ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም አንድነት በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የያዘውን ፕሮግራም እንዲያራዝም መጠየቁን ተከትሎ አንድነት ሰልፉን ለሚያዚያ 5 ቀን 2006 በማራዘም የእውቅና ደብዳቤ ጠይቆ ነበር፡፡ መስተዳድሩ በዕለቱ ሌላ ፕሮግራም መየዙን በማውሳት ሰልፉ ሚያዚያ 4 ቀን 2006 ሊደረግ እንደሚችል የእውቅና ደብዳቤ ለፓርቲው ጽፎ ነበር፡፡ ፓርቲው በበኩሉ ዕለቱ ለሰላማዊ ሰልፍ አመቺ አለመሆኑን አስረድቷል፣ መስተዳድሩ ፓርቲው […]

ሎንዶን ብሪታን ዉስጥ በዝቅተኝነት ከሚመደቡት ትምህርት ቤቶች በአንዱ ይማር የነበረ አዳጊ ኢትዮጵያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቢድ ካምሮንን ጨምሮ የሀገሪቱ 19 ሚኒስትሮች ወደተማሩበት ኮሌጅ የመግባት እድል አገኘ።

‘አረና ትግራይ’ በትግራይ ክልል ምሥራቃዊ ዞን አፅቢ ወምበርታ ሕዝባዊ ስብሰባ ለማካሄድ በተንቀሳቀሰበት ባለፈዉ ቅዳሜና እሁድ ከፍተኛ የአመራር አባላቱን ጨምሮ አባላቱና ደጋፊዎቹ መታሰራቸዉንና በድንጋይ መደብደባቸውን አመለከተ።

በአሁኑ ወቅት የአፍሪቃና የአውሮፓ የኤኮኖሚ ግንኙነት አዲስ አቅጣጫ እንዲከተል ያስፈለገበት ምክንያትና ጥቅሙ ምንድነው ? የኤኮኖሚ ግንኙነቱ በሁለቱ ክፍለ ዓለማት የፖለቲካና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይስ ምን ዓይነት ተፅእኖ ያሳድራል ?ከኤኮኖሚው ዓለም የሚያነሳቸው ጉዳዮች ናቸው ።

በዛሬው የሙዚቃ ቃና ፕሮግራም በአሜሪካ የቢል ቦርድ ሰንጠረዥ ላይ ከመቶዎቹ ምርጥ ዜማዎች መካከል በዚህ ሳምንት ከአንድኛ እስከ አስረኛ ደረጃ የወጡትን ምርጥ ዜማዎች ያጠቃልላል::

በማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ በአክራሪነት የተፈረጁት ‹አንዳንድ ግለሰቦች›÷ ‹‹አንዲት ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት›› የሚሉቱም ናቸው፡፡ ታዲያ ምን ይበሉ?! ‹‹በይፋ አክራሪ ናችኹ ያለን አካል የለም፡፡›› /ተስፋዬ ቢኾነኝ፤ የማኅበር ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ/ ‹‹በጉዳዩ ላይ የጠራ ነገር የለም፤ ነገር ግን ጢስ አለ፡፡ ከጢሱ በስተጀርባ ያለው እሳት ይኹን እሳተ ገሞራ ባይታወቅም ለጊዜው ግን ማኅበሩን በተመለከተ ግልጽ የኾነ ነገር የለም።›› /ዲ.ን ዳንኤል ክብረት/ …

የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እሁድ መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም የበጎ ፈቃድ ደም ልገሳ አደረጉ፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ የሴቶች ጉዳይ አስተባባሪነት የተዘጋጀው ይህ ፕሮግራም እሁድ መጋቢት 28 ቀን 2006 ከቀኑ 7 ሰዓት እስከ 9፡ 45 ‹‹በጎ ፍቃደኝነት ለነጻነት›› በሚል መርህ በፓርቲው ጽህፈት ቤት ተከናውኗል፡፡

ዋና ዓላማውን በወሊድ ጊዜ በሚፈጠር የደም መፍሰስ ምክንያት የሚከሰት የእናቶች ሞትን ለመቀነስ መሆኑን የፓርቲው የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ ወ/ሮ ሀና ዋለልኝ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

የለጋሾቹ ምስል በከፊል

የሚቀጥለውን ትረካ ለመጻፍ ብዙ ሀሳብ ውስጥ ገብቼ ነበር፡፡ ብጽፈውስ ምን ዋጋ አለው የሚል ስሜትም ተጭኖኝ ነበር፡፡ ሆኖም ‹ጅብ በማያውቁት ሀገር ቁርበት አንጥፋልኝ› እንዲሉ ከላይ የተጠቀሰው ብርሃኑ ደቡር አባ መላ በአዲሶቹ አለቆቹ የተረቀቁለትን ቃለ መጠይቆች ሲያነበንብ መስማቱ ስለሰለቸኝ ‹ማን ያውጋ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ› በማለት የልጅነት ጓደኛዬን ሳልወድ ለማጋለጥ ወሰንኩ፡፡ እኔና ብርሃኑ ዳምጤ በአንድ ማዕድ እየበላን […]

ወ/ሮ አስቴር  ማሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ማሻሻያ ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል፡፡

በኢትዮጵያ አንዲት ሴት እንዲህ ባለው ከፍተኛ ሥልጣን ላይ ስትቀመጥ ወ/ሮ አስቴር የመጀመሪያዋ ናቸው፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ

በደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ወገኖች መካከል ሲካሄድ የቆየው ድርድር ይህን ያህል ጊዜ በመውሰዱ ደስተኞች አይደለንም ሲሉ የምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች የጋራ ልማት ባለሥልጣን – ኢጋድ ዋና አደራዳሪ የቀድሞ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም መስፍን ተናግረዋል።

የመንግሥትና የተቃዋሚ ተደራዳሪዎች ደረስንበት ያሉት ስምምነትም የተፈቱትን ባለሥልጣናት ያላካተተ ነው ሲሉ እንደማይቀበሉት ገልፀዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ

ለአፍሪካ የጤና ባለሙያዎች የጋራ መድረክ ይፈጥራል የተባለ የመላ አፍሪካ የሕክምና ዶክተሮችና የጤና ጉባዔ ከሁለት ሣምንታት በኋላ አዲስ አበባ ላይ ይካሄዳል፡፡

በዓይነቱ በአፍሪካ የመጀመሪያ እንደሆነ የተገለፀው ጉባዔ የሚዘጋጀው በአሜሪካ፣ በአውሮፓና በአፍሪካ ከሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ማኅበራትና ድርጅቶች ጋር በመተባበር ነው፡፡

እስክንድር ፍሬው ከሚያዘጋጁት ድርጅቶች ተወካዮች ጋር ተነጋግሯል፤ ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይዘሮ አስቴር ማሞን የሲቭል ሰርቪስ ሚንስትር እና በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር እና ሪፎርም ክላስተር አስተባባሪ እንዲሆኑ በዛሬው ዕለት ሾመ። ምክር ቤቱ ይህን ሹመት ያፀደቀው በጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አቅራቢነት ነው።

«በቅርቡ ከአንድነት ለደሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጋር ለመዋሃድ ጥረት እያደረጋችሁ ነው ያላችሁት። ሂደቱ ምን ላይ ይገኛል ? » በሚል ከአዉስትራሊያ ከሚገኝ ኤስ፣ብ.ሲ ራዲዮ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የመኢአድ ሊቀመነበር አቶ አበባዉ መሃሪ በአንድነት እና በመኢአድ መካከል ያሉ ልዩነቶች ከባድ እንዳልሆኑ በመግልጽ ፓርቲዎቹ ዉህደት እንደሚፈጽሙ ያላቸውን ሙሉ ተስፋ ገልጸዋል። «ተበታትነን ገዢዉን ፓርቲ ለማሽነፍ ከአብድ ነው» ያሉት አቶ […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የዩክሬንና የሩስያ ውዝግብ ተባብሷል ። በሩስያ ስር መሆን እንፈልጋለን የሚሉ ኃይሎች ካለፈው እሁድ አንስቶ በአንዳንድ የምሥራቅ ዩክሬን ከተሞች ነፃነታችንን አውጀናል እያሉ ነው ። በነዚህ ኃይሎች ላይ ዩክሬን እርምጃ እንዳትወስድ ሩስያ እያስጠነቀቀች ነው ።

ኃይለኛ ትኩሳት፤ ራስ ምታትና የጡንቻ ህመም ከሚያስከትላቸዉ የህመም ስሜቶች ይጠቀሳሉ። በትንፋሽ ሳይሆን ከአካል በሚወጣ ፈሳሽና በመነካካት ይተላለፋል። እስካሁንም መድሃኒት አልተገኘለትም ኢቦላ ቫይረስ። ከሳምንታት በፊት ጊኒ ዉስጥ በሽታዉ ተከስቷል

በስዊድን በካሮሊንስካ ኢንስቲቱት እና በ«ሳይንስ ፎር ላይፍ» በተባለ ድርጅት መሪነት አምስት የስዊድን ዩኒቨርሲቲዎችን ያጠቃለለው የካንሰር ተመራማሪ የጥናት ቡድን በዓይነቱ ልዩ የካንሰር መከላከያ ዘዴ እንዳገኘ

የጥቁር ዓባይ ምንጭ የሆነው የጣና ሐይቅ እና አካባቢው በሚገባ ካልተጠበቀ እና እንክብካቤ ካልተደረገለት በመጪው ጊዜ አሳሳቢ መዘዝ ሊከተል እንደሚችል የጀርመን የተፈጥሮ ጥበቃ ድርጅቶች ጠበብት ጠቁመዋል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

ባለፉት አራት አስርታት ሀገሪቱ አያሌ ተግዳሮቶችን መጋፈጧ ባይዘነጋም፤ በተለያየ ጊዜ ሚሊዮኖችን ካረገፈው አሰቃቂው ረሃብ በማይተናነስ መልኩ ሕዝቦቿን ዋጋ ያስከፈለ ጉዳይ ቢኖር የፍትሕ አለመከበር ያስከተለው ሁለንተናዊ ምስቅልቅሎሽ ነው ብሎ ለመናገር የሚያስደፍሩ በርካታ ማሳያዎች አሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዛሬ እሁድ መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ/ም ዓረና ትገራይ ህዝባዊ ፖለቲካዊ ስብሰባ በምስራቃዊ ዞን አፅቢ ወንበርታ ወረዳ ጠርቶ ያካሄደ ሲሆን ከትናትና ጀምሮ ህዝቡን ወደ ስብሰባው እንዲመጣ የሚቀሰቅሱ አባሎችና አመራሮች ከድንጋይ ውርወራና የቡድን ረብሻ ባለፈ ከተከራዩት አልጋ አስወጥቶ ሌሌት የትም ተጥለው እንዲወድቁ ለማድረግ እጅግ ኢ-ሰብአዊ ተግባር መፈፀሙን ተገልፆ ነበር ፡፡ የአፅቢ ፖሊስ አባላቶቻችን ከተከራየትና ገንዘቡን ከፍለው […]

የአንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ንቅናቄ በሚል የጀመረው እንቅስቃሴ፣ በዉጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ድጋፍ እያገኘ መጥቷል። ኢትዮጵያዉያን በአካባቢያቸው ካሉ የአንድነት ድጋፍ ማህበራት ጋር በመሆን ከሚደግፉት በተጨማሪ፣ የተለያዩ ሲቪክ ማህበራት፣ በዉጭ አገር ያሉ የፖለቲካ ደርጅቶች እንዲሁም ግለሰቦች ሳይቀር፣ ጉዳዩ የአንድ ፓርቲ ብቻ ሳይሆን የሕዝብ ጉዳይ ነው፣ በሚል ከሚሊዮኖች አንዱ ነን እያሉ ነው። ከነዚህ፣ አገር ቤት እየተደረገ ያለዉን እንቅስቃሴ ከሚደግፉ […]

 

ሰኞ፤ መጋቢት 29 የዓለም የጤና ቀን ነው፤ ዕለቱን ምክንያት በማድረግም መንግሥታዊ ያልሆነው ዓለምአቀፍ ድርጅት ኸልፕኤጅ – ኢንተርናሽናል ዛሬ ባወጣው መግለጫ በዓለም ዙሪያ 76 ሚሊየን አዛውንት እጅግ አስፈላጊ የሆኑ የጤና አገልግሎቶችን ተነፍገው እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡

ኸልፕኤጅ “ዕድሜ ተግባር ይጠይቃል” ሲል በሰየመው ዘመቻው ከዕድሜ ጋር የተያያዙ ችግሮችንና የአገልግሎቶች አቅርቦቶች የሚገኙበትን ደረጃ ለማስተዋወቅ እየጣረ ነው፡፡

የኸልፕኤጅ-ኢንተርናሽናል የታንዛኒያ ዳይሬክተር የሆኑት አምለሰት ቴዎድሮስ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “ዕድሜ ተግባር ይጠይቃል” የሚለው ዘመቻ ግብ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ከመሪዎቻቸው ጋር በቀጥታ መነጋገር እንዲችሉ የተጠናከረ አቅም እንዲኖራቸው ማድረግ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን…

 

የጋዜጠኛና መምህርት ወ/ሮ ዓለምሰገድ ኅሩይ አስከሬን የቀብር ሥነ-ሥርዓት ዛሬ፤ ሰኞ፣ መጋቢት 29/2006 ዓ.ም በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መካነ-መቃብር ተፈፅሟል፡፡

ወ/ሮ ዓለምሰገድ ያረፉት ባለፈው ሣምንት መጋቢት 23/2006 ዓ.ም ነበር፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

አሜሪካ የሚገኘዉ የዓለም ዓቀፍ ወንዞች ተቋም፣ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጥናት ያካሄደዉ ቡድን ያወጣዉ ዘገባ፤ ግድቡ በተቀናጀ እና መጠነ ሰፊ ጥናት ላይ ያልተመሠረተ መሆኑን የሚጠቁም እንደሆነ ገለጸ።

ፓሪስ ውስጥ በተካሄደው የማራቶን ሩጫ ውድድር አሸናፊ የሆነው ቀነኒሣ በቀለ ጡንቻው ላይ ህመም ባይሰማው ኖሮ የበለጠ ፈጣን ሠዓት ሊያስመዘግብ ይችል እንደነበር ለዶቸቬለ ገለፀ። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ሊቨርፑል የዋንጫ ግስጋሴውን እያሳመረ ነው። ቸልሲ እና ማንቸስተር ሲቲ ዋነኞቹ የሊቨርፑል ተፎካካሪዎች ሆነዋል።

የምርጫዉ ሒደት፤ነፃነቱ፤ አፎካካሪ፤ አሳታፊነቱም፤ ያዩ እንደመሰከሩት ፤ለእልቂት ፍጅት ማዕከሊቱ ታሪካዊት ሐገር አዲስ ታሪክ ነዉ።አፊቃኒስታን።ዘንድሮ አስራ-ሰወስት ዘመን የተዋጋባትን-የዉጪ ጦር ሸኝታ የአስራ-ዘመን ታሪኳን ለሚቀይር ሌላ ታሪክም ተሞሽራለች።

የአዲስ አበባ መስተዳድር የሰላማዊ ሰልፍና የፖለቲካ ስብሰባ ክፍል ኦፊሰር የሆኑትን አቶ ማርቆስ ብዙነህን ለማነጋገር ዛሬ ጠዋት ወደ ቢሯቸው ያቀኑት ሶስት የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ አመራሮች በኦፊሰሩ ጥያቄያቸው ተቀባይነት ማግኘቱ እንደተነገራቸው ገልጸዋል፡፡ አንድነት ፓርቲ የ‹‹እሪታ ቀን›› በማለት የሰየመውን ሰላማዊ ሰልፍ ለመጋቢት 28 ቀን 2006 ለማድረግ ለመስተዳድሩ የእውቅና ጥያቄ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም መስተዳድሩ በከተማው የህዳሴ ግድቡን የተመለከቱ […]

አንድነት ፓርቲ ለመጋቢት 28/2006 ጠርቶት በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ለህዝብ የተዘጋጀ በራሪ ወረቀት ሲበትኑ በህገ ወጥ መንገድ በቁጥጥር ስር ከዋሉት የአንድነት ፓርቲ አባላት መካከል በስድስተኛ ፖሊስ ጣብያ የሚገኙት አክሊሉ ሰይፉና ወርቁ እንድሮ መታሰራቸውን በመቃወም የርሃብ አድማ መምታታቸው ታውቋል፡፡ ሁለቱ ወጣቶች እስከ ነገ የማይለቀቁ ከሆነ ሚክሲኮ በሚገኘው ፍርድ ቤት ከፖሊስ ጣብያ እንደሚቀርቡ ይጠበቃል፡፡ አንድነት የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ […]

መግቢያ በዚህ ጽሁፍ ሥር ለውይይት ይሆን ዘንድ የምናነሳው ኣሳብ constitutional patriotism ወይም ህገ መንግስታዊ ቀናዒነት ወይም ኣርበኝነት የሚባለው ጽንሰ ሃሳብ ባለፈው በተከታታይ ካቀረብኳት የ Conventional Cultural Unity ወይም በስምምነት ላይ የተመሰረት ባህላዊ ውህደት ካልኩት ኣሳብ ጋር እንዴት እንደሚለያይና በኢትዮጵያ ሁኔታ ከሁለቱ ኣሳቦች የትኛው ተገቢና ችግር ፈቺ ሊሆን እንደሚችል ኣሳብ ለማፍራት ነው። በቅድሚያ ኣንድን ፖለቲካዊ የሆነ […]

እኛ የምናውቃት ኢትዮጲያ ከግማሽ በላይ ህዝቧ በመብራትና በውሃ እጦት የሚሰቃይባት ፣ በስልክና በኔትወርክ ችግር የሚማረርባት ፣ በመልካም አስተዳደር እጦት አሳሩን የሚበላባት ፣ አብዛኛው ህዝቧ የዛሬን እንጂ የነገን ማቀድ የማይችልባት ፣ የተለያዩ ተንታኞችና አለማቀፍድርጅቶች “ችግር አለ” ብለው የሚያስጠነቅቋት ፣ ለዲሞክራሲ ፈር ቀዳጅ መሆን የሚገባው የፖለቲካ ስርዓት የሚያስፈራና ደም ደም የሚሸትባት፣ ብዙ ዜናና ትንታኔ ስለ አንዲት የመንግስት […]