የአፍሪቃ ኅብረት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት የተካሄደባትን ግብጽን ከአባልነት አገደ። ግብፅ ውስጥ፤ «የቁጣ ፣ የተቃውሞ ቀን ነው»ሲሉ የሙስሊም ወንድማማች ፓርቲ አባላት ባቀረቡት ጥሪ፣ ተከታዮቻቸው አደባባይ በመውጣት እንደተነገራቸው ፈጽመዋል።

ግብፅ ውስጥ፤ በሀገሪቱ በመላ ዛሬ ፣ «የቁጣ ፣ የተቃውሞ ቀን ነው»ሲሉ የሙስሊም ወንድማማች ማኅበር አባላት ባቀረቡት ጥሪ መሠረት ፣ ተከታዮቻቸው አደባባይ በመውጣት እንደተነገራቸው ፈጽመዋል። በቅርቡ የተከሠተውን ለውጥ የሚደግፉት ወገኖች በፊናቸው

በቤንቺ ማጂ ዞን የሚዛን ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ና መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ የመብት ጥያቄ በማንሣታቸው ለእሥር መዳረጋቸውን የታሣሪዎቹ ተማሪዎች ቤተሰቦች ገለጡ።

በቀደም በቀለበት መንገድ ላይ በመኪና ስሄድ ከጎናችን አንድ ነጭ ፒክ አፕ መኪና ይጓዝ ነበር፡፡ ዘወር ብዬ ሳየው በሩ ላይ የመሥሪያ ቤቱን ስም ለጥፏል፡፡ ያየሁትን ለማመን ስላቃተኝ በሞባይል ፎቶ አነሣሁት፡፡ የድርጅቱ ስም ግምማአድ (AISA) ይላል፡፡ ምን ሆነው ነው እንዲህ ያለ ክፉ ትርጉም የሚያጋልጥ ስም የሚያወጡት፡፡ ለመሆኑ ድርጅቱ በአማርኛ ሲጠራ ምንድን ነው የሚባለው? ‹ግም ማአድ› ማለትኮ በአማርኛ መልካም ትርጉም የለውም፡፡ አሁን እዚያ የሚሠራ ሰው የት ትሠራለህ ሲባል ‹ግምማአድ እሠራለሁ› ይላል ማለት ነው?

አንዳንድ ድርጅቶች የባለቤቶቹን ወይም የረጅዎችን ፍላጎት ማሳካታቸውን እንጂ በባለቤቶቹ ላይ የሚያመጡት ተጽዕኖ ግምት ውስጥ አይገባም፡፡ ያ ስም ከአካባቢው ባህልና እምነት አንጻር በተጠቃሚውም ሆነ በሠራተኛው ላይ ተጽዕኖ ማድረሱ አይገመገምም፡፡ በአንድ ወቅት ጃፓኖች ያመረቱትን መኪና የሰየሙበት ስም በፈረንሳይኛ ‹ሞት › የሚል ትርጉም በመስጠቱ ምክንያት የነበረውን ክርክር አስታውሰዋለሁ፡፡
ባለፈው ጊዜ በደቡብ ጎንደር በንፋስ መውጫ ከተማ በኩል ስናልፍ ‹ዝሙት በኛ ይብቃ› የሚባል የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ አየን፡፡ ስሙ ገረመንና ለመጠየቅ ጠጋ አልን፡፡ ሱቁ የተከፈተው ከዚህ በፊት በዝሙት አዳሪነት ይተዳደሩ የነበሩ ሴቶችን ከዚህ ዓይነት ተግባር በማውጣት መሆኑ ተነገረን፡፤ ይሁን ሃሳቡ መልካም ነው፡፤ ነገር ግን አንድ ሰው ምንስ ቢሆን ‹እኔ ዝሙት አዳሪ ነበርኩ› ብሎ በአደባባይ እንዲናገር እንዴት ይደረጋል? የእነዚያ ሴቶች ልጆችስ ‹ዝሙት በኛ ይብቃ ሱቅ የኛ ነው› ብለው በኩራት ይናገራሉ? ሰዎችስ ‹ዝሙት በኛ ይብቃ ሱቅ አጠገብ እንገናኝ› ተባብለው ይቀጣጠራሉ? እዚህ አልጽፈውም እንጂ የአካባቢው ሰዎች ሱቁን የሚጠሩት በሌላ ስም ነው፡፡
እስኪ ለዛሬ ‹ግምመአድ› የሚባለው ተቋም ወዳስታወሰኝ በሀገራችን ለንግድ፣ ለመንግሥታዊና መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት ስለሚወጡት ስሞች በተለይም ስለ የአሕጽሮት ስሞች እናውጋ፡፡ በታላላቅ ከተሞቻችን ውስጥ ድርጅትንና ሕንፃን በእንግሊዝኛ አሕጽሮት መሰየም እየተለመደ ነው፡፡ አንዳንዶቹ ስያሜዎች እንኳን እኛ ተመልካቾቹ ቀርተን ባለቤቱም ቢሆን ለመጥራት የሚቸገርባቸው ዓይነት ናቸው፡፡ ESLPTYGQ ሕንፃ የሚለውን እስኪ ምን ብላችሁ ትጠሩታላችሁ? አንድ ቦታ ደግሞ በአማርኛ ‹ትግድብም› የሚባል ሕንፃ አይቻለሁ፡፡ አሁን ይህንን እንዴት አድርጎ ማስታወስ ይቻላል? በተለይም በሀገራችን አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የወከሏቸውን ብሔር ብሔረሰቦች ሁሉ ለማካተት ሲጥሩ፣ ከዚያ በኋላ ደግሞ ‹ዴግ› የሚል ሲጨምሩበት ስማቸውን ጠርቶ ከመጨረስ የፖለቲካ ፕሮግራማቸውን አንብቦ መጨረስ ቀላል ይሆናል፡፡
እንደ ፈረንሳይ ባሉ ባደጉት ሀገሮች ለድርጅቶች ስምን የሚያወጡ የታወቁ ኩባንያዎች አሉ፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች የድርጅት ባለቤቶችን ሀሳብ፣ የስሙን ትርጉም፣ ለመጥራት ቀላል መሆኑንና ከሥነ ምግባር ጋር አለመጋጨቱን በማየት ስም ያወጣሉ፡፡ እኛ ሀገር ግን ብዙ ጊዜ የድርጅቱን ባለቤቶች ወይም የቤተሰቦቻቸውን አለበለዚያም ደግሞ የትውልድ ቦታቸውን ስም የመጀመሪያ ፊደሎች ብቻ በያዙ አሕጽሮቶች የሚጠሩ ድርጅቶችና ሕንጻዎች ናቸው ያሉት፡፡ እነዚህን ስሞች ራሳቸው ባለቤቶቹ ይመስሉኛል የሚሰጧቸው፡፡ እነርሱ የፈለጉትን ማድረጋቸውን እንጂ እኛ ደንበኞቻቸው ይመቸን አይመቸን፣ ይስማማን አይስማማን ግድ የላቸውም፡፡ 
የአሕጽሮት ስሞች እንዲሁ በፈቀደ የመጀመሪያ ስሞችን በመገጣጠም ብቻ የሚወጡ አይደሉም፡፡ የራሳቸው የሆነ መንገድና ሥነ ምግባርም አላቸው፡፡ ባለሞያዎቹ የአሕጽሮት ስሞችን ለሚያወጡ ሰዎች ቢያንስ እነዚህን አራት ነገሮች ግምት ውስጥ እንዲያስገቡ ይመክራሉ፡፡
  • አጭር መሆን፡- የአሕጽሮት ስም ሲወጣ በተቻለ መጠን ለመጻፍም ሆነ ለመጥራት አጭር የሆነ ቢሆን ይመረጣል፡፡ በእንግሊዝኛ ከሆነ ከሦስት እስከ ስድስት ፊደል፣ በአማርኛ ከሆነ ደግሞ ከሦስት እስከ ሰባት ፊደል ቢሆን ይመረጣል፡፡ UNESCO ከእንግሊዝኛው ጅንአድ ከአማርኛው መልካም ምሳሌዎች ናቸው፡፡
  • ለመጥራት ቀላል የሆነ፡- የምንኖረው ኢትዮጵያ ውስጥ በመሆኑ የምናወጣቸው የአሕጽሮት ስሞች ለአንድ ኢትዮጵያዊ ለመጥራት ቀላል የሚሆኑ መሆን አለባቸው፡፡ ከላይ እንዳየነው ESLPTYGQ እንደሚለው ዓይነቱን ስም አንድ ኢትዮጵያዊ እንዴት አድርጎ በቀላሉ ይጠራዋል? ይህንን መሰሎቹን አሕጽሮቶች ባለሞያዎቹ ‹የፊደላት ሾርባ› Alphabet soup ብለው ይጠሯቸዋል፡፡
  • ሌላ ትርጉም የማይሰጡ፡- የምናወጣው አሕጽሮት የባለቤቶቹን ስም መያዙ ብቻ መታየት የለበትም፤ በእንግሊዝኛም ሆነ በአማርኛ ወይም በሌላም ቋንቋ ቢሆን ሌላ ዓይነት ትርጉም የማይሰጥ መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ ‹ግምመአድ› ለአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ የመልካም ነገር መገለጫ አይደለም፡፡
  • ልዩ የሆነ(ያልተደገመ) የምንሰጠው አሕጽሮት የራሳችን የሆነና ከዚህ በፊት ያልተደገመ ቢሆን መልካም ነው፡፡ በአንዳንድ ሀገሮች አሕጽሮቶችን የሚመዘግቡ መዛግብት አሉ፡፡ የታወቁ አሕጽሮቶችን የሚይዙ ድረ ገጾችም አሉ፡፡ በመንግሥታዊም  ሆነ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች፣ ብሎም በታወቁ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች የታወቁትን አሕጽሮቶች መጠቀም ክርክርና መምታታትን ያስከትላል፡፡
የአሕጽሮት ስሞችን ለድርጅቶቻቸው ማውጣት ለሚፈልጉ አካላት በዓለም ላይ የተሻሉ መንገዶች ተብለው የሚመከሩትን ዘዴዎች ቢከተሉ ያዋጣቸዋል፡፡ ከእነዚህ የአሕጽሮት ማውጫ ዘዴዎች መካከል የሚከተሉት መንገዶች ልንጠቀምባቸው የምንችላቸው ናቸው፡፡
1.   ትርጉም የሚሰጥ ቃል መፍጠር፡- ቃላቱን በማሳጠር አሕጽሮት ስናወጣ በተቻለ መጠን ትርጉም እንዲሰጡ አድርጎ ማውጣት ማለት ነው፡፡ ለዚህ በሀገራችን ምሳሌ የሚሆነን ለረዥም ዘመን የምናውቀው ኩባንያ ‹በርታ› ነው፡፡ በርታ በአንድ በኩል በእንግሊዝኛው ‹ብርሃኔና ታደሰ› የሚባሉት ባለቤቶቹ ስም አሕጽሮት ሲሆን በአማርኛ ደግሞ ‹ጎብዝ፣ ጀግን› ማለት ነው፡፡ አንድ ቦታም ‹ድንበሩና በርይሁን› የተባሉ ጓኛሞች የመሠረቱትን ‹ድንበር› የተባለ ኩባንያ አይቻለሁ፡፡ በእንግሊዝኛም Radar – Radio Detention and Ringing, Interpol- International Police,  በምሳሌነት ይጠቀሳሉ፡፡ ይህንን ዓይነት ስያሜ ለመስጠት የግድ የስሞቹ የመጀመሪያ ፊደሎች ብቻ ሳይሆን ከስሞቹ የተወሰኑትን መውሰድ፣ ወይም አያያዦችንም ማካተት ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ MATYAS ሕንፃ በአንድ በኩል የባለቤቶቹ ስሞች አሕጽሮት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ትርጉም ያለውን የሐዋርያ ስም ይሰጣል፡፡
2. የመጀመሪያ ፊደል አሕጽሮት፡- የስሞቹን የመጀመሪያ ፊደል ብቻ በመውሰድ ቢቻል ትርጉም ያለው፣ ባይቻል ለአጠራር ምቹ የሆነ ስም መፍጠር ነው፡፡ ለዚህ በሀገራችን መልካም የሚሆነው ምሳሌ አዕማድ (አነስተኛ ዕደ ጥበባት ማስፋፊያ ድርጅት) ነው፡፡ አዕማድ የሚለው ስም በአንድ በኩል የድርጅቱ ስም አሕጽሮት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በግእዝና በአማርኛ ‹ምሰሦዎች› ማለት ነው፡፡ እነ FAO, WTO, FIFA, እና ሌሎቹ በዚህ መልክ የተፈጠሩ ናቸው፡፡
3. ድቅል አሕጽሮት፡- ፊደልን ከቃላት ጋር በማጣመር የሚፈጠሩ የአሕጽሮት ስሞች ናቸው፡፡ በእንግሊዝኛው Dormat – Digital format በዚህ መልኩ የተፈጠረ ሲሆን እስካሁን በአማርኛ የማውቀው ስም አላገኘሁም፡፡
እነዚህን መንገዶች እንዲያው ለማመላከት ያህል የጠቀስኳቸው አሕጽሮት እንዴው በደፈናው በዘፈቀደ የሚወጣ ሳይሆን አስበውበትና ተጠብበውበት የሚያወጡት መሆኑን ለመጠቆም ያህል ነው፡፡ ቢቻል ደግሞ ሞልቶ ከተረፈን ቋንቋ የራሳችንን ሀገር ቋንቋ አሕጽሮቶች ብንጠቀም ኩራትም ማንነትም ይሆንልናል፡፡ ባለሞያዎቹ እንዲያውም ቋንቋው ባለሆኑ ፊደሎች የተመሠረቱ አሕጽሮቶችን ‹‹Immigrant acronyms› ይሏቸዋል፡፡ የተሰደዱ አሕጽሮቶች እንደ ማለት ነው፡፡ ሰሞኑን እንዲያውም ሕገወጥ ስደት የሀገሪቱ መወያያ ጉዳይ እየሆነ ነውና እኛም ቢያንስ በሕገ ወጥ መንገድ እየተሰደዱ የሚመጡ ቃላትን ሃይ ብንላቸው ከመደናገረም፣ ከመወናገርም እንድን ይመስለኛል፡፡

ሰኔ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው በላከው መግለጫ   ቀኑ እንዲራዘም የተደረገው የከተማው ከንቲባ በእለቱ የተማሪዎች የምረቃ በአል ፣ የመንገድ ምርቃና የፖሊስ ሀይሉ በስልጠና ላይ በመሆኑ በቂ ሀይል የለም በሚል ፓርቲውን በጠየቀው መሰረት ነው። ፓርቲው በከንቲባው የቀረበውን ጥያቄ ተገቢ ሆኖ ስላገኘነው በጎንደር የሚደረገውን ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ከሰኔ 30 ቀን 2005 ዓ.ም ወደ …

ሰኔ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ከእሰራኤል አገር በደህህነት ሙያ ሰልጥነው በቴሌኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት  እና በተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት ከተመደቡት መካከል ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የደህንነት አባሎች ታሰሩ። አባሎቹ የታሰሩት መረጃውን ለኢሳት አቀብላችሁዋል በሚል ተጠርጥረው ነው። እስካሁን ምን ያክል የደህንነት ሰራተኞች ተይዘው እንደታሰሩ አልታወቀም። ኢሳት ከአስተማማኝ የደህንነት ምንጮች ባገኘው መረጃ ስልጠናውን አጠናቀው ወደ አገራቸው …

ሰኔ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የማእከላዊ ስታትስቲክስ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሳሚያ ዘካሪያ  የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት 85 ነጥብ 9 ሚሊዮን መድረሱን የገለጹ ሲሆን ፣ ከዚህ አሀዝ ውስጥ 81 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆነው ህዝብ በገጠር የሚኖር ነው። የ2005ዓም የህዝብ ብዛት ከአምናው ጋር ሲነጻጸር የ2 ሚሊዮን ሰዎች ጭማሪ አሳይቷል።። የወንዶች ቁጥር ከሴቶች ቁጥር በ500 …



የትምህርት ጉዞው የተጠናቀቀ ይመስላል፡፡ ተማሪዎች በምረቃ ቀን የሚለብሱትጋወን አስመራቂ ቤተሰቦቻቸው ወደ ምረቃውቦታ የሚገቡበት የመግቢያ ትኬት ከየትምህርት ክፍላቸው እየወሰዱ ነው፡፡ አንድ ከዚህበፊት ያልተለመደ ተግባር ግን ይቀራል፡፡ የአንድ ሙሉ ቀንስልጠና፡፡ ከጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት በመጡ ባለሙያዎችከምረቃ በኋላ ሊሰማሩባቸው ስለሚችሉባቸው የስራ አይነቶች፡፡

ገነትም ከነዚህ ሰልጣኞች መካከል አንዷ ስትሆን 3 አመትየዩንቨርስቲ ቆይታዋ Applied Biology ያጠናች ስትሆን ከተቻለ አንድ ፋርማሲ ውስጥ ሰራተኛሆና ለመቀጠር አለዚያም መምህር እሆናለው የሚል ህልም ነበራት፡፡በስልጠናው የሰማችው የስራ መስክ ግንአልተዋጠላትም፡፡ ተደራጅቶ የባልትና ውጤቶችን መሸጥ፣ የከተማ ግብርና ላይ መሰማራት፣ የኮብል ስቶን ማንጠፍስራ፣ ፓርኪንግ ..ተ፡፡

አሁን ስልጠና በመውሰድ ላይ የሚገኙት ተማሪዎችን ከሚያስተምሩት የዩንቨርስቲ መምህራን አንዱ የሆኑት አቶ ዳዊት ገብሩ (ስማቸው የተቀየረ) ግን የምሩቃኑ ብቃት አሳስቧቸዋል፡፡ አቶ ዳዊት የሚያስተምሩት የሞራል ፍልስፍና ትምህርት ሲሆን፤ ሰሞኑን የመጨረሻ ፈተና ለተመራቂ ተማሪዎቻቸው የፈተኑት ሲሆን አንድ የፈተና ወረቀት ግን ይጠፋባቸዋል፡፡ የመጥፋቱን ምክንያት ሲያጣሩም ኩረጃን ለመቀነስ በማሰብ ተማሪዎች ከሌላ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች ጋር ተደባልቀው የሚፈተኑ በመሆናቸው እና ፈተናው የጠፋባት ተማሪ የማታውቀውን የሶሻል አንትሮፖሎጅ ፈተና ተፈትና በመውጣቷ መሆኑን ይደርሱበታል፡፡ አቶ ዳዊት ተማሪዋን አስቀርበው ለምን እንዳልተፈተነች ሲጠይቋት፤ እንግሊዝኛ ማንበብ እንደማትችል እና የተፈተነችው ፈተናም የሞራል ፊሎሶፊ ፈተና እንደሆነ አስባ እንደተፈተነች ትናገራለች፡፡

የዲግሪ ምሩቋ የምትፈተነውን ፈተና አለማወቋ አቶ ዳዊትን ግራ ከማጋባትም አልፎ ተስፋ እንዲቆርጡ አድርጓቸዋል፡፡ እናም ትምህርት ወዴት ወዴት? ብለን እንጠይቅ ዘንድ ተነሳን፡፡
 
ትምህርት

የሰው ልጅ ሁሉን ያውቅዘንድ አይቻለውም ስለዚህም ስለ ክዋክብቱ መረዳቱ የበዛለት ላላወቀው እሱም ስለስነ ተዋልዶ እውቀቱ ከሌለው ከአዋቂው የሚቀስምበት ስርዓት ነው ትምህርት፡፡ አንድ ሰውአቃቂ ምሁር ይባል ዘንድበሁሉም የትምህርት ዘርፎች የዕውቀት ላቂያ ይኑረው ያኔም አዋቂይባላል፤ ይለናል Renaissance Man ሕልዮት፡፡ ለዛም ይመስላልበአብርሆትዘመን  የነበሩ ምሁራን ሁሉን አቀፍእውቀት ነበራቸው ልንል የምንችለው፡፡ የፍልስፍና፣ የሂሳብ፣ የስነክዋክብት፣የስነሰብ .. እውቀቶችን አንድ ምሁርአቅፎ ሊይዝ ይችል ነበር፡፡

ይሄ ትክክል አይደለም ይልቅስ በህብረተሰቡ ውስጥ እምርታ ይመጣ ዘንድየስራ ክፍፍል (Division of Labor) ወሳኝ ነው ብሎስኮትላንዳዊው የስነምጣኔ ምሁርአዳም ስሚዝ የሀሳብ ሽግግር ካደረገ ወዲህ፡፡ እያንዳንዱ ህብረተሰቡ አካል አንድየስራ መስክ ላይ በተለየ (Specialize) አድርጎ ጥናት ካደረገ እና ከተማረበዘርፉ ትልቅ አስተዋፅኦ ያመጣል በሚል የትምህርትስርዓቶቹም በዚህ ሀሳብ መቀረፅጀመሩ፡፡ ባጫ ምህንድስና አበበህግ አይዳ እርሻ.. እየተማሩበያዙት ሙያ ላቂያን ማሳት ይችላሉየሚለው Specialization ሕልዮት፤ አሁን ድረስ በትምህርቱዘርፍ ተግባራዊ እየሆነ ነው፡፡

ሱፍ ለባሽ ምሁር

በኢትዮጵያ የዘመናዊ ትምህርት ታሪክ መቶ አመትእንኳን አልደፈነም ፡፡ የመጀመሪያው ዘመናዊ የመንግስት ትምህርት ቤት 1908 ነው የተቋቋመው እስከ ጣልያን ወረራም ብዙ ተማሪዎችንማስተማር አልተቻለም በአብዛኛውም ከውጭ ተምረው የመጡ ኢትዮጵያዊያን ነበሩእንደ ምሁር የሚቆጠሩት፡፡ ከነዚህ በውጭ ተምረውየመጡ 120 ተማሪዎች ውስጥ ጣልያን በተለምዶ የሚያዚያ 28 ጭፍጨፋተብሎ በሚጠራው ድርጊት 75 በመቶዎቹን እንደ ገደላቸው የመንግስትን ሪፖርት ጠቅሰው Mrgery Perham, The Government of Ethiopia ባሉት መፅሃፋቸውያስረዳሉ፡፡

እንግዲህ በጣሊያን ወረራ 75 በመቶ የተማረሀይሏን ካጣች በኋላ እስከንጉሱ የስልጣን ዘመን ማክተሚያ ድረስ የተማሪዎችቁጥር (በውጭም በሀገር ውስጥም ተምረው የመጡት) በብዙ እጥፍ ጨምሯል፡፡ ነገር ግን አውሮፓን አይቶ የመጣው ምሁር ብዙ ፈተናዎች አጋጥመውታል፡፡ ከዋና ፈተናዎች አንዱ በተማረበት መስክ ስራ ያለማግኝቱ ነው፡፡ አለ ከተባለ የፈረንሳይ ህግ ትምህርት ቤት ህግ ተምሮ የሀረርጌ አውራጃ አስተዳዳሪ የእልፍኝ አሽከር፣ Literature 4 ዓመት ሙሉ እነ ሸክስፒርን እነ ሞንታኝን፣ እነ ዳንቴን እንዲያም ሲል እነ ቶልስቶይን ሲያጠና ከርሞ በንግድ ሚኒስቴር የወርሃዊ የዋጋ ጥናት ባለሙያ መሆን፣ የምጣኔ ሀብት ትምህርትን እንደ ውሃ ጨልጦ በበጌምድር አውራጃ የደምቢያ ወረዳ የመንግስት ሹም .. እየሆኑ ነበር እነዚህ እውቀትን እና አለባበስን ከአውሮፓ የቀዱ ምሁራን ወደ ስራ አለም የሚሰማሩት ፡፡


በርግጥ   ትውልድም  የዚህ ሱፍ ለባሽ ምሁር አካል ነበር፡፡

የተማረ ሁሉ ያስተምር

ደርጉ መጣ‹ሁሉንም ነገር ወደ ጦርግንባር; ከማለቱ በፊት የትምህርት ዘመቻ ጀመረ‹መሃይምነት አይነስውርነት ነው› በሚል መፈክርየገጠሩን ህዝብ ስሙን ይፅፍዘንድ ፊርማ በእርሳስ ይፈርም ዘንድ አስቻለው፡፡ነገር ግን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚወጡ ተማሪወች የተማሩትን ትምህርት የት አደረሱትከተባለ፤ ግማሾቹ አቢዮት ጠባቂ፣ ግማሾቹ የቀበሌ ሹም ወታደርቤትም የገቡ አሉ፡፡

ይልቁንም ደርጉ ተማሪዎችን ከነ ኢህአፓ ጋርንክኪአላቸው በሚል በጥርጣሬ ነበር የሚመለከታቸው፡፡ ይባስብሎም ከሀገር በፊት የምን ትምህርትብሎ በተለምዶምሁሩ ጦርየሚባለውን ወታደር ከዩንቨርስቲ አፍሶ ብላቴ ጦርማሰልጠኛ ከተተ፡፡ የተማሩት ትምህርትም አላማው ጠፋባቸው ለነዚህ ምሁር ወታደሮች፡፡

ስለምንስ ከምሁራን መካከል ትፈልጉኛላችሁ?!

ኢህአዴግ በስልጣን ዘመኑ ከሰራቸውአመርቂ ስራዎች አንዱ ትምህርትን በነፃ ተደራሽለማድረግ ያደረገው ጥረት እና ያምያመጣው ውጤት ነው፡፡ አጠቃለይ የትምህርት ፖሊሲ 1986 . ከወጣ በኋላ ብዙአዳዲስ ትምህርት ቤቶች ተሰርተዋል፣ የትምህርት ቤቶች የቅበላአቅም በብዙ እጥፍ ጨምሯል፣30 በላይ የመንግስት ዩንቨርስቲዎች ተገንብተዋል፡፡

ነገር ግን የትምህርት ፖሊሲውን ሁለት ዋነኛተግዳሮቶች አንቀው ይዘውታል፡፡

1. የትምህርት ጥራት ጉዳይ፡

መንግስትም እንደሚለው ዋነኛው የትምህርት ፖሊሲያችን ፈተና የጥራት መጓደል ነው፡፡ አሁን ባለውሁኔታዩንቨርስቲ Chemistry ምሩቅ ተማሪዎች Chemistry Khemistry እያሉ እንደሚፅፉ ይነገራል፤ አራቱን የሂሳብ ስሌቶች የመለየት ችግርም የምሩቃኑ ሌላው ጣጣ ነው፤ በሶሲዎሎጅ ተመርቀው ካርል ማርክስ ሲባል እሱ ደግሞ ማነው? ማለትም ያስደነግጣል፤ ህግ ተምረው Civil Right እና Civil Code ነትን አለማወቅም ይወራል፡፡
አዎ ጥራቱ ችግር ውስጥነው፡፡

2. ሁለተኛው እና አዲሱ የትምህርትፖሊሲው ችግር ሰዎች ተምረውበተማሩበት ትምህርት መስክ ሊሰሩ አለመቻላቸውነው፡፡

የማእከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን 2011 .የከተማ ስራ አጥነት 18 በመቶ እንደሆነመረጃው ያስረዳል ፡፡ሌሎች አለማቀፍ ተቋማት ደግሞ መጠኑከዚህ እንደሚልቅ ይገልፃሉ፡፡


እንግዲህ ከዩንቨርስቲ የሚወጡት ምሩቃን ከነዚህ ስራ አጦች ቁጥርላይ የሚደመሩ ናቸው፡፡ ይሄን ቁጥር ለመቀነስይመስላል መንግስት ሰሞኑን እንደምንሰማው ወጣቶችን በተለያዩ የጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት ተግባራት ላይ እንዲሰማሩእያደረገ የሚገኝው፡፡ ችግሩ ግን አንድ ሰው Computer Science ተምሮ የኮብል ስቶን ጠረባ ላይ የመሰማራቱን ጥቅም ስናሰላስለው ነው፡፡ ችግሩ ግን አንድ ወጣት Physics ተመርቆ በከተማ ግብርና ተግባር ላይ ሲሰማራ የተማረውን ትምህርት ተግባር ላይ እንዴት ሊያውለው ይችላል? ያልን እንደሆነ ነው፡፡ ችግር የሚሆነው Afan Oromo & Literature የተማረች ወጣት በባልትና ውጤት ስራ ላይ ተሰማርታ ስናይ ነው፡፡

ለመሆኑ: ይሄ ስኬት ነው እንዴ?


Nelson Mandela
በግለታሪካቸው ላይ ስለ ትምህርትሲናገሩ :

“Education is the great engine of personal development. It is through education that the daughter of a peasant can become a doctor, that a son of a mineworker can become the head of the mine, that a child of farm workers can become the president of a nation.”

አሁን ወዳለው ሀገራችን የትምህርት ውጤት ስንሄድ ማንዴላ እንደሚሉት ትምህርት የገበሬውን ልጅ ዶክተር የማዕድን ቆፋሪውን ልጅ የሀገር መሪ የሚያደርግመሳሪያ ነው ያሉትን የትምህርት Upgrade የማድረግ ሚና Downgrade በማድረግየተተካ ያስመስለዋል፡፡ አለዚያማ ስለ ፓለቲካል ህልዮት ሲማር የከረመወጣት እንዴት የብየዳ ስራ ላይ ይሰማራል?፡፡

ገነትስለ ስራ አስበሽ ታወቂያለሽ?›› ተብላ ስትጠየቅ ‹‹እኔ የምማረው እናቴ ተመርቄ ስታየኝ ደስ እንዲላት ነው እንጅ ስራ መስራት አልፈልግም›› ትላለች፡፡ የሞራል ፍልስፍና ፈተናን ከሶሻል አንትሮፖሎጅ ጋር ጋር መለየት አቅቷት ፈተናውን ሳትወስድ ቀረችው ምሩቅ ለስህተቷ የምትሰጠው ምላሽ ፈገግታ ነው፡፡ እንግዲያውስ ገነቶችን ከምሁራን መካከል መፈለግ ምን ይሆን እርባናው?

ግብፅ ውስጥ ፕሬዚዳንት ሞርሲ ከሥልጣን ተገግደው የሕገመንግሥታዊ ፍርድ ቤቱ ጠቅላይ ዳኛ አድሊ መንሱር ቃለ መሃላ ፈፅመው ሥልጣን ተረክበዋል፡፡

ለግብፅ ፕሬዚደንት ከሥልጣን መወገድ የሕዝብ አመፅ መነሻ ቢሆንም የአገሪቱ ሠራዊት የአገር ሰላምን ማስከበር አለብኝ በማለት ጣልቃ ገብቷል። 

በግብፅ ፖለቲካ የወታደሩን ሚናና የአገሪቱን ቀጣይ ሠላምና መረጋጋት እንዲገመግም ትዝታ በላቸው የፖለቲካ ተንታኙን ጃዋር ሲራጅ ሞሀመድን ጋብዛለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡት

በያዝነዉ ሳምንት ሰኞ በምዕራባዊትዋ አፍሪቃ አገር በማሊ ሚታየዉን ዉጥረት ለማርገብ በእንግሊዘኛ ምህጻሩ ኒኑስማ «MINUSMA»የተሰኘዉ የተመድ አረጋጊ ቡድን 12,600 ወታደሮቹን እንዳሰለፈ ተነግሮአል።

በግብጽ ለመጀመሪያ ጊዜ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት ፕሬዝደንት ሞሐመድ ሞርሲ በጦር ኃይሉ ከስልጣናቸዉ ከተነሱ ወዲህ የአገሪቱ የፖለቲካ አቅጣጫ ወዴትነት እስካሁን አለየለትም።

ሰኔ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ ግርማ ለፓርላማው ሁለት ሞሽን ያቀረቡ ሲሆን አንደኛው ሞሽን መንግስት በ2006 በጀት ዓመት የበጀት ጉድለቱን ለመሸፈን ከመንግስት ባንኮች ሊበደር ያሰበውን 16 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በግማሽ ያህል (8 ቢሊየን ብር) በመቀነስ በተለይ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሃብቶች የብድር ድጋፍ እንዲውል የሚጠይቅ ነው፡፡ ሁለተኛው የብሮድካስት ባለስልጣን ብሮድካስትን …

ሰኔ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሙርሲ ፍትሀዊ እና ግልጽ በሆነ ምርጫ ተመርጠው ለአንድ አመት ያክል በስልጣን ላይ ከቆዩ በሁዋላ በህዝብ ተቃውሞና በወታደራዊ ግፊት ከስልጣን እንዲወርዱ ተደርጓል። ፕሬዚዳንቱ በአንድ አመት የስልጣን ጊዜያቸው ፣ እርሳቸውን ለስልጣን ያበቃውን የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ አባላትን ከመጥቀም ባለፈ የፈየዱት ነገር የለም በሚል ተደጋጋሚ ተቃውሞ ሲቀርብባቸው …

ሰኔ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰላም አስከባሪነት ስም ሶማሊያ የሚገኘው የኬንያ ጦር የሶማሊ ጎሳዎች እርስ በርስ እንዲጋጩ  አድርጓል የሚል ክስ በሶማሊያ መንግስት ቀርቦበታል። ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ የተጻፈ ደብዳቤ በስህተት ለጋዜጠኞች በመላኩ ዜናው ይፋ መውጣቱን ቢቢሲ ዘግቧል። የኬንያ ጦር በኪስማዮ አካባቢ የተለያዩ ጎሳዎች እርስ በርሳቸው እንዲጋጩ በማድረጉ 65 ሰዎች መሞታቸውን ደብዳቤው ይጠቅሳል። …


በማናዬ በላይ

II.        በእሳት የተፈተነ ብረት – ዶ/ር ቢሂምራዎ ራምጂ አምበድከር
ዶ/ር ቢሂምራዎ ራምጂ አምበድከር እ.ኤ.አ ሚያዚያ 1889 ዓ.ም ማሀራሽትራ ክልል በአሁኑ ማድያ ፕራዲሽ ዉስጥ በምትገኝ ራትናግሪ በምትባል ወረዳ የተወለደ የዚያኔዉ ህፃን ያንን ሁሉ ጭቆናና በደል ያስተናገደ በኋላ ለህንድም ይሁን ለሌላዉ አለም ለፍትህ እና እኩልነት ትግል አርአያ የሆነ ታላቅ ሰዉ ነበር፡፡ አምበድከር በመላዉ የሹድራ ወይም አይነኬ ማህበረሰብ አባላት ላይ ይፈፀም የነበረዉ ጭቆናና በደል ማሳያ ነዉ፡፡ በዚህ ጽሑፍ የመጀመርያ ክፍል በቅድመ ታሪክ ላይ የተገለፁት ይህ ታላቅ ሰዉ በልጅነቱ የደረሰበትን ግፍ ከከተበበት የግል ማስታዎሻዉ ላይ ከታተመዉ “Waiting for Visa” ላይ የተወሰደ ነዉ፡፡ በህንድ በዉልደት የሹድራ አባል ከሆኑ ትምህርት፤ ገንዘብ፣ ክብር፤ ስልጣን ማግኘት የማይታሰብ ነዉ፡፡ እርስዎ ሲወለዱ ጀምሮ የተፈጠሩት ለአገልጋይነት ነዉ ተብሎ ይታሰባል፡፡ በአጋጣሚ የሚደርስብዎን ጭቆና ተቋቁመዉ ቢማሩ፤ ሀብት ቢያፈሩ፤ ስራ ወይም ስልጣን ቢይዙ ማህበራዊ ህይወትዎን ሊቀይረዉ አይችልም፡፡
አምበድርከርም በህንድ በነበረዉ የእንግሊዝ ጦር ሰራዊት ዉስጥ ይሰራ የነበረዉ እና የሰላ እሳቤ የነበረዉ አባቱ ምስጋና ይግባዉና መጻሕፍትን እና እገዛን ከአባቱ እያገኘ እንደ ሹድራ አባልነቱ የሚደርስበትን ግፍ ተቋቁሞ በ1907 ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባዉን ዉጤት ሲያመጣ በወቅቱ ለሚኖርበት ማኅበረሰብ አባል የመጀመሪያ ስለነበር ተራማጅ በነበሩ የማኅበረሰቡ አባላት ዝግጅት ተሰናድቶለት ተሞግሶ ነበር፡፡ ከዚያም በ1913 ከቦምቤ ዩኒቨርሲቲ በፐርሺያና እንግሊዝኛ፤ የጋይከዋር ስኮላር ተጠቃሚ በመሆንም ወደ አሜሪካ ተጉዞ ከኮለምቢያ ዩኒቨርሲቲ በሦስት አመት ቆይታ MA እና PhD በኢኮኖሚክስ ያገኘ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ የአንትሮፖሎጂ፣ ፖለቲካል ሳይንስ፣ ሶሾሎጂ አና ሌሎች ኮርሶችን ወስዶ ነበር፡፡ ከዚያም ከአሜሪካ ቆይታዉ በቀጥታ ያመራዉ ወደ ለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ስኮላርሺፑ አልቆ ስለነበር እና ተመልሶ የመስራት ግዴታ ስለነበረበት በ1917 ዶክትሬት ትምህርቱን አቋርጦ ወደ ህንድ በመመለስ በባሮዳ ማሃራጃ ስራ ቢጀምርም የማኅበረሰቡ ማግለል እና ህዝባዊ አገልግሎት መከልከል ሊያሰራዉ ባለመቻሉ ስራዉን ለቆ በወቅቱ ትንሽም  ቢሆን ይሻል ወደነበረዉ ቦምቤ ይመለሳል፡፡ በወቅቱ ዶ/ር መሆኑ በማኅበራዊ ህይወቱ ላይ ምንም የፈየደለት ነገር አልነበረም፡፡
ከአመት ስራ መፍታት በኋላ በሲንድንሀም የኮሜርስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የፖለቲካል ኢኮኖሚ መምህር ሆኖ ይቀጠራል፡፡ በዚህም ወቅት አብረዉት ይሰሩ የነበረት የበላይ ካስት ሂንዱ ፕሮፌሰሮች የጋራ ዉሃ እንዳይነካ ይከለክሉት ነበር፡፤ በዚህ ጊዜ ነዉ እንግዲህ አመበርከር የፍትህ ትግሉን አንድ ብሎ የጀመረዉ፡፡ በዚህ ወቅት የሹድራ አባላትን ንቃተ ህሊና ያሳድጋል ብሎ ያሰበዉን ሙክንያክ (የጭቁኖች ጀግና) የሚል በማራቲ ቋንቋ የሚዘጋጅ መጽሔት መሰረተ፡፡
አምበርከር ለማንኛዉም ትግል እዉቀት ከምንም በላይ የላቀ መሳሪያ ነዉ የሚል ጠንካራ እምነት ስለነበረዉ ስራዉን ለቆ የጀመረዉን የዶክትሬት ድግሪ ለመጨረስ በ1920 ወደ ለንደን በድጋሚ አቀና፡፡ በለንደን የኢኮኖሚክስ ት/ቤት የM.Sc እና D.Sc ትምህርቱን እንዲሁም በሌላ ኮሌጅ ሕግ ተምሮ በሕግ የሚሰራበትን ፍቃድ ጨምሮ በመያዝ በ1923 ወደ ህንድ ተመልሶ በሕግ ሙያ መስራት ጀመረ፡፡
አምበድከር በአሜሪካ ቆይታዉ በወቅቱ የነበረዉ የጥቁር አሜሪካዉያን ጥያቄ ያልበረደበት ጊዜ ከመሆኑ ባሻገር በአሜሪካ እና በለንደን ያየዉ የማኅበረሰብ ሁኔታ ለወደፊት ትግሉ አስተዋፅኦ እንደነበረዉ በጽሑፎቹ ላይ ገልጿል፡፡
III.        የአምበድከር ማህበራዊ እና ሐይማኖታዊ ጥያቄ
አምበድከር ከለንደን መልስ የመጀመሪያ ትግሉ የማኅበራዊ እና ሐይማኖታዊ እኩልነትን ለማስፈን ነበር፡፡ በ1924 ቀደም ሲል ተፈጥሮ በከፍተኛ ካስት ሂንዱ ጫና እና በገንዘብ እጦት የፈረሰዉን የተጨቆኑ የሹድራ አባላትን ጥያቄ ይዞ የተነሳ ማኅበር ባሂሽክሪት ሳባህ ን በድጋሚ በማቋቋም እና የማኅበሩ መሪ በመሆን educate, agitate and organize የሚል መፈክር ይዞ እዉቀቱን እንደ መሳሪያ መሰሎቹን እንደ ወታደር ይዞ በመንቀሳቀስ ሶስት የታወቁ ሰላማዊ ትግሎችን አከናዉኗል፡፡
አንደኛዉ በ1927 የተደረገዉ ማሀድ ሳትያግራህ (ሰላማዊ ትግል) ሲሆን አላማዉም ለዘመናት ለአይነኬዎች ተከልክሎ የነበረዉ የህዝብ ዉሀ ታንከርን መጠቀም ነበር፡፡ ይህ ታንከር ምንም እንኳን የህዝብ ቢሆንም አይነኬዎች ግን እንዲጠቀሙ አይፈቀድላቸዉም ምክንያቱም እነሱ ከነኩት ዉሀዉ ይበከላል ተብሎ ስለሚታሰብ፡፡ በሂደት ቦምቤ ሌግስሌቲቭ ካዉንስል ዉሀዉ ለሁሉም አገልግሎት እንዲዉል የሚል ህግ ያወጣል፡፡ ይህንን ተከትሎ ነዉ እንግዲህ አንበርከር ከ 10ሺህ በላይ አይነኬ ህዝቦችን አስከትሎ ዉሀዉን ተጠቅመዉ ተመለሱ፡፡ ከትንሽ ሰዓታት በኋላ ወደ ኋላ ዘግይተዉ የነበሩ የሹድራ ካስት  አባላት ተዘጋጅተዉ በመጡ ሌላ ካስት አባላት ተደበደቡ፡፡ በሂደትም የፖለቲካ ስርዓቱ ላይ ያሉትም ከአይነኬ ዉጭ የነበሩ ካስቶች ስለነበሩ ጫና ፈጥረዉ ህጉ እንዲቀየር አድርገዋል፡፡ ይህም የአይነኬ አባላትን አምበድከርን ጨምሮ በጣም ያሳዘነ ድርጊት ነበር፡፡

ሁለተኛዉ በ1930 የተከናወነ ካላራም የቤተ-ሐይማኖት የመግባት ሰላማዊ ትግል ነበር፡፡ አይነኬዎች በእምነት ሂንዱ ቢሆኑም ወደ ቤተ-እምነቱ ግን መግባት አይፈቀድላቸዉም ነበር፡፡ ቤተ-እምነቱን እንዳይበክሉ ተብሎ ጥላቸዉን ጨምሮ በግምት ትልቅ የሰዉ ቁመት ረጅም ጥላ ያህል ርቀዉ ካልሆነ በአቅራቢያዉ እንኳን ማለፍ አይፈቀድላቸዉም ነበር፡፡ ይህ በየትም ሀይማኖት የማይታይ ተግባርን ለመቃወም አምበድከር የመረጠዉ ወደ ቤተ-እምነቱ በቡድን የመግባት ስልትን ነበር፡፡  በናሲክ የሚገኘዉ ካራላም ቤተ-እምነት ለዚህ ተግባር በወቅቱ የተመረጠ ነበር፡፡ ይህ ትግል ለአንድ ወር የቆየ ቢሆንም ዉጤታማ አልነበረም፡፡ የደህንነት ስጋት እና የእርስ በርስ ግጭትን በመፍራት ቅኝ ግዥ የነበሩት እንግሊዞች ጣልቃ በመግባት አምበድከርን ለማሳመን ቢጥሩም ማስቆም ስላልቻሉ ግጭት ተፈጥሮ ብዙ ሰዎች ከተጎዱ በኋላ ቆሟል፡፡ ሶስተኛዉ ፖና ፐርቨቲ ቤተ-እምነት የመግባት ስርዓት ሲሆን በዋናነት በሌሎች ተዘጋጅቶ አምበርከር ያግዘዉ የነበረ ነዉ፡፡

ይቀጥላል፡፡
— 
ጸሐፊውን ለማግኘት [email protected] ላይ ይጻፉላቸው፡፡

       *እስክንድር ገብረ ክርስቶስ ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ፣ ሰኔ ፳፻፭ ዓ.ም /መጠነኛ አርትዖት ተደርጎበት የቀረበ/ በቤተ ክህነታችን አሠራርና አደረጃጀት ውስጥ የሚታየውን የሙስናና የጎጠኝነት ችግሮች በተመለከተ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ በቤተ ክርስቲያኒቱ ልሳናት በመጠቀም ያልጠቆመው ያላመላከተውና በመረጃ በማስደገፍ ይፋ ያላደረገው ብልሹ አሠራር ይኖራል ተብሎ አይገመትም፡፡ ከቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮዎች እጅጉን በተቃራኒው መንገድ የሚገለጹት የብልሹ አሠራር ምንጮች እንዲወገዱም ምንጮችን …

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ‹‹የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነት››በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ ንቅናቄ ይፋ ማድረጉና የንቅናቄው የመጀመሪያ የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር ከተማ ሰኔ 30 ቀን 2005 ዓ.ም ለማድረግ በህገ መንግስቱ መሰረት ለሚመለከተው አካል የማሳወቂያ ደብዳቤ በማስገባት የቅስቀሳ ስራውን በጎንደርና አካባቢው መስራት ቢጀምርም መንግስት ህገወጥ እስር እያካሄደ ይገኛል፡፡ ለቅስቀሳ ስራ ወደ ምዕራብ አርማጭሆ ተንቀሳቅሰው የነበሩ አራት የፓርቲው […]

ያለ መታደል ጎንደርን በአካል አላውቃትም። ነገር ግን እንደ ማንም ኢትዮጵያዊ በልቤ ዉስጥ ልዩ ቦታ አላት። ያለ ጎንደር ኢትዮጵያ የምትባል አገር ትኖር ነበር ለማለት ያስቸግራል። ግራኝ መሃመድ በቱርኮች እየተረዱ፣ አብዛኛዉ የኢትዮጵያን ክፍል ተቆጣጥረዉ በነበረ ጊዜ፣ ስመ ጥሩ ያልነበሩ፣ ብልሹዉ የሸዋ ንጉስ፣ አጼ ልብነህ ድንግል ይሞታሉ። አጼ ገላዉዲዮስ ይተኳቸዋል። የግራኝ ጦር በመጠንከሩ ሽሽት ወደ ሰሜን፣ ወደ ጎንደር […]

በአሜሪካ ዴንቨር ከተማ ከቤተሰባቸው ጋር የሚኖሩት አቶ ታምራት ላይኔ የጋዝ እስቴሽን በመክፈት በንግድ ስራ መሰማራታቸውን ምንጮች ገለፁ። በሙስና ወንጀል ተከሰው ለአስራ ሁለት አመት ታስረው የወጡት አቶ ታምራት ከተፈቱ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ፥ አማኝ ሆነው እንደሚቀጥሉና ነገር ግን በማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከማንም ፖለቲካ ድርጅት ጋር ሳይወግኑ ለአገር ይጠቅማል የሚሉትን ሃሳብ እንደሚያካፍሉ፣ መፅሃፍ እንደሚያዘጋጁ…ገልፀው […]

በያመቱ ፣ እ ጎ አ ከ 1901 ዓ ም አንስቶ በከፍተኛ ጉጉት የሚጠበቀውን የኖቤል ሽልማት ለማግኘት የማይመኝ የሳይንስ ተማራማሪ ይኖራል ብሎ መገመት ያስቸግር ይሆናል። ተሳክቶላቸው በየጊዜው ከፍኛውን ሽልማት የሚያገኙትና በሙያው አንቱ የሚሰኙት ሊቃውንት

የቀድሞይቱ ዩጎዝላቪያ ሬፑብሊክ ክሮኤሺያ ባለፈው ሰኞ 28ኛዋ የአውሮፓ ሕብረት ዓባል አገር ለመሆን በቅታለች። ሕብረቱ ክሮኤሺያን የተቀበለው በጋራ ምንዛሪው በኤውሮና በርከት ባሉ ዓባል መንግሥታት የበጀት ቀውስ ተወጥሮ በሚገኝበት ወቅት ነው።

ሙርሲ በቴሌቪዥን ሲነጋሩ ደጋፊ-ተቃዋሚዎቻቸዉ እዚያዉ ካይሮ ዉስጥ ይገዳደሉ ነበር።ጄኔራል ሲሲ የቆረጡት ገደበ-ሠዓትም አብቅቷል።እና ታንክ መትረየስ አስጠምደዉ ካይሮ ቤተ-መንግሥት ቢገቡስ? ምርጫዬ አሉ ሙርሲ «ሞት»

የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ትናንት በሴኔጋል፣ በደቡብ አፍሪቃ እና በታንዛንያ ያካሄዱትን የአንድ ሣምንት ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ። ኦባማ በጉብኝታቸው ወቅት በአህጉሩ ያለውን ግዙፍ የኤኮኖሚ ዕድል በማመልከት፣ ሀገራቸው በዚሁ ዘርፍ ከአፍሪቃ ጋ ግንኙነትዋን እንደምታስፋፋ አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያናብራዚል ግንኙነታቸዉን እንደሚያስፋፉ እና እንደሚያጠናክሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የበረራ መስመር ወደሪዮደጄኒሮ እና ሳኦፖሎ በዘረጋበት ወቅት አሳወቁ።

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመተማ ወረዳ በገንዳሆ ከተማ ሰኔ 25፣ 2005 ዓም ከሌሊቱ 5 ሰአት ከ30 ላይ በመከላከያ ሰራዊት እና ጸረ-ሽምቅ እየተባሉ በሚጠሩ ሀይሎች መካከል በተካሄደው የተኩስ ልውውጥ ከ4 እስከ 7 የሚደርሱ  ታጣቂዎችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲገደሉ፣ 2 የወረዳው ባለስልጣናት ደግሞ ቆስለዋል። በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ …

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ አበባን ለ5 አመታት ሲመራ የነበረው የኩማ አስተዳደር  ሐሙስ ሰኔ 27 ጀምሮ  ለአዲሱ ኢህአዴግ መራሽ ካቢኔ ሥልጣኑን እንደሚያስረክብ ተጠቆመ፡፡ በመልካም አስተዳደር ችግር፣ በሙስናና ብልሹ አሰራር የሚተቸው የኩማ አስተዳደር የምርጫ 97 ቀውስን ተከትሎ ከተመሰረተው የባለአደራ አስተዳደር ስልጣኑን በግንቦት ወር 2000 ዓ.ም በምርጫ ስም የተረከበ ሲሆን ባለፉት አምስት …

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ‹‹የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነት››በሚል መሪ ቃል በጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ በመንግስት ሀይሎች  እንቅፋት እየተፈጠረበት መሆኑን አስታውቋል። ፓርቲው የመጀመሪያውን  የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር ከተማ ሰኔ 30 ቀን 2005 ዓ.ም ለማድረግ በህገ መንግስቱ መሰረት ለሚመለከተው አካል የማሳወቂያ ደብዳቤ በማስገባት የቅስቀሳ ስራውን በጎንደርና አካባቢው መስራት ቢጀምርም፤ መንግስት …

አሁን ያለንበት ወቅት አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ልጆቻችን ቤት ውስጥ መዋል የጀመሩበት፣ ወይም የክረምት መክረሚያ ነገሮችን ማከናወን የጀመሩበት ጊዜ ነው፡፡ በበጋ ከነበረው የወላጆች ወከባ ዐረፍ ብለናል፡፡ ልጆችን ትምህርት ቤት ማድረስ፣ የቤት ሥራ ማሠራት፣ ግዙ፣ አምጡ፣ ኑ፣ ሂዱ ከሚሉ የትምህርት ቤቶች ትእዛዞች ዐረፍ ያልንበት ሰሞን ነው፡፡ አሁን ልጆቻችንን ስለሚመለከቱ ሌሎች ጉዳዮች ለመነጋገር ምቹ ጊዜ ነው፡፡ እኔ ሁለት ጉዳዮችን መርጫለሁ፤ ዛሬ አንደኛውን እናንሣው፡፡
ጉዳይ አንድ
ባለፈው ሰሞን አንዲት እናት ወደ ቢሮዬ መጥተው እንዲህ አወጉኝ፡፡ ‹‹ልጄ የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅና የ 5ኛ ክፍል ተማሪ ነው፡፡ አልፎ አልፎ የማይበት ጠባይ ግራ የሚያጋባኝ እየሆነ ተቸግሬ ነበር፡፡ ወደ ትምህርት ቤት ሲሄድ የእኔን ሽቱ ይቀባል፡፡ እኔም ይህን ሳይ የልጅ ነገር አድርጌ ትቼው ነበር፡፡ በኋላ ግን ከሌላው ነገር ጋር ሲደረብብኝ ነው ግራ የተጋባሁት፡፡ ፀጉሩን እንደ ሴቶች ማስተኛት ይፈልጋል፡፡ ጥብቅ ያለ ሱሪ ካልገዛሽልኝ ይለኛል፡፡ አንድ ቀን ትምህርት ቤት አድርሼው መኪናዬን አዙሬ ልመለስ ስል ከኋላ ያለውን መኪና እንዳልነካው ዞር አልኩ፡፡ ያን ጊዜ ያየሁትን ነገር ዓይኔ ሊያምን አልቻለም ነበር፡፡ ከአንድ ሌላ ወንድ ልጅ ጋር ከንፈር ለከንፈር ሲሳሳሙ አየኋቸው፡፡ ከኋላዬ የነበረው መኪና በጡሩንባ እየጮኸብኝ እንኳን የማየውን ተጠራጥሬ ለረዥም ሰዓት ፈዝዤ ነበር፡፡

 ሥራ ከገባሁ በኋላ እጅግ ፈዝዤ ነበር፡፡ የቢሮ ሰዎች ሁሉ እየደጋገሙ ምን እንደሆንኩ ይጠይቁኝ ነበር፡፡ ግን ለማን ምን ብዬ ልንገረው? ነገሩ እጅግ አሳፋሪ ነው የሆነብኝ፡፡ ቢቸግረኝ ወደ አንዲት ጓደኛዬ ባለቤት ጋር ደወልኩ፡፡ እርሱ ሐኪም ነበርና ምናልባት ከረዳኝ ብዬ አሰብኩ፡፡ በስልክ አነጋገሬ አደጋ የደረሰብኝ ይመስል ስለነበር እየከነፈ ቢሮዬ መጣ፡፡ ከእርሱ ጋር ተያይዘን ወጣንና አንድ ቦታ ቁጭ አልን፡፡ በልጄ ላይ ያየሁትን ነገር ሁሉ ነገርኩት፡፡ እርሱም ከሌሎች የሰማቸውን የባሱ ነገሮች እየነገረ አጽናናኝ፡፡ ከዚያም የበለጠ ርግጠኛ ለመሆንና ችግሩንም በሚገባ ለመረዳት ልጄ በማይኖርበት ሰዓት የልጄን ዕቃዎች እንድፈትሻቸው ነገረኝ፡፡

አንድ ቀን አባቱ ወደ መዝናኛ ቦታ እንዲወስደው ነገርኩትና እኔ ዕቃዎቹን መፈተሽ ጀመርኩ፡፡ ያኔ ነው የልጄን ጉዳይ በጥልቀት የተረዳሁት፡፡ እኔ ያልገዛሁለት አንድ ቀይ ቲሸርት አገኘሁ፡፡ ቲሸርቱ ላይ በእንግሊዝኛ ‹I am a gay› የሚል ተጽፎበታል፡፡ ዕንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም፡፡ አልጋው ላይ ተቀምጬ ለረዥም ጊዜ አለቀስኩ፡፡ ከዚያ በኋላ መቀጠል አልቻልኩም፡፡ ልጄን እንዳጣሁት ገባኝ፤ ልጄን እንደማላውቀው ገባኝ፤ ልጄና እኔ በተለያዩ መንገዶች እየተጓዝን መሆኑ ገባኝ፡፡
የጓደኛዬ ባለቤት በጉዳዩ ላይ እንዴት ከልጄ ጋር ልወያይ እንደምችል መንገዶችን አመላከተኝ፡፡ አንድ ቀን ከልጄ ጋር ከአዲስ አበባ ወጣ አልን፡፡ አብሬው ስጫወት ዋልኩና ለሻሂ ዐረፍ ስንል አንድ ስልክ አነሣሁ፡፡ እንደ ደነገጠ ሰው ሆኜ ነበር የማወራው፡፡ ልጄም ድምፄን እየሰማና ሁኔታዬን እያየ ተደናገጠ፡፡ ስጨርስ ምን እንደሆንኩ ጠየቀኝ፡፡ ‹‹አንዲት ጓደኛዬ ከባድ ነገር እንደ ደረሰባት፡፡ ልጇ ግብረ ሰዶማዊ እንደሆነባት፡፡ በዚህም ምክንያት በሕግ ሊጠየቅ መሆኑን›› ነገርኩት፡፡ እጅግ ደነገጠ፡፡ ‹‹የእኔ ልጅ መቼም እንዲህ ያለ ነገር አያደርግም›› ብዬ ተውኩት፡፡ አፍጥጦ ዓይን ዓይኔን ያየኝ ነበር፡፡ ‹‹በጣም ከባድ ነገር ነው የገጠማት፤ ግብረ ሰዶማዊ ማለትኮ በሃይማኖታችንም ትክክል አይደለም፤ እግዚአብሔር ግብረ ሰዶማውያንን አጥፍቷቸዋል፡፡ ከዚያም በላይ ግብረ ሰዶማውያን በኅሊናቸውም ሆነ በማኅበራዊ ኑሮአቸው ላይ ችግር እንደሚገጥማቸው፤ ከሕዝቡም እንደሚገለሉ፤ አኗኗራቸውም ከተፈጥሮ ሕግ ውጭ እንደሆነ፤ ወንድ ከሴት ጋር ሴትም ከወንድ ጋር እንጂ ወንድ ከወንድ፣ ሴትም ከሴት ጋር የሚደረገው ግንኙነት እንስሳት እንኳን የማይፈጽሙት መሆኑን፡፡ የወሲብ ግንኙነት ማንኛውም ወንድ ከ ተፈቀደለት ሴት ጋር ብቻ፣ ባህሉና እምነቱ፣ ሕጉም በሚፈቅደው እድሜና ሁኔታ የሚፈጸም መሆኑን›› እየዘረዘርኩ መግለጥ ጀመርኩ፡፡ ዝም ብሎ ነበር የሚያዳምጠኝ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ልጆቻቸውን ግብረ ሰዶማውያን እንደሚያደርጓቸው፤ እነዚህ ልጆችም ሌሎችን ልጆች አባብለው ወደዚህ እንደሚያስገቧቸው፤ እንዲያውም  ‹I am a gay› የሚል ልብስ የሚለብሱ እንዳሉ ነገርኩት፡፡
ግራ ሳይገባው አልቀረም፡፡ ስለ እርሱ እንደምናገር ገምቷል፡፡ ስጨርስ ‹‹የኔ ልጅ አንተ ግን እንደዚህ አታደርግም አይደል?›› አልኩት፡፡ ምንም አላለኝም፡፡ ዝም አለኝ፡፡ መሬት መሬት ያይ ጀመር፡፡ ‹‹ምነው የኔ ልጅ ችግር አለ እንዴ›› አልኩት፡፡ ዝም አለ፡፡ ‹‹አደራህን አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ያሉ ልጆች ሌሎች ልጆችን ሳያውቁት ወደዚህ ነገር እያስገቧቸው ነውና ተጠንቀቅ›› አልኩት፡፡ እሺም እምቢም አላለኝም፡፡ ‹‹አንተ ይህንን ስታደርግ ካየሁ፤ እኔ ወዲያው ነው የምሞተው›› ስለው ተስፈንጥሮ መጥቶ ጭኔ ላይ ተደፋ፡፡ ሲያለቅስ ይሰማኛል፡፡ ዕንባውም እግሬን ሲያሞቀው ይታወቀኛል፡፡ እኔም እያለቀስኩ ነበር፡፡
ከብዙ የዝምታ ልቅሶ በኋላ ‹‹እማዬ እኔኮ ጌይ ሆኛለሁ›› አለኝ፡፡ ቀድሜ ባውቅም ያ ሰዓት ግን መብረቅ የመታኝ ነበር የመሰለኝ፡፡ ከልጄ አንደበት ይህንን ስሰማ ኩምሽሽ ብዬ ትንሽ የሆንኩ መሰለኝ፡፡ የማደርገው ጨነቀኝ፤ ምን ልመልስለት? ምን ልበለው? ግራ ተጋባሁ፡፡ ‹‹ለምን ልጄ? ለምን?›› አልኩት፡፡ ከእኛ ራቅ ብለው የሚያዩን ሰዎች ሁኔታዬ ግራ አጋብቷቸው ሁሉም እኔን ያያሉ፡፡
‹‹እኛ ትምህርት ቤትኮ ብዙ ልጆች አሉ›› አለኝ፡፡
‹‹ምን ምን ታደርጋላችሁ?›› አልኩት
‹‹ሽቱ ተቀብተው ይመጣሉ፤ ደግሞ አንድ ዓይነት ማስቲካ ነው የምንበላው፤ ‹I am a gay› የሚል ቲሸርት እንለብሳለን›› አለኝ፡፡
‹‹ቲሸርቱን ማን ነው የሰጣችሁ?›› አልኩት
‹‹አንድ ልጅ ነው ያመጣልን፤ ለሁላችን ሰጠን፡፡ ግን ከዩኒፎርማችን ሥር እንድንለብሰው ነግሮናል››
‹‹ሌላስ?››
‹‹ደግሞ አንድ ልጅ የጌይ ፊልም በዕረፍት ጊዜ ያሳየናል››
‹‹የት ነው የሚያሳያችሁ?››
‹‹በኪሱ የሚያመጣው ሞባይል አለ፡፡ እናቴ ናት የምትጭንልኝ ብሏል››
የምሰማውን እንዴት ልመነው?
‹‹እርሱኮ [የልጁን ስም እየነገረኝ] አባቱ ትምህርት ቤት ሲሸኘው ሁልጊዜ ከንፈሩን ይስመዋል›› አለኝ፡፡ ይኼኔ ነቃሁ፡፡ አስታወስኩ፡፡ ሰውዬውንም ዐወቅኩት፡፡ እኔም ደስ አይለኝም ነበር፡፡ አባት ወንድ ልጁን፣ እናትም ሴት ልጇን ከንፈራቸውን መሳም እዚህ ትምህርት ቤት የማየው ነገር ነው፡፡ ይህ ነገር ልጆቻችን ይህንን መሰሉን ተግባር ከዕድሜ ቀድመው እንዲለምዱት ያደርጋል፡፡ ከዚያም አልፎ ነገ ሌሎች ግብረ ሰዶማውያን በልጆቹ ላይ ይህንን መሰል ተግባር ሲፈጽሙባቸው ምንም እንዳይመስላቸውና የፍቅር መግለጫ አድርገው እንዲወስዱት  ያደርጋቸዋል፡፡ ከባህላችን ያፈነገጡ ነገሮችን በልጆቻችን ላይ ማድረግ እነዚህ ነገሮች በልጆቻችን ላይ በሌሎች አካላት ሲደረጉባቸው እንዳያስተውሉት እንዳይጸየፉትም ያደርጋቸዋል፡፡
‹‹ለመሆኑ አብራችሁ ስትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ?›› አልኩት፡፡
‹‹አንዳንድ ወንዶች ልጆች ይሳሳማሉ፤ እኔ ግን ይደብረኛል፤ ደግሞ ይተሻሻሉ›› አለኝ፡፡ ከገጽታው የመቅፈፍ ስሜት አየሁበት፡፡ ይህንን ስሜት ስመለከት ወደ ችግሩ ውስጥ ዘልቆ እንዳልገባበት ተረዳሁ፡፡ እኔ የማዝነው በባህላችን ተከብሮ የኖረውን የወንድም ለወንድም፣ የእኅት ለእኅት ግንኙነት ግብረ ሰዶማዊነት እያጠፋብን በመሆኑ ነው፡፡ እኔ ከአክስቶቼ ልጆች ጋር አብሬ እየተጫወትኩ፣ አብሬ እየተኛሁ ነው ያደግኩት፡፡ ልጆቻችን ግን እንዲህ ማድረግ ላይችሉ ነው፡፡ ከአጎታችን፣ ከአክስታችን ጋር መተኛት ለኛ ደስታችን ነበር፡፡ ዛሬ ግን ዘመዶች በዘመዶች ላይ እንዲህ የሚፈጽሙ ከሆነ ዝምድናችን ሊጠፋብን ነው፡፡ መምህሮቻችንን፣ የሃይማኖት አባቶችን፣ የቤት ሠራተኞችን፣ የጥበቃ ሠራተኞችን እየተጠራጠርን ልንኖር ነው፡፡ ግብረ ሰዶምነት ባህላችንን እጅግ አድርጎ ነው የሚያበላሸው፤ ማኅበራዊ ግንኙነቶቻችንን ነው የሚበጣጥሰው፤ እንዴት ያለ ችግር ውስጥ ነው የገባነው በእግዚአብሔር?
በኋላ ከአንዳንድ የሕክምና ባለሞያዎች ጋር ስንነጋገር  ብዙ ነገር ሰማሁ፡፡ በከተማችን ውስጥ የግብረ ሰዶማውያን ማዘውተሪያዎች የታወቁ ናቸው፡፡ የራሳቸው የመግባቢያ ‹ቋንቋም› አላቸው፡፡ ትልልቆቹ ግብረ ሰዶማውያን ድራግ በመውሰድ ቀዳሚዎች ናቸው፡፡ እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ለሕፃናቱ ድራጉን በከረሚላ መልክ ይሰጧቸዋል፡፡ ከወላጆቻቸው ለመደበቅ ሲሉ ልጆቹ ግለኛነትን ይመርጣሉ፡፡ ከሌሎች ልጆች ወይም ከዘመዶቻቸው ጋር ከመጨዋት ይልቅ ከጌምና ከቴሌቭዥን ጋር ብቻ መሆንን ይፈልጋሉ፡፡ በተለይም ፌስ ቡክን በሚገባ ለዚህ አስተሳሰብ ማራመጃ ይጠቀሙበታል፡፡ ወላጆች ኢንተርኔትን ልጆቻችን ያለእድሜያቸው እንዳይጠቀሙበት ማድረግ አለብን፡፡ ስለ ኢንተርኔት አጠቃቀም፣ ስለ ጥቅምና ጉዳቱ ሳንነግራቸው ነው የምንፈቅድላቸው፡፡ ይኼኔ ከበጎው ይልቅ ክፉውን የመያዝ ዕድላቸው ይሰፋል፡፡ በቤታችን ውስጥ ያስገባናቸውን የቴሌቭዥን ቻነሎችንም መቆጣጠር አለብን፡፡ ልጆቻችን ክፉውንም ደጉንም ዝም ብለው እንዲያዩ ማድረግ የለብንም፡፡ ግብረ ሰዶምን የሚያበረታቱ ቻነሎች አሉ፡፡
‹አሁን ልጅዎ ከችግሩ በሚገባ ወጥቶልዎታል?›› አልኳቸው፡፡
‹‹ሙሉ በሙሉ ከችግሩ ወጥቷል ማለት አልችልም፤ አሁንም እጠራጠራለሁ፡፡ ፍርሃቱ ገና አልለቀቀኝም፡፡ ነገር ግን ክትትሌን አላቆምኩም፤ ከልጄ ጋር ያለኝን ቀረቤታም ጨምሬያለሁ፤ ስለ ብዙ ነገሮችም እንነጋገራለን፤ የሃይማኖት ትምህርት እንዲማርም እያደረግኩ ነው፡፡ አንድ የማውቀው የሥነ ልቡና ባለሞያ ስለ ግረ ሰዶም ጉዳት በሚገባ ነግሮታል፡፡ በተለይ በዚህ ክረምት የተለየ ነገር ለማድረግ እየሞከርኩ ነው፡፡ ትምህርት ቤቶቻችንን ግን ከትምህርት ጥራትና ከክፍያቸው ባለፈ ወላጆች መከታተል አለብን፤ ልጆቻችንም የተለየ ነገር ሲያዩ እንዲነግሩን ማሳሰብ ይገባል፡፡ ዘመኑ ወላጅነት ከባድ የሆነበት ጊዜ ነው፡፡ ›› አሉኝ፡፡
ወላጆች ሆይ
እስኪ በጉዳዩ ላይ እንምከርበት፡፡ ከልጆቻችንም ጋር እንነጋገር፤ መምህራን በተማሪዎች ላይ ይህንን ነገር ፈጽመዋል ተብለው የሚከሰሱበት ጊዜ ላይ ነንና ልጆቻችን እንዳይታለሉ እንንገራቸው፤ ከሃይማኖት፣ ከሥነ ምግባር፣ ከባህል፣ ከጤናና ከማኅበራዊ ኑሮ አንጻር የሚያስከትለውን ችግር እንንገራቸው፡፡ እኛም ስለዚህ ጉዳይ መረጃ እንዲኖረን እንጠይቅ፣ እናንብብ፣ እንመካከር፤ ከተለያዩ አካባቢዎች ከምሰማው አንጻር በተለይ በከተሞች ውስጥ ችግሩ ሳይታሰብ ሥር እየሰደደ ነው፡፡ ሰሞኑን የቀረበ አንድ ይፋ ያልሆነ ጥናት በአዲስ አበባ ከተማ መሰናዶ ትምህርት ቤቶች በሚማሩ 2000 ተማዎች ላይ በተደረገ ጥናት 48% ተማሪዎች የጌይና ሌዝቢያን ደጋፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡ እኒህ እናት እንዳሉት በዚህ ዘመን ወላጅነት ፈተና ውስጥ ገብቷል፡፡ ኃላፊነቱ ሰፍቷል፡፡ መሰናክሉ በዝቷል፡፡ እስኪ የፈጣሪን ርዳታ እየጠየቅን ይህንን ነገር የሰሞኑ የቤተሰብ አጀንዳ  እናድርገው፡፡

ባለፈው ሳምንት በአውሮፓ የወጣት ስራ አጥነት ላይ የመከሩት የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት መሪዎች ችግሩን ለመፍታት የሚውል 6 ቢሊዮን ዮሮ ለመመደብ ተስማ…

አሜሪካ ሚስጥራዊ መረጃዎችን አሳልፎ በመስጠት ወንጀል የምትፈልገዉ የቀድሞዉ የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ድርጅት ሰራተኛ ኤድዋርድ ስኖዉደን በ 21 ሀገራት

ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሚኒስትር ማእረግ ደረጃ እንዲቋቋም የታሰበው የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት መ/ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ከአንድ ሳምንት ዕይታ በኋላ ዛሬ ለፓርላማው ቀርቦ እምብዛም ውይይት ሳይደረግበት መጽደቁ ታውቋል፡፡ የኣመቱ ሥራውን ሰኔ 30 የሚያጠናቅቀውና ለዕረፍት የሚዘጋው ኢህአዴግ መራሹ ፓርላማ በተጣደፈ አሰራር ያጸደቀው በዚሁ አዋጅ መሰረት የሚቋቋመው መ/ቤት መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የመተንተንና የማቅረብ …

ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አር አይ ኤ የተባለው የዜና ማሰራጫ የሮስቦሮን ኤክስፖርት አርምስ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑትን አሌክሳንደር ሚካሄቨን ጠቅሶ እንደዘገበው ሩሲያ 18 ኤስ ዩ 30 ከ የተባሉ የጦር ጄቶችን ለኢትዮጵያ ለመሸጥ በድርድር ላይ ናት። ጄቶችን ለመሸጥ ከኢትዮጵያ ጋር እየተነገጋገርን ነው። የጄቶችን ቴክኒካዊና ታክቲካዊ ብቃት ከፍ ለማድረግ እንዲሁም ከአየር ወደ ምድር …

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በነደፉት የአሜሪካና የአፍሪካ ግንኙነቶች የሚመሠረቱበት አዲስ አቅጣጫና አካሄድ ከፍ ያሉ የምጣኔ ኃብት ዕድሎ