በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሜቴ አባላት ላይ ፖለቲካዊ ውሳኔ ተሰጠ::
በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሜቴ አባላት ላይ ፖለቲካዊ ውሳኔ ተሰጠ::
ምንሊክ ሳልሳዊ :- ለዛሬ የተቀጠረው የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የወያኔው መንግስት የመሰረተው የሃሰት ክስ ፖለቲካዊ ውስኔ ማግኘቱን ከሰሚት ፍርድ ቤት አከባቢ የተገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል::በዚህም መሰረት ከበላይ የመጣላቸውን ት እዛዝ የሚያነቡት ዳኞች የመጨረሻውን የፖለቲካ ውሳኔ በንባብ አስተላልፈዋል::
ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ ተፈጸመ::የካንጋሮው ፍርድ ቤት ከሰባት አመት እስከ 22 አመት ድረስ በህዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴዎችና አብረዋችው በታሰሩት ላይ ፈረደ፡፡ ዛሬ ፍርድ ቤቱ ባነበበው የቅጣት ውሳኔ ዝቅተኛው ፍርድ ሰባት አመት ከፍተኛው 22 አመት እንደሆነ መረጃው ያመለክታል፡፡
የካንጋሮ ፍርድ ቤቱ ከወያኔ ቢሮ ተወስኖ/ተጽፎ የመጣለት ውሳኔ ከዚህ የሚከተለው ነበር
– ኡስታዝ አቡበክር አህመድ፣ አህመዲን ጀበል፣ ያሲን ኑሩ እና ከሚል ሸምሱ – 22 አመት
– 5ኛ፣ 7ኛ፣ 8ኛ፣ 11ኛ እና 15ኛ ተከሳሾችን፥ በድሩ ሁሴን፣ ሳቢር ይርጉ፣ መሃመድ አባተ፣አቡበክር አለሙ እና ሙኒር ሁሴንን እያንዳንዳቸውን በ18 አመት ጽኑ እስራት
– ሼህ መከተ ሙሄ፣ አህመድ ሙስጠፋ፣ ሼህ ሰኢድ አሊ፣ ሙባረክ አደም እና ካሊድ ኢብራሂም የ15 አመት ጽኑ እስራት
– ሙራድ ሽኩር፣ ኑሩ ቱርኪ፣ ሼህ ባህሩ ዑመር እና የሱፍ ጌታቸውን በ7 አመት ጽኑ እስራት
የካንጋሮ ፍርድ ቤቱ ከእስራት ቅጣት በተጨማሪ ተከሳሾች ይህ ውሳኔ ከፀናበት እለት ጀምሮ ለአምስት አመታት እንዳይመርጡ ፣ እናዳይመረጡ ፣ በየትኛውም ቦታ ዋስም ምስክርም እንዳይሆኑ በአጠቃላይ ከማህበራዊ መብታቸው አግዷል ።
ችሎቱን ለመከታታል የሄደው ሕዝብ በፖሊስ ሲባረር

