“…የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄውን አልተቀበኩትም::” የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

ምላሹን አልቀበልም በማለቱም በፖስታ ቤት ተልኮለታል ህገ መንግስቱ እውቅና የቸረው ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት ሳይሸራረፍ መተግበሩን እንዲከታተል በአዋጅ የተቋቋመው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ መጋቢት 28/2006 ዓ.ም መነሻውን ፓርቲው ከሚገኝበት ቀበና በማድረግ በአራት ኪሎ አደባባይ በመዞር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ፊት ለፊት የሚጠናቀቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ በመግለጽ ለኦፊሰሩ ደብዳቤ አስገብቶ የነበረ ቢሆንም መስተዳድሩ በአዋጅ የተሰጠውን ጊዜ ገደብ አሳልፎ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ኦፊሰሩ በደብዳቤያቸው ‹‹በርካታ ትምህርት ቤቶች ዩኒቨርስቲና ፣የመንግስት ተቋማት በሚገኙበት አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የማይቻል በመሆኑ የተጠየቀውን የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ጥያቄ ተቀባይነት ያላገኘ መሆኑን እንገልጻለን፡፡››ብሏል፡፡ የአገሪቱ ፓርላማ ‹‹ስለ ሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ስነ ስርዓት ባወጣው አዋጅ ‹‹የከተማው ወይም የአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት ሰላማዊ ሰልፉ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባው ምን ግዜም በየትኛውም ቦታ ሊካሄድ አይችልም ማለት አይችልም››(አዋጅ ቁጥር 3/1983 )በማለት ያወጀውን በአዋጁ ስር የተቋቋመው ጽ/ቤት በማን አለብኝነት በመሻር የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄውን አልተቀበኩትም ብሏል፡፡

አንድነት አዋጁን የጣሰውን ደብዳቤ እንደማይቀበል በመግለጽ ለኦፊሰሩ ደብዳቤ በመጻፍ በአካል ቢሯቸው በመገኘት ለመስጠት ቢሞክርም በአስገራሚ ሁኔታ ኦፊሰሩ ደብዳቤውን አልቀበልም ብለዋል፡፡
የኦፊሰሩ ድርጊት ህገ ወጥ መሆኑን የተገነዘበው ፓርቲያችን ደብዳቤውን ቢሯቸው ጠረጴዛ ላይ ትቶ ከመውጣቱም በላይ በሪኮማንዴ እንዲደርሳቸው አድርጓል፡፡ ኦፊሰሩ እየሰሩ የሚገኙት ነገር ህገ ወጥ መሆኑን እንዲገነዘቡም ለፌደራል ፖሊስ፣ለአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በግልባጭ ደብዳቤው እንዲደርሳቸው መደረጉን የአንድነት የአዲስ አበባ ዋና ጸሐፊ አቶ ነብዩ ባዘዘው ተናግረዋል፡፡ በህገ ወጥ ደብዳቤ የሚሰረዝ ሰላማዊ የህዝብ ጥያቄ ባለመኖሩም ሰላማዊ ሰልፉ በተያዘለት ቀነ ገደብ እንደሚደረግ አቶ ነብዩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ Finotenetsanet
Image

Image

ሺህ ዘመናት በኢትዮጵያዊነቱ የኖረውን የትግራይ ህዝብን፤ከተፈጠረ 40 አመት ያልሞላው ህወሐት እኔ ከሌለሁ ትጠፋላችሁ ይላል፡፡ የትግራይ ተወላጅ ሺህ ዘመናትን የኖረው በኢትዮጵያዊነቱ እንጂ በህወሐት አባልነቱ አይደለም፡፡ ዘረኝነት ባታራምዱ የተሻለ ነው የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቶች የትግራይ ተወላጆች ሳይሆኑ / ሕወሓት/ ነው፡፤ ዋናው ትግላችንም ሕወሓትን ማስወገድ ነው። እናንተ የትግራይ ህዝብ ላይ አተኩራችሁ አቃቂር ስታወጡ ሕወሓት እናንተን እንደማስረጃ እየተቀሰ በትግራይ ውስጥ ጥላቻን እየዘራ ነው። ስለዚህ ዘር እየጠሩ ዘመቻ አያዛልቅም ለህዝቦች አንድነት እና ፍቅር ተባብረን ብንነሳ መልካም ነው።

በቅኝ አገዛዝ ታሪክ ብቻ ሳይሆን በአምባገነን ስር አት ውስጥም ባንዳዎች ይፈለፈላሉ ። ይህ የታወቀ ነገር ንው። ውዴታዊ ባንዳነት እንዳለ ሁሉ ግዴታዊ ባንዳነት ከዛ መላመድም እንዳለ ታሪክ ስናገላብጥ አንብበናል። ቢሆንም መልካም የህዝቦችን ታሪክ እየያዝን ለክፉው ታሪክ መቃብር እየማስን እየቀበርን በትግል ወደፊት በመገስገስ በኢትዮጵያ ላይ የተጫነውን የሕወሓት አምባገነናዊ ጁንታ መንግለን መጣል አለብን ።

እደግመዋለሁ !!! ሺህ ዘመናት በኢትዮጵያዊነቱ የኖረውን የትግራይ ህዝብን፤ከተፈጠረ 40 አመት ያልሞላው ህወሐት እኔ ከሌለሁ ትጠፋላችሁ ይላል፡፡ የትግራይ ተወላጅ ሺህ ዘመናትን የኖረው በኢትዮጵያዊነቱ እንጂ በህወሐት አባልነቱ አይደለም፡፡ ድርጅት ይወልዳል ያድጋል ይሞታል፣ህዝብ ግን ለዘላልም ይኖራል፡፡ ፍቅር ያሸንፋል!!!ምንሊክ ሳልሳዊ

ያኔ-ከ21ዱ የወታደራዊ ሁንታዉ አባላት ሁሉ ወጣት ነበሩ።ያን ሚስጥር-በመናገራቸዉ የካይሮ ሠልፈኞችን በቁጣ፤ የመብት በተለይም የሴቶች መብት ተሟጋቾችን በዉግዘት ከማንጫጫቱ ባለፍ፤ ድምፀ ለሥላሳዉ ወጣት ጄኔራል የሚፈልጉትን ለማደረግ-የፖለቲካዉን ትኩሳት የለኩበት መግለጫ መሆኑን ያሰበ-ያስተዋል አልነበረም።

‪በደሴ ከተማ የሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ለማስተባበር ወደ ስፍራው የተጓዙት የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ቀጠና ኃላፊ አቶ አዕምሮ አወቀ ድብደባና ዝርፊያ እንደተፈፀመባቸው ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡ ዓርብ መጋቢት 19 ቀን 2006 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡15 ላይ በደሴ ከተማ በተለምዶ ቶታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዕራት በልተው ሲወጡ ታርጋ የሌለውና መስታወቱ ጥቁር በሆነ ኮብራ መኪና አጠገባቸው መጥቶ ሲቆም ከውጪ ሁለት ሰዎች […]

በርካታ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የርቀት ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በ2005 ዓም ትምህርታቸውን ቢጨርሱም፣ ጊዚያዊ ዲግሪያቸውን ፣ ማለትም የዲግሪያቸውን ቅጂ ባለማግኘታቸው በስራ ፍለጋ ጥረታቸው ላይ እክል እንደደቀነባቸው በምሬት ገልጸዋል።

የጀርመን የልማት ትብብር ሚንስትር ጌርድ ሚውለር ሰሞኑን ደቡብ ሱዳንን እና ማሊን ጎብኝተውዋል። ሚንስትሩ ወደ ሁለቱ ሀገራት የተጓዙት በቦታው በመገኘት በዚያ ስላለው የመሠረተ ልማት ግንባታ፣

የአንድነት ፓርቲ መጋቢት 28 ቀን ሰልፍ እንደሚያደርግ፣ ለአዲስ አበባ አስተዳደር መጋቢት 15 ቀን ያሳዉቃል። «የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስብሰባና የሰላማዊ ሰልፍ አሰራር ሥነ-ሥርዓት በርካታ ትምህርት ቤቶች ዩኒቨርሲና የመንግስት ተቋማት በሚገኙበት አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የማይቻል በመሆኑ የተጠየቀዉን የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ጥያቄ ተቀባይነት ያላገኘ መሆኑን እንገልጻለን» ሲል አስተዳደሩ ከ48 ሰዓታት በኋላ መጋቢት 17 ቀን ምላሽ ይሰጣል። […]

ትናንት እሁድ መጋቢት 21, 2006 ዓም ዓረና ከእንደርታ ህዝብ ጋር ለመወያየት በኲሓ ከተማ ሐየሎም አዳራሽ ቀጠሮ መያዙ ይታወሳል። ለስብሰባው በስፒከር ለመቀስቀስ ሞክረን እንደተከለከልን፣ የአመራር አባሎቻችንም መታሰራቸው እንደዉጤቱም የቅስቀሳ ሂደቱ መተጓጎሉ ጠቅሼ ነበር። ሁኖም ግን የዓረና አማራጭ ሐሳብ የያዘ በራሪ ወረቀት ለኗሪዎች በማደል የተወሰነ ቅስቀሳ አድርገናል። ከሌሎች አከባቢዎች ለየት ባለ መልኩ በእንደርታ ወረዳ በስፒከር እንዳንቀሰቅስ የተፈለገበት […]

ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅሬታቸውን ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች ገልጸዋል የቤተ ክርስቲያንን እንጀራ እየበሉና በጀቷን አውጥታ እያስተማረቻቸው የሌላ እምነት በሚያራምዱ የስም ደቀ መዛሙርት ላይ ርምጃ እንዲወሰድ ተጠየቀ (አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፫ ቁጥር ፯፻፵፩፤ መጋቢት ፳ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.) የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ የኾኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን እምነትና ሥርዐት እንዲማሩ፣ ዕውቀታቸውንና ገንዘባቸውን በማቀናጀት ሞያዊ ድጋፍ …

በሀገራችን የኑሮ ውድነት ከእለት እለት እየከፋ የድሃውን ህዝብ ጉስቁልና እያበዛ እንደሆነ ነጋሪ የሚያስፈልግ አይመስለኝም፡፡ በቤተ መንግሰትና አካባቢ የሚኖሩት ይህ ጉዳይ አይመለከታቸውም፡፡ ለዚህ የኑሮ ውድነት አንዱ እና ዋነኛው ምክንያት የዋጋ ንረት መሆኑን ብዙዎች ይረዳሉ የሚል እምነት አለኝ፡፡ ዛሬ ለፅሁፌ ዋና ማጠንጠኛም የማደርገው የዋጋ ንረት ምንስዔው ምን እንደሆነ በተለይ የመንግሰት ሚና ከዚህ አንፃር ምን እንደሆነ ማስረዳት ነው፡፡ […]

በዛሬው እለት በቦስተን በተደረገው “የሕሊና እስረኛ አንዱአለም አራጌ የውደሳ እና የምስጋና ቀን” በርካታ ኢትዮጵያውያኖች በተገኙበት በደማቅ እና እጅግ በተሳካ ሁኔታ ተክናውኗል። በዚሁ ዝግጀት ላይ የሕሊና እስረኛ አንዱአለም አራጌ የሕይወት ታሪክ እና በኢትዮጵያ ውስጥ የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመፍጠር በሚደረገው የሰላማዊ ትግል ያደረገውን አስተዋጻኦ በተመለከተ የተዘጋጀ ዶክመንተሪ ፊልም የቀርበ ሲሆን፤ በወጣት ማሙሽ እና በወ/ሮ ደብረወርቅ የተዘጋጁ ጽሁፍ እና […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

መብራት ውሃ የስልክና የኢንተርኔት ኔትወርክ አገልግሎቶች መብቶች የህዝብ ናቸው!!!!! አቤቱታችን ከፖለቲካ ነጻነት እና ዲሞክራሲያዊነት ጎን ለጎን የመሰረታዊ አገልግሎቶች ጥያቄ ነው …ይህ ደሞ ለየት ባለ መልኩ አብዮታዊ ነው::እኛ በሰው አገር የምንኖር ዲያስፖራዎች በወገናችን ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ ከማውራት እና መኖሪያ ፍቃዳችን ሲታደስ ከመቀዝቀዝ ዉጪ በወያኔ ላይ የምናሳድረው ጫና እምብዛም ጉልፍ ስፍራ የለውም:: እርስ በርሳቸው የሚላተሙ የጆተኒ ተቃዋሚ […]

የደቡብ ሱዳን ጦርነት አዲሲቱን ሐገር እያነደደ ደሐ ሕዝቧን እየፈጀ-በገፍ እያሰደደ ነዉ።ተፋላሚ ሐይላት በምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን ( ኢጋድ ) ሸምጋይነት የተኩስ አቁም ሥምምነት ቢፈራረሙም ሥምምነቱ ገቢራዊ አልሆነም።

የአንድነት ፓርቲ ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድ የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው። በኢትዮጵያ የፌዴራልም ሆነ የክልል ባለስልጣናት የተለያዩ ሕጎችን ደንቦች ሊያወጡ ይችላሉ። ነገር ግን ሕገ መንግስቱ የሕጎች ሁሉ የበላይ ነው። በሕገ መንግስቱ የተቀመጡ መሰረታዊ የሕግ አንቀጾችን ማንኛዉም አካል ሊሽረው ወይንም ሊቀለብሰው አይችልም።የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት አንቀጽ 30 ዜጎች ነፍጥ ሳይዙ የመሰባሰብ፣ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች የማድረግ፣ ፔትሽኖችን የማሰባሰብ ሙሉ መብት […]

(ፋክት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፴፱፤ መጋቢት ፳፻፮ ዓ.ም.) ተመስገን ደሳለኝ በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም አዝማችነት በማኅበሩ ላይ የደቦ ዘመቻ ከተከፈተ ሰነባብቷል፡፡ በጥናት ስም በተከታታይ የሚወጡና በየመድረኩ የሚቀርቡ ወረቀቶች ማኅበሩን የኦርቶዶክስ አክራሪ ከማለት አሻግረው ‹‹የግንቦት ሰባት መንፈሳዊ ክንፍ/የግንቦት ሰባት ከበሮ መቺ/›› ሲሉ ይወነጅሉታል፡፡ የማኅበሩ አመራሮች እንዲኽ ዓይነቱን ውንጀላ በተመለከተ በተለያየ ጊዜ ከአቶ …

ኢህአዴግ የእምነት ተቋማትን በጥብቅ የሚቆጣጠርበት ህግ ሊያጸድቅ ነው።
ህጉ ጣጣ እንዳያመጣ የሰጉ ኢህአዴግን እየመከሩ ነው። ጎልጉል

ኢትዮጵያን ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ እየገዛ ያለው ኢህአዴግ የሃይማኖት ተቋማትንና ምዕመናኑን በጥብቅ የሚቆጣጠርበትን ህግ ለማጽደቅ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰማ። የህጉ ረቂቅ የደረሳቸው ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ኢህአዴግን አበክረው እየመከሩና በሚያመጣው አጠቃላይ መዘዝ ዙሪያ እያስጠነቀቁ ነው።

ጎልጉል ከዲፕሎማት ምንጮቹ ባገኘው መረጃ መሰረት ኢህአዴግ በእምነት ተቋማት ላይ ቁጥጥሩን የሚያጠብቅበትንና ከሃይማኖት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውጭ መሰብሰብን፣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግንና የተቃውሞ ድምጽ ማሰማትን የሚከለክል ህግ አዘጋጅቷል።

የዜናው ምንጮች ዝርዝር ህጉን ለጊዜው ይፋ ከማድረግ እንደሚቆጠቡ አስታውቀዋል። ይሁን እንጂ የሚደነገገውን አዲስ ህግ ጥሰዋል በሚል የሚከሰሱ ምዕመኖች እስከ እድሜ ልክ በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ የሚያዝ አንቀጽ አለበት። አዲሱ ህግ ከሽብርተኞች ህግ ጋር የሚጣቀስ እንደሆነም የጠቆሙት ክፍሎች ኢህአዴግ “ከእምነት ነጻነት” ጥያቄ ጋር በተያያዘና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ውስጥ ውስጡን እየነደደ ያለው ችግር ስላስጨነቀው ይህንን ህግ ለማውጣት መገደዱን አስረድተዋል። በሌላ በኩልም እስካሁን መፍትሔ ያላገኘው የሙስሊሞች ጥያቄ ከዚያም ጋር ተከትሎ የተከሰተው ደም መፋሰስ ወደፊት ሊያመጣ በሚችለው ጉዳይ ላይ ኢህአዴግን በብርቱ አሳስቦታል፡፡

ኢህአዴግ ከቀን ወደ ቀን ቀውስ እየተደራረበት እንደሆነ የተረዳችው አሜሪካ በከፍተኛ ባለስልጣኖቿ አማካይነት ኢህአዴግን እየመከረች እንደሆነ ከዲፕሎማቶች የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ከፖለቲካው ቀውስና በቀጠናው ካለው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ አሜሪካ በተደጋጋሚ የህወሃትን ሰዎች በተናጠል እያነጋገረች እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል። ዲፕሎማቶቹ እንደሚሉት አሜሪካ መለስ “ከተሰዉ” በኋላ አገሪቱን ማን እየመራት እንደሆነ በቅጡ ለመረዳት በሚያስቸግር ሁኔታ የስልጣን መዛነፍና ደረጃን የጠበቀ የስልጣን ተዋረድ አለመኖሩም አሳስቧታል። ኢህአዴግ ለህልውናዬ ያሰጋኛል በሚል መንግሥታዊ ባልሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች /መያዶች/ ላይ ያወጣውን አፋኝ ህግም ጠቅሰዋል። ዲፕሎማቶቹ በጉዳዩ ዙሪያ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ወቅቱ አሁን እንዳልሆነ አመልክተዋል። ጎልጉል

የበደለ፣ የአገር ሀብት ያባከነ፣ ሕገ የረገጠ ግለሰብ ማጥፋቱ እየታወቀ ይቀጣል ወይስ አይቀጣም ለሚለው ጥያቄ ወሳኙ ማስረጃ መሆኑ እየቀረ ነው፡፡ የፖለቲካ ገጠመኝ ሆኗል፡፡ ይታሰራል የተባለው ሊሾም፣ ተጠያቂ ይሆናል የተባለው ጠያቂ የሚሆንበት ሁኔታ አለ፡፡

መልካም አስተዳደር በሕግና በመርህ ደረጃ መከበር አለበት ተብሎ የታወጀ፣ የተነገረ፣ የተለፈፈለት ነው፡፡ በተግባር ደግሞ አቤት ብዬ ሰሚ አገኛለሁ፣ ቅሬታ አቅርቤ ይፈታልኛል የሚል ዜጋ የለም!!!! በዚህ ዙሪያም ጉቦና ጥቅማ ጥቅም የበላይነት እየያዙ ነው፡፡ የአቅም ማነስ ችግር ትልቅ እንቅፋት ነው፡፡ ስብሰባዎችና ሥልጠናዎች የችግር መፍቻ መድረኮች መሆናቸው ቀርቶ መደበቂያ እየሆኑ ነው፡፡ ‹‹በስብሰባና በሥልጠና ምክንያት ኃላፊ የለም›› የሚል ማስታወቂያ መለጠፍ ነው የቀረው፡፡ ኃላፊ ቢሮው ገብቶ አቤቱታ አንብቦ ችግር መፍታት መርህና ግዴታው መሆኑ ቀርቶ የፖለቲካ ገጠመኝ እየሆነ ነው፡፡

የሕግ የበላይነት እንዲኖር፣ ሰብዓዊ መብት እንዲከበር፣ የፕሬስ ነፃነት እንዲረጋገጥ፣ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን እንዲሆን የሚያደርጉ ሕገ መንግሥትና ሕጎች አሉን ????????? ከድህነት የሚያላቅቅ፣ መካከለኛ ገቢ ወዳላት አገር የሚያሸጋግር፣ የቤት፣ የጤና፣ የትምህርት፣ የትራንስፖርት፣ ወዘተ ችግሮችን የሚፈታ ዕቅድም አለን ???????????

እነዚህ አሉ ማለት ግን ዲሞክራሲ ተረጋገጠ፣ ልማት እውን ሆነ ማለት አይደለም፡፡ በመርህ ደረጃ ተግባር ላይ ካዋልናቸው ይጠቅማሉ፡፡ ካላከበርናቸው፣ ከረገጥናቸውና ከጣልናቸው ደግሞ ገጠመኝ ይሆናሉ፡፡ ፍትሕ ገጠመኝ እየሆነ ነው፡፡ምንሊክሳልሳዊ የፍትሕ መጓደል በሚያሳስብ ሁኔታ እየታየ ነው፡፡ በፍትሕ አካላት ውስጥ በአቅምና በአመለካከት ድክመት አለ፡፡ የሥነ ምግባር ጉድለት በትልቁ እየታየ ነው፡፡ በጠበቆች፣ በዳኞችና በዓቃቢያነ ሕግ በኩል አሳሳቢ የሥነ ምግባርና የአቅም ችግር እየተስተዋለ ነው፡፡

በአጠቃላይ የፍትሕ አካላት መጠናከር እያሳዩ ከመጓዝ ይልቅ እየተልፈሰፈሱና እየተንገዳገዱ ናቸው፡፡ በዚህ ምክንያት ፍትሕ ማግኘት መርህ መሆኑ ቀርቶ ገጠመኝ እየሆነ ነው፡፡ ጉቦ የአንቀጾች ሁሉ የበላይ አንቀጽ እየሆነ መጥቷል፡፡ሰላማችን፣ ሉዓላዊነታችን፣ አንድነታችንና ህልውናችን በመርህ ደረጃ ዋስትና ያላቸው መሆናቸው ቀርቶ የፖለቲካ ገጠመኝ ሆነዋል፡፡ የአገር እና የህዝብ ህልውና ገጠመኝ በመሆኑ ወያነ ደግሞ የዛፍ ላይ እንቅልፍ ተኝቷል፡፡ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በጋራ የዛፍ ላይ እንቅልፉን የሚለጥጠውን ወያነን በማውረድ ህዝባዊ የበላይነትን መቀናጀት የዜግነት ግደታችንን መወጣት አለብን::ምንሊክሳልሳዊ

መብራት ውሃ የስልክና የኢንተርኔት ኔትወርክ አገልግሎቶች መብቶች የህዝብ ናቸው!!!!!
ምንሊክ ሳልሳዊ

Image

አቤቱታችን ከፖለቲካ ነጻነት እና ዲሞክራሲያዊነት ጎን ለጎን የመሰረታዊ አገልግሎቶች ጥያቄ ነው …ይህ ደሞ ለየት ባለ መልኩ አብዮታዊ ነው::እኛ በሰው አገር የምንኖር ዲያስፖራዎች በወገናችን ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ ከማውራት እና መኖሪያ ፍቃዳችን ሲታደስ ከመቀዝቀዝ ዉጪ በወያኔ ላይ የምናሳድረው ጫና እምብዛም ጉልፍ ስፍራ የለውም:: እርስ በርሳቸው የሚላተሙ የጆተኒ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች በላም አለኝ ተስፋ ህዝባችንን አረንቋ ውስጥ እየጨመሩት ነው::

ለጋች አገራት የሚያወጧቸው ሃሰተኛ ጸረ አፍሪካ ሪፖርቶች በተለይ የምስራቅ አፍሪካን ተገን አድርጎ የተመቻቸው የብሄራዊ ጥቅማቸው ፎርሙላ ስኬት የአምባገነኖችን እድሜ በማስረዘም ህዝብ እንዲጭበረበር የህዝብ ጥያቄዎች እንዲደናቀፉ ለገዢዎቻችን የልብ ልብ ሰቷቸዋል:: ለብሄራዊ ጥቅም አስጊ ይሆናሉ የተባሉ የፖለቲካ ድርጅቶችን እስከማጨማደድ እየዘለቀ በኢጅ አዙህ ህዝባዊ ጥያቄዎች እንዲታፈኑ እየተደረገ አምባገነናዊ አገዛዝን አፍልተውብናል እንሱ ለጋሽ አገራት::

መሰረታዊ ፍላጎቶች እና የአገልግሎት ፍጆታችን በበቂ ሁኔታ ባልተሟላበት አገር መንግስት ፕሮጀክት ለመጨረስ የገንዘብ እጥረት ገጠመኝ በሚልበት አገር ብሄራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሬ የለኝም በሚልበት እና የመንግስት ካዝና ባዶ ሆኖ በዕቃ ግምጃ ቤት ሰነድ ጨረታ ከቱጃሮች መንግስት በሚበደርባት አገር ጥቂት ፖለቲካው የወለዳቸው ሃብታሞች እጅግ ብዙ የኢኮኖሚ ድቀት ያፈራቸው ደሃዎች በፈሉበት አገር ምን አይነት የኢኮኖሚ እድገት እንደተመዘገበ አነጋጋሪ ነው:; እስከመቼ የአምባገነኖችን ደጋፊዎች ዉሸት ተሸክመን እንዘልቃለን::

መብራት ውሃ ስልክ ሀገሪቷ ተሰርቶ እና ተበድራ ሳይሆን በተፈጥሮ የታደለችው ጸጋዋ እንደሆነም ያለን ሃብት ይመሰክራል ህዝቡ ያለውን ቴክኖሎጂ ከተፈጥሮ ሃብቱ ጋር አደባልቆ እንዳይጠቀም እኛ እናውቅላቹዋለን የሚሉ የወያኔ አውሬዎች ቀፍድደው ይዘውታል::
በቀላል ሊፈታ የሚችል ችግርን በፖለቲካዋ ሳንካ መተብተብ ምንም የሚጠቅም ስላልሆነ ህዝቡ አስፈላጊውን የአገልግሎቶች አቅርቦት እንዲያገኝ መደረግ አለበት ብለን ካሁን በፊት ብንጮህም ከቀድሞ በባሰ መልኩ ብሶበት ይገኛል::

በአለማችን በረሃ በተባሉት አገሮች የውሃ አቅርቦት በሰፊው ለህዝባቸው እየሰጡ ሲሆን የተጣሩ ውሃዎች ሳይቀር በርካሽ ዋጋ እየተሸጡ ነው::በኢትዮጵያችን ግን በተፈጥሮ የታደልነውን ውሃ በፖለቲካ ሹማምንት ልፍስፍስነት ልንጠቀምበት አልቻልንም ትልልቅ እና ገባር እንዲሁም ትንንሽ ወንዞች እና የተፈጥሮ ውሃ ምንጮች በሞሉባት ሃገራችን ህዝብ ውሃ ተጠማሁ ሲል መመልከት አስደንጋጭ ነው::ሃገሪቱ በውሃ ችግር ተውጣልች::የውሃ እጥረት ኖሮን ሳይሆን በአግባቡ አለመጠቀም እና ችግሩን የመፍታት ባህል ስላሌለን ነው::ለጎረቤት አገሮች ውሃ እንሰጣለን እየተባለ ባለበት የፕሮፓጋንዳ ጡዘት ውስጥ እኛ በጥማት ማለቃችን አሳፋሪ ነው::

ወድ መብራት ስንመጣ ደሞ መንግስት ያለ እንኳን ተደርጎ ማሰብ ይከብዳል:: የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ መብራት ጠፍቶ ሲመጣ መብራት መጣ ብሎ መጮህ ነው ተብሎ በሰው ሃገር ጋዜጦች እስኪቀለድብን ድረስ ወያኔ በህዝብ ጭንቅላት ጢባጢቦ እየተጫወተች ነው::ይህ እንደገጠመኝ እና እድል የሚታየው የመብራት እቃቃ ጨዋታ በአግባቡ መፍታት እየተቻለ ችግሩንም ማድረቅ እየተቻለ ለምን መዘናጋት እንደሚፈጠር ማስረዳት የሚችል ባለስልጣን አልተገኘም::በኤሌክትሪክ መጥፋትና ሥርዓት አልበኝነት ምክንያት በርካታ ኢንዱስትሪዎች ሥራቸውን እያቆሙ ናቸው፡፡ በርካታ ማሽኖች ከጥቅም ውጭ እየሆኑ ናቸው፡፡ በመኖሪያ ቤቶች ቴሌቪዥኖች፣ ፍሪጆችና ሌሎች የኤሌክትሪክ ዕቃዎች እየፈነዱና እየተቃጠሉ ነው፡፡ በመብራት መጥፋት ምክንያትም የየዕለቱ ኑሮ ይዘቱም ገጽታውም እየተበላሸ ነው፡፡ ከመኖሪያ ቤቶች አልፎ ካፌዎችም በመብራት መጥፋት ምክንያት ‹‹ተረኛ መድኃኒት ቤት›› እየመሰሉ ነው፡፡ ሻይ ታዞ ‹‹ይቅርታ መብራት የለም›› የሚል መልስ መስማት የተለመደ እየሆነ ነው፡፡ እውነት ኢትዮጵያ ለዜጎቿ፣ ለኢንዱስትሪዎቿም ሆነ ለሁሉም ዓይነት እንቅስቃሴዎቿ የሚሆን በቂ የኤሌክትሪክ ኃይል የላትም? አይኖራትም? አላትም ይኖራታልም፡፡ በቂ የውኃ ኃይል ማመንጫዎች የንፋስ የኃይል ማመንጫዎች የፀሐይ የኃይል ማመንጫ አቅም የጂኦ ተርማል የኃይል ማመንጫ አቅምም አለ፡፡ እንኳን ለራስዋ ለሌሎች አገሮችም የሚሆን የኤሌክትሪክ አቅርቦት ዕምቅ ሀብት አላት፡፡ ኦኖም ግን በአግባቡ የሚያዳርስ እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች አጣብቂኝ ውስጥ ስለከተቷት ህዝቧ አስፈላጊውን የአገልግሎት መብቶች እና አቅርቦቶች ሊያገኝ አልቻለም::በሃይል ግንባታ ሰበብ በህዝብ ላይ መንግስታዊ አሻጥር እየተፈፀመ ነው::ምንሊክ ሳልሳዊ

ወደ ስልክ እና ኢንተርኔት ኔትወርክ ስንመጣ በጸሎች የሚገኝ ያውም ተለቅሶ መፍትሄም የጠፋለት ጉዳይ ከሆነ ቆይቷል:: በአለማችን በስፋት ይህን የኔትዎርክ ችግር ተቀርፎ ባለበት ሰአት የወያኔ ባለስልጣናት ግን በአደናባሪዎቻቸው በኩል በፋይበር ቅንጠሳ እና በህንጻ መብዛት ቢያሳስቡም ከነሱ ቀድሞ ንቃተ ህሊናው ያደገውን ህዝብ ግን ሊሸውዱት አልቻሉም:: ያው እንደለመዱት በጠበንጃ እና ሽብር በመንዛት ዝም አሰኝተውታል:: የወያኔ መንግስት የህዝብን የአገልግሎት አቅርቦት ጥያቄዎች መፍታት እየቻለ እንዳይፈቱ በማድረግ በሚፈጸም አሻጥር እራሱ አጣብቂኝ ውስጥ እንደገባ ሊገነዘበው አልደፈረም:: የመልካም አስተዳደር ብልሃት የሞላበት አመራር ህግ አክባሪ እና አስከባሪ ባለስልጣንትን ለማግኘት ሁላችንም በትግሉ ላይ እንረባረብ።ምንሊክ ሳልሳዊ

March 29, 2014 የጎሠኛነት አጭር ትርጉም ዓለምን በራሱ ጠባብ ኢምንትነት የሚለካ ሰው ነው፤ ለኪው መለኪያው ነው፤ መለኪያውም ለኪው ነው፤ ጎሠኛነት የዘረኛነት የባሕርይ ልጅ ነው፤ ዘረኛነትም ሆነ ጎሠኛነት መሠረታቸው ድንቁርና ነው፤ የድንቁርናው ዓይነተኛ መገለጫ ‹‹ንጹሕ›› የሚለው ቃል ነው፤ ለዚህ ዋና ምስክር አድርጌ የማቀርበው አዶልፍ ሂትለርን ነው፤ ስለ‹‹አርያን ዘር›› ማንነትና ‹‹ንጹሕነት›› የሂትለር Mien Kampf የሚለውን መጽሐፍ ነው፤ […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት የሚመራው የመንግሥቱ ጦር እና የቀድሞው ምክትል ፕሬዚደንት ሪየክ ማቸርን በሚደግፉት ታጣቂ ኃይላት መካከል በሚካሄደው ውጊያ ሰበብ ሀገሪቱ ለምትገኝበት ውዝግብ መፍትሔ ለማፈላለግ የተጀመረው ጥረት ችግር እንደገጠመው ይገኛል።

አምስት የአንድነት ፓርቲ አባላት ታስረዋል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ መጋቢት 20 ቀን 2006 ዓ.ም. March 29, 2014)፦ ዛሬ ገዥው ፓርቲ በጎንደር ከተማ አደባባይ እየሱስ በጠራው ስብሰባ ለእያንዳንዳቸው ተሰብሳቢዎች 8ሺህ ብር ብድር በመስጠት መጭውን ምርጫ ግን ኢህአዲግን እንዲመርጡ በመቀስቀስ ላይ ባለበት ወቅት ምርጫን በገንዘብ መግዛት አይቻልም ብለው ጥያቄ ያቀረቡ አምስት የአንድነት ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን አቶ ሃብታሙ አያሌው ዛሬ ይፋ አደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሁሉንም ተቃዋሚ እንደአንድ መመልከትም ሆነ በአንድ አዕምሮ እንዲያስብ መጠበቅ የገዢው፣ የተገዢዎች፣ የተቃዋሚዎች ሁሉ የጋራ ችግር ነው። ሚሊዮን ችግሮች እና ሚሊዮን ተቃዋሚዎች ባሉበት አገር ውስጥ ተቃዋሚዎች ሁሉ አንድ ዓይነት ሊሆኑ አይችሉም። ይሁን እንጂ ሁሉም ተቃዋሚዎች ልዩነታቸውን በቅጡ ያውቃሉ ብሎ ለማለትም ያስቸግራል፤ ምክንያቱም “በስመ ተቃዋሚ ሲሳሳሙ” ማየት የተለመደ ነው። ተቃዋሚዎችን በተቃውሞ አካሔዳቸው መግባባት ላይ መድረስ እንዲያቅታቸው ከሚያደርጋቸው ችግር አንዱ ኢሕአዴግን የሚበይኑበት (define የሚያደርጉበት) መንገድ መለያየቱ ወይም ግልጽነት ማጣቱ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው።

ብያኔ ለምን ያስፈልጋል?

40 ዓመት ወደኋላ መለስ ብለን የአብዮቱን ልጆች ለመከፋፈል እና ለእርስበርስ እልቂት የዳረጋቸው ዋነኛውን፣ የሚታገሉትን አካል (ደርግን) የበየኑበት መንገድ ነው። የኢሕአፓ እና የመኢሶን ዋነኛ ልዩነት፣ የኢሕአፓና አንጃ እያለ የሚጠራቸው አባላቱ መካከል የተከሰተው የሐሳብ መሰነጣጠቅ፣ ብሎም እርስበርስ መጨራረስ ደርግን የሚበይኑበት መንገድ መለያየትን ተከትሎ የተወለደው ደርግን ለማስወገድ የመረጡት መንገድ ነው። ሁለቱ (የተቀናቃኝ ወገን ብያኔ እና የመቀናቀኛ መንገድ ምርጫ) ተሰናስለው የሚኖሩ ጉዳዮች ናቸው። በጥንቃቄ ሳይጤን የሚገበቡበት ገደል አይደለም።

ኢሕአዴግ፣ በዚህ ረገድ ራሱን ግልጽ የማድረግ ችግር የለበትም። ተቀናቃኞቹን አንዱን አሸባሪ፣ አንዱን የአሸባሪ ደጋፊ፣ ሌላውን ለዘብተኛ እያለ የሚኮረኩምበትን መንገድ አስቀምጧል። ኢሕአዴግ መሣሪያ ታጣቂ እንደመሆኑ ተቀናቃኞቹን ባይበይናቸውም ቅሉ ማሽመድመጃ መንገድ አይቸግረውም። ለተቃዋሚዎች ግን ‘ኢሕአዴግ ምንድን ነው?’ የሚለውን ጥያቄ መመለስ የሕልውና ጉዳይ ብቻም ሳይሆን ወዴት እና እንዴት እየሄደ እንደሆነ የሚያውቁበት ወሳኝ ጥያቄ ነው።

የበኩር ጥያቄ፤ ኢሕአዴግ ምን ያስባል?

ኢሕአዴግ እንደማንኛውም ገዢ ፓርቲ በፖለቲካዊ ብልጫ ሥልጣን ላይ የቆየ ፓርቲ ነው? በኃይል ሥልጣን ተቆጣጥሮ የሚኖር ፓርቲ ነው? እያጭበረበረ የሚኖር ፓርቲ ነው? በኃይል ሥልጣን ተቆጣጥሮ ሕጋዊ ዕውቅና አግኝቶ በሕጋዊ መንገድ ሥልጣን ላይ የቆየ ፓርቲ ነው? ሕዝባዊ ይሁንታ ባገኘ መንገድ ሥልጣን ላይ ከወጣ በኋላ ኃይሉን መከታ በማድረግ ሥልጣኑን ያለመጋራት የተቆጣጠረ ፓርቲ ነው? በኃይል ሥልጣን ተቆጣጥሮ በኃይል ሥልጣኑን እያስጠበቀ ያለ ፓርቲ ነው? ወይስ ምንድን ነው?…ብዙ ዓይነት ትርጉሞች (ሁሉም እውነት ያላቸውን) ማስቀመጥ ይቻላል። የራስንና አንድ ወጥ ትርጉም ማስቀመጥ የሚበጀው የሚከተሉትን የትግል ስልት ለማወቅ እና የሚጠብቁትንም (what to expect) ለማወቅ ነው።

በአማራጭ ፓርቲዎች መካከል እና ለዴሞክራሲያዊነት  በሚደረጉ ነጻ (የአራማጆች እና የሲቪል ማኅበረሰብ) ትግሎች ምን ዓይነት መሆን አለባቸው የሚለውን መወሰን የሚቻለው የሚታገሉለትን ነገር በማወቅ (ለምሳሌ ለዴሞክራሲ በዴሞክራሲያዊ መንገድ) ከሚለው በተጨማሪ ተቀናቃኝ አካላትን በሚገባ በማወቅና በመበየንም ጭምር ነው። የኢሕአዴግን ማንነትም በቅጡ መበየን የሚያስፈልገው አላስፈላጊ ጊዜ፣ ገንዘብና ጥረት ላለማባከን እና የጠበቁትን ውጤት ለማግኘት ነው።

‘ኢሕአዴግ ሥልጣኑን በኃይል ተቆጣጥሮ በኃይል እያስጠበቀ ያለ ድርጅት ነው’ ብለን ካልን ሠላማዊ ትግል የሚባለው ሁሉ ትርጉም ላይኖረው ይችላል። ግን ይህንን ለማለት የሚያስችል በቂ መረጃ አለ ወይ? ኢሕአዴግ ብረት ታጣቂውን ደርግ ለመገርሰስ ከኃይል ውጪ አማራጭ ነበረው? የሥልጣን ባለቤት ከሆነ በኋላ ሥልጣኑን ያላስረከበው በፓርቲው እምቢተኝነት [ብቻ] ነው ወይስ የተቀናቃኞቹም እጅ (ድክመት) አለበት? ኢሕአዴግን ከኃይል መለስ ባለ ነገር ከሥልጣን ለማውረድ የሚያስችሉት በሮች ሁሉ ተዘግተዋል? ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን አባላት ያሉትን ፓርቲ ‘ጠላት’ ብሎ ለመፈረጅ የሚያስችል ሁኔታ አለ? ይህ መሰሉ ድምዳሜ እና ፍረጃ በታሪክ ከተሠሩ ስህተቶች አንፃር ምን ያክል የተማረ/የታረመ ነው?

‘ኢሕአዴግ በኃይል ያገኘውን ሥልጣን በሕዝባዊ ይሁንታ (እንበል ምርጫ) ቀጥሎበታል’ ካልን ደግሞ ለስርዓት ለውጥ የሚደረጉ ትግሎች ፍፁም ሠላማዊና ግልጽ መሆን ይኖርባቸዋል ማለት ነው። ይህም እልፍ ጥያቄዎችን ይወልዳል። ኢትዮጵያ ውስጥ በምርጫ እውን የሥልጣን ርክክብ ማድረግ ይቻላል? ከምርጫ ውጪ የሥልጣን ሽግግር የሚመጣባቸው ሌሎች መንገዶች አሉ? ኢሕአዴግ ሕዝባዊ ይሁንታ ካለው ትግሉ (ለውጡ) ለምንድን ነው? በሠላማዊ መንገድ የሚመጣው ለውጥ ምን ዓይነት ነው?… ወዘተ።

እነዚህን ሁለት ጥያቄዎች እንደምሳሌነት ብንወስድም፣ ሌሎችም ጥያቄዎች በተለያዩ ብያኔዎች ላይ ተመሥርቶ ማውጣት ይቻላል። በምሳሌው ውስጥ የተካተቱትን ሁለት ብያኔዎች ተንተርሶም፥ ሁለቱን ብያኔዎች የሚሰጡ አካላት አብረው ሊሠሩባቸው የሚችሏቸው እና የማይችሏቸውን ጉዳዮች አብጠርጥሮ ማውጣትም ያስፈልጋል እንጂ በብያኔ ተለያይተናልና አብረን የምንሠራበት መንገድ የለም ማለት ላይሆን ይችላል። ይህን ባለማወቅ የሚደረግ ትግል ግን መነሻውንም፣ መድረሻውንም የማያውቅ ተራ ጥላቻ የሚመራው ጉዞ ነው።

መበየን ቀላልም፣ ከባድም፤ ትንሽም፣ ብዙም ነው

ኢሕአዴግን የተለያዩ አካላት የተለያየ ብያኔ ይሰጡታል። ኢሕአዴግ ኢትዮጵያዊ (ብሔራዊ) ስሜት የለውም ከሚሉት ጀምሮ ለኢትዮጵያ የመጨረሻው የመድኅን ስጦታ ነው እስከሚሉት ጽንፎች ድረስ የሚደርስ ብያኔዎች አሉት።

እኔ በግሌ ኢሕአዴግ በተለያዩ ሒደቶች ውስጥ የተለያየ ምልከታዎችን በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ እያጎለበተ የመጣ ቡድን ነው ብዬ አምናለሁ። ፕሮፌሰር ክላፋም እንዳሉት፥ ‘ሕወሓት በብሔር ዓይን ኢትዮጵያን እየተመለከተ መጥቶ ገዢ ሆነ፤ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ደግሞ ኢትዮጵያን ወክሎ (በኢትዮጵያዊ ዓይን) ኤርትራን ጦርነት ገጠመ፤ ይህም ሁለተኛ ዕይታ ሰጠው’። ምናልባት እዚህ’ጋ መጨመር ቢያስፈልግ ሕወሓት (የጠቅላላው ኢሕአዴግ ዕጣ ፈንታ ወሳኝ እንደመሆኑ) ከምርጫ 97 በኋላ ኢትዮጵያዊ (ኅብረብሔራዊ) ስሜት ማዳበር ባይችል እንኳን ያለሱ ብዙ እርምጃ መጓዝ እንደማይችል ተረድቷል። ስለዚህ ኢሕአዴግ በሦስት ደረጃዎች ውስጥ አልፎ እዚህ ደርሷል ባይ ነኝ፤ ሁሉንም ነገር በዘውግ-ብሔር ዓይን የሚመለከትበትና የሚተረጉምበት ደረጃ (አንድ)፣ ኢትዮጵያዊ ኅብረብሔርተኝነትን ለአጀንዳ ማስፈፀሚያነት (ለምሳሌ ለጦር መቀስቀሻነት) የሚያውልበት ደረጃ (ሁለት)፣ እና ያለኢትዮጵያዊ ኅብረብሔራዊ ስሜት እና መሰል እርምጃዎች (ምሳሌ የባንዲራ ቀን) መራመድ እንደማይችል የተረዳበት ደረጃ (ሦስት) ናቸው። ይሁን እንጂ የዘውግብሔርተኝነትን እና ሕብረብሔርተኝነትን ሚዛን የሚያስጠብቅበት ግልጽ አካሔድ የለውም፤ ይልቁንም እንደ ሕዝባዊው ስሜት አነፋፈስ ተስማምቶ ለመንፈስ ብቻ እየተፍጨረጨረ ነው።

ኢሕአዴግን ከላይ ልበይነው የሞከርኩት በኢተዮጵያዊነት ስሜቱ ነው። በተመሳሳይ መንገድ ሥልጣን ላይ ያለውን አመለካከትም በአካሔዱ ለመተርጎም ብሞክርም በርግጠኝነት ልበይነው አልቻልኩም። ኢሕአዴግ ከስኒ ማዕበል በላይ አቅም የሌላቸውን ተቃዋሚዎች ይቀበላል። ከዚያ በላይ ያሉትን ግን በቀና ልቦና እንደሚቀበል አላሳየም፤ ሆኖም በሙሉ አቅም ተፈትኗል ማለትም አይቻልም። የደኅንነት፣ የኮሙኒኬሽን እና የመከላከያውን ቁልፍ ሚናዎች በሕወሓት ቁጥጥር ስር እንዲውሉ እንዲሁም ኢኮኖሚው በመንግሥት ከፍተኛ ቁጥጥር ስር ማድረጉም ሥልጣኑን በሠላማዊ መንገድ ለመልቀቅ ያለውን ዝግጁነት አጠራጣሪ ያደርገዋል። ይሁን እንጂ እስከመጨረሻው ድረስ ተገፍቶ ያልተሞከረ በመሆኑ ለሠላማዊ ትግል በር ተዘግቷል ሊባል በማይቻል መወላወል ውስጥ አስቁሞናል።

ብያኔ ቸኩለው የሚገቡበት ጉዳይ አይደለም። ርዕሱን ከብዙ ገጾች ማየት ያስፈልጋል። ነገር ግን ያለብያኔ ቋሚ አቅጣጫ መያዝ አይቻልም፤ ባይሆን ብያኔንም አቅጣጫንም በየጊዜው መከለስ ያዋጣል።

እውነቱን ለመናገር በኢትዮጵያ ፖለቲካ ምክንያት እንደሰሞኑን በግኜ የማውቅ ኣይመስለኝም። ኣቤት ክህደታችን! እንዴት ተክነንበታልሳ ወገኖች! ረጋ ብላችሁ በጥሞና ኣንድታነቡኝ ብርታቱን ይስጣችሁ፥ 1• በዛሬይቱ ኢትዮጵያችን ነባራዊ ሁኔታ ብሄር ማለት ምን ማለት እንደሆነ በትክክል የሚነግራችሁ ሰው ኣታገኙም። የብሄር ፖለቲካ ኣቀንቃኞቹ ራሳቸው የሚግባቡበት ወጥ የሆነ የብሄር ትርጉም እንኳን የላቸውም። ብሄር ለኣንዳንዱ በቋንቋ ነው የሚገለፀው፤ ለሌላው በዘርና ትውልድ ሃረግ ነው […]

ሥርዐቱ በተለይም መንግሥታዊ ሥልጣናቸውን ለሃይማኖታዊ ተልእኮ የሚጠቀሙ ሓላፊዎችና አማሳኝ የደኅንነት ግለሰቦች አሁን በተያዘው መንገድ ቀጥለው ማኅበረ ቅዱሳንን አላግባብ ወደ መገዳደር ብሎም ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አማሳኝ ግለሰብ ሓላፊዎች ጋራ ተባብረው ወደ ማፍረስ የሚሸጋገሩ ከኾነ ያለምንም ጥርጥር የተቃውሞው ጎራ ይጠናከራል፡፡ ይህም አገሪቱን በልማታዊ ዴሞክራሲያዊ የአውራ ፓርቲ ሥርዐት ለአርባና ኃምሳ ዓመታት እመራለው ለሚለው ገዥው ፓርቲ ግብዓተ መሬት አፋጣኝ …


(ደጀ ሰላም፣ መጋቢት 20/2006 ዓ.ም፤ ማርች 29/2014/ PDF)፦ ሥርዓተ ቅዳሴውን ለመምራት  ተሰይመው ለተመለከታቸው ከረጅሙ ነጭ ጽህማቸው  ጋር ውብ  የሆነውን  መረዋ  ድምጽ ሲሰማ ምድራዊ  ሳይሆን  ከሰማይ የተገለጠ መልአክ ይመስሉ ነበር፡፡ ለስብከተ ወንጌል አገልግሎት የተለየ ፍቅር ስለነበራቸው በተጋበዙበት መድረክ ሁሉ አክብረው በሰዓቱ ይገኛሉ፡፡ ለማስተማር ከተነሱም በትርጋሜ  የተዋዛ  ምስር አዘል ትምህርታቸውን ለምእመናን ቀምመው ያቀርባሉ፡፡ ለሃይማኖት ያላቸውን ቀናዊነት ለመረዳት በትምህርታቸው መግቢያ  የሚናገሩትን  መልእክት መስማት ብቻ በቂ ነው፡፡ ይህ የመግቢያ መልእክታቸው ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ልተበረዘች ያልተከለሰች  መሆን የሚስረዱበት በተለያዩ ዘመናት የተነሱባትን መናፍቃን በመጥቀስ እነዚህ ሁሉ ያልበረዛት ያልከለሳት መሆናን የሚገልጹበት ነው፡፡ እናም በጥዑም አንደበታቸው ስለቤተ ክርስቲያን ሲናገሩ ለሰማቸው  የሊቃውንቱ ዘመን የእነ እትናቴዎስ ዘመን የሃይማኖት ቅናት በውስጣቸው እንዳለ ይረዳል፡፡ ብፁዕ አቡነ ቶማስ፡፡

በደብረ ሊባኖስ ገዳም መጻሕፍተ ሊቃውንትን ረዘም ላለ ጊዜ  በማስተማር  ቆይተው ነው  ወደ አዲስ አበባ የተዛወሩት፡፡ በገዳሙ ውስጥ ሲኖሩ የነበራቸውን መንፈሳዊ ሕይወት እና አንድምታውን የማስተማር ብቃት በወቅቱ የነበሩ አባቶች የሚመሰክሩት በታላቅ አድናቆት ነው፡፡ ሊቅነትን  ከመንፈሳዊነት   ጋር ይዘው በመገኘታቸውም ቤተ ክርስቲያን ለበለጠው አላፊነት አጭታ ለጵጵስና ማዕረግ በቅተዋል፡፡ መናፍቃንን  በተመለከተ ግልጽ የሆነ ቀጥ  ያለ አቃም ነበራቸው፡፡ፀረ  ማርያም  የሆነን  የተሐድሶ ጭፍራ መታገሥ አይችሉም፡፡ በቅዱስ ውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የነበረውን የተሐድሶ እንቅስቃሴ ሥሩን ነቅለው የጣሉበት የዲንነት ዘመናቸው ለዚህ ምስክር ነው፡፡ እንደእነ ቅዱስ ቄርሎስ የመናፍቃን መቀጥቀጫ መዶሻ ነበሩ፡፡ ላ ይህ ቀናነታቸው እና  አድርባይ ሊሆኑ ያለመቻላቸው ጉዳይ  በቤተ ክህነቱ ውስጥ በተሰገሰጉ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ስላልተወደደላቸው እንዲጠሉና እንዲገለሉ አድርቸዋል፡፡ ፓትርያክ አቡነ ጳውሎስ  ምርጥ ምርጡን ለወዳጆቼ በሚሉበት እንዳሻቸው ሃገረ ስብከት በሚያድሉበትም ዘመን አቃማቸውን ብዙም ስሎማይወዱላቸው ጠረፋማ ሥፍራዎች  ላይ እንዲመደቡ ሆነዋል፡፡ለነገሩ ብፁዕ አቡነ ቶማስ ስለሚመደቡበት ሃገረ ስብከት ብዙም የሚጨነቁ  ስላልሆኑ ወደተላኩበት ሁሉ በደስታ  ይሄዳሉ፡፡ ፍሬም ያፈራሉ፡ቤተ ክርስቲያን የሰው ያለህ በምትልበት በዚህ ወቅት እንዲህ ያለ አባት ማጣት ትልቅ ሀዘን ነው፡፡ ብፁዕነታቸው ወደ አገለገሉት አምልክ በክብር ቢሄዱም እኛ ግን በትልቁ ተጎድተናል፡፡
ወቅቱ በአጠገባችን ያሉ ጥቂት መንፈሳዊ አባቶችን በስስት የምንመለከትብት ነው፡፡አይቴ ሀለ ቀደምት ጳጳሳት የቀደሙ አባቶች ደጋጎቹ ሊቃነ ጳጳሳት ወዴት አሉ?” እያልን ዘመን ገድባቸው የተለዩንን በሀዘንና በቁጭት የምናስታውስበት ነው፡፡ በግል ቂምና በቀል ተ ክርስቲያንን ለመናፍቃን አሳልፈው የማይሰጡ፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን የሚገባቸውን መከራ ሁሉ በጥብዓት የሚቀበሉ፣ ከአላውያን ነገሥታት እምነት የለሽ መንግሥታት ጋር የማይዛመዱ፣ በፍልስፍናና በምድራዊ ተድላ ተይዘው  በእምነት ጉዳይ  ቸልተኛ ያሆኑ፣ መስሎ ለማደር ሲሉ ከቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ጋር የማይተባበሩበሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ የታሪክ ጠባሳ ለትውልዱ ላለመተው የሚጠነቀቁእኔ ካልተነካ ሕዝቡም ሆነ አገልጋዩ ያሻውን መከራ ቢቀበል ምን አግብቶኝ ሲሉ የማይገኙ አባቶችን ተጠምተናል፡፡
እንደ ሙሴ ሕዝብህ ከሚጠፋ እኔን ከይወት መጽሐፍ ደምስስ የሚሉ፣ እንደ ነ  ኤልያስ  ስለ እግዚብሔር ክብር የሚቀኑ፣ እንደ ነዩ ዳዊት የተቀመጡበት ዙፋን የሚኖሩት የተድላ ኑሮ የተነሱበትን የማያዘናጋቸውበመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ላፊያትና መጻዕያትን የሚረዱ፣ ሳይነገራቸው የመናፍቃንና የአላውያን ነገሥታት የጥፋት አካሄድ የሚገባቸው፡፡ እንደ ነቢዩ ኢሳይያስ እግዚአብሔር በክብሩ ዙፋን ተቀምጦ የሚታያቸው፣ ከምድራዊ ነገሥታት ከመዘመድ ይልቅ አደራውን ለሰጣቸው ለሰማዩ  ንጉሥ  መታዘዝ እንደሚበልጥ የሚረዱ፡፡ እንደ ሐዋርያት እስከ ሞት የሚታመኑ፡፡ እንደ ሊቃውንት መናፍቃንን የሚገስጹ አልመለስ ያሉትንም የሚያወግዙ አባቶችን ተጠምተናል፡፡
የቤተ ክርስቲያን አምክ ነገን እንደ አትናቴዎስ ያለ አትናቴዎስ፣ አባ ጊርጊስ ዘጋስጫን የሚተካ ሌላ አባ ጊርጊስ  እንዲተካ አጥብቀን  እንለምነው፡፡ ለእርሱ ምን ይሳነዋል? ይህ ሁሉ ወጀብ አልፎ ደግ ዘመን ያመጣልን ይሆናል፡፡ ለሁሉም በሕይወት ያሉትን  ለተዋሕዶ ጠበቃና አርበኛ የሆኑ አባቶች ድሜ ያርዝምልን፡፡ ያረፉትን አባቶች በረከትም በያለንበት ያድለን፡፡ አሜን፡፡                                                                                                                        ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን።  ቸር ወሬ ያሰማን።
Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

በቅ/ሲኖዶሱ በይፋ ከተወገዙና በኑፋቄ አራማጅነት ከሚጠረጠሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ጋራ ግንኙነት ያላቸውና በኅቡእ በሚንቀሳቀሱ ጥቂት ተማሪዎች የሚራመድ ነው ‹‹ችግሩን በዝምታ ለመመልከት ኅሊናችም ሃይማኖታችንም አይፈቅድልንም›› /ብዙኃኑ ደቀ መዛሙርትና የደቀ መዛሙርት ምክር ቤት አባላት ለእምነትና ሥርዓት የሚቆረቆሩ መምህራንና ተማሪዎች ‹ማኅበረ ቅዱሳንና ፖሊቲከኞች ናችኹ› በሚል እንዲሸማቀቁ ይደረጋሉ (ዕንቊ፤ ቅጽ ፮ ቁጥር ፻፲፬፤ መጋቢት ፳፻፮ ዓ.ም.) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን …

Image

የጋምቤላ ክልልን ሲመሩ ቆይተው ባለመስማማት የኮበለሉት የቀድሞው የክልሉ ፕሬዚዳንት ደቡብ ሱዳን ከሆቴል ውስጥ ታፍነው መወሰዳቸው ተጠቆመ። ዜናው በገለልተኛ ወገን ባይገለጽም ኖርዌይ በስደት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይኖሩ የነበሩት አቶ ኦኬሎ አኳይ በኢህአዴግ በጥብቅ የሚፈለጉ ሰው ነበሩ።

በመለስ ዜናዊ ውሳኔ በአኙዋክ ተወላጆች ላይ በጅምላ የተከናወነውን ጭፍጨፋ አስመልከቶ ተቃውሞ በማሰማት የኮበለሉት አቶ ኦኬሎ ወደ ደቡብ ሱዳን ከማምራታቸው በፊት ኬንያ እንደነበሩ፣ ከኬንያ ወደ ደቡብ ሱዳን ለምን እንደተጓዙ የዜናው ምንጮች በይፋ ከመናገር ተቆጥበዋል። ስማቸው እንዲደበቅላቸው የጠየቁ የጋምቤላ አስተዳደር ባልደረባ ለጎልጉል የአካባቢው ዘጋቢ እንደተናገሩት አቶ ኦኬሎ ደቡብ ሱዳን ሆቴል በተቀመጡበት መታፈናቸውን አረጋግጠዋል።

“ወያኔ እጅ ገብቷል” ሲሉ ያከሉት እኚሁ ሰው “አቶ ኦኬሎ ብረት በማንሳት ወያኔን ለመታገል ከተነሱ ጋር ተቀላቅለዋል በሚል ስማቸው መመዝገቡንና ወደ ደቡብ ሱዳን ማቅናታቸው በመታወቁ ህወሃቶች እጅ ሊወድቁ ችለዋል” ብለዋል። ምንጩ ይህንን ይበሉ እንጂ አቶ ኦኬሎ አክዋይ ወደ ደቡብ ሱዳን ያቀኑበትን ምክንያት በርግጠኛነት ሃላፊነት ወስዶ የገለጸ ወገን አልተደመጠም። ኢህአዴግም ቢሆን የቀድሞውን ሹመኛ ስለመያዙ ይፋ ያደረገው ነገር የለም። ከደቡብ ሱዳን ቀውስ ጋር በተያያዘ የኑዌር ተወላጅ ከሆኑት ሬክ ማቻር ጦር ጋር በመሰለፍ የሳልቫ ኪርን ሃይል ሲወጉ ከተገደሉ ወታደሮች መካከል የኢህአዴግን ሰራዊት መለያ የለበሱ ኑዌሮች መገኘታቸው ውዝግብ አስነስቶ እንደነበር ያመለከቱት ምንጭ “ደቡብ ሱዳን እየወጋት ካለው ኢህአዴግ ጋር አብራ የቀድሞውን የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳደር ከምድሯ ላይ እንዲታፈኑ መፍቀዷ ቅሬታ ያስነሳል” ብለዋል።

ከቤተሰባቸው ተነጥለው በስደት ከሚኖሩበት ኖርዌይ ወደ ደቡብ ሱዳን ያመሩት የቀድሞው የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳድር ደቡብ ሱዳን በህወሃት ሙሉ ቁጥጥርና ፈቃድ የምትንቀሳቀስ አገር መሆኗን እያወቁ ወደዛ ማቅናታቸውን ባሥልጣኑ “ታላቅ ጥፋት” ብለውታል። ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። በቅርቡ አቶ ኦሞት ኦባንግ መኮብለላቸውና በብዙዎች ዘንድ አውሮጳ እንዳሉ ቢነገርም በትክክል ያሉበት አገር በይፋ አለመታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።
goolgule.com/

የአንድነት ፓርቲ ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድ የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው። በኢትዮጵያ የፌዴራልም ሆነ የክልል ባለስልጣናት የተለያዩ ሕጎችን ደንቦች ሊያወጡ ይችላሉ። ነገር ግን ሕገ መንግስቱ የሕጎች ሁሉ የበላይ ነው። በሕገ መንግስቱ የተቀመጡ መሰረታዊ የሕግ አንቀጾችን ማንኛዉም አካል ሊሽረው ወይንም ሊቀለብሰው አይችልም። የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት አንቀጽ 30 ዜጎች ነፍጥ ሳይዙ የመሰባሰብ፣ ሕዝባዊ ሰላምዊ ሰልፎች የማድረግ፣ ፔትሽኖችን የማሰባሰብ ሙሉ […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ድርጅቱ እንደሚለው በዚሁ ዓመት በዓለማችን በአጠቃላይ 778 ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል ። በድርጅቱ መግለጫ መሠረት በይፋ ከተፈፀሙ ከእነዚህ ቅጣቶች በተጨማሪ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቻይና በድብቅ በሞት ተቀጥተዋል ።

የወጣቶቹ አላማ ጧሪ የሌላቸውን፣ ከጎዳና ላይ የተነሱ አረጋውያንንና የአዕምሮ ህሙማንን መርዳት ነው። ለዚህ ደግሞ 65 በጎ ፍቃደኞች አዲስ አበባ የሚገኘው «ሜቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከልን ተቀላቅለዋል።ሶስቱን አነጋግረናቸዋል።

ስብሓት የንግግራቸው መነሻ ያደረጓቸውና ወጣት ሲሉ የጠሯቸው መነኩሴ ማን ናቸው?

Image

‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የሚያስተኛ አይደለም›› /አቶ ስብሓት ነጋ/
(ኢትዮ-ምኅዳር ቅጽ 01 ቁጥር 34፤ ረቡዕ ነሐሴ ፳፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋራ በመተባበር በአዲስ አበባ በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ ከነሐሴ ፳፩ – ፳፪ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ‹‹የሃይማኖቶች በሰላም አብሮ የመኖር እሴት በማጎልበትና ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን በማክበር የሀገራችንን የሕዳሴ ጉዞ ለማሳካት እንረባረባለን›› በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ጉባኤ ላይ ‹አቦይ› ስብሐት ነጋ በመገኘት አነጋጋሪ ሐሳቦችን ሰንዝረዋል፡፡ አንጋፋው የህወሓት/ኢሕአዴግ መሥራችና የጀርባ ሰው የሚገልጹት ሐሳብ የመንግሥትን ቀጣይ ርምጃ ያመላክታል በሚል በአጭሩ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

አክራሪነት ይዘቱ ሃይማኖታዊ እንዳልኾነ ሕዝቡም የተገነዘበው ጉዳይ መኾኑ ተደጋግሞ ተገልጧል፡፡ ሃይማኖትን የፖሊቲካ መድረክ የሚያደርጉት የሽብርተኝነት ተግባር ለመፈጸም መኾኑ ግልጽ የኾነልን ይመስለኛል፡፡

አክራሪነትና ጽንፈኝነት በሃይማኖት ውስጥ ማስገባት የመጀመሪያው አደጋ ሲኾን በዚህ ኹኔታ ሃይማኖቱም ሃይማኖት አይኾንም፡፡ አማኞች፣ አክራሪነትና ጽንፈኝነት በየሃይማኖታቸው ውስጥ ሲታይ ሃይማኖታቸው አደጋ ላይ እንደወደቀ መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡

አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን (የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ) እንዳለውም፣ በጣም አስደናቂ የኾነውን የኢትዮጵያ ዕድገት ማደናቀፍ ከማንኛውም ወንጀል በላይ በሕዝብ ላይ ከባድ ወንጀል መፈጸም ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለብዙ ዓመታት ሲሠቃይ የነበረ በመኾኑ አሁንም ሕዝቡን ለሥቃይ መዳረግ ተወዳዳሪ የሌለው ወንጀል ነው፡፡

በማንኛውም ሃይማኖታዊ አክራሪነት እና ጽንፈኝነት፣ በምንም ዐይነት ኹኔታ አንድም ሰው ለአንድ ደቂቃ እንኳ ተዘናግቶ መተኛት የሌለበት ሲኾን በተለይ ይህን ነገር በጥብቅ በሁሉም መንገድ መታገል አለብን፡፡

አሁን በኢትዮጵያ ያለውን ዕድገት የሚቀናቀነው የውጭ ተቀናቃኝ ነው፡፡ የእነዚህን ተቀናቃኞች ዓላማ በመያዝ በአክራሪነትና በጽንፈኝነት መልክ ታላቅ ክሕደት መፈጸም ከባድ አገራዊ ክሕደት ነው፡፡ የውጭ ጠላት ቀላል ስላልኾነ አንድም ሰው ሳይቀር በጣም ተጠናክረን መመከት ይገባል፡፡ ሕገ መንግሥቱን መሠረት ያደረገ የፖሊቲካ ልዩነት ሊኖር ይችላል፤ ሕገ መንግሥቱን የመጣስ ዝንባሌ ግን እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ መንግሥቱ ብዙ ዋጋ ተከፍሎበታል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያጸደቀው የራሱ ሕገ መንግሥት ስለኾነ ሕዝብ በመራራ ትግል ያጸደቀውን ሕገ መንግሥት መጣስ የወንጀሎች ሁሉ ወንጀል ነው፡፡

በዚህ ስብሰባ ከፍተኛ ግንዛቤ መያዙ በጣም የሚያስደስት ነው፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ታላቅ ተስፋ ነው፡፡ ለውጭ ጠላት ደግሞ ሲጠብቀው የነበረ ብጥብጥ መቅረቱ ሕዝብን የሚያስደስት፣ ጠላትን ደግሞ የሚያሳፍር ነው፡፡

ሌላው ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተነሣ ነበር፡፡ አንድ አባታችን ካነሧቸው ብዙ ነገሮች አንዱ፣ ‹‹መንግሥት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እጁን ያስገባል›› የሚል ነው፡፡ መንግሥት በሃይማኖት ውስጥ በእስልምናም ይኹን በኦርቶዶክስ እጁን አያስገባም፡፡ በዚህ ጉዳይ የመጀመሪያ ተጠያቂው እምነቱ ነው፡፡ ሕገ መንግሥት የሰጠው መብት ሲጣስ፣ መንግሥት እጁን ሲያስገባ ለምን ዝም አለ? ለሕገ መንግሥታዊ መብቱ ለምን አልታገለም? ሁለተኛው ተጠያቂ ደግሞ መንግሥት ይኾናል፡፡

ስለዚህ በሩን ከፍቶ ሲያንቀላፋ መንግሥት እጁን ካስገባበት እምነቱ ይጠየቃል፡፡ ይኹን እንጂ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት እጁን እንዳላስገባ መቶ በመቶ አምናለኹ፡፡ አንዳንድ የመንግሥት ሰዎች ግን እጃቸውን አስገብተው ሊኾን ይችላል፡፡ ስለዚህ እነዚህን መመከት ነበረበት፡፡ በመጀመሪያ ተጠያቂው ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ራሱ ሲኾን እጃቸውን ያስገቡ ሰዎች ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ተጠያቂ ይኾናሉ፡፡

ሁለተኛ፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በአንድ ወጣት*የተነሣ ሐሳብ አለ፡፡ አክራሪነት አደጋ ነው ብሏል፡፡ በኋላ በእስልምና ሃይማኖት አካባቢ በአንዳንድ ሰዎች የሚታየው አክራሪነት አደጋ ነው፤ ዋናው ግን በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተቀበረው ፈንጅ ነው ትልቁ የአክራሪነት አደጋ ብሏል፡፡ አክራሪነት ማለት እምነቱን ለፖሊቲካ ጥቅም ማዋል፣ እምነቱን ለፖሊቲካ ጥቅም ክፍት ማድረግ ማለት ነው፡፡

አንዳንድ ማኅበራት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን የፖሊቲካ መድረክ እያደረጓት ነው፤ ማኅበሩ** እንኳ ባይኾን አንዳንድ ሰዎች ብሎ ጠቅሷል፡፡ ይህን ተጠንቅቆ ያቀረበው ይመስለኛል፡፡ ማኅበሩ ነው አክራሪ ወይስ በማኅበሩ ያሉ አንዳንድ ሰዎች ናቸው? መጣራት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡

በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ማኅበር ያሉ አንዳንድ ሰዎች ማኅበሩ ጤናው የተበከለ እንዳይኾን ማጣራት፣ ተጠንቅቆ መያዙ፣ እንደተባለው ፈንጅ ከኾነ አስቸጋሪ ነው፡፡ ወጣቱ* እና ዶክተር ሽፈራው ተክለ ማርያም (የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር) ሁለቱም ከባድ የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

እንደተባለው፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በእውነት የፖሊቲካ መድረክ እየኾነች ከኾነ፣ በዚህ አገር የትኛው አክራሪነት ነው ከተባለ፣ ትልቁ አደጋ ያለው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ነው የተባለው ትክክል ነው ወይስ ትክክል አይደለም የሚለው መጣራት የሚኖርበት ቢኾንም በሁለቱ ሰዎች የተጠቆመው ግን የሚያስተኛ አይደለም፡፡ ከእምነቱ ቦታ የኾንም መተኛት የለብንም፤ የሌሎች እምነት አማኞችም መተኛት የለባቸውም፡፡

* * *

ሐራዊ ማስታወሻ፡-

*አቶ ስብሓት ወጣቱ ሲሉ የጠሯቸው የስብሰባው ተሳታፊ ከከምባታ ሐዲያ ጉራጌና ስልጤ አህጉረ ስብከት ከሚገኘው ሃላባ ወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤትና ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የመጡ አባ ዮናስ የተባሉ መነኩሴን ነው፡፡ እኒህ ስመ መነኮስ እንደ በጋሻው ደሳለኝ ላሉ ሕገ ወጥ ሰባክያን ዐውደ ምሕረት በመፍቀድና ምእመኑን ሰላም በመንሳት በወረዳው የማኅበሩ ጽ/ቤት እንዲዘጋ ያደረጉ፣ ከትምህርቱም ከግብረ ገቡም የሌሉበት ግለሰብ ናቸው፡፡

መንግሥት አካሂደዋለኹ በሚለው የፀረ አክራሪነት ትግል አጋር መስለው የተጠጉ ግለሰቦች [የደብር አስተዳዳሪ ለማሾም 60,000 ብር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በመያዛቸው 60 ጎራሽ የተባሉትንና ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ምክትል ሥራ አስኪያጅነት ተነሥተው ወደ መ/ፓ/ጠ/ቤተ ክህነት የትምህርትና ሥልጠና መምሪያ ምክትል ሓላፊነት የተዛወሩትን የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢን ርእሰ ደብር በሪሁ አርኣያን ይጨምራል] ያላቸውን አግባብነትና የሚሰጡትን መረጃ ትክክለኛነት (ቅንነት) ማጤን ይገባዋል፡፡

አቶ ስብሓት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚያራምዱትና በልዩ ልዩ ዘገባዎች ሲገለጽ የቆየው አቋማቸው በተለይ ከ፳፻፩ ዓ.ም ጀምሮ በሚገባ ይታወቃል፡፡ ‹‹ሕገ መንግሥት የሰጠው መብት ሲጣስ፣ መንግሥት እጁን ሲያስገባ ለምን ዝም አለ? ለሕገ መንግሥታዊ መብቱ ለምን አልታገለም?›› ማለታቸው በአባባል ደረጃ ተገቢ ቢኾንም እርሳቸው የጠቀሱትን ሕገ መንግሥታዊ መብት ለማስከበር ቢያንስ በግንቦት ፳፻፩ ዓ.ም በመጠኑ የሞከሩ ብፁዓን አባቶች ምን እንደደረሰባቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ይህን የምንለው ሊቃነ ጳጳሳቱን ልናመሰግናቸው ፈልገን ወይም አቶ ስብሓት እንዳሉት ‹‹በሩን ከፍቶ ያንቀላፋ የለም›› ለማለት አይደለም፡፡ በሌላ መድረክ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ስለ ኹኔታው ምሬታቸውን በገለጹበት ወቅት ‹‹ብትሰየፉስ!›› ያሏቸው የመከራቸው ፍጻሜ ገና መኾኑን ስለሚያሳይ፡፡

አቶ ስብሓት ለቤተ ክርስቲያናችን ተቋማዊ ለውጥ በቅ/ሲኖዶሱና በቀድሞው ፓትርያርክ መካከል የተደረገው የውስጥ ትግል በተጧጧፈበት ወራትና ከዚያም ወዲህ በእጅጉ ይጠሏቸው ነበር የሚባሉትን የቀድሞውን ፓትርያርክ ከመንበራቸው ለማስወገድ ማኅበሩ በቅ/ሲኖዶስ ዕውቅና ካገኘበት የአገልግሎት ዓላማና ስልት ውጭ ሚና ለመስጠትና መሣርያ ለማድረግ የገፋፉበት ኹኔታ በማኅበሩ ቀጣይ ህልውና ላይ ያላቸውን ፍላጎት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ እንደነበር ይነገራል፡፡

ግፊታቸው በወቅቱ በማኅበሩ ጥቂት አመራሮች መካከል ልዩነት ፈጥሮ እንደነበር የሚገለጽ ቢኾንም ተቀባይነት ያገኘ ግን አልነበረም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ‹‹የቤተ ክህነት ዕዳ ነው›› በማለት ‹‹የተቃዋሚ ፖሊቲካ መድረክነት›› እንደሚታይበት ወዘተ ባለፈው ዓመት የፍትሕ ጋዜጣ ጽሑፋቸው የሰነዘሩበት ሒስም የዚያ ማወራረጃ እንደኾነ ይታሰባል፡፡

ማኅበሩ ከተመሠረተበት ዓላማና ከሚፈለግበት አገልግሎት አኳያ በድክመት የሚተችበትና ገና ብዙ እንደሚቀረው የብዙዎች እምነት ቢኾንም በሰሞኑ ስብሰባ አቶ ስብሓት ወጣቱ ባሏቸው አባ ዮናስ ጥቆማ በኩል አልፈውና የአባ ዮናስን ንግግር አጉነው ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሰጡት አስተያየት ወይ አቅጣጫ መነሻው ጥላቻ የወለደውና ቅንነት የጎደለው መረጃ እንደኾነ የመረጃው ጠቋሚ ሰው ስለ ማኅበሩ ባላቸው አቋምና በወረዳቸው ከማኅበሩ አባላት ጋራ ባላቸው ግንኙነት መረዳት አያዳግትም፡፡

መንበረ ፓትርያርኩን በመወከል በስብሰባው እንዲገኙ ጥሪ ከተደረገላቸው 50 ተሳታፊዎች መካከል ማኅበረ ቅዱሳን በዋና ጽ/ቤቱ ደረጃ እንደማኅበር እንዳልተጋበዘና ይህም በአክራሪነት ከተካሄደው ፍረጃ ጀምሮ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡበት እንደሚገኝ ተሰምቷል፡፡

አባ ዮናስ ከእውነት የራቀ ጥቆማቸውን፣ አቶ ስብሓትም በዚሁ ላይ የተመሠረተ አስተያየታቸውን/አቅጣጫቸውን በሰጡበት መድረክ ሊቃነ ጳጳሳቱ አቡነ ገብርኤል፣ አቡነ ናትናአል ፣ አቡነ ኄኖክ፣ አቡነ ጎርጎሬዎስ በአጸፋ የመናገርና ምላሽ የመስጠት ዕድል ተነፍገዋል፡፡ ይኸው የስብሰባው አካሄድ ከአዳራሹ ውጭ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱና በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች መካከል በከፍተኛ ደረጃ አጠያይቆ እንደነበር ተዘግቧል፡፡ በውይይቱ ቤተ ክርስቲያን ከአክራሪነት አንጻር የተገለጸችበትንና ማኅበሩን አስመልክቶ የተሰነዘሩ ሐሳቦችን መንበረ ፓትርያርኩ በቀላሉ እንደማይመለከተውና በጥብቅ እንደሚነጋገርበት ሊቃነ ጳጳሳቱ ለሚኒስቴሩ ሓላፊዎች እንዳሳሰቧቸውም ተገልጧል፡፡

Hara tewahdo

(የምዕራብ ጐጃም ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት – ፍኖተ ሰላም) የብፁዕነታቸው ልደትና ዕድገት ብፁዕ አቡነ ቶማስ በቀድሞው አጠራር በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በቆላ ደጋ ዳሞት አወራጃ በደጋ ዳሞት ወረዳ በመንበረ ስብሐት ዝቋላ ፬ቱ እንስሳ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ ከአባታቸው ብላታ ተገኘ ይልማ ገብረ ሕይወት ከእናታቸው ከወ/ሮ ውድነሽ ቸሬ መጋቢት 14 ቀን 1935 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ‹‹ዘእንበለ እፍጥርከ አእመርኩከ ወዘእንበለ …


(ደጀ ሰላም፣ መጋቢት 19/2006 ዓ.ም፤ ማርች 28/2014/ PDF)፦ በዚህ የዘመነ ብላ ተባላ፣ ጸረ ሊቃውንት እና መፍቀሬ ተሐድሶ ዘመን በቤተ ክህነት ከቁንጮው እስከ ግርጌው ባሉ በልቶ አደሮች ሲገፉ ከኖሩት አባቶች መካከል አንዱ ብፁዕ አቡነ ቶማስ ነበሩ። አፈር ይቅለላቸው። ዕረፍታቸው እጅግ ቢያሳዝነንም ማንም ከዚያ ስለማይቀር የምንጸጸትበት አይደለም። እንዲህ የተማሩ ሊቃውንት እንደ ተርታ ሰው ወደጎን ተገፍተው ዳዊት ባልደገመ አፋቸው ነገረ ቤተ ክርስቲያንን የሚዘነጥሉ፣ ንብረቷን የሚዘርፉ፣ አሰረ ክህነታቸውን ያልጠበቁ ሰዎች የሚፏንኑበት እንዲሁም በፖለቲካ ቀረቤታቸው የቤተ ክርስቲያን ሳይሆኑ መቅደሷን የሚረመርሙ ሰዎች የሰለጠኑበት ዘመን መሆኑ ግን ያሳዝነናል። ሐዘን ብቻ ባይበቃም።

አቡነ ቶማስ አርፈዋል። ተተኪ ቶማስ እንዳይገኝ ግን የተዘራውን መልካም ዘር የሚያበላሹ ጥቃቅኑን ቀበሮዎች ማን አጥምዶ ይያዝልን? (መኃልይ 215) ሊቃውንት በወንበራቸው እንደተከበሩ እንዲኖሩ የሚያደርገው ማነው? ይህ ሁሉ ፀረ ሊቃውንት ሹመኛ ሌላ የተዋሕዶ አርበኛ የሆነ ቶማስ እንዳይፈጠር ተግቶ ሲለፋ ርቱዕ እምነት የያዘው ኦርቶዶክሳዊ የአቅሙን ለማድረግ የሚተባበርበት ዘመን መቼ ይቀርባል?
የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን፣
ጸሎታቸው ትድረሰን፤ አሜን
ቸር ወሬ ያሰማን።
Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

ሰሞኑን አንድ ኢትዮጵያዊ በቶሮንቶ የህሊና እስረኞችን ለመዘከር በግሉ አዳራሽ ተከራይቶ የአንዱዓለም አራጌን “ያልተሄደበት መንገድ” የሚለውን መጽሃፍ ለሽያጭ በአቀረበበት ቦታ ተገኝቼ ነበር። በዚህ አዳራሽ አንዱዓለምን፣ እስክንድርን፣ ርዕዮትን …ወዘተ ለመዘክር ብለው የተሰባሰቡ ሰዎች ብዛት ስመለከት “በእውነቱ እስረኞች እኛ ነን ወይስ እነ ዓንዱአለም?” የሚል ጥያቄ ጫረብኝ። አገርን ያህል ትልቅ ነገር ከራሳችን የፖለቲካና የግል ጠባብ ፍላጎት ዙርያ ቀንበበን ልንከተው […]

ወያኔ ኢህአዲግ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም የቆመ መንግስት አይደለም :: ሀገር ማለት የተለያዩ ብሄሮች ፣ የተለያዪ ጓሳዎች እና የተለያዩ ሃይማኖቶች ያሎቸው ሰዎች መኖሪያ ናት :: እኛም ሀገራችን ብለን የምንጠራት ሀገራችን ኢትዮጵያ አኩሪ ታሪክ ያላት የተለያዩ ህዝቦች መኖሪያ ሀገር ስትሆን ሕዝቦቾም ለዘመናት በፍቅር፣ በመተሳሳብ ፣ በመከባባር እና በመተባባር አብሮ ሲኖር የነበሩ ህዝቦች እንደነበሩ ከታሪክ መረዳድ […]