የሕወሐት አባል የሆነውና በአሜሪካ የሚኖረው ብስራት አማረ በርካታ ወንጀሎችን እንደፈፀመ የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። ሕወሐት በረሃ እያለ የባዶ 6 እስር ቤት ዋና ሃላፊ የነበረው ብስራት አማረ የኢ.ህ.አ.ፓ አባላት የነበሩት እነ ፀጋዬ ገ/መድህን (ደብተራው) ጨምሮ በሕወሐት የተያዙትን በሙሉ ወረኢ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በነበረ እስር ቤት በጅምላ አሰቃይቶ እንደገደላቸው ምንጮቹ አረጋግጠዋል። በሺህ የሚቆጠሩ የትግራይ ሰዎች « ኢዲዩና ፊውዳል..» […]

“ ነፃነቴን ካልሰጣችሁኝ ሞትን እመርጣለሁ” ፓትሪክ ሔንሪ Give me Liberty or Give me Death ፍሬደሪክ ዳግላስ (1818- 1895) ከባርያ እናትና ከነጭ አባት የተወለደና ራሱም ቢሆን በቦልቲሞር (ሜሪላንድ) የቤት አሽከር ሆኖ የቆየ ሰው ነበር። አንድ ማለዳ ጁላይ 4 ቀን 1852 ን ተንተርሶ (አንተርሶ) በሮቼስተር ከተማ (ኒውዮርክ) ንግግር እንዲያደርግ ጥሪ ይደርሰዋል። ደብዳቤው ሲደርሰው እንደ እብድ ከራሱ ጋር […]

የ2006 ዓ/ም የኢትዮጵያ ሰማእታት ቀን በየካቲት ወር 12 ሐገሮች በሚገኙ በ27 ከተሞች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተከናውኗል። የአከባበሩም ስነሥርአት በሰላማዊ ሰልፍ፤ በሕዝባዊ ጉባኤ፤ ወይም በጸሎት ነበር። አዲስ አበባ የተከናወነው የካቲት 12 አደባባይ ሲሆን የአበባ ጉንጉን ኃውልቱ ሥር በማስቀመጥና ንግግር በማሰማት ነበር። እንደሚታወቀው፤ የሰማእታት ቀን በየዓመቱ የሚከበረው፤ በየካቲት 19-21፣ 1929 ዓ/ም ፋሺሽቶች አዲስ አበባ በሶስት ቀኖች ውስጥ […]

Image

የሕወሐት አባል የሆነውና በአሜሪካ የሚኖረው ብስራት አማረ በርካታ ወንጀሎችን እንደፈፀመ የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። ሕወሐት በረሃ እያለ የባዶ 6 እስር ቤት ዋና ሃላፊ የነበረው ብስራት አማረ የኢ.ህ.አ.ፓ አባላት የነበሩት እነ ፀጋዬ ገ/መድህን (ደብተራው) ጨምሮ በሕወሐት የተያዙትን በሙሉ ወረኢ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በነበረ እስር ቤት በጅምላ አሰቃይቶ እንደገደላቸው ምንጮቹ አረጋግጠዋል። በሺህ የሚቆጠሩ የትግራይ ሰዎች « ኢዲዩና ፊውዳል..» በሚል ባዶ 6 ተብሎ ይጠራ በነበረው እስር ቤት ተሰቃይተው እንዲገደሉ የተደረጉት በብስራት አማረ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮቹ ከዚህ በተጨማሪ የድርጅቱን በርካታ አባላት እንዳስገደለ አያይዘው ገልፀዋል። እነተክሉ ሃዋዝ በዚህ ወንጀለኛ ከተገደሉት ይጠቀሳሉ ሲሉ ያክላሉ።

በ1983ዓ.ም ሕወሐት/ኢህአዴግ አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ የሟቹ የደህንነት ሹም ክንፈ ገ/መድህን ምክትል የነበረው ብስራት አማረ ከቤተ መንግስት የጃንሆይ የነበረ ከፍተኛ ወርቅ በመዝረፍ መውሰዱን ያጋለጡት ምንጮቹ በዚህ የዘረፋ ወንጀል ሆለታ እስር ቤት እንዲገባ መደረጉን ያመለክታሉ። በነስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ ትእዛዝ እንዲፈታ ተደርጐ ወደ አሜሪካ የተሸኘው ብስራት አሜሪካ ሲጓዝ የዘረፈውን ወርቅ ይዞ እንደነበረ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ምንጮች በግርምት ይገልፃሉ። ብስራት አማረ አሜሪካ ከመጣ በኋላ ቅርስ የሆኑትንና የዘረፋቸውን ወርቆች መሸጡንና አንዲት ሴት ለማሻሻጥ የተቀበለችውን 1ኪሎ ወርቅ ከወሰደች በኋላ እንደካደችው ማወቅ ተችሎዋል። ብስራት አማረ ስለዚሁ ጉዳይ ተበሳጭቶ የነገራቸው ምንጮች ማረጋገጫ ይሰጣሉ።

የብስራት ታናሽ ወንድም የሆነውና በደህንነት ቢሮ ይሰራ የነበረው ታጋይ ጠስሚ (ጠስሚ -ትርጉሙ ቅቤ ማለት ነው) ከስራው በመልቀቅ የአስመጪና ላኪነት ትልቅ ቢዝነስ መክፈቱን የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም፥ ድርጅቱ የተከፈተው ብስራት አሜሪካ ከገባ በኋላ በላከለት ገንዘብ መሆኑን አስታውቀዋል። (ስለዚሁ ጉዳይ በ1995 ዓ.ም በኢትኦጵ ጋዜጣ መረጃው ይፋ መደረጉና የብስራት ወንድም ቅቤ ኢትኦጵ ቢሮ ድረስ በመምጣት የጋዜጣውን አዘጋጅ በድንጋጤ ተውጦ “የራሴን ቢዝነስ ተቋም ነው፤ እነማን መረጃ እንደሚሰጧችሁ አውቃለሁ። እባካችሁ የእኔንም፣ የወንድሜንም ስም አታንሱ?” በማለት ተማጽኖ አቅርቦ ነበር።)

ብስራት አማረ ከሽማግሌው ስብሃት ነጋ ጋር ባለው የጠበቀ ግንኙነት ወደ ኢትዮጵያ ሲመላለስ መቆየቱን ያወሱት ምንጮቹ፣ ወንጀለኛውና ዘራፊው መቀሌ ሄዶ አስገደ ገ/ስላሴን እንደከሰሰ አስታውቀዋል። የደርግ ወንጀለኞች ከአሜሪካ በገዢው ፓርቲ እየተወሰዱ ነገር ግን የኢ.ህ.አ.ፓ አባላትንና ሌሎች ንጹሃን ዜጎችን በጅምላ የፈጀና የአገር ቅርስ የዘረፈ ወንጀለኛ ጠያቂ ማጣቱ አስገራሚ ነው ብለዋል ምንጮቹ። ጠያቂ አካል ካለ በወንጀለኛው ብስራት አማረ ላይ ለመመስከር ፈቃደኛ መሆናቸውን አክለዋል። ይህን ምስክርነትና ማረጋገጫ ሊሰጡ የሚችሉና በአሜሪካ የሚኖሩ ሶስት የቀድሞ የሕወሐት ሹሞች እንዳሉና የብስራትን ወንጀል ጠንቅቀው የሚያውቁ መኖራቸውን አያይዘው ጠቁመዋል።
===ከኢየሩሳሌም አርአያ ከኢየሩሳሌም አርአያ ከኢየሩሳሌም አርአያ ===

ዘወትር ቅዳሜ ማታ ከደሳለኝ መኮንን ጋር፣ምርጥና አዳዲስ የካንትሪ ማለትም የአሜሪካ አገር ሰብእ፣ የሮክ፣ተሶል፣የፖፕ፣የአር-ኤን-ቢ፣ብሉዝ፣የሬጌና የሂፕ-ሃፕ ዜማዎችን እንዲያደምጡ ተጋብዘዋል።

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ግምገማ

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ያተኮረ ውይይት ጄኔቭ ስዊትዘርላንድ ውስጥ ዛሬ ተካሂዷል ። የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ባዘጋጁት በዚሁ ውይይት ላይ በኢትዮጵያ ይፈፀማሉ የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በዝርዝር ቀርበዋል።

Image

መንግሥት የሰብዓዊ መብት አያያዙን እንዲያሻሽል ያግዛሉ የተባሉ ሃሳቦችም ተሰንዝረዋል ። በስበሰባው ላይ የተካፈሉት የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች ለተሰነዘሩት ወቀሳዎች የበኩላቸውን መልስ መስጠታቸው ተገልጿል ። በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ያተኮረው ውይይት ዛሬ የተደረገው ከ25,ተኛው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጉባኤ ጎን ለጎን ነው ። የውይይቱ ዓላማም በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ያተኮረ ዝርዝር ዘገባ ለተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በመጪው ግንቦት ከመቅረቡ አስቀድሞ ስለሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው ። ስበስባውን ካዘጋጁት ዓለምዓቀፍ ድርጅቶች አንዱ መቀመጫውን ጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪቃ ያደረገው ሲቪኩስ የተባለው ድርጅት የፖሊሲና የጥብቅና ጉዳዮች መኮንን ቶር ሆድንፌልድ ስብሰባው በተለይ በሶስት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መወያየቱን ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።

ከነዚህም እጎአ በ2009 ዓም የወጣው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራት ህግ አንዱ ነው ። ህጉ ከባድ ተፅዕኖ ማሳደሩና መዘዞቹም በውይይቱ መነሳታቸውን ሆድንፌልድ ገልፀዋል ። « በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ መብት ለሚታገሉ ድርጅቶች በሚለገሰው ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ እርዳታ ላይ በተጣሉትን ገደቦች ላይ ተነጋገግረናል በዚህ ህግ ምክንያት በኢትዮጵያ ዓለም ኦቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች አይሰሩም ። በርካታ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶችም ከሰብዓዊ መብት ጋር የተገናኙ ሥራዎች ማካሄድ አቁመዋል ወይንም ከነጭራሹ ተዘግተዋል »

መድረኩ ትኩረት ሰጥቶ የተወያየበት ሌላው ጉዳይ ደግሞ ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት ላይ ያደርጋል የተባለው ጫና ነበር ።

«ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከተገቢው የህግ ሂደት ውጭ እንዲሁም በልዩ ደንቦች ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት ላይ የተጣሉትን ገደቦችም በውይይቱ ተነስተዋል ። በተለይ ስብሰባው በኢትዮጵያ 12 ጋዜጠኞች በቨረ ሽብሩ ህግ ምክንያት መከሰሰሳቸውኢትዮጵያ ውስጥ በህጋዊ መንገድ የጋዜጠኝነት ተግባራቸውን ሲያከናውኑ ርዕዮት ዓለሙና እስክንድር ነጋ የመታሰራቸውም ጉዳይ ላይም ትኩረት ሰጥቶ ተነጋግሯል ።

ሆድንፌልድ እንደሚሉት በውይይቱ በኢትዮጵያ የነጻ ሚዲያ መገደብም ተነስቷል ። በጎርጎሮሳውያኑ 2012 5 ጋዜጦች መዘጋታቸው በአሁኑ ሰዓትም ኢንተርኔ ት ከሚጠበቀው በላይ ቅድመ ምርመራ ይካሄድበታል ዓለም ዓቀፍ መገናኛ ብዙሃንንና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን የሚያነሱ ድረገፆች በኢትዮጵያ እንዳይሰሙና እንዳይታዩ በመንግሥት ይታገዳሉ ሲሉ ተወያዮቹ መገለፃቸውን ተናግረዋል ሆድንፌልድ የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ መብት አያያዙን እንያሽሽልም ሃሳቦች ተሰንዝረዋል ።

« የ2009 ዓም የበጎ አድራጎት ና የሲቪክ ማህበራት መተዳደሪያ ደንብ እንዲሰረዝ ወይም እንዲሻሻል ሁለተኛ የፀረ ሽብር ህግ በደል መፈፀሚያና ጋዜጠኖችን ማፈኛ እንዳይሆን እንዲሰረዝ በፀረ ሽብሩ ሕግ ምክንያት የታሰሩ ጋዜጠኞችና የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች በሙሉ እንዲፈቱ እንዲሁም ተቃዋሚዎችና ሰላማዊ ሰልፈኞች ከሚቀጥለው ዓመት ምርጫ በፊት የመሰብሰብ መብታቸውን እንዲጠቀሙ እንዲደረግ ሃሳብ ቀርቧል ።»

ዶቼቬለ ስለ ውይይቱ ና ስለተሰጡት አስተያየቶች የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮችን ለማነጋገር ያደረገው ሙከራ አልተሳካም ። ሆኖም በውይይቱ ላይ የተካፈሉት የሰብዓዊ መብት ተመራማሪው አቶ ያሬድ ኃይለ ማርያም ያኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮችለመድረኩ የሰጡትን አስተያየት አጋርተውናል ።

http://www.dw.de/%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1% … a-17495793

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የጀርመን ፍርድ ቤት ዛሬ ተገቢዉን ግብር ሳይከፍሉ በማጭበርበር በተከሰሱት የባየር ሙኒክ የእግር ኳስ ቡድን ሥራ አስኪያጅ ዑሊ ሆነስ ላይ የ3 ዓመት ተመንፈቅ እስራት በየነ።

ወያኔ/ኢሕአዴግ ጥሩምባ ነፍቶ የብሔሮች፣ የብሔረሰቦችና የሕዝቦች ነጻነት ብሎ ከአወጀና ሁሉንም ለሃያ ሁለት ዓመታት በተስፋ ከአስፈነደቀ በኋላ ችግር ተፈጠረበት፤ ችግሩ ምንድን ነው? ችግሩ የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች የሚባለው ነው፤ ችግሩ አፍ ከሚችለው በላይ ለመጉረስ ከራስ ጋር መተናነቅ ሆነ፤ ችግሩ የማሰብ ድርቀት ነው፤ ችግሩ ከአሜሪካና ከአውሮፓ መንግሥታት ጀምሮ እስከቀበሌ መዋቅር ያሉትን ሁሉ በአንድ ዘዴ እያባበሉና እያታለሉ ማደናበር ነው፤ ችግሩ በሃያ ሁለት ዓመታት ውስጥ ዘዴው ሻግቶ ዓላማው ደብዛው መጥፋቱ ነው፤ ቸግሩ የዘዴው መሻገትና የዓላማው መክሸፍ መጋለጡ ነው፤ ችግሩ ወያኔ የተቀመጠበት የሥልጣን ወንበር መቆርቆር መጀመሩ ነው።

የግለሰብ ነጻነት ታፍኖ የጎሣ ነጻነት መታወጁ ፋይዳ እንዳላመጣ ታየ፤ የግለሰብን ነጻነት ለመደፍጠጥ ሲባል የጎሣዎች ነጻነትም አብሮ ተደፍጥጦ ነበር፤ ይህንን አስቀድሞ ለማየት ለምን ሳይቻል ቀረ? የሚል ጠያቂ ከመጣ መልሱ ቀላል ነው፤ በሚልዮኖች ብር እየወጣ መንገድ ሲሠራና አስፋልት ሲለብስ ቆይቶ ከጥቂት ወራት በኋላ የባቡር ሀዲድ ለመዘርጋት ተብሎ የተሠራውን አስፋልት የለበሰ መንገድ ማፍረስ እንዳስፈለገ አይተናል፤ የባቡሩ ጉዳይ ለምን አስቀድሞ አልታየም? የጎሣን ነጻነት ለማጉላት ሲባል የግለሰብን ነጻነት መደፍጠጡ ዞሮ ዞሮ የጎሣውንም ነጻነት አንደሚደፈጥጠው ያልታየበት የተለየ ምክንያት የለውም፤ አሰቀድሞ አለማየት የባሕርይ ነው፤ በተጠቀሱት ምሳሌዎች ሁለቱም ዋጋ ያስከፍላሉ፤ ልዩነቱ የአንዱ ዋጋ የሚከፈለው በፖሊቲካ ኪሳራ ሲሆን፣ ሌላው የሚከፈለው በኢኮኖሚ (በሀብት) ኪሳራ ነው፤ ሆኖም የፖሊቲካውም ሆነ የሀብቱ ኪሳራ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በሙሉ ያለምንም የጎሣ ልዩነት ሲጫንበትና ችጋር ሲያንዣብበት በሥልጣኑ ወንበር ላይና በዙሪያው የሚንሳፈፉት ፈጣሪዎቹ ናቸውና የችግሩ ሸክም ሲያልፍም አይነካቸው! እንኳን ለፖሊቲካና ለሀብት ኪሳራ ለሕይወት ኪሳራም ቢሆን የማይጠየቅ መሆኑን በምክር ቤት በሚባለው ውስጥ በድፍረት የተነገረበት አገዛዝ ነው።

የትግራይ ሕዝብ የአገዛዙ ጉልበትና የጥቅም ተካፋይ ነው እየተባለ እስቲያምመው ድረስ በሐሜት ተለበለበ፤ የሚናገርለት ቡድንና የሚናገርበት መድረክ ሳያገኝ ሃያ ሁለት ዓመታት ያህል ኢትዮጵያዊ ትእግስቱን አሳየ፤ ዛሬ አረና የሚባለው የትግራይ የፖሊቲካ ቡድን ወያኔ ለብቻው በትግራይ ሲቆጣጠረው የቆየውን የፖሊቲካ መድረክ ለመጋራት ፊት ለፊት በሰላማዊ የፖሊቲካ ትግል እየተጋፈጠው ነው፤ ይህ አዲስ ሁኔታ በትግራይ ብቻ ሳይሆን በመላ ኢትዮጵያ የፈጠረውንና ሊፈጥር የሚችለውን የፖሊቲካ እንቅስቃሴ እንኳን ሌሎች በሩቅ የሚከታተሉ ወያኔዎችም ገና አልገባቸውም፤ በፖሊቲካውም ሆነ በኢኮኖሚው አገዛዙ ችግርን አስቀድሞ የማየት ብቃት እንዳላሳየ ከላይ በተጠቀሱት ምሳሌዎች አረጋግጠናል፤ ስለዚህም አገዛዙ በትግራይ የገጠመውን ሰላማዊ ፉክክር ለመቋቋም አዲስ ዘዴ አላገኘም፤ እስካሁን በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች እንደተደረገው ሁሉ በትግራይም ተቀናቃኞቹን በእስርና በዱላ ለማገድ እየሞከረ ነው፤ ሌላ ዘዴ ገና አላገኘም፤ የሚፈልግም አይመስልም፤ በዱላ መጠቀም ሲለመድ አንጎል ይደነድናል፤ ወገንን ጠላት ያደርጋል፤ ወገን ጠላት ከሆነ ማን ወዳጅ ሊሆን ነው? ትልቁ አደጋ ይህ ነው።

መሠረታዊ ችግርም አለበት፤ በእውነተኛ የጎሣ ፖሊቲካ ውስጥ የማይታዩ ነገሮች እየተከሰቱ ነው፤ በአንድ ጎሣ ውስጥ ከባድ የሆነ የአስተሳሰብ ልዩነት፣ የሥልጣን ክፍፍልም ሆነ የሀብት ልዩነት ጎልቶ ሲወጣ የጎሣው ሥርዓት መክሸፉንና መምከኑን ያመለክታል፤ መስታወት ሆኖ የመሠልጠንና የመለወጥ ልዩነት የሚታየው በዚህ ጊዜ ነው፤ መሠልጠን የማይለውጣቸውን ሰዎች መማር ይለውጣቸዋል፤ ከማትጊያ ጋር በሚሰጥ የቡድን መመሪያ የሚሠሩትን ሰዎች በግል ማንበብና ማሰብ ይለውጣቸዋል፤ ይህንን የማይቀርና ሊታገድ የማይችል የለውጥ አቅጣጫ ማየት የማይችሉ ለዛሬ እንጂ ለነገ የሚኖሩ አይደሉም፤ በትግራይ በመታየት ላይ ያለው የነጻ ሰዎችን፣ የነጻ ግለሰቦችን አስተሳሰብ የሚገልጽ አንቅስቃሴ ለትግራይ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ነው፤ የመንጋ አስተሳሰብን ለመረዳት ፌስቡክን ማጥናት ነው፤ የወያኔ የካድሬ ሠራዊት በሻገተው አስተሳሰቡ (መለስ ዜናዊ በጸያፍ ቃላት ገልጾታል፤) እያየው በዚያው በለመደውና ባስለመዱት የዱላና የጉልበት ዘዴ ሊያመክነው እየጣረ ነው፤ ወጣቶቹ ግን እየተደረገ ያለውን በአለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት ከተጫነባቸው የተስፋ ክምር ጋር እያስተያዩ ማን እንደጠገበና ማን እንደተራበ ያያሉ፤ ያመዛዝናሉ፤ አቅዋማቸውንም ያስተካክላሉ፤ የትግራይ ወጣቶች የፖሊቲካ ንቃትና ነጻ አስተሳሰብ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ወጣቶች ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽእኖ የወያኔ ካድሬዎች አስበው ሊደርሱበት አይችሉም፤ የተለመደው አስቀድሞ አለማየት አወዳደቅን የሚጎዳ፣ የሚያስከፋና የሚያሳፍር ያደርገዋል!

የጭቆና ሠራዊት እንዲሆን የሚሠለጥነው የካድሬ ሠራዊት ጸረ-ማሰብ ነው፤ አስቦ ሳይሆን ለትእዛዝና ለሆዱ የሚገዛ ነው፤ ከላይ እስከታች በአንድ አስተሳሰብ ብቻ የሚንቀሳቀስ በመሆኑ የአገር ጉዳዮችን ለሕዝባዊ ሙግት አይከፍትም፤ ስለዚህም ሀሳቡ አይናፈስም፤ ስለዚህም አስተሳሰቡ የጊዜ መጫወቻ ይሆናል፤ ይሻግታል፤ ጸረ-ማሰብ ሆኖ ከመሻገት መዳን አይቻልም፤ መለስ ዜናዊ ይህንን በደንብ ያውቅ ነበር! ዛሬ እነኮኸንና እነሺን (ኮኸን በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ውስጥ የአፍሪካ ክፍል ኃላፊ የነበረ ሲሆን ሺን ደግሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ነበር፤) በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ የሚናገሩት በኤርትራና በሶማልያ ላይ የተነደፈው መመሪያ አልሠራምና እንደገና መፈተሽ አለበት እያሉ ነው፤ እነዚህ ሰዎች የሚናገሩት የማንን መሠረታዊ ጥቅም ለማራመድ ነው? በጊዜው ጥያቄውን ለመመርመርና በትክክል ለመመለስ ካልተቻለ በሚቀጥሉት ሁለትና ሦስት ዓመታት የአፍሪካ ቀንድ ሁኔታ ሲለዋወጥ የኢትዮጵያ አገዛዝ ይጨማደድና ብዙ ባዶ ቀፎዎችን ይዞ ይቀራል።

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ያተኮረ ውይይት ጄኔቭ ስዊትዘርላንድ ውስጥ ዛሬ ተካሂዷል ። የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ባዘጋጁት በዚሁ ውይይት ላይ በኢትዮጵያ ይፈፀማሉ የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በዝርዝር ቀርበዋል።

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ባለቀለም ፊልም በሆነው «ጉማ» በተሰኘው የሚሸል ፓፓታኪስ ፊልም ስም የተሰየመው የፊልም ስራ ሽልማት ለመጀመሪያ ጊዜ በብሄራዊ ቴአትር ባለፈው ሰምወን እለት ምሽት በድምቀት ተከናውኗል።

የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የዩክሬይንን የሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚንስትር አርሴኒ ያዜንዩክ ትናንት በዋይት ሀውስ ቤተ መንግሥት ተቀብለው አነጋገሩ። ግዛቷ ክሪሚያ በሩስያ የተያዘባትን ዩክሬይን ዩኤስ አሜሪካ እንደምትደግፍ ኦባማ ለያዜንዩክ አረጋገጠዋል።

የካቲት 30 ቀን 20006 ዓ.ም በታሪካዊቷ የሐረር ከተማ በጀጎል ሸዋበር በደረሰው ቃጠሎ እና ከዚያም በኋላ የክልሉ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ በዜጎች ላይ ጉዳት መድረሱ የፓርቲያችንን አመራሮች፣ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ያሉ አባላትና ደጋፊዎችን በእጅጉ አሳዝኗል፡፡ ምንም እንኳን የቃጠሎው መንስኤ ተጣርቶ ይፋ ያልተደረገ ቢሆንም በጀጎል ሸዋ በር እየደረሰ ያለው ተደጋጋሚ ቃጠሎ ድንገቴ ነው ለማለት የሚያስደፍር አይደለም፡፡ […]

አንድነት ን በተመለከተ ============= አንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ ወይም አንድነትን በተመለከተ የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነቱ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው በበኩላቸው ተጠይቀው በቅድሚያ ፓርቲያቸው በምርጫ የሚያምን ፓርቲ እንደመሆኑ ሕዝቡ ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ ተጠቃሚ መሆን አለበት ብሎ እንደሚያምን ገልፀዋል። ለ2007ቱም ምርጫ ፓርቲያቸው የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች እያደረገ መሆኑን፣ የመጀመሪያው ፓርቲው የቆመለትን ፖሊሲ ለሕዝብ ለማቅረብ በሚመች መልኩ የአማራጭ ፖሊሲ ትንተና […]

የፖለቲካ ምህዳር መስፋት፣ የ2007 ምርጫ፣ የታሳሪዎች ጉዳይ በአጀንዳነት ተነስቷል በአውሮፓ ኅብረት የአፍሪካና የኢትዮጵያ ቋሚ አምባሳደር የኢትዮጵያ መንግስትንና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን እያነጋገረ ነው። የኅብረቱ ቋሚ አምባሳደር አማካኝነት መካሄድ የጀመረው ውይይት በሀገሪቱ የፖለቲካ መህዳር መስፋት፣ በ2007ቱ ምርጫ፣ ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች እንዲሁም በሀገሪቱ ስላለው የሰብአዊና የዴሞክራሲ መብቶች ዙርያ መሆኑ ታውቋል። ባለፈው ዓመት የኅብረቱ ቋሚ አምባሳደር በመሆን […]

“ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ” ማለት ይሄ ነው፡፡
ለጋራ ጥቅማችን ብሎ ለራሱ ከሚጠቀምብን ያድነን፡፡ ከሃዲዎች የዕጣ-ፈንታቸዉን ያገኛሉ::

ተነስ ሲሉት የሚነሳ፣ ተኛ ሲሉት የሚተኛ …” ዞሮ ዞሮ ወዶ-ገባ ያሉትን መፈፀም ግዴታው ነው፡፡ ወዶ-ገባ ዝርያው ብዙ ነው፡፡ የፖለቲካ ወዶ-ገባ አለ፡፡ ፖለቲካው ምንም ይሁን ምንም ለጥቅሜ እገባበታለሁ ይላል፡፡ የኢኮኖሚ ወዶ-ገባ አለ፡፡ ኢኮኖሚው ምንም ይሁን ምን ሆዴን እሞላበታለሁ ይላል፡፡ የማህበራዊ ወዶ-ገባ አለ፡፡ ከማናቸውም ማህበራዊ ቀውስ እኔ ጥቅሜን ካካበትኩ ያሉኝን አደርጋለሁ ባይ ነው፡፡ ብልህ ሰው የውሾቹን ዓይነት ዕጣ-ፈንታ ያስተውላል፡፡ አበሻ፤ “አብዶም ሠግዶም ውሉን አይስትም” የሚል አባባል አለው፡፡ ይሄንንም ልብ-ልንበል፤ የህግ-ወዶ-ገባም አለ፡፡ በፍትሕ ሽፋን ጥቅሙን የማያጋብስ፡፡

አገርን የሚያጠፋ ማንኛውም ጥፋት ጥፋት ነው፡፡ ሚሥማርም አቀበልን ድንጋይ ያው ነው፡፡ በወገናዊነት ላንድ ቡድን መጠቀሚያ አመቻቸንም፣ በሙስና ውስጥ ተዘፈቅንም፤ ዞሮ ዞሮ “ጌታ ተሰቅሏል”፡፡ አገርና ህዝብ በድለናል፡፡ እገሌ አድርግ ብሎኝ ነው እንጂ እኔ በራሴ አላደርገውም ነበር ማለት የኋላ ኋላ ከተጠያቂነት አያድንም፡፡ በሥርዓቱም ማሳሰብ በግልና በቡድን ከሠራነውና አንዱን የእናት ልጅ፣ አንዱን የእንጀራ ልጅ አድርገን ካጠፋነው ጥፋት ተጠያቂነት አያድንም፡፡ ሰው ሰውን መበዝበዙ ነው ሀቁ፡፡ ፊት ለፊቱም ግልባጩም ያው ነው እንደ ማለት ነው፡፡

ስለዚህ ሥርዓት ሰበብ አይሆንም፡፡ ዕውነቱ ሰው ሰውን መበዝበዙ ነው፡፡ ሊበራል፣ ኒዮ ሊበራል፣ አብዮታዊ፣ ኮሙኒስታዊ፣ ፋሽስታዊ፣ ቦናፓርቲዝማዊ፣ ልማታዊ፣ ሉአላዊ፣ ፀረ-ሽብራዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ኢጋዳዊ፣ … ሁሉም የሰውና ሰው ተቃርኖና ፍጭት መልኮች ናቸው፡፡ ዋናው ከህዝብና ከሀገር ጥቅም አኳያ ምን ይመስላሉ ተብሎ መመርመር ያለባቸው ናቸው፡፡ የሰውና ሰው ግንኙነት የጨቋኝና ተጨቋኝ፣ የወገናዊና ኢወገናዊ፣ የፍትሐዊና ኢፍትሐዊ፣ ወይስ ቡድናዊና ኢቡድናዊ? ምን ይመስላል፡፡ የሳንቲሙ ገፅ ምን ዓይነት ነው? ዘውድ? ጎፈር? ወይም በሠያፍ የቆመ? መፈተሽ አለበት፡፡

አንዱ ለአመራሩ ሚሥጥር ቅርብ በመሆኑ አስቀድሞ ኢንፎርሜሽን ያገኛል፡፡ ቤቱን ከውርስ ያድናል፡፡ ሌላው ለኢንፎርሜሽኑ እሩቅ ነውና ላዩ ላይ ይታወጅበታል፡፡ ለብዙሃኑ ጥቅም ሲባል ጥቂቶቹ ቢጎዱም ምንም አይደለም የሚለውም አስተሳሰብ መመርመር ይኖርበታል፡፡ የአብዮቱ ጦስ ይሁን የካፒታሊዝም ጦስ ባልለየበት አገር አዋጆችና መመሪያዎች ሲከለሱ ማየት ቢያንስ ያስገርማል፡፡ አቀንቃኙ Protagonist እና ተቃራኙ antagonist በቀላሉ አይለዩም፡፡ ከሥልጣን ይባረራሉ፡፡ ተባራሪዎቹ ያወጡት ህግና መመሪያ ምን እንደሚሆን ዕጣ-ፈንታው አይታወቅም፡፡ ከሁሉም ይሰውረን! ህዝብ ብቻ ግራ እንደተጋባ ይቀጥላል፡፡ “ሰው ይጫኑብህ ግንድ? ቢሉት፤ ግንድ ከተጫነኝ ሰው ያነሳልኛል፣ ሰው ከተጫነኝ ማን ያነሳልኛል፤ አለ” የሚባለው ግራ-ገብ ዘመንን የሚያመላክተን ነው፡፡ ከዚህም ይሰውረን! ከሚጫነን ይገላግለን፡፡ ከወዶ-ገባነት ይቅር ይበለን!!#MinilikSalsawi

አገራችን ኢትዮጵያ ያለችበትን አሳዛኝ ሁኔታ ከማንም የበለጠ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይረዳዋል ብለን እናምናለን። የኢሕአዴግ መንግስት፣ ላያ ላዩን «በዴሞክራሲ አምናለሁ» ቢልም፣ ፍጹም አምባገነን በሆነ መልኩ ፣ ሕዝቡን አፍኖ፣ እያሰራ፣ እየገደለ፣ ዜጎችን እያፈናቀለ፣ ከሃያ አመታት በላይ ቆይቷል። በአብዛኛዉ ሕዝብ ዘንድ እየተጠላ፣ ይሄን ያህል አመት በስልጣን መቆየት የቻለው፣ አገዛዙ በዋናነት ኢትዮጵያዊያን መከፋፈል በመቻሉና ዜጎች ደፍረው ለመብታቸው እንዳይቆሙ በፍርሃት እንዲተበተቡ በማድረጉ ነው። ይሄንን ለማስቆም ሕዝቡን ማስተባበርና ማደራጀት ቀዳሚና ብቸኛ አማራጭ ነው።

አገር ቤት በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ በርካታ የፖለቲካ ድርጅቶ አሉ። ከነዚህ ድርጅቶች መካከል አንዱ የአንድነት ፓርቲ ነው። የአንድነት ፓርቲ «የሚሊዮኖች ድምጽ ለፍትህ» እና «የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት» በሚል ሰላማዊ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ተዘጋጅቷል። ይህ እንቅስቃሴ የአንድ ፓርቲ እንቅሳቅሴ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንቅስቃሴ እንደመሆኑ፣ በአገራችን ዴሞክራሲና የስርዓት ለዉጥ እንዲመጣ የሚፈልጉ ዜጎች ሁሉ ሊቀላቀሉት፣ ሊደግፉት፣ የራሳቸው ሊያደርጉት የሚገባ እንቅስቃሴ ነዉ። ይህ እንቅስቃሴ የሚሊዮኖች እንቅስቃሴ ነው። የእያንዳንዳችን እንቅስቃሴ ነው።

በቅርቡ በባህር ዳር አስደናቂ ሰልፍ መደረጉ ይታወሳል። በቦታዉ የተገኙ ወገኖች ድምጻቸውን ያሰሙት አንድን ፓርቲ ብለው አልነበረም። ኢትዮጵያን ብለው ነዉ እንጂ። የባህር ዳሩ ሰልፉ ያማከለው በአንድ ድርጅት ዙሪያ አልነበረም። ነገር ግን በኢትዮጵያ ዙሪያ እንጂ። ይህ በባህር ዳር የተደረገውን አይነት የነጻነት እንቅስቃሴ በተጧጧፈ መልኩ በመላው አገሪቷ ማድረጉ አስፈላጊ ነው።

በአገሪቷ ሕገ መንግስት አንቀጽ 30 መሰረት፣ የዜጎች የመሰባሰብ ፣ በሰላም ትእይንተ ሕዝብ የማድረግ ሙሉ መብት የተረጋገጠ ነው። በመሆኑም ይህ የሚሊዮኖች ለነጻነት ንቅናቄ ሰላማዊና የአገሪቷ ሕግ በሚፈቅደው መሰረት የሚደረግ በማንም ዜጋ ወይንም ቡድን ላይ ያላነጣጠረ፣ የተወሰኑትን ጠቅሞ ሌላዉን የሚጎዳ ያልሆነ፣ በዘር፣ በሃይማኖት፣ በመደብ፣ በጾታ ልዩነት ሳያደርግ፣ ኢትዮጵያዉያንን በሙሉ ለፍትህና ለነጻነት ለማሰባሰብና ለማንቀሳቀስ ታሰቦ የታቀደ እንቅስቃሴ ነው።

በዳያስፖራ ያለው ማህበረሰብም የኢትዮጵያ ሕዝብ አካል እንደመሆኑ፣ የድርሻዉን መወጣት ይጠበቅበታል። በመሆኑም ይሄን የሚሊዮኖች ድምጽ ወይንም በባህር ዳር የተደረገዉን አይነት እንቅስቃሴ በሌሎች ከተሞች እንዲደረግ ለመርዳትና ለማጠናከር፣ የዳያስፖራ የሚሊዮኖች ድምጽ ግብረ ኃይል ተቋቁሟል። ይህ ግብረ ኃይል በዳያስፖራ ባሉ የአንድነት ፓርቲ ድጋፍ ማህበራት አነሳሽነትና በዉጭ ካሉ የአንድነት ፓርቲ ድጋፍ ማህበራት በተጨማሪ፣ ከተለያዩ የሲቪክ ማህበራት፣ አገር ቤት የሚደረገዉን ሰላማዊ ትግልን በሚደገፉ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሲቪክ ማህበራት ፣ ፓልቶክ ክፍሎችና ግለሰቦች ተባባሪነት፣ «እኛም የሚሊዮኖች አንዱ አካል ነን» እያሉ ቀናና የሚያኮራ ኢትዮጵያዊ ምላሽ እየሰጡ ያሉና ለመስጠትም የተዘጋጁ፣ በአለም ዙሪያ ሁሉ ያሉ ኢትዮጵያዉያንን ለነጻነትና ለፍትህ ለማሰባሰብ የተዋቀረ ነው።

የሚሊየነሞች ንቅናቄ አዲስ አበባ እና ድረደዋ አስተዳደሮችን ጨምሮ፣ በኦሮሚያ የአዳማ፣ የላፍቶና የነቀምቴ ከተሞችን፣ በደቡብ ክልል፣ የአዋሳ፣ የጂንካና የቁጫ ወረዳዎችን፣ በትግራይ ክልል የመቀሌ ከተማን፣ በአማራዉ ክልል ደሴ፣ የወልዲያ፣ ደብረ ታቦር ፣ ደብረ ማርቆስ እና በምእራብ አርማጭሆ የአብርሃ ጅራ ከተማን ፣ በቤኔሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳን ከተማ፣ በጋምቤላ ክልል የ ጋምቤላ ከተማ የሚያዳርስ ይሆናል።

የሚሊየምን እንቅስቃሴን በተመለከተ በየጊዜዉ ወቅታዊ መግለጫ የምንሰጥ መሆናችንን እየገለጽን። በዉጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ እንደከዚህ በፊቱም ታላቅ ድጋፉን እንዲያበረክት በአክብሮት እንጠይቃለን። አገራችን ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ አገር ናት። ለአገራችን መነሳታችን ሊያስከፋ የሚችለው፣ ወይንም ዝምታን ተስፋ ቆርጠን መቀመጣችን ሊያስደስት የሚችለው አምባገነኖችን ብቻ ነው። በሕዝባችን ላይ ግፍ የሚፈጽሙ አይደሰቱ። እንነሳ። የድርሻችንን እንወጣ። ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁን !

በምትኖሩበት ከተማ ተደራጅታችሁ፣ ከዚህ ግብረ ኃይላ ጋር በመስራት በአገር ቤት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ስፖንሰር ማድረግ የምትፈልጉ በሚከተሉት አድራሹ ሊያገኙን ይችላሉ

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !

[email protected]
404- 518-7858

“ዳውድ ኢብሳ ሲሞት ጥሩኝ” በሚል ርዕስ በለጠፍኩት አነስተኛ ሐተታ ላይ ሁለት ዓይነት ተቃውሞዎች ቀርበውብኛል፡፡ አንደኛው “ኦነግ በአማራው ላይ የሰራውን ሴራ እና ሸፍጥ እያወቅክ ጥብቅና ቆመህለታል” የሚለው ሲሆን ሁለተኛው “የኦፒዲኦን ድርጅታዊ ህልውና አንኳሰስክ፤ አቶ አለማየሁንም ረገጥክ” የሚል ነው፡፡ ስለ ኦፒዲኦ የጻፍኩት አዲስ ነገር አይደለም፡፡ የድርጅቱ አባላት እራሳቸው በየአጋጣሚው የሚናገሩትን ነው በፌስቡክ የደገምኩት፡፡ በተለይ ደግሞ አባላቱ ከስራቸው ሲባረሩ፣ ወይ ደግሞ ከድርጅቱ ከድተው ወደ ውጪ ሀገር ሲኮበልሉ “ኦፒዲኦ የኦሮሞን ህዝብ ለማጭበርበር ሆን ተብሎ የተፈጠረ ድርጅት ነው” የሚል ጩኸት በማሰማት ነው የሚታወቁት፡፡ እነ ዮናታን ዲቢሳ፣ ዱባለ ጃሌ፣ ኢብራሂም መልካ ሲያደርጉት የነበረው ይህንኑ ነው፡፡ ነገር ግን እኔ የነርሱን ፈለግ በመከተል አይደለም እንዲያ ብዬ የጻፍኩት፡፡ ከነርሱ በፊትም እንደዚያ ስል ነበር፡፡
——
ኦነግን ለመጀመሪያ ጊዜ ካየሁበት ግንቦት 1983 ጀምሮ የድርጅቱን የፖለቲካ መስመር ስደግፍ ቆይቻለሁ፡፡ ዩኒቨርሲቲ ስገባ ግን ድርጅቱ በሚያራምደው ርዕዮተ ዓለምና በፖለቲካ ፕሮግራሙ ላይ ጥያቄዎች ማንሳት ጀመርኩ፡፡ በዋነኛነትም “የመገንጠል ፖለቲካው የኦሮሞን ጥያቄ የትም አያደርሰውም” የሚል ሀሳብ አነሳሁ፡፡ እንዲሁም የሚከተላቸው ስትራቴጂዎቹ ፍጹም ሊዋጡልኝ አልቻሉም፡፡ በዚህም ከኦሮሞ ወንድሞቼ ጋር ብዙ ጊዜ እነታረክ ነበር፡፡ በተለይም በዚያ ጊዜ ኦነግን መተቸት Taboo ተደርጎ ይቆጠር ስለነበር ከቅርብ ጓደኞቼ ጭምር እስከመጣላት ደርሰናል፡፡ እናም ከ1990 ጀምሮ የድርጅቱ ተቃራኒ እንጂ ደጋፊ አይደለሁም፡፡

እንዲህ በመሆኑ ግን ድርጅቱን በሐሰት መክሰስ ያለብኝ አይመስለኝም፡፡ ድርጅቱን በሰራው ጥፋት ብወቅሰው ማለፊያ ነው፡፡ ባልሰራው ወንጀል መክሰስ ግን ለማንም የሚበጅ አይሆንም፡፡ እንደምሳሌም ኦነግ የሚከሰስባቸውን ጭፍጨፋዎች እንመልከት፡፡ በደኖ፣ አርባ ጉጉ፣ ወተር፣ አረካ፣ አሰቦት ገዳም ወዘተ…

እነዚህ ጭፍጨፋዎች መከሰታቸው ሁላችንንም ያሳዝነናል፡፡ አንድ ቀን እውነቱን ፈልፍለን የማውጣት ግዴታም ተጥሎብናል፡፡፡ ነገር ግን በርካታ ሰዎች በሁሉም ጭፍጨፋዎች ኦነግን ተጠያቂ ሲያደርጉ በጣም እገረማለሁ፡፡ በተለይም ዛሬ በህትመት ላይ የሌሉ ሁለት የግል ጋዜጦች ይህንን ፕሮፓጋንዳ እየደጋገሙ ሲያስተጋቡት ሳይ “ስለ የትኛው ሀገር ነው የሚያወሩት” እያልኩ እደነቅባቸው ነበር፡፡ እንዲህ የምለው ጋዜጦቹ የመረጃ እጥረት የነበራቸው መሆኑን በማወቄ ብቻ አይደለም፤ የጂኦግራፊ እውቀትም ያጠራቸው ስለሚመስለኝም ጭምር ነው፡፡ ለምሳሌ “አረካ”ን እንውሰድ፡፡ ይህቺ ከተማ የት ነው ያለችው? ኦሮሚያ ውስጥ ነው? ወይስ ሌላ ቦታ?

ይገርማል! አረካ ማለት በደቡብ ክልል በወላይታ አውራጃ ከሶዶ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ ያለች ከተማ ናት፡፡ እኔ እስከማውቀው ድረስ ኦነግ እዚያ ድረስ ሄዶ ሀገር አላስተዳደረም፡፡ “አረካ የኦሮሚያ ግዛት ናት” ብሎ የሚያውቅም አይመስለኝም፡፡ እናም ጂኦግራፊን በትክክል የሚያውቅ ጋዜጠኛ የአረካውን ግጭትና ጭፍጨፋ ለኦነግ አይሰጥም ነበር፡፡ በተጨማሪም የአረካው ግጭት የደረሰው ኦነግ የሽግግር መንግሥቱን ለቆ ከወጣና በእጁ የነበሩት መሬቶች በሙሉ በኢህአዴግ ቁጥጥር ስር ከወደቁ በኋላ ነው፡፡

የአረካው ግጭት በሽግግሩ ዘመን ለነበረው የተወካዮች ምክር ቤት የውይይት አጀንዳ ሆኖ እንደቀረበ ይታወሳል፡፡ በከተማዋ ያለቁት የ31 ሰዎች ግድያ በመከላከያ ሰራዊቱ እንደተፈጸመ መንግሥቱ በይፋ አምኗል፡፡ ዳሩ ግን ለግድያው የተሰጠው ምክንያት በጣም አነጋጋሪ ነበር፡፡ መንግሥት ያቀረበው ምክንያት “ሰልፈኞቹ የተገደሉት ቦንብ በመወርወራቸው ሳቢያ የመከላከያ ሰራዊቱ ራሱን ለመከላከል በወሰደው እርምጃ ነው” የሚል ነው፡፡ ይሁንና ይህንን ምክንያት ብዙዎች አልተቀበሉትም፡፡ ብዙዎች እንደተጠራጠሩት እስከ ዛሬ ድረስ ቆይቷል፡፡ በነገራችን ላይ በአረካ የሞቱት የቀድሞ መንግሥት ወታደሮች ነበሩ፡፡ እነዚያ ወታደሮች “የጡረታ መብታችን ይከበርልን” በማለት የተቃውሞ ሰልፍ በማድረጋቸው ነው ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር የተጋጩት፡፡
——–
በሚያዚያ ወር 1984 በወተር ከተማ በተካሄደ ጭፍጨፋ የሞቱትም በተመሳሳይ መልኩ በመከላከያ ሰራዊቱ እንደተገደሉ የሽግግር መንግሥቱ በወቅቱ አምኗል፡፡ ይሁን እንጂ በወተር የተገደሉት 230 ሰዎች በሙሉ ኦሮሞዎች እንጂ አማራዎች አልነበሩም፡፡ እነዚያ ሰዎች የተገደሉት ኢህአዴግ ከከተማቸው ወጥቶ ኦነግ ወደ ከተማዋ እንዲመለስ በመጠየቃቸው ነው (ወተር ለአንድ ዓመት ያህል በኦነግ ቁጥጥር ስር ነበረች፤ ኦነግ ከከተማዋ ሲወጣ ኢህአዴግ ገብቶባታል፤ ነዋሪዎቹ “እንደ ቀድሞው ጊዜያችን ኦነግ ወደ ከተማዋ ይመለስ” በማለታቸው ነው ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር የተጋጩት)፡፡ ጋዜጦቹ ግን “ኦነግ አማራዎችን ጨፈጨፈ” እያሉ ነበር የሚዘግቡት፡፡
——-
በ1984 (ወሩን አላስታውሰውም) በአሰቦት ገዳም በተካሄደ ግድያ ሰባት መነኮሳት ሞተዋል፡፡ ይህንን ግድያ የፈጸሙትም በወቅቱ የአሰቦት ከተማን ለትንሽ ጊዜ ተቆጣጥሮ የነበረው የኦሮሞ ነጻነት እስላማዊ ግንባር (IFLO) ታጣቂዎች ነበሩ፡፡ ግድያው ስር ሳይሰድ በአፋጣኝ ያስቆሙት ደግሞ ኢህአዴግና ኦነግ ነበሩ፡፡ ሁለቱ ድርጅቶች አንድ ጥምር ኮሚቴ በማቋቋም በወሰኑት ውሳኔ መሰረት IFLO ከከተማው ተባርሮ አካባቢው በኢህአዴግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል፡፡
——
በአርባ ጉጉ የተፈጸመው እልቂት በሁለት ተጎራባች መንደሮች መካከል በተካሄደ ግጭት ነበር የተለኮሰው፡፡ እያደር ግን መርቲ ጀጁ እና አሰኮ የሚባሉ የአርባ ጉጉ ወረዳዎችን አዳርሷል፡፡ በግጭቱ የኦሮሞ እና የአማራ ተወላጆች በእኩል ደረጃ ተጎድተዋል፡፡

በአርባ ጉጉ ግጭት የራሳቸውን የፖለቲካ ትርፍ ለማጋበስ የፈለጉ ወገኖች እጃቸውን አስገብተውበታል ይባላል፡፡ በመሆኑም በውጤቱ ከሁሉም ግጭቶች የከፋ ሊሆን ችሏል፡፡ በዚህ ግጭት ከሁለቱም ወገን እስከ ስድስት መቶ ያህል ሰዎች መሞታቸው ይነገራል፡፡ ከመቶ ሺህ ያላነሰ ሰው ወደ ሀረርጌና ሸዋ ክፍለ ሀገሮች ተፈናቅሏል፡፡ ሆኖም ኦነግ በዚህ ግጭት ውስጥ እጁን ማስገባቱን የሚያረጋግጥ ፍንጭ እስከ አሁን ድረስ የለም፡፡ ኦነግ በወቅቱ በአርባ ጉጉ አውራጃ ምንም ይዞታ አልነበረውም፡፡ የመላው አማራ ህዝብ ድርጅትም ቢሆን በግጭቱ የከሰሰው ኦህዴድን (OPDO) እንጂ ኦነግን አልነበረም፡፡ በተለይም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የምዕራብ ሸዋ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ የነበረው ኮሎኔል ዲማ ጉርሜሳ ከግጭቱ ጋር ተያይዞ ስሙ በሰፊው ይነሳ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ በዚያን ጊዜ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ሐሰን ዓሊ ከእፎይታ መጽሔት ጋር (ግንቦት 1985) ባደረጉት ቃለ-ምልልስ “አቶ ዲማ ጉርሜሳ ንጹሕ ነው” በማለት ከመከላከላቸውም በላይ ለግጭቱ ዋነኛ ተጠያቂ ያደረጉት መአሕድን እንጂ ኦነግን አልነበረም፡፡

የግል ጋዜጦች ግን ነገሩን አራግበው በኦነግ ላይ አላከኩት፡፡ ነገሩን ሳያውቁት ቀርተው የተደረገ አይመስለኝም፡፡ አንዳንድ ጋዜጦች -ተከፍሎአቸው እንዲህ እንደሚያደርጉ በደንብ እናውቃለን፡፡
——–
የበደኖ ጭፍጨፋ! አዎን! ኦነግ ሊጠየቅበት የሚገባው ብቸኛው ትራጄዲ ይህኛው ነው፡፡ በርግጥም እልቂቱ በተፈጸመበት ወቅት በደኖ በኦነግ ቁጥጥር ስር ነበረች፡፡ የሞቱት ሀምሳ ያህል ሰዎች ለምን እንደተገደሉ ባይታወቅም አድራጎቱ በኦነግ ወታደሮች እንደተፈጸመ ድርጅቱ ራሱ አምኗል፡፡ ኦነግ በወቅቱ በወታደሮቹና በአዛዦቹ ላይ እርምጃ ወስጃለሁ ቢልም የተወሰደውን እርምጃ ምንነት አልገለጸም፡፡ በነገራችን ላይ በዚህኛውም እልቂት ከሞቱት መካከል ግማሽ ያህሉ ኦሮሞዎች ነበሩ፡፡
—–
ከላይ በዝርዝር እንዳስረዳሁት የኦነግ ጭፍጨፋ ተብለው ከሚጠቀሱ ትራጄዲዎች መካከል አብዛኛዎቹ በኦነግ የተፈጸሙ አልነበሩም፡፡ ኦነግ ሊጠየቅበት የሚገባው ብቸኛው ድርጊት በበደኖ የተፈጸመው ነው፡፡ የእውነት ቀን ሲመጣ ያንን ፋይል ማውጣታችንም አይቀሬ ነው፡፡ ይሁንና በኦነግ ያልተፈጸመውን ከርሱ ጋር አያይዞ መጻፍ ጥቅሙ ምን እንደሆነ ሊገባኝ አይችልም፡፡ እንዲያውም የያኔዎቹ የግል ጋዜጦች የሚያራግቡት ወሬ በተወሰነ መልኩ የኦነግ ጨካኝነትን ከመግለጽ ይልቅ “ኦሮሞ ጨካኝ ነው” የሚል እድምታ ለመፍጠር የታለመ ነበር የሚመስለው፡፡

እርግጥ የኦነግ ወታደሮች በብዙ አጋጣሚዎች ልዩ ልዩ የጭካኔ ተግባራትን ሲፈጽሙ ተስተውለዋል፡፡ እርሱን አንክድም፡፡ የነርሱ ገፈት ቀማሽ ሆኖ የዘለቀው ግን በአብዛኛው ኦሮሞው ነው እንጂ የሌላ ብሄረሰብ ተወላጅ አልነበረም፡፡ በተለይ አንዳንዶቹ የኦነግ ወታደሮች “ጎበና፤ ቢተምቱ.፤ ወዘተ..” ለሚሏቸው ግለሰቦች ምህረት አልነበራቸውም፡፡ እንዲሁም ተጻራሪ ድርጅት ሊያቋቁሙ ነው በሚል ፍርሃት አባላቶቻቸውን ጭምር እስከ መግደል ይደርሱ ነበር (የኦነግ የሀረር ቢሮ ሃላፊ የነበሩትን አቶ አራርሶ ወዳይን እና በመቻራ ከተማ የተገደለውን የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ካሊድ ሃጂ ኑራን መጥቀሱ ይበቃል)፡፡ ሆኖም ጋዜጦቻችን ድርጅቱ የፈጸመውን ማውራት ይተውና ድርጅቱ ያልፈጸመውን ወንጀል ይነግሩን ነበር! ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ማለት ይህ ነው፡፡

ለማጠቃለል ያህል እኔ ለኦነግ አልተከላከልኩለትም፡፡ አንዳች ጥብቅና አልቆምኩለትም፡፡ የጻፍኩት የማውቀውን ሐቅና የማምንበትን አቋሜን ነው፡፡ ይሁንና ይህ አባባሌ ኦነግን ከመፍራት እንዳይወሰድብኝ አደራ እላለሁ! አስፈላጊ ከሆነ በኦነግም የተፈጸሙ ስህተቶችና ጥፋቶችን አንድ በአንድ መዘርዘር እችላለሁ፡፡

ሰናይ ቀን ይሁንላችሁ!!

[ውንብድና ካርቱም በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ]

ሁዳ የሚባል እስር ቤት 35 ጠያቂ የሌላቸው እስረኞች ይማቅቃሉ – አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

በዓለም ዉድድር አለ። ዉድድሩ በህዝቦች መካከል ነው። ህዝቦች ዉድድሩን ለማሸነፍ አብሮነትን ይፈልጋሉ። በአብሮነት የራሳቸው ደህንነትና ጥቅም ማስከበር ይሻሉ። ደህንነታቸውንና ጥቅማቸው ለማስከበር ሀገር ይመሰርታሉ። ሀገር መስርተው በመንግስት ይወከላሉ። የመንግስት ተግባር ታድያ የህዝቡን ጥቅምና ደህንነት መጠበቅ ነው። በዚሁ መሰረት መንግስት የህዝቦች ተወካይ ጠበቃ መሆን ይጠበቅበታል።

የህዝቦች ወኪል (ጠበቃ) ለመሆን መንግስት በተለያዩ ሀገሮች ኤምባሲ ይከፍታል። የኤምባሲው ሰራተኞች የሚወክሉትን ህዝብ ጥቅምና ደህንነት ይጠብቃሉ፣ ያስጠብቃሉ። ለዚሁ ተግባራቸው ሲባል ህዝብ ደሞዛቸውን ይከፍላቸዋል። ደሞዛቸው የሚከፈላቸው ከመንግስት ካዝና ነው። የመንግስት ገንዘብ የሚሰበሰበው ከህዝብ ነው፤ በግብር መልክ።

ካርቱም የሚገኙ ጓደኞቼ እንደላኩልኝ ከሆነ የኢትዮጵያ ኤምባሲ (በካርቱም) ሰራተኞች በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ተግባር ተሰማርተው ኢትዮጵያውያንን አደጋ ዉስጥ እየጣሉ ይገኛሉ። የሰዎች ደህንነት ከመጠበቅ ይልቅ ሰዎችን አደጋ ዉስጥ ማስገባት ምን ይሉታል? የመንግስት አካላት ወንጀልን ከመከላከል ይልቅ ቁማርተኞች ሲሆኑ ምን ማድረግ ይቻላል?!
የኢትዮጵያ መንግስትም (መንግስት ልበለው) ከህዝብ ኪስ የሚከፈሉ የኤምባሲ ሰራተኞች አሉት። በተለያዩ ሀገሮች ያሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች በህዝብ ገንዘብ እየተዳደሩ የሚከፍላቸውን ህዝብ የሚበድሉ መሆናቸው እናውቃለን። ዛሬ ትኩረቴ የሳበ ግን በካርቱም ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነው።

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች ሱዳን ዉስጥ የሚቸገሩ ዜጎቻችንን ደህንነት ከመከታተል ይልቅ ከሱዳን መንግስት ጋር በመተባበር ኢትዮጵያውያን እስርቤት ይከታሉ። እስካሁን ድረስ በሱዳን ብዙ ኢትዮጵያውያን ያለ ምንም ጠያቂ በወህኒቤቶች እየማቀቁ ነው። የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች በሱዳን ሀገር የሚደርስባቸው ችግር፣ እስር፣ እንግልት እያወቁ በሰዎች ንግድ መሰማራታቸው ይገርማል። የኤምባሲው ሰራተኞች በሀገራቸው ሰዎች ንግድ ነው የተሰማሩ።

በሱዳን ያሉ ኢትዮጵያውያን መንግስት እንደሌላቸው (መንግስት አልባ እንደሆኑ) ነው የሚቆጠረው። “ሑዳ” በሚባል ወህኒቤት 35 ጠያቂ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን አሉ። እነዚህ እስረኞች ያለ ምንም የፍርድቤት ዉሳኔ የተያዙና ከ8-12 ዓመት በወህኒቤቱ የቆዩ ናቸው። ተሰቅለው የተገደሉም መዓት ናቸው። በሱዳን የኢትዮጵያውያን ህይወት ርካሽ ነው። መስከረም አያሌው የተባለችም በሰባት ሱዳናውያን መደፈሯ ይታወሳል።
ኢትዮጵያውያን መንግስት አልባ (stateless) ሁነው ሲሰቃዩ የኤምባሲው ሰራተኞች ግን ሰዎች እየገዙና እየሸጡ (በሰዎች ንግድ ተሰማርተው) ገንዘብ ይሰበስባሉ። ዘመናዊ መንግስታዊ የንግድ ባርያ መሆኑ ነው።

ኢትዮጵያውያን ክብራችንን የምናስመልስበት ግዜ ሩቅ አይሆንም። አቶ መሐመድ ቱፋና አቶ በላቸው ግን ተግባራቹሁ ሁሉ እየተከታተልነው እንገኛለን።

ኦሎምፒያ አካባቢ የሚገኘውን የቀለም ባለሞያውን የጌታሁን ሄራሞን ቢሮ በጎበኘሁ ቁጥር በሁለት ነገሮች እደሰታለሁ፡፡ በአንድ በኩል ስለ ቀለማት በሚሰጠው ሕይወት ያለው ትንታኔ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ባከማቻቸው የኢትዮጵያውያን ሰዓሊዎች ሥራዎች፡፡ የእርሱ ወንበርና ጠረጲዛው የቢሮውን አንድ ሦስተኛ ብቻ ነው የያዘው፡፡ ቀሪውን የቢሮውን ክፍል ዋናው ባለ አክስዮን ስብስብ ሥዕሎቹ ይዘውታል፡፡ መቼም ሰው ሥራውን ለምንዳዕ ብቻ ሳይሆን በፍቅርም ሲሠራው ሕይወትን በሌሎች ላይ የመዝራት ዐቅም ይኖረዋል፡፡

እዚያ ከተሰበሰቡት ሥዕሎች ውስጥ በመጀመሪያው ክፍል ከጠረጲዛው ከፍ ብሎ ግድግዳው ላይ የተሰቀለው ካንቫስ የፈጠራ ሃሳብ ያስደንቀኛል፡፡ በመስተዋቱ ውስጥ ሁለት ጥቋቁር ካልሲዎች በጫማ አቀማመጥ ቅርጽ ተለጥፈዋል፡፡ አንደኛው ምንም ያልነካው ‹አዲስ› ካልሲ ነው፡፡ ሁለተኛው ግን ተረከዙ ላይ ተቀድዷል፡፡

የጥበቡ ርእስ ‹ጥንድ የመሆን ፈተና› ይላል፡፡ ምን ማለት ነው? ደጋግሜ አየሁት፡፡ ‹‹ወፍ ስትበር የሚያሳይ ሥዕል ሳሉ›› ተብለን በሥዕል ትምህርት ቀልደን ላደግን ሰዎች የሥዕልን ጥበብ ዘልቆ ምሥጢሩን መረዳት እንደ ዋድላ ቅኔ ከባድ ምርምርን ይጠይቃል፡፡ ለረዥም ሰዓት ነው አፍጥጬ ያየሁት፡፡ እንዲያውም በመሐሉ የሥዕሉን ምሥጢር ከመመርመር ወጥቼ እኛ ቤት የነበረች አንዲት የቤት ሠራተኛችን ትዝ አለችኝ፡፡ የምገዛቸው ካልሲዎቼ ሁሉ ከጥቂት ቀናት በኋላ ከትዳር ተፋትተው ላጤ ሆነው ነበር የማገኛቸው፡፡ ‹‹ምንድን ነው?›› ስላት ‹አይጦቹ ናቸው›› ትለኛለች፡፡

ግርም ይለኝ የነበረው የነዚህ የስምንተኛው ሺ አይጦች ጠባይ ነበር፡፡ የሀብታም ትምህርት ቤት እንደገባ ልጅ ‹ለአንድ ቀን አንድ ዓይነት› የሚል መርሕ ሳይኖራቸው አይቀርም፡፡ ቢሞቱ ሁለቱንም ካልሲዎች አይበሏቸውም፡፡ ከሁለቱ አንዱን ብቻ ነው የሚመገቡት፡፡ አንዳንዱን ካልሲ ወስደው ለሆቴላቸው በያይነቱ ያዘጋጁበትም እንደሁ እንጃ፡፡ አንዱ ጓደኛዬ ደግሞ የለም ልጂቱ ባለ አንድ እግር ወዳጅ ሳይኖራት አይቀርም ይለኛል፡፡ ከሁለቱ አንዱ ነው፤ ወይም ሌላም ሊሆን ይችላል፡፡

አሁን እዚህ ደግሞ ካልሲ ጥበብ ሆኖ በፍሬም ተሰቅሎ ሳየው ገረመኝ፡፡

‹‹ጥንድ የመሆን ፈተና››

በኋላ ጌታሁን አንድም እያለ ተረጎመልኝ፡፡ ‹‹እስኪ እየው፤ ይኼኛው ካልሲ ደህነኛ ነው፡፡ እንዲያውም ቅድም እንዳልከው አዲስ ይመስላል፡፡ ተጣማሪው ግን ተቀድዷል፡፡ ካልሲ ሊደረግ የሚችለው በጥንድ ብቻ ነው፡፡ በዚህ በተቀደደው ምክንያት ያልተቀደደው ካልሲም ከጥቅም ውጭ ሆኗል፡፡ ቤቴ ውስጥ በተደጋጋሚ ሲያጋጥመኝ ጊዜ ይህንን ሃሳብ አሰብኩት፡፡ የዚህ የደህነኛው ካልሲ ጥፋቱ ምንድነ ነው?አልኩ፡፡ ሳስበው ጥፋቱ አንድ ብቻ ነው፡፡ የቀዳዳው ካልሲ ተጣማሪ መሆኑ፡፡ በቃ ተጣማሪው ስለ ተቀደደ እርሱም ይጣላል፤ ያለበለዚያም ለልጆች ኳስ መሥሪያነት ይውላል፡፡ ጥንድ የመሆን ፈተና ይኼ አይደለም ታድያ?›› አለኝ፡፡

እርሱ ይሄንን ሲነግረኝ ባለትዳሮች፣ ጓደኛሞች፣ የንግድ ሸሪኮች፣ የጥበብ ወዳጆች፣ የሥራ አጋሮች፤ እንዲቀያየር ሆኖ እንደተጫነ የኮምፒውተር ስክሪን ሴቨር በዓይነ ኅሊናዬ ቦግ እልም እያሉ አለፉ፡፡ ምርጥ ባል፤ የባሎች ሁሉ መለኪያ ሊሆን የሚችል፤ አባትም ባልም ተብሎ የሚነገርለት ተጣማሪው ተበላሽታ ሲበጠበጥ፣ ሲታመስ፣ ሲመሳቀል፣ ዐቅሙ ሲደክም፣ ሥራው ሲበላሽ፣ አእምሮው ሲናወጥ፣ ይኖራል፡፡ አይቆርጠው አካል፣ አይተወው ሕመም ሆኖበት፤ አይናገር ምሥጢር፣ ዝም አይል ብሶት ሆኖበት፤ ከዕረፍት እንደተመለሰ እሥረኛ ቤቱ እያስጠላው፣ ጥንድ መሆን ፈተና ላይ ጥሎት ይኖራል፡፡

ምን የመሰለች ሚስት፣ ዐፄ ቴዎድሮስ ‹ሚስት ናት ገረድ› ያሏት ዓይነት፣ ልጆቿን አፍቃሪ፣ ባሏን አክባሪ፣ ትዳርዋን አሥማሪ የሆነች ሚስት፣ ባሏ ተበላሽቶባት፣ ይኼው

ትዳር ምን ዕዳ ነው፣ ጎጆ ምን ዕዳ ነው

ከገነት ተባርሮ ገሐነም መኖር ነው

እያለች ታንጎራጉራለች፡፡ ሥራዋ፣ ሀብቷ፣ መልኳ፣ ዕውቀቷ፣ ጠባይዋ፣ ሥልጣኗ፣ ክብሯ፣ ዝናዋ ከሰው በላይ ሆኖ የትዳር አጋሯ ግን የተቀደደ ጣራ፣ የፈረሰ ግድግዳ፣ የማይዘጋ በር፣ የሚዋጋ ጫማ፣ የሚኮሰኩስ ልብስ፣ የሚያቃጥል ወጥ፣ የሚኮመጥጥ እንጀራ ሆኖባታል፡፡ አትተወው ትዳር፣ አትኖረው ሲኦል ሆኖባት፤ ስንት ውስብስብ ችግር  በቢሮዋ የፈታች ሊቅ፣ የአጋርን ችግር መፍታት ቸግሯት ተጣማሪ ካልሲ ሆናለች፡፡

በአምስት ጣት የሚበላ ሰው መቼም አብሮ መሥራትን አይጠላም፡፡ ‹ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር›፣ ‹ለአንድ ብርቱ ሁለት መድኃኒቱ›፣‹ለአንድ ጉርሻ ሠላሳ ሁለት ጥርስ› እያለ የሚተርት መቼም አብሮ ተባብሮ መሥራትን አይጠላም፡፡ ማበር የሚያስጠላው፣ ሽርክና የሚያስመርረው፤ ኅብረት፣ አንድነት፣ ማኅበር፣ ቡድን፣ ኮሚቴ፣ የሚያቅለሸልሸው እንደ ካልሲው ከተጣማጆቹ የሚቀዳደድ ካለ ነው፡፡ አብሮ ለመሥራት፣ አብሮ ለማደግ፣ አብሮ ለመልፋት፣ አብሮ ለመትጋት ወስነው አጋና ከመቱ በኋላ አንዱ ወገን እንደ ካልሲው የተቀደደ ከሆነ፣ የቀዳዳው ዕድል ፈንታ በደህናው መወሰን ሲኖርበት፣ የደህናው ዕድል በቀዳዳው መወሰን ከጀመረ፣ ያኔ ነው አብሮ መሥራት እሴት ከመሆን ይልቅ ዕዳ የሚሆነው፡፡

ይህንን ካልሲ ሳይ መኪና ታወሰኝ፡፡ አራት እግር ያለው መኪና አንዱ ጎማ ሲተነፍስ የሚቆመው ለምንድን ነው? ጥንድ የመሆን ፈተና ገጥሞት አይደል፡፡ ያልተነፈሱት ሦስት ጎማዎች በተነፈሰው አንድ ጎማ ምክንያት መቆማቸው የግድ ነው፡፡ ስንት የተጣመሩ ፓርቲዎች ከመካከላቸው እንደ ካልሲው የተቀደደ፣ እንደ ጎማው የተነፈሰ ሲያጋጥማቸው አይደል ቆመው ወይም ፈርሰው የቀሩት፡፡

አንዳንዴ ምንም ያህል ብንፈልገው ብቻችንን ልንሆነው የማንችለው ነገር አለ፡፡ ብቻችንን ብንሠራው እንኳን ከማናውቅ አካል ጋር የምንጣመርበት ጉዳይም አለ፡፡ ‹አይ የታክሲ ሾፌር፣ አይ አስተናጋጅ፣ አይ ነጋዴ፣ አይ ቀበሌ፣ አይ ተቃዋሚ፣ አይ ደጋፊ፣ አይ ጋዜጠኛ፣ አይ ፖሊስ› እየተባልን በምናውቀውም በማናውቀውም፤ ባደረግነውም፣ ባላደረግነውም የምንወቀሰውኮ ‹ጥንድ በመሆን ፈተና› ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ እኛ ብቻችንን መልካም ብንሠራ፣ ንጹሕና ጻድቅ ብንሆን እንኳን፣ የሆነ ቦታ በሚገኙ ሳናውቅና ሳንፈቅድ በተጣመርናቸው የሞያ አጋሮቻችን ጥፋት መወቀሳችንና ሕዝባዊ አመኔታ ማጣታችን አይቀሬ ነው፡፡

ጥቂት የዚያ ብሔረሰብ ሰዎች፣ የተወሰኑ የዚያ ቡድን አባላት፣ እፍኝ የማይሞሉ የዚያ ሀገር ዜጎች፣ በጣት የሚቆጠሩ የዚያ ሃይማኖት አማኞች፣ ውክልና የሌላቸው የዚያ ማኅበር አባላት፣ ለራሳቸው ብቻ ሲሉ ወጥ በረገጡ የዚያ ሞያ ባለቤቶች፣ ከሁለት ወንበር በማይበልጡ የዚያ መሥሪያ ቤት ባልደረቦች ጥፋት ‹እንደ አህያ ጆሮ እንደ ጦር ጉሮሮ‹ ሁሉንም አንድ አድርጎ የመኮነን አባዜ የመጣው ጥንድ ከመሆን ፈተና ነው፡፡ በተቀዳደዱ ካልሲዎች ምክንያት የሚያገለግሉትም አብረው እንደሚጣሉት፡፡

ምርጥ የባለሞያ ወጥ፣ በስሕተት በበዛ ጨው ምክንያት ተመጋቢ የሚያጣው ጥንድ የመሆን ፈተና ገጥሞት ነው፡፡ ‹በጨው ደንደስ በርበሬ እንደሚወደሰው› ሁሉ በጨው ጥፋትም በርበሬ ከጥቅም ውጭ ሊሆን ይችላል፡፡

ዘመናዊ ኑሮ የጉርብትና ሥርዓት ነው፡፡ ዐውቀነውም ይሁን ሳናውቀው ከብዙ ነገሮች ጋር ተጣምረንና ኅብረት መሥርተን ነው የምንኖረው፡፡ ሰው ብቻውን መጥፎ፣ ብቻውንም ጥሩ መሆን አይችልም፡፡ ብቻውን ንጹሕ፣ ብቻውንም ቆሻሻ ለመሆን አይችልም፡፡ እኛ ቤት የምትመጣው ዝንብ ከየት መነሣት እንዳለባት ልንወስንላት አንችልም፡፡ አንዳንድ ጊዜ በአንድ መንደር መብራት፣ ውኃና መንገድን ለማስገባት፤ ጸጥታ፣ ንጽሕናና ውበትን ለመጠበቅ መንደሩ ሁሉ ይስማማና ጥቂት ጎረቤቶች ግን እምቢ ይላሉ፡፡ አልከፍልም፣ አልሠራም፣ አልሰበሰብም፣ አልተባበርም፣ አያገባኝም ይላሉ፡፡ የስንት ጎበዞችን ዕቅድ የጥቂት ቀዳዳ ካልሲዎች ችግር ከጥቅም ውጭ ያደርገዋል፡፡

ጥንድነት የማይቀር የኑሮ ሥርዓት ከሆነ ከባዱ ነገር ጥንድ የመሆንን ፈተና እንዴት እንለፈው ነው፡፡

‹‹ትንሽ በር በሬ ብደቁሰው፣ ብደቁሰው

ሀገሩን ሁሉ አስነጠሰው፣ አስነጠሰው››

የተባለው ይህንን ይነግረናል፡፡ ለማስነጠስ በርበሬ መደቆስ አያስፈልገንም፡፡ የሌላው ጎረቤት በርበሬ በቂ ነው፡፡ በቢሯችን ውስጥ መልካም ሽቱ የተቀባ ሰው ካለ ለሁላችን መዓዛው እንደሚተርፈው ሁሉ፣ የጫማውን ጠረን ማስወገድ ያልቻለውም የቢሯችን ባልደረባም በተቃራኒው እንዲያ ነው፡፡

ጥንድነት የሚያመጣውን ፈተና ለመወጣት አንድም የዳበረ የኑሮ ጥበብ ያሻል፣ አንድም የታሰበበትና ተገቢ የሆነ የጥንድነት ልማድና ሕግ ያስፈልጋል፤ አንድም ደግሞ ከፈተናው የመውጫ ውጤታማ የአደጋ ጊዜ በር ሊሠራ ይገባል፡፡ ጥንድነት የሚያመጣውን ፈተና ለመከላከል፣ ካልሆነም ለመፍታት የሚያስችል ከማኅበረሰቡ ጋር የተዋሐደ የኑሮ ጥበብ ያስፈልጋል፡፡ ይህንን የኑሮ ጥበብ ለመገንባት ደግሞ የሃይማኖት ትምህርቶች፣ ሥነ ቃል፣ ሚዲያና ዘመናዊ የኑሮ ዘዴ ትምህርቶች ታላቅ አስተዋጽዖ ያደርጋሉ፡፡

አብሮነት የሚያስከትላቸውን ፈተናዎች ማራቂያ፣ ሲመጡም የከፋ ጉዳት ሳያደርሱና እንደ ቀዳዳው ካልሲ ለመጣል ሳያበቁ፣ ማስወገጃ የዳበረ ሀገራዊ ልማድና ሕግም ወሳኘው ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፈተናውን አምቀን ብቻ እንድንይዘው፣ ያለ መውጫ እንድናስበው፣ የዐርባ ቀን ዕድል አድርገን እንድንቆጥረው፣ መፍትሔው አብሮ መውደቅ ብቻ አድርገን እንድናየው የሚያደርግ ሀገራዊ ልማድና ሕግ ካለ ጥንድነት እሴት ሳይሆን ዕዳ ብቻ ይሆናል፡፡

ፍየል ቀንዷ ለምን ወደ ኋላ ዞረ? ሲባል፤ ስትገባ መውጫ መውጫውን ለማየት ነው አሉ፡፡ የምንገባበት ነገር ሁሉ አንዳች የመውጫ የአደጋ ጊዜ በር ሊኖረው ይገባል፡፡ የአደጋ ጊዜ በር በማናቸውም ጊዜ፣ በፈለገው ሰው፣ ለማናቸውም ዓይነት ምክንያት አይከፈትም፡፡ የሚከፈትበት ምክንያት፣ ጊዜ፣የመክፈት ሥልጣን ያለው አካል አለ፡፡ በጥንድነት ፈተናም እንዲሁ ነው፡፡ እንደ መግቢያው በር ሁሉ የመውጫ የአደጋ ጊዜም በር ያስፈልጋል፡፡ መግቢያ ብቻ ያለው ባለ አንድ በር ቤት ለጥንድነት አይመከርም፡፡ ዐውቀን የዘጋነው፤ በአደጋ ጊዜ ግን ልንከፍተው የምንችለው፣ የመጨረሻው አማራጫችን እርሱ ሲሆን ዘለን የምንወጣበት የአደጋ ጊዜ በር ያስፈልጋል፡፡ ‹እኔ በዚህ አልስማማም፣ የእኔ ሃሳብ የተለየ ነው፣ እኔ በዚህ መኪና ተሳፍሬ እስክገለበጥ ድረስ አልጓዝም› ብለን ልንናገርበት የምንችለው በር፡፡ ጥንድነት ዕድልና መብት እንጂ ዕዳና ግዴታ እንዳይሆን፡፡

ከአዲስ አበባ ወደ ፍራንክፈርት፣ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ

ነገሩ የሆነው አዋሳ ዩኒቨርሲቲ ነው። ቆነጃጅት ወጣት ሴት ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውጭ ባሉ የከተማው ደለላዎች ጋር በመተባበር እጅግ ዘግናኝ ስራ ይሰራሉ። ደላሎቹ የቆነጃጅቶቹን ተማሪዎች ፎቶ የያዘ ትልቅ ካታሎግ ይዘው ከአዲስ አበባም ሆነ ከአቅራቢያው ከተሞች አለዚያም ከዚያው ከአዋሳ ከተማ ብቅ የሚሉ ሃብታም ደንበኞቻቸውን የተማሪ ኮረዶችን ፎቶ በመስጠት ያስመርጣሉ። ሰውየው ውብ ወጣት ተማሪ ኮረዳ እንደሚፈልግ በሰው […]

አገራችን ኢትዮጵያ ያለችበትን አሳዛኝ ሁኔታ ከማንም የበለጠ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይረዳዋል ብለን እናምናለን። የኢሕአዴግ መንግስት፣ ላያ ላዩን «በዴሞክራሲ አምናለሁ» ቢልም፣ ፍጹም አምባገነን በሆነ መልኩ ፣ ሕዝቡን አፍኖ፣ እያሰራ፣ እየገደለ፣ ዜጎችን እያፈናቀለ፣ ከሃያ አመታት በላይ ቆይቷል። በአብዛኛዉ ሕዝብ ዘንድ እየተጠላ፣ ይሄን ያህል አመት በስልጣን መቆየት የቻለው፣ አገዛዙ በዋናነት ኢትዮጵያዊያን መከፋፈል በመቻሉና ዜጎች ደፍረው ለመብታቸው እንዳይቆሙ በፍርሃት እንዲተበተቡ […]

በዴሞክራሲያዊ መንገድ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ህገመንግስታዊ መብቴን ጥሰውብኛል ሲል አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ክስ የመሰረተባቸው ሶስት የመንግስት ተቋማት በትናንትናው ዕለት በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 8ኛ ፍትሃብሔር ችሎት ቀርበው መቃወሚያቸውን አሰሙ። ፓርቲው ክስ የመሰረተባቸው የአዲስ አበባ ከንቲማ ጽህፈት ቤት ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የአዲስ አበባ ፖለስ ኮሚሽን ሲሆኑ በጠበቆቻቸው በኩል የክስ መቃወሚያቸውን በፍ/ቤቱ አቅርበዋል። […]

አትክልት አሰፋ (ቫንኩቨር)

ነገሩ የሆነው ዲላ ዩኒቨርሲቲ ነው። ቆነጃጅት ወጣት ሴት ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውጭ ባሉ የከተማው ደለላዎች ጋር በመተባበር እጅግ ዘግናኝ ስራ ይሰራሉ። ደላሎቹ የቆነጃጅቶቹን ተማሪዎች ፎቶ የያዘ ትልቅ ካታሎግ ይዘው ከአዲስ አበባም ሆነ ከአቅራቢያው ከተሞች አለዚያም ከዚያው ከዲላ ከተማ ብቅ የሚሉ ሃብታም ደንበኞቻቸውን የተማሪ ኮረዶችን ፎቶ በመስጠት ያስመርጣሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

«ሃኪምዎን ይጠይቁ» በተከታታይ በሚያቀርባቸው ቅንብሮች፤ ሱስ በአንጎልና በባሕሪ ላይ የሚያሳድረውን ጫና እና የጤና ጉዳቶች፤ እንዲሁም የሕክምና አማራጮች ይመለከታል።

በህክምናው አነጋገር በእንግሊዝኛ Dependancy በመባል የሚታወቀው የጤና ሁኔታ ምንነትና ዓይነተኛ ጠባይም ይመረምራል።

በሱስና በአንጎል አሠራር ላይ ለሚያተኩሩት ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡት በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ በአሪዞና ክፍለ ግዛት ሜዮ ክሊኒክ፥ የነርቭና የአዕምሮ ሕክምና ባለሞያው ዶ/ር ዮናስ እንዳለ ገዳ ሲሆኑ፤ በተለይ ሱሰኝነትንና ባሕሪን አስመልክቶ በቀረቡ ጭብጦች ዙሪያ ሞያዊ ትንታኔ የሚሰጡት ደግሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው የአእምሮ ሃኪሙ ዶ/ር አታላይ ዓለም ናቸው።

ዘወትር ቅዳሜ ማታ ከደሳለኝ መኮንን ጋር፣ምርጥና አዳዲስ የካንትሪ ማለትም የአሜሪካ አገር ሰብእ፣ የሮክ፣ተሶል፣የፖፕ፣የአር-ኤን-ቢ፣ብሉዝ፣የሬጌና የሂፕ-ሃፕ ዜማዎችን እንዲያደምጡ ተጋብዘዋል።

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ባለፈው ዓመት ፣ የዩናይትድ ስቴትስና የብሪታንያ የስለላ ድርጅቶች ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ የድርጅቶችን ፣ የግለሰቦችን የታወቁ የሀገር መሪዎችን የግል ተንቀሳቃሽ ስልኮች የድምጽ፤ የጽሑፍና ስዕል አገልግሎት ጭምር ይጠልፉ ነበር ተብሎ፣ ዜናው በዓለም

ፕሬዝዳንት ኪር ባለፈዉ ታሕሳስ በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሐላፊዎችን ከመንግሥት እኩል ሐገር ለመምራት ይሞክራሉ በማለት ወንጅለዋቸዉ ነበር።በቀደም ጁባ ዉስጥ ለተሰለፉት ወጣቶች ንግግር ያደረጉት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄምስ ዋኒ ኢጋ የአለቃቸዉን አባባል ደገሙት

የአፍጋኒስታን ምርጫ ከመካሄዱ አንድ ወር በፊት ታዛቢዎች በዚህ አጋጣሚ ለፉክክር የሚቀርቡ 11 እጩዎች ሶስቱ የሕዝቡን ቀልብ እንደያዙ ያመለክታሉ። የፕሬዝደንት ሃሚድ ኻርዛይ ወንድም ቃዩም ኻርዛይ ከፉክክሩ ራሳቸዉን አግልለዉ የቀድሞ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩትን ዛልማይ ራሶልን እንደሚደግፉ ገልጸዋል።

በማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ በቀድሞ የሴሌካ ሙሥሊም ዓማፅያን አንፃር የሚንቀሳቀሱት ራሱን ፀረ ባላካ ብሎ የሚጠራ የወጣት ክርስትያን ሚሊሺያ ቡድን አባላት ሽብራቸውን አስፋፉ። ሚሊሺያዎቹ ሙሥሊሞቹን ዜጎች መግደል ብቻ ሳይሆን

በጀርመናዊቷ የሀኖፈር ከተማ ባለፈው እሁድ የተከፈተው እና አምስት ቀናት የሚቆየው ትልቁ የኮምፒውተር ትርዒት የመረጃ ቴክኖሎጂን አጠባበቅ እንዴት አስተማማኝ ማድረግ ይቻላል ለሚለው ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶዋል።

Share:

ለኢትዮጵያ የዛሬ አርባ አመት ነው አዲስ ህይወትና ምዕራፍ የተከሰተው፡፡ ሆኖም 1966 ዓ.ም የነገሮች ሁሉ መነሻ አልነበረም፡፡ በዛች ወቅትና አመት በተከሰተው ሁኔታ ብቻ አይደለም ወጣቱ ህይወቱን ለመስጠት የተሰናዳው፡፡ ነገር ግን የአብዮት መፈንዳት የእያንዳንዳችን የውስጥ ስሜት ስለነካ ይመስለኛል፡፡ ለዚህም ምሳሌ የማደርገው ራሴን ነው፡፡ ማህበረሰብ እንዲለወጥ የአንድ ጊዜ የጋራ እርምጃ ሳይሆን የተጠራቀመ ነገር ያስፈልገዋል፡፡ በወቅቱ ወደ 11ኛ ክፍል አልፌ ነበር፡፡ እኔ እኖር የነበረው ከአዲስ አበባ ውጭ ፍቼ ከተማ ነው፡፡ ይህም ለገጠሩ ህዝብ ቅርብ እንድሆን አድርጎኛል፡፡ ቤተሰቦቼ የሀይማኖት ሰዎች ናቸው፡፡ አባቴ ቄስ ነው፡፡ የአባቴ ወንድሞች፣ የአባቴ አባት፣ የእናቴ ወንድሞች፣ የእናቴ አባት…ብዙዎቹ ቄስና የሀይማኖት ሰዎችና ቤተሰብ ነበሩ፡፡ እንደሚታወቀው በነበረው ስርዓት የቤተ ክርስትያን ሰዎችና የመንግስት አስተዳደር ቅርብ ነበር፡፡ በመሆኑም እኔም ለሀይማኖት ቅርበት ነበረኝ፡፡ ቅረበቴ ግን ለእኔ የሰጠኝ ከስርዓቱ ጋር መሳሳብና መዋደድ አልነበረም፡፡ እኔ የቄስ ልጅ እንደመሆኔ የሀብታም ልጅ አልነበርኩም፡፡ (መቼም ዛሬ ካልሆነ ቄስ ሀብታም ሆኖ አያውቅም፡፡)
ለቤተ-ክርስቲያን ቅርብ ስትሆኑ ለጪሰኛውና ለመሬት ቅርብ ትሆናላችሁ፡፡ ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን ‹‹እኩል ከእርስት›› የሚባል ነገር ስለነበራት ነው፡፡ እኔ ቤት ባይሆንም የአባቴ ቤተሰቦች ቤት ይህን ስርዓት በግልጽ ማየት ችያለሁ፡፡ ገና 6ኛ እና 7ኛ ክፍል ሆኜ ጭሰኞች ከገጠር እህል ሲያመጡ፣ ግብር ሲበላ፣ ድግስ ሲደገስ፣ ሲስተናገድ (እንዴት ህዝብ በየ ደረጃው ይስተናገድ እንደነበር) በቅርብ ማየት ችያለሁ፡፡ በነገራችን ላይ ገና 6 እና 7ኛ ክፍል ሆኜ ይመስለኛል ፍቅር እስከ መቃብር የታተመው፡፡ ፍቅር እስከ መቃብርን አነበብኩ፡፡ ፍቅር እስከ መቃብር ላይ የፊውዳልና የጭሰኛውን ግንኙነት ሳነብም በስርዓቱ የተማረርኩት እኔ ብቻ አለመሆኔን አመንኩ፡፡ ፍቅር እስከ መቃብር ለልቤ ጥያቄ መልስ ሰጠኝ፡፡ ከእኔው ውጭ ሌሎች ሰዎች እንደሚከፋቸው ማየት ችያለሁ፡፡ ከዛ በፊት ግን የጭሰኞችን ግንኙነት አይቻለሁ፡፡ አንድ ሰው ሁለት አጥር ይኖረዋል፡፡ ጭሰኞች የውስጠኛውን አጥር ከመግባታቸው በፊት ማደግደግና፣ አጋሰሶቻቸውን ማራገፍ አለባቸው፣ እህሉን ተሸክመው ለመግባት፡፡
6ኛ ክፍል ሆኜ ትምህርት ቤት ስሄድ ትንሽ ልጅ የሚመራቸው አንድ መንገድ ዳር ላይ የሚለምኑ ሽማግሌ ነበሩ፡፡ እናም በዛች ትንሽ ጭንቅላቴ ብዙ አስብ ነበር፡፡ ጭሰኞቹ ሲያረጁ እንደዚህ ሰውዬ እንደሚሆኑ አስብ ነበር፡፡ ምክንያቱም ያፈሩትን እየሰጡ ነው፤ ሲያረጁ ደግሞ ከመሬታቸው ይነሳሉ፡፡ እናም ግን ለምን? ግን ለምን? ግን ለምን? የሚል ጥያቄ በብዛት በአዕምሮዬ ይመላለስ ነበር፡፡ ፍቅር እስከ መቃብርን እንዳገኝና እንዳነብ ያደረገኝ ወንድሜ ስለ ችግሮቹ እንድጽፍ ያደርገኝ ነበር፡፡ የተሰማኝን መጻፍ ጀመርኩ፡፡
እስከ 9ኛ ክፍል እስክደርስ ድረስ ሶስትና አራት ባለ 50 ገጽ ደብተር ጻፍኩ፡፡ በ1966 የጻፍኳቸውን ደብተሮች ብቻ ይዤ አዲስ አበባ በመምጣት ንግድ ስራ ትምህርት ቤት ገባሁ፡፡ በ1967 ዘመቻ መሄድ ነበረብኝ፡፡ ዘመቻ እንደሄድኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ያነበብኩት የማኦን ስለ ጭሰኞች የሚያወራ ‹‹The peasant uprising›› የሚለውን መጽሃፍ ነበር፡፡ ውስጤ ያለውን የሚነካ ነገር ተፈጠረ፡፡ ይህ ነገር (አብዮት) ያስፈልገናል ብዬ አመንኩ፡፡ የቄስ ልጅ፣ አክራሪ ኦርቶዶክስ ነበርኩ፡፡ ሆኖም በዘመቻው ወቅት በመጾምና ባለመጾም ተፈትኛለሁ፡፡ ወጣት ስትሆኑ ደግሞ አዲስ ነገር መቀበልና መሆን አለባችሁ፡፡ በሶሻሊዝም መጾም የለም፣ እንዲያውም በሶሻሊዝም ስም ማረድ (መባረክ) አለብን ሁሉ ይባል ነበር፡፡ በዚህ ጉዳይ ለ6 ወር ያህል ተፈትኛለሁ፡፡ በኋላ ተሸነፍኩና ተቀላቀልኩ፡፡ ስለ ኮምኒዝም የሰማሁት 7ኛ ክፍል ሆኜ ነው፡፡ ስለቻይና ሶቬት አብዮት ነው፡፡ ኮሚኒስት ከሆንን መኪና የለም፣ ቤት የለም፣ ሱፐር ማርኬት ሄዶ መግዛት የለም፣ በካርድ ብቻ መግዛት ነው የሚል ነው፡፡ ይህ ለእኔ በውስጤ የነበር ነው፡፡ የማኦ መጽኃፍና ሌሎች መጽሃፎች ሲጨመሩ ሶሻሊዝም ለኢትዮጵያ እንደሚያስፈልጋት አመንኩ፡፡ ይህ መነሻ ሆኖ ዘመቻ ጣቢያ እያለሁ ዴሞክራሲያን ሳነባት ደግሞ ይበልጡን አመንኩበት፡፡ እንዲያውም ዴሞክራሲያን የሚጽፉት ሰዎች መላዕክት ይመስሉኝ ነበር፡፡ እስከዚያ ድረስ የሚመስጥ ጽሁፍ ነበር፡፡ ያ መመሰጥ ውስጤ ከነበረው መመሳሰል ጋር በመመሳሰሉ ነው ኢህአፓ ውስጥ ያስገባኝ፡፡ ማንም ቀስቅሶኝ አይደለም፡፡ እኩል ተቀስቅሰን እኩል መሄድ አልቻልንም፡፡ እኩል እንደ እኔ ቢቀሰቀሱም ከዘመቻ ተመልሰው ትምህርታቸውን የቀጠሉና ሌላ አቅጣጫን የመረጡ ነበሩ፡፡ ስለዚህ ውስጤ ያለውን ነገር ስለነካ ነው ገብቼ የቀረሁት፡፡ ባላምንበት ኖሮ ከተቀሰቀስኩ በኋላ ቤት ስመለስ በተውኩት ነበር፡፡
1966 አብዮት በእኔ ምሳሉ ሳየው ድንገተኛ አልነበረም፡፡ የካቲት ወር በአንድ ሰልፍ ዩኒፎርም ለብሰን መንገድ ላይ ስንወጣ ‹‹እንኳን ደስ አላችሁ!››፣ ‹‹እንኳን ጀግና ሆናችሁ!›› እንባል ነበር፡፡ ነባራዊ ሁኔታው፣ የኑሮ ውድነት (ከዛሬው ጋር የሚወዳደር አልነበረም) አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ አባቴ በርካታ ቤተሰብን በ80 ብር ማስተዳደር ይችል ነበር፡፡ የዛን ጊዜና የአሁኑን ማመሳሰል አይቻልም፡፡ የተወደደው ቅቤ ሳንቲም ጨምሮ 3 ብር፣ ዘይት ሁለት ብር፣ ጤፍ 50 ብር ይሸጥ ነበር፡፡ የ1966ቱ የኑሮ ውድነት ከዛ በፊት ከነበረው ርካሽ ኑሮ ጋር የሚነጻጸር ነው፡፡ ከድሮው ጋር ሲነጻጸር የኑሮ ውድነቱ እሳት እንደነደደ ይቆጠራል፡፡ ያ የምርት ግንኙነት፣ ማህበራዊና ስነ ልቦናዊ ችግር ጋር ሲደማመር እንጅ ወታደሩና ተማሪው ስለተሰለፈ ብቻ የመጣ አይደለም፡፡ ያን ሁኔታ ወደ አንድ ሁኔታ (አብዮት) ለመቀየር፣ የታክሲ ሾፌሮች፣ የወታደሩ የደሞዝ ጭማሬ፣ የሴክተር ሪቪው ተጨምሮበት 1966ን የኢትዮጵያ አንድ ምዕራፍ አደረገው፡፡ ስርዓቱ ጠንቃቃ ባለመሆኑና ብዙ ስላልተሰራ ነው አብዮቱ የፈነዳው፡፡ አሁን እኮ እየተመለስን ያለነው ወደ ካፒታሊዝም ነው፡፡ ስርዓቱ ጠንቃቃ ቢሆን ያለምንም ውጣ ውረድ የተሳካ ስርዓት በገነባን ነበር፡፡ የከፈልነው መስዕዋትነት የማይገባ ነበር፡፡
በዘመቻው ወቅት ከአዲስ አበባ ወጥተን ገጠር በመግባታችን ለማንበብም ሆነ ለህዝብ ቅርብ መሆን ችለናል፡፡ ውስጣችን የነበረውን እምነት የቀየረው ይህ ነው፡፡ ወጣቱም አንዴ ከተነሳ መመለስ ያቃተው ለዚህ ነው፡፡ ኢህአፓ ውስጥ ስገባ ያጋጠመኝ ነገር ደግሞ በፊት ከማስበው የተለየና እምነቴን ያሳደገልኝ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች እንደ ሰው አይደሉም የሚለውን እምነቴን አጠናክሮልኛል፡፡ በወጣት ማህበራት እንገናኝ ነበር፡፡ የፓርቲው ሳይሆን ኢህአወሊ (የወጣት ማህበሩ) አባል ነበር፡፡ ኢህአወሊ ራሱን የቻለ ፓርቲ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ከወጣት ሊጉ ከገባሁ በኋላ ሀይለኛ ስብዕና አግኝቻሁ፡፡ ከዛ በፊት የነበረኝ አላማ ዩኒቨርሲቲ መግባት የዩኒቨርሲቲ መምህር፣ ፕሮፌሰር ሆኜ የምሁር ህይወት መኖር ነበር፡፡ ያ ሁሉ ህልሜ ቀርቶ ከዘመቻ ስንመለስ ‹‹ከትግል በኋላ ትምህርት›› የሚለው የወጣት ሊጉን መፈክር ይዘን ትግል ገባን፡፡ ትግሉ እየከረረ መጣ፡፡ ደም በደም ሆነ፡፡ የመጀመሪያው ደም በሚኒስትሮቹ ጀመረ፡፡ በእነሱ የተጀመረው ግድያ ወደ ሌላ ግድያ ተቀየረ፡፡
ኢህአፓ ውስጥ ከገባን በኋላ የሰዎቹ መልካምነት፣ እድገት በህብረት ሄጄ የዩኒቨርሲቲ ካየሁ በኋላ ባገኘኋቸው ተማሪዎች ስብዕና በማየቴ ከውስጤ ነው ያመንኩት፡፡ ምክንያቱም ኢህአፓ የውስጣችን ስሜት ነው የነካው፡፡ ፓርቲ ውስጥ ያየሁት ደግሞ ይበልጡን ልቤን የሚሞላ ነበር፡፡፡ ለራሳችን መኖርና ስብዕናችንን መጠበቅ እንዳለብን፣ ነገር ግን ቅድሚያ ለህዝብ እድንኖር በተግባር አስተምረውናል፡፡ ኢህአወሊ እያለሁ አንድ ሰልፍ ነበር፡፡ ለማምለጥ ስንሮጥ አንድ ሰፈር ውስጥ የተደረመሰ ሽንት ቤትና ውጭ ደግሞ የሚመጥ የቆመ መኪና ላይ ደረስን፡፡ በዚህም ምክንያት አስም ተቀሰቀሰብኝ፡፡ ትንሽ እንደሄድን መራመድ አቃተኝና ተቀመጥኩ፡፡ ሌላው እየሮጠ አንድ በእድሜ የሚበልጠኝ ሰው ቆሞ ይጠብቀኛል፡፡ ‹‹ለምንድን ነው የቆምከው? አምልጥ!›› ስለው ‹‹ለምን ጥየሽ እሮጣለሁ? ይልቁን ጥቂት እርጅኝና ጥግ አስይዤሽ እሄዳለሁ›› አለኝ፡፡ ጥይት እየተተኮሰ እኔን ይጠብቃል፡፡ ይህ ድርጅቱ ለእኔ እንደሚቆም ማወቅ ስላስቻለኝ ብርታት ሰጥቶኛል፡፡ አስሙ እየባሰብኝ ሲሄድ ባልጠበኩት ሁኔታ የአስም መድሃኒት ተላከልኝ፡፡ ይህኛውም ሌላ ጉልበት ነበር፡፡
ሌላ ጊዜ ደግሞ አዲስ አበባ ላይ መኖር ከባድ ሆነ፡፡ ወደ አሲምባ ለመሄድም አይቻልም ነበር፡፡ ናዝሬት ላይ አንድ ቤዝ ሊቋቋም ነበር፡፡ ያኔ ከእኛ ሰፈር ሶስት ወጣቶች ወደ ቤዙ ሊሄዱ ነበር፡፡ ግን መድረስ ባለመቻላቸው ተመልሰው መጡ፡፡ ከተመለሱ በኋላ ታሰሩ፡፡ ልጆቹ በመታሰራቸው ለእኔ ሂስ መጣልኝ፡፡ ቁጭ ብየ አነበብኩት፡፡ ሂሱም ልጆቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በሚተዋወቁት ሰዎች መካከል ሊሆን እንደሚችልና፤ መረጃ ከእኔ በኩል አፈትልኮ እንደሆነ የሚያሳይ ጠንከር ያለ ሂስ ነው፡፡ እኔ የት እንደሄዱ ስላላወቅሁ በጣም አዘንኩ፡፡ መልስ መጻፍ እንዳለብኝ አሰብኩ፡፡ እኔም ለእንዲህ አይነት ድርጅት ከሆነ አባል የሆንኩት መሳሳቴንና ከድርጅቱ እንደምወጣ ጻፍኩ፡፡ በሳምንቱ ግን የሚገርም መልስ ጻፉልኝ፡፡ መልሱ ለእኔ ለትንሹዋ ልጅ የሚሰጥ አልነበረም፡፡ ‹‹ተንበርክከን ይቅርታ እንጠይቃለን›› የሚል ከጸኃፊው ማብራሪያ ጋር ተዳምሮ ይቅርታ ተጻፈልኝ፡፡ ‹‹እንደ አንቺ ያለ ጠንካራ አባል ስላለን እንኮራለን›› አሉኝ፡፡ ይህም ሌላ ጉልበት ነበር፡፡ ይህን የጻፉልኝ ለአባላት ትልቅ ክብር እንዳላቸው መሆኑን አምኛለሁ፡፡ ሂስና ግለሂስን የተማርኩት ያኔ ነው፡፡
ብዙዎቹ ጓደኞቻችን ሞቱ፣ የተረፍነው ዳንን፣ ከእስር ተፈታን፣ መኖር የግድ ነውና መኖር ጀመርን፡፡ ያ ውስጤ የነበረን አላማ የነካውን ኢህአፓና ኢህአወሊ ውለታ ተሸክሜ መኖር አቃተኝ፡፡ በእርግጥ 20ና 30 አመት አልፎታል፡፡ ያ ትውልድ የሞተው፣ እኔ ያን ሁሉ የሆንኩት ኢትዮጵያን ለማጥፋት ባይሆንም በርካቶች ግን መኖር እንዳንወድ አድርገው ይወቅሱናል፡፡ በእርግጥ ስለማያውቁን ነው የሚል ጥያቄ ይመላለስብኝ ነበር፡፡ አንድ ወቅት ይህን መልስ እንዳገኝ አደረገኝ፡፡ አንድ ዓለም አቀፍ ድርጅት በምሰራበት ወቅት አንድ ቡድን ይዤ ለልምድ ልውውጥ ወደ ኬንያ ሄድኩ፡፡ በእረፍት ሰዓት ሰብሰብ ብለን ስናወራ ስለ ‹‹ያ ትውልድ›› መወራት ጀመረ፡፡ አጥፍተውት አለፉ እያሉ ይወቅሱታል፡፡ የአንድን ነገር ውጤቱን ብቻ አይቶ መገምገምና መውቀስ ተገቢ አይደለም፡፡ ‹‹ለምን እንዲህ ትወቅሷቸዋላችሁ?›› ስለቻው፤ ‹‹አታውቂያቸውም!›› አሉኝ፡፡ ‹‹እኔን አታውቁኝም? እንዴት ነው እኔ የማላውቃቸው? ያ ትውልድ ማለት እኔ ነኝ!›› አልኳቸው፡፡ ‹‹አንቺ ምንድን ነሽ?›› አሉኝ፡፡ ‹‹ኢህአፓ ነበርኩ!››፡፡ አላመኑም፡፡ ‹‹እኔ አላማ የለኝም? ጭራቅ ነኝ? እኔ ክፉ ነኝ? እኔ ኢትዮጵያን አልወድም?›› የሚል ጥያቄ አነሳሁላቸው፡፡ ‹‹አትቀልጅ! ያ ትውልድማ እንዲህ ሊሆን አይችልም›› አሉኝ፡፡ በእርግጥ በደርግ ጊዜ ሲማሩ ኢህአፓን እንደ ጭራቅ አድርገው ይስሉላቸው ስለነበር ነው፡፡ ‹‹እንግዲያውስ የጠፋው ጠፍቷል ነገር ግን አውቀን አላጠፋነውም አልኳቸው፡፡›› አንድ ነገር መለካት ያለበት በውጤቱ ብቻ አይደለም፡፡ የእኛ አጀንዳ ኢትዮጵያን ማጥፋት አልነበረም፡፡
ልጆቹን ‹‹ስለዛ ትውልድ፣ ስለ ኢህአፓ ማወቅ ትፈልጋላችሁ ልጻፍ?›› አልኳቸው፡፡
‹‹አዎ ጻፊ!››
‹‹ምን አይነት ልጻፍ?››
‹‹ትንሽ እንጨት እንጨት እንዳይል እንጅ ጻፊ!››
‹‹ምንድን ነው እንጨት እንጨት እንዳይል ማለት?
‹‹ትንሽ ፍቅር ቢጤ ጣል አድርጊበት?
‹‹እንዴ! እኛም እኮ ፍቅር እናውቅ ነበር ከየት አምጥቼ ነው ጣል የማደርገው?››
ከዛም ‹‹ምርኮኛ››ን መጻፍ ጀመርኩ፡፡ ከ30 አመት በኋላ ይህን መጽኃፍ የጻፍኩት የዛ ዘመን ፖለቲካ ስላሳመነኝ ነው፡፡ ከአንድ ነገር ጋር ለመዝለቅ ውስጣችን መነካት አለበት፡፡ ሌላ አጀንዳ ካለን፣ ሌላ የምናስበው ነገር ካለን፣ ያንን አጀንዳ ብለን የምንገባ ከሆነ በጊዜ መውጣት ነው የሚያዋጣው፡፡ እኔ የምችለውን ያህል ሄጃለሁ ብዬ አስባለሁ፡፡ ተሂዶ ተሂዶ መዝለል የማይቻል ጎርጅ ላይ ሲደረስ የግዱን ይቆማል፡፡ ከዛ በኋላ ያ ትውልድ ለምንድን ነው ያልቀጠለው የሚለው ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ በደርግ ዘመን የደረሰውን ስነ ልቦናዊ ችግር ሲታሰብ ከባድ ቢሆንም ከዛም በኋላ ግላዊ ህይወት ባሻገር ለአገር መስራት አይቻልም ነበር ወይ? የሚለው የእኔም ጥያቄ ነው፡፡ የትውልዱ አለመቀጠል ግን በርካታ ምክንያቶች ይኖሩታል፡፡
የ1966 አብዮት ሲፈነዳ ከላይ የጠቀስኳቸው እርሾዎች ሆነው አብላልተውታል፡፡ ተማሪውም ጥያቄ የጀመረው ቀደም ብሎ ስለነበረ ነው፡፡ የዓለም የፖለቲካ ሁኔታም ስላገዘው ነው፡፡ ይህ ጉዳይ የ1966ን አብዮት አዲስ ምዕራፍ ቢያስከፍተውም ያ ምዕራፍ ግን መዝለቅ አልቻለም፡፡ ምክንያቱም አንዳንዴ ያልታሰበ ውጤትና ስኬት ሰውን ወደ ሰማይ እንዲመጥቅ ያደርጋል፡፡ በዚህም ምክንያት መነሻን አለማሰብ ነገር ተከስቷል፡፡ ብዙ ፖለቲካ ብስለት ሳይኖር ብዙ ነገሮች ተከሰቱ፡፡ ስለዚህ የ1966 አብዮት ለውጥ አምጥቶ ነበር፡፡ ሆኖም የመከነ ለውጥ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ በሌላ በኩል ለብዙዎቻችን ዛሬ ድረስ የተሻገረ የአገር ፍቅር ሰጥቶን አልፏል፡፡ ስብዕናችንን እንድንሞርድና እንድንሻሻል አድርጎናል፡፡ እኔ ስለ እራሴ ብቻ ነው መናገር የምፈልገው፡፡ ቢያንስ እኔ አጭበርብሬ አላውቅም፡፡ እንዳላጭበረብር ያደረገኝ ግን እኔ ልዩ ሰው ሆኜ ሳይሆን ያኔ የተፈተሸው ማንነቴ ይመስለኛል፡፡ እኔ ለራሴ ጥቅም ብዬ በማንም ላይ ተራምጄ አላውቅም፡፡ ዛሬ 55 አመት ያለፈኝ ትልቅ ሰው ነኝ፡፡ ግን አጭበርብሬ አላውቅም፡፡ ይህን ያላደረኩት ግን የሚፈትነኝ ነገር ጠፍቶ አይደለም፡፡ ህይወትን ለማሸነፍ ይህኛውን መንገድን (ማጭበርበሩን) ብመርጥ እንደሚያዋጣኝ አጥቸው አይደለም፡፡ ግን በዛን ወቅት የተሞረደው ስብዕናዬ ዛሬም ድረስ አብሮኝ ስላለ ነው፡፡ ብዙዎቹ ይህ ስብዕና አላቸው፡፡ እናም 1966 ብዙ ሰው ፈጥሯል፣ ብዙ ሰው ገድሏል፡፡ የገደለው ግን ያመዝናል፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ኢትዮጵያ አሁን ለምትገኝበት ሁኔታ የደረሰችው፡፡ የትም አልደረስንም፤ መዋሻሸት አያስፈልግም፡፡ ዛሬም የትም አይደለንም፡፡ የኢትዮጵያን ህዝብ ወደ ውስጥ ገብተን ካየነው ዛሬም የምንበላው የለንም፣ ዛሬም ድሃ ነን፣ እኔ በዙሪያዬ ብዙ በልተው የማያድሩ ሰዎች አሉኝ፡፡ በዙሪያየ የሚኖረው ህብረተሰብ በታክሲ መሄድ የማይችልና ድሃ ነው፡፡ ጤፍ መግዛት የማይችል ማህበረሰብ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ምክንያት ከ1966 በኋላ በተከሰተው ችግር ነው፡፡ እሴቶቻችንን አጥተናል፡፡ እምነታችንን አጥተናል፡፡ ድሮኮ የእኛ ቤተሰቦች የሆነ ቦታ መሄድ ፈልገው የተሸከሙትን ነገር ቁጥቋጦ ውስጥ ደብቀው ተመልሰው ያገኙት ነበር፡፡ ይህን መጣል ነበረብን? በምን ተክተነው? መጣል አልነበረብንም፡፡ ነገር ግን እምነትን ጣልን፣ መታመንን ጣልን፡፡ አገር ባላደገበት ግን ለራሳችን ለማደግ ብንፍጨረጨርም ከመውደቅ አንድንም፡፡ አንድን ነገር ይዞ ለመዝለቅና ለመነሳሳት ከውስጥ እርሾ ታስፈልጋለች፡፡ 1966ንም የወለደው ያ እርሾ ነበር፡፡ ነገር ግን መነሻው ጥሩ አልነበረምና የተጋገረው ዳቦ ሊጥ ሆነብን፡፡ እናም እዚህ ደረስን፡፡

(ከአዘጋጁ:- ይህን ጽሑፍ ያሰናዳነው ቆንጅት ብርሃኑ ባለፈው ቅዳሜ በሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ተገኝተው ለወጣት የፓርቲው አባላት የትግል ልምዳቸውን ባካፈሉበት ወቅት ከተናገሩት ውስጥ ነው፡፡)