የደህንነት መስሪያ ቤቱን አፈና እና ግድያን ለማጠናከር ሁለተኛ ዙር የበጀት ጭማሪ ማሻሻያ ተደረገ::
#Ethiopia የሃገሪቱን ሃብት ለስልጣን ማስረዘሚያ ያዋለው የወያኔው ጉጀሌ አገዛዝ ለደህንነት ቢሮው በስድስት ወር ውስጥ ብቻ ለሁለተኛ ጊዜ የበጀት ጭማሪ ማሻሻያ ማድረጉ የወስጥ አዋቂ ምንጮች ገለጹ:: Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ፓርላማው ሳይቀፈድ አሊያም ለውይይት ሳይቀርብ በዘፈቀደ በግለሰቦች ትእዛዝ ብቻ ከገንዘብ ሚኒስቴር ወጥቶ ደህንነት ቢሮ የሚገባው በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ልክ እንደ መከላከያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የዋናው ኦዲተር ቢሮ ሂሳብ ምርመራ የማያውቀው መሆኑን ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ጠቁመዋል::የተመደበው በጀት በብዛት የሚውለው ዜጎችን ለማፈን እና በደህንነት ቢሮ ለሚሰማሩ ገዳዮች አፋኞች እና ዘራፊዎች በከፍትኛ ክፍያ አበል እንደሚሰጣችው ተጠቁሟል::ብተለያየ ምክንያት ከድርጅቱ የተሰናበቱ የቀድሞ የኢሕአዴግ የደህንነት አባላት ወደ ስራቸው ተመልሰው እንዲያገለግሉ ለማድረግ ታሶ የተመደበ በጀት እንደሆነ የገለጹት ምንጮች ወያኔ ም ያህል አጣብቂኝ ውስጥ እንዳለ ያሳብቅበታል ሲሉ ተናግረዋል::
ስልጣን ለማስረዘም አደገኛ የሆኑ ተግባራትን በዜጎች ላይ የሚፈጽምው ሕወሓት በአሁኑ ወቅት በደህንነት አካላቱ ውስጥ 98% የአንድ ብሄር ተወላጆችን የሞላቸው ቢሆንም እርስ በርስ መተማመ ባላመኖሩ አብዛኛው የደህንነት አባል በገንዘብ እየተደለለ በጥቅም ተገዝቶ የሚሰራ መሆኑ ታውቋል:: ለእናት ሃገር ሉአላዊነት እና ለሕዝብ ደህንነት ጥበቃ የሚሉ አላማዎች ተሰሚነትም ሆነ ተፈጻሚነት እንዳሌላቸው የሚናገሩት ምንጮች የሕወሓት ደህንነት ቢሮ ከአደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪዎች እና ከሲሲሊ ማፊያዎች ተለይተው እንደማይታዩ እና ተግባራቸው ሁሉ በአደገኛ የሽብር ስራ ላይ እንደሆነ ተናግረዋል::የሃገሪቷን ሃብት በከፍተአ ደረጃ በጥቅም ሰዎችን እየገዙ ለክፉ ተግባራቸው የሚያውሉት የሕወሓት ባለስልጣናት አሁንም በደህንነቱ ውስጥ ጥርጣሬ እና መተማመን የሌለ ስለሆነ ይህ ጉዳይ በሰራዊቱ እና በደህነቱ ውስጥ ችግሮችን በቅርቡ ሊያፈነዳ ይችላል ተብሎ ይገመታል::#MinilikSalsawi