ሰበር ዜና ከወላይታ – በወላይታ የአንድነት ሹፌር ተደበደበ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በወላይታ ከተማ በሚያከናውነው ህዝባዊ ስብሰባ የሚሳተፉ አመራሮችን ከአዲስ አበባ በመጫን የተንቀሳቀሰው ሹፌር ዛሬ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ወላይታ ማርያም ሰፈር አካባቢ ሞንታርቦና በግዢ የተገኘ ጀነሬተር ለመጫን ሲሞክር በተከለከለ መንገድ ቆመሃል ያለ የትራፊክ ፖሊስ የሹፌሩን መንጃ ፈቃድ በመንጠቅ ይሰወራል፡፡ሹፌሩ የተወሰደበትን መንጃ ፈቃድ ለማስመለስ ትራፊኩ ወዳመራበት […]

ሰበር ዜና፤ ከመቀሌ የአንድነት አመራሮች ከነ መቀስቀሻ ሞንታረቮአቸው በቀዳማይ ወያኔ ፖሊስ ጣቢያ ታሰሩ የአንድነት ፓርቲ አመራር የሆኑት አቶ አርአያ፣ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ እንግዳ ወ/ፃዲቅ እና የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ፀሀፊ አቶ ክብሮም ብርሀነ በመቀሌ ከነ መቀስቀሺያ ሞንታረቮአቸው ቀዳማይ ወያነ ክፍለከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታስሩ፡፡ አቶ እንግዳ ወ/ፃዲቅ እና አቶ ክብሮም ብርሀነ ለሁለተኛ ጊዜ […]

ታርጋ አልባዎቹ ሞተር ሳይክሎችና ዳንኤል ሺበሺ August 2, 2013 at 6:14pm በወላይታ ሶዶ ከተማ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በ28/11/05 ለሚያደርገው የህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ ለማካሄድ በስፋራው የተገኙት የፓርቲው አመራሮችና በወላይታ የፓርቲው አባላት የተለያዮ ህገ ወጥ ድርጊቶች እየተፈጸመባቸው ይገኛል፡፡በአመራሩና በአባለቱ ላይ እየደረሰ የሚገኘው ህገ ወጥ ድርጊት የተለያየ መልክ የተላበሰ ሲሆን በዋናነትም ታርጋ አልባ በሆኑ ሞተር ሳይክሎች የተፈናጠጡ […]

የኦሮሞ ተወላጆች ዋሽንግተን ላይ ተሰለፉ
ከዩናይትድ ስቴትስ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የኦሮሞ ተወላጆች ዛሬ በዋይት ሃውስ ቤተመንግሥትና በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሰልፎችን አካሄደዋል፡፡

በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ያሰሙት ሰልፈኞች ከመልዕክቶቻቸው መካከል “በምሥራቅ ሐረርጌ እየደረሰ ያለው ግፍ ይቁም፤ በኦሮሞ ምሁራንና ተማሪዎች ላየ እየበረታ ያለው የመብት ረገጣ ይቁም፤ በኦሮሞ ገበሬዎች ላይ እየደረሰ ያለው ከመሬት የማፈናቀል ሥራ ይቁም” የሚሉ ይገኙባቸዋል፡፡

ሰልፉ የተዘጋጀው በኦሮሞ ጥናቶች ማኅበር መሆኑ ታውቋል፡፡

ዝርዝሩን ሰልፎቹን የተከታተለውን የሶራ ሃለኬን ዘገባ ከያዘው የድምፅ ፋይል ይስሙ፡፡

ዐሥራ አንዱ የተነሡት በዝውውር ነው፤ ቀሪዎቹ ሦስቱ ከአስተዳዳር ሥራ ውጭ ተደርገዋል ከአስተዳደር ሥራ ውጭ ከተደረጉት ውስጥ የደ/ጽጌ ቅ/ዑራኤል እና የደ/ሰላም ቅ/እስጢፋኖስ አስተዳዳሪዎች ይገኙበታል የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት ሙስናና ብልሹ አሠራር የገነገነባቸውን፣ የካህናትና ምእመናን አቤቱታ የበረታባቸውን 14 አድባራት አስተዳዳሪዎችን የማዘዋወር፣ ከአስተዳዳሪነት ሓላፊነት የማራቅ እና በጡረታ የማግለል ውሳኔ ማሳለፉ ተገለጸ፡፡ የአስተዳዳሪዎች ዝውውር የተካሄደባቸው አድባራት፡- የገነተ ጽጌ ቅዱስ …

በወላይታ በመንግስት ተደራጅተው ዝርፊያ የሚፈፅሙት ታርጋ አለልባ ሞተር ሳይክለኞች፡፡ ‪#‎millionsofvoicesforfree‬ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎UDJ‬

ሐምሌ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ፖሊስ አባላት በአዲስ አበባና በአንዳንድ የክልል ከተሞች በብዛት መታየታቸውን ተከትሎ በከተሞች የሚታየው አለመረጋጋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄዱን ዘጋቢዎቻችን ገልጸዋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ትናንት ባወጣው መግለጫ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘወትር አርብ የሚደረገውን የጁመአ ስግደት አስታኮ የተቃውሞ ድምጹን የሚያሰማ ከሆነ እርምጃ እንደሚወስድ መዛቱ ይታወቃል። የፖሊስን መግለጫ ተከትሎ የድምጻችን ይሰማ …

ሐምሌ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቡሪሞዲያቶ ወረዳ አባ በርሀቤ ቀበሌ አቶ ሀሰን በረከት የተባሉ ነዋሪ የተገደሉት አንድ ሾፌር የቤት እንስሶቻቸውን መግደሉን ተከትሎ በተፈጠረ ውዝግብ መሀል ነው። አቶ ሀሰን ካሳ እንዲሰጣቸው ሹፌሩን በሚጠይቁበት ወቅት ጉዳዩን በትክክል ያልተረዱ የፌደራል ፖሊስ አባላት በግለሰቡ ላይ ተኩስ ከፍተው ገድለውታል። በቅርቡ በአፋር እና በፌደራል ፖሊሶች መካከል የተጀመረው ግጭት ለግለሰቡ …

ሐምሌ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ያለመከሰሰ መብታቸው በፓርላማ እንዳይነሳ ከተወሰነ በኋላ እንደገና ፓርላማው ውሳኔውን በማጠፍ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳውና ወዲያውኑ ባልታወቀ ሁኔታ ከአገር እንዲወጡ ተደርገው የነበሩት የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ቃሲም ፊጤ በትላንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር ዋሉ፡ የኦህዴድ አባልና የፓርላማ አባል የነበሩት አቶ ቃሲም ፊጤ ከመሬት …

27 ተፎካካሪዎችን ያወዳደረው የማሊው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፣ ባንድ ዙር እልባት ሊደረግለት ባለመቻሉ ነሐሴ 5 ቀን 2005 ዓ ም ፤ በ 2 ኛ ዙር ውድድር እንደሚደመደም ተነገረ። ያኔ የሚቀርቡት 2 ተወዳሪዎች ብቻ ሲሆኑ እነርሱም ፤ የቀድሞው ጠ/ሚንስትር

የዩናይትድ እስቴትስ ብሔራዊ የስለላ ድርጅት አባል የነበረውና ፤ ከ2 ወራት ገደማ በፊት ከድቶ፤ ምሥጢሮችን በማጋለጥ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመነጋገሪያ አጀንዳ ያስከፈተው ኤድዋርድ ስነውደን ፤ ትናንት ሩሲያ ውስጥ ለአንድ ዓመት ጊዜያዊ ተገን ማግኘቱ ፤

በአፍሪቃ በህፃናት ላይ የሚካሄድ ወሲባዊ ንግድ እንዲገታ ህብረተሰቡና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ተጠየቁ ። በቅርቡ አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደ ስብሰባ ላይ እንደተገለፀው በአፍሪቃ በሚሊዮች የሚቆጠሩ ወጣቶችና ህፃናት የወሲብ ንግድ ሰለባ ናቸው ።

ፖሊስ ከዚሁ መስጊድ ፣ ሶላት ከመጀመሩ በፊት አንድ ምዕመን ከሶላቱ በኋላ ደግሞ ወደ 15 የሚሆኑ ምዕመናን ጊዜያዊ ማረፊያ ቤት ማሰሩን ፣ በአካባቢው እስከነበረበት ጊዜ ድረስ መመልከቱን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ተናግሯል ።

ዜና ከወላይታ መንግስት አንድነት ፓርቲ ላይ የክስ ድራማ እያዘጋጀ መሆኑ ተደረሰበት መንግስት በወላይታ ሶዶ በአንድነት ፓርቲ ላይ የሀሰት ድራማ በመስራት ላይ ነው፡፡ መንግስት በመስጊድ ውስጥ በድብቅ ያሰራጨው ሙስሊሙን ህብረተሰብ ለአመፅ የሚቀሰቅስ በራሪ ወረቀት የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን አመራር የሆኑት ወ/ሮ ሀድያ መሀመድ እንዳሰራጩት በማስመሰልና የሀሰት ምስክሮችን በማጋጀት ስራ ተጠምዷል፡፡ ወ/ሮ ሀድያ መሀመድንም “በራሪ ወረቀቱን እንድበትን […]

ወያኔዎች በጣም እየከፉ ነው፡፡ ክፋታቸው ጠርዝ እየለቀቀ መጥቷል፡፡ ይሉኝታና ሀፍረት ወትሮውንም ወያኔዎች ጋ እንደሌለ የታወቀ ቢሆንም አሁን አሁን ግን በጣም የለየላቸው ጋጠ ወጦችና ኅሊናቢሶች እየሆኑ ነው፡፡ እነሱን በሰው ልጅነት ለመፈረጅ እንኳን በጭራሽ የማይሞከር የሚገርሙ ፍጡራን ናቸው፡፡ ይቅርታችሁንና ወያኔዎች ዞሮ የሚያይ አንገት ያልፈጠረባቸው ባልጩት ራስ መሆን አለባቸው፡፡ የሚሠሯቸውን የሕጻን አይሏቸው የዐዋቂ ሞኛሞኝ ሥራዎች ስታዩ ከዚህም በላይ […]

በባህርዳር ከተማ እሁድ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም. የሚደረገው የተቃውሞ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል በመላ ሀገሪቱ የጀመረውን ህዝባዊ ተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አባላቱ በከተማዋ በተሸከርካሪ መኪና እና ድምፅ ማጉያ በመታገዝ አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ ከድምፅ ቅስቀሳው ጎን ለጎን በከተማዋ ፖስተሮች የመለጠፍና በራሪ ወረቀቶችንም የመበተን […]

ሰበር ዜና፤ ከባህር ዳር፤ ከወላይታ፤ ከጅንካ እና ከመቀሌ ከተሞች‬ – ፍኖተ ነጻነት ባሕር ዳር፤ አንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ በባህር ዳር ከተማ ለሚያደርገው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ የመኪና ላይ ቅስቀሳ እንዳያካሂድ እየተከለከለ ነው፡፡ የኢህአዴግ ካድሬዎችም ለቅስቀሳ የወጣውን መኪና በመክበብ ሁከት ለመፍጠር እየሞከሩ ነው፡፡ ለቅስቀሳ የወጣውን መኪና በማገትም የሹፌሩን መንጃፍቃድ ነጥቀዋል፡፡ የከተማዋ ነዋሪዎች የካድሬዎቹን ክልከላ በመቃውም ከፀጥታ ሀይሎቹ […]

የቃሊቲ እንግልት፤ – ከግርማ ሠይፉ ማሩ ጎበዝ እንግዲህ እዚህ ሀገራችን ኢትዮጵያ ጉድ ሳይሰማ አይታደርም አይደል፡፡ ዛሬ ከአቤል አለማየሁ ጋር አንዱዓለም አራጌን እና ርዕዮት ዓለሙን እንጠይቅ ተባብለን ወደ ቃሊት ወረድን፡፡ ለዛሬው የነበረን ዕቅድ ሁለቱን ብቻ የማየት ነበር፡፡ ለዚህም እንዲሆን በቂ የሚባል ሰዓት ይዘን ልክ ከቀኑ አምሰት ሰዓት ላይ ቃሊት በር ደረሰን፡፡ በቅርቡ ቃሊት የሚገኙትን ወዳጆቻችን ለመጠየቅ […]

‹‹በድል ኮረብታ ላይ ወጥታችኋል፤ መምህራን ኮርተናል›› /ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ካሣ/ ‹‹የተቃወምነው ሰውን ሳይኾን ሥርዐቱን ነው›› /የደቀ መዛሙርቱ መማክርት አመራር/ የደቀ መዛሙርቱ ምረቃ ሐምሌ ፳፯ ቀን ይካሄዳል በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሐዲስ ኪዳን መምህር በኾኑት ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ካሣ አገላለጽ የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት ያሣመሯት የዛሬ ሐምሌ ፳፭ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ምሽት ለሚቀጥለው ትውልድ የተሰጠች …

ልዩነታችን ዉበታችን ነዉ ! የሚሊዮኖች ድምጽ በጂንካ – ግርማ ካሳ ሐምሌ 25 ቀን 2005 ዓ.ም የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መርህ ሥር፣ ታላቅ ሕዝባዊ ሰላማዊ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ መጀመሩ ይታወቃል። በደሴና በጎንደር በአሥር ሺሆች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን የሰላም፣ የመብት የእኩልነትና የነጻነት ጥያቄዎቻቸዉን አስምተዋል። በፊታችን እሁድ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም፣ የአንድነት ፓርቲ በአራት ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እየተዘጋጀ […]

በጦር ኃይሎች፣ ቤትል ጎጃም በረንዳና መሳለሚያ ከመስጊድ የወጡ ሙስሊሞች ታፍሰዋል፡፡ በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች በርከት ያሉ ፌደራል ፖሊሶች ይታያሉ፤ ከሌሊቱ 5 ፡00 ሰዓት ጀምሮ መኪናዎች ላይ ከባድ ፍተሻ እየተደረገባቸው ነው፡፡ የሙስሊሙን የመብት እንቅስቃሴ የሚመራው ድምፃችን ይሰማ የተባለው የሶሻል ሚዲያ ግሩፕ ከቤተመንግስት በቅርብ ርቀት በሚገኘው ተውፊቅ መስጊድ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ብሶቱን እንዲያሰማ ጥሪ ማስተላለፉ አይዘነጋም፡፡

ሐምሌ ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው በመጪው እሁድ በመቀሌ፣ ባህርዳር፣ ጅንካ እና አርባ ምንጭ የሚያደርገውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ የገዢው ፓርቲ ሰዎች ሰልፎችን ለማደናቀፍ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው። በመቀሌ የአንድነት አመራሮች መጉላላት የደረሰባቸው ሲሆን፣ በጅንካ ደግሞ አካባቢው የሽብርተኞች ጥቃት ኢላማ በመሆኑ ሰልፉን ማድረግ አይቻልም የሚል መመሪያ እስከ ማስተላለፍ ተደርሶ ነበር። የአንድነት አመራሮች ባሳዩት የአቋም …

ሐምሌ ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዚህ ሕግ መሠረት የሕዝብ ገንዘብ ዘርፈው ወደውጪ አገር ፈርጥጠዋል የሚባሉ ሰዎች ተጠያቂ ይሆናሉ ተብሎ ይገመታል ፡፡ የሚሻሻሉት ሕጎች የተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የስነስርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅ እንደገና ለማሻሻል የወጣውን ረቂቅ አዋጅ፣ የተሻሻለውን የስነምግባርና የጸረ ሙስና ኮምሽን ማቋቋሚያ አዋጅ እንደገና ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅ እና የሙስና ወንጀሎችን እንደገና ለመደንገግ …

ሐምሌ ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አሶሺየትድ ፕሬስ እንደዘገበው የተመድ ሠራተኞችን ጭኖ ወደ ደቡብ ሱዳን ሲጓዝ የነበረው ሄሊኮፕተር በመከስከሱ በርካታ የተመድ ወራተኞች ጉዳት ደርሶባቸዋል። የ ኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በበኩላቸው አደጋው መድረሱን በማረጋገጥ የጉዳቱ ዝርዝር መጠን እንዳልደረሳቸው ተናግረዋል። የመንግስታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ ፈረሀን ሀቅ-ሄሊኮፕተሩ  የተባበሩት መንግስታት የምግብ ፕሮግራም በጆንገሊ …

ሐምሌ ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2005 የክዋኔ ኦዲት ግኝቶች ሪፖርት የህዝብና የመንግስት ሃብት አጠቃቀም አሳሳቢ የሆነ ክፍተት እንዳለባቸው ተጠቅሷል፡፡ መስሪያ ቤቱ  በመጠናቀቅ ላይ ባለው አመት በኢንዱስትሪ ከተማ ልማት ቢሮ ፤ በገጠር መንገዶች ባለስልጣን ፤ በጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጅንሲ ፤በባህል እና ቱሪዝም ና ፓርኮች ልማት ቢሮ …

የግብፅ ጦር የሰየመዉ ጊዚያ መንግሥት ግን ጥሪ ማሳሰቢያዉን የተቀበለዉ አይመስልም።የጊዚያዊ መንግሥቱ ካቢኔ መፈንቅለ መንግሥቱን በመቃወም በሁለት አደባባዮች የከተመዉን ሕዝብ «ለሐገሪቱ ፀጥታ አስጊ» እና «አሸባሪ» በማለት ወንጅሎታል።ፖሊስ ሕዝቡን ከሁለቱም አደባባዮች እንዲያባርርም አዟል።

ኢትዮጵያ የኤርትራን መንግስት ወደሰላማዊ የድርድር መድረክ ለማቅረብ 250 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል በነጻ ለመስጠት አስባለች መባሉንየሚጠቁም ዜና በድረገጾች እየተነበበ ነዉ።

የዛኑ ፒኤፍ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ምርጫውን አሸንፈናል ፣ ተቀናቃኛችን የዲሞክራሲያዊ ለውጦች ንቅናቄ MDC አልቋለታል ተቀብሯል እያሉ ነው ። ስማቸውን ያልጠቀሱ አንድ ነፃ የዚምባብዌ የምርጫ ታዛቢም የድምፅ ቆጠራ የመጀመሪያው ውጤት ለቻንጋራይ ታላቅ ውድቀት እንደሚመስል ለሮይተርስ አታውቀዋል ።

የረመዳን የጾም ወር ተጋምሶ ፍችዉ የኢድ አልፈጥር በዓል እየተቃረበ ነዉ። በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች በቀን ወደ 18 ሰዓት ያህል ይጾማሉ። በዕለቱ ዝግጅታችን በቦን ከተማ አቅራብያ በምትገኘዉ በብሩል ከተማ የሚኖሩ አንድ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ቤተሰብ ቤት ጎራ ብለን የእፈጠር ምሽትን አብረን አሰልፈን ልናካፍላችሁ ይዘናል፤

ሰበር ዜና ከመቀሌ – የአንድነት ከፍተኛ አመራር እና የፓርቲው አባል ታሰሩ መቀሌ ውስጥ አንድ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ እንግዳ ተክለፃዲቅ እና በዚህ ሳምንት “መቀሌን በ24 ሰዓት ለቀህ ውጣ” ተብሎ የነበረው የአንድነት ፓርቲ አባል አቶ የማነህ አበራ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በፖሊስ በህገወጥ መንገድ ታስረዋል፡፡ ‪#‎millionsofvoicesforfreedom‬ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎UDJ‬

ከሁሉ አስቀድመን ፣ በየመልኩ በዉጭ ለምንኖር ኢትዮጵያዉያን፣ ባህላችንን፣ ታሪካችንን ችግሮቻችንና የአገራችንን እሴቶ፣ በየወቅቱ በመከታተል፣ ግንዛቤ እንድናገኝ ለምታደርጉት ጥረት፣ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን። ዛሬ አገራችን አጣብቂኝ ሁኔታ ዉስጥ እንዳለች፣ የሁላችንም ግንዛቤ ነዉ። ከሁሉም በላይ፣ እንደ ማንኛዉም አገር ሕዝብ፣ የሃይማኖት የብሄረሰብ የቋንቋ ልዩነቶች ቢኖሩም፣ የእኛ የኢትዮጵያዉያን ልዩ እሴት፣ ልዩነቶቻችንን አቻችለን፣ በፍቅርና በሰላም መኖራችንና መቻቻላችን ቀዳሚነቱን ስፍራ የሚይዝ […]

መግቢያ፡- (ከ18 ዓመት ዕድሜ በታች የሆነ ሰው እንዲያነብ የማይመከር) የሰው ልጆች በሃይማኖት መከፋፈላቸውን አምርሬ ብቃወምም፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሃይማኖቶች የውሸትና ለብዝበዛም የተፈጠሩ መሆናቸውን ባምንም፣ እጅግ ብዙዎቹ ሃይማኖቶች ሰይጣን የተጣባቸው ወይም የሰይጣናዊነት መንፈስና አሠራር በጉልህ የሚታይባቸው መሆናቸውን ብረዳም በትውልድና በገዛ ፈቃዴ ይዤው ያለሁት ሃይማኖት ክርስትና ነው፡፡ ክርስትና በራሱ በመቶዎችና ከዚያም በላይ የተከፋፈለ መሆኑንም አውቃለሁ – አንዳቸው ለአንዳቸው […]

የጅንካ ወጣቶች ታሪክ እየሰሩ ነው፡፡ አንድነት ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ በንቃት ለመሳተፍ ከመንቀሳቀሳቸውም በላይ በጅንካና በአካባቢዋ በራሳቸው ተነሳሽነት ቅስቀሳ እያከናወኑ ነው፡፡ በተያያዘ ዜና የደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሞሎካ ውብነህ በ22/11/2005 ዓ.ም በቁጥር 417/107/05 በፃፉት ደብዳቤ ለአንድነት አመራሮች የእንወያይ ጥሪ አድርገው ከ14 የሀገር ሽማግሌዎችና ከጅንካ ከተማ ከንቲባና የተለያዩ የከተማው ባለስልጣናት ጋር በመሆን አንድነት ሰላማዊ ሰልፉን […]

የኢህአዴግ መንግስት በኢቲቪ በኩል ስለ ‘ሽብር’ና የ‘ፀረሽብር ሕግ’ አስፈላጊነት ያወራል። አንዳንድ ተቃዋሚዎች ደግሞ ስለ ‘ፀረሽብር’ ሕጉ ኢ-ሕጋዊነት ይሰብካሉ። እኔም የፀረሽብር ሕጉ ከማይደግፉ ሰዎች ጋር እንደምሰለፍ ካሳወቅኩ ከጥቂት ግዜ በኋላ አንድ የምወደው የህወሓት አባል የሆነ ጓደኛዬ እንዲህ ሲል በውስጥ መልእክት ላከብኝ፣ “ፀረሽብር ሕግ መቃወም ኮ ሽብርን መደገፍ ነው። አንዳንድ አክራሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ ስም ሽብርተኝነትን ማስፋፋት ይፈልጋሉ። […]

ከምሽቱ አራት ሰዓት ተኩል ላይ ወደ አውሮፕላኑ እንድንገባ ተጋበዝን፡፡ በቀኜም በግራዬም ከፊቴም ከኋላዬም የተቀመጡት የእስያ ዝርያ ያላቸው ተጓዦች ናቸው፡፡ እንዲህ ኤስያውያን በሞሉበት አውሮፕላን ስሄድ የመጀመሪያዬ ነው፡፡ አስተናጋጆቹ ከዚህ በኋላ ወደ ቀጣዩ መዳረሻችን ለመድረስ የስምንት ሰዓት ከሩብ ጎዳና ይቀረናል አሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ ሌላ አውሮፕላን እንይዛለን፡፡ ድሮ ሦስተኛ ክፍል ስንማር ‹ንብ አበባ ለመቅሰም የምታደርገውን ጉዞ በአንድ መሥመር ብታደርገው ኖሮ፣ ዓለምን ትዞር ነበር› የሚል ነገር ተምሬ ነበር፡፡ አሁንም የኔ ነገር እንደዚያ ሳይሆን አይቀርም፡፡

‹ይህ ነው ምኞቴ እኔ ለሕይወቴ› የሚል የቆየ የማርሽ መዝሙር  ትዝ አለኝ፡፡ እዚያ መዝሙር ውስጥ ደግሞ

ረዥሙን ጉዞ ትግሉን ዐውቄ

ተነሥቻለሁ ትጥቄን አጥብቄ

የሚል ነገር ነበረው፡፡ ምን ይደረግ ሰው ከሀገሩ ሲወጣ ትዝታ ነው የሚተርፈው፡፡ ከወሎ መቄት ወደ አዲስ አበባ መጥተው የኖሩት አለቃ ለማ ኃይሉ አይደሉ እንዴ ቢቸግራቸው ‹‹እግር አዲስ አበባ ልቡና መቄት›› ያሉት፡፡ አንዳንድ ጊዜ ‹ሀገር ማለት ምንድን ናት?›› ያሰኛል፡፡ በሀገራችን ተሰቃየን፣ ታሠርን፣ ተንገላታን፣ ግፍ ተፈጸመብን ብለው ከሀገር የሚወጡ ወገኖቻችን እንኳን መልሰው ‹ሀገሬ› ሲሉ ሳያቸው ይህቺ ሀገር የምትባል ‹መንፈስ› ምንድን ናት? እላለሁ፡፡ አንድ ጊዜ ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ አዲስ አበባ ስመጣ ከጎኔ አንድ በጎልማሳነት እድሜ ላይ የደረሰ ኢትዮጵያዊ ወገን ተቀምጦ ነበር፡፡ አውሮፕላኑ ሲነሣ እጁ ይንቀጠቀጣል፡፡ ያመመው መሰለኝና ዘወር ብዬ ‹‹አመመህ›› ስል ጠየቅኩት፡፡ ግንባሩን በመሐረብ እየጠረገ ‹‹ደኅና ነኝ፣ ምንም አልል›› አለኝ በእንግልጣር፡፡ አሁንም እጁ ይንቀጠቀጣልና ዘወር አልኩ፡፡

‹‹ይገርምሃል ከሀገሬ ከወጣሁ ሠላሳ ዓመቴ ነው፡፡ ወደ ሀገር ለመሄድ ሳስብ ሁልጊዜ ሰውነቴ ይንቀጠቀጣል፡፡ አንዳች ነገር መጥቶ ይወርረኛል፡፡ ልቤ ምቱ ይጨምራል፡፡ አሁንማ አውሮፕላን ውስጥ ስገባ ባሰብኝ፡፡ ውስጤ ብርድ ብርድ ይለኛል፤ እንደገና ይሞቀኛል፡፡ ምን እንደሆነ ማወቅ አልቻልኩም›› አለኝ፡፡ እያየሁት እገረም ነበር፡፡ ከሕይወቱ አብዛኛውን፤ ያውም ነፍስ ያወቀበትን ዘመን ያሳለፈው አሜሪካ ነው፡፡ ግን ‹ኢትዮጵያ› የሚለውን ሲያስበው አንዳች ስሜት፣ እርሱም የማይገባው ስሜት ይወርረዋል፡፡ ‹‹ሀገር ምንድን ነው?››

ደግነቱ አንድ ወዳጄ ‹‹ዜጋን ከሀገሩ ማስውጣት ቀላል ነው፤ ሀገርን ከዜጋው ልብ ማስውጣት ግን አይቻልም›› ብሎኝ ነበር፡፡ እኛ ልብ ውስጥ ልዩ የሆነች ሀገር አለች፡፡ ማንም የማይነካት፣ ማንም የማይወስዳት፣ ማንም የማያጠፋት፡፡ አለቃ ለማ ‹ልቡና መቄት› ያሉትኮ መቄት ከልባቸው አልወጣ ብላቸው ነው፡፡

ይህንን ሁሉ እያሰብኩ አውሮፕላኑ ተነሥቶ ወደ ሕንድ ውቅያኖስ አቅጣጫ ማምራት ጀመረ፡፡ እኔም የሕይወት ተፈራን Tower In The Sky አውጥቼ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ ያ ትውልድ አሁንም አብሮኝ ሕንድ ውቅያኖስን ሰንጥቆ ሊጓዝ ነው፡፡ ዓላማ፣ ትጋት፣ ቆራጥነት፣ መሥዋዕትነት፣ ጽንዓት የነበረው አንድ ትውልድ ጠፍቷል፡፡

በማርክሲስት ሌኒኒስት ቀንበር ተቀይዶ፣ የሁሉንም ነገር መፍትሔ ከመጻሕፍት ውስጥ ሲያስስ፣ እርስ በርስ ተከራክሮና ተወያይቶ በመተማመን ወይም ባለመተማመን መፍታት ሲቻል፤ ተምሮ እንዳልተማረ፣ ዐውቆ እንዳላወቀ ሲጨራረስ ማየት አሳዛኝ ነው፡፡ ሁሉንም ነገር በሳጥን ውስጥ ብቻ ለመመልከት የሚተጋ ትውልድ የ‹ኢስት› ብዛት፡- ማርክሲስት፣ ማኦኢስት፣ ቾቭኒስት፣ ፌሚኒስት፣ ካፒታሊስት፣ አናርኪስት፣ ፋሺስት፣ ትሮትስኪስት፣ ኮሙኒስት፣›› የ‹ኢዝም› መዓት፡፡ ሁሉንም ሃሳቦች፣ ሁሉንም አመለካከቶች በሳጥኖች ብቻ አድርጎ የመመልከት አባዜ፡፡ ማርክስ፣ ሌኒንና ኤንግልስ የሚባሉ ሐዋርያት ያመጡት አዲስ ሃይማኖት፤ ቦልሼቪስት፣ ማኦኢስት፣ ማርክሲስት የሚባሉ ምእመናን፤ አናርኪስት፣ ትሮትስኪስት፣ የሚባሉ መናፍቃን፤ ኢምፔሪያሊስት፣ ፊውዳልና ቡርዧ የሚባሉ አጋንንት፣ ተፈጥረው አማኝና ከሃዲ ሲወጋገዙና ሲጫረሱ የኖሩባቸው ዘመናት፡፡

መጽሐፉ እያሳዘናችሁ እያስገረማችሁ፣ እያበሳጫችሁም ይጓዛል፡፡ የአንድ ፓርቲ ሰዎች ትናንትም ይከፋፈላሉ፤ ዛሬም እንዲሁ፤ ተከፋፍለውም ይወጋገዛሉ፤ ዛሬም እንዲሁ፤ ተወጋግዘውም ይገዳደላሉ፤ ዛሬም እንዲሁ፤ ለአብዮቱ ሲባል፤ ለትግሉ ሲባል፤ አድኅሮት ኃይላትን ለማስወገድ ሲባል በጓዶች ላይ ርምጃ ይወሰዳል፡፡ ድመት ይመስል አብዮት ልጆቿን ትበላለች፡፡ እስካን አይጥ ለማጥመጃ ስንት መሣሪያ ሲሠራ፤ ምነው ይህቺን ልጆቿን የምትፈጅ ‹የአብዮት ድመት› ማጥፊያ መድኃኒት ጠፋ?

የዚያ ዘመን ሰዎቹ ዐልፈዋል፤ ሥርዓቱ ዐልፏል፤ ታሪኩ ዐልፏል፤ መንፈሱ ግን አለ፡፡ ‹‹ግደል ተጋደል በርታ ወገኔ›› የሚለው ዛር ግን አለ፡፡ ፖለቲካዊ ጽንፈኛነት፤ ደጋፊነትና ጠላትነት፤ ሥር ነቀልነትና ደምሳሽነት አሁንም አሉ፡፡ ይህንን መንፈስ የሚያጠፋ ትምህርት፤ የሚደመስስ ጸሎት፤ የሚያስቀር ሥርየት አልተገኘም፡፡

መጽሐፉን እንዲህ እያነበብኩ እያለ አስተናጋጆቹ ምግብ ይዘው በጎናችን መጡ፡፡ ከጎኔ ላለው ሰውዬ የሰጠችው ምግብ ስሙን የጠራችው በቻይንኛ ሳይሆን አይቀርም፡፡ የነዚህ የእስያውያን ነገርኮ ምን እንደሚበሉና ምን እንደማይበሉ አይታወቅም፡፡ ቢጨንቀኝ ዓሣ አዘዝኩ፡፡ የመጣውን ነገር አልነግራችሁም፡፡ ምናልባት ምግብ ላይ ትሆናላችሁና ይቅር፡፡ አንድ ወዳጄ ‹‹እነዚህ ሰዎችኮ ሰውን ባሕር ውስጥ ቢያገኙት ዓሣ ነው የሚሉት›› ያለኝ ትዝ አለኝ፡፡ እንኳን ልበላው ኢትዮጵያ የበላሁትም ምግብ ሆዴ ውስጥ ሆኖ እንደ ኤርታሌ ይተራመስ ጀመር፡፡

ከድኜ ተውኩትና መጽሐፉን ቀጠልኩ፡፡ አይ ሕይወት እግዜር ይይልሽ፡፡ ልደታ ብስኩት ቤት፣ ፒያሳ ጮርናቄ ቤት፣ ሐረር ምግብ ቤት፣ ምናምን ክትፎ ቤት እያለች የአዲስ አበባን ምግብ ቤቶችና ሻሂ ቤቶች ትዘረዝራለች፡፡ ይህም አልበቃ ብሏት በመቀሌ መንገድ ላይ ‹‹ምን የመሰለ ዱለት በላሁ›› ትላለች፡፡ እኔ እዚህ በአንድ በኩል የሚዘጋ ምግብ ከፊቴ ተቀምጦ ይተናነቀኛል፤ በሌላ በኩል ደግሞ የሀገሬን ምግብ ቤትና ምግብ እያነበብኩ ረሃቤ ይቀሰቀስብኛል፡፡ ተርቦ ስለ ረሃብ ማንበብን የመሰለ ቅጣት መቼም የለም፡፡

ዘሚካኤል ትዝ አለኝ፡፡ ዘሚካኤል ኤርትራዊ ነው፡፡ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ከዐሥራ ሁለት ዓመታት በፊት ባዘጋጀው አንድ ሴሚናር ላይ ለመሳተፍ ተጋብዘን ኡጋንዳ ኢንሴንዜ የምትባል መንደር ተገናኝተን ነበር፡፡ እዚያ ከአሥራ ስድስት የአፍሪካ ሀገሮች የመጡ ወጣቶች ነበሩ፡፡ ከሁሉም የእኔና የዘሚካኤል የምግብ ምርጫ ነበር የሚገርማቸው፡፡ ከምንበላው የማንበላው ይበልጣል፡፡ አንደ ቀን ሴሚናር ላይ ውለን አምሽተን ተመለስን፡፡ እኔ ቀደም ብዬ ጨለም ወዳለው የማምሻችን ቦታ መጣሁ፡፡ እሳት ነድዶ ጨዋታው ቀልጧል፡፡ ዘሚካኤል መታጠቢያ ቤት ገብቶ ዘገየ፡፡ ስደርስ የሆነ ነገር ሸተተኝ፡፡ አሻግሬ ሳይ ጠረጲዛው ላይ ያለውን ነገር ይሻሙበታል፡፡ በጨለማው ውስጥ ያለው የእሳት ብርሃን ብቻ ስለነበር ልለየው አልቻልኩም፡፡ ራቅ ብዬ ተቀመጥኩ፡፡

ዘሚካኤል መጣና ጠረጲዛ ላይ ያለውን ነገር አየው፡፤ ‹‹ዘቢብ ሳይሆን አይቀርም›› አለኝ፡፡

‹‹አይ እኔ ይቅርብኝ አንተ ሞክረው›› አልኩት፡፡

‹‹ዘቢብ መሆን አለበት፤ መልኩ እንደዚያ ነው›› አለና ሊያመጣ ሄደ፡፡ ልክ ጠረጲዛው ጋ ሲደርስ ‹‹ቧ፣ አተ›› አለና ፈጠን ፈጠን ብሎ ወደ ማደሪያው ገባ፡፡ ምን ሆነ ብዬ ደነገጥኩና ተከተልኩት፡፡ ባንኳኳ ባንኳኳ አልከፍትም አለ፤ በስንት መከራ ሳስከፍተው ፊቱ በውኃ ርሷል፡፡

‹‹ምን ሆነህ ነው?›› አልኩት

‹‹ጉድ ሠሩኝኮ›› አለኝ

‹‹ምን አደረጉህ››

‹‹ምን እንደሆነ ዐውቀሃል››

‹‹ምንድን ነው?››

‹‹የተጠበሰ ክረምት አግባ›› በሳቅ ፈረስኩ፡፡ ለካስ እንደ ዘቢብ አምሮ የታየው እኛ ክረምት አግባ የምንለውን ሰብስበው ቆልተውት ነው››

ዛሬ የደረሰብኝ በዘሚካኤል በሳቅኩት ግፍ ነው፡፡

ከዱባይ ወደ ብሩናይ መንገድ፣ ሕንድ ውቅያኖስ ላይ

ሐምሌ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዞኑ ነዋሪዎች ከመንግስት ጋር ምንም አይነት ትብብር እንደማያደርጉ መግለጻቸውን ተከትሎ፣ ከጠቅላይ ሚ/ሩ ጀምሮ ያሉ ባለስልጣናት ከቦረና ሽማግሌዎች ጋር ውይይት ቢያደርጉም ችግሩ አልተፈታም። ውዝግቡ የተጀመረው መንግስት ገሪ እየተባሉ የሚጠሩትን የሶማሊ ጎሳ አባላት በቦረና ዞን ለማስፈር እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ ነው። በቅርቡ የ50 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው ግጭት ከመከሰቱ በፊት መንግስት …

ሐምሌ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመቃብር ቦታ ጥያቄያችን አልተመለሰም ፤ ለመስጊዶቻችንን  የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር ተከልክለናል፡፣ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ፍትህ አጥቷል” በማለት ሙስሊሞች ተናግረዋል። የጎንደር ከተማ ኗሪ የሆኑት ሐጅ ሙርፉቅ ሙስሊሙ ከመንግስት ጋር ሆድና ጀርባ መሆኑን ገልጸዋል። በየቀኑ ደብዛቸው እየጠፋ በአፋልጉኝ የሚጠሩት ህዝበ ሙስሊሞች የመንግስት የአፈና ውጤት መሆናቸውን የተናገሩት የጎንደር ህዝበ ሙስሊሞች፤ያለምንም ፍትህ የሚያስረውና …

ሐምሌ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ዞንና ወረዳዎች በበጎ አድራጊዎች ድጋፍና በህብረተሰቡ የተገነቡ ከ110 በላይ  የውሃ ተቌማት ላይ የእጅ ፓምፕ ዝርፊያ በመፈጸሙ በውሀ አቅርቦቱ ላይ ችግር ተፈጥሯል። ዝርፊያውን ተከትሎ የወረዳ አመራሮች ለህዝቡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ናቸው እያሉ ፤ ፓርቲዎችን የማሰጠላት ዘመቻ እያከናወኑ ነው፡፡ በተለያዩ  አካባቢዎች እየተከሰተ ባለው የውሃ ተቋማት ዝርፊያ …

የዝምባብዌው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ በዛሬው ምርጫ የሚሸነፉ ከሆነ ሥልጣናቸውን እንደሚለቁ አስታወቁ። አያሌ ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆዩት ሙጋቤ፣ ተፎካካሪአቸውን ጠ/ሚንስትር ሞርጋን ቻንጊራይን ለማሸነፍ ሙሉ በሙሉ እንደሚተማመኑም ገልጸዋል። በሃራሬ

«ጨው ሲበዛ ያቅራል ፤ በርበሬ ሲበዛ ይመራል» ይባላል፣

ለሰውና እንስሳ ጠቀሚ ከሆኑ ማዕድናት መካከል አንዱ ጨው ነው፤ የዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት(WHO) እንደሚመክረው ከሆነ እያንዳንዱ ሰው በየቀኑ መጠኑ ፣ከ 5 ግራም የማይበልጥ ጨው መመገብ