የአዲስ አበባ አንድነት ወጣቶች ኮሚቴ፣ በአዲስ አበባ ለመስከረም 11 ቀን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ እየተዘጋጀ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። እንቅስቃሴው በዋናነት ፣ የአዲስ አበባን ህዝብ ለታሰሩ የፖለቲካ መሪዎች፣ ብሎገሮች፣ ጋዜጠኞች፣የሰባአዊ መብት ተሟጋቾች …ሶሊዳሪቲዉን በማሳየትና ሻማ በማብራት እስረኞች በማሰብ ላይ ያተኮረ እንደሚሆን አዘጋጆቹ ለአቡጊዳ ገልጸዋል። የአንድነት ፓርቲ ከዚህ በፊት የሚያደርጋቸው የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓቶች፣ በጽ/ቤት ብቻ እንደነበረ፣ የገለጽት […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በአለም አቀፍ ደረጃ ስለ ሽብርተኝነት ያለው አረዳድ እና ወያኔ ሽብርተኝነትን የሚተረጉምበት መንገድ ለየቅል ናቸው። በአለም አቀፍ ደረጃ የሽብርተኝነት ጉዳይ እንደ ዋና አጀንዳ ተይዞ ለመጀመሪያ ጊዜ መነጋገሪያ የሆነው በ1934 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ነው። በዛሬው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተተካው የሊግ ኦፍ ኔሽን በሽብርተኝነት ዙሪያ ሲመክር ቆይቶ በ1937 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ሽብርተኝነትን ለመከላከል እና ለመቅጣት የሚያስችል አንድ ድንጋጌ (Convention for […]

ባለፉት ጥቂት ወራት በዩክሬንና ክራሚያ ውስጥ የተቀሰቀሰው ሁኔታ እና አሁን የደረሰበት ደረጃ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር አንጻር ብዙ ዕድምታዎች አሉት፡፡ እነዚህን ዕድምታዎች መመርመር በሀገራችን ውስጥ ያለፉና የወደፊት ጉዞ ላይ የተከሰቱ፤ እና ሊከሰቱም የሚችሉ ጉዳዮችን ከወዲሁ በግምት ውስጥ በማስገባት ሀገራዊ ራዕያችንን ፣ የትግል አቅጣጫችንን አና አጋርና ተቀናቃኝ ሊሆኑ የሚችሉትን ሃይሎች ለይቶ ለማወቅ ያግዛል ብዩ አሰባለሁ። ይህን ማወቁ […]

የዛሬ ወር ገደማ የቪኦኤ አማርኛ ሪፖርተር የሆነውና አወዛጋቢና የተዛባ መረጃ በማቅረብ በስፋት የሚታወቀው ሄኖክ ሰማእግዜር ሙሉ በሙሉ ሃሰት የሆነ ዘገባ በአሜሪካን ሬድዎ አማካኝነት አሰራጨ። የዘገባው አላማ በካሊፎርኒያ የሚገኘው አዙሳ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲ ለአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሰጥቶ የነበረውን የክብር ሽልማት መልሶ መንጠቁንና ዝግጅቱ መሰረዙን በማስመልከት የቀረበው ዘገባ ሃሰት ነው ብሎ ለማስተባበል እና እኔን፣ አለማቀፉን የኢትዮጵያዊያን መብት የጋራ […]

የህወሃት ፍጹም ታማኝ ነበር። በተለያዩ ሃላፊነቶች በህጻናት፣ በወንድሞቹ፣ በእህቶቹ፣ በእናቶቹ፣ በአባቶቹ አጠቃላይ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በሰራው ወንጀል በህግ ይፈለጋል፣ በህግ የሚፈልጉት ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆኑ ዓለም አቀፍ የፍትህና የመብት ተሟጋቾች ናቸው። ህወሃትን ክዶ በስደት ከሚገኝበት አገር እጁን እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቦለታል። ይህ “ሰው” በጋምቤላ ክልል የፖሊስና የጸጥታ ሃላፊ የነበረ። የደህንነት አመራር ነበረ። ክልሉን በፕሬዚዳንትነት ለዓመታት የመራ፣ በጅምላ […]

«እኔ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ወደ እረፍቱ ብሄድ የምመኘው ነው ነገር ስለሆነ፣ አሁንም ለወጣቶቹ አቅማችሁን ባካችሁ ባካችሁ አዳብሩ፤ እኔንን በአስቸኳይ፣ በአስቸኳይ ተኩ ነው የምለው» ይህን የተናገሩት የአንድነት ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ነበሩ፣ ከሰባት ወራት በፊት። ወጣቶችን ወደ አመራሩ በማምጣት ዙሪያ ከአንድነት ራዲዮ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ። ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ለትግሉ […]

እስከ ጳጉሜ 4 2006 ዓ.ም ድረስ የተካሄደው የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ በርካታ እንግዳ ክስተቶችን ይዞ የተገኘ እንደነበር ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል:: በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ለሶስተኛ ጊዜ በተካሄደው በዚሁ የድርጅቱ ስብሰባ ብአዴን እና ኦህዴድ ድርጅታዊ ተልእኮዎችን የማስፈጸም ውስንነት እንደታየባቸው አልፎ ተርፎም የኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎች በተለይም ከኦሮሚያ ክልል ወለጋ ኢሊባቡር እና አምቦ የኦነግ ምሽግ የሆኑ […]

መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመዠንገር ብሄረሰብ ተወላጆች ጎደሬና ሜጫ በሚባሉት አካባቢዎች እንደ አዲስ በጀመሩት ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውንና እስካሁን አስከሬኖች እንዳልተነሱ የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። ከጋምቤላ ብሄረሰብ ውጭ ያሉ የሌሎች አካባቢ ተወላጆች በሙሉ ይወጡ በሚል የተጀመረው ግጭት ፣ ደም አፋሳሽ ሆኖ ከመቀጠሉ ባሻጋር፣ በትናንትናው እላት ብቻ ከ1 ሺ ያላነሱ ሰዎች ተፈናቅለው ቴፒ ከተማ መግባታቸው ታውቋል። …

መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ሆነው ለግንቦት7 የአርባ ምንጭና አካባቢው ወጣቶችን በመመልመል ወደ ኤርትራ ይልካሉ በሚል ጥርጣሬ ተይዘው ለሳምንታት በአርባ ምንጭ እስር ቤት ታስረው የቆዩት የፓርቲው የአርባ ማንጭ ምክትል ሰብሳቢ በፍቃዱ አበበ እንዲሁም የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው ኢንጂነር ጌታሁን  ወደ ማእከላዊ እስር ቤት መወሰዳቸውን የፓርቲው ድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ለኢሳት ገልጸዋል። …

መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል አቃቢ ህግ በ17 የጅቡቲ፣ ህንድ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ ሲሪላንካና እና አሸራፍ አወል አብዲ  በሚባል ኢትዮጵያዊ ላይ በመሰረተው ክስ፣ ግለሰቦቹ ለኢትዮጵያውያን በተፈቀደው የንግድ ስራ ህገወጥ በሆነ መንገድ በመነገድ መንግስት ማግኘት የነበረበትን 700 ሚሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ እንዲያጣ አድርገዋል ብሎአል። በክሱ ዱባይ ኦቶ ጋላሪ ኤል ኤል ሲ እና ወርልድ ኢንተርናሽናል ፍሪዞን ኩባንያ …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ኦስካር ፒስተርየስ ጊዜ ጠብቆ ፤ አቅድ አውጥቶ ሰው የገደለ ወንጀለኛ አይደለም ሲሉ ዋና ዳኛ በየኑ ።የካቲት 7 ቀን 2005 ዓ ም ፣ ፈረንጆቹ (Valentine Day) በሚሉት ፣ ወንዶች ለሚያፈቅሯ ቸው የአበባ ሥጦታ በሚያበረክቱበት ዕለት ፣

ለሌሎቹ የአዘቦት ቀን በሆነበት የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት ዕለት ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በዓሉን እንዴት አከበሩት? ባህልን በማስተዋወቁ ረገድስ ምን ያህል ዝግጁ ናቸው?

በ2017 የሚካሄደውን የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ የነበረችው ሊቢያ በሃገሪቱ በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን እድሉን ለሌሎች ሃገሮች ለመስጠት ተገዷል።ኢትዮጵያ፤ኬንያና ጋና ደግሞ የውድድሩን የማዘጋጀት እድል ለማግኘት የመጨረሻውን ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ናቸው

CPJ በሚል ምፃረ-ቃል የሚጠራዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት እንዳስታወቀዉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ሐገር ጥለዉ የተሰደዱት ኢትዮጵያዉን ጋዜጠኞች ቁጥር ከሠላሳ በልጧል።ሰሞኑንም ሰወስት ጋጠኞችና አሳታሚዎች ተሰደዋል

ነሐሴ 23 ቀን 2006 ዓም ማለዳ 10 ሰዓት ነው ከዕንቅልፌ የነቃሁት፡፡ ዲያቆን  ሙሉቀን ብርሃን ከጎንደር፣ ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ ከፍኖተ ሰላም መንገድ ላይ ይጠብቁኛል፡፡ ለመንገዱ የሚሆነውን የቱሪስት መኪና ያዘጋጀልኝ የኦሪጂንስ ኢትዮጵያ አስጎብኝ ድርጅትባለቤት ሳምሶን ተሾመ ነው፡፡ ክብር ይስጥልኝ ብያለሁ፡፡ የምተርክላችሁን ታሪክ ስትጨርሱ ትመርቁታላችሁ ብየ አምናለሁ፡፡ የምጓዘው አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ ለማደርገው ጥናት ተጨማሪ መረጃዎችን ፍለጋ ነው፡፡

ሾፌራችን ደምስ ይባላል፡፡ ዝምታና ትኩረት ገንዘቦቹ የሆኑ፣ በሁሉም ነገር ለመንገድ የተዘጋጀ፡፡ ለተራራ ቢሉ ለቁልቁለት፣ ለበረሐ ቢባል ለደጋ የሚሆኑ መሣሪያዎችን ሸክፎ የያዘ ልምድ ያለው ሾፌር ነው፡፡

ዓባይ በረሐ መግቢያ ላይ

የምንጓዘው ከምድር ሥር ከሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎቻችን ወደ አንዱ ነው፡፡ በጎጃም በር በኩል ወጥተን ፍቼና ጎሐ ጽዮንን አቋርጠን በክረምት ውበቱ እጥፍ ድርብ ወደሚሆነው ዓባይ በረሐ መንደርደር ቀጥለናል፡፡ ዓባይ በረሐ የሚባል ቦታ መቼም አያልፍለት፡፡ አበሻ ቢሠራው፣ ጣልያን ቢሠራው፣ ጃፓን ቢሠራው መሬቱ እንደሆነ ድንጋይ ላይ እንዳስቀመጡት ሰው ሲንቀሳቀስ ይኖራል፡፡
ይንሸራተታል ተጠንቀቁ

ተሻገርንና ደጀንን አለፍናት፡፡ ከደጀን እስከ ደብረ ማርቆስ ያለው መንገድ በመሠራት ላይ ስለሆነ መኪኖቹን ሁሉ ለአካባቢው መንደሮች እጅ ሲያስነሣቸው ይውላል፡፡ አንዳንዱን መንገድ እንኳን መኪና ዝንጀሮም ያለ ስዕለት የሚወጣው አይመስልም፡፡ በግራ በቀኝ ሽው እልም እያሉ የሚከንፉት መኪኖች ሁሉ መዘጋጃ ቤት እንደ ረሳው ጎዳና በተቆፋፈረው መንገድ ላይ ሲደርሱ ለቆጠራ እንደወጣ እሥረኛ ሰልፍ ይይዛሉ፡፡ 
እኛም ስንችል ስንበር፣ ሳንችል ስንሰለፍ ደብረ ማርቆስን አልፈን ወደ ደምበጫ ማቅናቱን ተያያዝነው፡፡ ሙሉቀንና ስምዐ ኮነ ከአዲስ አበባ 360 ኪሎ ሜትር ርቀት ደምበጫ ላይ ነው የሚጠብቁን፡፡ እነርሱን ከምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት የቅርሳ ቅርስ ክፍል ኃላፊና ከደጋ ዳሞት ወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ጋር አሳፍረን የባሕርዳርን መንገድ ትተን ወደ ቀኝ በመታጠፍ የፈረስ ቤትን መንገድ ተያያዝነው፡፡

ሰቀላ ማርያም ደን
ከፊት ለፊታችን የሰቀላ ማርያም ደን ጫፍና ጫፉን ገጥሞ በመካከሉ ሲያሳልፈን ሙሽራ ለመቀበል የወጣ የአዲስ አበባ ሚዜ ይመስል ነበር፡፡ በአንጀኒን በኩል አለፍንና ሰነቦ ተራራው ላይ ደረስን፡፡ መቼም የፈረስ ቤት የጠጠር መንገድ ከአንዳንዱ የአዲስ አበባ አስፓልት ይመረጣል፡፡ በስተግራችን ተራራውን ተደግፈን፤ በስተ ቀኛችን በረሐውን እያማተርን መኪናችንን ከአካባቢው ፖሊስ መጠበቂያ ጎን አቆምናት፡፡


አሁን ከባዱ መንገድ ሊመጣ ነው፡፡ የምንወርደው ከምድር ሥር ወደ ታች ነው፡፡ በተራራው ወገብ እየታከክን፣ እንደ ዝንጀሮ ተንሸራትተን እንደ ጦጣ እየዘለልን መጓዝ ይጠበቅብናል፡፡ ዕቃዎቻችንን ሁሉ ሸከፍንና የማይቀረውን ቁልቁለት ተያያዝነው፡፡ ለጉልበት ፋታ የማይሰጠው ቁልቁለት መቅኔያችን ያለቀ እስኪመስለን ድረስ ያንተፋትፈናል፡፡ የገበሬዎችን እርሻና መንደር እያቆራረጥን፣ ወንዝና ገደሉን እየተሻገርን የተራራውን ሥር ለማግኘት እንኳትናለን፡፡

ውረድ- ወደ ሰነቦ
የተራራውን ወገብ ካለፍን በኋላ ዓለምን ተሰናብተናት ዓለምን ወደረሳና ዓለምም ወደረሳችው ክልል ወረድን፡፡ በጫካ የተሞላ፣ የፏፏቴ ድምጽ ከሩቅ የሚጣራበት፣ ወፎቹ በተሲዓት የሚዘምሩበት፣ የፋርስ ምንጣፍ የተነጠፈበት የሚመስል ሸለቆ ተቀበለን፡፡ እስካሁን ዋሻውን አላገኘነውም፡፡

ወደ ቀኝ ታጥፈን አንዲት ጅረት መሰል ውኃ ከተሻገርን በኋላ የግቢው መግቢያ በር ጋ ደረስን፡፡ ጭንቁ እዚህ ላይ ይጀምራል፡፡ እኔ ለራሴ ቁልቁለቱን ለመውረድ እንደ ቅቤ ቅል ስናጥ ስለቆየሁ ጉልበቴና እግሬ ተለያይተው ለየብቻ የሚሄዱ መምሰል ጀምረዋል፡፡ እዚህ ደግሞ ለከተማ ሰው የከበደ ቀኖና ጠበቀን፡፡ ከገዳሙ ክልል መግቢያ ጀምሮ በባዶ እግር ነው የሚገባው፡፡ ፊት ለፊት የማያቸው ደንጋዮች ሆያ ሆዬ እንደሚሉ ልጆች እጅብ እጅብ ብለው ቆመው፣ እንደ ፋስ መጥረቢያ የተሳሉ ናቸው፡፡ አንድ እግሬን የመግቢያው ርብራብ ላይ አሳርፌ ሁለተኛውን የት ላድርገው፡፡ በግራ በቀኝ የማያቸው ድንጋዮች እንደ ጥሬ ሥጋ ቆራጭ ቢላዋቸውን አሹለው ይጠብቁኛል፡፡ በብኾር ላይ ቆረቆር እንዲሉ ከተራራው ላይ ባለማቋረጥ የሚወርደው ውኃ አካባቢውን ስላራሰው እግሬ በብርዱ ወደ መደንዘዝ ደርሷል፡፡


መጨነቄን ያየው የቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪ የሆነው የዐቢ እንደ አቡነ ገሪማ አገልጋይ በግራ ጎኔ በኩል መጥቶ ደገፍ አደረገኝ፡፡ አይቀርምና እግሬን ወደ አንዱ ሹል ባልጩት ሰደድኩት፡፡ የእግሬ ድንዛዜና የባልጩቱ ስለት ተባብረው ዋጋዬን ሰጡኝ፡፡ ድምጽ እንደሰማች ዕንቁራሪት ዘልዬ ወደ ሌላው ድንጋይ ተሻገርኩ፤ እርሱም እንደ ጓደኞቹ በጠረባ አወራረደኝ፡፡ የዐቢ እየደገፈኝ፣ እኔ ጥርሴን ነክሼ እየዘለልኩ የውኃው ድምጽ እንደ ነጎድጓድ ከሚያስገመግምበት ሥፍራ ደረስን፡፡ ሰነቦ ተክለ ሃይማኖት፡፡


ጠበሉ ከቤተ ክርስቲያኑ በላይ ካለው ተራራ ላይ ነው የሚወርደው፡፡ በሦስት ቦታ ተጠማቂዎቹ ይገለገላሉ፡፡ ለሴቶች፣ ለወንዶችና ለካህናት የተዘጋጁ ናቸው፡፡ በሌሎች የመጠመቂያ ቦታዎች ለካህናት የተዘጋጀ የተለየ ቦታ አልገጠመኝም፡፡ በዚህ ሰነቦዎች ይመሰገናሉ፡፡ የቤተ መቅደሱ በር ከተራራው ሥር ይታያል፡፡ ዋሻው ግራና ቀኝ ተገንብቶ በበር ተዘግቷል፡፡ በስተ ግራ በኩል የካህናት መግቢያ ሌላ ሰርጥ አለ፡፡ ዋናው በር ተከፈተልንና ገባን፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ስትገቡ በስተግራ ይገኛል፡፡ መጀመሪያ ቅኔ ማኅሌቱን፣ በእንጨት በተከለለው ሥፍራ ደግሞ መቅደሱን የዋሻው ውስጥ ደግሞ ቅድስቱን ታገኛላችሁ፡፡ 
የመቅደሱ ግንብ
ከቤተ ክርስቲያኑ በስተ ቀኝ ማለቂያው የማይታወቅ የዋሻ  ውስጥ መንገድ ይገኛል፡፡ ያውም መንገዱ በውኃ የተሞላ ነው፡፡ አንዳንድ አገልጋዮች የአራት ሰዓት መንገድ ተጉዘው መጨረሻውን ሊያገኙት እንዳልቻሉ ገልጠውልናል፡፡ እንደ አካባቢው ቃላዊ ታሪክ ከሆነ ዋሻው ከደብረ ሊባኖስ ጋር ይገናኛል፡፡ ገዳሙ ‹ሰነቦ ደብረ ሊባኖስ ተክለ ሃይማኖት ገዳም› የተባለውም ለዚህ ነው ይላሉ፡፡
የገዳሙን የምሥረታ ጊዜ በትክክል ለማወቅ አልቻልኩም፡፡ አገልጋዮቹ ከሚተርኩት ትረካና በትረካቸው ውስጥ ከሚጠሯቸው ሰዎች ስንነሣ ግን ከግራኝ ዘመን ቀደም ብሎ የተተከለ መሆኑን ለመገመት ይቻላል፡፡ አሁን ባለበት ሁኔታ የተተከለው በአድያም ሰገድ ኢያሱ ዘመን(1674-1698ዓም) መሆኑን አንዳንድ የገዳሙ መዛግብት ያሳያሉ፡፡ አድያም ሰገድ ኢያሱ በዚህ ዋሻ ውስጥ አንድ መነኩሴ ጽላት እንደያዙ መስቀል ጨብጠው ዐጽማቸው እንደሚገኝ የሰሙትን ለማረጋገጥ ከጎንደር ተነሥተው መጡ፡፡ ሲመጡም የሰሙት ትክክል መሆኑን አዩ፡፡ ገዳሙን ገድመው፣ ርስት ሰጥተው አከበሩት፡፡ በወቅቱ 500 መነኮሳት ነበሩት(300 ወንዶችና 200 ሴቶች)፡፡

ወደ ዋሻው በዐለት ፍላጭ ላይ ጉዞ
አድያም ሰገድ ኢያሱ ያሠሩት የቤተ መቅደሱ ግንብ ፍርስራሹ አሁንም ይታያል፡፡ የመንበሩን ሥዕል ያሠሩት ወ/ሮ መለኮታዊት (ያረፉት በ1618 ዓም ነው) መሆናቸውን የገዳሙ ካህናት ይገልጣሉ፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ የገዳሙ ትክል ከአድያም ሰገድ ኢያሱ ዘመን ቀደም ይላል ማለት ነው፡፡ ወ/ሮ መለኮታዊት የነበሩት በዐፄ ሱስንዮስ ዘመን ነው፡፡ ካልሆነ ደግሞ በዐፄ ቴዎፍሎስ ዘመን የነበሩትና በ1701 ያረፉት መለኮታዊት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በአንዳንዱ የገዳሙ መጻሕፍት ላይ ከዐፄ ፋሲል የተሰጠ መሆኑን ስለሚገልጥ ታሪኩ ከአድያም ሰገድ ኢያሱ ዘመን ቀደም ያለ መሆኑን ያሳየናል፡፡

የዋሻው ውስጥ መንገድ
ምሽቱን የአካባቢው ሕዝብ ከዝናብና ጭቃ ጋር እየታገለ ለክብረ በዓሉ ሲጎርፍ ነው ያመሸው፡፡ ያች ዋሻ ከአፍ እስከ ገደፏ ሞላች፡፡ ማኅሌቱ ሌሊቱን በሙሉ ከዋሻው ሲሰማ አደረ፡፡ ቅዳሴውን ያስቀደስነው ከታች ካለው ቅዝቃዜና ከጎን ከሚመጣው ብርድ ጋር እየታገልን ነው፡፡ ፈውስ ፍለጋ ከየቦታው የመጡት ሕሙማን እንደ ሰሊሆም መጠመቂያ ማለዳውን ይጠብቃሉ፡፡ ቅዳሴው እንዳለቀ የሚጀመረውን የዋሻ ውስጥ ጥምቀት፡፡

የሌሊት ማኅሌት
ቅዳሴው አብቅቶ ትምህርት ከተሰጠ በኋላ ለደመራ የሚበራውን ችቦ የሚያስንቁ አራት አምስት ችቦዎች በርተው መጡ፡፡ ሕዝቡም ወደ ዋሻው መንገድ ተሰባሰበ፡፡ ከግራ ከቀኝ በአገልጋዮች ተደግፌ ከተሳሉት የዋሻ ውስጥ ድንጋዮች ላይ እግሬን እያሳረፍኩ፣ በብርዱ የደነዘዘውን እግሬንም ትቼው የመጣሁ እስኪመስለኝ እየረሳሁ ከካህናቱ ጋር ወደ ዋሻው ውሳጣዊ ክፍል ገባን፡፡ በዐለቶች ላይ እንደ ጦጣ ተንጠላጥለን የጠበሉ ጫፍ ላይ ደረስን፡፡

ይህ አሁን ከፊታችን የሚታየው ጠበሉ ነው፡፡ ተጠማቂው ወገቡን በገመድ ይታሠርና ወደ ጠበሉ ይገባል፡፡ ወገቡን የሚታሠረው የዋሻው ጥልቀት ስለማይታወቅ ነው፡፡ አንድ ሰው አራት ሸንበቆ ተቀጣጥሎ ወለሉን እንዳልደረሰበት ነግረውኛል፡፡ በኋላ እንደገመትነው ጥልቀቱ ከ20 ሜትር በላይ ነው ማለት ነው፡፡ ጥልቀቱ ብቻ ሳይሆን የዋሻው መጨረሻም አይታወቅም፡፡ ቆርጦ ከሄደ መመለሻውን እንጃ፡፡ ‹ተክልየ ነው የሚይዙት›› ብለውኛል፡፡ እውነትም፡፡
በጨለማው ውስጥ ወደ ጠበሉ ጉዞ
ካህኑ መስቀል ይዘው እያጠኑ መጡ፡፡ ተጠማቂውም እየጮኸ ወገቡን በገመድ ታሥሮ ቀረበ፡፡ እርሳቸው ወደ ጠበሉ ዳር ገቡና ተጠማቂውን ጠሩት፡፡ ገባ፡፡ ታሪክ ተጀመረ፡፡ መስቀል ከመያዝና ጸሎት ከመድገም በቀር ካህኑ ምንም አላደረጉትም፡፡ እርሱ ግን መናገር ጀመረ፡፡ የተደረገበትን፣ ማን መድኃኒት እንዳደረገበት፣ ለምን እንዳደረገበት፣ ይለፈልፍ ጀመር፡፡ በአራት ጎረምሶች ተይዞ የገባው ጎልማሳ ኅሊናው ተመልሶለት ራሱ ከጠበሉ ወጣ፡፡ እንዲህ እያለ አንድ ሦስት ሰው ተጠመቀ፡፡

ካህኑ ወደ ጠበሉ ሲገቡ

ካህኑ በቃ አሉ፡፡ እንደሰማነው በወር አንድ ወይም ሁለት ቀን ወደ ዋሻው ጠበል ይገባል፡፡ እዚያ ገብቶ ሳይድን የሚወጣ የለም፡፡ ሕሙማኑም እነዚያን ሁለትና ሦስት ቀናት በተስፋ ነው የሚጠብቋቸው፡፡
በውኃው ላይ ወደ ጠበሉ ጉዞ

ከአንድ ሰዓት በኋላ ከዋሻው ወጣን፡፡ እኔም ከሹሉ ድንጋይ ላይ ዝናብ፣ ብርድና ጭቃ ተጨምረውበት እየዘለልኩና እየተደገፍኩ የገዳሙን ክልል ለቅቀን ወጣን፡፡ ወደ ማረፊያችን ገብተን ምሳ ከበላን በኋላ ከጫማችን ጋር ተገናኘን፡፡ ለካስ ጫማም ይናፍቃል፡፡

ተጠማቂው በገመድ ታሥሮ ወደ ጠበሉ ኩሬ ሲገባ

ስንመጣ ቁልቁል ያየነውን አሁን ቀና ብለን ልናየው ነው፡፡ በትናንቱ መንገድ ላይ ዝናብና ጭቃ ተጨምሮበታል፡፡  የጫማዬ መልክና ቁመና ጠፍቶ ከተራራው ጋር እየታገልኩ መውጣት ቀጠልኩ፡፡ አንድ ጎኔን የዐቢ ደግፎኝ በአንድ እጄ መቋሚያ ይዣለሁ፡፡ የተጎረዱ መሬቶችን መዝለል፣ በጭቃው ተንሸራትቶ ወደ ኋላ መመለስ፣ ከፊት ለፊት እንደ ጅብራ የተገተረ ተራራን ማየት እንዴት አድካሚ መሰላችሁ፡፡ 
ተራራውን ከታች ወደ ላይ ሲያዩት

ይባስ ብለው ሙሉቀንና ስምዐ ኮነ እየጣሉኝ ወደ ተራራው ጫፍ መድረሳቸውን ሳይ የምደርስ አልመስልህ አለኝ፡፡ የዐቢ እኔን ደግፎ ተራራውን ለመውጣት ይፈጋል፡፡ የወረዳው ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና የአካባቢው ካህናት ‹በርታ በርታ› ይላሉ፡፡ አሳብ የለሽ ሀብታሙ ደግሞ ከጎኔ ሆኖ ‹ምክርና ቡጢ ለሰጭው ይቀላል› ይላል፡፡ ልቤ እንደ ጾም ፍርፍር ፍርስ ልትል ነው፡፡

በተስፋ፣ ከታች ወደ ላይ

ተመስገን የተራራው መጨረሻ ላይ ደረስኩ፡፡ የቀደሙኝን ሁሉ መንገዱ ዳር መኪናው ጋ አገኘኋቸው፡፡ ጫማየን አውልቄ በፌስታል ጠቅልየ መኪናው ላይ ጣልኩት፡፡ ከዚያም ወደ ኋላ ተመልሼ የመጣነውን ተራራ አየሁት፡፡ 
ሸለቆው ከሩቁ

ድካሙ ሲቀነስ ውበቱ አሁንም አለ፡፡ ከእኔ እናንተ ትበረታላችሁና ሰነቦን እዩት፡፡ በተለይ ከአኩስምና ላሊበላ በጎንደርና ባሕርዳር በኩል የምትመጡ ተጓዦች ጎራ ብትሉ ቅርብ ነው፡፡ ሌሎቻችሁም ዛሬ ሄዳችሁ ነገ መምጣት ትችላላችሁና ተነሥታችሁ ሂዱ፡፡ ውጣ ውረዱ ራሱ እንዴት ልዩ ትዝታና በረከት መሰላችሁ፡፡ ደኅና እንሰንብት፡፡
ተራራው ላይ ደረስን


ደጋግመን ብናወራ፤ብንቋሰል፤ደጋግመን እዬዬ ብንል ለሀገራችን ጠብ የሚል ነገር የለም ! እርግማን ነው ! ደጋግመን በመሳደብ፣ደጋግመን በማማት ምንም አላፈራን ! መሬት ላይ ያለው ችግር አሁንም መሬት ላይ ነው፡፡ የማይወራ ወሬ፣ የማይሰደብ ስድብ፣ የማይቀርብ ሃሳብ የለም፡፡ ችግሩ ግን ወሬ የትም አያደርሰንም፡፡ እፎይ ያሰኘናል – ከምን ? ከትግል ! በወሬ ወጣልና ! ልክ ልካቸውን ነገራቸው ! ብለን ለጥ […]

መስከረም ፩(አንድ)ቀን ፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአሉ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየተከበረ መሆኑን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። ኢትዮጵያውያን ስልክ በመደወል የመልካም ምኞት መግለጫ መልእክቶችም አስተላልፈዋል ከበአሉ ጋር በተያያዘ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች መከናወናቸውን  የደረሱን መረጃዎች ያሳያሉ። በበአሉ ዋዜማ ወቅት ከፍተኛ አደጋ የታየው በጋምቤላ ክልል በጎደሬ ዞን በጎሸም ቀበሌ ሲሆን፣ የመዠንገር ብሄረሰብ አባላት 9 ሰዎችን ገድለዋል። ግጭቱ አሁንም ድረስ …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

መስከረም 1 ቀን ለኢትዮጵያውያን የአዲስ ዓመት መባቻ በመሆኑ ፣ በያመቱ ሲከበር የኖረና፣ የሚኖር ርእሰ ዐውደ ዓመት ነው። ለዩናይትድ ስቴትስ ደግሞ ፤ ከመስከረም 1 ቀን 1994 ዓ ም አንስቶ በያመቱ ፣

መስከረም 1 ቀን ለኢትዮጵያውያን የአዲስ ዓመት መባቻ በመሆኑ ፣ በያመቱ ሲከበር የኖረና፣ የሚኖር ርእሰ ዐውደ ዓመት ነው። ለዩናይትድ ስቴትስ ደግሞ ፤ ከመስከረም 1 ቀን 1994 ዓ ም አንስቶ በያመቱ ፣

እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ ፤ እንቁጣጣሽ በየዓመቱ ያምጣሽ ብለናል በድጋሚ፤ ለመሆኑ የዘመን መለወጫ እንቁጣጣሽ ትርጉሙ ምን ይሆን ፤ በክብረ በዓሉ ወቅት የሚከናወኑትስ ሃይማኖታዊ ባህላዊ ማህበራዊ ክንዋኔዎችስ እንዴት ይታያሉ፤

እንኳን ከዘመን በሰላም አሸጋገራችሁ አሸጋገረን እንኳን ለአዲሱ 2007 ዓመት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን። ዶቼ ቬለ የአማርኛዉ አገልግሎት ለመላዉ ኢትዮጵያ ህዝብ አዲሱ ዓመት የጤና የሰላም እና የፍቅር ዓመት እንዲሆን ይመኛል።

ራስ መንገሻ ስዩም ጉልህ ሚና ይዘዋል:: በኢትዮጵያ ከቀን ወደ ቀን እየከረረ የሚሄደው የጥላቻ ደረጃ ያሳሰባቸው “የህወሃት ወዳጆች” ህወሃት ለእርቅ እንዲነሳሳ የማግባባት ስራ እየሰሩ መሆናቸው ተሰማ። የአቶ መለስና “የህወሃት ወዳጅ” ወይም ቅርብ ናቸው የሚባሉት ራስ መንገሻ ስዩም ጉልህ ሚና ይዘዋል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ተባባሪዎች እንደዘገቡት ከሆነ በህወሃት መንደር እርቅ አስፈላጊ እንደሆነ የሚያምኑ ወገኖች በህወሃትና በተቀረው ህዝብ […]

በቦስተን እና አካባቢዋ ነዋሪ የሆኑት ኢትዮጵያውያን የ2007 አዲስ ዓመት በይኸው በዓል ሴፕቴምበር 6 ቀን 2014 ዓ. ም ወተር ታውን በሴይንት ጀመስ አርመኒያን አፖስቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ በጣም እጅግ በርካታ ሕዝብ በተገኝበት በድምቀት ተከበሯል። በእለቱም የኢትዮጵያውያን ወዳጅ የሆኑት የማሳቹሴትስ ስቴት ሴናተር የሆኑት የተከበሩ ሴናተር ዊል ብርውንበርገር በክብር እንግድነት መገኘታቸው ታውቋል:: በዓሉን በተመለከተ ወ/ሮ ገነት መሰለ የበዓል […]

ባለፈው ሳምንት በማህበራዊ ሚዲያው ‹‹ጥቁር ሳምንት›› (black week) በሚል ለአምስት ቀናት ዘመቻ (campaign) መካሄዱ ይታወሳል፡፡ በዚያ የጥቁር ሳምንት ዘመቻ ወቅት በመጨረሻው ቀን አስተባባሪዎቹ አዲስ አመትን በማስመልከት ‹አዲስ አመት በዓልን ከነጻነት ታጋዮች ጋር› በሚል የታሰሩ የነጻነት ታጋዮች እንዲጠየቁ ጥሪ መተላለፉ አይዘነጋም፡፡ በመሆኑም የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችና የነገረ ኢትዮጵያ ዝግጅት ክፍል ጳጉሜ 5 ቀን 2006 ዓ.ም በቂሊንጦ የሚገኙ የዞን 9 የጡመራ ቡድን አባላትንና የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን በመጠየቅ የዘመቻውን አካል አከናውነዋል፡፡ ቀጥሎም የጥቂት እስረኞችን መልዕክት በአጭር በአጭሩ አቅርበናል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ነቢዩ ሲራክ

አዲስ የነበረውና ዛሬ ገና 12 ወር 5 ቀኑያረጀ ያፈጀየምንለው 2006 ዓ.ም ለመገባደድ ጥቂት ሰአታት ብቻ ነው የቀሩት 2006 ዓ.ም በሳውዲ ለምንገኝ ኢትዮጵያውያን ልዩ የማይጠፉ ትዝታዎቸን አስተናግደንበታል

* ፍጹም የማይረሱኝ ትዝታዎች
በ2006 ተከስተው የማይረሱኝ የተለያዩ ክስተቶች እና አስደሳችና መራራ ትዝታዎች ብዙ ቢሆኑም የተጨመቁትንና ፍጹም ከአዕምሮየ የማይጠፉት በአዲሱ አመት መግቢያና በአሮጌው አመት መሸኛ የመጨረሻ ሰአታት ላድታውሳቸው ግድ አለኝ …

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይህ አመት አንደተለመደው አይነት አመት ቢሆን ኖሮ በዚህ ወቅት የዞን9 ጦማርያን በጦማሪት ማህሌት አስተባባሪነት ፣ በአጥናፍ ብርሃኔ እና በጆማኔክስ ካሳዬ ትብብር የአመቱን ታላላቅ ክስተቶች አሰባስበው ከመታተሙ በፊት ለቡድኑ ክለሳ የሚያቀርቡበትና የተረሱ እና ለክስተትነት የማይበቁ የምንላቸውን ሁነቶች የምንለይበትና የአመቱን የጊዜ መስመር የምናወጣበት ወቅት ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ባለፉት ወራት የአገር ቤቶቹንም ሆነ ውጪ ያሉትን የሚዲያ አውታሮች በተለያየ መልክ ያነጋገረው የበአሉ ግርማ አሟሟት ላለፉት 30 አመታት ሲያነታርክ ቆይቶአል ። እስከደርግ መጨረሻ ድረስ በድብቅ ፤ ከዚያ በኋላ ደግሞ በግልፅ አነታርኳል ። ይህም የሆነው በሁለት ምክንያቶች ነው ። አንደኛው ምክንያት በአሉ ግርማ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ስነ-ፅሁፍ አቻ የማይገኝለት ደራሲ በመሆኑና በብዙ አንባቢዎቹ ልብ ውስጥ ልዩ ቦታ […]

ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉእላዊነት የ 2006 ዓ/ም ዘመነ ማርቆስ ተገባዶ ወደ 2007 ዓ/ም ዘመነ ሉቃስ እንካን በሰላም አሸጋገረን በማለት አዲሱ ዘመን የሰላም ‘የደስታና የብልፅግና ኣመት እንዲሆንል በማለት ለመላ የኢትዮåያ ህዝቦች የመልካም ምኞት መግለጫውን ያቀርባል ፡፡ ኣዲሱ ኣመት የሰላም ‘የደስታና የብልፅግና ኣመት እንዲሆንልን ማደረግ በኛው ኢትዮåያውያን ዜጎች እጅ ነው፡፡ አዲሱ ዓመት የሰላም ፣ የደስታና የብልፅግና ዓመት […]

የሕወሐት ታጋይ ጄ/ል ዮሃንስ ገ/መስቀል ቦሌ ቴሌ መድሃኒያለም ባለ6 ፎቅ ህንፃ እንዳስገነቡ የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። ከ95ሚሊዮን ብር በላይ በሚደርስ ወጪ እንደተገነባ የተነገረለት ይኸው ባለ6 ፎቅ ዘመናዊ ህንፃ ለተለያዩ የግልና የመንግስት ባንኮች፣ ኢንሹራንስ ድርጅቶች፣ ንግድ ቤቶችና የተለያዩ ድርጅት ቢሮዎች እንደተከራየ የጠቆሙት ምንጮቹ በወር ከ2.1 ሚሊዮን ብር የሚገመት ኪራይ ጄኔራሉ እንደሚሰበስቡ አስታውቀዋል።

ሌ/ጄ ዮሃንስ በግላቸው ባለ6 ፎቅ ዘመናዊ ህንፃ በከፍተኛ ወጪ በማስገንባትና ከፍተኛ የኪራይ ሂሳብ በየወሩ በመሰብሰብ ከሌሎቹ በቢዝነስ ከተሰማሩ የሕወሐት/ኢህአዴግ ጄኔራል መኮንኖች የተለየ እንደሚያደርጋቸው ምንጮቹ አመልክተዋል። በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የመረጃ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሆነው ለረጅም አመታት ሲሰሩ የቆዩት የህወሐቱ ጄኔራል ዮሃንስ ገ/መስቀል ከ1995ዓ.ም ጀምሮ ከጄ/ል ሳሞራ የኑስ ጋር የከረረ ቅራኔ ውስጥ ገብተው እንደቆዩና በሁለቱ የህወሀት ጄኔራሎች መካከል የተፈጠረው ቅራኔ እየተባባሰ ሄዶ ጄ/ል ዮሃንስ ከሃላፊነት እንዲነሱ መደረጉን ያስታወሱት ምንጮቹ የሁለቱ ቅራኔ ሙስናን መሰረት ያደረገ እንደነበረ አስረድተዋል።

(በወቅቱ ስለግጭታቸውና መለስ ዜናዊ ዘንድ ቀርበው ስለተነጋገሩት በኢትኦጵ ጋዜጣ መረጃው ይፋ ተደርጐዋል) ጄ/ል ዮሃንስ ከመከላከያ ሃላፊነታቸው እንዲነሱ የተደረጉት በጄ/ል ሳሞራ መሆኑን ያስታወሱት ምንጮቹ በወቅቱ “ጡረታ” በሚል እንደተነሱና ሲነሱም በሜ/ጄኔራል ማእረግ እንደነበሩ አስታውቀዋል። በሙስና ባገኙት በመቶ ሚሊዮን የሚገመት ገንዘብ ሕንፃ ወደማስገንባት የግል ቢዝነስ የተሰማሩት ጄ/ል ዮሃንስ ከአራት አመት በኋላ በመከላከያ የሌተና ጄኔራልነት ማእረግ ባሳለፍነው ሰኔ ወር ተሰጥቷቸው በደቡብ ሱዳን የሚሰማራውን የተመድ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት በጦር አዛዥነት እንዲመሩ መመደባቸው አስገራሚ ነው ያሉት ምንጮቹ ምክንያቱም ጡረታ ተብለው የተሰናበቱት ዮሃንስ የሌተና ጄኔራል ማእረግ እድገት ተሰጥቷቸው መመለሳቸው በመከላከያ ታሪክ የመጀመሪያው ሊያደርጋቸው ስለሚችል ግርምት ሊፈጥር ችሏል ብለዋል። ዮሃንስ የአገር መከላከያ ሚ/ር የሌ/ጄኔራል ማእረግ እንዲሰጣቸውና በተመድ እንዲመደቡ የተደረገው በአሜሪካ ትእዛዝ መሆኑን ምንጮቹ አመልክተዋል። በቦሌ ለንደን ካፌ ፊት ለፊት ዘመናዊ መኖሪያ ካስገነቡት ጄኔራሎች አንዱ ናቸው።

(በፎቶው ጄ/ል ዮሃንስ ገ/መስቀል)

የመብት፣ የዲሞክራሲ ፣ የሕግ የበለይነት፣ የነጻነትና የፍትህ ጥያቄ የጥቂት «ፖለቲከኞች» ወይም የፖለቲክ ፓርቲ መሪዎች ብቻ ጥያቄ አይደለም። የሚሊዮኖችም እንጂ። መብታችንን አስረግጠን፣ ልእልናችንን አስደፍረን፣ በአገራችን እንደ ባሪያ የምንኖር ጥቂቶች አይደለንም። «የምትናገሩትን እኛ ነን የምንነግራችሁ። የሚጠቅማችሁን እኛ ነን የምናውቅላችሁ።በዚህ ሂዱ ስንላችሁ ትሄዳላችሁ፣ በዚህ ዉጡ ስንላችሁ ትወጣለች..» እያሉን፣ የግፍ ቀንበር በላያችን ላይ ጭነው፣ እኛ የኑሮ ዉድነት እያቃጠለን፣ እነርሱ […]

በመሳሪያ ኃይልና በውጭ መንግሥታት ድጋፍ የስልጣን እርካብ የተቆናነጠጠው፤ በጠባብ ብሄርተኛው በህወሓት ፍጹም የበላይነት የሚመራው፤ የኢህአዴግ መንግሥት ከተመሰረተበት ጀምሮ የኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት፤ ደህንነትና ነጻነት፤ የዘጠና አራት ሚሊዮን ሕዝቧ ሉአላዊዊነት፤ እውነተኛ እኩልነት፤ ማህበራዊ ጥቅም፤ መሰረታዊ ትብብር፤ ነጻነትና ዲሞክራሳዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ ተናግተዋል፤ ተገፈዋል። በማንኛውም የዘመናዊነት መስፈርት ቢፈረጅ፤ ኢትዮጵያን ከባሰ አደጋ፤ ሕዝቧን ከከፋ ድህነት እና የእርስ በርስ ግጭት፤ ወጣቱን ትውልድ ለሁላችንም ከሚያሳፍር ስደተኛነትና ውርደት ሊያድነው የሚችለው ተተኪ የአገዛዝ ስርአት (አማራጭ) በሕግ የበላይነት፤ በእውነተኛ የኢትዮጵይያውያን እኩልነት፤ በሕዝብ ስልጣን የተመሰረተ ዲሞክራሳዊ አገዛዝ ብቻ ነው። ሰፊ ለም መሬት፤ ዝናብ፤ ወንዝ፤ ተስማሚ አየር፤ ከመሬት በታች ገና የማይታወቅ ሃብት ያላት አገር ለሁሉም አስተናጋጅ ለመሆን እንደምትችል አልጠራጠርም። ፍትህ-ርትእ ከሌለ ይኼን የማይገኝ ሃብት የሚጠቀሙበት የውጭ ኢንቬስተሮችና አጋር የሆኑ የውስጥ ሃብታሞች ሆነው ይቆያሉ። ገዢው ፓርቲና ተቃዋሚዎች የሚስማሙበት አንድ አበይት ጉዳይ አለ። ይኼውም ዲሞክራሳዊ አማራጭ አስፈላጊ ነው የሚል። ከጽንሰ ሃሳብ ባሻገር ግን ሁለቱም ወገኖች ዲሞክራሳዊ አሰራርን በተግባር አላሳዩም፤ ለማሳየትም የተዘጋጁ አይመስልም። አንዱ በሌላው እያመኻኘ ሃያ ሶስት ዓመታት አልፈዋል። የሚቀጥለው ምርጫ ዘጠኝ ወሮች ቀርተውታል። ሑኔታው ከቀጠለ የሚቀጥለው ምርጫ ከአሁኑ ተወስኗል ለማለት እንችላለን፤ የገዢው ፓርቲ የበላይነት ብቻ ይሆናል። መቶ በመቶ አሸነፍኩ ቢል አንገረም። የሚወዳደረው ከራሱ ጋር ይሆናል።

ገዢው ፓርቲ መከፋፈልን ወደ ሳይንስ ለውጦታል። ተቃዋሚው ይኼን ሳይንስ አልቀበም በማለት ፋንታ እርስ በርሱ መናከሱን ቀጥሎበታል። በተደጋጋሚ የሚታየው የራእይ፤ የግብ፤ የአደረጃጀትና የአመራር ደሃነት በቀላሉ አለመፈታቱ ተቃዋሚውን ፍሬ ቢስ አድርጎታል። በአገር ውስጥ ብቻ ያለው ሳይሆን በውጭም ያለው፤ በነጻነት ለመወያየትና አብሮ ለመስራት ገዢው ፓርቲ ሊቆጣጠረው የማይችለው። ቢቀበለውም ባይቀበለውም ተቃዋሚው የገዢው ፓርቲ አገልጋይ ሆኗል ለማለት ያስችላል። የምናውቀው የሃገሪቱን አስተዳደር በቋንቋ የቀየሰው አምባገነን መንግሥት ቆይታውንና የኢኮኖሚ ጥቅሙን ለማጠናከር ህዝብን እርስ በርሱ እንዲጋጭ፤ ተቃዋሚዎች እርስ በርሳቸው እንዲናከሱ በማድረግ ላይ ይገኛል። ይኼ የመከፋፈልና ስልጣንና ሃብትን የማስተማመኛ ስልት ከታወቀ፤ በአገር ቤትም ሆነ በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎች በሰከነ መንገድ አስበው፤ ተፈላልገው፤ ተከባብረው፤ “ተናበው”፤ በዋናው ዓላማ ላይ ተስማምተው ለመስራት የገዢው ፓርቲ ፈቃድ አያስፈልጋቸውም ነበር። ችግሩ ጥበባዊና ዘመናዊ በሆነ መንገድ የማደራጀትና የመምራት ድክመትና ክፍተት መኖሩ ነው። ስርዓቱ የራሱን መቆያ ያጠናከረውና የሚያጠናክረው የሃገሪቱን ባጀት፤ የተፈጥሮ ሃብትና ሌላ ጥሪት ለጥቂቶች አገልጋይ የሆነ ተከታታይ የብልጭልጭ እድገት በማሳየት፤ “እኔ እስካለሁ የእድገቱ ተጠቃሚዎች ትሆናላችሁ፤ እኔ ከሌለሁ፤ ትበላላችሁ” በሚል ዘዴ ነው።

ስርዓቱ የሚሰራውን ያውቃል ማለት ነው። የሚሰራውን የማያውቀው ተቃዋሚው ሆኗል። የተበታተነው ተቃዋሚ የሚለው በኢትዮጵያ እድገት የለም አይደለም። ፍትህ የለም። የአብዛኛው ሕዝብ ኑሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ታች በመሄድ ላይ ይገኛል፤ የኑሮ ውድነት የተራውን ዜጋ የመግዛት አቅም አስጊ በሆነ ደረጃ ቀንሶበታል። የወጣቱ ትውልድ እድል ተምሮ መሰደድ ሆኗል። በዘመነ ኢህአዴግ የሃገሪቱ ለም መሬትና ወንዝ ለውጭ ኢንቬስተሮች በእርካሽ ዋጋ ሲሰጥ ቆይቶ በአሁኑ ጊዜ አላሙዲ ብቻ የሚያመርተው በዓመት አንድ ሚሊዮን ቶን ሩዝ ለሳውዲ ገበያ ይቀርባል። እንደ ካሩቱሪ ያሉ የህንድ ኢኒቨስተሮችም የጋምቤላን ለም መሬት ተረክበው ምርታቸውን ለውጭ ገበያ ያቀርባሉ። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ እየተነገደባት ነው። ሳውዲዎች እየተመገቡ ብዙ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ይራባሉ፤ አገሪቱ በዓመት ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ለምግብ ግዢ ታወጣለች። ህይወቱ የተናጋው አብዛኛው ሕዝብ መብቱ ሰለታፈነ፤ ድምፁን ለማሰማት ስላልቻለ መከራውን ተቀብሎ ይኖራል ወዘተ የሚሉ ናቸው።

ስለሆነም፤ ተቃዋሚው የጠራ አማራጭ ለማቅረብ ነባራዊው ሁኔታ ይፈቅድለታል። የሚጎድለው የዓላማ አንድነትና የአመራር ብልሃት ነው። እርግጥ ነው፤ የገዢው ፓርቲ አቅም ከፍተኛ ነው። መንግሥትን ከተቆጣጠረ ባጀትንም እንደፈለገው ፈሰስ ለማድረግ ይችላል።

ስንቅ ብቻውን አቅም አይሆንም
የተቃዋሚው ክፍል አቅም ጠንካራ ሊሆን የሚችለው ከሕዝብ ከሚያገኘው ድጋፍ፤ ከመተባበሩ፤ ያለውን የቁሳቁስ አቅም በጋራ ከመጠቀሙ፤ በብልሃት ከመስራቱ፤ በአንድ ድምፅ ከመነሳቱ፤ ለዓላማው ጠንክሮ፤ በውስጥ አመራር ሳይበከል መስዋት ለመክፈል ፈቃደኛ ከመሆኑ ላይ ነው። በውጭ ያለው አገር ወዳድ፤ ዲሞክራትና የሰብአዊ መብቶች ጠበቃ ኃይል ያልተቆጠበ ድጋፍ ለማድረግ አቅምና ፍላጎት አለው። “ተባበሩ ወይንም ተሰባበሩ” እያለ ሲመክር ቆይቷል። ገንዘቡን፤ እውቀቱን፤ ድጋፉን ችሯል። ወደፊትም ይችራል የሚል እምነት አለኝ። ሆኖም፤ ስንቅ አቀባይነት ያለ ድርጅትና አመራር ብቃት ኢትዮጵያን አይለውጥም። ለዚህ ነው፤ ደጋፊዎች ተስፋ እየቆረጡ “ተቃዋሚ ነኝ” ማለቱን ቀልድ አታድርጉት፤ “ጩኸቱን ወደ ተግባር ለውጡት፤ በፍርሃትና በመጠላለፍ ዓለም መኖራችሁን አቁሙ፤ ነጻነት፤ ፍትህና ዲሞክራሳዊ ስርአት ያለ መስዋእትነት ስኬታማ ሊሆኑ አይችሉም። የእርስ በርስ ጦርነቱን አቁሙ። በውጭ ኃይሎች ማምለኩን አቁሙ። ድርጅት አፍርሳችሁ በድርጂት መተካቱን ተውት። አትጠላለፉ። መገናኛ ብዙሃኖችን ለእርስ በርስ ጦርነት አትጠቀሙ፤ አትወነጃጀሉ፡ የራሳችሁን የውስጥ አመራር ሳታጠናክሩ ሁሉን ነገር በገዢው ፓርቲና በሌላው ላይ አታመኻኙ፤ ተቃውሞ ብቻውን የማህበራዊ ጥቅም አይኖረውም” ወዘተ፤ ወዘተ የሚሉት።

በጀ፤ ታዲያ መፍትሄው ምንድን ነው?
ይኼ አጭር የፖለቲካ ኢኮኖሚ ስእል በተደጋጋሚ ያሳየው የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች ጥቃቅን ልዩነቶችን ወደ ጎን ትተው ለሃገሪቱ ዘላቂነት እና ለመላው ሕዝቧ ደህንነት ሲባል መተባበር፤ ቢቻል መዋሃድ አለባቸው የሚለውን ባለፉት አስር አመታት በተደጋጋሚ ሁሉን በሚመለከት ያቀርብኩትን ምክርና ጥሪ ነው። ምክር እንጅ ትእዛዝ አይደለም። ማንም ግለሰብ ወይንም ቡድን ከውጭ ሆኖ ትእዛዝ ለመስጠት አይችልም። ትግሉ በአገር ቤት ካልተጠናከረ፤ አገር አቀፍና አሳታፊ ካልሆነ የፈለገው ጥረት ቢደረግ ዲሞክራሳዊ መሰረት ለመጣል አይቻልም። የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገው አብሮና ተሳስቦ መኖርን ነው። ቂም በቀልነትን አይፈልግም። አንዱን አምባገነን በሌላ አምባገነን መተካት አይደፈልግም። ይኼማ ከሆነ ኢህአዴግ ምን አደረገ፤ የተካው ደርግ ምን አደረገ፤ አጼ ኃይለ ሥላሴስ ምን አደረጉ? የኢትዮጵያ ሕዝብ ራሱ የስልጣኑ፤ የመንግሥቱ፤ የመሪዎቹ ባለቤት ለመሆን ይፈልጋል። ለዚህ ብዙ መስ ዋት ከፍሏል። ስለሆነም፤ ሁሉም ተቃዋሚ ኃይሎች በዓላማ እንድነት በመንቀሳቀስ ታሪክ የሚጠይቀውን ሃላፊነት መወጣት አለባቸው። ሕዝብን ካጎለመሱ ተመጣጣኝ አቅም ይኖራቸዋል። ወሳኙ ሕዝብ ብቻ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ በምርጫ ዘጠና ሰባት ለቅንጅትና ለህብረት የሰጠው ያልተቆጠበ ድጋፍና የከፈለው መስዋእት እንዲያንሰራራ ከተፈለገ በአገር ቤትና ከአገር ውጭ የሚገኙ የፖሌቲካና የማህበረሰብ ድርጅቶች፤ የሞያ ስብስቦች፤ ግለሰሶብችና ሌሎች ከቡድን፤ ከፓርቲ፤ ከግል ዝናና ጥቅም በላይ ለኢትዮጵያ ዘላቂነትና ለመላው ስብጥር ሕዝቧ ደህንነት አብረው መነሳትና አምባገነኑን መንግሥት ማንበርከክ፤ ቢያንስ ለድርድር እንዲስማማ ማድረግ ይኖርብናል። ከሁሉም በላይ የተቀነባበረ የሕዝብ አመፅ አገር አቀፍና ዘላቂነት ባለው ደረጃ ከተካሄደ ገዢው ፓርቲ ለመደራደር ይገደዳል።

ይኼን ትንተና ለማዘጋጀት የተገደድኩበት ዋና ምክንያት የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት የለመደውን መንገድ እየተጠቀመ፤ ከመጭው ምርጫ በፊት በሰላማዊ መንገድና በሁለገብ ትግል የሚንቀሳቀሱና ተባብረው ለመስራት ፈቃደኛ የሆኑትን ተቃዋሚዎች ሁሉ ተባብረው እንዳይሰሩ በማሰብ በመከፋፈል ላይ ይገኛል። ይኼ አዲስ ነገር አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋ ጥሎበት የነበረው የመኢአድና የአንድነት ውህደት ሂደት አሳዛኝና ተስፋ በሚያስቆርጥ መልክ ስኬታማ አለመሆኑ ለገዢው ፓርቲ ቆይታ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርጓል። ይኼ ችግር የገዢው ፓርቲ ሳይሆን የተቃዋሚው ነው። በቅርቡ የተከሰተም ሌላ የተቃዋሚውን ክፍል ከጥያቄ ውስጥ ያስገባ አከራካሪ ጉዳይ አለ።

እንደማንኛውም አገር ወዳድ በ August 28, 2014 ሶስት በውጭ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ድርጅቶች በዜናና በድህረገጾች ያሰራጩትን፤ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ትኩረት የሰጡትን የጋራ መግለጫ በሰከነ መንገድ ተመልክቻለሁ። መግለጫው እንዲህ ይላል። “ኢትዮጵዮጵያንና ሕዝቧን ካሉበት አዘቅት በማውጣት ሕዝቡ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የጋራ ትግልና መስዋእትነት የግድ የሚለን ደረጃ ላይ መድረሳችንን፤ የወያኔን ቡድን በሁለገብ ትግል እየተፋለምን ያለን ድርጅቶች ተጣምሮና አንድ ሆኖ መታገል እንዳለብን ካመንን ዓመታት አስቆጥረናል። ስለሆነም፤ ወደፊት ለመዋሃድ የተሰማማነው ድርጅቶች፤

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር
የግንቦት 7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ
የአማራ ዲሞክራሳዊ ኃይሎች ንቅናቄ ነን” የሚል መግለጫ ወጥቶ ሲያነጋግር ቆይቷል።

ከአንድ ሳምንት በኋላ በ September 6, 2014, በኮሎኔል አለበል የሚመራው የአማራ ዲሞክራሳዊ ኃይሎች ንቅናቄ ማስተባበያ አውጥቶ “ከግንቦት 7 ጋር አልተዋሃድኩም” ብሏል።

በእኔ ግምትና እምነት ምንም እንኳን የጋራ ስምምነቱ በምን አጀንዳ ላይ እንደተቀረጸ ባላውቅም፤ አሰራሩ በግልፅነት፤ በሃላፊነት፤ በዲሞክራሳዊነት፤ በዘላቂነትና ሌሎችን በሚያበረታታ መንገድ የውህደቱ ድርድር እንዲካሄድ ያለኝን ተስፋና ምኞት ለማቅረብ እፈልጋለሁ። በተመሳሳይ፤ በአንድነትና በመኢአድም በውስጥና በመካከላቸው መካከል የተከሰቱ ልዩነቶችም በውይይት፤ በግልፅነት፤ በሃቀኝነት፤ በብልሃት፤ በዲሞክራሳዊ ስልት እንዲፈቱ የታሪክ አደራ እሰነዝራለሁ። ዛሬ ለፍትህ- ርትእ፤ ለህግ የበላይነት፤ ለሰብአዊ መብቶች መከበር፤ አገርን ከአደጋ ለመከካለክ፤ ለእውነተኛ እኩልነትና ለዲሞክራሲ የሚታገሉ ኃይሎች “ኢህአፓ፤ መኤሶን፤ እሴፓ፤ ፓሪስ አንድ፤ ፓሪስ ሁለት፤ ኢዲዩ፤ እዴፓ፤ ቅንጅት፤ ህብረት፤ ታንድ፤ ኦነግ፤ መድረክ፤ አሬና፤ ግንቦት 7፤ አርበኞች፤ የአማራ ዲሞክራሳዊ ኃይሎች፤ አንድነት፤ ሰማያዊ፤ መኢአድ፤ አንድ ሁለትና ሶስት ወዘተ የሚሉበትና እርስ በርስ የሚወቃቀሱበት ዘመን አልፏል ለማለት የሚያስችሉ ብዙ ክስተቶች አሉ። የኼን ስል፤ ሁላችሁም ተዋሃዱ ማለቴ አይደለም፤ ብዙ ተሞክሮ አለተቻለም። ዲሞክራሳዊ ለውጥ ከተፈለገ ለመተባበርና ለመደጋገፍ ይቻላል። ይኼም ፈቃደኛነት ካለ ብቻ ነው። “አገር ትሸጥ ሲባል ስንት ታወጣለች” የሚል አዲስ ባህልና አዲስ ባለሃብት መደብ መፈጠሩን እያየን እርስ በርሳችን የምንናከስ ከሆነ ከትግሉ ዓለም መውጣት አለብን። አዲሱ ትውልድ ለራሱ ህይወት ሲል ይታገልበት ለማለት መድፈር አለብን። በምትካችን አዲስ ትውልድና አዲስ ዓመራር እየታገለ አመራሩን እንዲይዝ ቦታውን እንልቀቅለት። መሰናክል አንሁን። መቀበል ያለብን፤ እኛ ራሳችን ለመምከር ወይንም ለመመከር ስለማንፈልግ ሌሎች፤ በተለይ ፈረንጆች ለእኛ ተናጋሪ ሆነዋል። ለምሳሌ፤ ለኢትዮጵያ የሚለግሱ መንግሥታትና ድርጅቶች ደጋግመው የሚነግሩን በአንድ ላይ፤ በአንድ ድምፅ ለመናገርና አግባብ ያለው አማራጭ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማቅረብ እስካልቻላችሁ ድረስ ማንም አያዳምጣችሁም ነው። ሃቁ፤ ያለውን መንግሥት እንደግፋለን ነው የሚሉት። የተበታተነ ተቃዋሚ ውጤቱ ይኼው ነው። አንፈረድባቸው። የሚያኮራ ታሪክ እያለን የራሳችን ህብረተሰብ ለመታገድ ካልቻልን ሌሎች ያዙብናል። እያዘዙብን ነው። ከዚህ የበለጠ የጠነከረ ምክር መጠበቅ ራስን ማታለል ነው።

ለማጠቃለ፤ በሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጭ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎች እንዲያስቡበት የምመኘውና አደራ የምለው የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት እድሜውን ለማራዘም ለሚያደርገው ያልተቆጠበ ሴራና ሰለባ ምርኮኛ መሆን የለባችሁም/የለብነም የሚል ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገውና የሚመኘው የእርስ በርስ መጠላለፍና ለስልጣን መሻማትን አይደለም፤ አብሮና ተባብሮ አምባገነኑን ስርዓት በዲሞክራሳዊ ስርዓት መተካትና ዘላቂነትና ፍትሃዊነት ያለው የእድገት በርና መሰረት እንዲከፈትለት ነው። ስለሆነም፤ የተቃዋሚዎች ሙሉ እምነት በኢትዮጵያ ሕዝብ አቅም ላይ ይሁን አላለሁ።

ለታሰሩ ብሎገሮችና ጋዜጠኖች፣ የአንድነት፣ የሰማያዊ፣ የመድረክ እንዲሁም ሌሎች የፖለቲክ ድርጅት መሪዎች አጋርነቱን፣ ሕዝቡ በነቂስ ይገልጽ ዘንድ ፣ የአዲስ አበባ የአንድነት ወጣቶች በአዲስ አበባ በሚገኝ ትልቅ አደባባይ ሕዝባዊ ስብሰባና የእስረኞች መታሰቢያ ፕሮግራም እንዳዘጋጁ ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል። በአማራጭነት ሁለት ትላልቅ አደባባይ ፣ ሕጉ በሚጠይቀው መሰረት ፣ ለአዲስ አበባ አስተዳደር ያቀረቡት የአንድነት ወጣቶች፣ ዝግጅቱን መስከረም 11 […]