ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት በድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ላይ ሊሰጥ የነበረውን ፍርድ ያራዘመ ሲሆን፣ ፍርዱ ለምን እንደተራዘመ ግን በግልጽ የታወቀ ነገር የለም። በአቶ አቡበከር አህመድ መዝገብ 18 የኮሚቴው አባላት በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው የመጨረሻውን ፍርድ ለመስማት ችሎት የተገኙ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ የክሱን …

ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመከላከያ ሰራዊት ያወጣው አዲስ የቅጥር ማስታወቂያ ተቀባይነት አለማግኘቱን ከተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በሰሜን ሸዋ ከሁለት ሳምንት በፊት የወጣውን የቅጥር ማስታወቂያ ተከትሎ ተመዝጋቢ በመጥፋቱ፣ የአካባቢው ባለስልጣናት የሚያደርጉት ጠፍቷቸዋል። በአርባምንጭ ደግሞ የኢህአዴግ ካድሬዎች በመኪና እየዞሩ ወጣቱ ለመከላከያ አባልነት እንዲመዘገብ እየቀሰቀሱ ነው። ይሁን እንጅ ለጥሪው ወጣቱ የሚሰጠው ምላሽ …

ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ መንግስት ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ በማንኛውም መልኩ የህግ ትምህርት በግል ተቋማት እንዳይሰጥ የከለከለ ሲሆን፣ የአቶ ደመቀ ከፊል ንብረት የሆነው ሚሸከን ኮሌጅ ግን ተማሪዎችን እያሰተማረ እንደሚገኝ መረጃዎች አመልክተዋል። ተመሳሳይ ድርጊት የፈፀሙ ኮሌጆች ቢዘጉም፣ ለሚሽከን ኮሌጅ ግን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት ጥራት ኤጀንሲ ከማሰጠንቀቂያ ያለፈ ውሳኔ አልሰጠውም። የሚሽከን ኮሌጅ …

ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኔ 19 ቀን 2007 ዓም ከጧቱ 1 ሰአት ላይ መድሃኒአለም በሚባል አካባቢ ሁለት መኪኖች ኮንትሮባንድ እቃ ጭነዋል በሚል ምክንያት ሲከተሉዋቸው የነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት በድንገት ተኩስ በመክፈታቸው አንደኛው መኪና መስመሩን ስቶ ከወጣ በሁዋላ በመገልበጡ 7 ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎች ደግሞ ተጎድተው ሆስፒታል ገብተዋል። …

በርካታ ድርጅቶች በግል ጡረታ አዋጅ ማሻሻያ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ለፓርላማ አቀረቡ

በርካታ የግል ድርጅቶችና የሲቪክ ማኅበራት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቀረቡ፡፡ የምክር ቤቱ የማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ማሻሻያውን አስመልክቶ

ባዘጋጀው የሕዝብ አስተያየት መስጫ መድረክ ላይ የተጋበዙ ከ300 በላይ የሚሆኑ የግል ድርጅቶችና ሲቪክ ማኅበራት፣ ማሻሻያውን ያረቀቀው የግል ድርጅት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ባለድርሻ አካላትን ሳያነጋግር ወይም ሳያወያይ ይህንን ረቂቅ ማሻሻያ ለፓርላማ ማቅረቡ ፍፁም ተገቢ አይደለም ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ 

በዋናነት ከተካተቱት ማሻሻያዎች መካከል በግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 715/2003 ቀደም ሲል የፕሮቪደንት ፈንድ ሥርዓት በፈቃደኝነት እንዲቀጥል ቢወሰንም፣ በማሻሻያው ግን ወደ ግል ሠራተኞች ጡረታ ፈንድ ይዞራል የሚለው ይገኝበታል፡፡ 

ይህ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ከቀረበ በኋላ ግን አርቃቂው አካል የግል ድርጅት ሠራተኞች ማኅበራዊ ኤጀንሲ ማሻሻያውን በድጋሚ በማየት ፕሮቪደንት ፈንዱ በቀጥታ ይዞራል ወይም የተጠራቀመው ገንዘብ ወደ ጡረታ ፈንድ ይገባል የሚለው እንዲስተካከል ማድረጉን የኤጀንሲው የሥራ ኃላፊዎች በውይይቱ መጀመርያ ላይ ተናግረዋል፡፡ 

በውይይቱ እንዲገኙ የተጋበዙት ድርጅቶች በሙሉ ሠራተኞቻቸውን በፕሮቪደንት ፈንድ ዋስትና የሚያስተዳድሩ በመሆናቸው፣ በመጀመርያ እፎይታቸውን ገልጸዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አረጋ ይርዳው ይገኙበታል፡፡ 

‹‹ይህንን ማሻሻያ በመስማቴ ደስ ብሎኛል፤›› ያሉት ዶ/ር አረጋ መንግሥት ስለ ግል ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና ማሰብ ከመጀመሩ በርካታ ዓመታት ቀደም ብሎ፣ የግል አሠሪዎችና ሠራተኞቻቸው ተነጋግረው ፕሮቪደንት ፈንድ ሥርዓትን መፍጠራቸውን አስታውሰዋል፡፡ 

‹‹ስለዚህ ፕሮቪደንት ፈንድ የአሠሪና የሠራተኛው የግላቸው ነው፡፡ ማንም ሌላ ሰው ሊወስንበት አይችልም፤›› ብለዋል፡፡ በዚህም መልክ መወሰኑን ጥሩ ነው ብለዋል፡፡

ሲአርዲኤ የተባለው የሲቪክ ማኅበራት ጥላ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶ/ር መሸሻ ሸዋረጋ፣ በተመሳሳይ የማሻሻያ አዋጁ አርቃቂዎች ባለድርሻ አካላትን አወያይተናል በማለት ያቀረቡት ሪፖርት ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡ 

በሲአርዲኤ ሥር ከ350 በላይ ሲቪክ ማኅበራት የሚገኙ መሆኑንና ኢትዮጵያ ከዚህ ዘርፍ በዓመት ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደምታገኝ አስታውሰው፣ ይህንን ዘርፍ እንደ ባለድርሻ አካል ሳያወያዩ ሪፖርት ማድረግ ተገቢ አለመሆኑን ጠቁመዋል፡፡ 

የአዋጁ አርቃቂዎች ባለድርሻ አካላትን አወያይተናል የሚሉት የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽንና የአሠሪዎች ፌዴሬሽን ነው፡፡ 

‹‹ዛሬ በድፍረት መናገር ያለብኝ ይመስለኛል፡፡ እነዚህ ተቋማት እንደማይወክሉን ታውቃላችሁ፡፡ እንዲያውም ለመንግሥት ነው የሚሠሩት፤›› ሲሉ ዶ/ር አረጋ ይርዳው ተችተዋል፡፡ 

ዶ/ር መሸሻ ፕሮቪደንት ፈንድን በቀጥታ ወደ ጡረታ እንዳይዞር በመጨረሻ መወሰኑን ተቀብለዋል፡፡ ‹‹ይሁን እንጂ ፕሮቪደንት ፈንድ ምንም እንዳልሠራ መቆጠር የለበትም፡፡ በ2003 ዓ.ም. እንደተፈቀደው ሁሉ አሁንም በሠራተኞች ምርጫ ሊቀጥል ይገባል፤›› ብለዋል፡፡ 

የሲቪክ ማኅበራት ፀባይ ከሌሎቹ ስለሚለይ ሠራተኞች የሚቆዩት ፕሮጀክቶች እስካሉ ድረስ ብቻ ስለሆነ፣ ፕሮጀክቶች ሲያበቁ እንደሚሰናበቱ አስታውሰዋል፡፡ 

ዶ/ር መሸሻ ሠራተኞች በሚሰናበቱበት ጊዜ ለሥራ መፈለጊያም ሆነ ቤተሰቦቻቸውን ማስተዳደሪያ ሆኖ የሚያገለግለው ፕሮቪደንት ፈንድ በመሆኑ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡ ምክንያቱም እንደ ሌላው አገር ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ‹ኢምፕሎይመንት ፈንድ› ወይም ሥራ አጥ በሚኮንበት ወቅት የኑሮ ዋስትና አለመኖሩን ጠቅሰዋል፡፡ ‹‹እኛ አገር ይህ ባለመኖሩ ፕሮቪደንት ፈንድን ይዞ መቀጠል ምን ችግር አለው?›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ 

የሴንተር ፎር ዲስኤቢሊቲስ ዴቨሎፕመንት ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ የትነበርሽ ንጉሤ በበኩላቸው፣ ‹‹የፕሮቪደንት ፈንድ ሊቀጥል ይገባል፡፡ ምክንያቱም በተለይ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን የሚያበረታታ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ወጣቶች እስከ 60 ዓመት ዕድሜያቸው በተቀጣሪነት ቆይተው የጡረታ ተከፋይ እንዲሆኑ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡ 

የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤትን ወክለው የተገኙት የሕግ ባለሙያው አቶ ዮሐንስ ወልደ ገብርኤል፣ ‹‹የፕሮቪደንት ፈንድ ማኅበራዊ ዋስትና ሥርዓት የራሱ ደካማ ጎኖች አሉት፡፡ እነዚህ ደካማ ጎኖች ግን መንግሥት ለፕሮቪደንት ፈንድ ጥበቃ ለመስጠት ኃላፊነት ባለመውሰዱ የተከሰቱ ችግሮች እንጂ የግሉ ዘርፍ የፈጠረው አይደለም፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ፕሮቪደንት ፈንድ ለግሉ ዘርፍ ትልቅ ዋስትና ነው፡፡ አሠሪው ለሠራተኛው ዋስትና እንዲኖረው የሚያደርግ ነው፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ምክትል ፕሬዚዳንት በበኩላቸው፣ ኮንፌዴሬሽኑ ከኤጀንሲው ጋር በተወያየበት ወቅት ፕሮቪደንት ፈንድን በተመለከተ ኮንፌዴሬሽኑ ያቀረበው ሐሳብ የጡረታ ዐቅድ እየሰፋ በሄደ ቁጥር ፕሮቪደንት ፈንድ እየተዋጠ እንደሚሄድ፣ በመሆኑም በራሱ ጊዜ ሊሞት ስለሚችል መነካካት አያስፈልግም የሚል እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ 

አሁንም ቢሆን ፕሮቪደንት ፈንድን የማይፈልጉ ድርጅቶች ብቻ ወደ ጡረታ በምርጫቸው እንዲመጡ መደረግ እንዳለበት ኢሠማኮ እንደሚያምን ተናግረዋል፡፡ ሌሎች በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ግለሰቦችም ፓርላማው ይህንን አዋጅ በዚህ ዓመት ሊያፀድቀው እንደማይገባ ተከራክረዋል፡፡ 

ይህንን ያሉበት ምክንያት የረቂቅ አዋጁ አንቀጽ 19 ላይ የተደረገው ማሻሻያን በመቃወም ነው፡፡ አንቀጹ ‹‹በተቀጠረ ሦስት ዓመት ወይም ከዚህ ባነሰ ጊዜ ውስጥ በጡረታ የሚገለል ሠራተኛ፣ በጡረታ ከሚገለልበት ወር ሦስት ዓመት አስቀድሞ ባለው ወር ሲከፈለው ከነበረው መደበኛ የወር ደመወዝ በ25 በመቶ የሚበልጥ ዓመታዊ አማካይ የደመወዝ ጭማሪ ያገኘ እንደሆነ፣ በየዓመቱ 25 በመቶ ያለው የደመወዝ ጭማሪ ብቻ በደመወዙ ላይ ተደምሮ የሦስት ዓመት አማካይ የወር ደመወዙ ተይዞ ይታሰባል፤›› ይላል፡፡ 

ይህንን የተቃወሙት የድርጅት ተወካዮቹ አገሩን በዝቅተኛ ደመወዝ ሲያገለግሉ የነበሩ የመንግሥት ሠራተኞችን፣ ወታደሮችንና የመሳሰሉትን የሚጎዳ ነው ሲሉ ተቃውመዋል፡፡ በዕድሜው መጨረሻ ላይ የተሻለ ገንዘብ ቢያገኝ ለአገሩ ያበረከተውን በገንዘብ የማይለካ አስተዋጽኦ ወደጎን በመተው፣ 25 በመቶ ጭማሪውን ብቻ ማሰብ ተገቢ አይደለም በማለት ተቃውመዋል፡፡ 

የኤጀንሲው የሕግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግርማ ሲሳይ ፕሮቪደንት ፈንድን በተመለከተ በሰጡት አስተያየት፣ ፕሮቪደንት ፈንድ ዘለቄታዊ ማኅበራዊ ዋስትና መሆን አይችልም ብለዋል፡፡ 

‹‹የፕሮቪደንት ፈንድ ገንዘብን የወሰደ ሠራተኛ ገንዘቡ ካለቀበት አለቀበት ነው፡፡ በማኅበራዊ ዋስትና (በግል ጡረታ) ቢታቀፍ ግን አሥር ዓመት ብቻ አገልግሎ ዕድሜ ልኩን እስከነ ተተኪዎቹ ሚስቱንም ጨምሮ ዕድሜው ስልሳ ዓመት ከደረሰ በኋላ ማግኘት ይችላል፤›› ብለዋል፡፡ 

አንቀጽ 19 ላይ የተደረገውን ማሻሻያ በተመለከተ በሰጡት አስተያየት፣ አንድ ሠራተኛ በመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ ከ25 ዓመት በላይ ያገለግልና በ25/55 የጡረታ መብት መሠረት በአምስት ሺሕ ብር ጡረታውን አስከብሮ፣ ቀሪውን ዕድሜ ማለትም አምስት ዓመቱን በግል ድርጅት በወር እስከ 30 ሺሕ ብር ቢቀጠር አጠቃላይ የጡረታ አበሉ የሚሰላው በ30 ሺሕ ብር ደመወዝ ተመን ነው፡፡ ያላዋጣውን በመብላት ፈንዱን የሚያደርቀው በመሆኑ ገደብ ሊጣልበት የሚገባ ነው ብለዋል፡፡ 

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ፀጋዬ ገብረ ሚካኤል በበኩላቸው፣ ማኅበራዊ ዋስትናን በተመለከተ በየትም አገር ስምምነት ኖሮ እንደማያውቅ ገልጸዋል፡፡ በኋላ ላይ የኅብረተሰቡን ዋስትና ማስከበር የመንግሥት ኃላፊነት በመሆኑ ኃላፊነቱን እንደሚወጣ ተናግረዋል፡፡ 

የፓርላማው የማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ፣ ከውይይቱ በርካታ ቁም ነገሮችን መገኘታቸውን፣ ለፓርላማ የቀረበ ነገር ሁሉ እንደማይፀድቅ፣ በተደረገው ውይይት ላይ በድጋሚ በመነጋገር ተጨማሪ የሕዝብ ውይይት ካስፈለገም ሊጠራ እንደሚችል አስረድተዋል፡፡ 

 

አዳዲስ የፋይናንስ ድጋፎች በሚጠበቁበት ፎረም የቻይና ባለሥልጣናትና ኩባንያዎች ታድመዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝን ጨምሮ የቻይናና የኢትዮጵያ መንግሥታት የፋይናንስና የኢኮኖሚ ሚኒስትሮች፣ የዓለም ባንክና የሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎችና ኢንቨስተሮች የተገኙበት ፎረም፣ ቻይና በአፍሪካ

ስለምታካሂደው የኢንቨስትመንትና የንግድ ልውውጥ እየመከረ ነው፡፡ አዳዲስ ስምምነቶችና የፋይናንስ ድጋፎች ይፋ እንደሚደረጉበት ይጠበቃል፡፡ 

‹‹ኢንቨስቲንግ ኢን አፍሪካ ፎረም›› በሚል ስያሜ የመጀመሪያውን ጉባዔ በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም እንዳስታወቁት፣ በአፍሪካ ከ2,200 ያላነሱ ኩባንያዎች በተለያዩ መስኮች ኢንቨስት አድርገዋል፡፡ በኢትዮጵያም ኋጂዬን ግሩፕ የተባለው ጫማ አምራች 3,500 ሠራተኞችን በመቅጠር፣ በዓመት ሁለት ሚሊዮን ጫማዎችን በማምረት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ 

ከካቻምና ጀምሮ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ካደረጉ የውጭ ኩባንያዎች የሚገኘው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት 1.2 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የቱርኩ አይካ አዲስን ጨምሮ የታይዋኑ ጆርጅ ሹ ኩባንያና ሌሎችም ሥራዎችን እያስፋፉ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል፡፡ አዳዲሶቹ ፒቪኤችና ኤችኤንድኤም የተባሉ ትልልቅ ኩባንዎች ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውም፣ በዓመት 13 በመቶ እያደገ ለሚገኘው አምራች ኢንዱስትሪው ትልቅ ተስፋ እንደሆነ አቶ ኃይለ ማርያም ተናግረዋል፡፡ 

የቻይና ምክትል የፋይናንስ ሚኒስትሯ ሊዩ ዢያንሁዋ፣ እንዲሁም የቻይና ልማት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዩዋን ሊ ባደረጉት ንግግር፣ አገራቸው ከአፍሪካ ጋር ያላትን የንግድና የኢንቨስትመንት ትስስር ለማጠናከር እንደምትፈልግ አስታውቀዋል፡፡ በተለይ ዩዋን ሊ እንዳሉት፣ ባንካቸው በ34 የአፍሪካ አገሮች ውስጥ በቻይና-አፍሪካ ልማት ፈንድ በኩል እ.ኤ.አ. በ2006 በ82 ፕሮጀክቶች ላይ ኢንቨስት ካደረገው የ3.15 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ በተጨማሪ፣ 16 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት የማድረግ ሐሳብ አለው፡፡ ይህም ወደ አፍሪካ የሚመጣውን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለማሳደግ፣ የአፍሪካን የወጪ ንግድ በየዓመቱ በሁለት ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ፣ እንዲሁም የታክስ ገቢንም በአንድ ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡ በአንፃሩ እስካሁን በቻይና ኩባንያዎች አፍሪካ ውስጥ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት አማካይነት የተመዘገበው አራት ቢሊዮን ዶላር መሆኑን የገለጹት ምክትል ፕሬዚዳንት ሊ፣ የሁለትዮሽ ንግዱ ግን 222 ቢሊዮን ዶላር ማስመዝገቡን ጠቅሰዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ አብዛኛው ከቻይና ወደ አፍሪካ የሚገቡ ሸቀጦች የሚሸፍኑት መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ 

በኢትዮጵያ ቻይናውያን ያስመዘገቡት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በሚመለከት የዓለም ባንክ ካቻምና አካሂዶት በነበረው ጥናት መሠረት፣ እ.ኤ.አ. ከ2004 እስከ 2011 ባለው ጊዜ ውስጥ ከቻይና ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣው ኢንቨስትመንት በየዓመቱ በአማካይ የ58 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል፡፡ ይህም ቢባል ግን የቻይና ኩባንያዎች በመንግሥት የታክስና ጉምሩክ አስተዳደር የሚታዩ ውጣ ውረዶች፣ በውጭ ምንዛሪ በኩል መንግሥት ግልጽነት አለማሳየቱን፣ በሠራተኛ ሕግ፣ በሠለጠነ የሰው ኃይል አቅርቦትና በመሳሰሉት መስኮች ላይ ችግሮች እያጋጠሟቸው እንደሚገኙ የዓለም ባንክ በጥናቱ አሳይቷል፡፡ 

በሰው ጉልበት ዋጋ መወደድና በማምረቻ ወጪዎች ከፍተኛነት ሳቢያ ከቻይና እየነቀሉ ወደ አፍሪካ የሚመጡ የቻይና ኩባያዎች እንደሚበራከቱ ከሰባት ዓመት በፊት ጀምሮ ሲነገር ነበር፡፡ በዚህ መስክ ኢትዮጵያ መጠቀም አለባት በማለት ደጋግመው ሲናገሩ እንደነበር የሚታወሱት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ናቸው፡፡ ሆኖም የተገመተውን ያህል ግን በርካታ የቻይና ኩባንያዎች ሳይመጡ ቀርተዋል፡፡ ይህንን በሚመለከት ሪፖርተር ያነጋገራቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ልዩ ረዳት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ አገሪቱ ይህንን ዕድል ለመጠቀም በሚያስችላት ደረጃ ዝግጁ እንዳልነበረች ገልጸዋል፡፡ ይህም ሆኖ በአሁኑ ወቅት በኢንዱስትሪ ፓርኮች አማካይነት የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችንና ሌሎች እንደ ጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ያሉ አገልግሎቶችን በፋብሪካዎቻቸው ደጅ ማግኘት የሚችሉበት ሥርዓት መዘርጋቱን ጠቅሰዋል፡፡ 

በአፍሪካ ኢንቨስት ስለማድረግ በዝግ እየመከረ የሚገኘው ጉባዔም መሠረታዊ በሚባሉ ችግሮች ላይ ከመነጋገር ባሻገር፣ በአፍሪካ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባት ረገድ አዳዲስ ስምምነቶች ላይ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በሌሎችም የመሠረተ ልማት መስኮች ላይ የቻይና መንግሥት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአፍሪካ አገሮች የሚደረጉ አዳዲስ ብድሮችንና የፋይናንስ ድጋፎችን ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ 

በአፍሪካ የዓለም ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ማክታር ዲዮፕ እንዳስታወቁት፣ በአፍሪካ በየዓመቱ የ90 ቢሊዮን ዶላር የመሠረተ ልማት ግንባታ ፍላጎት ቢኖርም፣ የአፍሪካ አገሮች ኢንቨስት ማድረግ የቻሉት ግን ከ20 ቢሊዮን ዶላር ያልዘለለ ነው፡፡ ይህንን በመንተራስ የቻይና ኩባንያዎች በቋሚ ንብረቶች ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው፣ የቻይና የፋይናንስ ተቋማትም አስፈላጊውን ፋይናንስ ለማቅረብ ፍላጎት እንዳላቸው ታውቋል፡፡ 

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴርን ጨምሮ የዓለም ባንክ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) እንዲሁም የቻይና መንግሥት ያዘጋጁት ይህ ፎረም፣ በየዓመቱ በአፍሪካና በቻይና እየተፈራረቀ በቋሚነት እንዲካሄድ ስምምነት መደረጉን የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አህመድ ሺዴ አስታውቀዋል፡፡ 

 

 

  

 

ኤጀንሲው 31 ሺሕ ያህሉ ከፍለው መዋዋላቸውን አስታውቋል

-የተዋዋሉት ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ከፍለዋል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአሥረኛ ጊዜ ባወጣው የኮንዶሚኒየም ቤት ዕጣ ዕድለኛ ከሆኑ የከተማው ነዋሪዎች መካከል አራት ሺሕ ተመዝጋቢዎች ለክፍያ ይጠበቃሉ፡፡

ክፍያቸውን በሁለት ሳምንት ውስጥ ካላጠናቀቁ ቤቶቹን እንደማያገኙ ተገለጸ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ ዕጣ ከወጣላቸው 35 ሺሕ ዕድለኞች ውስጥ 31 ሺሕ ያህሉ ውል መፈጸማቸውን አስታውቋል፡፡

ዕጣው ከደረሳቸው መካከል 31 ሺሕ ያህሉ ውል ተዋውለው መጨረሳቸውንና ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ቅድመ ክፍያ መፈጸሙን አስታውቋል፡፡ ቀሪዎቹ ዕድለኞችም እስከ ሐምሌ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ ውላቸውን ፈጽመው መጨረስ እንዳለባቸው አሳስቧል፡፡ ውል የመፈጸሚያ ጊዜው ካለፋቸው ቤቱን እንደማያገኙም አስታውቋል፡፡ 

መክፈል ያልቻሉ ዕጣው የወጣላቸው ዕድለኞች ደግሞ ቅድመ ክፍያ (ሃያ በመቶውን) ለመክፈል ከፍተኛ ችግር ውስጥ መግባታቸውን ይናገራሉ፡፡ ብዙዎቹ በብድርና በተለያዩ ወገኖች ድጋፍ ሊከፍሉ መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡ ከአቅማቸው በላይ የሆነ ኪራይ እየከፈሉ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎቹ፣ ለደረሳቸው ኮንዶሚኒየምና ለሚኖሩበት የቤት ኪራይ በየወሩ መክፈል ስለማይችሉ፣ ክፍያውን በሁለት ሳምንት አጠናቁ በመባላቸው ከወዲሁ ሥጋት ገብቷቸዋል፡፡ 

አራት ኪሎ፣ ልደታና ለመሀል ከተማው ቀርበው በተሠሩ ኮንዶሚንየም ቤቶች የደረሳቸው ዕድለኞች፣ ኮንዶሚኒየም ቤቱ ባይፀዳ እንኳን ገብተው ለኪራይ የሚከፍሉትን እየከፈሉ እንደሚኖሩ የገለጹት ዕድለኞቹ፣ ከመሀል ከተማው በ10 እና በ15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የደረሳቸው ግን ግራ እንደተጋቡ ተናግረዋል፡፡ 

ቤቶቹ የተገነቡት አገር ውስጥ በተመረቱ የግንባታ ግብዓቶች በመሆኑ ቅናሽ እንዲደረግላቸው የሚጠይቁት ነዋሪዎቹ፣ የመሠረተ ልማት ባልተሟላባቸው አካባቢዎች ዕጣ የደረሳቸው በኮንዶሚኒየም ቤቶቹ አካባቢ ትምህርት ቤቶች እስከሚከፈቱና ትራንስፖርት ተሟልቶ እስከሚገባ ድረስ፣ የባንክ ክፍያ መጀመሪያው ጊዜ እንዲያራዝምላቸው ጠይቀዋል፡፡ በተለይ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ያለፉና በመሰናዶ ትምህርት ቤት የተመደቡ ልጆቻቸውን እንዴት አጓጉዘው ማስተማር እንደሚችሉ ሥጋት ውስጥ እንደከተታቸው ተናግረዋል፡፡ 

በሌላ በኩል ዕጣ የወጣላቸው የተወሰኑ ዕድለኞች ቅድሚያ ክፍያ የሚከፍሉት አጥተው በየመሥሪያ ቤቱ፣ በካፌ፣ በሬስቶራንትና በመዝናኛ ቦታዎች በመገኘት እውነቱን እየተናገሩ ዕርዳታ እየጠየቁ መሆኑ ታውቋል፡፡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንዳንዶቹ ዕድለኞች ከአሥር ዓመታት ቆይታ በኋላ የደረሳቸው ዕድል መሆኑን ገልጸው፣ ይህ ዕድል ካመለጣቸው ዳግመኛ ስለማያገኙት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸውን ዕርዳታ በመጠየቅ ለማሟላት እየተሯሯጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በልመና ምን ያህሉን መሸፈን እንደሚችሉ አለማወቃቸውን የሚናገሩት ዕድለኞቹ፣ እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ የቻሉትን ጥረት አድርገው ካልሞላላቸው ምንም ማድረግ ስለማይችሉ ሳይወዱ በግድ እንደሚተውት ተናግረዋል፡፡

የቤቶች ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ ግን ቤቶቹን ለማዋዋል የተቀመጠው ቀነ ገደብ ሐምሌ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ስለሚያበቃ፣ በአስቸኳይ መዋዋሉን እንዲያጠናቅቁ አስታውቋል፡፡ የዕጣ ዕድለኞች የሆኑት አራት ሺሕ ያህል ግለሰቦች በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ የማያጠናቅቁ ከሆነ ቤቶቹን እንደማያገኙ ገልጿል፡፡ 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በተለይ በአሥረኛው ዙር ዕጣ የወጣባቸው ኮንዶሚኒየም ቤቶች ዋጋ በመጋነኑ ምክንያት፣ ልዩ ኮሚቴ አቋቁሞ የዋጋውን ሁኔታ ማጥናት መጀመሩ የታወቀ ቢሆንም፣ አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡   

 

ከአዲስ አበባ እስከ ጂቡቲ ወደብ ድረስ የተዘረጋው የባቡር መስመር ጥቅምት 2008 ዓ.ም. ሥራ የሚጀምር ቢሆንም፣ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያበረክት የሚችለውን ነዳጅ ለማጓጓዝ፣ የሚያስፈልገው የመሠረተ ልማት ቀደም ብሎ አለመጠናቀቁ አለመግባባት ፈጠረ፡፡ 

ኢትዮጵያ የምትጠቀመው አብዛኛው ነዳጅ የሚገባው በጂቡቲ በኩል ሲሆን የሚጫነውም ከሆራይዘን ተርሚናል ነው፡፡ ነገር ግን የተገነባው የባቡር መስመር ቀጥታ ወደ ጂቡቲ ወደብ የሚያመራ ነው፡፡ የአገሪቱ ነዳጅ ወደሚጫንበት ሆራይዘን ተርሚናል የባቡር ሐዲድ አለመገንባቱ አለመግባባት መፍጠሩን የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡ 

ከሆራይዘን ተርሚናል ባቡሩ ነዳጅ ቢጭን እንኳን የተጫነው ነዳጅ ኢትዮጵያ ከደረሰ በኋላ የሚያራግፍበት ዲፖ አለመገንባቱ ሌላ ችግር እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ ጉዳዩ ላይ የበለጠ አለመግባባት የፈጠረው የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ የትራንስፖርትና የዕቃ ማጓጓዣ ባቡሮችን እንዲያመርት ከቻይናው ኩባንያ ኖሪንኮ ጋር አስቀድሞ ውል መግባቱ ነው፡፡ ኖሪንኮ በበኩሉ ከአገር በቀሉ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር በገባው ውል መሠረት ከ50 በላይ የሚሆኑ የነዳጅ ማመላለሻ ባቡር ፉርጎዎች ተመርተው ለሥራ ዝግጁ መሆናቸውን እየገለጸ ነው፡፡ 

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ኃይለ ማርያም ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የእሳቸው ኩባንያ ከውጭ ነዳጅ ገዝቶ ጂቡቲ ሆራይዘን ተርሚናል ያራግፋል፡፡ ከዚህ በኋላ የነዳጅ ኩባንያዎች በተሽከርካሪዎች ለአገር ውስጥ ገበያ ያቀርባሉ፡፡ ነገር ግን ነዳጅን በባቡር ለማጓጓዝ ወደ ሆራይዘን ተርሚናል የሚጓዝ የባቡር ሐዲድ አልተገነባም፡፡ በአገር ውስጥም ማጠራቀሚያ ዲፖ አልተገነባም፡፡ ‹‹ጉዳዩ በደንብ መታየት ነበረበት፡፡ ትንሽ ክፍተት አለው፤›› በማለት አቶ ታደሰ የጉዳዩን አሳሳቢነት ገልጸዋል፡፡ 

ይህ ጉዳይ ክፍተት እንዳለው ዘግይቶ የተገነዘበው ትራንስፖርት ሚኒስቴር አጀንዳ ቀርጾ መሠረተ ልማት ለማሟላት ውይይት ማካሄድ መጀመሩ ታውቋል፡፡ 

ትራንስፖርት ሚኒስቴር፣ በሥሩ የሚገኘውን ትራንስፖርት ባለሥልጣን፣ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ኢንተርፕራይዝንና አሥሩን ነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች በማሰባሰብ በመፍትሔ ሐሳቦች ላይ እየተነጋገረ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

በዋናነት የቀረበው መፍትሔ ከጂቡቲ ወደብ ወደ ሆራይዘን ተርሚናል የሚወስድ የባቡር ሐዲድ መዘርጋትና በሆራይዘን ተርሚናል ባቡሮቹ ነዳጅ የሚጭኑባቸውን መሣሪያዎች ማሟላት ነው፡፡

በአገር ውስጥ ደግሞ አዲስ አበባ (ሰበታ) አካባቢ በሚገኘው ግዙፍ የባቡር ተርሚናል ውስጥ የነዳጅ ማራገፊያ ዲፖ መገንባት ዋነኛ ጉዳይ ሆኗል፡፡ በአሁኑ ወቅት እነዚህ ጉዳዮች በውይይት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ ግንባታዎቹን ለማካሄድ የበጀት ጉዳይ ቀጣዩ መነጋገሪያ ይሆናል ተብሏል፡፡ 

ምንጮች እንደገለጹት፣ በጀት ተወስኖ የግንባታ ቦታ ከተዘጋጀ ግንባታው ከሁለት እስከ ሦስት ዓመት የሚፈጅ በመሆኑ፣ በባቡር መሠረተ ልማት ነዳጅ ለማመላለስ ረዥም ጊዜ ሊወስድ ይችላል፡፡ ይህ ፕሮግራም ቀድሞ ባለመታሰቡ ብቻ የተገነባው የባቡር መሠረተ ልማት ላልተወሰነ ጊዜ ነዳጅ ከማመላለስ ውጪ ይሆናል፡፡

በጂቡቲ ሆራይዘን ተርሚናል ነዳጅ በተሽከርካሪ የሚያቀርቡ ኩባንያዎች አሥር ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ኢንተርፕራይዝ በወር በ250 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በሚያቀርበው ነዳጅ ትልቅ ድርሻ ያላቸው ኖክ፣ ቶታል፣ ኦይል ሊቢያና የተባበሩት ናቸው፡፡ እነዚህና ሌሎች ስድስት ኩባንያዎች በመላው አገሪቱ ባላቸው ከ250 በላይ ነዳጅ ማደያዎች አማካይነት ነዳጅ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ 

ሰበታ አካባቢ የነዳጅ ዲፖ እንደሚገነባ የሚጠበቀው በግል ኩባንያዎቹ ሲሆን፣ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከጂቡቲ ነዳጅ እያጓጓዙ በዲፖው የማራገፍ ኃላፊነት እንዳለበት ይጠበቃል፡፡ ኩባንያዎቹ ደግሞ በተሽከርካሪዎች ወደ ነዳጅ ማደያዎች ያደርሳሉ በሚለው ዕቅድ ላይ ውይይት እየተካሄደ መሆኑም ታውቋል፡፡ 

ከአዲስ አበባ (ሰበታ) እስከ ጂቡቲ ወደብ ድረስ የተዘረጋው የባቡር መስመር 656 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው፡፡ መስመሩ እስከ አዳማ ድረስ ሁለት ባቡሮች በአንዴ የሚያስተናግድ ሲሆን፣ ከአዳማ እስከ ጂቡቲ ድረስ ደግሞ አንድ መስመር ይኖረዋል፡፡

የባቡር መስመሩ ለመንገደኞችና ለዕቃ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ የትራንስፖርት ወጪን በ50 በመቶ ይቀንሳል ተብሏል፡፡ በሁለት የቻይና ኩባንያዎች እየተገነባ ያለው ይህ የባቡር መስመር የሐዲድ ማንጠፍ ሥራው የተጠናቀቀ በመሆኑ፣ በመጪው ጥቅምት አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሏል፡፡ ነዳጅ ለማጓጓዝ በተፈጠረው ክፍተት ላይ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ጌታቸው በኩረ አስተያየት እንዲሰጡ የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡  

 

ከ123 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣበት የአፍሪካ የሰላም ማዕከል በአዲስ አበባ ተገነባ

ለአፍሪካ ሰላምና ደኅንነት እንቅስቃሴዎች ድጋፍ እንዲሰጥ ታስቦ በአዲስ አበባ የተገነባውና ከ123 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣበት የሰላም ማዕከል፣ ሰኔ 20 ቀን 2007 ዓ.ም. ተመርቆ ተከፈተ፡፡ 

ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ መርቀው የከፈቱት ይኼ የደኅንነት ተቋም፣ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ ግጭትን ለመፍታት ለሚደረጉ የሰላም ማስከበር ጥረቶች አስፈላጊ የሥልጠናና የጥናት ማዕከል ሆኖ እንዲያገለግል ታስቦ የተገነባ ነው፡፡

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንቱ እንዳሉት፣ የተሳካ ሰላም የማስከበር ሥራዎች ለማከናወን ማዕከሉ ትልቁ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ማዕከሉን አስመልክተው ሲናገሩ፣ ‹‹የሰላም ማዕከሉ ወታደራዊና የሰላም አስከባሪ ተቋማት ዓላማቸውን በተሳካ ሁኔታ እንዲወጡ የምርምርና የሥልጠና አገልግሎት በመስጠት የሰላም ማስከበር ሥራዎች ማዕከል ሆኖ ያገለግላል፤›› ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጪ ሰላምና ደኅንነት ከማስጠበቅ አንፃር ላደረገው አስተዋጽኦ አድናቆታቸውን ለመከላከያ ሚኒስቴር የቸሩት ፕሬዚዳንት ሙላቱ፣ የአገሪቱ መረጋጋትና የኢኮኖሚ ዕድገት ምክንያት ኢትዮጵያ በአካባቢው የሰላምና የፀጥታ ተምሳሌት መሆን በመቻሏ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ 

የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ በበኩላቸው፣ በዓለም አቀፍ ደረጃም ኢትዮጵያ ሰላምን በማስከበር ሥራዎች የማይተካ ሚና እየተጫወተች እንደምትገኝ ገልጸው፣ ማዕከሉ ይህንን ጥረት በዕውቀትና በምርምር ለመደገፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ የተገነባው ይኼው የሰላም ማዕከል ግጭትን ለመከላከል፣ ዕርቅ ለመፍጠርና ሰላም ለማስከበር ለአካባቢውና ለመላው አፍሪካ ጥቅም ይውል ዘንድ፣ በተለይ ከአፍሪካ ኅብረትና ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ጋር በትብብር እንደሚሠራ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታ ማጆር ሹም ጄኔራል ሳሞራ ዩኑስን ጨምሮ፣ በርካታ የመከላከያና የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በክብር እንግድነት ተገኝተዋል፡፡    

 

የአይኤስ አሸባሪ ቡድን ሊቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ በፈጸመው አሰቃቂ ግድያ ምክንያት መንግሥት በጠራው ሰላማዊ ሠልፍ ላይ ረብሻ በመፍጠር ተከሰው የተፈረደባቸው የሰማያዊ ፓርቲ አባላት፣

የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው ሲወጡ ከማረሚያ ቤት በራፍ ላይ ተይዘው ከተመሠረተባቸው ክስ በዋስ እንዲለቀቁ ብይን ተሰጠ፡፡

የፓርቲው አባላት ሰኔ 23 ቀን 2007 ዓ.ም. እያንዳንዳቸው በ5,000 ብር ዋስ እንዲለቀቁ የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቄራ ምድብ ችሎት ብይን የሰጠው በወይንሸት ሞላ፣ በኤርሚያስ ፀጋዬ፣ በዳንኤል ተስፋዬና በቤተልሔም አካለ ወርቅ ላይ ነው፡፡

በተከሳሾቹ ላይ ሰኔ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ፍርድ ተሰጥቶ የነበረው፣ ሰላማዊ ሠልፉን በማወክ የተለያዩ ስድቦችን መንግሥትንና ዜጎችን በመሳደብ፣ ሥርዓቱን በማንጓጠጥና በፖሊስ አባላት ላይ ድንጋይ በመወርወር ወንጀል ተከሰው ነው፡፡

ፍርደኞቹ ሰኔ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ለፍርድ በቀረቡበት ዕለት ሁለት ወር ከአንድ ቀን በእስር መቆየታቸው በመረጋገጡ፣ በዕለቱ ከእስር እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም ፖሊስ ሌላ ወንጀል መፈጸማቸውን በመግለጽ፣ ሰኔ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ከእስር ተፈትተው ወደ ቤታቸው ለማምራት ማረሚያ ቤት ደጃፍ ላይ ሲደርሱ ተይዘው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል፡፡

ፖሊስ ለፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ፣ ተከሳሾቹ ቀደም ብሎ በተከሰሱበት ወንጀል ላይ በምስክርነት ያቀረባቸውን ማስፈራራታቸውንና መዛታቸውን በመግለጽ ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ ክሱን ተቀብሎ ለሰኔ 23 ቀን 2007 ዓ.ም. መዛታቸውን የሚያስረዱለትን ምስክሮቹን እንዲያቀርብ ቀጠሮ የሰጠ ቢሆንም፣ ፖሊስ ምስክሮቹን በተለያዩ ምክንያቶች ሊያቀርብ አለመቻሉን ገልጾ፣ ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል፡፡ 

ተከሳሾቹ ግን ፖሊስ ምስክሮቹን በተሰጠው ቀጠሮ ቀን ማቅረብ እንደነበረበት ገልጸው፣ ፍርድ ቤቱ ዋስትና እንዲፈቅድላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ጥያቄውን ተቀብሎ እያንዳንዳቸው በ5,000 ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፈቅዷል፡፡ በሌላ በኩል ተከሳሾቹ ቀደም ብሎ ሰኔ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ሁለት ወራት ተፈርዶባቸው በነበረውና እስራቸውን ጨርሰው በወጡበት ክስ፣ ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ እንዳለባቸውና ሰኔ 24 ቀን 2007 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ተጠቁሟል፡፡

 

አፍሪካ ከእስያ አገሮች ትልቅ ፉክክር ይጠብቃታል  

የአሜሪካና የአፍሪካ የእርስ በርስ የኢኮኖሚ ግንኙነት ላይ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ታምኖበት ላለፉት 15 ዓመታት ሲተገበር የቆየውን ከታሪፍና ከኮታ ነፃ የገበያ ዕድል፣ ለተጨማሪ አሥር ዓመታት ማራዘሙን የአሜሪካ ኮንግረስ ይፋ አደረገ፡፡ 

ከታሪፍና ከኮታ ነፃ የገበያ ዕድል ወይም ‹‹አፍሪካ ግሮውዝ ኤንድ ኦፖርቹኒቲ አክት – አጎዋ›› ሚያዝያ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. በአምባሳደር ማይክል ፍሮማንና አምባሳደር ሱዛን ራይስ በኩል ቀርቦለት ሲመክር የከረመው ሕግ መወሰኛው ምክር ቤት፣ ለመጪዎቹ አሥር ዓመታት እንዲራዘም ይፋ ያደረገው አጎዋ እንደከዚህ በፊቱ ሳይሆን በእስያ አገሮች ዘንድ ፈተና እንደሚገጥመው እየተነገረለት ነው፡፡ አምባሳደር ፍሮማን የአሜሪካ የንግድ ዘርፍ ተወካይ ሲሆኑ፣ የቀድሞዋ የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ሱዛን ራይስ በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ናቸው፡፡ በአምባሳደሮቹ የቀረበው የአጎዋ ረቂቅ ሕግ ለአሥር ዓመታት የሚራዘም ከሆነ ከ30 በላይ ለሚሆኑ የአፍሪካ አገሮች ትልቅ እፎይታ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በኮንግሬሱ ተቀባይነት አግኝቶ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በፊርማቸው እንዲያፀድቁት መርቶታል፡፡ 

እ.ኤ.አ. በ2009 ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በጋና ተገኝተው አሜሪካ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ትስስር የማጠናከር አስፈላጊነት ሲገልጹ፣ ‹‹ለልጆቻችን ማውረስ የምንፈልገውን ዓለም በመቅረፅ ረገድ አፍሪካ የአሜሪካ አጋር ነች፡፡ አጋርነታችንም በጋራ ኃላፊነትና በመከባበር ላይ የተመሠረተ መሆን ይኖርበታል፤›› ብለው ነበር፡፡ ባለፈው ዓመት የአፍሪካና የአሜሪካ የመሪዎች ጉባዔ በተካሄደበት ወቅት፣ ፕሬዚዳንቱ የአፍሪካ የዕድገትና የገበያ ዕድል የሚያበቃበት ጊዜ ማለትም የመጪው ዓመት መስከረም ወር ደርሶ ከመጠናቀቁ በፊት፣ የጊዜ ገደቡ እንዲራዘም ኮንግረሱን መጠየቃቸውም ይታወሳል፡፡ በዚህ መሠረት አጎዋ እንዲራዘም መጠየቅ ብቻ ሳይሆን፣ ማሻሻያዎች ተደርገውበት የበለጠ ውጤታማ የሚሆንበት መንገድ እንዲመቻች ሲጠየቅ እንደቆየ አይዘነጋም፡፡

ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ዕድገትና የገበያ ዕድል ለመፍጠር በሚል መነሻ እ.ኤ.አ. በ2000 ሕግ ሆኖ የፀደቀው አጎዋ፣ በአሜሪካና በአፍሪካ መካከል እያደገ ስለመምጣቱ ለሚነገርለት አጋርነት መጠናከር አስተዋጽኦ ማድረጉን በማስረጃ ደፍገው የሚያቀርቡት የአሜሪካ ባለሥልጣናት ብቻ አይደሉም፡፡ አፍሪካውያንም ይጠቀሳሉ፡፡ በአፍሪካ ወሳኝ የልማትና የዕድገት መርሐ ግብሮች እንዲከናወኑ፣ የተለያዩ የአኅጉሪቱ ቀጣናዎች የኢኮኖሚ ጥምረት እንዲፈጥሩ፣ ኩባንያዎች ተወዳዳሪ እንዲሆኑና የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ለሚያደርገው የካፒታልና የኢንቨስትመንት ፍሰት ምቹነትን በመፍጠር በኩል ሚናው አሌ እንደማይባል የሚገልጹ አሉ፡፡  

በአልባሳት ንግድ ዘርፍ ከተሰማሩ ተቋማት በተገኘ መረጃ መሠረት ከነዳጅ መስክ ውጭ ያለው የወጪ ንግድ፣ መርሐ ግብሩ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ በቀጥታ ወደ 350,000 ለሚቆጠሩ ሰዎች የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር፣ በተዘዋዋሪም ሌሎች በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩትን በማገዝ ዘርፉን በሦስት እጥፍ አሳድጎታል፡፡ 

የአፍሪካን ልማት ከመደገፍ ባሻገር አጎዋ ለአሜሪካ ተጨባጭ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎችንም አስገኝቷል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2000 ጀምሮ አሜሪካ ከሰሃራ በታች ወዳሉት አገሮች የምትልካቸው ሸቀጦች መጠን ይበልጥ እየጨመረ መምጣቱን የሚያመላክቱ ክስተቶች በአፍሪካ እየታዩ ነው፡፡ መካከለኛ ገቢ ያለው የኅብረተሰብ ክፍል እያደገ መጥቶ ከሩብ ቢሊዮን በላይ እንደሚደርስ የኢኮኖሚ ትንበያዎች ይጠቁማሉ፡፡ በመሆኑም በአሜሪካ የተመረቱ ሸቀጦችን የመሸመት አቅማቸው በማደጉ፣ የሸቀጦች ወጪ ንግድ መጠን በሦስት እጥፍ ሊጨምር ችሏል፡፡ በአፍሪካ የሚገኙ የንግድ ተቋማት የአሜሪካ ግብዓቶች፣ ዕውቀት፣ ክህሎትና አጋርነት አስፈልጓቸዋል፡፡ አሜሪካ በአፍሪካ የምታደርገው የኢንቨስትመንት ፍሰት፣ በአፍሪካም ሆነ በአሜሪካ ለሚገኙ ሠራተኞች የሥራ ዕድሎችን ከመፍጠሩም በላይ፣ ገቢያቸው እንዲያድግ ምክንያት ሆኗል፡፡ 

አሜሪካ በአጎዋ በኩል ከአፍሪካ ጋር የምታደርገውን የንግድ ልውውጥ እንዳፋጠነ የሚነገርለት ቢሆንም፣ አብዛኞቹ የአፍሪካ አገሮች ግን ተጠቃሚ ሳይሆኑበት እንደቀረ ይታወቃል፡፡ በግብርና ውጤቶች፣ በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ በቆዳና የቆዳ ውጤቶች አኳያ ተጠቃሚ መሆን ከሚገባቸው አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ እንደነበረች ይታመናል፡፡ ቢሆንም በአጎዋ በኩል አገሪቱ ከቀረጥና ከኮታ ነፃ ወደ አሜሪካ የላከቻቸው ምርቶች መጠን እጅግ ዝቅተኛ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ 

ኢትዮጵያ ባለፉት አሥራ አምስት ዓመታት ውስጥ በአጎዋ በኩል ከላከቻቸው ምርቶች በአማካይ በዓመት ከ40 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማግኘት አልቻለችም፡፡ ከሪፖርተር ጋር ቆይታ ያደረጉት የአሜሪካ ከፍተኛ የንግድ ባለሙያና በኢትዮጵያ የአሜሪካ የውጭ ንግድ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ታንያ ኮል እንዳስታወቁት፣ አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ በአጎዋ በኩል ከምትልካቸው ምርቶች ቦይንግ አውሮፕላንን ጨምሮ በዚህ ዓመት ብቻ ከ1.6 ቢሊዮን ዶላር በላይ ስታገኝ፣ ኢትዮጵያ ግን ከ225.6 ሚሊዮን ዶላር የዘለለ ገቢ አላገኘችም፡፡ በመሆኑም ምርቶችን በገፍ ማምረትም ሆነ ወደ አሜሪካ መላክ ፈተና ሆኖ ይገኛል፡፡ ለሚቀጥሉት አሥር ዓመታት አጎዋ በመራዘሙ ግን እየተስፋፉ ያሉት የቆዳና የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ትልቅ የገበያ ዕድል እንደሚያገኙ ይጠበቃል፡፡ በአንፃሩ አሜሪካ ከታሪፍና ከኮታ ነፃ የገበያ ዕድል ለእስያ አገሮች ‹‹ትራንስ ፓስፊክ ፓርትነርሺፕ›› በተሰኘው ማዕቀፍ ውስጥ ተመሳሳይ የነፃ ገበያ ዕድል መስጠቷ ግን በርካታ ጨርቃ ጨርቅ አምራቾችን ሥጋት ውስጥ የጣለና የአፍሪካን የተወዳዳሪነት አቅም የሚፈታተን ተብሎለታል፡፡ የሥጋቱ ምክንያት ደግሞ በእስያ አገሮች ውስጥ የማምረቻ ወጪዎች ከአፍሪካ ይልቅ ዝቅተኛ መሆናቸው ነው፡፡ 

 

የዶ/ር አርከበ ዕቁባይ አዲስ መጽሐፍ ለኢትዮጵያ ገበያ ቀረበ

ዋጋው በጣም ውድ ነው ተብሏል

ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ ‹‹ሜድ ኢን አፍሪካ ኢንዱስትሪያል ፖሊሲ ኢን ኢትዮጵያ›› በሚል ርዕስ ያሳተሙት አዲስ መጽሐፍ፣ በኢትዮጵያ ገበያ ቀረበ፡፡

መጽሐፉ በዓለም ገበያ ግንቦት 19 ቀን 2007 ዓ.ም. የቀረበ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በቡክ ወርልድ አማካይነት ገበያውን ተቀላቅሏል፡፡

ዋቢና ኢንዴክስን ጨምሮ 348 ገጽ ያለው ይህ የዶ/ር አርከበ ዕቁባይ መጽሐፍ፣ ከአፍሪካ አጠቃላይ ሁኔታ በመነሳት የኢትዮጵያን ኢንዱስትሪ በጥልቀት ይተነትናል፡፡

ዶ/ር አርከበ ለዚህ መጽሐፍ መነሻ የሆናቸው በለንደን ስኩል ኦፍ ኦርየንታል ኤንድ አፍሪካን ስተዲስ ለተከታተሉት የዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ያቀረቡት ጽሑፍ ነው፡፡

ዶ/ር አርከበ በአራት ዓመት የሚጠናቀቀውን ትምህርታቸውን በዩኒቨርሲቲው ባልተለመደ ሁኔታ በ23 ወራት ውስጥ በከፍተኛ ማዕረግ በማጠናቀቃቸው፣ በወቅቱ ከፍተኛ አድናቆትን ተችሯቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡

የተመረቁበትን ዴቨሎፕመንት ስተዲስ የዶክትሬት ዲግሪ የጥናት ጽሑፍ በማስፋት በመጽሐፍ መልክ ያዘጋጁት ሲሆን፣ የተማሩበት ለንደን ስኩል ኦፍ ኦርየንታል ስተዲስ ይኼንን መጽሐፍ እንዲታተም ለኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ልኮታል፡፡

ለዶ/ር አርከበ ቅርበት ያላቸው የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ ዶ/ር አርከበ ይኼንን መጽሐፍ ያዘጋጁት በዘርፉ ጥልቅ ጥናት አካሂደው ነው፡፡

ዶ/ር አርከበ መጽሐፉን ለማዘጋጀት በ150 ኩባንያዎች ላይ ጥልቅ ጥናት ማድረጋቸው፣ ሃምሳ ፋብሪካዎችን በአካል በመገኘት ማጥናታቸው፣ ለዚሁ ጽሑፍ 250 ጥያቄዎችን በማዘጋጀት ከፋብሪካዎች መረጃ እንደሰበሰቡና ከሁለት እስከ አራት ሰዓት የፈጁ 200 ቃለ መጠይቆችን ማድረጋቸው ተሰምቷል፡፡ ለኢንዱስትሪ ልማት ማነቆ ናቸው የተባሉ ችግሮችን ለመለየት በውጭና በአገር ውስጥ የሚገኙ ፋብሪካዎች ላይ ጥናት ማድረጋቸው እንዲሁ ተነግሯል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በሌሎች ጥናቶች መረጃ ሆነው ያልቀረቡ አንድ ሺሕ ሰነዶችን በማገላበጥ የተሟላ ጥናት ማድረጋቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ይህ አጠቃላይ ጥናት አራት ዓመት የፈጀ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ይህ የዶ/ር አርከበ መጽሐፍ የተወሳሰቡ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ሐሳቦችን በጥልቅ አረዳድ የተነተነ ነው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ገልጸዋል፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው ‹‹ጸሐፊው በንድፈ ሐሳብ ብቻ ሳይሆን በተግባራዊ ልምዳቸውና በፖሊሲ ቀረፃ የረዥም ጊዜ ልምድ ስላላቸው ነው፤›› በማለት የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ሀ ጁን ቻንግ ለመጽሐፉ ያላቸውን አድናቆት በመጽሐፉ ላይ ገልጸዋል፡፡ 

የቀድሞ የዓለም ባንክ ዋና ኢኮኖሚስት ጀስቲን ይፋ ሊን በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ በልማት ተዓምር እየፈጠረች በመሆኑ ለአፍሪካ አገሮች መነቃቃት፣ በራስ መተማመንና መልካም ተሞክሮ ማካፈል ትችላለች ያሉ ሲሆን፣ ዶ/ር አርከበ ይኼን ለውጥ በመጽሐፉ በግሩም ሁኔታ እንደተረኩት መስክረዋል፡፡ ጃፓን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ለምሥራቅ እስያ አገሮች ምሳሌ እንደሆነችው ሁሉ፣ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ አገሮች ተመሳሳይ አስተዋጽኦ ማበርከት ትችላለች ብለዋል፡፡ መጽሐፉ ኢትዮጵያ ዕድገቷን እንዴት እያፋጠነችና ባለሁለት አኃዝ ዕድገት እያስመዘገበች እንደመጣች፣ ጥልቅ ግንዛቤ ይሰጣል በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ 

መጽሐፉ በእንግሊዝ ገበያ ውስጥ 55 ፓውንድ ሲሸጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ 1,815 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡

ከቡክ ወርልድ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው፣ የመጽሐፉ ዋጋ መወደዱን ከተለያዩ አቅጣጫዎች አስተያየት እየተሰጠበት ነው፡፡ መጽሐፉ ሊወደድ የቻለው ሐርድ ከቨር ያለውና ደረጃውን ጠብቆ በመታተሙ፣ እንዲሁም በጣም የተለፋበት በመሆኑ ነው ተብሏል፡፡

መጽሐፉ በዋነኛነት ትኩረት የሚያደርገው በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት መሄድ ባለባቸው አቅጣጫዎች ላይ ነው፡፡ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍን ማሳደግ ለግብርና የላቀ ዕድገት ወሳኝ መሆኑም ተተንትኗል፡፡

ዶ/ር አርከበ በመጽሐፉ መግቢያ ላይ እንደጠቀሱት፣ በመጽሐፉ ያንፀባረቋቸው ምልከታዎች የመንግሥትንም ሆነ አብረዋቸው እየሠሩባቸው ወይም የሠሩባቸው ተቋማትን አይወክሉም፡፡ የመጽሐፉ ዋናው ዓላማ የተለያዩ ምልከታዎች፣ ልምዶችና ተግዳሮቶችን ለማቅረብ ለተጨማሪ ጥናትና ውይይት መጋበዝ መሆኑም ተገልጿል፡፡

 

ሁለት የአላባማ ካውንቲ ፍርድ ቤቶች ውሳኔውን ውድቅ በማድረግ ምንም አይነት የተመሳሳይ ጋብቻ የምስክር ወረቀት የማይሰጡ መሆናቸውን ገልጸው ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ዳግም እንዲያጤነው ጠይቀዋል። ከዚህም በተጨማሪ የቴክሳስ ከፍተኛ አተርኒ ተመሳሳይ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በግለሰብ ነጻነት ስም ሰዎች ሰብአዊ ክብራቸውን እንዲያዋርዱ መፍቀድ የለብንም የሚሉ አሜሪካውያን በየግዛቱ ተቃውሞ በማሰማት ላይ ናቸው። አንድ ታዋቂ የቤተክርስትያን ፓስተር በበኩላቸው በሚያገለግሉበት […]

ሰኔ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ዲያስፖራውን በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ለመያዝ ያደረገው ተደጋጋሚ ጥረት መክሸፉን ተከትሎ ፣ የዲያስፖራውን ቀልብ ሊስቡ ይችላሉ ያላቸውን አዳዲስ ዘዴዎች እያሰላሰለ ነው። በቅርቡ በኢትዮጵያ በሚካሄደው የዲያስፖራ ሳምንት ዝግጅት ዙሪያ አስመልክቶ ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲያስፖራ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በክልልና በፌደራል ደረጃ ከሚገኙ የዲያስፖራ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ሃላፊዎች …

ሰኔ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ወንጀል አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ለመኢአድ አባላት መከላከያ ምስክር መሆን መቻል አለመቻላቸው ላይ ነገ ሰኔ 24፣ 2007 ዓ.ም ብይን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ በግንቦት ሰባት አባልነት የተከሰሱት 5 የመኢአድ አባላት ‹‹በአንዳርጋቸው ፅጌ አሰልጣኝነት የሽብር ተግባር ለመፈፀም ተንቀሳቅሳችኋል፡፡›› በሚል ክስ …

ሰኔ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለሚቀጥለው አምስት አመታት ይተገበራል ተብሎ በተዘጋጀ የሁለተኛ ዙር የ5 አመታት እቅድ ላይ በተዘጋጀ የመወያያ ሰነድ እንደተመለከተው ባለፉት ሶስት አመታት 2 ሺ 995 ፕሮጀክቶች ወደ አገር ውስጥ ገብተው ስኬታማ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ተሰርዘዋል። በአማራ ክልል በባህርዳር እንዲሁም በኦሮምያ ክልል አዳማ የተደረገውን የምክክር ጉባኤ አስመልከቶ የተዘጋጀው ሰነድ እንደሚያሳየው፣ በዚህ …

ሰኔ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ከ2003 እስከ 2005 ዓ.ም ድረስ የሳምባ ምች በሽታ የመጀመሪያው ገዳይ በሽታ የነበረ ሲሆን፣ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ኤች አይ ቪ ኤድስ አንደኛ የአእምሮ ጭንቀት ደግሞ የሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል። ኤ አይ ቪ ኤድስ በኢትዮጵያ እየቀነሰ መምጣቱ ቢነገርም፣ በሽታው አሁንም ቀዳሚ ገዳይ በሽታ ተብሎአል። የአእምሮ ጭንቀት ሁለተኛ ገዳይ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ኢሳት ዜና (ሰኔ 23 2007) ሰሞኑን ፍርድ ቤት ከእስር እንዲፈቱ ወስኖላቸው ፖሊስ በድጋሚ ለእስር በዳረጋቸው አራት የፓርቲ አባላት ላይ አቃቢ ህግ ይግባኝ ጠየቀ። ተከሳሾች የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ጉዳያቸው ከውጭ ሆነው ለመከታተል ጥያቄን ቢያቀርቡም ከሳሽ አቃቢ ህግ ተቃውሞን እንዳቀረበ ከሀገር ቤት የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ጉዳዩን ለማየት የተሰየሙት ዳኛ ተከሳሾች እስካሁን ድረስ በእስር ቤት ስለመቆየታቸው የሚያውቁት ነገር …

ለደብሩ ማኅበረ ካህናት፣ ማኅበረ ምእመናንና ለየሰንበት ት/ቤቱ ታላቅ ድል፤ በየአጥቢያው ለተጋጋለው የፀረ ሙስና እና ፀረ ኑፋቄ ንቅናቄ ታላቅ የምሥራች፤ የንቅናቄውን ኃይሎች በነፍስ ግድያ ዛቻዎች ጭምር ለማዳከም ለሚሯሯጡት አማሳኞች ከባድ ድንጋጤ እና መርዶ ኾኗል !!! በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ባለፈው ሳምንት ዓርብ ረፋድ ባሳለፈው የቅጣት ውሳኔ፣ የደብሩ ዋና ሒሳብ ሹም ዲያቆን ተስፋዬ …

ኢሳት ዜና (ሰኔ 22 2007 ዓም) በሚቀጥለው ወር በኢትዮጵያ ጉብኝት የሚያደርጉት የአሜሪካ ፕሬዘዳንትን ጉዞን በመቃወም የፊታችን አርብ በዚህ በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ከተማ በሚገኘው “ ሁዋይት ሀውስ ‘’ የተቃውሞ ሰልፍ መጠራቱን አዘጋጆቹ ገለጹ ። በዋሺንግተን ከተማ ዙሪያ በሚገኘው የወጣቶች ግብረ ሀይል የተዘጋጀው የተቃውሞ ሰልፍ ፕሬዘዳንት ኦባማ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲያስቡበትና እንዲሰርዙት የሚጠይቅ መሆኑ ታውቋል። ፕሬዘዳንቱ በቀጣዩ ወር …

32ኛው በሰሜን አሜሪካ በድምቀት እየተከበረ የሚገኘው የኢትዮጲያዊያን የሰፖርትና የባህል ፌስቲቫል ላይ ከተዘጋጁት ዝግጅቶች መሀከል በጉጉት የሚጠበቁት የሃሙስ እና የዓርብ የሙዚቃ ዝግጅቶች በወጣላቸው ፕሮግራም መሰረት እንደሚደረጉ ተረጋገጠ። ቴዲ አፍሮና ጎሳዬ ተስፋዬ ቪዛቸውን ለማግኘት የአሜሪካ ኤምባሲ የሲስተም መበላሸት ያዘገየው ቢሆንም አሁን ከደቂቃዎች በፊት ኤንባሲው ችግሩን እንዳስተካከለ የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል። U.S. Embassy Addis Ababa በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን […]

በቱርክ ዋና ከተማ ኢስታንቡል የተሰባሰቡ ግብረሰዶማውያን ሊያደርጉት አቅደው የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ የአገሪቱ መንግስት ህገወጥ ነው ሲል በውሃ መርጫ ካኖን መበተኑ ተሰምቷል። ከሰሞኑ በዓለም ላይ እየተከበረ ያለውን የግብረሰዶማውያን ቀን ለማክበር ወጥተው የነበሩት እነዚህ ሰልፈኞች በታቅሲም አደባባይ አቅራቢያ በመሰባሰብ ላይ እንዳሉ በፖሊሶች እንዲበተኑ መደረጉን በስፍራው የነበረ የሮይተርስ ዘጋቢ ተናግሯል። ፓሊሶች የሰልፉ መሪዎችን ካሰሩ በኋላ ከተማዋ ወደ ቀድሞው […]

ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ብአዴን እያስተዳደርኩት ነው በሚለው የአማራ ክልል የጀመራቸው የተለያዩ ተቋማት ውጤት አልባ በመሆናቸው ብዙዎቹ እየፈረሱና ዜጎችን ለችግር እያደረጉ መሆኑን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል። የክልሉ ቴክኒክ እና ሙያ ኢንተርፕራይዝ እና የክልሉ ጥቃቅን እና አነሰተኛ ቢሮዎች በክልሉ የሚገኙ በሚልዮን የሚቆጠሩ ስራ አጦችን በተለያየ ሙያዎች በማሰልጠን የክልሉን የስራ አጥ ቁጥር …

ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስባ የሆነው መድረክ ባወጣው መግለጫ በ2007 ዓ ም በሀገራችን ተካሄደ የተባለው ምርጫ በሕግና ሥርዓት ያልተመራና በሕገ-መንግሥቱና በምርጫ ሕጎች የተደነገጉትን የነፃ፣ፍትሐዊና ታአማኒነት ያለው ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መርሖዎች በኃይል በተጣሱበት ሁኔታ የተፈጸመ በመሆኑ መድረክ የምርጫውን ሂደትም ሆነ ውጤት እንደማይቀበለው ገልጾ፣ ለዚህ አሁን ሀገራችን ለገባችበት አስቸጋሪ ሁኔታ …

ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግል ሠራተኞች የፕሮቪደንት ፈንድ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ያለውን ገንዘብ ወደመንግስት በማስገባት ሠራተኞቹ በጡረታ እንዲታቀፉ በሚያስችል መልኩ የተደነገገው የግል ድርጅቶች የማህበራዊ ዋስትና አዋጅ ማሻሻያ በገጠመው ከባድ ተቃውሞ ምክንያት ለፓርላማው ሳይቀርብ በቋሚ ኮምቴዎች ውሳኔ እንዲሻሻል መደረጉን ዘጋቢያችን ገልጿል። የማሻሻያ ሕጉ ከአንድ ወር በፊት ለፓርላማ ሲቀርብ አሁን በስራ ላይ …

ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከዚህ ቀደም በ1997 ምርጫ ወቅት በቅንጅት መሪዎች፣ በጋዜጠኞችና በሲቪክ ተቋማት መሪዎች ላይ የቀረበው ክስ ፣ 24 ሰአታት አስቂኝ ፊልም የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ነበር። በፍርድ ቤቱ የነበረውን ሁኔታ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና የቃሊቲው መንግስት በሚል ርእስ ዘርዝሮ ማቅረቡ ይታወቃል። በቅርቡ አይ ኤስ ኤስ የተባለው አሸባሪ ድርጅት በ30 ኢትዮጵያውያን …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ እስር ላይ ቆይተው ሰኔ 15/2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት እንዲፈቱ ተወስኖላቸው ሰኔ 16/2007 ዓ.ም ከእስር ቤት ሲወጡ እንደገና በፖሊስ ተይዘው የታሰሩት ወንይሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለወርቅ ዛሬ ሰኔ 22/2007 ልደታ ፍርድ ቤት 11ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው ቀደም ሲል ‹‹ሁከትና ብጥብጥ አስነስተዋል›› […]

አይ ኤስን ለመቃወም ከተጠራው ሰልፍ በኋላ ፖሊስና አቃቤ ህግ በየ ችሎቱ ኢህአዴግ ላይ ሰልፍ በመጥራት ስድብ እያዘነቡበት ነው፡፡ በሚያዝያ 14ቱ ሰልፍ ላይ በቦታው ያልነበሩት የሰማያዊ፣ የቀድሞው አንድነትና የቀድሞው መኢአድ አባላትና አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ወጣቶችን ያስሩና እነዚህ ወጣቶች ያላሉትን ክስ ብለው ያቀርባሉ፡፡ ይህ ክስ ደግሞ ለእነሱ የሰልፍ መፈክር መሆኑ ነው፡፡ የስድብ ውርጅብኝ፡፡ በቃ ችሎት የቁጭት መውጫቸው […]

ዛሬ በጥዋት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ሊሰጥ የተቀጠረውን ውሳኔ ተመልክቼ ለመዘገብ ልደታ በሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አምርቼ ነበር፡፡ 3፡30 ሰዓት ገደባ በታችኛው መግቢያ በር ጋር ስደርስ፣ ቁጥራቸው በዛ ያሉ፣ የሚሊተሪ ልብስ የለበሱ የጸጥታ ሃይሎች እና የአዲስ አበባ ፖሊሶች በፍርድ ቤቴ ቅጥር ግቢ በር ላይ ሆነው ሰዎችን በጥብቅ እየተፈሹ ሲያስገቡ አስተዋልኩ፡፡ በአጋጣሚ ከጠበቃ […]

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ እንዲሰፍን እየታገልኩ መሆኔ በክስ ማቅለያነት እንዲወሰድልኝ›› ወጣት ቴዎድሮስ አስፋው በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰልፍ ሰበብ ታስረው ‹‹ኢህአዴግ ሌባ ነው፣ ህገ መንግስቱ ወረቀት ነው፣ ታፍነናል፣ ታስረናል፣ መለስ የሞተው ደንግጦ ነው፣ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በቁሙ የሞተ ነው፣ ቴዎድሮስ ለህዝብ ነው የሞተው›› በሚል ብጥብጥና ሁከት ፈጥራችኋል፣ የሀሰት […]

ትላንት እሑድ ከጸሎተ ቅዳሴው ፍጻሜ በኋላ ለኹለተኛ ጊዜ ደብሩ፣ በአለቃው ‹‹የመንግሥት ያለኽ›› ጩኸት እና በምእመናን ‹‹ኃይል የእግዚአብሔር ነው፤ አንፈራም፤ አንሰጋም›› መዝሙር እና ተቃውሞ ውሏል *           *           * የቤተ ክርስቲያንን ነገር አደራ ብለው መባረኪያ መስቀላቸውን የሰጡ እንደ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ እና ብፁዕ አቡነ መልከ ጸዴቅ ያሉ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

በድርጅት ከዚያም ከፍ ብሎ በመንግስት ደረጃና በሃገር ደረጃ ግምገማ ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ ሁሉ ያምናል። የኣንድ ድርጅት ብቃትም በግምገማው ችሎታና ጥራት ሊለካ ይችላል።የኣንድ ሃገር የፖለቲካ መረጋጋት በፖለቲካ ለሂቆቹ የጠራ የሃገር የምናብ ስእልና ብስለት ሊለካም ይችላል። የፖለቲካ ቤቶች ሲኮለኮሉ፣ ፖሊሲዎች ሲቀረጹ ከፍ ያለ ግምገማን ይጠይቃል። ሃገሪቱ ያለፈችበትን የህይወት ጎዳና፣ የገጠማትን ችግር መንስዔና ውጤቶች በሰፊው መገምገም ለሚመሰረቱ […]

በክፍል አንድ፤ የሰላማዊ ትግሉ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ምን እንደሆነ ገልጫለሁ። በዚሁ ላይ፤ የሰላማዊ ትግሉ ከተወዳዳሪ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ጋር ያለውን ልዩነት አሳይቻለሁ። በተጨማሪ ደግሞ፤ የሰላማዊ ትግሉ የሚካሄደው በአንድ የሕዝባዊ ንቅናቄ ድርጅት ሥር ብቻ መሆኑንና፤ አማራጭና ተለዋጭ እንደሌለው አስምሬበታለሁ። በሂደቱ መሰባሰቢያ የሆኑትን ሀገር አቀፍ የትግል ዕሴቶች አስቀምጫለሁ። በዚህ ክፍል ሁለት ደግሞ፤ ስለተሳሳተው የሰላማዊ ትግሉ ግንዛቤያችን አስረዳለሁ። ባጠቃላይ፤ […]

ኤርትራውያን ስደተኞች አገራቸው ከአፍሪካ ኅብረት አባልነት እንድትሰረዝ ጥያቄ አቀረቡ

በኢትዮጵያ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ሰኔ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያና በተለያዩ አገሮች ባደረጉት የተቃውሞ ሠልፍ፣ በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራውን የኤርትራ አስተዳደር በማውገዝና ሕጋዊ የሆነ መንግሥት

የማያስተዳድራት አገር የአፍሪካ ኅብረት አባል መሆን እንደማትችል በመግለጽ፣ ኤርትራ ከኅብረቱ አባልነት እንድትሰረዝ ጥያቄ አቀረቡ፡፡

በአዲስ አበባ በሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት ቁጥራቸው ከ1,000 የሚበልጡ ስደተኛ ኤርትራውያን ባሰሙት ተቃውሞ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ግንቦት 28 ቀን 2007 ዓ.ም. ኤርትራን በሚመለከት ያወጣውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ ሪፖርትን ደግፈዋል፡፡ ‹‹ኢሳያስ አፈወርቂ ከሥልጣን መውረድ አለበት፤›› የሚለውንና ሌሎችንም መፈክሮች በማሰማት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤርትራ መንግሥት በተለይ በኤርትራውያን ወጣቶች ላይ እየፈጸመው የሚገኘውን ስቃይ፣ በደልና ሌሎች በዝርዝር ያቀረባቸውን ሪፖርቶች ኅብረቱ እንዲያፀድቀው ጠይቀዋል፡፡

ሕጋዊነት የሌለው መንግሥት የኅብረቱ አባል ሆኖ መቀጠል እንደሌለበት የጠቆሙት ኤርትራውያኑ፣ ፕሬዚዳንቱ ከሥልጣናቸው እንዲወገዱ ኅብረቱ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል፡፡ 

ለአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ዶ/ር ንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ ደብዳቤ ያስገቡ ሲሆን፣ በተመሳሳይ ለአውሮፓ ኅብረት ጽሕፈት ቤትም ተመሳሳይ ደብዳቤ አስገብተዋል፡፡

የቀይ ባህር አፋር ነፃ አውጭ በሚባለው ድርጅት በተዘጋጀው የተቃውሞ ሠልፍ ላይ ቁጥራቸው ከ30 ሺሕ በላይ የሆኑ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ፣ በሰመራ፣ በዱብቲ፣ በበራ ኃይሌ ካምፕ መገኘታቸው ሲታወቅ፣ በውጭ አገሮች በኒውዮርክና በጄኔቭም የተቃውሞ ሠልፉ መደረጉንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሠልፍ በማድረግ ለአፍሪካ ኅብረት ያቀረቡትን ደብዳቤ፣ የዶ/ር ድላሚኒ ዙማ ጸሐፊ ተቀብለው፣ ሊቀመንበሯ አስቸኳይ ምላሽ እንደሚሰጧቸው ነግረዋቸዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ግንቦት 28 ቀን 2007 ዓ.ም. ኤርትራን አስመልክቶ ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ፣ በእርስ በርስ ጦርነት እየወደመች ከምትገኘው ሶሪያ ቀጥላ ወጣት ዜጐቿ ወደ ስደት የሚጐርፉባት አገር መሆኗን ገልጿል፡፡

የኤርትራ ሰብዓዊ መብት አጣሪ ኮሚሽን በቀጥታ ኤርትራ ውስጥ ሆኖ በአገሪቱ ዜጐች ላይ የሚደርሰውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት መከታተልና መመራመር ባይችልም፣ ከ550 በላይ ስደተኛ ኤርትራውያንን በማነጋገርና የተለያዩ ጥናቶችን በማድረግ 484 ገጾች ያሉት ሪፖርት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ 24ኛ ዓመት የነፃነት ቀኗን በቅርቡ ያከበረችው ኤርትራ ላለፉት 24 ዓመታት ዜጐቿ የስቃይ፣ የሞትና የእስራት ሰለባ መሆናቸውን ሪፖርቱ አካቷል፡፡ የሚፈጸሙባቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችም ሆን ተብሎና ታስቦበት የሚደረጉና የዘር ማጥፋትን የሚያካትቱ መሆናቸውን ሪፖርቱ እንደሚያስረዳ መዘገባችን አይዘነጋም፡፡ 

 

በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የኦዲት ሪፖርት አተገባበር ላይ ትችት ቀረበ

የፓርላማው የመንግሥት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተሾመ እሸቱ፣ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የሚቀርብበትን የኦዲት ትችት ማስተካከል አልቻለም ሲሉ ከፍተኛ ወቀሳ ሰነዘሩ፡፡ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወቀሳውን ተቃውመዋል፡፡

የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ በከር ሻሌ የተቋማቸውን የአሥር ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ሰኔ 18 ቀን 2007 ዓ.ም. አቅርበዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ በሪፖርታቸው ገጽ 19 ላይ ከተለያዩ አካላት ለመሥሪያ ቤታቸው የተሰጡ አስተያየቶች ትልቅ ጠቀሜታ እንደነበረው ገልጸዋል፡፡ ‹‹የፌዴራል ዋና ኦዲተር በተቋማችን ላይ የሚያደርገውን ኦዲት ተከትሎ የሚላክልን የኦዲት ግኝት ለሥራ አፈጻጸማችን ትልቅ መሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጎልናል፤›› ብለዋል፡፡

የሪፖርት አቀራረብ ትክክል አይደለም ብለው ያመኑት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰበሳቢ አቶ ተሾመ እሸቱ፣ በአቶ በከር ላይ ትችታቸውን ሰንዝረዋል፡፡

የኦዲት ግኝትን በተመለከተ መቅረብ የነበረበት ሪፖርት በዝርዝር የተወሰደውን ዕርምጃ የሚገልጽ መሆን ነበረበት ያሉት አቶ ተሾመ፣ ይህንን ሕጋዊ ግዴታ ወደ ጎን ትቶ በደምሳሳው የኦዲት ሪፖርቱን ግብዓት አድርገነዋል ብሎ ማስቀመጥ ተገቢ አይደለም ብለዋቸዋል፡፡ 

የፌዴራሉ ዋና ኦዲተርን የሚከታተለው የፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ተሾመ፣ ‹‹ምናልባት የወሰድነውን ዕርምጃ ብንዘረዝር ከፓርላማው ክርክር ይገጥመናል ወይም ሪፖርቱ እንዳይረዝም ብዬ ነው የሚል ምላሽ ይቀርብ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከፋኝ ተብሎ ሕግ አይጣስም፡፡ የከፋን ቀን ሕግ ጥሰን መሄድ አንችልም፤›› ብለዋል፡፡

ችግሩ ለአምስት ዓመታት መቆየቱን ጠቅሰው፣ በዚህ  የሕግ ጥሰት ላይ ምን ዕርምጃ እንደተወሰደ ጠይቀዋል፡፡ ለቀረቡላቸው ትችት አዘል ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት የጀመሩት አቶ በከር፣ ‹‹ዋና ኦዲተር ያቀረበውን ሪፖርት አልካድኩም፤›› ብለዋል፡፡

ዋና ኦዲተር በትክክል ግኝት እንዳገኘ የተናገሩት አቶ በከር፣ ከዋና ኦዲተሩ ጋር በማጠቃለያ ስብሰባ ተነጋግረው ችግሮቹን ማየት መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡

‹‹ነገር ግን በፖሊሲ አስተዳደር ቦታ ላይ ተቀምጦ ማየትን ይጠይቃል፡፡ ግብር የተጣለበት ከፋይ ቅሬታ አቅርቦ ሲከራከር የተጣለው ግብር ለረዥም ጊዜ ሳይሰበሰብ ይቀራል፡፡ ይህ በኦዲት ቋንቋ ያልተሰበሰ ሒሳብ ነው፤›› ብለዋል፡፡

‹‹ሌላው አምራች ኩባንያዎችን ለመደገፍ የታክስ ክፍያ ጊዜያቸውን እያሰፋንላቸው እንሄዳለን፡፡ ይኼንን በማድረጋችንም ባለሀብቶችን እየደገፍን የመንግሥትን ግብር እያስከፈልን ነው፤›› ብለዋል፡፡

በቂ መረጃ እያለ ያልተሰበሰቡ ገቢዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም  የዋና ኦዲተርን አስተያየት እንደ ግብዓት እየተጠቀሙበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተለያዩ ኬላዎች የተያዙትን የውጭ ገንዘቦችና የከበሩ ማዕድናት በተመለከተ ተገቢውን የሕግ ሥርዓት አለመከተል ተገቢ ባይሆንም፣ ሕግን ባለማወቅ ሠራተኞች የፈጸሙት ስህተት ነው ብለዋል፡፡

 

ከአጋሮቹ ጋር በመሆን የፓርላማውን ወንበሮች ሙሉ በሙሉ ያሸነፈው ኢሕአዴግ፣ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት አገሪቱ በምትመራበት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውይይት ላይ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን እንደሚያሳትፍ አስታወቀ፡፡ 

ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ኢሕአዴግና አጋር ፓርቲዎች ሙሉ በሙሉ ማሸነፋቸው መገለጹ ይታወሳል፡፡ በዚህ መሠረት በሕዝብ ተወካዮችም ሆነ በክልል ምክር ቤቶች ውስጥ ተቃዋሚዎች ሐሳባቸውን የሚገልጹበት ዕድል ባለመኖሩ፣ ገዢው ፓርቲ ተቃዋሚዎች በአገራዊ ጉዳዮች ላይ እንዲሳተፉ እንደሚመቻች፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንንና የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን አስታውቀዋል፡፡

በዚህ መሠረት በዚህ ሳምንት በመላ አገሪቱ በሚጀመረው የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውይይት ላይ ተቃዋሚዎች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ከሰኔ 22 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት በሚካሄደው ውይይት ተቃዋሚዎች እንዲሳተፉ ባይጋበዙም፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚኒስትሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለዕቅዱ ግብዓት ወይም ሐሳብ የሚሰጡበት ራሱን የቻለ መድረክ ይዘጋጃል፡፡ 

‹‹ተቃዋሚዎች ከሕዝብ ጋር ተቀላቅለው ለውይይት ቢቀርቡ ሐሳባቸው ሊዋጥና በሚገባ ላይስተናገዱ ይችላሉ፤›› በማለት አቶ ሬድዋን ተቃዋሚዎች ለብቻቸው መድረክ እንደሚዘጋጅላቸው ገልጸዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ሁለት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተለያዩ ሐሳቦችን አራምደዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ጉዳዩን አጣጥለውታል፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ችግር በእንደዚህ ዓይነት መንገድ አይፈታም፡፡ ሥር የሰደደ ችግር አለ ከተባለ ሥር የሰደደ መፍትሔ ነው መቅረብ ያለበት፡፡ ለብ ለብ ሊሆን አይችልም፤›› በማለት በውይይቱ መሳተፍ ኢሕአዴግን እንደማጀብ አድርገው ገልጸዋል፡፡ 

የኢዴፓ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ወንድወሰን ተሾመ በበኩላቸው፣ መንግሥት በዕቅድ ሰነዱ ላይ ለመወያየት ይፋዊ ጥያቄ ያላቀረበ ቢሆንም ኢዴፓ ከመኢአድና ከኢራፓ ጋር በመሆን ሰላማዊ ትግሉ በሚቀጥልበት መንገድ ላይ መምከር መጀመራቸውንና በቅርቡም መግለጫ እንደሚሰጡበት አስታውቀዋል፡፡ በኢዴፓ በኩል መንግሥት ጥያቄ ካቀረበ በሥራ አስፈጻሚው በኩል ውይይት ተደርጎ እንደሚወሰን አቶ ወንድወሰን ተናግረዋል፡፡ 

በአቶ መኮንን ማንያዘዋል በሚመራው ብሔራዊ ፕላን ኮሚሽንና በከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በሚመሩ ኮሚቴዎች የተዘጋጀው ሁለተኛው የአምስት ዓመት ዕቅድ ሰነድ በዘርፍ፣ በዘርፍ ተከፍሎ ለውይይት ይቀርባል፡፡ 

በአዲስ አበባ ከተማ በተዘጋጁት አምስት መድረኮች አቶ ሬድዋን፣ ከንቲባ ድሪባ ኩማና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ዓባይ ፀሐዬ ውይይቱን ይመራሉ፡፡ 

በክልሎች የሚካሄዱትን የውይይት መድረኮች በተለይ በትግራይ ክልል የሚካሄደውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል፣ በአማራ ክልል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ በኦሮሚያ ክልል በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደርና ሲቪል ሰርቪስ ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሯ ወ/ሮ አስቴር ማሞና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙክታር ከድር፣ በደቡብ ክልል የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ በሐረሪ ክልል የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ መመደባቸውን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ 

ሁለተኛው የአምስት ዓመት ዕቅድ ሰነድ ውይይት የሚካሄደው በዘርፍ በዘርፍ ተከፋፍሎ ሲሆን፣ ጥሪ ከተደረገላቸው መካከል ወጣቶችና ሴቶች ለየብቻ፣ የግሉ ዘርፍ ተወካዮች፣ የመንግሥት ሠራተኞችና ምሁራን፣ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችና የአካባቢ ልማት ኮሚቴ ተወካዮች ይገኙበታል፡፡ 

አቶ ሬድዋን እንደገለጹት፣ ከፋፍሎ ማወያየቱ አስፈላጊ የሆነው ሁሉም በተሰማራበት መስክ በቂ ጊዜ ወስዶ ለመነጋገርና ስትራቴጂውን ለማሳካት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡ 

ጥሪ የተደረገላቸው ተወያዮችም በኢሕአዴግ መዋቅር ውስጥ ያሉ ብቻ ሳይሆኑ፣ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል የሚወክሉ እንደሆኑ አቶ ሬድዋን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 

 

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የፌዴራልና የክልል የጋራ ገቢ ተብሎ ከሚሰበሰበው ገቢ ውስጥ ድርሻው እንዲከፈለው ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያቀረበው ጥያቄ፣ የክልል መንግሥትነት ዕውቅና የሌለው በመሆኑ ውድቅ ተደረገ፡፡

የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 98 የፌዴራሉ መንግሥትንና የክልሎችን የጋራ ታክስና የግብር ሥልጣንን ይደነግጋል፡፡

በዚህም መሠረት የፌዴራል መንግሥትና ክልሎች በጋራ በሚያቋቁሟቸው የልማት ድርጅቶች ላይ የንግድ ትርፍ ግብር፣ የሥራ ግብር፣ የሽያጭና የኤክሳይስ ታክስ በጋራ እንደሚጥሉና እንደሚሰበስቡ ይገልጻል፡፡ በተጨማሪም በድርጅቶች የንግድ ትርፍ ላይና በባለአክሲዮኖች የትርፍ ድርሻ ላይ የግብርና የሽያጭ ታክስ በጋራ እንደሚጥሉና እንደሚሰበስቡ፣ በመጨረሻም በከፍተኛ የማዕድን ሥራዎች፣ በማናቸውም የፔትሮሊየምና የጋዝ ሥራዎች ላይ የገቢ ግብርና የሮያሊቲ ክፍያዎች በጋራ እንደሚጥሉና እንደሚሰበሰቡ ይደነግጋል፡፡ 

ይህንኑ ድንጋጌ መሠረት በማድረግ ከሚሰበሰበው የጋራ ገቢ ክልሎች ድርሻቸውን በመውሰድ ለልማት እያዋሉ የሚገኙ መሆኑን፣ በዚሁ አግባብም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የጋራ ገቢ ክፍፍል ድርሻውን እየወሰደ እስከ 2001 ዓ.ም. ድረስ ለልማት ሲያውል መቆየቱን፣ አስተዳደሩ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በደብዳቤ አሳውቋል፡፡ ከ2001 ዓ.ም. በኋላ ግን የገቢ ድርሻው መቋረጡን በመጥቀስ እንዲለቀቅለት ጥያቄውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አቅርቧል፡፡ የአስተዳደሩን ጥያቄ ለበጀት ድጐማና የጋራ ገቢዎች ድልድል ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመራው የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ ቋሚ ኮሚቴው ያቀረበለትን የውሳኔ ሐሳብ ሰኔ 17 ቀን 2007 ዓ.ም. አዳምጧል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የትምህርት ሚኒስትሩና የደቡብ ክልል ምክር ቤት ተወካዩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት፣ ቋሚ ኮሚቴው በድሬዳዋ አስተዳደር ጥያቄ ላይ በጥልቀት ከተወያየ በኋላ ሕገ መንግሥታዊ ትርጉም የሚያስፈልገው መሆኑ ስለታመነበት፣ ለሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ እንዲመራ በማድረግ ምላሽ ማግኘቱን አስታውቀዋል፡፡

የሕገ መንግሥት አጣሪ ጉባዔው ባደረገው ምርመራ ‹‹የኢፌዴሪ መንግሥት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 46(1) መሠረት በክልል መንግሥትነት ዕውቀና የተሰጣቸው ዘጠኙ ክልሎች መሆናቸውን፣ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 49(1) የፌዴራል መንግሥቱ አካል ተደርጐ የሚወሰደው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነው፤›› በማለት መግለጹን አቶ ሽፈራው ገልጸዋል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በፌዴራል መንግሥት በወጣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 416/1996 መሠረት ለጊዜው የፌዴራል መንግሥት አስተዳደራዊ አካል ቢሆንም፣ በሕገ መንግሥቱ በክልልነትም ሆነ በፌዴራል መንግሥት የአስተዳደር መዋቅር ውስጥ የሌለ በመሆኑ የሕገ መንግሥት ትርጉም የሚያስፈልገው ጥያቄ አይደለም በማለት ጉባዔው እንደወሰነ ተናግረዋል፡፡

በዚሁ መሠረትም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ውሳኔውን እንዲያውቀው መደረጉን አቶ ሽፈራው ለምክር ቤቱ አስረድተዋል፡፡

‹‹በሌላ በኩል ግን ከኅብረተሰቡ የልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት አንፃር የከተማ አስተዳደሩ ያቀረበው ጥያቄ አግባብነት ያለው መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው ያምናል፤›› ሲሉ አቶ ሽፈራው ተናግረዋል፡፡ 

ጉዳዩን በተመለከተ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የድሬዳዋ ከተማ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ፈቃዱ በየነ የከተማው አስተዳደር በውሳኔው ደስተኛ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ ‹‹የድሬዳዋ ከተማ በሕገ መንግሥቱ የክልል መንግሥትነት ዕውቅና እንደሌላት የታወቀ ነው፡፡ ነገር ግን የፌዴራል መንግሥት ከከተማው የሚሰበሰበው ገቢ ተቋዳሽ መሆን አለበት፡፡ ከተማዋ ወደ ኢንዱስትሪ መንደርነት እየተቀየረች ነው፡፡ መሠረተ ልማት ማሟላት ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ደግሞ ተጨማሪ ገቢ የከተማው አስተዳደር ሊያገኝ ይገባል፤›› ብለዋል፡፡

ከከተማው የሚሰበሰውን ገቢ የፌዴራል መንግሥት ብቻ እየወሰደ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ በሲሚንቶ ፋብሪካዎች ወይም አሁን በሚፈጠሩት ኢንዱስትሪዎች የሚለቀቅ ጢስና የአካባቢ ጉዳት ገፈት ቀማሽ ብቻ መሆን የለባቸውም ብለዋል፡፡ አስተዳደሩ በካቢኔ ደረጃ ተነጋግሮ ምላሽ የሚሰጥ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ 

የኦሮሚያ ክልልና የሶማሌ ክልል በድሬዳዋ ላይ ባነሱት የይገባኛል ጥያቄ የፌዴራሉ መንግሥት ባወጣው አዋጅ፣ ድሬዳዋ በጊዜያዊነት የፌዴራሉ መንግሥት መዋቅር አካል እንድትሆን መደረጉ ይታወሳል፡፡  

 

ግንባታው በመገባደድ ላይ ባለው የአዲስ አበባ-ሜኤሶ የባቡር መስመር ላይ በሐዲዶችና በመጋዘን የተከማቹ ንብረተቶች ላይ ተደጋጋሚ የዘረፍ ሙከራ እየተካሄደበት መሆኑ ተጠቆመ፡፡ ፖሊስ መሠረተ ልማቱንም ሆነ በግንባታ የሚሳተፉ

ሠራተኞች ደኅንነት ለማስጠበቅ የተጠናከረ ጥበቃ ማድረጉንና ዘራፊዎችንም ለሕግ ማቅረቡን ገልጿል፡፡

በተለይ በአዳማ ከተማ አካባቢ በመገንባት ላይ ባለው ጣቢያ ተደጋጋሚ ዘረፋ እንደሚፈጽም ተነግሯል፡፡ የጥበቃ ሠራተኞችና ቻይናዊያን ባለሙያዎችም በዘራፊዎች ተኩስ ተከፍቶባቸው እንደነበር ሪፖርተር ሥፍራው ድረስ በመሄድ ለመገንዘብ ችሏል፡፡

በግንባታ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞች ዘራፊዎች በጦር መሣሪያ ጭምር በሌሊት ካምፑን ሰብረው በመግባት በመጋዘን የሚገኙ ብረታ ብረቶችንና የግንባታ ግብዓቶችን ለመስረቅ ሙከራ እንደሚያደርጉም ጠቁመዋል፡፡

ከአዲስ አበባ-ሜኤሶ ባለው አጠቃላይ መስመር ላይ አንድ ሻምበል የተጠናከረ ፌዴራል የፖሊስ ኃይል የሚጠበቅ ቢሆንም፣ በአዳማ መጋዘኖች በሚገኙ ቦታዎች ግን ዘራፊዎች ከሠራተኞች ጋር በመመሳጠርም ዘረፋ ለማድረግ መሞከራቸው ተገልጿል፡፡

ግንባታውን እያካሄደ ከሚገኘው የቻይናው ሲአርሲሲ የተገኘ መረጃ፣ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከ100 ጊዜ በላይ የዘረፋ ሙከራዎች መፈጸማቸውን ያሳያል፡፡

የአዳማ 03 ቀበሌ አስተዳደር ኃላፊዎች በበኩላቸው፣ ተጠርጣሪ ዘራፊዎችን አድነው በመያዝ ለሕግ እያቀረቡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን እስካሁን ድረስ ምን ያህል የዘረፋ ሙከራ እንደተካሄደ ባይገልጹም፣ ሁለት ተጠርጣሪዎች ተይዘው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑን አንድ የአዳማ ከተማ አስተዳደር ኃላፊ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ሪፖርተር ከፖሊስ መረዳት እንደቻለው፣ ዘራፊዎች በምርመራ ወቅት ሲጠየቁ የዘረፉት ንብረት የአገሪቱ ሳይሆን የቻይና እንደሆነም አድርገው ይቆጥሩታል፡፡

የጥበቃ ሥራውን እያስተባበሩ የሚገኙት ምክትል ኢንስፔክተር እንግዳው ባዬ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በአብዛኛው ሕዝብ ዘንድ የመሠረተ ልማቱን በተመለከተ የተሻለ ግንዛቤ ያለ ቢሆንም፣ በጥቂቶች ዘንድ ያለው ግንዛቤ በተቃራኒው ስለሆነ ሰፊ የግንዛቤ ትምህርት መሰጠት አለበት፡፡

ኩባንያው በበኩሉ በቡድን የተደራጁና የጦር መሣሪያ የታጠቁ ዘራፊዎች በኢትዮጵያውያንና በቻይናውያን ሠራተኞች ላይ በተደጋጋሚ ማስፈራሪያ ሲፈጽሙ፣ በተለያዩ ካምፖች ግንባታ የሚቆምበት ጊዜ እንደነበር ገልጿል፡፡ 

የአገር አቀፍ የባቡር ትስስር አካል የሆነው የሰበታ-ሚኤሶ የባቡር መስመር  ግንባታው በቻይናው ሲአርሲሲ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ 329 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ይኼ ፕሮጀክት በቅርቡ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ለግንባታው 1.8 ቢሊዮን ዶላር በጀት እንደወጣበት ይነገራል፡፡ 

 

ድርጅታቸውን ለመታደግ አገር ቤት የተመለሱት የሆላንድ ካር ባለቤት ያቀረቡት ሐሳብ ውድቅ ተደረገ

በኪሳራ የተዘጋውን ሆላንድ ካር የመኪና መገጣጠሚያ ኩባንያቸውን ለመታደግ፣ ከሦስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ግንቦት 4 ቀን 2007 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት ኢንጂነር ታደሰ ተሰማ፣ ኩባንያውን እንዴት ሊታደጉት እንደሚችሉ

ያቀረቡትን ሐሳብ 201 የሚሆኑ ገንዘብ ጠያቂዎች ውድቅ አደረጉት፡፡

ኩባንያውን ከጨረታ ሽያጭ ያድናል ያሉትን ዕቅድ ነድፈውና ለመንግሥት አቅርበው ተቀባይነት በማግኘታቸው ወደ አገር ቤት የተመለሱት ኢንጂነር ታደሰ፣ ስድስት ሚሊዮን ብር ይዘው መምጣታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

201 የሚሆኑት የኩባንያው ደንበኞች መኪና ለመግዛት ከ62 ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ የፈጸሙ ቢሆንም፣ ኩባንያው በገባው ቃል መሠረት ሊፈጽም ባለመቻሉ ኪሳራ አሳውጆ ነበር፡፡

ቁጥራቸው 201 መሆናቸው የተጠቀሰው ገንዘብ ጠያቂዎች፣ ሰኔ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. የኩባንያው ባለቤት፣ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሬጅስትራርና የተለያዩ ኮሚቴዎች ተሰብስበው በኩባንያው ባለቤት ሐሳብ ላይ ውሳኔ አስተላልፈዋል፡፡

በጠበቃቸው አቶ ጥላሁን ምትኩ አማካይነት የኩባንያው ባለቤት ሐሳብ ተገልጿል፡፡ በዚህም መሠረት ኩባንያው ከኪሳራ ወጥቶ የባለገንዘቦቹን መብት እንደሚያስጠብቅ፣ በመገጣጠሚያ ፋብሪካው ውስጥ ያሉ 174 መኪኖችን ገጣጥሞ ለገበያ ለማቅረብ ስድስት ሚሊዮን ብር እንደተዘጋጀ፣ ተሽከርካሪዎቹ ተገጣጥመው እስከሚሸጡ ድረስ ንብረቶቹ በሙሉ በንብረት ጠባቂና መርማሪ ዳኛ ሥር እንደሚቆዩ ተናግረው፣ በሐራጅ ቢሸጡ ግን የሚገኘው ገንዘብ ከመንግሥት ግብር፣ ከባንክ ዕዳ፣ ከሠራተኞች ክፍያና ከንብረት ዕዳ ማጣሪያ ክፍያ እንደማይተርፍ በመግለጽ፣ በኢንጂነሩ ሐሳብ መስማማት ምርጫ የሌለው መሆኑን ጠበቃው አብራርተዋል፡፡ 

ገንዘብ ጠያቂዎቹ በበኩላቸው በሰጡት ምላሽ እንዳብራሩት፣ ኢንጂነር ታደሰ ያቀረቡት ሐሳብ ቀደም ብሎ በእንግሊዝኛ ካቀረቡላቸው የሚለየው በአማርኛ መቅረቡ ነው፡፡ የቀረበው የአፈጻጸም ዕቅድ ተዓማኒ እንዳልሆነና ለገንዘብ ጠያቂዎቹ ገንዘባቸው እንዴት እንደሚመለስና ምን ያህል ወለድ እንደሚያካትት አይገልጽም፡፡ ለ174 መኪናዎች መገጣጠሚያ ብለው ያቀረቡት ገንዘብ፣ ባለአንድ ፎቅ የሆነ ቤት እንኳን መግዛት አይችልም ብለዋል፡፡ ኩባንያው ሐሳብ ሲያቀርብ ስለዕዳው አከፋፈል በቅድሚያ የገንዘብ ዋስትና ማቅረብ ቢኖርበትም አለማቅረቡን፣ የከሰረው ኩባንያ ከፍተኛ ዕዳ ቢኖርበትም ከባንክና ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከፍተኛ ግብር ከፋዮች መሥሪያ ቤቶች ጋር ምን ዓይነት ስምምነት ላይ እንደደረሰ ባለማሳወቁ፣ ሐሳቡን ለመቀበል እንደማይችሉ አስረድተዋል፡፡

የከሰረው ኩባንያ ንብረት ጥበቃ ሹም አቶ ግርማ ዓለሙ የሚባሉት ግለሰብ ደግሞ፣ የኢንጂነር ታደሰን ሐሳብ ሌላ ጊዜ ጽፈው ከሚያቀርቡት የተለየ አለመሆኑን ተናግረው፣ የመክሰር ሥርዓት ሒደቱን ለማቋረጥና በስምምነት ሐሳቡ ለመቀጠል የሚያስችል፣ በንግድ ሕጉ ያሉ አስገዳጅ ሁኔታዎችን አሟልተው አለመቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡ ስድስት ሚሊዮን ብር እንዳቀረቡ ኢንጂነሩ ቢናገሩም፣ በቅድሚያ መፍትሔ ማግኘት ያለባቸው የቀድሞ ሠራተኞች ክፍያ፣ የፎርክሎዠር (በሐራጅ የመሸጥ) መብት ያለው ዘመን ባንክ ብድር ጉዳይና ለሌሎች የመንግሥት ክፍያዎች የሚበቃ ገንዘብ ስለመኖሩ ተጨባጭ ማረጋገጫ እንደሌለ ገልጸዋል፡፡

በንግድ ሕግ ቁጥር 1064(3) መሠረት የስምምነት ሐሳቡ በኩባንያው ሥልጣኑ በተሰጠው አስተዳዳሪ የፈረመበት ሆኖ ባለመገኘቱ፣ የኢንጂነር ታደሰ ውክልና ሥልጣን የተሰጣቸው ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ ስላልቻሉ፣ ሐሳቡ ተቀባይነት እንደሌለውም ተናግረዋል፡፡

በሕግ መሟላት የሚገባቸው ነገሮች ሳይሟሉ ስምምነት ላይ ቢደረስና ሥራ ቢጀመር፣ ንብረቶች ሊሸሹና ሊጠፉ ስለሚችሉ ሊመለስ የማይችል ጉዳት ሊደርስ እንደሚችልም አክለዋል፡፡

በመጨረሻም በውይይቱ ላይ የተለያዩ አስተያየቶች በመቅረባቸው ድምፅ እንዲሰጥበት ተደርጐ፣ በዕለቱ የተመዘገቡ 201 ግለሰቦች ወይም 62,516,068 ብር ካላቸው ገንዘብ ጠያቂዎች ውስጥ 54,982,120 ብር ያላቸው 134 ሰዎች ሐሳቡን ውድቅ አድርገውታል፡፡ በመሆኑም በንግድ ሕግ ቁጥር 1084 (1) መሠረት የስምምነት ሐሳቡ ተቀባይነት አለማግኘቱን፣ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዋና ሬጅስትራር አቶ መሠረት አያሌው በፊርማቸው አረጋግጠዋል፡፡