ የቆየው የገንዘብ መጠን ሦስት ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን፣ በዚህ ዓመት መጨረሻ ወደ አምስት ቢሊዮን ማደጉን ጂያንግ ይፋ አድርገዋል፡፡
በአፍሪካ የቻይና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እያደገ መምጣቱ ቢነገርም፣ ከዚህ ይልቅ ከፍተኛውን ድርሻ የያዘው የንግድ መጠን ነው፡፡ የቻይና ኩባንያዎች በአፍሪካ ኢንቨስት ያደረጉት መጠን ከአራት ቢሊዮን ዶላር እንደማይበልጥ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በአንፃሩ ለቻይና በሚያደላው የንግድ ልውውጥ ከ220 ቢሊዮን ዶላር በላይ ግብይት እንደሚፈጸም የቻይና ልማት ባንክ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በኢትዮጵያ በቀጥታ ኢንቨስት ካደረጉ ኩባንያዎች መካከል ኋጂዬን ግሩፕ፣ ሐንሰም ኢንተርናሽናል ግላስ ኃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ፣ እንዲሁም በቅርቡ ወደ አገር ውስጥ የገባው ጆርጅ ሹ ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች ለሙከራ ኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨስትመንትን እንዴት ልታስተናግድ እንደምትችል ለመገምገም ሲባል የመጡ መሆናቸውን ጂያንግ ገልጸዋል፡፡ በእነዚህ ኩባንያዎች ኢንቨስትመንት ፈተናዎች አጋጥመዋል ያሉት ጂያንግ የጉምሩክ፣ የኃይል አቅርቦት፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ የአስተዳደርና የሰው ኃይል፣ የገበያና የቴክኖሎጂ ችግሮች ማጋጠማቸውን አስታውቀዋል፡፡
አቶ አህመድ ሺዴ በበኩላቸው፣ አገሪቱ ለኢንዱስትሪ መስክ ጀማሪ በመሆኗ ያጋጠሙ ችግሮች እንዳሉ፣ በተለይ በኢንዱስትሪ ዞን ግንባታና አስተዳደር ላይ ከዜሮ በመነሳት ልምድ ለማካበት እየሞከረች መሆኗን ጠቅሰው፣ የቻይና ኢንቨስትሮች መምጣት መጀመራቸውንና ወደፊትም እየተበራከቱ እንደሚመጡ እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ለ40 ዓመታት የራሱ ያደረገው ንብረት ለባለቤቶቹ እንዲመለስ ተወሰነ

በደርግ መንግሥት ከ13 ዓመታት በላይ ታስረው ኢሕአዴግ ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ ሲቆጣጠር በ1983 ዓ.ም. ከእስር የተፈቱት አምባሳደር ታደለች ኃይለ ሚካኤልና ቤተሰቦቻቸው፣ ለ40 ዓመታት በመንግሥት እጅ የነበረን
ንብረታቸውን በፍርድ ቤት ክርክር በመርታታቸው እንዲመለስላቸው ፍርድ ተሰጠ፡፡
በአዋጅ 47/67 ተወርሶ ንብረትነቱ ለመንግሥት እንደተዘዋወረ በመግለጽ፣ የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ በእነአምባሳደር ታደለች የቀረበበትን ክስ ያስተባበለ ቢሆንም፣ ያቀረባቸው ማስረጃዎች ፍርድ ቤቱን ሊያሳምኑ ባለመቻላቸው፣ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 14ኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት፣ ንብረቱን ለከሳሾች እንዲያስረክብና በክስ ሒደቱ ወቅት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ እንዲከፍል ፈርዶበታል፡፡
እነአምባሳደር ታደለች ከሁለት ዓመታት የፍርድ ቤት ክርክር በኋላ አሸናፊ ሆነው ፍርድ ያገኙበት የንብረት ክርክር የጀመረው፣ ደርግ የከተማ ቦታና ትርፍ ቤት አዋጅን ካወጀ ከ1967 ዓ.ም. ጀምሮ፣ በአባታቸው አቶ ዋኬኔ ፊሊጶስ (በኋላ ኃይለ ሚካኤል ፊሊጶስ ተብሏል) ነበር፡፡
የኅብረተሰባዊ ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት በ1967 ዓ.ም. ባወጣው የከተማ ቦታና ትርፍ ቤት አዋጅ ቁጥር 47/67 መሠረት፣ ማንኛውም ትርፍ ቤት ያለው ነዋሪ አንዱን መርጦ እንዲወስድ ሲደረግ፣ አቶ ኃይለ ሚካኤል በአሁኑ አራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ ወደ እሪ በከንቱ መውረጃና ወደ እቴጌ ጣይቱ ሆቴል መታጠፊያ አካባቢ የሚገኘውን ቤታቸውን (የአሁኑ ፓርክ ሆቴልን) ይመርጣሉ፡፡ በወቅቱ ቤቱ ኮሎኔል ሥዩም ኃይሌ የሚባሉ ባለሥልጣን ይኖሩበት ነበር፡፡ ቤቱ በባለሀብቱ የተመረጠ መሆኑ ተገልጾ ለኮሎኔል ሥዩም እንዲለቁ ደብዳቤ ይጻፍላቸዋል፡፡ አቶ ኃይለ ሚካኤል የመረጡት ቤት እስከሚለቀቅላቸው ድረስ፣ 160 ብር እየከፈሉ ተከራይተው ይኖሩበት የነበረው ቤት ኪራይ እንዲቆምም ተደርጓል፡፡ ኪራዩ እንዲቆም የተደረገው በሥራና ቤቶች ሚኒስቴር የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ነው፡፡ ቤቱን የያዙት ኮሎኔል ሥዩም ኃይሌ ግን ቤቱን ሊለቁ ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡
በሌላ በኩል ኮሎኔሉ ቤት አለቅም ቢሉም፣ አቶ ኃይለ ሚካኤል ለጊዜው የሚኖሩበት ቤት ለሌላ ሰው ሊሰጥ መሆኑ ተገልጾ ቤቱን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ይደርሳቸዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ከማስጠንቀቂያው ቀን በኋላ አቶ ኃይለ ሚካኤልን ከቤት አስወጥተው እንዳይጥሏቸው ሲባል በአስቸኳይ ቤት ተፈልጐ እንዲሰጣቸው፣ ለከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ኃላፊ ለነበሩት አቶ ኃይሌ ተድላ ደብዳቤ እንደተጻፈላቸው ለፍርድ ቤቱ በማስረጃነት የቀረቡ ሰነዶች ያስረዳሉ፡፡
ከላይ የተጻፉ ማስረጃዎች በእነአምባሳደር ታደለች በኩል የቀረቡ ሰነዶች መሆናቸውን ፍርድ ቤቱ በፍርዱ ገልጿል፡፡ ፍርድ ቤቱ በደረሰበት ድምዳሜ በ1969 ዓ.ም. እና በ1978 ዓ.ም. የተሰጡ የሰነድ ማስረጃዎች (በተለያዩ የመንግሥት አካላት) የሚያመለክቱት ቤቱ የአቶ ዋኬኔ (ኃይለ ሚካኤል) ፊሊጶስ መሆኑን እንደሆነ ገልጿል፡፡
አቶ ኃይለ ሚካኤል ሕይወታቸው እስካለፈበት 1972 ዓ.ም. ድረስ የመረጡትና እንዲረከቡ የተወሰነላቸውን ቤት ማግኘት አልቻሉም፡፡ እሳቸውን በመተካት ባለቤታቸው ወ/ሮ ብርአልጋ አንብሬ ክርክራቸውን ቀጥለዋል፡፡ ነገር ግን በ1978 ዓ.ም. ደግሞ ቤቱ መኖሪያ ቤት ሳይሆን ድርጅት መሆኑ ተገልጾ፣ ጉዳዩ እስከሚጣራ በሚል ለአቶ ኃይለ ሚካኤል ቤተሰቦች አንድ ቤት ተመርጦ እንዲሰጣቸው ትዕዛዝ ተላለፈ፡፡
ተከሳሽ የሆነው የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ (ኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት) ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 47/67 የተወረሰ መሆኑን የሚያስረዱለትን ማስረጃዎች ማቅረቡንም ፍርዱ ይገልጻል፡፡ በወቅቱ ቤቱ እንዲመለስላቸው ለከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር አቤቱታ አቅርበው፣ በ1982 ዓ.ም. መመለስ እንደማይቻልና ማካካሻ ግምት እንዲሰጣቸው መወሰኑን የሚያሳይ ሰነድ ለፍርድ ቤቱ ማቅረቡንም አስረድተዋል፡፡
ኤጀንሲው ያቀረበው ሰነድ ግን አቶ ኃይለ ሚካኤል ወይም ቤተሰቦቻቸው ያቀረቡት ሰነድ ሳይሆን፣ ቤቱን አለቅ ብለው አሻፈረኝ ያሉት የኮሎኔል ሥዩም መሆኑን እንደሚያስረዳ ፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡
ቤቶች ኤጀንሲ ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 47/67 የተወረሰ መሆኑን የኢትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ሥራ አመራር ቦርድ ማረጋገጡን ገልጾ ሰነድ ያቀረበ ቢሆንም፣ ሰነዱ የሚያስረዳው ግን ስለቤቱ የተነሳው ጉዳይ ለኤጀንሲው ከተሰጠው ሥልጣን ውጪ መሆኑን ጠቅሶ መዝገቡን እንደዘጋው መሆኑን ፍርድ ቤቱ ጠቅሷል፡፡
አዋጅ ቁጥር 47/67 አንቀጽ 16(1) የሚደነግገው፣ በአንድ ከተማ ውስጥ ከአንድ መኖሪያ ቤት ውጪ ትርፍ ቤት ያለው ሰው፣ በራሱ ፍላጐት አንድ መኖሪያ ቤት በመምረጥ መልሶ መረከብ እንደሚችል ነው፡፡ የንግድ ቤት ወይም ከአንድ ቤተሰብ በላይ የሚያስተናግድ መሆኑ በከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር የተረጋገጠ ከሆነ፣ የማይመለስና ማካካሻ የሚሰጥ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ጠቅሷል፡፡
በመሆኑም ቤቶች ኤጀንሲ ቤቱ የንግድ እንደሆነና ከሳሾች ማካካሻ እንዲወስዱ የተከራከረ ቢሆንም፣ ማስረጃ አለማቅረቡን ገልጿል፡፡ በአዋጅ ቁጥር 47/67ም ቤቱን እንደመረጡና ለአቶ ኃይለ ሚካኤል እንደተወሰነላቸው እንጂ፣ ንግድ ቤት ስለመሆኑ ምንም ያለው እንደሌለ አስረድቷል፡፡ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲም ማረጋገጡን አክሏል፡፡ ፍርድ ቤቱ በአጠቃላይ ከሳሾች ካቀረቡት የሰነድ ማስረጃ አኳያ ከሳሾች ቤቱን በውርስ ያገኙት ስለመሆኑ መገንዘቡን አውስቷል፡፡
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 14ኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ሰኔ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. የአቶ ኃይለ ሚካኤል ፊሊጶስ ወራሾች፣ አምባሳደር ታደለች ኃይለ ሚካኤልና አቶ ዓለማየሁ ኃይለ ሚካኤል ንብረቱ ይገባቸዋል የሚል ፍርድ የሰጠው ባደረገው የሰነዶች ምርመራ ነው፡፡
ክሱ በ2005 ዓ.ም. ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍትሐ ብሔር ችሎት ቀርቦ ተከሳሽ የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ፣ ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 47/67 የተወረሰ መሆኑንና ከሳሾች ወራሾች ባልሆኑበት የመንግሥት ንብረት መከራከር እንደማይችሉ ገልጾ ያቀረበውን መከራከሪያ ሰምቶ፣ ሐምሌ 17 ቀን 2005 ዓ.ም. ክሱን ውድቅ አድርጐት ነበር፡፡ በክሱ ላይ ግን ከሳሾች አሁን ፍርድ እንዲያገኙ ያደረጓቸው ሰነዶችን አያይዘው አቅርበው ነበር፡፡
እነአምባሳደር ታደለች ግን ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማለታቸው፣ ፍርድ ቤቱ ሰኔ 17 ቀን 2007 ዓ.ም. ብይን ሰጥቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ብይን እንደገለጸው፣ ከሳሾች ያቀረቧቸው ሰነዶች ቤቱ በአቶ ዋኬኔ (ኃይለ ሚካኤል) ፊሊጶስ ስም ነው፡፡ በመሆኑም ወራሾች የአቶ ዋኬኔ ፊሊጶስ ወራሾች ናቸው፡፡ በመሆኑም ክሱ ውድቅ የሚሆን ባለመሆኑና ብይኑ ግድፈት ያለበት መሆኑን በመጥቀስ፣ የሥር ፍርድ ቤት ወደ ፍሬ ነገሩ በመግባት ሁለቱን ወገኖች አከራክሮ ተገቢውን ውሳኔ እንዲሰጥ በማዘዝ መዝገቡን መመለሱን ሰነዶች ያስረዳሉ፡፡ ክሱ የተመለሰለት የሥር ፍርድ ቤት (አሁን ፍርድ የሰጠው ፍርድ ቤት) አምስት ጭብጦችን ይዟል፡፡ ከሳሾች ባለቤት መሆን አለመሆናቸውን፣ ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 47/67 መወረስ አለመወረሱን፣ ካልተወረሰ ተከሳሽ ለከሳሾች ቤቱን ማስረከብ አለበት የለበትም፣ በኤጀንሲውና ቤቱን በተከራየው ሁለተኛ ተከሳሽ አሁን ቤቱን ፓርክ ሆቴል ብሎ እየሠራበት ያለውና ከኤጀንሲው የተከራየው ነጋዴ መካከል ያለው የኪራይ ውል ካልፈረሰ፣ ቤቱን ለከሳሾች ማስረከብ አለበት የለበትምና ወራሾች የቤቱ ባለቤት ስለመሆናቸው የግድ በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሠረት ማስረዳት አለባቸው የለባቸውም የሚሉ ጭብጦችን በመያዝ፣ ከላይ የተዘረዘሩትን ምርመራዎች በማድረግ ፍርድ መስጠቱን ሰነዶቹ ያብራራሉ፡፡ ኤጀንሲው ቤቱን እንዲያስረክብ፣ የወጪና ኪሳራም ተሰልቶ ሲቀርብ እንዲከፍል ተፈርዶበታል፡፡
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ሐምሌ 04, 2015
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና
የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ሰበካ ጉባኤ: “ለሕይወት የሚያሰጋ የአድማ እንቅስቃሴ እየተደረገብኝ ነው” አለ
በ7 ወራት ውስጥ ከብር 1.5 ሚልዮን በላይ የሙዳይ ምጽዋት ገንዘብ ተመዝብሯል የፓትርያርኩ የኦዲት ክንውን ትእዛዝ “ከቃለ ዐዋዲው ውጭ ነው” በሚል ተጓትቷል “ታማኝ እና ብቁ የኾነ የሰው ኃይል ምደባ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል” (ሰበካ ጉባኤው) (አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፭ ቁጥር ፰፻፯፤ ቅዳሜ ሰኔ ፳፯ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.) የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መቀመጫ የኾነችው የቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ሰበካ …![]()
ተቃዋሚዎች የኦባማን ጉብኝት ተቃወሙት
በኢትዮጵያ ስላለው የመብት ረገጣ 90 ሚሊዮን ህዝብ ምስክር ነው” – ለእድገታችን አሜriካ ምስክር ሆነችልን ማለት ውጤት አያመጣም – ዶ/ር መረራ በአለማቀፍ ታላላቅ የሚዲያ አውታሮች መነጋገሪያ ሆኖ የዘለቀው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን የመጐብኘት ውጥን አሜሪካ አምባገነን መንግስታትን ከመደገፍ የመነጨ በመሆኑ እምብዛም ትኩረት የሚሠጠው ጉዳይ አይደለም ብለዋል – የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፡፡ ዶ/ር መራራ ጉዲና በአዲስ አበባ […]![]()
በኤርትራ ላይ ምርመራው እንዲቀጥል ተወሰነ – ሐምሌ 04, 2015
UN Human rights commission decided in favor of extension of hr investigations in Eritrea 07-03-15
የአሜሪካው ነፃነት በአብዮት ጦርነት – ሐምሌ 04, 2015
American independence and the Revolutionary war 07-03-15
የኢትዮጵያ ፖለቲካና የዘንድሮ ተማሪዎች – ሐምሌ 04, 2015
Ethiopian students in the politics of the day – 07-03-15
ሰበር ዜና አርበኞች ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል በወያኔ ሰራዊት የኃይል ጥቃት ሰነዘረ፥
ሰበር ዜና ================================================ ትናንት ሀሙስ ዕለት ሰኔ 25 2007 ዓ.ም የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት በትግራይ ክልል ቀፍታ መሲል፣ ሆርጃሞ እና ማይሰገል ላይ ህወሓት ከሚቆጣጠረው የ24ኛ ክፍለ ጦር፣ ፌደራል ፖሊስና ልዩ ኃይል ጋር ባደረገው ለአራት ሰዓታት የዘለቀ ከባድ ጦርት ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ፡፡ የአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ተጋዮች በትግራይ ቀፍታ መሲልና ሆርጃሞ ላይ መሽጎ […]![]()
ኢሳት ቴሌቪዥን ስርጭቱን በአዲስ ሳተላይት እንደገና ጀመረ
ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአንድ ወር በላይ ተቋርጦ የነበረው የኢሳት ቴሌቪዥን አገልግሎት በአዲስ ሳተለይት ስራ ጀምሯል። ከኢህአዴግ መንግስት በሚደርስበት ከፍተኛ ጫና የተነሳ ስርጭቱ በተደጋጋሚ ሲቋረጥ የቆየው ኢሳት ቴሌቪዥን ኤ ኤም 44 በሚባል ሳተላይት የቴሌቪዥን ስርጭቱን ከትናንት ሰኔ 25፣ 2007 ዓም ጀምሮ እንደገና ጀምሯል። በአለማቀፍ የፕሬስ ድርጅቶች ሳይቀር ሃሳብን በማፈን የሚወነጀለው …
የጦር መሳሪያቸውን ያስመዘገቡ ሰዎች አስገዳጅ መመሪያ ተላለፈባቸው
ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የኢህአዴግ መንግስት የግል የጦር መሳሪያ የያዙ ዜጎች ህጋዊ ፈቃድ ከመንግስት በመውሰድ፣ የጦር መሳሪያቸውን እንደንብረት እንዲይዙ አዲስ መመሪያ በማውጣት፣ በተለያዩ አካባቢዎች ነዋሪዎች መሳሪያዎቻቸውን እያስመዘገቡ ፈቃድ ውሰደዋል። ይሁን እንጅ ገንዘብ እየከፈሉ ፈቃድ የወሰዱ ባለንብረቶች፣ በራሳቸው ገንዘብ የገዙትን መሳሪያ መሸጥ፣ መለወጥ ወይም ለሌላ ሰው ማውረስ እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል። መሳሪያውን …
መንግስት በተለያዩ የሙያ ትምህርቶች አሰለጥናችሁዋላሁ በማለት የወሰዳቸው ተማሪዎች አብዛኞቹ ተበተኑ
ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአንድ አመት በፊት የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት ወደ ስራ አሰማራችሁዋለሁ በሚል መንግስት ካሰበሰባቸው ከ2 ሺ 500 ያላነሱ ወጣቶች 1 ሺ 500 የሚሆኑት ስልጠናውን አጠናቀው በተለያዩ የመከላከያ ተቋማት ቢመደቡም፣ ቃል የተገባላቸው እና በተግባር የሚያዩት ነገር ባለመጣጣሙ ስራቸውን ጥለው መጥፋታቸውን ሰልጣኖች ተናግረዋል። አሚባራ በሚባለው አካባቢ የሚገኝ ጫካ መንጥረው ህንጻ …
ወጣት ሳሙኤል አወቀን ገድሏል የተባለው ሰው ቃል የግድያውን ድራማ ያመለክታል ተባለ
ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት፣ የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም አደራጅ የሆነውን የወጣት ሳሙኤል አወቀን ገዳይ በ19 አመታት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል። ይሁን እንጅ ገዳይ ተብሎ የቀረበው አቶ ተቀበል ገዱ ለፍርድ ቤት የሰጠው ቃል እና ፖሊስ በወቅቱ የሰጠው መግለጫ ሊጣጣሙ አልቻሉም። ገዳይ ተብሎ የቀረበው ሰው ለፍርድ ቤቱ …
ሜሮን አለማየሁ ተፈረደባት!
ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ሰበብ ታስራ ‹‹ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ በማወክ›› ወንጀል የተከሰሰችው ሜሮን አለማየሁ የ6 ወር እስር ተፈርዶባታል፡፡ ሜሮን አለማየሁ ሚያዝያ 14 በተጠራው ሰልፍ ላይ ‹‹ወያኔ ሌባ፣ መንግስት የለም፣ አትነሳም ወይ፣ የታረደው ወገን ያነተ አይደለም ወይ›› በሚል ሁከትና ብጥብጥ ፈጥራለች …
የኢትዮጵያ የውጭ አገር ሥራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅ ወጣ
ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የውጭ አገር ሥራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅ ስምንተኛ ክፍል ያልደረሰ/ች ሠራተኛ ወደውጭ ሀገር መላክ የሚከለክል ሲሆን በሥራው የሚሰማሩ ኤጀንሲዎች ወደ 2 ሚሊየን ብር ወይም 100 ሺ ዶላር ለዋስትና ማስከበሪያ ካላስያዙ ወደስራ እንዳይገቡ ክልከላ አስቀመጠ፡፡ አሁን በስራ ላይ ያለውን አዋጅቁጥር 632/2001 ሙሉ በሙሉ የሚሰርዘው ይህ ረቂቅ አዋጅ …
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ሐምሌ 03, 2015
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)
በምስራቅ ጎጃም ዞን ከምርጫ ጋር በተያያዘ አርሶ አድሮች እየታሰሩ ነው
ኢሳት ዜና (ሰኔ 26 2007) በቅርቡ በምስራቅ ጎጃም ዞን በወጣት እጩ የፓርላማ ተወዳዳሪ ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ በርካታ ሰዎች በፖለቲካ አመለካከታቸው በመታሰር ላይ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጡ ። በዞኑ የሚገኙ አርሶ አደሮች ከ 15 አምት በፊት ያልከፈላቹት የማዳበሪያ እዳ አለባችሁ እየተባሉ በጅምላ መታሰራቸውን የተናገሩት እማኞች ገበሬዎቹ በሞት የተላዩዋቸውን ዘመዶች እዳ ጭምር እንዲከፍሉ መገደዳቸውም ታውቋል። …
የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች እና ዕረፍታቸው
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 2 ባሉት ቀናት ውስጥ ተሰጥቷል። ከሌላው ክፍል ተማሪዎች ጋር ሲነፃፀር አንድ ወር ግድም ቀድሞው ዕረፍት ላይ የሚገኙት የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወሳጆች በአሁኑ የዕረፍት ጊዜያቸዉ ምን እያደረጉ ይገኛሉ?
በህወሓት መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች መካከል ተፈጥሮ የቆየው መከፋፈል ተካሯል
በህወሓት መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ተፈጥሮ የቆየው መከፋፈል በሁለት ፅንፍ የቆመ ሲሆን አንደኛው ቡድን በኤታማጆር ሹሙ ጀነራል ሳሞራ የኑስ ስር ሁለተኛው ቡድን ደግሞ የምስራቅ ዕዝ አዛዥ ከነበረው ሌ/ጀነራል አብርሃ ወ/ማርያም ጎን የተሰለፉ ናቸው፡፡ ሌ/ጀነራል አብርሃ ወ/ማርምን ከዕዝ አዛዥነቱ አንስቶ ወደ መከላከያ መምሪያ የማዛወሩ የእነ ጀነራል ሳሞራ የኑስ ቡድን ዕቅድ በሌ/ጀነራል አብርሃ ቡድን የበላይነት ሊከሽፍ ችሏል፡፡ ሆኖም […]![]()
ሮን አለማየሁ 6 ወር ተፈረደባት
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ ታስራ ‹‹ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ በማወክ›› የተከሰሰችው ሜሮን አለማየሁ የ6 ወር እስር ተፈረደባት፡፡ ሜሮን አለማየሁ ሚያዝያ 14 በተጠራው ሰልፍ ላይ ‹‹ወያኔ ሌባ፣ መንግስት የለም፣ አትነሳም ወይ፣ የታረደው ወገን ያነተ አይደለም ወይ›› በሚል ሁከትና ብጥብጥ ፈጥራለች ተብላ በተከሰሰችበት በዋስ ወጥታ ጉዳዩን ስትከታተል የቆየች ሲሆን ዛሬ […]![]()
በምስራቅ ጎጃም ዞን አርሶ አደሮች በጅምላ እየታሰሩ ነው ተባለ
ዜጎች በፖለቲካ አመለካከታቸው ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ነው በምስራቅ ጎጃም ዞን አርሶ አደሮች ‹‹የማዳበሪያ ዕዳ አልከፈላችሁም›› በሚል በገፍ እየታሰሩ መሆኑን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ አርሶ አደሮቹ ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ ወስዳችኋል የተባሉትን የማዳበሪያ እዳ እንዲከፍሉ እየተጠየቁ እንደሆነ የገለጹት ምንጮች በአንድ ቀበሌ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች በጅምላ መታሰራቸውን ገልጸዋል፡፡ አርሶ አደሮች እነሱ ወስደውታል የተባለውን ብቻ ሳይሆን በሞት የተለዩትን […]![]()
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ሐምሌ 02, 2015
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት
የሕዝብ አመፅ በትያትር መድረክ
በቀድሞው የራድዮ ጣብያችን መቀመጫ በኮሎኝ ከተማ ለአስር ቀናት የአፍሪቃ ትያትር ፊልም እና ሙዚቃ ትርኢት ተካሂዶአል። ባለፈዉ ሳምንት መጠናቀቅያ ላይ ባበቃዉ በዚህ ትርኢት የአፍሪቃ ሃገራት ፖለቲካዊ ጉዳዮችን የሚያንፀባርቁ አጫጭር ቲያትሮችና የሙዚቃ ድግስ ለታዳሚዉ ቀርበዋል።
ከምርጫ 2007 በሁዋላ በስፖርታዊ ውድድሮች የተለያዩ የተቃውሞ ክስተቶች እየታዩ ነው ተባለ
ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽን በድንገት በተጠራው ስብሰባ ኮሚሽነር ያየህ አዲስ ፣ የብሄራዊ ሊጉ ጨዋታዎች በሚካሄዱበት ከተሞች ከምርጫ 2007 በኋላ የሚታዩ የስፖርታዊ “ጨዋነት ጉድለቶች” አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡ ወቅቱ የምርጫ ውጤት ይፋ የሆነበት በመሆኑ በተለያዩ ስፖርታዊ ጨዋታዎች ላይ ልዩ ጥንቃቄ እንዲደረግም ተናግረዋል። ኮሚሽነር ያየህ ” …