ሄኖክ የሺጥላ
“አወይ ጉዴ ወይ መላ ጉዴ
ብቸኛው ልቤ ሰው በመውደዴ”

ነው ያለው አረጋሃኝ ወራሽ አሁን እንደሱ ልፋትና ጥረት ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ ሙዚቃ የት በደረሰ። ለነገሩ ይሄ ትውልድ የተሠራውን ሁሉ በመናድ፣ የተጣፈውን ሁሉ በመካድ ነው የሚታወቀው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Bedele Beers በደሌ ቢራክንፉ አሰፋ
በጋዜጠኛ ስህተት የወጣች አንዲት ጽሑፍ ምክንያት 18 ሺህ ፊርማ በኢንተርኔት መሰባሰቡን ሰማን። ጽሑፉን ያሳተመው መጽሔት ስህተቱን አረመ። ይቅርታም ጠየቀ። ዘመቻው ግን እንደቀጠለ ነው። ቴዲ አፍሮ ይንን እንዳልተናገረ መግለጫ ቢሰጥም ጉዳዩ እልባት ሊያገኝ አልቻለም። ከቶውንም አንድነታችንን የማይፈልጉ ምዕራባውያን ጭምር ይህችን ምክንያት በመያዝ ጉዳዩን ማራገብ ጀመሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ታህሳስ ፳፬( ሃያ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመከላከያ ውስጥ የሚገኙ ወታደራዊ አዛዦች ለኢሳት እንደገለጹት የህወሀት ባለስልጣናት ጄኔራል ሳሞራ የኑስን ለመተካት የተሻለ ቦታ ላይ የነበሩትን ጄ/ል አበባው ታደሰን አድማ ለማድረግ አስበዋል በሚል ሰበብ ማእረጋቸውን እንደያዙ የሚሰጣቸው ሃላፊነት እንዲቀነስና ከውድድር ውጭ እንዲሆኑ አድርገዋል። ለዚህም ስራ ጄኔራል ማሞ ሀይለማርያም እና ጄኔራል ሰሐረ መኮንን ተባባሪ መሆናቸውን ገልጸዋል። …

ታህሳስ ፳፬( ሃያ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴሬሽን ምክርቤት ላለፉት 18 ዓመታት በስራ ላይ የነበረውና የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ ታምራት ላይኔን ጨምሮ የተለያዩ ባለስልጣናት ጉዳያቸው የታየበት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 8  ተራ ቁጥር 1 እና የተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 7 ተራቁጥር 1 ሕገመንግስቱን እንደሚጥሱ …

ታህሳስ ፳፬( ሃያ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ አፍሪካ በስደት ላይ የሚገኙት የሩዋንዳ የደህንነት ዋና አዛዥ የነበሩት ፓትሪክ ካሪጋያ የተገደሉት ጆሀንስበርግ  በሚገኝ ሆቴል ውስጥ ነው። የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ እንዳለው የሩዋንዳ መንግስት ተቃዋሚ የሆኑት ካሪጋያ የተገደሉት በገመድ ታንቀው ሳይሆን አይቀርም። የ53 አመቱ ሚ/ር ካሪጋያ ላለፉት 6 አመታት  በደቡብ አፍሪካ ውስጥ በስደተኝነት ቆይተዋል። ኮሎኔል ካሪጋያ ከፕሬዚዳንት …

Boy Scout ቦይ ስካውትአበራ ለማ
“አስካውት! …”
“ምን ጊዜም ዝግጁ!!!”
ዱሮ ዱሮና በኛም ዘመን የቦይ ስካውት ክለብ (Boy Scout) እንቅስቃሴ ሞቅና ደመቅ ያለ ነበር። ሰላሌ ፍቼ፣ የአበራና አስፋው ወሰን የ1ኛ ደረጃና ወሊሶ የደጃዘማች ገረሱ ዱኪ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ እያለሁ (ከ1953-1960 ዓ.ም.) የቦይ ስካውት ክለብ አባል ነበርኩ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ደቡብ ሱዳን ውስጥ የተቀሰቀሰው ግጭት መላውን ዓለም አሳስቧል ማለት ይቻላል።

ደም አፋሳሽ የሆኑትን ግጭቶች ለማስቆም የታቀደውና በምሥራቅ አፍሪካው የጋራ ልማት ተቋም – ኢጋድ የተዘጋጀው የሰላም ንግግር የመጀመሪያው ዙር ውይይት በሸራተን አዲስ ነገ እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡

የደቡብ ሱዳንን ሁኔታ እንዲገመግሙ ዶክተር ሰሎሞን መብሪን ጋብዘናል፡፡

ዶ/ር ሰሎሞን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስና ዓለምአቀፍ ትምህርት ክፍል መምህር ናቸው። እስክንድር ፍሬው ነው ያነጋገራቸው።

ለሙሉው ውይይት የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Image
“ፓርቲው ወደ ፊት ተራመደ ወይስ ወደኋላ” – በተቃዋሚ ፓርቲዎች ካምፕ የአመራር ንጥፈት ማሳያ
“የፖለቲካ ኃይሌ ተሟጦ አልቋል” በማለት ከፖለቲካው መድረክ የተገለሉት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ውስብስቡን የውህደት ማመልከቻ የመመርመር ታሪካዊ ኃላፊነት የወደቀባቸው ይመስላል። ኢንጂነር ግዛቸው የወጣቶች ሚና መጉላት እንዳለበት ደጋግመው ቢገልፁም፤ የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ ፓርቲው በእጃቸው ላይ እንዲወድቅ ሆኗል። ……የኢህአዴግ ፋሽን የሆነው “መተካካት” በተቃዋሚው ጎራ ውጤታማ እንዳልሆነም የሚገልፁ አልጠፉም። በተመሳሳይ መንገድ የእነ አቶ አዲሱ ለገሰን ወደ አመራር መመለስ በማየት በገዢውም ሆነ በተቃዋሚ ጎራ “መተካካት” ሳይሆን በስልጣን “መመላለስ” አድርገው የተገነዘቡም ይመስላል።የሀገሪቱን ፖለቲካ በትውልድ መነፅር የሚለኩ ወገኖች ዛሬም ቢሆን “የ60ዎቹ ትውልድ” የሀገሪቱን የፖለቲካና ኢኮኖሚ ተቆጣጥሯል የሚል ቅሬታ እየተደመጠ ነው። አንድነትም ቢሆን የወጣት አመራር በማጣቱና በመቸገሩ በኢንጂነር ግዛቸው ስር መጠለሉን እንደመረጠና አማራጭም እንዳጣ በመግለፅ በማሳያነት የሚያቀርቡ አሉ።
http://minilik-salsawi.blogspot.com/201 … -post.html

ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም Prof. Al-Mariamእ.ኤ.አ. የ2013 ዓመት የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው (ወጣቱ ትውልድ) መነሳሳት ሲገመገም
ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)

እ.ኤ.አ በጃንዋሪ 2013 “እ.ኤ.አ 2013 የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው ትውልድ ዓመት ይሆናል” በማለት ትንበያ ሰጥቸ ነበር። እንዲህ ስልም ቃል ገብቸ ነበር፣ “የኢትዮጵያ ወጣቶች ለፍትህና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚያደርጉትን ትግል ለመደገፍ እና ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ እንዲል የእራሴን ሙሉ አስተዋጽኦ እንደማደርግ እንዲሁም ትግሉ ወደ አዲስ ምዕራፍ እንዲሸጋገር ወጣቱ ትውልድ እንዲነሳሳ ሳደፋፍር ነበር።”

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሶማሊያ መዲና መቅዲሾ በሚገኝ አንድ ሆቴል አጠገብ ትናንት ምሽት በተከታታይ በደረሱ የቦምብ ፍንዳታዎች የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 13 ከፍ ማለቱ ተዘግቧል ። ከሟቾቹ መካከል ፖሊሶችም ይገኙበታል ። የሶማሊያው ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አሸባብ ለጥቃቱ ሃላፊነቱን ወስዷል ።

የሳዉዲ መንግስት የሰጠዉ የምህረት አዋጅ የጊዜ ገደብ ካለቀ በኋላ በሪያድ መንፉአ በኢትዮጵያዉያን ላይ የሞትና የመቁሰል አደጋ ከደረሰ ወዲህ ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸዉም ሆነ ካመጣቸዉ አሠሪ ጋ የማይሠሩ ማናቸዉም ዜጎች እንደህገወጥ እንደሚቆጠሩ በማሳሰብ፤

የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ወገኖች ተደራዳሪዎች ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ የሰላም ንግግር ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል ። አደራዳሪዎቹና ተደራዳሪዎቹ ግን ድርድር የሚጀምሩበትን ትክክለኛ ቀን እስካሁን በይፋ አላሳወቁም ።

የጎርጎሪዮሳዊውን የቀን ቀመር ለሚያሰሉ አዲስ ዓመት ማለትም 2014 ከጠባ ዛሬ ማግስቱ ነው። የአዲስ ዓመት በዓል ዋዜማ አቀባበልን በአውሮጳ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን እንዴት ይመለከቱታል? ከዝግጅቱ የምናገኘው ይሆናል።


“ሲፒጄ የሃገራችንን ስም ለማጥፋት ስለሚፈልግ ነው እንጂ፣ በጻፈው ጽሑፍ የታሰረ አንድም ጋዜጠኛ የለም፡፡ 3 ጋዜጠኞች የታሠሩት አሸባሪ ተብለው ነው” ~ አቶ አንተነህ አብርሃም (የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጋዜጠኞች ኅብረት /ኢብጋኅ/ ፕሬዚደንት)
“[ሲፒጄ] ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር ሁለተኛ ናት ብሏል፡፡ ይሄ ከዚህ በፊትም ሆኖ የማያውቅ ግነት ነው፡፡ የታሰረ የለም።” ~ አቶ ወንደወሰን መኮንን (የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ማኅበር /ኢነጋማ/ ሊቀመንበር)
“በጻፈው ተፈርዶበት የታሰረ አለ ከተባለ ዶክመንቶችን ማገላበጥ ያስፈልጋል፡፡ ማንም ደግሞ አልታሰረም። ይህ አልሆነም፡፡ ከምላሴ ላይ ፀጉር ይነቀላል፡፡” ~ አቶ ሽመልስ ከማል (የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ)
ከላይ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ከወጣ ቃላቸው ቀንጭቤ ያስነበብኳችሁ አስተያየቶች ውስጥ ምንም ዓይነት መሠረታዊ ልዩነት የለም፡፡ ነገር ግን አንዱ በመንግሥት ባለሥልጣን እና የቀደሙት ሁለቱ ደግሞ የጋዜጠኞችን ጥቅም ለማስጠበቅ በጋዜጠኞች ስም ከተመሠረቱ ማኅበራት ኃላፊዎች የተደመጡ ንግግሮች ናቸው፡፡
በኢትዮጵያ ስምንት የጋዜጠኞች ማኅበራት ሲኖሩ ሦስቱ እንደአካባቢና ጤና ባሉ የተለዩ ጉዳዮች ላይ ብቻ አተኩረው የሚሠሩ ሲሆን ቀሪዎቹ የተለያዩ ጋዜጠኞችን እንወክላለን በሚል የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ ሆኖም በአብዛኛው ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጋር ጋብቻ በመፈፀም የመንግሥትን (የገዢውን ፓርቲ) ጥቅም በማስጠበቅ ሥራ ላይ ተሰማርተው እናገኛቸዋለን፡፡ በመሀከላቸው ፉክክር ቢኖር እንኳን ለማኅበራቱ መሪዎች ጥቅም እንጂ በጋዜጠኞች ጥቅም ላይ የተመሠረተ አይደለም፡፡ ማኅበራቱ አንዳንዶቹ የአሳታሚ ድርጅቶች ባለቤቶች በመሆናቸው መንግሥት ድርጅታቸውን እንዳይጣላባቸው ሲሉ ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰውን በደል በሙሉ አፍ ማጋለጥ አይደፍሩም፡፡ ሌሎቹ አሉን የሚሏቸው አባላት ቢኖሯቸው እንኳን የማኅበሩ አባላት የሚያገኙት ጥቅም የላቸውም፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ጭራሹኑ እራሳቸው ለጋዜጠኞቹ ደኅንነት አደጋ ናቸው፡፡

የአንጋፋው ኢጋማ /ኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማኅበር ፕሬዚደንት/ አቶ መሠረት አታላይ ለምሳሌ‹የሚሚ ጠረጴዛ› በመባል በሚታወቀውና የኢሕአዴግ ደጋፊ ጋዜጠኞች ብቻ በሚሰየሙበት በዛሚ ኤፍ ኤም 90.7 ላይ በሚቀርበው ‹‹የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ›› የውይይት መድረክ ላይ በተደጋጋሚ ይቀርባሉ፡፡ ‹‹ክብ ጠረጴዛው›› በብዛት በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር እና ‹እነእከሌ ይታሰሩ› የሚል ብያኔ የሚበዛበት ሲሆን፣ የጋዜጠኞች ጉዳይ ሲነሳም ተመሳሳይ ዝንባሌዎች የሚታይበት ነው፡፡ ባጭሩ አቶ መሠረት አታላይ ከሚሚ ስብሃቱ ጋር በመሆን መታሰር ስላለባቸው ጋዜጠኞች ከመወያየት በቀር ለጋዜጠኞች ወገንተኝት ያሳዩበት አጋጣሚ የለም፡፡
የኢብጋኅ ፕሬዘዳንቱን – አቶ አንተነህን ከዚህ በፊት አግኝቻቸው የነበረ ሲሆን በነበረን ጫወታ የታዘብኩት ሦስት ነገሮች፤ አንድ – ማኅበሩን እንደግል የቢዝነስ ድርጅታቸው እንደሚቆጥሩት፣ ሁለት – ራሳቸውን ከኢሕአዴግ አባል ለይተው እንደማያዩ እና ሦስት – የብስለት ደረጃቸው አዋቂነት ላይ ያልደረሰ እንዲያውም የልጃልጅ ዓይነት መሆኑን ናቸው፡፡ በነገራችን ላይ ሦስተኛውን ነጥብ የቀድሞው የኅብረቱ ፕሬዚደንት የነበሩትና በአሁኑ ወቅት በስደት የሚገኙት ጋዜጠኛ ደረጄ ሀብተወልድ ‹የአመራር አባላቱን ብስለትም እጠራጠረዋለሁ› በማለት ነበር የገለጹልኝ፡፡
አንደኛውን ነጥቤን ለመደገፍ ያክል፣ አቶ አንተነህ ለምሳሌ ከአቶ አላሙዲ (ወይም ከድርጅቶቻቸው) ኅብረቱ የተለገሰውን አንድ ሚሊዮን ብር አስመልክተው ሲናገሩ ‹‹አላሙዲ አንድ ሚሊዮን ብር ሰጠኝ›› ብለው ነው፡፡ ሼክ አላሙዲ (ወይም ድርጅቶቻቸው) ለአቶ አንተነህ የጋዜጠኞች ኅብረት የሰጡት አንድ ሚሊዮን ብር አዋዋሉ የሼኩን ድርጅቶች የሚያጥላሉ ጽሑፎችን ብቻ የሚጽፈው ጋዜጣ – ሪፖርተር – ባለቤት  አቶ አማረ አረጋዊ የሚመራውን ‹ሀፒ› የተሰኘ ማኅበር እንዲቀናቀን ነው፡፡ በእርግጥም ኅብረቱ ተልዕኮውን በመወጣት አባል የሆነበት የዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ፍዴሬሽኑ (IFJ) አባላት በኢትዮጵያ ጉብኝት ሲያደርጉ አቶ አንተነህ የሚድሮክን ድርጅቶች በማስጎብኘት ስለጋዜጠኞች ሳያወሯቸው መለሷቸው፡፡  በነገራችን ላይ አቶ አንተነህ በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች ታሪክ መርሴዲስ የሚነዱ ብቸኛው ሀብታም ‹‹ጋዜጠኛ›› ናቸው፡፡
አቶ አንተነህ ራሳቸውን ከኢሕአዴግ ለይተው አያዩም እንድል ያሰኘኝ ደግሞ በታሰሩ ጋዜጠኞች እና በኢትዮጵያ ባለው የሚዲያ አያያዝ ላይ የሚሰጡት አስተያየት ነው፡፡ እንደእርሳቸው አስተያየት፣ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የሥነ ምግባር ጉድለት ያለባቸው እና ያለመንግሥት ቁጥጥር መረን የሚወጡ ሰዎች ናቸው፡፡ ይህ አስተሳሰባቸው የጋዜጠኞች ኅብረት ፕሬዚደንት ሳይሆን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ኃላፊ ያስመስላቸዋል፡፡
አቶ አንተነህ አብርሃም የምስራቅ አፍሪካ ጋዜጠኞች ማኅበራትም ምክትል ፐሬዘዳንት ናቸው፡፡ ይህ የምስራቅ አፍሪካ ጋዜጠኞች ማኅበር የሚባለውም ከእርሳቸው የኢትዮጵያ ማኅበር የተሻለ ነው ለማለት የሚያስደፍር ነገር አላገኘሁበትም፡፡ የማኅበሩ ፕሬዚደንት ሶማልያዊው ኦማር ፋሩክ በሲቪል ማኅበረሰቡ ዘንድ በተለያዩ ማጭበርበሮች ይታማሉ፤ ሌላው ቀርቶ ዘንድሮ በአዲስ አበባ የተካሄደውን የአፍሪካ ጋዜጠኞች መድረክን ለመታደም በተጭበረበረ ፓስፖርት ወደአዲስ አበባ ሲገቡ ተይዘው ታስረው እንደነበር አውቃለሁ (እስካሁንም መፈታታቸውን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡) ለዚህም ነው ኢብጋኅ አባል የሆነበትን IFJን በሙሉ ልብ ማመን የሚሳነኝ፡፡
አቶ ደረጄ ሀብተወልድን ስለኢብጋኅ በጠይቅኳቸው ጊዜ የሰጡኝ መረጃ ጠቅላላ ይዘት ‹‹የኅብረቱ የመጀመሪያ ሊቀመንበርና መሥራች የነበሩ ሲሆን፣ ኅብረቱ በጥቅመኞች የተያዘና ለኢሕአዴግ ወገንተኛ ነው›› የሚል ነው፡፡ እርሳቸውም የኃላፊነት ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ በፊት በግል ፈቃዳቸው የለቀቁት በዚሁ ሳቢያ እንደሆነ አጫውተውኛል፡፡
ስለኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማኅበራት የገዢው ፓርቲ አሽከርነት ብዙ ነገር ማለት ይቻላል፡፡ ሆኖም – ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም እንዲሉ – ከላይ የተጠቀሰው ላይ አንባቢዎች የየራሳቸውን ትዝብት እንዲሞሉበት መተዉ የተሻለ ነው፡፡ ከመደምደሜ በፊት ግን አዲስ የጋዜጠኞች ማኅበር ለመመሥረት በሒደት ላይ መሆኑን ላስታውሳችሁ እወዳለሁ፡፡ የዚህ ጽሑፍ ዓላማም አዲስ ለሚመሠረተው ማኅበር ከሌሎቹ መማር የሚችሉበትን ዕድል ለመስጠት የሚያስችል መልዕክት ማስተላለፍ ነው፡፡
እንደመዝጊያ አቶ አንተነህ (የኢብጋኅ ፕሬዚደንት) በመቋቋም ላይ ስላለው ማኅበር ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ የሰጡትን አጭር ፖለቲካዊ (የመንግሥት ወኪል የሰጠው የሚመስል) አስተያየት እንመልከት፡-

‹‹…ሊቋቋሙ ይችላሉ መብታቸው ነው፡፡ ነገር ግን እነማን ናቸው የሚያቋቁሙት፣ እንዴት ነው የሚቋቋሙት፣ ከጀርባ እነማን አሉ —- ይሄን ጠንቅቀን እናውቀዋለን፡፡ ትልቅ ጉዳይ አይደለም፤ ኖረንበታል፡፡ ለእኛ አዲስ ነገር አይደለም፡፡…››

በፍራቻ የተዋጡ የመንግስት ሰራተኞች = የፍትህ ያለህ ….
ጥቅማ ጥቅምን ሽፋን አድርጎ የመንግስት እና የፓርቲ ስራ ደባልቆ መስራት ከባድ አደጋ አለው::

መርዛማዊ ሃይል ያዘለ የፖለቲካ መስፋፋት የመንግስት ሰራተኛውን የመስራት እንዲሁም የመኖር ህልውና አደጋ ውስጥ ከቶታል::
ምንሊክ ሳልሳዊ :- በኢያንዳንዱ የመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ ሁሉንም ፖለቲካኛ የማድረግ እና ለፖለቲካ ፍጆታው ለመጠቀም የሚፈልገው ሕወሓት መራሹ መንግስት ህገመንግስታዊ የዜጎችን የመስራት/ሰርቶ የመኖር መብት እየደፈጠጠ ነው:: በኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኛው የከተማው ነዋሪ በመንግስት ስራ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል:; ይህ ዜጋ በተለያዩ አስተሳሰቦች እና እምነቶች የራሱ በሆነ ሂደት ውስጥ የሚጓዝ መሆኑ የማይካድ ሃቅ ነው::በተለያዩ ጊዜያት የተፈራረቁ መንግስታት ኢላማ የሆነው የመንግስት ሰራተኛው ዛሬም የፍትህ ያለህ የነጻነት ያለህ በማለት ላይ ነው::

በየትኛውም የአለም ክፍል ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ የሚያገለግለው ለቀጠረው ህዝባዊ አካል ሲሆን በመንግስት ሰራተኛው መሃል የተላያዩ የፖለቲካ አስተሳሰቦች ድጋፎች እና ተቃውሞዎች የመኖራቸውን ያህል ለፖለቲካ ግድ እስከሌለው ጀምሮ ፖለቲካ መስማት እስከማይፈልጉ እና ስራቸው ላይ ብቻ ማተኮር የሚፈልጉም ዜጎች አሉ :: ይህ ደሞ ህገመንግስታዊ መብታቸው እስከሆነ ድረስ ሊከበርላቸው ይገባል::

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው መርዛማዊ ሃይል ያዘለ የፖለቲካ መስፋፋት የመንግስት ሰራተኛውን የመስራት እንዲሁም የመኖር ህልውና አደጋ ውስጥ ከቶታል::ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ አለም አቀፍ የሰብኣዊ መብት ድርጅቶችም ይህንን በመንግስት ሰራተኞች ላይ የሚፈጸመውን በመስራት/በመኖር ላይ ያነጣጠረ ደባ አሳሳቢነት በይፋ ገልጸዋል::ከመንግስታዊ ጥቅማ ጥቅምም እንዲታገዱ እየተደረገ እንደሆነም ጩኸታችንን አሰምተናል::መንግስት ስንል ህዝብ ማለታችን መሆኑን ይገንዘቡልን..መንግስት የሚለው ቃል ወያኔን አይወክልም::

ወያኔ በህዝቦች ላይ የሚያራምደው አደገኛ የአገዛዝ ስልት የሚመለከቱ አብዛኛዎች የፓርቲው አባላት እና ካድሬዎች የትግል ቁርጠኝነታቸው ከመላሸቁም ሌላ ከፓርቲ ስራዎች ይልቅ በጥቅማዊ ጉዳዮች ላይ ማተኮራቸው ያሳሰበው ወያኔ አንድ ለአምስት በሚባል አደረጃጀት የፓርቲውን ስራ ከመንግስት ስራ ጋር ጎን ለጎን ለመተግበር ደፋ ቀና በማለት የዜጎችን ህልውና አደጋ ውስጥ ጥሎታል::የወያኔን ድርጅታዊ ስራ ከመንግስት ስራዎች ጋር ቀይጦ ለመተግበር መሞከር አደጋው ወደማይወጡበት አዘቅት ሊከት እንደሚችል መታወቅ አለበት ::

ወያኔ የስልጣን ጊዜውን ለማስረዘም ብቻ በሚያደርገው መፍጨርጨር በህዝብ እና በሃገር ላይ ሊመጡ የሚችሉትን አደገኛ እንቅፋቶች ከግንዛቤ አለማስገባቱ በላይ ማንጫውን ዜጋ ህዝብን በሚያገለግልበት የመንግስት ስራዎች ላይ መፈጸም የሚገባውን እንዳይፈጽም እና በድርጅታዊ ስራ ስፋን ለቢሮክራሲ ለሙስና ለህዝቦች እንባ በር መክፈት መሆኑን ልብ አለማለቱ የወያኔ ዝቅጠት ገሃድ አድርጎታል::
በልማት ስም እየተፈጸሙ ያሉት ደባዎች እና ሴራዎች አልበቃ ብሎት በኢኮኖሚ ድቀት እየተንገፈገፍ ያለን ህዝብ በድርጅታዊ ስራ ለመወጠር ማሰብ የፈነዳ እለት የሚያስከትለውን ችግር ማንም ሊወጣው እንደማይችል ለማረጋገጥ እንወዳለን ስለዚህ በመንግስት ሰራተኞች ዙሪያ እየተካሄደ ያለው እሽክርክሪት ሊታሰብበት ይገባል::

ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መምህራኑ አድማውን የጀመሩት ያለፍላጎታችን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ደሞዛችን እየተቆረጠብን ነው በሚል ነው። መምህራኑ ለይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር፣ ለጌዲዮ ዞንና ልክልሉ ትምህርት ቢሮ በጻፉት ደብዳቤ ላይ ” ከ ሀምሌ 2005 ዓም ጀምሮ ለህዳሴ ግድብ የሚቆረጠው ገንዘባችን እኛ ያለፈቀድነውና ያልተስማማንበት በመሆኑ ጥቅምት 28፣ 2006 ጀምሮ  ስራችንን በአግባቡ እየሰራን …

ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪፖርተር ባወጣው ዘገባ 18 የቻይና ኩባንያዎች ቤጂንግ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በግልባጭ ደግሞ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በላኩት ደብዳቤ ቀደም ብለው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የቻይና ኩባንያዎች ከአንዳንድ ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ስራ እንዳናገኝ እንቅፋት ፈጥረዋል ብለዋል። ኩባንያዎቹ የተሰማሩባቸው መስኮች የኃይል፣ የመስኖ፣ የመንገድና የንፁህ የመጠጥ ውኃ ግንባታዎች መሆናቸውን የዘገበው …

ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲሲቷ አፍሪካዊት አገር የተጀመረው የእርስ በርስ ጦርነት በሺ የሚቆጠሩ የአገሪቱ ዜጎች ህይወት ከቀጠፈ በሁዋላ የሁለቱም ተፋላሚ ሀይሎች ተደራዳሪዎች በአዲስ አበባ ቢገኙም አሁንም ጦርነቱ ቀጥሎአል። በአዲስ አበባ ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቀው የሰላም ድርድር የተኩስ አቋም ስምምነት እንዲፈረም ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። የተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር በበኩላቸው የተኩስ ማቆም ስምምነት …

ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሞቃዲሹ አየር ማረፊያ አካባቢ የሚገኘው ጃዚራ ሆቴል ውስጥ በሁለት መኪኖች የተጠመዱ ቦንቦች ፈንድተዋል። ፍንዳታው ከመድረሱ በፊት በጠባቂዎች እና ፍንዳታውን ባደረሱት መካከል የተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል። በአሁኑ ፍንዳታ ምን ያክል ሰዎች እንደተጎዱ አልታወቀም። ባለፈው ሳምንት በአንድ ምግብ ቤት ውስጥ በደረሰ ፍንዳታ 11 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። አልሸባብ አሁንም የደቡብ የሶማሊያ …

ባለፈው ኅዳር 14 እና 15 ,2006 በለንደን ብሪታንያ፤ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ባዘጋጁት ዓለም አቀፍ የዕውቀት ልውውጥ ነክ ጉባዔ ተሳትፈው ከተመለሱት አንዱ ናቸው። በጎንደር ዩንቨርስቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፣ «ባዮ -ሜዲካል እና ላበራተሪ ት/


(An excerpt from ‘Ethnicity and Political Parties in Africa: The case of ethnic-based parties in Ethiopia by Dr. Wondwosen B. Teshome /sub-titles are mine/)

At present, both in established democracies and emerging democracies ethnic-based parties are expanding. In many Western countries that have more homogenous society ethnic parties are rare. But, in Canada and other heterogeneous European countries (e.x. Belgium, Macedonia, Spain, and United Kingdom), in Asia (E.x. India, Russia, Srilanka), and in the Middle East (e.g. Israel) we find ethnic parties (Alonso 2005, Chandra 2004: 1). According to Cheeseman and Ford (2007:23), in Africa between 2001 and 2006 the number of ethnic parties decreased while the number of non-ethnic parties increased.

Moreover, Cheeseman and Ford (2007) revealed that the proportion of ethnic ruling parties dropped from 40% in 2001 to 30% in 2003 and to 20% in 2006. On the other hand between 2003 and 2006 the proportion of ethnic opposition parties increased. In rich countries ethnic parties are less dominant (Banerejee and Pande 2007: 6). It is generally believed that when societies develop and the economy shifts from agriculture towards heavy industry and then service economy, traditional social identities would be eroded. In other words, as argued by Crewe and Denver (1985), Dalton et al (1984), and Norris (2003) high literacy rate, geographic mobility, societal modernization, access to the news media would loosen the grip of ethnicity in developing countries. Hence, “Better-educated and more cognitively sophisticated citizens….have less need to rely upon the traditional social cues of ethnicity in electoral choices” (Norris & Mattes (2003:5).


Electoral Advantage

In countries which are dominated by ethnic party competitions ethnic parties which represent the largest ethnic group have an electoral advantage(Banerejee and Pande 2007:2, Chandra 2004). According to Gunther and Diamond (2001: 23), “the principal goal of the ethnic party is not any universalistic program or platform, but rather to secure material, cultural, and political benefits and protections for the ethnic group in its competition with other groups”. Moreover, the major aim of ethnic party, as argued by Gunther and Diamond (2001: 23), is “to harden and mobilize its ethnic base with exclusive, often polarizing appeals toethnic group opportunity and threat, …. electoral mobilization is not intended toattract additional sectors of society to support it”. The objectives of the policies of ethnic parties, almost at all times, are the preservation of the culture and the promotion of the interests of their co-ethnics. In order to achieve these, ethnic parties are established at the state level (Kantor 2006: 160-161).

The Domino Effect

Though ethnic party is usually presumed to be detrimental to democratic stability in the so-called “patronage-democracies,” it usually survives and flourishes, but only in two conditions: “when it has competitive rules for intraparty advancement and when the size of the ethnic group(s) it seeks to mobilize exceeds the threshold of winning or leverage imposed by the electoral system” (Chandra 2004: 1). According to Chandra (2002:1-2), ethnic parties are more stable than multi-ethnic parties and non-ethnic parties since the elites that hold the leadership of the party belong to the same ethnic group. Law (2005: 52-53) argues that “the formation of one ethnic party is likely to produce a chain reaction that leads to the formation of an ethnic political party system.” That is to say, theoretically speaking the transformation of one party into an ethnic party would also accelerate similar transformation of other parties. This is because once a party turns into an ethnic party it snatches voters (co-ethnics) away from the other non-ethnic parties.

Kantor (2006: 160) indicated that in societies that are structured along ethnic or national cleavages ethnic parties are formed. Countries that are ethnically diverse and low income tend to be organized along ethnic lines (Chua 2003; Horowitz 1985; Law 2005: 47; Posner 2005). The chances for ethnic parties to get electoral vote from non-members (i.e. members of ethnic groups) is very slim. Therefore, their existence depends on the vote and support they receive from their own co-ethnics. In ethnic-based party systems “those voters who crossed ethnicparty lines were subject, not just to the usual group pressures, but also to actual intimidation and even physical violence,”say Norris and Mattes (2003: 5) based on their studies conducted in Ghana, Trinidad and Guyana.

According to Banerejee and Pande (2007: 7), most of the time, ethnic political parties easily succeed in getting the support of their ethnic groups. This is because a voter favors his own ethnic group “for historical, social or symbolic reasons”. In ethnically diverse countries, ethnic parties get higher advantages over other parties during election due to the following factors: (1) The voters will be instinctively pulled towards their co-ethnics (Shils 1957; Huntington 1996) (2) A shared language (common language) and social network facilitates political organization along ethnic lines (Bates 1983; Fearon and Laitin 1996) (3) It is much easier to target patronage along ethnic lines (Chandra 2004; Glaeser and Goldin 1995) (4) It is easy for ethnic party to dominate an election and political power in its ethnic constituency since other political parties get very less chance in the constituency (Fearon 1999, Caselli and Coleman 2005).

Ethnic-based Parties and Stability

Many scholars (Horowitz 1985, Lijphart 1977, Rabushka and Shepsle 1972) have indicated that ethnic parties and the politicization of ethnic differences create instability and are assumed to be a major threat. Party systems where ethnically based parties dominate “are prone to conflict, exacerbating existing ethnic divisions…because holding the reins of power in state office is often seen as a zero-sum game, rather than a process of accommodation” (Norris and Matts 2003:3, citing Donald Horowitz). This theory is strongly advocated by Horowitz (2000: 294) and Wolf (2002). Other works (Deegan 2003: 2; Nikiwane 2000) also consider ethnic divisions as one of the causes for the weaknesses of political parties in Africa. By using South Africa as a case study Nikiwane (2000) said, “The biggest weakness of these opposition parties is that they are regional, at best, and tribal in orientation. Their only hope was to unify their organizations. But because of their fundamental structures (parochialism), they have consistently been unable to come together, let alone to agree on unified positions.” Deegan (2003: 2) also described the problems and weaknesses of African political systems as follows:
“Often parties had no constituencies or were ethnic-based; equally, political programmes, interaction with the populace and financial transparency were nonexistent. Internal party democracy was often unknown and many opposition parties actually disbanded between elections.”

Kaufmann and Conversi (n.d.) argue the emergence of ethnic party systems in divided societies due to democratization usually leads countries into inter-state conflict and intense ethnic divisions. To sum up, ethnic party system usually leads a country to three directions: military regime, one-party authoritarian regime, or the establishment of multi-ethnic parties and coalitions (Law 2005: 59). On the other hand, there are few scholars who attempted to justify the need for ethnic parties in Africa due to various compelling reasons. For instance, for Walraven (2000) ethno-regional groupings are the logical strategies for political parties to challenge incumbent parties in Africa. It is argued that the lack of class divisions and the absence or the weakness of strong civil society led African political parties to be established along ethnic lines. Another scholar, Lawson (1999: 12), also argued, “In the absence of formal associations clearly apart from the state and capable of engaging the population, the introduction of liberal democratic procedures, at the behest of external donors, had led political parties to appeal to the only available alternative: ethnic identity.”
[…]
According to Bogaards (2008: 6), the ban of ethnic party is usually a form of political engineering aimed at ethnic conflict prevention and management. Perhaps, the first nation in Africa that banned particularistic parties was Ghana. Kwame Nikurmah, the first leader of independent Ghana, passed a law banning such parties in the 1960s. In contemporary Africa, twenty-two African countries have laws directly or indirectly banning particularistic parties. Sometimes, African leaders who come from minority ethnic group ban the formation of ethnic-based parties fearing that the leaders of the major ethnic groups can easily snatch political power. The best example here is Kenya, where the long time president, Daniel Arap Moi, belongs to a minority tribe or ethnic group (Basedau et al 2007: 618).

Ethnic-based Parties and Democracy

Horowitz (1991, 1985) argues that in countries where ethnic-based parties dominate the quality of democracy is likely to suffer. This assumption, according to Chandra (2002: 23), is based on the concept of the so-called “out bidding effect” concept. This concept (i.e. “ethnic outbidding”) states that the rise of ethnic party, which is always the result of ethnic divisions “infects” the political system, destroys competitive politics, and threatens the survival of democratic institutions. For Sisk (1996) ethnically-dominated party system lowers the quality of democracy because it limits peoples’ electoral choices only to the members of a particular ethnic group. Ethnic-dominated party systems also decrease the quality of democracy because in such system politicians are focused more on the interests of their respective ethnic groups at the expense of the country’s interest.

As Posner (2004) notes, elites struggle to win the maximum rights and privileges for their ethnic groups. This condition fuels ethnic competition with the hope of gaining influence in national politics (Wantchekon 2003). On the other hand, for Chandra (2004, 2006) the quality of democracy will not be affected by the domination of ethnic-based parties. Another scholar, Birnir (2007) also voiced similar argument and claimed that ethnic-based parties might contribute for the improvement of the quality of democracy.

በጋዜጠኛ ስህተት የወጣች አንዲት ጽሁፍ ምክንያት 18 ሺህ ፊርማ በኢንተርኔት መሰበሰቡን ሰማን። ጽሁፉን ያሳተመው መጽሄት ስህተቱን አረመ። ይቅርታም ጠየቀ። ዘመቻው ግን እንደቀጠለ ነው። ቴዲ አፍሮ ይንን እንዳልተናገረ መግለጫ ቢሰጥም ጉዳዩ እልባት ሊያገኝ አልቻለም። ከቶውንም አንድነታችንን የማይፈልጉ ምእራባውያን ጭምር ይህችን ምክንያት በመያዝ ጉዳዩን ማረገብ ጀመሩ። አንድ የዳች ጋዜጣ አጼ ምኒሊክን ከሂትለር ጋር አመሳስሎ በመጻፍ ጋዜጣውን በዚህ […]

* ዱባይ በአስደናቂ 400 ሽህ ርችቶች አለምን አስደመመች! * እፁብ ድንቅ ርችቶች የአለምን ሪኮርድ ሰብረዋልም ተብሏል * ሳውዲና ባህሬንን በሚያገናኘው ድልድይ ተጨናንቋል * እኛም እያዘንን ለመደሰት በመሞከር ላይ ነን ከአመታት በፊት 828 ሜትር እርዝመት ያለው የቡርጅ ከሊፋን ሰማይ ጠቀስ ህንጻ በመገንባት የአለምን ሪኮርድ የሰበሩት ኢምሬቶች ዛሬ በጀመርነው አዲሱ አመት 400 ሽህ እፁብ ድንቅ በህብረ ቀለማት […]

የ ኒዎርክ ታይምስ ጋዜጣ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር) የዛሬ 96 አመት ስለ ዳግማዊ ምንሊክ የፃፈው ፅሁፍ ለአሁኑ ትውልድ ታሪካዊ ማስረጃ ነው
KING MENELIK HAS INVESTMENTS HERE; Abyssinia’s Ruler Said to be a Heavy Buyer of American… ታች ያለውን ሊንክ ከፍተው ያንብቡ።

ኢትዮጵያ በየዘመኗ በሕልውናዋ ላይ የተቃጣባት የመበታተን አደጋን ያለፈችበት መንገድ የጦርነት መንገድ ብቻ አይደለም።ሆኖም ግን ከነበሩን የግጭት ታሪኮች በዘለለ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ የነበሩ እና በሕዝብ ዘንድም የተወደዱ መሪዎች ነበሩን።ከእነኝህ ውስጥ ዳግማዊ ምንሊክ አንዱ ነበሩ። አፄ ምንሊክ ሀገር የማስተዳደር ጥበብን የተማሩት በአፄ ቴዎድሮስ እጅ ሆነው እድገታቸውን በንጉሡ ቤተመንግስት ማድረግ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ።ንጉሡ የቀደሙ አባቶቻቸው አፄ ቴዎድሮስ እና አፄ ዮሐንስ ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ አላማቸው እውን እንዲሆን ያደረጉ እድለኛ ንጉስም ናቸው።

አፄ ምንሊክ ኢትዮጵያን አንድ ከማድረግ አልፈው እስከ ኬንያ፣ሱዳን እና ሱማልያ ግዛት ድረስ ዘልቀው ገብተው በቅኝ ግዛት ይማቅቁ የነበሩ ህዝቦችን ነፃ ያወጣሉ የሚል ስጋት የነበረባቸው እና በወቅቱ በእነኚሁ የጎረቤት ሃገራት ላይ የጥቅም ፍላጎት የነበራቸው የአውሮፓ ሃገራት በብርቱ ተፈታትነዋቸው ነበር።በመሆኑም አዲስ የድንበር ውል ከኢትዮጵያ ጋር የመፈራረም ፍላጎት ከእንግሊዝ፣ፈረንሳይ እና ኢጣልያ በኩል ጥያቄ መነጻቱን የወቅቱ የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ።

ዛሬ ዛሬ በምንሊክ ላይ ታሪካዊ መሰረት የሌላቸው ቀድሞ አፄ ምንሊክ የቅኝ ግዛት ጥማታቸውን በገቱባቸው እና ቂም በያዙ ፀሐፊዎች የተፃፉ ናቸው ብለው ከሚነግሩን አስገራሚ ”የታሪክ” ፅሁፎች ውስጥ ”በምኒሊክ ዘመን እስከ አስር ሚልዮን ኦሮሞዎች አለቁ” የሚል ፅሁፍ በአንዳንድ የማህበራዊ ድህረ ገፆች ተለቀው ሲነበቡ መመልከት አስገራሚ የሰሞኑ ክስተት ነው።በፖለቲካው አለም በቂ ርዕዮተ አለምም ሆነ ፖለቲካዊ ፍልስፍና የጠፋባቸው አንዳንድ ወገኖች ”ትርፋማ” ብለው ያሰቡት የዘር ፖለቲካ በኢትዮጵያውያን መካከል መዝራት እና ከመቶ አመት በፊት የሆነውን የታሪክ ክስተት የአሁኑን ትውልድ በመውቀስ ትኩረት ለማግኘት ሲታትሩ መመልከት የዘመኑ አስቂኝ ተውኔት ነው።ዳግማዊ ምንሊክ ገና ብዙ የሚጠና ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ እና ወታደራዊ ክህሎት ባለቤት ለመሆናቸው በወቅቱ ከወጡት የዓለማችን ድንቅ ጋዜጦች አንዱ የ ኒውዮርክ ታይምስን እትም መመልከት ይበቃል።

ከእዚህ በታች በሚገኘው የኒውዮርክ ታይምስ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላላ ሕዝብ ብዛትን 7,000,000 (ሰባት ሚልዮን) መሆኑን ያስቀምጣል። እዚህ ላይ አንዳንድ እራሳቸውን የታሪክ ምሁራን ነን በሚል ባልተጨበጠ ይልቁንም በምኒሊክ የቅኝ ግዛት ህልማቸው ከተደናቀፈባቸው ቂመኛ ፀሐፊዎች አነበብን የሚሉት እና የኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ያማለሉ መስሏቸው ”ምንሊክ 10 ሚልዮን ኦሮሞ ገደሉ” እያሉ ኢትዮጵያ ከነበራት የህዝብ ብዛት (7 ሚልዮን) በላይ ቁጥር ሲጠሩ እፍረት አልተሰማቸውም።

”ማን ያውራ የነበረ” እንዲሉ የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ላይ ጋዜጣው አዲስ አበባ በነበረ በልዩ ዘጋቢው አማካይነት ስለንጉሡ እና ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሁኔታ ፅፎ ነበር።ጋዜጣው አፄ ምንሊክ እና አስተዳደራቸውን ከገለፀበት አረፍተ ነገር ውስጥ እነኝህ ይጠቀሳሉ –

– ኢትዮጵያን ወደ ህገመንግስታዊ የንጉሥ አስተዳደር ለመቀየር ሂደት ላይ መሆኗን፣

– የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት 7 ሚልዮን መሆኑን፣

– አፄ ምንሊክ ንጉሰ ነገስት ሲሆኑ ጦርነት የነበረው የአፄ ዮሐንስ ተተኪ እሳቸው መሆናቸውን ካልተቀበሉት ጋር ብቻ እንደ ነበር፣

– የአውሮፓውያንን ስልጣኔ ወደሀገራቸው ለማምጣት የባርያ ንግድን ከመዋጋታቸውም በላይ ነፃ ትምህርት ዕድል ዜጎች እንዲያገኙ መሰረት መጣላቸውን፣

– ምንሊክ እራሱ ልዩ ችሎታ ያላቸው ሰው መሆናቸውን። ከችሎታዎቻቸው መካከል ዲፕሎማት፣የፋይናንስ ባለሙያ እና ወታደር የሚሉት እንደሚጠቀሱ እና

– እንደ ዲፕሎማት እና ወታደር የጣልያንን ወረራ ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ያደረጉበት ጥበብ መሆኑን፣

የሚሉ ይገኙበታል።የጋዜጣውን ሙሉ ፅሁፍ ከእዚህ በታች ያለውን ሊንክ ከፍተው ያንብቡ።
የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ለማንበብ ይህንን ሊንክ ይክፈቱ።

http://query.nytimes.com/mem/archive-fr … 5B898CF1D3

ከሩሲያውያኑ ቦልሼቪክና ሜንሼቪክ አንስቶ፣ የእኛዎቹ ኢህአፓና መኢሶን በፊት-አውራሪነት እስከ ተሳተፉበት ድረስ ያሉ በደም የጨቀዩ አብዮቶች በሙሉ በከተሞች የተካሄዱ ሲሆን፣ አብዛኛው አጋፋሪዎቻቸው
ደግሞ ልሂቃኖች እንደነበሩ በጉዳዩ ዙሪያ የተፃፉ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ ይሁንና እነዚህ አብዮቶች (የተሳኩትም ሆነ የከሸፉት) ሰላማዊውንና ህጋዊውን መንገድ የተከተሉ ባለመሆናቸው ዛሬም ይዘገንናሉ፤ ለወደፊቱም ባልተደገሙ ያሰኛሉ፡፡ ስለምን ቢሉ? ግድግዳው ላይ የተቸከቸከው ፅሁፍ እንዲህ የሚል ምላሽ ያስነብባልና፡- በጭቁን ሕዝብ ስም የብዙሀኑን ቤት አፍርሰዋል፤ ሀገርና ታሪክ ለመቀየር የማይሳናቸው አፍላ ወጣቶችን እርስ በእርስ አጫርሰዋል፤ ‹አንቱ› ሊባሉ የሚችሉ ምሁራንን በአንድ ጀንበር ወደ ትንታግ ነፍሰ-ገዳይነት ቀይረዋል፤ ክስረቱም ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ጠባሳ ሆኖ ዛሬ ላይ ደርሷል…

በርግጥም ያ ወቅት መደማመጥ፣ መነጋገር፣ መወያየት፣ መቻቻልን… የመሳሰሉ ምክንያታዊ እሴቶች ህቡዕ ገብተው፤ መጯጯኽ፣ መነቋቆር፣ መፈራረጅ፣ መገዳደል… የገነኑበት ነበር፤ ለዚህም ይመስለኛል ሀገር ሊረከብ የተዘጋጀ አንድ ትውልድ፣ በተኮረጀ ርዕዮተ-ዓለም፣ ባልጠራ ፕሮግራም እቅሉን ስቶ ‹ማርክስ እንደፃፈው›፣ ‹ሌኒን እንዳብራራው›፣ ‹ማኦ እንዳስተማረው›፣ ‹ሆጃ እንደመከረው›… በሚል ጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት ስቶ-በማሳት፣ ሀገር ምድሩን የጦር አውድማ አድርጎ ማለፉ የትላንት የቁጭት ትዝታ የሆነብን፡፡ በአናቱም ዛሬ ‹‹ነፃ አወጣናችሁ›› እያሉ ጃሎታ የሚመቱት የኢህአዴግ መሪዎች ከዚሁ ምንጭ የተቀዱ፣ ግና በቃላት ስንጠቃና በጎሳ ጠባብ አስተሳሰብ የተለዩ የትውልዱና የመንፈሱ ተጋሪ በመሆናቸው፣ የሁነቱ ‹ታሪክ›ነት ለተሰዉት እንጂ፣ ለእነርሱ ‹ሀገር እየመራንበት ነው› የሚሉበት ‹ፖለቲካ› ነውና፣ የነገይቷ የምንወዳት ኢትዮጵያችን መፃኢ ዕድል ገና ከእርስ በእርስ ግጭት ስጋት አለመላቀቁን ያመላክታል፡፡ በዚህ ፅሁፍም የምንዘመርለት የ‹አትነሳም ወይ?› ድምፅ አደገኛውን ስርዓት የመቀየሪያው ጊዜ አሁን በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ግን እነኢህአፓ ተቸንፈው የተሰናበቱበትም ሆነ ኢህአዴግ ድል አድርጎ የመጣበት መንገድ ለዘመኑ መልካም ተሞክሮ ሊሆን ይችላል እንደማለት አይደለም፤ ምክንያቱም በእኔ እምነት የእነርሱ ‹ፋኖተሰማራ…› ጊዜው በበየነበት ሙዚየምና የታሪክ ትምህርት ክፍል ውስጥ ብቻ ካልተገደበ ጉዳቱ በቀላሉ የሚጠገን ካለመሆኑም ባለፈ፣ የምንመኘውን ለውጥ ሊያመጣ አይችልምና ነው፡፡

የሆነው ሆኖ ለትውልዱ ክቡድ ጥያቄ ስኬታማነት መንገድ መሪ አብርሆት መሆን የሚችሉ የደም ግብር ያልጠየቁ፣ ፍፁም ሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ በከተሞች ተካሂደው ሀገርና ህዝብ ያለ ብዙ ኪሳራ በአሸናፊነት የወጡባቸው በርካታ አብነታዊ አብዮቶች (እንደ አረቡ ፀደይም ሆነ እንደ አውሮፓውያኑ ጆርጂያና ዩክሬን ብርቱካናማ-አብዮቶች) መኖራቸው እውነት ነው፤ እንዲሁም በእነርሱ መንፈስ መቀደስ፣ በእነርሱ ፀበል መጠመቅ የአምባገነኑንና የበደለኛውን ሥርዓት እድሜ ለማሳጠር የሚያበረታ ኃይል ማስረፁ እውነት ነው፡፡

ከተማን እንደ ጠላት

የ‹ያ ትውልድ› የጠብ-መንጃ ትንቅንቅን በድል የተሻገረው ኢህአዴግ (ከልቡ አምኖበት ባይሆንም) ይህንን ሁሉ መስዋዕትነት የከፈለው በተለይም ለአርሶ አደሩ ጥቅም መሆኑን በአገኘው አጋጣሚ ሳይናገር አያልፍም፡፡ በግልባጩ ደግሞ የከተማ ነዋሪዎችን ‹ጠላት› አድርጎ በመፈረጅ ሲገነግን ተደጋግሞ ተስተውሏል፤ በርግጥ የዚህ መግፍኤ በብሔር እና በሀይማኖት የከፋፈለውን ሕዝብ፣ በመደብም ለያይቶ የሥልጣን ዕድሜ ማራዘሚያ ለማድረግ እና በየአምስት ዓመቱ በሚያካሄደው የይስሙላ ‹ምርጫ› ኮረጆ ገልብጦ ሲያበቃ የፈረደበት ምስኪን አርሶ አደር ‹መርጦኛል› ለሚለው የተለመደ ሰበቡ ‹ይጠቅመኛል› በሚል ለማመቻቸት ‹አዛኝ ቅቤ…› ተቆርቋሪ በመሆኑ ይመስለኛል፡፡ ይህም ሆኖ ድርጅቱ ይህንን የማጭበርበሪያ ስልት በደደቢት በረሃ ራሱ የቀመረው ነው ብሎ ለመከራከር የሚያስችል ገፊ ጭብጥ ይኖራል ብዬ አላስብም፤ ምክንያቱም በአንዳንድ የዓለማችን ሀገራት የፖለቲካውን ኃይል ከጨበጡ በኋላ በሕዝባቸው ላይ ነጋሪት ጎስመው ሞትን ከነዙ፣ ስቃይን ከረጩ እርኩሳን መሪዎች (ፓርቲዎች) ድርሳናት ቃል-በቃል የተገለበጠ መሆኑን የሚያስረግጡ (በስነ-አመክንዮ) የተቀኙ ማሳያዎች ማቅረብ ይቻላልና፤ እንደምሳሌም አንዱን በአዲስ መስመር እንምዘዘው፡-

የ‹ኬመር ሩዥ› መንገድ

በተለምዶ ‹ኬመር ሩዥ› (Khmer Rouge) በመባል የሚታወቀውና አክራሪ ኮምኒስታዊ የገበሬዎች ድርጅት እንደሆነ የሚነገርለት ‹‹Communist Party of Kampuchea /CPK/›› እ.ኤ.አ ከ1975-1979 ዓ.ም ድረስ፣ በወጣት የገበሬ ሠራዊት ታግዞ በካምቦዲያ መንግስታዊ ሥልጣን ተቆናጥጦ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ጨካኝና አፍቃሪ ቻይና የሆነው የፓርቲው ሊቀ-መንበር ፖል ፖትም (Pol Pot)፣ ማኦ ዜዱንግ ‹‹የሀገሬን ኢኮኖሚ ያሳድግልኛል›› በማለት ያረቀቀውንና በግብርና ላይ የሚያተኩረውን ‹‹Great Leap Forward›› ፕሮግራም፣ ‹‹Super Great Leap Forward›› በሚል ተቀጥላ እንደወረደ በመኮረጅ ‹‹ሙሉ የካምቦዲያን ሕዝብ ወደ ‹እርሻ መር-ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ› (Agrarian Society) እቀይራለሁ›› ብሎ ያደረገው ሙከራ ወጪ-ኪሳራን ያወራረደው ሁለት ሚሊዮን ዜጎቹንለህልፈት በመዳረግ እንደ ነበር የታሪክ መፃህፍት ያትታሉ፡፡

ከሁሉም የከፋው ግን ፖል ፖትና ጓዶቹ ‹‹እውነተኛ ዜጋ ገበሬ ብቻ ነው›› በማለት የከተማ ነዋሪዎችን በጠላትነት ከፈረጁ በኋላ ‹‹ማህበረሰባችንን ለማንፃት›› በሚል የቁም-ቅዠት ምዕራባዊ አስተሳሰብ የተንፀባረቀበትን ማንኛውንም ጉዳይ፣ የከተማ ሕይወትን፣ ኃይማኖትን፣ ትምህርትን፣ አንድ ብርም ቢሆን በግል መያዝን… በአዋጅ ማገዳቸው ነበር፤ እንዲሁም ኢምባሴዎችን፣ ጋዜጣና ቴሌቪዥን ጣቢያን ዘግተዋል፤ በሁሉም የሀገሪቱ ከተሞች የሚኖሩ ዜጎችን በማፈናቀል ወደ ገጠር አግዘው፣ በግዳጅ የእርሻ ሥራ ላይ አሰማርተዋል፤ ከዋና ከተማዋ ‹ፈኖሞ ፔንህ› (Phnom Penh) ብቻ ሁለት ሚሊዮን ዜጎች ወደገጠር በእግር እንዲጓዙ በመገደዳቸው ሃያ ሺህ የሚሆኑት በጉዞ ላይ ወድቀው እንደወጡ ቀርተዋል፤ ገጠር የደረሱትንም ቢሆን ‹የግድያ ወረዳዎች› እያሉ በሚጠሯቸው የእርሻ ሥራ ላይ አሰማርተው ለአንድ ሰው በነፍስ ወከፍ በየሁለት ቀኑ አንዴ 180 ግራም ሩዝ ብቻ በመስጠት በረሀብ፣ በበሽታ፣ ብስቅየት እና በግድያ እንዲያልቁ አድርጓል፡፡ በመጨረሻም አገዛዙ በቬትናም ጣልቃ ገብነት እ.ኤ.አ በ1979 ዓ.ም በኃይል በመወገዱ፣ ፖል ፖት ከእነተከታዮቹ ሀገሩ ከታይላንድ ወደምትዋሰንበት ጠረፍ አካባቢ በመሸሽ፣ የትጥቅ ትግል እንደአዲስ ጀምሮ ለረዥም ዓመታት ከታገለ በኋላ፣ እ.ኤ.አ በ1997 ዓ.ም እርጅና ተጭኖት በህግ ቁጥጥር ስር በዋለ፣ በዓመቱ ከልብ ጋር በተያያዘ ህመም ምክንያት ህይወቱ ማለፉ ይታወቃል (በነገራችን ላይ ይህ ድርጅት የሽምቅ ውጊያ ከመጀመሩ በፊትም ሆነ በኋላ የተጠናከረበትን ምስጢራዊ መንገድ ጨምሮ የተከተለው ስልት ከሞላ ጎደል ከኢህአፓና ህወሓት አፈጣጠር ትርክት ጋር ተመሳሳይነት አለው)

ኢህአዴግ እንደ ‹ኬመር ሩዥ›

ከሁለት አስርተ ዓመታት የሥልጣን ቆይታም በኋላ፣ የከተማ ነዋሪዎችን በጠላትነት ካሰፈረበት ጥቁር መዝገቡ ላይ መሰረዙ ያልሆነለት ኢህአዴግ ‹እንደ ኬመር ሩዥ ሁሉንም የጭካኔ ተግባራት በአደባባይ ፈፅሟል› ተብሎ ባይወነጀልም፣ ተመሳሳይ ስልቶችን በመኮረጅ በረቀቀ መንገድ አለዝቦ መተግበሩን ግን መካድ አይቻልም፡፡ እንዲሁም የሁለቱ ድርጅቶች ዋነኛ ልዩነት ወደ እንዲህ አይነቱ የጥላቻ ጠርዝ
የተገፉበት ምክንያት ይመስለኛል፤ ይኸውም ፈላጭ ቆራጩ ፖል ፖት በከተሜው ላይ የከፋ ቂም የቋጠረበት መነሾ፣ ከገበሬ ቤተሰብ መገኘቱን ጨምሮ፣ ከአስተዳደጉ ጋር በሚያያዙ ‹ህመማቸው-ህመሜ› በሚል ሲባጎ የተቋጠረ ሲሆን፣ መለስና ጓዶቹ ደግሞ የሥልጣን ዕድሜያቸውን ለማራዘም በማስላት ብቻ መሆኑ ነው፤ መቼም መሬት የረገጠውን እውነታ ተመልክቶ የሀገሬ አርሶ አደር ከፕሮፓጋንዳ ፍጆታ በዘለለ፣ ከከተሜው የተለየ የመልካም አስተዳደርም ሆነ የመሰረተ-ልማት ተጠቃሚ አለመሆኑን መረዳቱ አዳጋች አይደለም፡፡ የሆነው ሆኖ የኢህአዴግ ‹ፀረ-ከተሜነት› እንዲህ በግላጭ አፍጥጦ የወጣው ከምርጫ 97 በኋላ ነው፤ በወቅቱ ጠቅላይ ሚንስትሩ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርቦ፣ ድርጅቱ በከተሞች መሸነፉን ከገለፀ በኋላ፣ በገጠር ሙሉ በሙሉ ስለተሳካለት መንግስት ለመመስረት የሚያስችል የመራጭ ድምፅ ማግኘቱን አውጇል፤ ይህንንም ተከትሎ ግንባሩን ያልመረጡ የከተማ ነዋሪዎች በተቀነባበረ ሴራ የጥቃት ዒላማ መሆናቸውን የሚያመላክቱ በርካታ እርምጃዎችን ወስዷል፡፡ በተለይም በድህረ-ምርጫው ከተሜውን ዒላማ ያደረጉ በስራ ላይ የዋሉ አፋኝ ህጎች እና ፖሊሲዎችን ጨምሮ በደባ የተፈፀሙ መንግስታዊ ጥፋቶችን ዘርዘር አድርገን እንያቸው፡፡

መሬትን በተመለከተ የወጣውን የሊዝ አዋጅ በቀዳሚ ምሳሌነት እናንሳው፤ ፓርቲው በ1987 ዓ.ም ባፀደቀው ህገ-መንግስት የመሬት ፖሊሲውን አንዱ ዕማድ አድርጎ በማካተቱ፣ የመንግስት ጭሰኝነትን (Tenants of the state) በገጠሩ ክፍል ሲያሰፍን፣ የመሬት ከፊል ባለቤትነትን ደግሞ ለከተሞች እንዲፈቅድ አድርጎት ነበር፡፡ እናም የግል ይዞታን መሸጥ (መንግስት ለሚፈልጋቸው ‹‹ልማቶች››ም ሆነ
በሊዝ ለመቸብቸብ ዜጎችን የማፈናቀል መብት ከማግኘቱ ውጪ) እስከ 97ቱ ድህረ-ምርጫ ድረስ ተፈቅዶ የዘለቀበት ሂደት፣ በዚህ የሊዝ አዋጅ በመሻሩ የተነሳ፣ ነዋሪው መሬት በመሸጥ ሊያገኝ ይችል የነበረው ገቢ ተጨምቆ ወደ መንግስት ካዝና እንዲሻገር ሆኗል፡፡ የዚህን አዋጅ ‹ፖለቲካዊ ንባብ› ውስጥ የምናገኘው ጭብጥ፣ በከፊልም ቢሆን መሬት ላይ የቆመውን የሀብት መሰረት በመናድ፣ የተቃውሞ ኃይሉ የድጋፍ መዕከል እንደሆነ ያመነውን የማህበረሰብ ክፍል ክፉኛ ማድቀቁን ስንረዳ ነው፡፡ አዋጁን እንለጥጠው ካልን ደግሞ ግንባሩ በገጠሩ ያነበረውን የዜጎች የመንግስት ጭሰኝነት በጠመዝማዛ መንገድ፣ በተለይም በአዲስ አበባ የመፈጸም ዕቅዱ አድርገን ልንወስደው እንችላለን፡፡

የኢህአዴግ ከተማንና ከተሜዎችን የመፍራት አባዜ ከጫካ ትግሉ ጋርም በረዥሙ የሚተሳሰር ነው፡፡ በወቅቱ በጥላቻ ከመተያየት አልፎ ደም የተቃባቸው ኢህአፓን መሰል ኃይሎች መሰረታቸው ከተሞች ላይ እንደነበረ ይታወቃል፤ በአናቱም በትግሉ መጠናቀቂያ ዋዜማ እና ማግስት ሊገዛለት ያልቻለው (ማማለሉ ያልተሳካለት) ልብ በተለይ የአዲስ አበቤዎችን ነበር፤ በ1980ዎቹ መጀመሪያም ፓርቲው አንገት ላይ ታንቆ ሊደፋው የነበረው ዋነኛ ጉዳይ፣ ብሔር ተኮር ስርዓቱ ህገ-መንግስታዊ ድጋፍ ሲያገኝና የብሄር ፖለቲካ ብቸኛው የድጋፍም የተቃውሞም ተዋስኦ እንዲሆን መደረጉ ነበር፡፡ ይህንንም ተከትሎ በኢትዮጵያዊብሔርተኝነት መንፈስ ከተገራው የአዲስ አበቤ ብሔር ዘለል ማንነት ጋር እንዲህ በፊት ለፊት መጋጨቱ፣ ከተማይቱን በወረራ የያዛት እስኪመስል ድረስ በጥላቻ እንዲዘምቱበት አነሳስቷል፡፡

ሁለተኛው ምዕራፍ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን ተከትሎ የመጣው የአሰብ ወደብን ወደ ኢትዮጵያ ግዛት እንዲካለል የመፈለግ የከተሜዎቹ ግፊት ነው፡፡ ጦርነቱ ሲያበቃና የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ኋላ እንዲያፈገፍጉ ሲገደዱ የነዋሪው ቁጣ ብርቱ እንደነበር እናስታውሳለን፡፡ ይህ እውነትም ሌላኛው ፓርቲውን ቂም ያስቋጠረ ክስተት ሆኖ አልፏል፡፡ በድህረ-ምርጫ 97 የፀደቀውና አፋኝነቱ በተግባር የተረጋገጠው የሲቪል ማህበረሰቡን የሚመለከተው አዋጅም ‹የብዙዎች ተቋማት ዋናመቀመጫ አዲስ አበባ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የወጣ ነው› በማለት ከየአቅጣጫው ይነሳ የነበረውን የተቃውሞ ውግዘት አጣጥሎ፣ በሥራላይ ባዋለበት ዓመት በርካታ ተቋማትን ከማፈራረሱ አኳያ፣ መጀመሪያውንም ለእንዲህ አይነቱ ክፉ እርምጃ ታስቦ የተዘጋጀ ነው ወደሚል ጥርዝ ይገፋል፡፡ በተጨማሪም ያለፉትን ሃያ ሁለት ዓመታት ሙሉ በአይኑ መዓት የሚያያቸው ምሁራን፣ የነፃው ፕሬስ አባላት እና በየዘመኑ ከባድ ተግዳሮት የፈጠሩበት የተቃውሞ ስብስቦች ጠንካራ መሰረት በከተማይቱ ውስጥ መሆኑ ጥላቻ እና የጭካኔ እርምጃዎቹን አብዝቶታል፡፡

ሌላው አገዛዙ በከተሜዎች (በሸማቾች) ላይ ያለውን ስር የሰደደ ጥላቻ የሚያሳዩት፡- ከምርጫው በኋላ ጤናማ ያልሆነ የዋጋ ንረት በከፋ ደረጃ ማሻቀቡ፣ ፍትሃዊ ያልሆኑ የተለያዩ የግብር ህጎች በእንጀራ እና ሽንኩርት ቸርቻሪዎች ላይ ሳይቀር መተግበራቸው ነው፡፡ በተለይም ካለፉት ስምንት ዓመታት ወዲህ የተከሰተው ከፍተኛ የዋጋ ንረት ዋነኛ አባባሽ ኃይል የምግብ ዋጋ መናር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በዚህ
የምግብ ዋጋ መናር በዋነኝነት ቋሚ ደሞዝ ተከፋዩ የከተማ ነዋሪው ተጎጂ መሆኑን የስርዓቱ ባለስልጣናትም ይቀበላሉ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ከሁለት ወራት በፊት በ‹‹አዲስ ዘመን›› መፅሄት የተጠየቀው የፋይናስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ ‹‹በ2006 ዓ.ም የሚጨመር ደሞዝ አይኖርም›› ከማለቱ ባለፈ ‹‹ነገ ይችን አገር ወደተሻለ የሚያደርስ በጎ መስዋዕትነት ነው›› ሲል በከተሜው መከራ ላይ አላግጧል፡፡ በርግጥ ይህ ሁሉ መዓት ከመውረዱ በፊት በ1998 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ራሱ አቶ መለስ በደቡብ ክልል ወደምትገኘው ይርጋለም ከተማ ድረስ ሄዶ የሙዝ አምራች አርሶ አደሮችን ሰብስቦ ካነጋገረ በኋላ፣ እንዲህ ለፍተው የሚያገኙትን ምርት ለከተሜው በርካሽ መሸጣቸው አግባብ አለመሆኑን ቀስቅሶ ዋጋውን በአራት እጥፍ እንዲጨምሩ በማድረጉ የተፈጠረው የገበያ እጥረት፣ ምንም እንኳ መልሶ አምራቾቹን ሰለባ ቢያደርግም፣ ኩነቱ የጠቅላይ ሚንስትሩን ቀጣይ ዕቅድ የሚያመላከት ነበር፡፡

በከተሞች ውስጥ እየተደረገ ያለው ‹‹የሰፈራ ፕሮግራም››ም (Urban Resettlement) አንዱ ሊነሳ የሚገባው ነጥብ ነው፡፡ በእርግጥ በዚህ ዕቅድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የተሻለ የመኖሪያ ቤቶች ተጠቃሚ እንደሆኑ ማየት እንችል ይሆናል፡፡ ጥያቄው የሚነሳው ግን፣ የአንድ አካባቢ ነዋሪዎችን ከሌሎች የፈረሱ የከተማዎቹ ክፍሎች ከሚመጡት ጋር በአንድ አዳብሎ በኮንዶሙኒየም ቤቶች አጥሮ የማስቀመጡ አንደምታ ላይ ነው፡፡ የዚህ ዕቅድ ክፉ ገፅ የሚገባን በረዥም የአብሮነት መስተጋብር (ሶስት መንግስታትን መሻገር የቻለ የአንድ አካባቢ ነዋሪነት) የተገነባው የጋርዮሽ ፖለቲካው አረዳድ እና የእርስ በእርስ ፍፁም መተማመን፣ 97ን ጨምሮ በተለያዩ ወቅቶች በተነሱ ተቃውሞዎች ወጥ ምላሽ እንዲሰጡ ማደፋፈሩን (አራት ኪሎን የመሳሰሉ አካባቢዎች) አስታውሰን፣ በመልሶ ማስፈሩ ደግሞ የአንዱን አካባቢ ነዋሪ በታትኖ ወደተለያዩ ሳይቶች መውሰዱን ስንመለከት ነው፤ ይህ መራራ እውነታም የገዥዎቻችን ጥላቻ ስር የሰደደ መሆኑን እና የአምባገነናዊ ስርዓቱን ዕድሜ ለማራዘም ያለመ እንደሆነ ይጠቁመናል፡፡

(ስርዓቱ በከተሜዎች ላይ የሰረፀበትን ጥልቅ የጥላቻ ፅንፍ እንዲህ ከተመለከትን፣ የከተማ አብዮት፣ ማኦኢዝም ከሚያዘው ከገጠር ከሚነሳው ብረታዊ ትግል ጋር ያለውን ልዩነት፣ በአረቡ ፀደይ ተሞክሮ በመንተራስ መፈተሹን፤ እንዲሁም የኢህአዴግ ግድፈቶች (Achilles’ heel) የከተማ አብዮትን ለማስነሳት ያላቸውን አስተዋፅኦ፣ በአደባባይ ሊያሰባስቡ የሚችሉ ጥያቄዎች ምን ቢሆኑ የተሻለ ነባራዊውን እውነት ያንፀባርቃሉ… የሚሉትን ጉዳዮች እና መንገዱን ስለሚመሩ የሚችሉትን መልከአ-ቡድኖች ማንነት ሳምንት እመለስበታለሁ)

ኢትዮሚድያ – Ethiomedia.com

ታህሳስ ፳፪( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሳዑዲ መንግስት የመኖሪያና የስራ ፈቃድ የሌላቸውን ኢትዮጽያዊያን ማባረሩን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ ኤጀንሲዎች መካከል ከ100 በላይ በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ተሳትፈዋል የተባሉ ኤጀንሲዎች ላይ ክስ ለመመስረት መዘጋጀቱን ከአዲስ አበባ ከተማ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የተገኘ መረጃ ጠቆመ፡፡ በኢትዮጽያ በአጠቃላይ 470 የውጭ ሃገር የስራ ስምሪት ኤጀንሲዎች …

ታህሳስ ፳፪( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የወጡ መረጃዎች እንዳሳዩት በአፍሪካ ባለፉት 6 ዓመታት በጉዲፈቻ ስም ወደ ውጭ ከተላኩት 34 ሺ 342 ህጻናት ውስጥ 63 በመቶ ወይም 21 ሺ 365 ሰዎችን በመላክ ቀዳሚ ናት። በሃገሪቱ በሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ፈቃድ የተሰጣቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ጉዳይ አስፈፃሚ የጉዲፊቻ ደላሎች ተበራክተዋል፡፡ በአብዛኛው ለጉዲፈቻ በሚቀርቡ ህፃናት …

ታህሳስ ፳፪( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመሰራት ላይ ያለው አዲስ ፊልም ኦነግ ፤ ኦብነግ እና ግንቦት ሰባትን በሽብርተኝነት የሚያወግዝ ነው። ኢህአዴግ በዚህ ሰአት ፊልሙን ለምን ለመስራት እንደፈለገ ግልጽ የሆነ ነገር የለም። አንዳንዶች እንደሚገምቱት ከሆነ ግን ገዢው ፓርቲ በድርጅቶች እንቅስቃሴ ስጋት እየገባው ነው። እየተሰራ ባለው ፊልም ውስጥ ኢሳትንም ለመወንጀል እየታሰበ መሆኑን ምንጮች አስታውቀዋል። …

ታህሳስ ፳፪( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለኤ ኤፍ ፒ እንደገለጹት ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር እና የተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር ለውይይት በአዲስ አበባ ይገኛሉ። ማቻር የሰላም ድርድሩን የተቀበሉት የዩጋንዳው መሪ ዩዎሪ ሙሰቬኒ አገራቸውና የኢጋድ አባላት በደቡብ ሱዳን ግጭት ውስጥ እጃቸውን በማስገባት አማጽያኑን እንደሚወጉ ማስጠንቀቃቸውን ተከትሎ ነው የሚለውን …

ታህሳስ ፳፪( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎርጎሪያን ካላንደር የሚቆጥሩ አገሮች አዲስ ዓመታቸውን በልዩ ድምቀት እያከበሩት ይገኛሉ። በጎርጎሪያን ቀመር መሰረት ኢየሱስ  በዳዊት ከተማ በኢሩሳሌም በምትገኘው ቤተ-ልሔም ከተወለደ 2014 ዓመት ሆኖታል ። እንደ ቢቢሲ ዘገባ አዲስ ዓመትን ከሁሉም ቀደም ብላ የተቀበለችው አገር  ኒውዚላንድ ነች። ቤጅንግን ጨምሮ የምስራቅ እስያዎቹ  ጃካርታ እና ሲንጋፓር አዲስ ዓመቱን በደመቀ ሁኔታ …

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት የቀድሞው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር የአቶ መላኩ ፈንታን ጉዳይ ለማየት ሥልጣን ያለውን ፍርድ ቤት ለመለየት የሚያስችለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሣኔ ዛሬም እንዳልደረሰው አስታውቋል፡፡

ተለዋጭ ቀጠሮም ሰጥቷል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን የችሎት ውሎ ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ማቸር ለመደራደር ፍቃደኛ ከመሆናቸዉ ጋር ተኩስ እንደማያቆሙ እንዳስታወቁ ሁሉ ፕሬዝዳት ሳልቫ ኪርም ዉጪ ጉዳይ ሚንስትራቸዉን ለድርድር ወደ አዲስ አበባ ከመላካቸዉ እኩል ሥልጣን እንዲለቁ ወይም አዲስ ምርጫ እንዲደረግ ተቃዋሚዎች ያቀረቡትን ሐሳብ ዉድቅ አድርገዉታል