11.10.13 ዜና 16:UTC
የዓለም ዜና
የዓለም ዜና
ደራሲ፤ ዓለማየሁ ገላጋይ
ቅኝት፤ መስፍን ማሞ ተሰማ
መንደርደሪያ
ሰቀቀን ጭንቀታቸውን እንደ ተጋቦ የሚያጋቡ፤ ግፍና በደሉን ጠኔና ጣዕሩን እንደ ሾተል አሹለው፤ ከልብ የሚቸክሉ ከአእምሮ ጓዳ የሚቀብሩ፤ አዝነው የሚያሳዝኑ፤ ተቃጥለው የሚያሳርሩ…ፍትህ ተሟጋች፤ ነፃነት ተፋራጅ፤ ጧፍ ነዳጅ…ደራሲያን፤ ቀመረ ቃላት ጠቢባን…ቢኖሩም…የብዕር ትሩፋታቸው ጨለማን ተጋፍቶ ጨለማን ተዋግቶ የወጣው – ‘ኢምንቱ’ ነው። እነርሱም ቢሆኑ ታዲያ፤ በጨለማ እንደሚተኮስ ርችት ወጋጋናቸው አድማስ ካድመስ የሚያሳይ ብርሃን ሆኗልና፤ እሰየው!!
አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ሰማያዊ ፓርቲ ተከራይቶት የነበረዉን ቤት ‘ለወሔነት’ ባርና ሬስቶራንት ለፔንሲዮን አገልግሎት እንዲሚጠቀምበት ቢሆንም የፔንሲዮኑ ባለቤት የሆኑት አቶ በላቸዉ በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር እና የወረዳ 3 አስተዳደር በግዴታ እንዲከራዩ የእያስገደዷቸዉ ሲሆን አቶ በላቸዉና የቤቱ ባለቤቶች እኛ ተገደን ነዉ ብለዋል፡፡ በተጨማሪም በመነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቤቱን ለፓርቲ ጽ/ቤት እንዳይከራይ እየተከራከሩ ያሉት በአቶ ያለዉ እዉነቱ የጉለሌ ክፍለ ከተማ የህዝብ አደረጃጀት ሃላፊ የሚመሩ የመስተዳድሩ አካላት መሆናቸዉ በይበልጥ ለፓርቲዉ ጽ/ቤትነት ለመጠቀም እንዳንችል መንግስት እጁ እንዳለበት መገንዘብ ተችሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት በመነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ስር የነበሩት የፓርቲ አመራሮች ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ መወሰዳቸዉን አሁን የደረሰን መረጃ ይገልፃል፡፡
በአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ህዝባዊ ንቅናቄ ንቁ ተሳትፎ ያደርጉ ከነበሩ ወጣቶች መካከል ሁለት ደህንነቶች ዘላለም ደበበን ወደ ሚሰራበት የአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ግቢ በመዝለቅ በህገ ወጥ መንገድ ከወሰዱት በኋላ በማስፈራራትና ተራ የስድብ ቃላትን በማዝነብ በመጨረሻ ያለ ምንም ክስ መልቀቃቸው ታውቋል፡፡ እንደሁልግዜው ማልዶ በስራ ገበታው የተገኘው ዘላለም በሚሰራበት የአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ቤተ መጻህፍት ለአዳዲስ […]
ታዋቂው የፖለቲካ ተንታኝና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በሚገኝበት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር በተላለፈ ትዕዛዝ መሰረት የጎብኚዎቹ ቅጥር መወሰኑን የማረሚያ ቤቱ ምንጮች ለፍኖተ ነጻነት ገለጹ፡፡ የመስከረም 19/2006 ሰላማዊ ሰልፍ ብስጭት ከፈጠረባቸው አካላት መካከል አንዱ የሆነው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ብስጭቱን አደባባይ ያወጡበትን እርምጃዎች መውሰድ መጀመሩ እያነጋገረ ነው፡፡ለአንዷለም አራጌ የጎብኚዎቹን ስም እንዲሰጥ ካልሆነ ግን በማንም እንደማይጎበኝ የነገረው አስተዳደሩ የእስክንድርን […]
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ዉስጥ ለሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ተከራይቶ የነበረዉን ቤት ከዛሬ ጥቅምት 1 2006 ጀምሮ ለመጠቀም በሄዱበት ጊዜ የክፍለ ከተማዉ ፍትህ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌታሁን አማረ ፤ የወረዳዉ አስተዳደር ሃላፊዎች ፤- የወረዳ 3 ስራ አስፈፃሚ አቶ አማረ ቤካ ፤ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ አማረ አቡጤ ፤ መነን አካባቢ ፖሊሶች ፤ ፌደራል ፖሊሶች እና ሲቪል የለበሱ የደህንነት አካላት በጋራ በመሆን በማይመለከታቸዉ ጉዳይ የፓርቲዉን ከፍተኛ አመራሮች
1. ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት(ሊቀ መንበር)
2. አቶ ስለሺ ፈይሳ (ምክትል ሊቀመንበር)
3. አቶ ይድነቃቸዉ ከበደ (የህግ ጉዳይ ሃላፊ)
4. አቶ እንዳሻዉ እምሻዉ (የጽህፈት ቤት ሃላፊ)
5. አቶ በቃሉ አዳነ (ምክር ቤት አባል )
6. አቶ ዮናስ ከድር (የምክር ቤት አባል)
7. አቶ ብርሃኑ ተክለ-ያሬድ (አባል)
ወደ መነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እንገልፃለን፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ቀድሞ ከነበረበት ጽ/ቤት ወደ የካቲት 12(መነን) አካባቢ አዲስ ፅ/ቤት ተከራይቶ ከቤቱ ባለቤቶች ጋር ለ2 ዓመት የሚቆይ ውል የተዋዋለ ሲሆን በውሉ እንደተገለፀውም ከዛሬ ጥቅምት 1/2006 ዓ.ም ጀምሮ ቤቱ የሰማያዊ ፓርቲ በመሆኑ ቤቱን ለመረከብ በሄዱበት ወቀት ቤቱን እኛም ተከራይተንዋል በሚሉ ግለሰቦች ቤቱን በፖሊስ ሀይል ታግዘው ይዘውታል፡፡ የፓርቲው አመራሮችም ቤቱን በህጋዊ መንገድ እንደተከራዩትና ከዛሬ ጀምሮ የቤቱ ባለመብቶች እንደሆኑ ለፖሊስ ያስረዱ ሲሆን ይህ ዜና እስከደረሰን እስከ ቀኑ 9 ሰዓት ድረስም አብዛኛው የፓርቲው አመራሮች በፖሊስ ጣቢያ እንደሆኑና በስልክም ማነጋገር አስቸጋሪ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በቀጣይነት የሚኖረውን ሁኔታ እየተከታተልን እናሳውቃችኋለን፡፡
(ፎቶ፡- ፓርቲው ከአከራዮቹ ጋር የገባው ውል)
ለማንበብ http://wp.me/p3MQOW-aH ይጫኑ!
መስከረም ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በ2005 ዓም የስራ ክንውንና በ2006 ዓም የስራ እቅድ በሚል ርእስ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የኢህአዴግ አባላት ግምገማዎች እየተካሄዱ ነው። በኦሮሚያ ክልል በርካታ የኢህአዴግ አባላት የሆኑ የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች አክራሪነትንና ሽብረተኝነትን በተመለከተ ኢህአዴግ የሚከተለውን ፖሊሲ መተቸታቸውን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል። በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ባለው ግምገማ ደግሞ በርካታ የብአዴን አባላት በፓርቲውና …
መስከረም ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነት ጋር በተያያዘ ባለፈው አመት የተጀመረውን ተቃውሞ ተከትሎ 40 ሰዎች በቅርቡ ከእስር ቢፈቱም፣ ከተፈቱት መካከል 20ዎቹ ከስራ ተባረዋል። ከተባረሩት መካከል ዳኞችና አቃቢ ህጎች ይገኙበታል። 14 ቱ ቀደም ብለው የተባረሩ ሲሆን፣ 6ቱ ደግሞ በትናንትናው እለት መባረራቸው ታውቋል። እንዲሁም በወረዳው ሌላ ተቃውሞ እንዲቀሰቀስ እየመከሩ ነው የተባሉ 6 ሰዎች ደግሞ ካለፈው ሀሙስ …
መስከረም ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጣው እንደዘገበው መላኩ ደምሴ ሐሙስ መስከረም 30 ቀን 2006 ዓ.ም. እኩለ ቀን ላይ አዲስ አበባ ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ ከሚገኘው የሪፖርተር ቢሮው በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል የፖሊስ ኃይል አባላት ተይዞ ወደ ሐዋሳ ከተማ ተወሰዷል፡፡ ጋዜጠኛው ለጥያቄ የተወሰደው ሪፖርተር ጋዜጣ ረቡዕ ነሐሴ 29 ቀን 2005 ዓ.ም. በጋዜጣው የፊት ገጽ ላይ ‹‹የደቡብ …
መስከረም ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው ሊቢያው አምባገነን መሪ ቻርለስ ቴለር በጦር ወንጀለኝነት ተከሰው ዘ ሄግ በሚገኘው አለማፉ የወንጀል ፍርድ ቤት የ50 አመታት እስር ከተፈረደባቸው በሁዋላ፣ የእስር ጊዜያቸውን በእንግሊዝ እንደሚፈጽሙ ታውቋል። ቻርለስ ቴለር በሴራሊዮን ጦርነት ወቅት በተቃዋሚዎች የተፈጸመውን ኢሰብአዊ ድርጊት ደግፈዋል በሚል ነበር ጥፋተኛ የተባሉት። የ65 አመቱ ቴለር ቀሪ ህይወታቸውን በእንግሊዝ እስር ቤት እንደሚያጠናቅቁ …
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
News, Cultural Mosaic, Kebele Lives and Environment or Tech
በአክሱም መንግሥት መደበኛ ቋንቋ እንደነበር ይነገራል፤ የግዕዝ ቋንቋ። ዛሬም ድረስ የግዕዝ ቋንቋ በኢትዮጵያ፤ በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እንዲሁም በኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጥቅም ላይ ይዉላል።
ማይ አይኒ በተባለው የስደተኞች ካምፕ ወደ ኢጣልያ ለመሻገር ሲሞክሩ ባለፈው ሳምንት የሞቱትን ኤርትራውያን ለማሰብ ባለፈው ቅዳሜ ማታ ስደተኞቹ ካዘጋጁት የሻማ ማብራት ስነስርዓት በኃላ ባካሄዱት ሰልፍ ብሶታቸውን ሲያሰሙ ነበር ።
አጋቾች ኋላ ላይ እንዳስታወቁት ጠቅላይ ሚንስትሩን ያገቱት፥ ዩናይትድ ስቴትስ በ1990 የናይሮቢና የዳሬ-ሰላም ኤምባሲዎቿን ካጋዩ «አሸባሪዎች አንዱ» ያለችዉን አቡ አነስ አል ሊቢን ባለፈዉ ሳምንት ከሊቢያ አፍና ስትወስድ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተባብረዋል በሚል ለመበቀል ነዉ።
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ለማኝበብ እዚህ ይጫኑ
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር ፊታውራሪነት የአለማቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤትን አሰራር ለመቃወም አፍሪካ መንግስታት በአዲስ አበባ ለአስቸኳይ ስብሰባ መጠራታቸው ታውቋል። ጠ/ሚ ሀይለማርያም ሰሞኑን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ቀርበው የወንጀል ፍርድ ቤቱን ተችተው ነበር። ይህን ተከትሎ በሚመስል ሁኔታ የወቅቱ የህብረቱ ሊቀመንበር መሪዎችን ከጥቅምት 1 እስከ 2 በሚካሄደው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ …
መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የአራት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን የሥራ ዝውውር በዚህ ሳምንት እንደሚያደርግ ሪፖርተር ዘገበ። ጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ጽሕፈት ቤቱ ዝውውሩን የሚያደርገው በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ዓባይ ፀሐዬ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የተፋሰስ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር በሆኑት አቶ ሽፈራው ጃርሶ፣ የአውሮፓ ኅብረትና ቤኔሉክስ አገሮች አምባሳደር …
መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ2005 በጀት ዓመት የአገሪቱ ኢኮኖሚ 9 ነጥብ 7 በመቶ ማደጉን የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር አብርሃም ተከስተ በበርካታ ፈተናዎች ባሉበት ወቅት እንዲህ አይነት እድገት መመዝገቡን አወድሰዋል። የግብርና ዘርፍ በ2005 በጀት ዓመት የ7 ነጥብ 1 በመቶ የአገልግሎት ዘርፉ ደግሞ የ4 ነጥብ 9 በመቶ እድገት መመዝገቡ ተገልጿል። …
መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሰኞ አዲስ ፕሬዚደንት በመምረጥ የዚህን ዓመት ሥራውን የጀመረው የኢትዮጵያ ፓርላማ በፕሬዚደንት ሙላቱ ተሾመ በንባብ የቀረበውን የመንግስት የዚህ ዓመት የትኩረት አቅጣጫና ዕቅድ ጋር በተያያዘ በቀጣይ ሳምንት ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በተገኙበት በሚቀርቡ የድጋፍና የተቃውሞ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ይወያያል፡፡ ፓርላማው በትላንት ውሎው መስከረም 27 ቀን 2006 ዓም አዲሱ ፕሬዚደንት ያደረጉትን …
መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ውይይታቸውን ያደረጉ የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ ጋዜጠኞች ሚዲያዎቹ በመንግስት የአፈና እና የእጅ አዙር ቁጥጥር ስር የወደቁ ናቸው ብለዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተካሄደው የባለሙያዎች የጥናት እና ምርምር ግኝት ስራዎች ላይ ተመርኩዞ ከባለሙያዎች ጋር በተደረገው ውይይት ላይ በቀረቡት ጽሁፎች እንደተገለፀው የኢትዩጵያ ሚዲያዎች አዲስ የሚቋቋሙትም ሆነ ነባር …
መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሱፐር ኤግልስን ካሸነፉ መንግስት እንደሚሰጣቸው ቃል የገባላቸው ቦነስ በቂ እንዳልሆነና ስሜታቸውን የሚያነሣሳ እንዳልሆነ ነው ተጫዋቾቹ የተናገሩት። አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ከቀናት በፊት የ22ቱን ተጫዋቾች ስም ይፋ ያደረጉ ሲሆን፤ በቡድኑ ውስጥ ወሳኝ ተጫዋቾች የሆነው ጌታነህ ከበደ በጉዳት ምክንያት በቡድኑ ውስጥ አልተካተተም። በቀራቸው የደርሶ መልስ ጨዋታ ናይጀሪያን አሸንፈው ለዓለም ዋንጫ ካለፉ …
ሙሉ የመጽሐፉ ይዘት ለማንበብ http://wp.me/p3MQOW-at ይጫኑ!
ላለፉት ሶስት ወራት ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ፣ ሕዝባችን በአራቱም ማእዘናት ለነጻነትና ለዲሞክራሲ ያለዉን ጥማት ለመግለጽና በሚታዩት የዜጎች የሰብአዊ መብት ረገጣ ላይ ያለዉን ተቃዉሞ ለማስተጋባት፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መርህ ስር ሲንቀሳቀስ እንደነበረ በስፋት ተዘግቧል። በጂንካ፣ በአርባ ምንጭ፣ በወላይታ/ሶዶ፣ በባሌ/ሮቢ፣ በፍቼ፣ በአዳማ/ናዝሬት፣ በመቀሌ (በሙሉ ባይሳካም) ፣ በደሴም በባህር ዳርና ፣ በጎንደር የተደረገው የመጀመሪአዉ ዙር የሚሊየነሞች […]
News, Ethiopians in America, Americana, Democracy and Women and Family
ከ 318 ዓመታት በፊት ፣ እ ጎ አ በ 1705 ዓ ም መሆኑ ነው፣ ታላቁ እንግሊዛዊ የፊዚክስ ና የሒሳብ ሊቅ አይዛክ ኒውተን፤ ስለ ስበት ኃይልና ስለብርሃን ምንነት ካደረገው ምርምር ውጭ ፣ ስለ ኅልፈተ ዓለም በማንሳት፤ እ ጎ አ በ 2060 ዓ ም፣
የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አልአሳድ ጀርመን የሶሪያውን ቀውስ እንድትሸመግል እንደሚፈልጉ አስታወቁ። ፕሬዝዳንቱ ለአንድ የጀርመን መጽሔት እንዳሉት የጀርመን ልዑካን ሶሪያ መጥተው የሃገሪቱን አጠቃላይ ይዞታ እንዲመለከቱና በተጨባጩ ሁኔታ ላይ ከደማስቆ መንግሥት ጋር እንዲወያዩ ጠይቀዋል። ይሁንና የጀርመን መንግስት የአሳድን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።
አፍሪቃ ውስጥ ሥራ እያላቸውም በልተው ማደር ያቃታቸው ጥቂቶች አይደሉም። እንደ ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ድርጅት በምህፃሩ ILO መዘርዝር ከሆነ 40 ከመቶ የሚሆን አፍሪቃዊ የሚተዳደረው በቀን ከ25 ብር በታች በሆነ ገቢ ነው።
በተመስገን ደሳለኝ
የኢህአዴግ ታጋዮች የመንግስት ‹‹ጠንካራ ይዞታ›› የሚባሉ ከተሞችን ሳይቀር መቆጣጠር ችለዋል፤ ወደ አዲስ አበባ የሚያደርጉት ግስጋሴም ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃ/ማርያምን እንቅልፍ ነስቷል፡፡ በአንዳች ተአምር ግስጋሴውን መግታት ካልቻሉ፣ በጥቂት ወራት ውስጥ ሁሉም ነገር ታሪክ እንደሚሆን በማወቃቸው፣ መላ በማፈላለጉ ላይ ተጠምደዋል፡፡ በዚህ ጊዜም ነበር (የሃሳቡ አመንጪ ተለይቶ ባይታወቅም) ‹‹ለዩንቨርስቲ ተማሪዎች የአጭር ጊዜ ስልጠና ሰጥቶ፣ ከ ገሪቱ ሠራዊት ጎን ማሰለፍና የ‹ወንበዴ›ውን ጦር መድረሻ ማሳጣት›› የሚለው ሃሳብ እንደ መፍትሄ የተወሰደው፡፡
ክንፉአሰፋ
ትላንት ምሽት። እለተ እሁድ፤ ኦክቶበር 6፣ 2013። ታማኝ በየነ እና ቴዲ አፍሮ በስልክ ያወራሉ። ንግግራቸው ከወትሮው የተለየ አልነበረም። እንደ ቀድሞው እየተቀላለዱ ይሳሳቃሉ። ታማኝ ከዴንቨር–ኮሎራዶ፣ ቴዲ ደግሞ ከሲድኒ– አውስትራሊያ በስራ ላይ ነበሩ። በዚህ የሶስትዮሽ የስልክ ጨዋታ ላይ እኔና ጴጥሮስ አሸናፊም ገብተናል።
(ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ፤ 19ኛ ዓመት ቁጥር 255፤ ነሐሴ 16 – ጳጉሜ 5 2004 ዓ.ም) ዲ/ን ታደሰ ወርቁ* ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ መንግሥታዊ አካላት የወጡ ሰነዶችና የሚሰሙ ንግግሮች ማኅበረ ቅዱሳንን የኦርቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖት አክራሪዎች ማንጸርያ አድርጎ የመውሰድ አዝማሚያዎች እየታዩ ነው፡፡ ይህን የተሳሳተ አቻ ፈጠራ አፅራረ ቤተ ክርስቲያን የራሳቸውን ፍላጎት ሲያራግቡበት ይታያል፡፡ ተከታዩ ጽሑፍ መንግሥት አቋሞቹን የገለጸባቸውን …![]()
‹አቢሲኒያውያን (በተለይ አማራ እንዲሁም ትግራይ) በተለይ ላለፉት 130 ዓመታት በተለይ በኦሮሞ ሕዝብ (እና እንዲሁም በደቡብ ሕዝቦች ላይ) ‹‹ኢትዮጵያውነትን የመጫን›› (ወይም በሌሎች አነጋገር በኢትዮጵያ ክልል አጥሮ በማስገባት እና በጉልበት በማስገበር) ቋንቋቸውን፣ ባሕላቸውን፣ እምነታቸውን እና ጠቅላላ ማንነታቸውን የሚያጠፋ (ወይም በአማራነት የሚተካ – amharanize የሚያደርግ) በደል /ጭቆና/ አድርሰውባቸዋል› የሚለው ከሞላ ጎደል ጉዳዩን የሚገልጸው ቢሆንም በተለያዩ አካላት ግን የተለያየ አተረጓጎምና የቃላት አጠቃቀምም ጭምር ይኖረዋል፡፡
ለማንበብ http://wp.me/p3MQOW-a4 ይጫኑ!
መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከአማራ ክልል ባለስልጣናት ባገኘው መረጃ የጃን አሞራ፣ የማይጸብሪ አዋሳኝ፣ ራስዳሸንን ጨምሮ የአዲአርቃይን አካባቢዎች ወደ ትግራይ፣ በመተማ በኩል ደግሞ የተወሰነውን ክፍል ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለመስጠት ድርድር በመካሄድ ላይ ነው። ባለስልጣናቱ ቀደም ብለው የህዝቡን የልብ ትርታ ለማዳመጥ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር የደረሰን መረጃ የሚያመለክት ሲሆን፣ አንዳንድ የወረዳ ባላስልጣናት ጉዳዩን ወደ …
መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰማያዊ ፓርቲ ትናንት ባወጣው መግለጫ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በምስራቅ ጎጃም በአዋበልና አነደድ ወረዳ የሚገኙ ስምንት አብያተ ክርስትያናት ከሚያዚያ እስከ ነሐሴ 2005 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ብቻ በእሳት ተቃጥለው በቤተክርስቲያናቱ ውስጥ የሚገኙ ነዋየ ቅድሳት፣ ልዩ ልዩ አልባሳት፣ ብዙ መጽሐፍትና ንብረት መውደሙን ጠቅሷል። ፓርቲው እንዳለው የአካባቢው ነዋሪዎች በመንግስት በኩል ምክንያቱ …
መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከፍተኛ የአመራር ደረጃ የሚገኙ የኦህዴድ ባለስልጣናት ለ10 ቀናት በአዳማ ከተማ በአክራሪነት እና ሽብርተኝነት ዙሪያ ስልጠና ሲሰጣቸው ከቆየ በሁዋላ፣ አሁን ደግሞ ስልጠናው ወደ ታች አመራር አባላት በመውረዱ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የሚገኙ ሰራተኞች ለ10 ቀናት ያክል ጽህፈት ቤቶቻቸውን ዘግተው ስልጠናውን እየወሰዱ ነው። ህዝቡ ጉዳይ ለማስፈጽም ወደ ተለያዩ መስሪያ ቤቶች ሲሄድ …
መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደቡብ ሱዳን ውጪ ጉዳይ ምኒስትር የሆነው ባርናባ ማርያል እንደተናገረው ህዝበ ውሳኔ ባፋጣኝ መደረጉ በአበየ ግዛት ለሚኖሩ ነዋረዎች አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚሰጥና በውሳኔው መሰረት ነዋሪው ወደ ደቡብ ሱዳን ካልሆነ ወደ ሰሜን ሱዳን መቀላቀል እንደሚችል ገልፅዋል:: የደቡብ አፍረካ ሽምጋይ የሆኑት ታቦ እምቤኪይ የሚመራወ የአፍረካ ከፍተኛው አስፈጻሚው አካል የአብየ ሪፈረደም በዚህ ወር …
News, Ask the Doctor, Agriculture and Business
የeለቱ ዜና
ዩኤስ አሜሪካ በሶማልያ እና በሊቢያ በልዩ ኮማንዶዎችዋ ባለፈው የሣምንት መጨረሻ የወሰደችው የጥቃት ርምጃ ከአብራሪ የለሽ የጦር አይሮፕላኖችዋ ይልቅ በልዩ ኃይል ላይ ያተኮረ ሥልት መከተሏን አመላካች ሆኖ ታይቶዋል።
ግዛቲቱን የሚያወድመዉ ጦርነት ለወትሮዉ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ማዕከላዊ መንግሥት እና በሩዋንዳና በዩጋንዳ ይታገዛሉ የሚባሉት የM23 አማፂያን ነበር።ከቅርብ ጊዜ ወዲሕ ግን የኮንጎ መንግሥት ጦር፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጦር፥ በዉጤቱም ጦር ያዋጡት መንግሥታት እና የአማፂያን እና የአማፂያኑ ደጋፊዎች ዉጊያ ሆኗል።
የሰማዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሥለሺ ፈይሳ እንደሚሉት ደግሞ የአዲሱ ፕሬዝዳት አዲስ ነገር በራሳቸዉ ተንቀሳቅሳዉ እንግዳ መቀበል የሚችሉ መሆናቸዉ ነዉ።ዶክተር ሙላቱ ቻይና እና ዩናይትድ ስቴትስ የተማሩ፥ ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በምክትል ሚንስትርነት፥ በሚንስትርነት፥ በአፈ-ጉባኤነት፥ በአምባሳደርነት ያገለገሉ ናቸዉ።
በቅርብ ጊዜ የአውሮፓ የጀልባ ስደተኞች ታሪክ እጅግ አስከፊው አደጋ ነው ። ባለፈው ሃሙስ በኢጣልያዋ የላምፔዱዛ ደሴት አቅራቢያ ወደ 500 የሚጠጉ ስደተኞችን ያሳፈረች ጀልባ በእሳት ከተያያዘች በኋላ ሰጥማ የደረሰው አደጋ ። እንደ እድል ሆኖ 155ቱ ቢተርፉም የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 274 ከፍ ብሏል ።
ወባ ዛሬም ገዳይ በሽታ ነዉ በተለይ በአፍሪቃ። በበሽታዉ በግምባር ቀደምትነት የሚጠቁት ህጻናትና ነፍሰጡር እናቶች መሆናቸዉን የህክምና ባለሙያዎች ያመለክታሉ። በወባ በሽታ በዓለማችን በየዓመቱ ከሚያልቀዉ ህዝብ ቁጥር 80 በመቶዉ የሚገኘዉ አፍሪቃ ነዉ።
የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ልዑካን በአዲስ አበባ ከአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽን ባለሥልጣናት ጋ ምክክር አካሄዱ። ባለሥልጣናቱ ከአንዱ ቀን ውይይት በኋላ ባወጡት የጋራ መግለጫ አፍሪቃ በአህጉሯ ለሚታዩ ውዝግቦች መፍትሄ ለማሰገኘት በምታደርገው ጥረትዋ የዓለሙ መንግሥታት ድርጅት ድጋፍ እንደማይለያት ተገልጾዋል።
በዚህች ቅጽበት በጣም ተናድጃለሁ፡፡ አንዳንዴና መጻፍ ስፈልግ በጣም መናደዴን ብዙም አልከፋበትም፡፡ ካልተናደድኩ የምጽፈው ነገር አለ በቂ ምክንያት ሰዎችን እንዳያስቀይም ወይም ለማስደሰት ብቻ አለ በቂ ምክንያት እንዳያስደስት በማደርገው ሀበሻዊ ይሉኝታ አዘል ጥንቃቄ ወረቀት ላይ የሚቀመጠው ነገር አንዳንዴ ለራሴም ስሜት አልባ የሚሆንብኝ አጋጣሚ አለ – ይህንን ስል ግን ተናድጄ የምጽፈው ሁሉ ቱሪናፋ ነው ማለቴ እንዳልሆነ ግንዛቤ እንድትወስዱ […]