የዛይ ሕዝብ የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ አቅርቧል

የአማራ ክልል ምክር ቤት የቅማንት ሕዝብ ላነሳቸው ተጨማሪ የማንነትና ራስን የማስተዳደር ጥያቄ፣ ከዚህ ቀደም ዋናውን ችግር ለመፍታት በሄደበት መንገድ እንዲፈታ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ፡፡ 

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የመጨረሻ የሥልጣን ዘመኑን ማጠቃለያ ጉባዔ ሰኔ 17 ቀን 2007 ዓ.ም. ባካሄደበት ወቅት፣ የምክር ቤቱ የሕገ መንግሥትና ክልሎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ በቅማንት ሕዝቦች የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ ላይ ያቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ ነው ውሳኔውን ያሳለፈው፡፡ 

በአማራ ክልል የሚኖሩ የቅማንት ሕዝቦች የማንነትና ራስን የማስተዳደር ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄያቸውን በመጀመርያ ያቀረቡት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ነው፡፡ ምክር ቤቱም ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የሕገ መንግሥትና የክልል ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ኃላፊነቱን እንዲወስድ ማድረጉን የቋሚ ኮሚቴው ሪፖርት ያስታውሳል፡፡ 

ቋሚ ኮሚቴው የጥናት ቡድን አቋቁሞ ከአማራ ክልል፣ ከሰሜን ጎንደርና በየደረጃው ከሚገኙ የወረዳና የቀበሌ አመራሮችና ከአቤቱታ አቅራቢ ኮሚቴ ጋር በመተባበር ጥናት ማካሄዱን ይገልጻል፡፡ በዚሁ ጥናት በላይ አርማጭሆ፣ በጭልጋና በመተማ ወረዳዎች የወረዳ አመራሮችና የጥያቄ አቅራቢው ሕዝብ አስተባባሪ ኮሚቴ በመስማማት በመረጧቸው ናሙና ቀበሌዎች ባደረገው ጥናት ዕድሜ ጠገብ አዛውንቶች፣ አልፎ አልፎም ወጣቶች ቋንቋውን እንደሚናገሩና ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ሕፃናት ቋንቋውን ለመማር ከፍተኛ ጉጉት እንዳላቸው የጥናት ቡድኑ ማረጋገጡን የኮሚቴው ሪፖርት ይገልጻል፡፡ 

በጥናቱ ያልተሸፈነ ነው ያለውን ማኅበረሰቡ በተያያዘ መልከዓ ምድር መኖር ያለመኖራቸውን ያካተተ ጥናት ተጠንቶ እንዲቀርብለት ቋሚ ኮሚቴው ለጥናት ቡድኑ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውሷል፡፡ 

የጥናት ቡድኑ ከላይ በተገለጸው መሠረት ጥናቱን ለመቀጠል በተንቀሳቀሰበት ወቅት፣ የክልሉ መንግሥት በራሱ ተነሳሽነት ለጥያቄው ምላሽ ለመስጠት ኮሚቴ አቋቁሞ ሥራ መጀመሩን ገልጿል፡፡ በቋሚ ኮሚቴው የተላኩ አጥኚዎች ተልዕኮ ለጊዜው እንዲቆይና የክልሉ መንግሥት በራሱ ጥያቄውን ለመመለስ የጀመረው እንቅስቃሴ ውጤት እንዲጠበቅ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት፣ ጥያቄውን ቋሚ ኮሚቴው እንደተቀበለው ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡ 

ክልሉ ባካሄደው ጥናት የራስ አስተዳደር ጥያቄውን ዕውቅና ሰጥቶ የቅማንት ሕዝብ ራሱን ችሎ በኩታ ገጠም በሚኖርባቸው የጭልጋና የላይ አርማጭሆ ወረዳዎችን ማዕከል በማድረግ፣ ከሐምሌ 1 ቀን 2007 ጀምሮ የአስተዳደር በጀት ለመመደብና ሌሎች አስፈላጊ ሥራዎችን ለመሥራት የአማራ ክልል ምክር ቤት በ14ኛ መደበኛ ጉባዔው ውሳኔ ማሳለፉን በመግለጽ፣ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ሪፖርት ማድረጉን ቋሚ ኮሚቴው ገልጿል፡፡ የክልሉ መንግሥት ችግሩን ለመፍታት በተነሳሽነት ያሳየው ትብብርና ቁርጠኝነትን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አድንቆታል፡፡ 

ይሁን እንጂ የማኅበረሰቡ ተወካዮች የክልሉ ምክር ቤት የሰጠው ውሳኔ ሁሉንም ቀበሌዎች ያላካተተና የተሸራረፈ ውሳኔ ነው በማለት ተቃውሟቸውን በድጋሚ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ማቅረባቸውን፣ የሕገ መንግሥትና የክልል ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሪፖርት ይገልጻል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው በጥያቄው ላይ ውይይት በማድረግ የቀረበውን ተጨማሪ ጥያቄ ክልሉ ከዚህ በፊት ከፈታው ችግር በላይ ሊሆን እንደማይችል ግንዛቤ በመውሰድ፣ የክልሉ መንግሥት በጀመረው አግባብ ተጨማሪ ጥያቄውን እንዲፈታ የሚል አቋም በመያዙ የፌዴሬሽን ምክር ቤትም ይህንን ውሳኔ በመቀበል ለክልሉ ኃላፊነቱን በመስጠት እንዲወስን ሲል ጠይቋል፡፡ በቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ በመወያየትም ምክር ቤቱ ውሳኔውን ተቀብሎ አፅድቆታል፡፡ 

የቅማንት ሕዝብ በአማራ ክልል በስምንት ወረዳዎች በሚገኙ 126 ቀበሌዎች ውስጥ የራስ አስተዳደር ጥያቄ ያነሰ ቢሆንም፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ግን ባካሄደው ጥናት ላይ ተመሥርቶ መጋቢት 2 ቀን 2007 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ በሁለት ወረዳዎች በሚገኙ 42 ቀበሌዎች ላይ ነው፡፡ የቅማንት ሕዝብ ተወካዮች ለሪፖርተር በጽሑፍ እንደገለጹት፣ የክልሉ መንግሥት ጥያቄያቸውን እየሸራረፈና ተጨማሪ ጥያቄዎችን እያነሱ ባሉት ተወካዮች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡ 

‹‹ከዚህ ሁሉ የችግር ጫና ውስጥ የቅማንት ሕዝብ እየገባ ያለው ጥያቄው በይግባኙ መሠረት በፌዴሬሽን ምክር ቤት መመለስ ባለመቻሉ ነው፡፡ ይግባኝ የቀረበለት የፌዴሬሽን ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 251/1993 በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት የማያዳግም ውሳኔ ቢያስተላልፍ ይህ ሁሉ ችግር ውስጥ አይገባም ነበር፡፡ አሁንም በቀረበለት ይግባኝ መሠረት ውሳኔ እንዲያስተላለፍ አቤቱታችንን እናሰማለን፤›› ሲሉ ሰኔ 9 ቀን 2007 በጻፉት ደብዳቤ ፌዴሬሽን ምክር ቤትን ጠይቀዋል፡፡ 

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግሥትና የክልል ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ግን በአዋጁ መሠረት ኃላፊነት ቢኖረውም፣ ለክልል መንግሥታት ቀርበው ውሳኔ በተሰጠባቸው የማንነት ጥያቄዎች ቅር በመሰኘት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚቀርቡ አቤቱታዎችን በመመርመር፣ በምክር ቤቱ የውሳኔ ሐሳብ እንደሚያቀርብ በተሻሻለው የምክር ቤቱ የአሠራርና የአባላት ሥነ ምግባር ደንብ ቁጥር 1/1999 ኃላፊነት የተሰጠው በመሆኑ የክልሉን ውሳኔ በመመርመር እንደተቀበለው ገልጿል፡፡ 

ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ኃላፊነት በመውሰድ ጥናት ጀምሮ የነበረው አጥኚ ቡድንና የክልሉ ምክር ቤት ባካሄደው ጥናት ላይ በመመሥረት ያሳለፈው ውሳኔ ተመሳሳይነት ያላቸው በመሆኑ፣ ተጨማሪ ጥያቄውን የክልሉ መንግሥት በቀደመው አግባብ ቢመልሰው ችግር እንደማይኖረውም ቋሚ ኮሚቴው እምነቱ እንደሆነ ገልጿል፡፡ 

ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ ክልል ዝዋይ ሐይቅ ደሴት ላይ የሚኖሩት የዛይ ማኅበረሰብ የማንነትና ራስን የማስተዳደር ጥያቄ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡ የምክር ቤቱ የሕገ መንግሥትና የክልሎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ፣ የክልሉ መንግሥትና ምክር ቤት የዛይ ማኅበረሰብ ጥያቄን በተመለከተ ውይይት እያደረጉ መሆኑን በመጥቀሳቸው ጉዳዩ ለክልሉ ተትቷል፡፡ 

 

በደቡብ ክልል በጋብቻ ምክንያት በሐዲቾና በወላቢቾ ጎሳዎች መካከል የተቀሰቀሰውን ከፍተኛ ግጭት፣ የክልሉ ፖሊስ በአስቸኳይ እንዲቀርፍና ጥፋተኞችን ለሕግ እንዲያቀርብ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አሳሰበ፡፡ 

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሰኔ 17 ቀን 2007 ዓ.ም. ለደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በጻፈው ደብዳቤ፣ የፌዴራል ፖሊስን ወደ አካባቢው ማሰማራት አግባብነት እንደሌለው፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ሰላምና ፀጥታ ለማስፈን በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት ኅብረተሰቡ ተረጋግቶና ደኅንነቱ ተጠብቆ እንዲኖር ለማድረግ የሕዝብ አደራና ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስቧል፡፡ 

በዚህ የጎሳ ግጭት ተሳታፊ የሆኑት ሕገወጥ ድርጊት ፈጻሚዎች ላይ ምርመራው ተጣርቶ ለሕግ እንዲቀርቡ፣ የተፈናቀሉ ዜጎችም ወደ ቀድሞ መኖሪያ ቤታቸው እንዲመለሱ እንዲደረግ አሳስቧል፡፡ 

በሒዲቾና በወላቢቾ ጎሳዎች መካከል ግጭቱ የተቀሰቀሰው ከግንቦት 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ወዲህ ሲሆን፣ ምክንያቱ ደግሞ የሐዲቾ ጎሳ አባል የሆነ ግለሰብ ከወላቢቾ ጎሳ አባል ከሆነች አንዲት ግለሰብ ጋር በመጋባቱ ነው፡፡ 

ይህንን ጋብቻ ያልተቀበሉ የወላቢቾ ጎሳ አባላት፣ ‹‹እንዴት አናሳ ዘር ከእኛ ዘር ይጋባል?›› በማለት በአንድ ላይ በመነሳት በሐዲቾ ጎሳ አባላት ላይ ጥቃትና የንብረት ውድመት መፈጸማቸውን ከአካባቢው ለፌዴራል መንግሥት ተቋማት አቤት ለማለት ተወክለው የመጡ ግለሰቦች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 

የወላቢቾ ነዋሪዎችን ቤቶችና ንብረቶች በማቃጠልና ያገኙትን በመደብደብ፣ በበርካታ ነዋሪዎች ላይ ጉዳት ከማድረሳቸው በተጨማሪ ሰዎችን መግደላቸውን ተወካዮቹ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 

ጉዳዩን በተመለከተ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የወንዶ ገነት ወረዳ ፖሊስ ኃላፊ የተፈጠረው ግጭት በአሁኑ ወቅት መቀረፉን ገልጸው፣ የሞተ ሰው አለ መባሉን አስተባብለዋል፡፡ 

የፖሊስ ኃላፊው ይህንን ይበሉ እንጂ፣ የሐዲቾ ጎሳ አባላት በርካቶቹ እስካሁን ወደ መኖሪያቸው እንዳልተመለሱና አሁንም ሥጋት ውስጥ መሆናቸውን ተወካዮቹ ይናገራሉ፡፡  

 

በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ተገንብተው አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ ተብለው የሚጠበቁ ስምንት የዓለም አቀፍ ብራንድ ሆቴሎች መምጣትን ተከትሎ፣ ኢትዮጵያ ከአሥር ዋና ዋና የአፍሪካ አገሮች ውስጥ አንዷ

ለመሆን እንደቻለች ታወቀ፡፡ በአፍሪካ በሆቴል ኢንቨስትመንት ውስጥ ስማቸው ከሚጠቀስ ኩባንያዎች መካከል ሒልተን ዓለም አቀፍ፣ በአዳዲስ ሆቴሎች ግንባታና በመኝታ ክፍሎች ብዛት ቀዳሚውን ሥፍራ መያዙን ጥናቶች ጠቁመዋል፡፡ 

ላለፉት አራት ዓመታት ‘አፍሪካ ሆቴል ኢንቨስትመንት ፎረም’ በሚል ርዕስ ዓመታዊ ጉባዔ በማካሄድ ላይ የሚገኘው የእንግሊዙ ቤንች ኤቨንትስ ይፋ ባደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ መሠረት፣ በኢትዮጵያ የሚገነቡት ስምንት ሆቴሎች በጠቅላላው ከ1,300 በላይ ክፍሎች እንደሚኖሯቸው ይጠበቃል፡፡ በአንፃሩ በአፍሪካ ከ270 በላይ ሆቴሎች እንደሚገነቡ ሲጠበቅ፣ ከ30 ሺሕ ያላነሱ ክፍሎች እንደሚይዙም ቤንች ኤቨንትስ ጥናቶችን ጠቅሶ ያሠራጨው መግለጫ ያመለክታል፡፡ 

በአፍሪካ ግብፅ በ18 አዳዲስ ሆቴሎች ግንባታ የመጀመሪያውን ረድፍ በመያዝ እየመራች ትገኛለች፡፡ ሞሮኮ፣ ናይጄሪያ፣ አልጄሪያ፣ ቱኒዝያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሊቢያ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሩዋንዳ በቅደም ተከተል ከአንድ እስከ አሥር ያለውን ደረጃ በመያዝ ግብፅን ይከተላሉ፡፡ በእነዚህ የሆቴል ግንባታዎች ላይ ትልቁን ድርሻ የያዘው ሒልተን ዓለም አቀፍ መሆኑም ታውቋል፡፡ በክፍሎች ብዛት ቀዳሚነቱን የያዘው ሒልተን ከ7,200 በላይ ክፍሎች ያሏቸውን 29 ሆቴሎች በአፍሪካ እየገነባ እንደሚገኝ ሲገለጽ፣ ማሪዮት ሆቴል በበኩሉ በ36 ሆቴሎች እየመራ ቢሆንም፣ በክፍሎች ብዛት ግን 6,412 ላይ በመወሰኑ ከሒልተን ባሻገር በካርልሰን ሬዚዶር ተቀድሟል፡፡ 

በሌላ በኩል ከወራት በፊት በአዲስ አበባ ተካሂዶ ዓለም አቀፍ ትኩረትን ስቦ የነበረው የአፍሪካ ሆቴል ኢንቨስትመንት ፎረም፣ በመጪው ዓመት መጀመሪያ ላይ በድጋሚ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የፎረሙ አዘጋጆች ከወራት በፊት ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ ለአራተኛ ጊዜ ተካሂዶ በነበረው ፎረም ሪከርድ የሰበረ ተሳትፎና ያልተጠበቀ ዓለም አቀፍ የሚዲያ ሽፋን ማግኘቱ በአዲስ አበባ በድጋሚ እንዲካሄድ ለመወሰን ምክንያት ሆኗል፡፡ ከዚህም ባሻገር በሆቴልና በሌሎች የኢንቨስትመንት መስኮች የተሰማሩ ትልልቅ ኩባንያዎች ያሳዩት ፍላጎትና ተሳትፎም ጉባዔው በድጋሚ አዲስ አበባ እንዲካሄድ ማስገደዱን፣ ፎረሙን የሚያዘጋጀውና መገኛው እንግሊዝ የሆነው ቤንች ኤቨንትስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ማቲው ዌይስ ገልጸው ነበር፡፡ 

ከአምስት ዓመት በፊት ጀምሮ የአፍሪካ ሆቴሎች ኢንቨስትመንት ፎረም በአዲስ አበባ እንዲካሄድ ለማድረግ ሲንቀሳቀስ የቆየው አገር በቀሉ ካሊብራ ሆስፒታሊቲ ኮንሰልታንሲ ኤንድ ቢዝነስ ኩባንያ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡ ስለፎረሙ በድጋሚ መምጣት ከሪፖርተር ጥያቄ የቀረበላቸው የካሊብራ አማካሪ ኩባንያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ነዋይ ብርሃኑ፣ በመጪው ዓመት መስከረም ወር አጋማሽ ላይ እንዲካሄድ ቀነ ቀጠሮ የተያዘለት ፎረም እንዲመጣ መወሰኑ እንደማይቀር ከዚህ ቀደም የታየው ስኬታማ ዝግጅት ጠቋሚ እንደነበር መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡

ከሆቴሎች ባሻገር በካሊብራ አማካሪ ኩባንያ በኩል ድርድር እያደረጉ ከሚገኙ መካከል ሦስት ተጨማሪ ሆቴሎች፣ ቀጣዩ ፎረም ከመካሄዱ በፊት ስምምነት ይፈጽማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ ነዋይ ለሪፖርተር መግለጻቸውን በመጥቀስ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ለሁለተኛ ጊዜ በሸራተን አዲስ ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው ፎረም፣ በቅርቡ ሥራ የጀመረው የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅትና የኢትዮጵያ ቱሪዝም ምክር ቤት እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተሰምቷል፡፡ ቤንች ኤቨትንስ ኩባንያም ለእነዚህ መንግሥታዊ ተቋማት ፎረሙ በድጋሚ በአዲስ አበባ እንዲካሄድ የኩባንያው ቦርድ መወሰኑን በደብዳቤ እንዳሳወቃቸው ታውቋል፡፡

በዚህ ቀደም የተካሄዱትን የአፍሪካ ሆቴል ኢንቨስትመንት ፎረሞችን ሞሮኮ አንድ ጊዜ፣ ኬንያ ሁለት ጊዜ ያስተናገዱ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ መጪውን ጨምሮ ለሁለተኛ ጊዜ በማስተናገድ ኬንያን ትስተካከላለች፡፡ ከስድስት መቶ በላይ ተሳታፊዎች፣ በርካታ የአገር ውስጥና የውጭ ዓለም አቀፍ ሆቴሎችና አማካሪዎች፣ እንዲሁም የሆቴል አስተዳዳሪዎች በስፖንሰርነት የታሰተፉበት ከፍተኛው ፎረም በአዲስ አበባ መካሄዱን ቤንች ኤቨንትስ አስታውቋል፡፡ በመጪው ፎረም በስፖንሰርነት ለመሳተፍ ከወዲሁ ከተመዘገቡት መካከል ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ኩባንያ ግንባር ቀደምት ሆኗል፡፡ 

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ብራንድ ያላቸው ሆቴሎች ቁጥር ሦስት ብቻ መሆናቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በመጪዎቹ አምስት ዓመታት አገሪቱ ይኖራታል ተብሎ የሚጠበቀው ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን የሚያሟሉ ብራንድ ሆቴሎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን እንደሚጨምር ትንበያዎች ይጠቁማሉ፡፡ በአገሪቱ ያሉ ጠቅላላ ባለ ኮከብ ሆቴሎች ቁጥር 120 ሲሆን፣ ያሏቸው የመኝታ ክፍሎች ብዛትም ከአንድ ሺሕ በታች ነው፡፡ 

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከግንቦት 1988 እስከ ሚያዝያ 1997 ዓ.ም. ድረስ ባሉት ጊዜያት በሕገወጥ መንገድ የተያዙ ይዞታዎችን ሕጋዊ ለማድረግ ባወጣው መመርያ ለመስተናገድ ከቀረቡ 91 ሺሕ ጥያቄዎች፣ ለተወሰኑት ሕጋዊ ካርታ ተሰጠ፡፡ 

የአዲስ አበባ ይዞታ አስተዳደር ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የቀረቡለት ጥያቄዎች ላይ ባካሄደው ማጣራት 32 ሺሕ የሚጠጉት ጥያቄዎች ቦታውን የያዙት ከ1997 ዓ.ም. በኋላ በመሆኑ ውድቅ ሲያደርግ፣ በበጀት ዓመቱ ለአምስት ሺሕ ሕገወጥ ባለይዞታዎች ሕጋዊ ካርታ መስጠቱ ታውቋል፡፡  

የአዲስ አበባ ከተማ ይዞታ አስተዳደር ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ደረጀ ላቀው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ የተያዙ ቦታዎች 44,547 ናቸው፡፡ ነገር ግን ምዝገባ በሚካሄድበት ወቅት ከ91 ሺሕ በላይ ጥያቄዎች መቅረባቸውን አቶ ደረጀ ገልጸው፣ 32 ሺሕ ያህሉ በመመርያው መሠረት ሊስተናገዱ የማይችሉ ናቸው ብለዋል፡፡

በዚህ ወር መጨረሻ በሚጠናቀቀው የበጀት ዓመት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ አምስት ሺሕ ቦታዎች ሕጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ሰጥቷል፡፡ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ አጠቃላይ ሥራውን በዚህ በጀት ዓመት የማጠናቀቅ ዕቅድ ቢኖረውም፣ የማጣራት ሥራው በመብዛቱ በሚቀጥለው በጀት ዓመት ቀጣይ ሥራዎች እንደሚኖሩ አቶ ደረጀ አስረድተዋል፡፡

ከ1988 እስከ 1997 ዓ.ም. ባለው ጊዜ የተያዙ ይዞታዎች ቢሆኑም፣ ከማስተር ፕላኑ ጋር የሚቃረኑ በመሆናቸው 2,346 ባለይዞታዎች ምትክ ቦታ እንዲሰጣቸው ለመሬት ባንክና ማስተላለፍ ኤጀንሲ መላካቸውን አቶ ደረጀ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከሕጋዊ ይዞታ ውጪ አስፋፍተው መሬት ከያዙና የይጠቃለልኝ ጥያቄ ካቀረቡ 14 ሺሕ ባለይዞታዎች ውስጥ፣ 3,160 የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንደታተመላቸው፣ ከሁለት ሺሕ በላይ የሚሆኑት ከማስተር ፕላኑ ተቃርኖ ያለው ይዞታ አጠቃለው በመያዛቸው ጥያቄዎቻቸው ተቀባይነት እንዳላገኙ አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ1988 ዓ.ም. በፊት የተያዙ 65 ሺሕ ሰነድ አልባ ይዞታዎች ጥያቄ ማስተናገዱም ይታወቃል፡፡ ከዚህ በኋላ ከ1988 እስከ 1997 ዓ.ም. ድረስ የተያዙ ቦታዎች ከማስተር ፕላኑ ጋር ተቃርኖ የሌላቸው መሆኑ ከተረጋገጠ እንዲያስተናግዱ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

ነገር ግን አሁንም ቢሆን ከ1997 ዓ.ም. በኋላ በሕገወጥ መንገድ ይዞታ የያዙ ግለሰቦች መንግሥት እንዲያስተናግዳቸው በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

 

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

በነ ዘመነ ካሴ መዝገብ የተከሰሱት 5 የመኢአድ አባሎች ናቸው አንዳርጋቸው ፅጌን በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርብላቸው ነው የጠየቁት የተከሰሱት የግንቦት 7 አባል ናችሁ ተብለው ነው በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ስልጠና ተሰጥቷችሁ የሽብር ተግባር ለመፈጸም ስትንቀሳቀሱ ነበር ተብለው ላለፉት ሁለት አመታት በእስር የሚገኙት እነዚህ ተከሳሾች አንዳርጋቸው ፅጌ የሚባል ሰው አናውቅም አንዳርጋቸው አሱ አውቃቸዋለሁ አሰልጥኛቸዋለሁ የሚል ከሆነም በናንተ ቁጥጥር ስር […]

ምርጫው ወያኔ በሚፈልገው እንደውም ባቀደው መንገድ አጠናቋል። “እረጭ ያለ ምርጫ”። እስከቅርብ ጊዜ እንዲደርሰን የተደረገው መረጃ ምርጫውን በመቶ ፐርሰንት ማሸነፋቸውን ነበር። አሁን ለይቶለታል። በመቶ ፐርሰንት ማሸነፋቸውን ብቻ ሳይሆን በተወሰኑት ምርጫ ጣቢያዎች ላይ አገኘንም የሚሉት ድምጽም በተመሳሳይ መቶ ፐርሰንት እንደሆነም ነው። ሌብነቱ እንዳለ ሆኖ ምርጫውን ከዚህ በተሻለና በሚመስል መንገድ ከውኖ በመንግስትነት ለመቀጠል መሞከሩን የሚያውቁት ነበር። አልፈለጉትም እንጂ […]

ብቻውን ሆኖ ከጥግ ቆሞ ይቆዝማል። ጸጉሩን እየፈተለ ይናደዳል . . . ብቻውን ያልጎመጉማል። ትንሽ ቆይቶ ያለቅሳል። ለጉድ! ያነባዋል። ሰው እንዳለ እንደሌለ አካባቢውን ይቃኛል። ገና ወደዚህ አካባቢ እንደመጣ ሲብስበት በሰው ፊት ያለቅስ ነበር። አሁን አሁን ግን ሲያለቅስ ሰው ሲያየው አይወድም። መጀመሪያ አካባቢ ጎረቤቶቹ ሲያለቅስ ሲመለከቱ ያጽናኑት ነበር። በኋላ ግን ቀውሷል ብለው ደመደሙ። እንዲያው በደፈናው ግማሾቹ ፍቅር […]

‹‹ደቀ መዛሙርቱ ከየአህጉረ ስብከቱ ተመርጠው ሲላኩ የቤተ ክርስቲያን ልጆች መኾናቸው እና የሃይማኖታቸው ጥንካሬ ታይቶ እንዲመለመሉ አህጉረ ስብከት ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል፡፡›› ‹‹ወደ ኮሌጅ የሚገቡ ተማሪዎች እና የሚያስተምሩ መምህራን መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ዕውቀታቸው እና መንፈሳዊ ሕይወታቸው እየታየ ወደ ኮሌጁ ገብተው እንዲማሩ እና እንዲያስተምሩ  ይደረግ፡፡›› /የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የጥቅምት ፳፻፬ ዓ.ም. ውሳኔ/ ‹‹የቤተ ክርስቲያን ከፍተኛየትምህርት ተቋማት እና …

መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ እስር ላይ ቆይተው እንዲፈቱ ተወስኖላቸው ከእስር ቤት ሲወጡ እንደገና በፖሊስ ተይዘው የታሰሩት ወንይሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለወርቅ ላይ ፖሊስ አዲስ ክስ አቀረበ፡፡ እነ ወይንሸት ሰኔ 18/2007 ዓ.ም ቀደም ብለው ተከሰውበት በነበረው ተመሳሳይ ‹ወንጀል› ፖሊስ የምርመራ መዝገብ ይዞ ቀደም ብለው ውሳኔ ባገኙበት በተመሳሳይ ቄራ ፍርድ ቤት ቀርበው ዳኞቹ ‹‹እኛ ፈርደናል፤ እንዲለቀቁም […]

“ለቤተመጻህፍታቸው ጥሩ ፎቶዎች ያገኛሉ” ዳግም የመመረጥ ጭንቀት በማይኖርበት በሁለተኛው የአስተዳደር ዘመን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደታየው የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች አፍሪካን ለዕረፍት ይጎበኛሉ፤ ይዝናናሉ፡፡ የዱር እንስሳትን ያያሉ፤ “የአገራቸውን ባህል ልብስ” ከለበሱ የአፍሪካ ሹመኞች ጋር ጥሩ ፎቶዎችን ይነሳሉ፤ የሥልጣን ዘመናቸው ካለቀ በኋላ ለሚመሠርቱት ቤተመጻህፍት ማስዋቢያ የሚሆን ለየት ያሉ ፎቶዎችን ይሰበስባሉ፡፡ መጪው ወር (July) መገባደጃ አካባቢ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ […]

The post ኦባማ “የዕረፍት ጊዜ ለማሳለፍ” ወደ ኢትዮጵያ ይጓዛሉ appeared first on ሳተናው .

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“በኢትዮጵያ ያሉ ሚንስትር ድኤታዎች ድምፅ አልባ እና ተሳትፎ የሌላቸው ደካማዎች ናቸው” ሲል የኢህአዴግ ጽ/ቤት የአመራር ግንባታ የመለስ ዜናዊ የአመራር ግንባታ ክፍል ያወጣው ደብዳቤ አመለከተ። ደብዳቤው ዝቅተኛ እና መካከለኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ያላቸውን ሚኒስትር ድኤታዎች ዘርዝሮ አስቀምጧል። በአቶ አዲሱ ለገሰ የሚመራው እና ከፍተኛ የኢህአዴግ አባላትን ብቻ የሚያሰለጥነው …

ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምንጮች እንደገለጹት የሮመዳንን ጾም ተከትሎ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ተቃውሞ እንደገና ሊያገረሽ ይችላል በሚል ስጋት፣ 53 ሚሊየን ብር በጀት በመመደብ የመስጊድ ኢማሞችን በአክራሪነት ዙሪያ የማሰልጠን እና የማግባባት ስራውን እያከናወነ ነው፡፡ አንዴ ሞቅ ሌላ ጊዜ ቀዝቀዝ ሲል የሚታየው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አሁንም መንግስትን እንቅልፍ እንደነሳው ነው፡፡ በሁሉም ክልልች ለሚገኙ …

ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በብዙ መቶ ሚሊዮኖች ብር ወጪ ይሰራል የተባለውን የመለስ ፋውንዴሽን ለማስገንባት ህዝቡ በፈቃደኝነት ገንዘብ ያዋጣል ተብሎ ሲጠበቅ፣ የህዝቡ መልስ አስደንጋጭ መሆኑን የተረዳው በወ/ሮ አዜብ መስፍን የሚመራው ፋውንዴሽን፣ የመንግስት ስልጣንን በመጠቀም የመንግስት ደሞዝ ተከፋይ ሁሉ ገንዘብ እንዲያዋጣ ለማስገደድ ሞክረዋል። ግምገማ በመፍራትና በግዳጅ ገንዘብ እንዲያዋጡ ከተደረጉት መካከል የመከላከያ ሰራዊት …

ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወጣት ተመስገን ታፈሰ ተሰማ ዕድሜው 22 ዓመት ሲሆን በትምህርት ደረጃውም በማኔጅመንት የመጀመሪያ ድግሪ ያገኘ ወጣት ነው፡፡ ትውልዱና ዕድገቱ በደቡብ ክልላዊ መንግስት በቡርጂ ወረዳ ውስጥ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የኢማዴ-ደህአፓ/መድረክ አባል ሆኖ ለመታገል የወሰነና በመድረክ አባልነታቸው ምክንያት በሀገራቸው ሠርተው የመኖር የዜግነት መብታቸውን እየተነፈጉ አስተዳደራዊ ግፍ እየተፈጸመባቸው ካሉ …

ኢሳት ዜና (ሰኔ 18፥ 2007) በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ ባለው ዘረኝነትና አስተዳደራዊ በደል በመንገፍገፍ ከሰራቱ የሚለዩት የበረራ ባለሙያዎች ቁጥር እየጨመረ መገኘቱን እንዲሁም ሙስና በከፍተኛ ደረጃ መስፋፋቱን የአየር ሀይል ምንጮች ለኢሳት ገለጹ።  በህገ-ወጥ የሰው ዘውውር የአየር ሀይል አባላት የታሰሩ መሆናቸውንም  ለመረዳት ተችሏል። በ2007 አ/ም ብቻ አስር የበረራ ባለሙያዎች ስርአቱን በመክዳትና ወደ እስር ቤት በመጋዝ ከአየር ሀይሉ …

የእንግሊዝ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 18/2007 ዓም በአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ ባወጣው መግለጫ የኢህአዴግ/ወያኔን መንግስትን ማስጠንቀቁን ሮይተርስ ዘገበ አቶ አንዳርጋቸው የህግ ድጋፍ በማያገኙበትና ይግባኝ ሊጠይቁ በማይችሉበት ሁኔታ በአስከፊ ሁኔታ መታሰራቸውን የእንግሊዝ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ፊሊፕ ሀሞንድ አውግዘዋል። የአቶ አንዳርጋቸው አያያዝ እና ደህንነት እንደሚያሳስበን በተደጋጋሚ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሃኖም ብንገልጽም ከቃል ያለፈ መልስ አለገኘንም፣ […]

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ሰኔ ፲፰ (አስራ ሰምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንም አይነት መረጃ ወደ ውጭ እንዳይወጣ ከፍተኛ ቁጥጥርና ክትትል የሚደረግበት ከሰኔ አንድ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን አዘጋጅነት የተጀመረው ግምገማ ፈታኝ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። ግምገማውን ተከትሎ አንዳንድ ፖሊሶች በደህንነቶች ተደብድበዋል። በጉለሌ ክፍለከተማ መምሪያ ስር የሚገኙ አንድ የሳጅን ማእረግ ያለውና አንድ ተራ ፖሊስ የአቶ …

ሰኔ ፲፰ (አስራ ሰምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ አንዳርጋቸው የህግ ድጋፍ በማያገኙበትና ይግባኝ ሊጠይቁ በማይችሉበት ሁኔታ በአስከፊ ሁኔታ መታሰራቸውን የእንግሊዝ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ፊሊፕ ሀሞንድ አውግዘዋል። የአቶ አንዳርጋቸው አያያዝ እና ደህንነት እንደሚያሳስበን በተደጋጋሚ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሃኖም ብንገልጽም ከቃል ያለፈ መልስ አለገኘንም፣ የምክር እና ራሳቸውን መከላከል የሚችሉበት መብትም አላገኙም ሲሉ የገለጹት …

ሰኔ ፲፰ (አስራ ሰምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤትን በመጥቀስ ሪፖርተር እንደዘገበው በማዕድን ሚኒስቴር ላይ በ2006 ዓ.ም. አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም ላይ ባደረገው የክዋኔ ኦዲት አገሪቱ ከፍተኛ ገንዘብ ማጣቷን አረጋግጧል፡፡ የማዕድን ሥራ አዋጅ ቁጥር 678/2002 የከበሩ ማዕድናት ላይ ስምንት በመቶ ፣ያልከበሩ ማዕድናት ላይ ደግሞ ስድስት በመቶ የሮያሊቲ ክፍያ መጣሉን ሪፖርቱ …

እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለትግሬዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለኦሮሞዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለአማራዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለሶማሌዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለአፋሮች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለኦጋዴኖች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለአኙዋኮች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለሲዳማዎች ጥብቅና […]

‘የአፍሪቃ ድሃ ባይጠግብም እንኳ ቀምሶ ካደረ ይበቃዋል’ አይነት ንቀት የተሞላው የምዕራቡ አለም ምልከታ ከመቼውም ጊዜ በከፋ መልኩ አፍጦና አግጦ እየታየ ነው፡፡ በርሃባችንና በእርስ በእርስ መናቆራችን ለዘመናት ሲነግዱበትም ሲማረሩበትም ቆይተዋል፡፡ ዛሬ ዛሬ የመጫወቻው ካርድ ተቀይሮ ለአፍሪቃ አንባገነኖች አንድ ቃል ተለጥፎላቸው ካሳላፍነው ታሪክ ምናልባትም በከፋ መልኩ ጉዟችንን ቀጥለናል፤ የኋሊት ይሁን ወደፊት እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ነገር ግን የምዕራቡ አለም […]

ኢትዮጵያዊያን፤ ተከታታይ አምባገነን መሪዎችን ከነአገልጋዮቻቸው ለማስወገድና የሕዝቡን የሥልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ የምናደርገው ትግል፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ ነው። በ ፲፱፻፷፮ ዓመተ ምህረት ሕዝቡ የተነሳባቸው የመብትና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄዎች አሁንም አልተመለሱም። ይኼው ሃምሳ ዓመት አለፈው። ይባስ ብሎ ሕዝቡን የመንግሥት አገልጋይ አድርጎ የሚጠቀም ጠባብ አምባገነን ገዢ፤ በሀገራችን ነግሷል። ይኼን መንግሥት ለማስወገድ የሚደረገው ትግል ማዕከል የለውም። በሀገር ቤት ከፍተኛውን […]

በሕብረተሰባች ውስጥ ንዝህላልነት ወይም ዳተኛነት ጎልቶ ይታያል፤ ራሱን፣ ትውልዱን ፣ሀገሩን ጭምር፣ለዘለቄታው ለሚጠቅሙ ጉዳዮች ላይ ያለው ተሣትፎ የቀዘቀዘ ነው። መንስዔውን ለመግለጽ በተረጋገጠ እውነት ላይ የተመሠረተ ማስረጃ የለኝም። ሆኖም በጋራም ሆነ በተናጠል ለሚመራበት፣ የፖለቲካ ሥርዐት በአሉታም ሆነ በአዎንታ ፍላጎቱን በነፃነት መግልጽ አይችልም፤ ላለፉት ሁለተ አሥርት ዓመታት በቁርጥኝነት ራሱን ገልፆ ለራሴም ለሀገሬም ይጠቅማሉ በሎ ያመነበትን ይዞ የቀጠለበት ሁኔታ […]

ወጣቱ ፖለቲከኛ ዳዊት አስራደ የሚወዳቸውን ቤተሰቡንና ልጁን ትቶ ከሀገር መሰደዱ ተሰምቷል፡፡ ዳዊት ከ13ቱ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ እንዲሁም የብሄራዊ ምክር ቤት አባልና የአንድነትን የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድም ከሌሎች የፓርቲው አመራሮች ጋር በመሆን የነደፈ ሙሉ ማንነቱን ለሀገር ትግል የሰጠ ቁርጥ ኢትዮጵያዊ ልጅ ነው፡፡ በ2002 ዓ.ም በአማራ ክልል ምርጫ ቅስቀሳ ላይ እያለ በመኪና ተገጭቶ ለ6 […]

ከሀገር ውጭም በስደት በሕውሓት ሰላዮች ክትትል ይደረግባቸው የነበሩ ኢትዮጵያውያኖች ከሰዳን ወደሊቢያ ገዞ ላይ እንዳሉ የሕውሓት ሰው ከሱዳን አቻው ጋር በመሆን በሱዳን ወታደራዊ ተሽከርካሪ ስደተኞቹ የተሳፈሩበትን ተሽከርካሪ በመግጨት አና እንዲገለበጥ በማድረግ አዳጋ ከደረሰባቸው መካከል የሥርዓቱ ሰው የነበረን ቁስለኛ ከሌሎች ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል ፎቶ ከኪሱ በማውጣት ከፎቶው ካስተያየ በኋ በያዘው ሽጉጥ እንደረሸነው የአይን ምስክር ከሞት በተረፉት ሊጋለጥ […]

የተከሰሱት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እስር ተፈረደባቸው

መንግሥት በጠራው ሰላማዊ ሠልፍ ላይ ሁከት ፈጥረዋል ተብሎ ክስ የተመሠረተባቸው የሰማያዊ ፓርቲ አባላት፣ በሁለት ወራት እስራት እንዲቀጡ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምብድ ችሎት ሰኔ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ፍርድ ሰጠ፡፡

በሊቢያ አይኤስ የተባለው ቡድን በኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመውን አሰቃቂ ግድያ ለማውገዝ፣ መንግሥት ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በጠራው ሰላማዊ ሠልፍ ላይ ረብሻ በመፍጠር፣ በመሳደብና ድንጋይ በመወርወር ሰላማዊ ሠልፉን አውከዋል ተብለው የተከሰሱት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ወይንሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤተልሔም አካለወርቅ መሆናቸው ይታወሳል፡፡

ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ የቀረበባቸውን ክስ ሊከላከሉ እንዳልቻሉ ገልጾ ጥፋተኛ ካላቸው በኋላ፣ የቅጣት አስተያየት ጠይቋል፡፡ ዓቃቤ ሕግ ቅጣቱ ከብዶ እንዲቀጡ አመልክቷል፡፡ ተከሳሾቹም የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን፣ በተለይ ወይንሸት ሞላ ረብሻ ተፈጠረ በተባለበት ዕለት ጠዋት የታሰረች መሆኗንና የታሰረችበትን ፖሊስ ጣቢያ ገልጻ ቅጣቱ እንዲቀልላት ጠይቃለች፡፡

ፍርድ ቤት በሰጠው ፍርድ ቅጣቱ ከብዶ እንዲቀጡ የሚለው የዓቃቤ ሕግን የቅጣት ማክበጃ አስተያየት የተቀበለ ቢሆንም፣ በቡድን ስለመረበሻቸው ያቀረበው ማስረጃ እንደሌለ ገልጿል፡፡ በመሆኑም እያንዳንዳቸው እጃቸው ከተያዘበት ጀምሮ ያለው ጊዜ ተቆጥሮ፣ በሁለት ወራት እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ሰጥቷል፡፡ ተከሳሾቹ ሁለት ወራት ከአንድ ቀን የታሰሩ በመሆናቸው በዕለቱ እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ፍርደኞቹ የማስፈቻ ትዕዛዝ ተዘጋጅቶላቸው ከማረሚያ ቤት የተፈቱት ሰኔ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ቢሆንም፣ ከማረሚያ ቤት ሲወጡ ተይዘው በፀጥታ ኃይሎች ወደ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸውን ሰማያዊ ፓርቲ አስታውቋል፡፡ 

 

 

መድረክ የሟች አባላቱ ቁጥር አራት መድረሱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ግንቦት 16 ቀን 2007 ከተካሄደው አምስተኛውን ዙር ጠቅላላ ምርጫ በኋላ፣ ለሞት የተዳረጉ አባላቱ ቁጥር አራት መድረሱን አስታወቀ፡፡

በዚህም መሠረት ቀደም ሲል መሞታቸው ከተነገረው ሦስት የመድረክ አባላት በተጨማሪ፣ በደቡብ ክልል በሐድያ ዞን ሶሮ ወረዳ በዳና ቶራ ቀበሌ ነዋሪና የመድረክ አባል ድርጅት የሆነው የኢትዮጵያ ማኅበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ሕዝቦች አንድነት ፓርቲ (ኢማዴ-ደሕአፓ) መሠረታዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት አቶ ብርሃኑ ኤረቦ መገደላቸውን አስታውቋል፡፡ 

‹‹በ2007 ጠቅላላ ምርጫ በቅስቀሳ ላይ ተሰማርተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያበረክቱ የቆዩት አቶ ብርሃኑ ኤረቦ፣ ሰኔ 11 ቀን 2007 ዓ.ም. ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ በመኖሪያ መንደራቸው በተፈጸመባቸው ድብደባ ከተገደሉ በኋላ ወንዝ ውስጥ ተጥለው ተገኝተዋል፤›› ሲሉ የመድረክ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጥላሁን እንደሻው ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በሥፍራው ካሉ የፓርቲው አደረጃጀቶች መረጃ እንደሚሰባሰብ የገለጹት አቶ ጥላሁን፣ ‹‹መጀመርያ ቀን ላይ በአካባቢው ያሉ ፖሊሶችንና ሌሎች ካድሬዎችን ያካተተ አካል እየተንቀሳቀሱ፣ ሟችንና ሌሎች ለመድረክ የምርጫ እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አባላትና ወጣቶችን ‹የማዳበሪያ ሒሳብ እንዳይከፈል ሕዝቡም በመንግሥት ላይ እንዲያምጽ ቅስቀሳ እያደረጋችሁ ነው፤› በማለት ሟችንና ወጣቶችን ለማስፈራራትና ለማሰር ሲንቀሳቀሱ ነበር፤›› በማለት፣ አጋጠመ ያሉትን አስረድተዋል፡፡

‹‹በተለይ ‹ማዳበሪያን በሚመለከት ዕዳው እንዳይከፈል ያደረጋችሁት እናንተ ናችሁ› ተብለው ፖሊስ ሊይዛቸው ሲል ሸሽተው ነበር፤›› ያሉት አቶ ጥላሁን፣ ‹‹ሟች ሸሽቶ ከቆየበት ሥፍራ ምሽት ላይ ወደ ቤቱ በሚያመራበት ወቅት ነው ግድያው የተፈጸመበት፤›› በማለት የፓርቲውን አባል የአሟሟት ሁኔታ አስረድተዋል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በሥፍራው የመድረክ ተወካይና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ የነበሩት ግለሰብ ስለሁኔታው ለማጣራት ፖሊስ ጣቢያ ቢሄዱም፣ በፖሊስ ጣቢያው የዕለት ሁኔታ መመዝገቢያ ላይ የተመዘገበው ‹‹ሰክሮ ውኃ ውስጥ ወድቆ›› የሚል እንደሆነ መመልከታቸውን፣ አቶ ጥላሁን ከደረሳቸው ሪፖርት ለመረዳት መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡

‹‹የምናካሂደው ሰላማዊ ትግል ብዙ መስዋዕነት እንደሚያስከፍለን እናውቃለን፤›› ያሉት አቶ ጥላሁን፣ ‹‹ቢሆንም ግን ሰላማዊውን ትግል አጠናክረን እንቀጥላለን፤›› በማለት አስተያየታቸውን አጠቃለዋል፡፡

ሟች አቶ ብርሃኑ ኤረቦ የ40 ዓመት ጎልማሳና የአምስት ልጆች አባት እንደሆኑ መድረክ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ ላይ አስታውቋል፡፡

መድረክ ከምርጫው ዕለት ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሚዳ ቀኝ ወረዳ አቶ ጊዲሳ ጨመዳ፣ በምዕራብ  አርሲ ዞን ቆራ ወረዳ አቶ ገቢ ጥቤ፣ እንዲሁም በትግራይ ክልል ምዕራብ ትግራይ ዞን በማይካድራ ከተማ አቶ ታደሰ አብርሃ የተባሉ ዕጩዎቹ መገደላቸውን ቀደም ብሎ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

 

ማዕድን ሚኒስቴር በአገሪቱ የሕግ አግባብ መሠረት ባለመሥራቱ፣ መንግሥት በከፍተኛ ደረጃ የማዕድን ማምረት ሥራ ላይ ከተሰማራው ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ማግኘት የሚገባውን ከ429 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማሳጣቱን የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት አስታወቀ፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በማዕድን ሚኒስቴር ላይ በ2006 ዓ.ም. አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም ላይ ባደረገው የክዋኔ ኦዲት ነው መንግሥት ከፍተኛ ገንዘብ ማጣቱን ያረጋገጠው፡፡ 

የማዕድን ሥራ አዋጅን በተመለከተ የወጣው የ1986 ዓ.ም. አዋጅ ከከበሩ ማዕድናት ሽያጭ አምስት በመቶ የሮያሊቲ ክፍያ እንደሚወስን፣ ባልከበሩ ማዕድናት ላይ ምንም የሚለው ነገር እንደሌለ የኦዲተሩ የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ያስረዳል፡፡

ይህ አዋጅ ግን በአዋጅ ቁጥር 678/2002 መሻሻሉን በዚህ መሠረትም የከበሩ ማዕድናት ላይ ስምንት በመቶ የሮያሊቲ ክፍያ መጣሉን፣ ያልከበሩ ማዕድናት ላይ ስድስት በመቶ መጣሉን ሪፖርቱ ያትታል፡፡

ይሁን እንጂ ማዕድን ሚኒስቴር ከሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኩባንያ የከበሩና በከፊል የከበሩ ማዕድናት ላይ አምስት በመቶ ብቻ ሮያሊቲ ክፍያ በመሰብሰቡ፣ ከ2004 ዓ.ም.  እስከ 2006 በጀት ዓመት ከሚድሮክ የወርቅ ሽያጭ መንግሥት ሊያገኝ የሚችለውን 252.9 ሚሊዮን ብር ማጣቱን፣ እንዲሁም ካልከበሩ ማዕድናት በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ብቻ 413,394 ብር ማጣቱን፣ በድምሩ በሁለት ዓመታት ውስጥ 253.37 ሚሊዮን ብር ለመንግሥት ገቢ መደረግ የነበረበት የሮያሊቲ ገንዘብ አለመሰብሰቡን ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡

በተጨማሪም ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በ2000 ዓ.ም. ማምረት የጀመረ ቢሆንም፣ ማዕድን ሚኒስቴር ግን ይህንን ተቋም በየወቅቱ እየተከታተለ ሒሳባቸውን እንዳልመረመረ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ማረጋገጡን ይገልጻል፡፡ ይህም በመሆኑ በሮያሊቲ ሥሌቶች ላይ በሕግ ማሻሻያዎች የሚመጡ ለውጦችን በመከተል የመንግሥትን ገቢ ለማስገባት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እንዳልቻለ ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡ 

ከዚህ በተጨማሪም መንግሥት በሚድሮክ የወርቅ ማዕድን አክሲዮን ማኅበር ላይ ያለውን የነፃ ድርሻ በሕግ አግባብ ማስላት ባለመቻሉ፣ እስከ 2005 ዓ.ም. ድረስ 108.7 ሚሊዮን ብር እንዲሁም እስከ መጋቢት 2006 ዓ.ም. ድረስ 67.4 ሚሊዮን ብር በድምሩ 176.2 ሚሊዮን ብር አገሪቱ ማጣቷን ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡

ይህ በመሆኑም የተፈጠረውን ስህተት በማረም መንግሥት ያጣው ገንዘብ እንዲመለስ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ማዕድን ሚኒስቴሩን አሳስቧል፡፡

 

ከ17.7 ሚሊዮን ብር በላይ መመዝበሩ ተጠቅሷል

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደቡብ ሱዳን ሊሚትድ ጁባ ቅርንጫፍ ከ17.7 ሚሊዮን ብር በላይ በተጭበረበረ መንገድ ለግለሰቦች እንዲውል አድርገዋል ተብለው የሙስና ክስ የተመሠረተባቸው አምስት የባንኩ ሠራተኞች፣ ዋስትና

ተከልክለው ወደ ማረሚያ ቤት ወረዱ፡፡ አንዲት የቅርንጫፍ ባንኩ ከፍተኛ ኦዲተር በዋስ ተለቀቁ፡፡

የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ክስ የመሠረተባቸው የባንኩ ሠራተኞች፣ የሒሳብ ሹም አቶ ረሚላ ለወይ ኡስማን፣ የደንበኞች ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍፁም ብርሃን ዓለም ስምኦን፣ ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ሀብታሙ ዮሴፍ ማርዬ፣ ማኔጂንግ ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ሚካኤል ተክለ እግዚ ገብረ ማርያም፣ የንግድ አገልግሎት መኰንን አቶ ደስታው ፈንታሁን መንበር (ያልተያዙ)፣ ዋና ኦዲተር ወ/ሮ ሙሉሸዋ ክብረት፣ እንዲሁም አቶ መሐመድ ሁሴን ጣቢር (ያልተያዙ) እና አቶ ሁሴን ለወይ ኡስማን የተባሉ ግለሰቦች ናቸው፡፡ 

የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው ክስ እንደሚያስረዳው፣ ሲቴፕ ፎር ትሬድ ኤንድ ኢንቨስትመንት ካምፓኒ ሊሚትድ የተባለ ድርጅት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጁባ ቅርንጫፍ ደንበኛ ነው፡፡ በባንኩ በኩል 4,360,000 ዶላር ኤልሲ በደቡብ ሱዳን ማዕከላዊ ባንክ ይፈቀድለታል፡፡ ዶላሩ የሚለቀቅለት በሦስት ጊዜ ክፍያዎች ነው፡፡ ክፍያው የሚፈጸመው ገንዘቡ ኬንያ ወደሚገኘው ስታንቢክ ባንክ ከተላለፈ በኋላ ነው፡፡ የመጀመርያው 1,453,33 ዶላር ተልኮለታል፡፡ ለድርጅቱ የሚላከው ዶላር ከደቡብ ሱዳን ፓውንድ ጋር ተመጣጣኝ የሆነና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በደቡብ ሱዳን ማዕከላዊ ባንክ ካለው ሒሳብ ተቀንሶ መሆኑን ክሱ ያስረዳል፡፡

ነገር ግን አንደኛ ተከሳሽ አቶ ረሚላ ለድርጅቱ የተላከውን የገንዘብ መጠን መቀነስ ሲገባው ሳይቀንስ መቅረቱን ክሱ ያክላል፡፡ አንደኛ ተከሳሽ ሒሳብ ሲሠራ (Reconciliation) ሳይቀነስ የቀረው ገንዘብ ተንጠልጣይ ሆኖ ሲያየው ማዕከላዊ ባንኩ እንዲቀንስ ማድረግ ቢገባውም አለማድረጉ ክሱ ጠቅሷል፡፡ አንደኛ ተከሳሽ በሌሉበት ክሱ በተመሠረተባቸው አቶ መሐመድ ሁሴን ጣቢር ስም በ200 የደቡብ ሱዳን ፓውድ አካውንት እንዲከፍቱ ማድረጋቸውም ተጠቅሷል፡፡ በመቀጠልም በተለያዩ ጊዜያት በድምሩ 3,008,813 የደቡብ ሱዳን ፖውንድ የያዙ አራት ቼኮች ወደ  ኬንያ ንግድ ባንክ ለቼክ ማጣራት በማዕከላዊ ባንኩ በኩል ሲላኩ፣ የኬንያ ባንክ በግለሰቡ ገንዘብ እንደሌለው የገለጸ ቢሆንም አንደኛው ተከሳሽ ቼኮቹንና ተያያዥ ቅጾችን በማጥናት ግለሰቡ ገንዘብ ያለው ማስመሰሉ ክሱ ያብራራል፡፡ አንደኛ ተከሳሽ የዴቢት ትኬት በማዘጋጀትና ከሁለተኛ ተከሳሽ ጋር አቶ ፍፁም ብርሃን ጋር በጣምራ ፈርመው የተንጠለጠለው ገንዘብ መሐመድ ሁሴን በተባለ ተከሳሽ ስም ወደ ተከፈተው ሒሳብ እንዲገባ በማድረግ በባንኩ ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡ በአጠቃላይ ገንዘቡ በኢትዮጵያ ብር ሲሰላ 17,768,589 ብር መሆኑን፣ ተከሳሾቹ በሥልጣን ያላግባብ መጠቀም የሙስና ወንጀል ክስ እንደተመሠረተባቸው የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

ተጠርጣሪ ተከሳሾቹ ከላይ የተገለጸውን ገንዘብ በሕገወጥ መንገድ የተገኘ መሆኑን እያወቁ፣ በሐሰተኛ መንገድ በስድስተኛ ተከሳሽ አቶ መሐመድ ስም በተከፈተ ሒሳብ የተቀመጠውን ገንዘብ ከተለያዩ አካውንቶች የተላኩ በማስመሰልና ወደተለያዩ የባንክ ሒሳቦች አዘዋውረናል፡፡ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን፣ አንድ ባለሁለት መኝታ የኮንዶሚኒየም ቤት በመግዛት፣ በአጠቃላይ አንደኛ ተከሳሽና ስድስተኛ ተከሳሽ የአንደኛ ተከሳሽን ወንድም ሰባተኛ ተከሳሽ አቶ ሁሴን ለወይንን በመጠቀም፣ ገንዘቡን ማቀናነሳቸውንና በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስለው በማቅረብ የሙስና ወንጀል መከሰሳቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡

ሁለተኛ ተከሳሹ አቶ ፍፁም ብርሃን ዓለም የወንጀል ሕግ አንቀጽ 411 (2)ን በመተላለፍ የመንግሥትን ሥራ በማያመች አኳኋን በመምራት በሕጋዊ መንገድ ማግኘት ከሚገባቸው በላይ 6,620,600 ብር ይዘው መገኘታቸውንና ይኼም የሙስና ወንጀል መሆኑን ክሱ ይገልጻል፡፡ ሦስተኛ ተከሳሽ አቶ ሀብታሙ ዮሴፍም ማግኘት ከሚገባቸው በላይ 8,298,880 ብር ከሕጋዊ ገቢያቸው በላይ ይዘው በመገኘታቸውን፣ አራተኛም ተከሳሽ አቶ ሚካኤል ተክለ እግዚም 27,930,429 ብር ከሕጋዊ ገቢያቸው በላይ ይዘው በመገኘታቸው፣ አቶ ደስታው ፋንታሁንም 2,684,876 ብር ከሕጋዊ ገበያቸው በላይ ይዘው በመገኘታቸው፣ በፈጸሙት ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ ይዞ መገኘት የሙስና ወንጀል መከሰሳቸውን ክሱ ያብራራል፡፡

በቅርንጫፉ ዋና ኦዲተር የነበሩት ወ/ሮ ሙሉሸዋ ክብረት ሒሳቦችን በአግባቡ ባለመቆጣጠራቸውና የሥራ ኃላፊነትን ባለመወጣት የሚፈጸም የወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸዋል፡፡ ተጠርጣሪ ተከሳሾቹ ችሎት ቀርበው ክሱ ከተነበበላቸው በኋላ በጠበቆቻቸው አማካይነት ክሱ ዋስትና እንደማያስከለክል፣ ምክንያቱ ደግሞ አዲስ በወጣው የኮሚሽኑ አዋጅ መሠረት ዋስትና የሚከለክል አንቀጽ መሻሩን ጠቅሰው በዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡

ዓቃቤ ሕግ የተጠቀሰው አንቀጽ ዋስትና እንደሚከለክልና በአዲሱ አዋጅ ዋስትናን የሚመለከተው አንቀጽ እንዳልተሰረዘ በመግለጽ ጥያቄውን ተቃውሟል፡፡ ፍርድ ቤቱ የደቂቃዎች ረፍት ወስዶ በሁለቱ ወገኖች ክርክር ላይ ከተወያየ በኋላ፣ በድጋሚ በመሰየም ከኦዲተር በስተቀር ሌሎቹን ተከሳሾች ዋስትና ከልክሏቸዋል፡፡ ኦዲተሯም ዋስትና ተፈቅዶላቸዋል፡፡ የክስ መቃወሚያ ለመስማት ለሐምሌ 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

 

 

የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በደረሱት የአስተዳደራዊ በደል ጥቆማዎች ላይ ተመሥርቶ በሚያደርገው ምርመራ የመፍትሔ ሐሳቦችን ቢያቀርብም፣ አንዳንድ መሥሪያ ቤቶች እምቢተኝነት እያሳዩ መሆናቸውን አስታወቀ፡፡ ከእነዚህም መካከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትልቁን ድርሻ እንደሚይዝ ገለጸ፡፡

 

ዋና የሕዝብ እንባ ጠባቂዋ ወ/ሮ ፎዚያ አሚን የተቋማቸውን የአሥር ወራት የሥራ ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ባቀረቡበት ወቅት፣ በአስተዳደር ጥፋት ምክንያት የደረሰ በደል እንዲታረም የተመርማሪ መሥሪያ ቤቶች ኃላፊዎች ትብብርና ድጋፍ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የአስተዳደር በደል አቤቱታዎች ሲደርሱት አልያም በተደጋጋሚ ከሚደርሰው ጥቆማ በመነሳት የራሱን ምርመራ እንደሚያደርግ የገለጹት ወ/ሮ ፎዚያ፣ በምርመራው መሠረት የመፍትሔ ሐሳቦችን ለሚመለከታቸው ተቋማት እንደሚልክና የመፍትሔ ተቀባይነትም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡

ሆኖም የተወሰኑ አስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች በተቋሙ የምርመራ ውጤት ላይ ተንተርሶ በተላከላቸው የመፍትሔ ሐሳቦች መሠረት አለመፈጸም ወይም የማይፈጸሙበት በቂ ምክንያት ካላቸው ለተቋሙ ያለመግለጽና በምርመራ ሒደት አስፈላጊውን ትብብር ያለማሳየት እንቢተኝነት እንደሚታይ ገልጸዋል፡፡

ከእነዚህም ተቋማት መካከል በተደጋጋሚ ስሙ የተገለጸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነው፡፡ ከአስተዳደሩ አካላት መካከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽሕፈት ቤትና ክፍለ ከተሞች ይገኙበታል፡፡

በተጨማሪም የኦሮሚያ የአርሲ ዞን አስተዳዳር ጽሕፈት ቤት፣ የምሥራቅ ሸዋ ዞን አስተዳዳር ጽሕፈት ቤት፣ የሐዋሳ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤትና በሐረሪ ክልል የፍትሕና የፀጥታ ጉዳይ ቢሮ በእነዚህ ችግሮች የተጠቁ መሆናቸውን ዋና እንባ ጠባቂዋ ወ/ሮ ፎዚያ ገልጸዋል፡፡

የተገለጹት ተቋማት በቀረበላቸው የመፍትሔ ሐሳቦች መሠረት የእርምት ዕርምጃ ባለመውሰዳቸው ልዩ ሪፖርት ለፓርላማው የሕግ፣ ፍትሕና አስተዳዳር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዝርዝር መላካቸውን የጠቀሱት ወ/ሮ ፎዚያ፣  ቋሚ ኮሚቴው ባደረገው ክትትል በደሎቹ በከፊል የታረሙ መሆኑን ነገር ግን ሙሉ በሙሉ አለመቀረፋቸውን ገልጸዋል፡፡

ራሱ ተቋሙ ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ ለምን እነዚህን ተቋማት እንደማያስቀጣ የተጠየቁት ዋና እንባ ጠባቂዋ፣ በአስተዳደራዊ በደል አቤቱታ ላይ ምርመራን መሠረት ያደረገ የመፍትሔ ሐሳብ አቤቱታ ለቀረበበት ተቋም የሚቀርብ መሆኑን ገልጸው፣ ተቋሙ በቂ ምክንያት ካለው ይኼንኑ ገልጾ የመፍትሔ ሐሳቡን ላለመተግር እንደሚችል በአዋጁ መደንገጉን ተናግረዋል፡፡

‹‹በቂ ምክንያት ካለው›› የሚለው ሐረግ ለትርጉም ክፍት በመሆኑ ዕርምጃ ለመውሰድ እንዳላስቻላቸው የገለጹት ወ/ሮ ፎዚያ፣ ይኼን ችግር ለመቅረፍ አዋጁን ለማሻሻል በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

 

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) መንግሥት ድጎማ  እንዲያደርግለት ያዘጋጀውን ፕሮፖዛል፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ሊያቀርብ ነው፡፡

ታኅሳስ 26 ቀን 2006 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትሩና በኢሠማኮ አመራሮች መካከል በተደረገ የምክክር መድረክ ላይ፣ ኢሠማኮ ለመንግሥት ይደረግልኝ ብሎ ያቀረበውን ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃል አወንታዊ ምላሽ ሰጥተው እንደነበር ይታወሳል፡፡

 

በዚሁ ምላሽ መሠረት ኢሠማኮ የመንግሥትን ድጎማ እሻባቸዋለሁ ያላቸውን ጉዳዮች በዝርዝርና በፕሮፖዛል መልክ አዘጋጅቷል፡፡ ያስፈልገኛል ያለውንም የገንዘብ መጠን በመጥቀስ  ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር አቅርቦ ነበር፡፡

ይህንን ፕሮፖዛል ያቀረበው ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ ቢሆንም፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ምንም ዓይነት ምላሽ ሳይሰጠው ቆይቶ ነበር፡፡ ቆይቶም ግን ኢሠማኮ ለሚኒስቴሩ ያቀረበው ጥያቄ መቅረብ ያለበት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ነው የሚል ምላሽ ስለተሰጠው፣ ‹‹ድጎማ ይሰጠኝ›› የሚለውን ጥያቄውን በድጋሚ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ለማቅረብ እየተዘጋጀ መሆኑን፣ የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

‹‹መንግሥት ድጎማ እንዲያደርግልን የፈለግነው ለግንዛቤ ማስጨበጫና ለአቅም ግንባታ ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ የሚውል ነው፤›› ያሉት አቶ ካሳሁን፣ ይህንንም በፕሮፖዛላቸው ላይ ማስፈራቸውን ተናግረዋል፡፡

በተከታታይ በየዓመቱ የአሠሪና ሠራተኞችን ግንኙነት በሚመለከት የኢንዱስትሪ ሰላምን ለመፍጠር በሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት፣ ሁሉም ወገን መብትና ግዴታውን እንዲወጣ ለማድረግ ለሚያስፈልገው ወጪ መንግሥት ድጎማ እንዲያደርግ በኢሠማኮ ተጠይቋል፡፡ ሥልጠናዎቹና የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞቹ በአሠሪና በሠራተኛ ዘንድ አሉ የሚባሉትን ችግሮች ለመፍታት፣ ሠራተኛውና አሠሪውን የሚመለከቱ ሕጎች ምን እንደሚመስሉ ለማሳየትና በዚሁ መሠረት ተፈጻሚ እንዲሆን ለማስቻል ጭምር ነው፡፡ ድጎማው ለተፈለገው ዓላማ ብቻ የሚውል ነው ያሉት አቶ ካሳሁን፣ ከመንግሥት የሚገኘው የገንዘብ ድጎማ ለኢሠማኮ ውስጣዊ በጀት ወይም ለአስተዳደር ሥራ እንደማይውልና ደመወዝን ለመሰሉ ወጪዎች ማስፈጸሚያም እንደማይጠቀምበት ገልጸዋል፡፡

ኢሠማኮ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተመራው ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር አድርጎት በነበረው የምክክር መድረክ ላይ፣ ሊፈጸሙልኝ ይገባሉ ብሎ ካቀረባቸው ከ30 በላይ ጥያቄዎች ውስጥ አንዱ ‹‹መንግሥት ኢሠማኮን ይደጉም›› የሚል ሲሆን፣ መንግሥትም ኢሠማኮን ለመደገፍ ፈቃደኝነቱን አሳይቷል፡፡

በወቅቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ድጎማ የሚለው ቃል ጸያፍ ነው…በድጎማ ያደገ አገርና ድርጅት የለም፡፡ ሥራ ለመሥራት የገበያ ክፍተት ስላለ እንደ ልማታዊ መንግሥት ለዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አጋር ይሆናል ተብሎ እስከታመነ ድረስ በኢሠማኮ የተጠየቀውን እንሰጣለን፤›› ብለው፣ ‹‹ይህ ድጎማ ግን ለሽርሽር የምትጠቀሙበት አይደለም፤›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋቸው እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ሠራተኞችን ማስጨብጨቡ ይታወሳል፡፡

በወቅቱ ሊፈቱልን ይገባል ተብለው ከኢሠማኮ ከቀረቡት ጥያቄዎች ውስጥ አብዛኞዎቹ አዎንታዊ ምላሽ እንዳገኙ የተነገረ ሲሆን፣ ከቀረጥ ነፃ ተሽከርካሪዎችም እንዲገቡ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ አሠሪዎች ለሠራተኞቻቸው የሚያቀርቡት ምግብ ታክስ እንዳይደረግ የሚለውም ጥያቄያቸው አወንታዊ ምላሽ እንዳገኘም ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

 

በአሁኑ ወቅት 85 በመቶ የተጠናቀቀው ከአዲስ አበባ-ጂቡቲ ድረስ እየተገነባ ያለው የባቡር መስመር በሚቀጥለው ዓመት አገልግሎት ይስጣል ተባለ፡፡

በሎስጂቲክስ ችግሮች ላይ መሠረታዊ ለውጥ ከማምጣቱም በላይ፣ ከውጭ ለሚገባ ከፍተኛ መጠን ያለው ማዳበሪያ ትራንስፖርት ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

የኢትዮጵያ ግብርና ግብዓት አቅራቢ ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስኪያጅ ተወካይ አቶ በየነ ገብረ ሥላሴ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ባቡሩ ሥራ የሚጀምር ከሆነ ማዳበሪያው ታሽጎ ወይም በብትን ይግባ የሚለው ይታያል፡፡ ነገር ግን ባቡሩ ሥራ ከጀመረ በብትን ማስገባቱ አዋጭ ይሆናል ሲሉ አቶ በየነ አስረድተዋል፡፡

ለሚቀጥለው ምርት ዘመን የሚፈለገውን ማዳበሪያ መጠን ለማወቅ ግብርና ሚኒስቴር ቅኝት እያደረገ መሆኑም ተገልጿል፡፡ ግብርና ሚኒስቴር ዘርፉ የሚፈለገውን የማዳበሪያ መጠንና ዓይነት ከክልሎች እየሰበሰበ ሲሆን፣ በይደር የሚቆየውን ማዳበሪያ መጠን በመገምገም ላይ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

የአገሪቱ ግብርና ዘርፍ የሚፈለገውን የማዳበሪያ መጠን እንደታወቀ፣ የግብርና ግብዓት አቅራቢ ኢንተርፕራይዝ በጥቅምት 2008 ዓ.ም. ጨረታ አውጥቶ ግዥ እንደሚፈጽም ተጠቁሟል፡፡

ለ2007 ዓ.ም. ምርት ዘመን 894 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ዩርያና ኤንፒኤስ ማዳበሪያዎች ግዥ ተፈጽሞ፣ አብዛኛው አገር ውስጥ መግባቱ ይታወሳል፡፡ አገር ውስጥ የገባው ማዳበሪያ በኩንታል 1,200 ብር አካባቢ በመሸጥ ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡

ነገር ግን በ2007 ዓ.ም. ግዥ ከተፈጸመው ማዳበሪያ ውስጥ አንድ መርከብ ማዳበሪያ በአሁኑ ወቅት በጂቡቲ ወደብ በመራገፍ ላይ ይገኛል፡፡ አቶ በየነ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ግብርና ሚኒስቴር አገሪቱ የምትፈልገውን የማዳበሪያ መጠንና ዓይነት እንዳሳወቃቸው ግዥ ለመፈጸም ወደ ገበያ ይወጣሉ፡፡

የግብርና ሚኒስቴር ግብርና ግብዓት ዳይሬክተር አቶ ተሾመ ላቀው በበኩላቸው፣ ክልሎች የማዳበሪያ ፍላጎታቸውን በነሐሴ ወር እንደሚያሳውቁና በጥቅምት ወር ወደ ግዥ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

በዚህ የምርት ዘመን ግዥ የተፈጸመው 894 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ ሲሆን፣ አንዱ ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ ከ412 ዶላር እስከ 480 ዶላር ግዥ ተፈጽሟል፡፡ በምርት ዘመኑ ለማዳበሪያ ዘርፍ አስቸጋሪ ጉዳይ የነበረው የትራንስፖርት ጉዳይ ሲሆን፣ ይህም የሆነው ማዳበሪያን በዝቅተኛ ዋጋ ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ ሲባል በትራንስፖርት ሒሳብ ላይ ተመን በመውጣቱ ነበር፡፡

ይህም የትራንስፖርት ድርጅቶችን ትኩረት መሳብ ባለመቻሉና በወቅቱ በርካታ ዕቃዎች ጂቡቲ ወደብ ደርሰው የነበረ በመሆኑ፣ ማዳበሪያ ወደ አገር ውስጥ ለማጓጓዝ ችግር ተፈጥሮ ነበር፡፡

አቶ በየነ እንዳሉት፣ በሚቀጥለው ዓመት ይህንን ችግር ለመፍታት ከወዲሁ ከባህር ትራንስፖርትና ከሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ጋር ንግግር ይጀመራል፡፡ ከአዲስ አበባ ጂቡቲ ድረስ በሚገነባው የባቡር መስመር ችግሩ ሊቀረፍ እንደሚችል አቶ በየነ ያላቸውን እምነት ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የዓለም አቀፍ የማዳበሪያ ዋጋም በዚህ የምርት ዘመን ከተገዛበት ዋጋ ቅናሽ ይኖረዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሚናገሩት አቶ በየነ፣ በሚቀጥለው ምርት ዘመን ለአርሶ አደሩ የሚቀርበው ማዳበሪያ የዋጋ ቅናሽ ሊኖረው ይችላል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ የሚፈልገው ማዳበሪያ መጠን እያደገ ከመሆኑ በተጨማሪ፣ አፈሩ የሚፈልገው ማዳበሪያ ዓይነትም ተለይቶ እንደታወቀ ተገልጿል፡፡ በግብርና ዘርፍ ውስጥ ብዙም  የማይታወቀው ኤንፒኤስ ማዳበሪያ፣ የአገሪቱን ግብርና የተቀላቀለ በመሆኑ በአገሪቱ አምስት ማዳበሪያ ፋብሪካዎችም አፈሩ የሚፈልገውን ማዳበሪያ በማቅረብ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

 

ኢሕአዴግና አጋር ድርጅቶቹ ምርጫውን ሙሉ በሙሉ ማሸነፋቸውን ምርጫ ቦርድ አረጋገጠ

‹‹መድረክና ሰማያዊ ፓርቲዎች ሁለተኛና ሦስተኛ ሆነዋል›› ፕሮፌሰር መርጋ በቃና

-የጊምቦ ገዋታ የምርጫ ውጤት አልተካተተም

በመላው ኢትዮጵያ (ከጊምቦ ገዋታ ምርጫ ጣቢያ በስተቀር) ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. የተካሄደውን የሕዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤቶች አገራዊ ምርጫ ኢሕአዴግና አጋር ድርጅቶቹ ሙሉ በሙሉ ማሸነፋቸውን፣

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. በሒልተን ሆቴል ይፋ አደረገ፡፡

የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እንደገለጹት፣ ቦርዱ በአዋጅ ቁጥር 532/99 አንቀጽ 77 መሠረት አጠቃላይ የምርጫውን ውጤት ይፋ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም ለአምስተኛው አገራዊ ምርጫ 36,851,461 ሕዝብ በመራጭነት ተመዝግቦ፣ 34,351,444 ሕዝብ ድምፁን ሰጥቷል፡፡ በመሆኑም ኢሕአዴግና አጋር ድርጅቶቹ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 334 ወንዶችና 212 ሴቶች በዕጩነት አቅርበው አሸናፊ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ምክር ቤቱ ካለው 547 መቀመጫዎች 546ቱን ሲያሸንፉ፣ ላለፉት አምስት ዓመታት ብቸኛው የግል የፓርላማ አባል የነበሩት ዶ/ር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስና የኢሕአዴግ ዕጩ ዶ/ር መብራቱ ገብረ ማርያም (የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት) የሚወዳደሩበት የቦንጋ ጊምቦ ገዋታ ምርጫ ክልል ውጤት  ይፋ ባለመደረጉ፣ ከተገለጸው ውጤት ጋር አለመካተቱን ሰብሳቢው ተናግረዋል፡፡

ለክልል ምክር ቤቶች ኢሕአዴግና አጋሮቹ፣ 1187 ወንዶችና 800 ሴቶች በድምሩ 1,987 አባላት በዕጩነት አቅርበው ሙሉ በሙሉ ማሸነፋቸውን ፕሮፌሰሩ አክለዋል፡፡

ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 52 የፖለቲካና ዘጠኝ የግል ዕጩዎች ለ547 መቀመጫዎች የተወዳደሩ ቢሆንም፣ ኢሕአዴግ በአምስት ክልሎች ማለትም በአማራ፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በሐረሪ፣ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች 27,347,332 ድምፅ በማግኘት 500 መቀመጫዎችን ያለምንም ተቀናቃኝ ማሸነፉን ፕሮፌሰሩ አብራርተዋል፡፡

ለሁለቱ ምክር ቤቶች 40,536,607 የድምፅ መስጫ ወረቀቶች መቅረቡን የገለጹት ፕሮፌሰሩ፣ 1,130,390 ድምፅ መስጫ ወረቀቶች ዋጋ አልባ መሆናቸውንና 520,379 ድምፅ መስጫዎች መበላሸታቸውን ተናግረዋል፡፡

በምርጫ ውድድሩ መድረክና ሰማያዊ ፓርቲዎች ሁለተኛና ሦስተኛ መውጣታቸውን የገለጹት ፕሮፌሰር መርጋ፣ የምክር ቤቶቹን መቀመጫዎች የሚያስገኝ ድምፅ ባለማግኘታቸው ተሸናፊ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡ ቦርዱ የሕዝብ ድምፅ ማስከበር እንዳለበት የተናገሩት ሰብሳቢው፣ ይኽንኑ ተግባራዊ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡ በደቡብ ክልል የጊምቦ ገዋታ ምርጫ ክልል የምርጫ ውጤት ለቦርዱ መድረሱን ጠቁመው፣ ቦርዱ ውጤቱን ባለማፅደቁ በዕለቱ በገለጹት ውጤት ላይ አለመካተቱን፣ ነገር ግን  በቅርቡ ፀድቆ በቦርዱ ድረ ገጽ ይፋ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡

ሰኔ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. በደቡብ ክልል በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ በጊምቦ ገዋታ ምርጫ ክልል በተካሄደው ምርጫ፣ የኢሕአዴግ ዕጩ ዶ/ር መብራቱ ገብረ ማርያም የግል ዕጩውን ዶ/ር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስን በሰፊ ውጤት ማሸነፋቸውን ከምርጫ ጣቢያዎቹ ከተገኘው መረጃ መረጋገጡን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

 

የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ አዲስ አበባ እስከ አዳማ የተገነባው የፍጥነት መንገድ አካል የሆኑ ሁለት መንገዶች በከፊል ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ሊሆኑ ነው፡፡

ከአቃቂ ለቡና ከአቃቂ የረር በመገንባት ላይ ያሉት መንገዶች አንደኛው መስመራቸው ለትራፊክ ክፍት እንዲሆን፣ ግንባታቸው በፍጥነት እንዲካሄድ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡

ሁለቱ መንገዶች ግንባታቸው በየካቲት 2008 ዓ.ም. ይጠናቀቃል ተብሎ ቢታቀድም፣ በአካባቢው እየተፈጠረ ያለው የትራፊክ መጨናነቅ በጣም እየጨመረ በመምጣቱ ትራንስፖርት ሚኒስቴር በሰጠው መመርያ፣ አንደኛው ረድፍ በአፋጣኝ ተገንብቶ ለትራፊክ ክፍት እንዲሆን ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡

በዚህ መሠረት የቻይናው ግዙፍ የኮንስትራክሽን ኩባንያ ሲሲሲሲ ግንባታው በማገባዳደድ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በቅርቡ ለትራፊክ ክፍት እንደሚደረግ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጠን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሳምሶን ወንድሙ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የፍጥነት መንገዱ መጨረሻ ከሆነው አቃቂ ተነስቶ ለቡ ድረስ ያለው 13.6 ኪሎ ሜትር እና ከአቃቂ ተነስቶ አይሲቲ ፓርክ (የረር ጎሮ) ድረስ የሚገነቡት መንገዶች ናቸው ለትራፊክ ክፍት የሚሆኑት፡፡

እነዚህ መንገዶች በአጠቃላይ ስድስት መኪኖችን በአንድ ጊዜ የሚያስተላልፉ ሲሆን፣ በቅርቡ ለትራፊክ ክፍት የሚሆነው አንደኛው ረድፍ ሦስት መኪኖችን በአንድ ጊዜ ያስተላልፋል ተብሏል፡፡ በአጠቃላይ ሁለቱ የመንገድ ፕሮጀክቶች 4.6 ቢሊዮን ብር ወጪ የሚደረግባቸው ሲሆኑ፣ ከአጠቃላይ ወጪ 75 በመቶ የቻይና ኤግዚም ባንክ ቀሪውን 25 በመቶ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ይሸፍናሉ፡፡

የመንገዶቹ ግንባታ ባለፈው 2006 ዓ.ም. መጨረሻ ነው የተጀመረው፡፡ በሁለት ዓመት ከስምንት ወር ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡ ነገር ግን አንዱ ረድፍ የግድ ማለቅ አለበት በመባሉ ግንባታው እየተፋጠነ በመሆኑ በቅርቡ ለትራፊክ ክፍት ይሆናል፡፡

እነዚህ ሁለት መንገዶች ከአዲስ አበባ-አዳማ ድረስ የተገነባው ግዙፍ የፍጥነት መንገድ አካል ናቸው፡፡ የአዲስ – አዳማ የፍጥነት መንገድ 84.6 ኪሎ ሜትር ርዝመት ሲኖረው  12.2 ቢሊዮን ብር ወጥቶበታል፡፡ ሁለቱ መንገዶች እንደተጠናቀቁ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ከቃሊቲ እስከ አቃቂ ድረስ ያለውን መንገድ ደረጃ የሚያሻሽል መሆኑ ታውቋል፡፡

ይኼ መንገድ ብቸኛው የአገሪቱ ወጪና ገቢ ንግድ የሚከናወንበት በመሆኑ ተለዋጭ መንገድ ሳይገነባ የመንገዱን ደረጃው ማሻሻል አይቻልም ተብሎ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የፍጥነት መንገዱ በሁለት አቅጣጫዎች ወደ አዲስ አበባ ከተማ በመዘርጋቱ፣ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ወደ ግንባታ ይገባል በማለት ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፍቃዱ ኃይሌ አገር ውስጥ ባለመኖራቸው አስተያየታቸውን ማካተት ሳይቻል ቀርቷል፡፡

 

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ገጣሚና ጸሐፊ ተውኔት የማንቸስተር ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆነ

በእንግሊዝ ማንችስተር ዩኒቨርሲቲ ለቻንስለርነት ከተወዳደሩ ሦስት ግለሰቦች መካከል ትውልደ ኢትዮጵያዊው ገጣሚና ጸሐፈ ተውኔት ለምን ሲሳይ አብላጫውን ድምፅ በማግኘት አሸነፈ፡፡

ለምን በወድድሩ የተሳተፉትን የሙዚቃ ባለሙያውን ሰር ማርክ ኤልደርና የቀድሞውን የእንግሊዝ ፖለቲከኛ ሎርድ ፒተር ማንዴልሰንን ሰፊ በሆነ የድምፅ ብልጫ አሸንፏል፡፡

ለምን ውድድሩን ያሸነፈው 7,131 የማንቸስተር ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞችና የቀድሞ ተማሪዎችን ድምፅ በማግኘት ሲሆን፣ ሰር ማርክ ኤልደር 5,483 ድምፅ በማስመዝገብ ሁለተኛ ሆነዋል፡፡ እንዲሁም ፖለቲከኛው ሎርድ ፒተር 5,269 ድምፅ በማግኘት ሦስተኛ ሆነዋል፡፡

ለምን ከምርጫው በኋላ የዩኒቨርሲቲው ቻንስለር ለመሆን ያበቃውን ድምፅ የሰጡትን መራጮች አመስግኗል፡፡ ከነሐሴ አንድ ጀምሮ በሥልጣን ላይ ያሉትን ቶም ብሎክሳምን ተክቶ ለሰባት ዓመታት እንደሚሠራ ታውቋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ዴም ናንሲም ዩኒቨርሲቲውን በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡ 

ገጣሚና ጸሐፊ ተውኔት ለምን ሲሳይ እ.ኤ.አ. በ1967 በዊጋን ከተማ ከኢትዮጵያዊ ቤተሰቦች የተወደለ ሲሆን፣ ከወላጆቹ ዘንድ ለማደግ አልታደለም ነበር፡፡ እስከ 12 ዓመቱም እንግሊዛዊ አሳዳጊዎቹ ዘንድ ቆይቷል፡፡ በኋላም በአካባቢው በሚገኝ ሕፃናት ማሳደጊያ ዕድሜው 17 እስኪሆን ቆይቷል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1988 በ21 ዓመቱ የግጥም መድበል አሳትሟል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1995 ‹ኢንተርናል ፍላይት› የሚባል በቢቢሲ ዘጋቢ ፊልም አዘጋጅቶ ለዕይታ አብቅቷል፡፡ ሌሎች በርካታ ስኬቶችም ተቀዳጅቷል፡፡

 

ኢሳት ዜና (ሰኔ 17, 2007) የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኞ ከእስር እንዲፈቱ የወሰነላቸው አራት የፓርቲ አባላት ከእስር ቤት ከወጡ በኋላ የመንግስት ጸጥታ ሀይሎች በድጋሚ በቁጥጥር ስር ውለዋል። አራቱ ተከሳሾች ፍርድ ቤት ከተከሳሾች ፍርድ ቤት ካስተላለፋቸው ከሁለት ወር በላይ በእስር ቤት በመቆየታቸው ምክኒያት ሰኞ ከእስር እንዲፈቱ ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል። አራቱ ተከሳሾች ማክሰኞ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እንዲወጡ …