በመሀል አዲስ አበባ ለዘመናት ታጥረው በተቀመጡና ግንባታ ባልተካሄደባቸው ቦታዎች ላይ ጠበቅ ያለ ዕርምጃ እንደሚወስድ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሀል አዲስ አበባን በድጋሚ መገንባት ያስፈልጋል በማለት ነዋሪዎችን ማስነሳቱ ይታወሳል፡፡ አስተዳደሩ በርካታ ኪስ ቦታዎችን ለባለሀብቶች ቢሰጥም፣ ባለሀብቶቹ ግንባታ ከማካሄድ ይልቅ አጥረው የያዟቸው ቦታዎች በርካታ ናቸው፡፡ 

እነዚህ ሕግን ያልተከተሉ አሠራሮች በነዋሪዎች ላይ ቅሬታ እያሳደሩ መሆኑ በተገኙ መድረኮች እየተገለጸ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ የ2007 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ካካሄደ በኋላ፣ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ አሠራሩን ማጥበቅ እንደሚያስፈልገውና የወጡ ሕጐችን በብቃት ማስፈጸም እንደሚገባ መግባባት ላይ መድረሱን አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኃየሎም ጣውዬ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ለመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች ተይዘው ወደ ግንባታ ያልተገባባቸው ቦታዎች ያለባቸውን ችግር በተቀናጀ መንገድ ለመፍታት በዓመቱ ወደ ሥራ ለመግባት ታቅዷል፡፡ በዚህ መስክ ያለውን ችግር አቶ ኃየሎም ሲያስረዱ፣ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ አስፈላጊውን ሥራ ቀደም ብሎ ማጠናቀቅ ቢችልም ለተወሰኑ ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት የማቅረብ ችግር አጋጥሟል፡፡ ‹‹ከዚህ በተጨማሪም ሙሉ በሙሉ ቦታው እስኪፀዳም ግንባታ በመጀመር በኩል መጓተት አለ፡፡ ይህንን ችግር ለመፍታት ከመሠረተ ልማት ተቋማት ጋር በጋራ መሥራት ይኖርብናል፡፡ መንግሥታዊ ተቋማትም በተሰጣቸው ቦታ ላይ ተነሺዎችን በማይጐዳ ሁኔታ ግንባታ እንዲካሄዱ እናደርጋለን፤›› ብለዋል፡፡ 

በርካታ አልሚዎች የወሰዷቸውን ቦታዎች አጥረው ማስቀመጣቸውን በተመለከተም፣ ‹‹በዚህ በኩል ያሉ ችግሮችን በመለየት ውል እንዳይራዘም በማድረግ መሬቱን ወደ መሬት ባንክ የማስገባት ሥራ ይሠራል፤›› በማለት አቶ ኃየሎም ተናግረዋል፡፡ መሥሪያ ቤታቸው ከወትሮው በተለየ ዘንድሮ ጠንካራ ዕርምጃዎችን እንደሚወስድ አስገንዝበዋል፡፡ 

በመልሶ ማልማት ሥራ ከተያዙት አንዱ የሸራተን አዲስ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ይገኝበታል፡፡ ለዚህ ቦታ በ2002 ዓ.ም. ነዋሪውን የማንሳት ሥራ ቢጠናቀቅም በዚህ ቦታ ላይ የሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ጋራዥ ባለመነሳቱ ብቻ ወደ ግንባታ ሳይገባ ቆይቷል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ ተለዋጭ ቦታ የተሰጠው የራሱን ግንባታ ሳያካሂድ ከዚህ ቦታ ላይ የመነሳት ፍላጐት አላሳየም ተብሏል፡፡ ነገር ግን የአካባቢው ነዋሪዎች ቦታውን ከለቀቁ ከአምስት ዓመት በላይ ተቆጥሯል፡፡  

ከዚህ በተጨማሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስፋፊያ፣ አሮጌው ቄራ ቁጥር አንድና ቁጥር ሁለት ማስፋፊያ፣ ተክለ ሃይማኖት መልሶ ማልማት፣ ሸበሌ ሆቴል ጀርባ መልሶ ማልማት ቦታዎች ይገኛሉ፡፡

እነዚህና ሌሎች በሒደት ላይ ካሉ የመልሶ ማልማት ቦታዎች ላይ ነዋሪዎች እንዲነሱ ቢደረግም፣ የተወሰኑ መኖሪያ ቤቶችንና መንግሥታዊ ተቋማትን ማንሳት ባለመቻሉ ቦታዎቹ ታጥረው ለዓመታት እንዲቀመጡ ምክንያት ሆኗል፡፡ ይህም የነዋሪዎችን ኑሮ አስቸጋሪ ከማድረጉም በላይ በተነሱበት ምክንያት ላይም ጥያቄ እያነሱ እንደሚገኝ እየተገለጸ ነው፡፡ አቶ ኃየሎም እንዳሉት በአሁኑ ወቅት ከመሠረተ ልማት ድርጅቶች ከኤሌክትሪክ፣ ከውኃ፣ ከቤቶች ልማት ጋር በተጠናከረ ሁኔታ በጋራ በመሥራት መሬቱን ነፃ በማድረግ ወደ ልማት ለማስገባት እየተሠራ ነው፡፡

‹‹አስቸጋሪ ሁኔታ እንኳ ቢፈጠር ግንባታውን ከሥር ከሥር ለማካሄድ ዕቅድ ተይዟል፤›› በማለት አቶ ኃየሎም የዘንድሮን ዕቅድ አስረድተዋል፡፡

ከንቲባ ድሪባ ኩማ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ፣ 360 ሔክታር መሬት በመልሶ ማልማት ፕሮግራም ለማልማት ታቅዷል፡፡ ይህ ልማት የሚካሄደው እንደ አዲስ ሲሆን፣ ለቦታው ለቤቶች ልማት፣ ለቢዝነስና ለባለ ኮከብ ሆቴል የሚውል ነው፡፡  በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለ90 ባለሀብቶች የተሰጠ መሬት ግንባታ ያልተካሄደበት በመሆኑ መናጠቁን ገልጸዋል፡፡

ከንቲባው እንዳሉት፣ በተካሄደው ግምገማ በአዲስ አበባ ከተማ መሬት ወስደው ግንባታ ያላካሄዱ አልሚዎች ከፍተኛ አቅም ያላቸው ናቸው፡፡ እነዚህ አልሚዎች ለምን ግንባታ እንዳላካሄዱ በሚመረመርበት ወቅት የከተማው አስተዳደር ችግር አንዱ ምክንያት ሆኖ ተገኝቷል፡፡ 

በዚህ ምክንያት አስተዳደሩ ያለበትን ችግር በመቅረፍ በዚህ ዓመት ወደ ግንባታ እንዲገባ ግፊት እንደሚደረግ፣ አልሚዎቹ ወደ ግንባታ የማይገቡ ከሆነ ግን ዕርምጃ ይወስዳል በማለት ከንቲባው አስረድተዋል፡፡ 

 

መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ የቀድሞው የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ትህዴን) ሊቀመንበር አቶ ሞላ አስጎደም ለ14 ዓመታት የነበሩበትን ድርጅት ከድተው ለኢህአዴግ ባለስልጣናት እጃውን መስጠታቸውን ተከትሎ ገዢው ፓርቲ እየሰራ ያለው የቅስቀሳ ስራ በህዝብ ዘንድ የተለያዩ አስተያየቶችን እያስተናገደ ነው። የመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ትህዴን የአርበኞች ግንቦት7 አንድ የጦር ክፍል እንደሆነ አድርገው ማቅረባቸው፣ …

መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ከሆኑት መካካል ኡስታዝ ያሲን ኑሩ፣ ሳቢር ይርጉ፣ አቡበከር ዓለሙ እና ገጣሚው ሙኒር ሁሴን ከእስር መለቀቃቸውን አስመልክቶ ድምፃችን ይሰማ ባወጣው መግለጫ፣ ሁሉም እስረኞች ካለምንም ቅድመ ሁኔታዎች እስካልተፈቱ ድረስ ትግላቸው እንደሚቀጥሉ በአጽንኦት ገልጿል። ድምፃችን ይሰማ ፣ ” ተፈቺዎቹም ይሁኑ ታሳሪዎቹ ጀግኖቻችን ሃይማኖታችን በተደፈረበት፣ …

መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በለቡ መዝናኛ ውስጥ ከሴት ጓደኛዋ ጋር በመዝናናት ላይ የነበረችው ሰሎሜ ጉልላት የተባለችው የ20 ዓመት ወጣት ”አንቺ ሰው የማታናግሪው ለምንድ ነው?” በሚል ተልካሻ ምክንያት መሳሪያ የታጠቀው የፌደራል ፓሊስ አባል ተኩሶ ገድሏታል። ታጣቂው በወቅቱ እራሱንም ለማጥፋት ጭንቅላቱ አካባቢ ላይ ያቆሰለ ሲሆን፣ ሳይሞት በሕይወት መትረፉንና በሕክምና ላይ እንዳለ ለማወቅ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ የወንጀል ምድብ ችሎት በብርሃኑ ተክለ ያሬድ መዝገብ በተከሰሱ አራት የሰማያዊ አመራር አባላት ላይ ብይን ለመስጠት ዛሬ ቢሰየምም ለውሳኔው ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ።

በፍኖተ-ዴሞክራሲ ሬዲዮ ለቀረበው ውንጀላ የተሰጠ አጸፋዊ መልስ ሠሞኑን የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ንብረት የሆነው «ፍኖተ-ዴሞክራሲ» በመባል የሚታወቀው የሳተላይት ሬዲዮ ጣቢያ በዐማራው ነገድ ተወላጆች ላይ የጅምላ ክስ አቅርቧል። ክሱ «በአማራ ሕዝብ ስም ሌሎችን መዝለፍ የሚወገዝ ነው» በሚል ርዕስ ያዘጋጀውንመግለጫ ነሐሴ ፳፪ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. በሬዲዮ አስተላልፏል[1]፤ በጽሑፍ ደግሞ በተባባሪ ድረ-ገፆች «አሲምባ[2]» እና «ደብተራው[3]»አሠራጭቷል። ከሁሉም የሚያሣዝነው […]

ኢትዮጵያ ውስጥ እያደገ የመጣው የሰብዓዊ ዕርዳታ ፍላጎት ከሚሰጠው ምላሽ ጋር ሊጣጣም እንዳልቻለ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ – ኦቻ የአዲስ አበባ ፅሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

(ሪፖርተር፤ ነአምን አሸናፊ፤ መስከረም ፪ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.) የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፖፕ እና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ካልዕ፣ በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ላይ ለመታደም እና የአራት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ፣ መስከረም ፲፭ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. ከቤተ ክርስቲያኒቱ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋር በመኾን አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡ ፓትርያርክ አቡነ ቴዎድሮስ አራት ቀናት …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌዴራል የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን የባለስልጣናትን ሐብት ምዝገባ ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ እንደተሳነው የኮምሽኑ ምንጮች አጋለጡ፡፡ ለጠ/ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑትን የኮምሽኑ ኮምሽነር ዓሊ ሱሌይማን ትዕዛዝ ተቀብለው ብቻ የሚያስሩና የሚፈቱ በመሆናቸው በአዋጁ መሰረት ለህዝብ ይፋ መደረግ የነበረበት የባለለስጣናት የሐብት ምዝገባ በወቅቱ ለማከናወን ድፍረት ማጣታቸው ታውቆአል፡፡ የሐብት ምዝገባ ሥራን በኢንፎርሜሽን …

የኢትዮጵያ፤ የሱዳንና የግብፅ የጋራ ኮሚቴ ባለፈዉ መጋቢት ጥናቱን እንዲያደርጉ የመረጣቸዉ ሁለቱ ኩባንዮች የጥናት ዉጤታቸዉን ባለፈዉ ነሐሴ ማብቂያ ለኮሚቴዉ ማቅረብ ነበረባቸዉ

”ከሚያዚያ ወር ጀምሮ የ7ዓመት ግምገማ እያደረግን ቆይተናል። በዚህም ሞላ በፖለቲካ አመራር ድርጅቱን አዳክሞታል የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰናል። ሰራዊቱ የአመራር ለውጥ በሚፈልግበት ጊዜ ላይ በተካሄደው በዚሁ ግምገማ ሞላ ከፍተኛ ተቀውሞ ከድርጅቱ አመራሮችና አባላት ደርሶበታል። ” ”ይዞ የወጣው ታጋይ ቁጥሩ ተጋኗል። ያም ቢሆን ለስራ ተብለው(የኪነት ቡድኑ ለበዓል) የተታለለ ነው። በተቻለን መጠን አብዛኛውን መልሰናል። የተዋጋው ከእኛው ጋር ነው። […]

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፋይናንሻል ታይምስ እንደዘገበው ባለፈው ታህሳስ ወር 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዳላር ከግል ባንኮች የተበደረው መንግስት፣ ተጨማሪ በድር ለመውሰድ እንቅስቃሴ ጀምሯል። በሚቀጥለው ሳምንት የመንግስት ባለስልጣኖች ከአበዳሪ ተቋማት መሪዎች ጋር ለንደን ውስጥ ይገናኛሉ። ላዛርድ የተባለ የመንግስት የገንዘብ አማካሪ ድርጅት ባለስልጣኖቹን ከጀርመኑ ዶች ባንክና ከአሜሪካው ጄፒ ሞርጋን ሃላፊዎች ጋር እንደሚያገናኛው የዘገበው …

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቀድሞው የህወሃት አባልና በሁዋላም የአፋር ፓርቲ መስርተው የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆነው ለ20 አመታት በስልጣን ላይ የነበሩት አቶ እስማኤል አሊ ሴሮ ከስልጣናቸው ከተነሱ በሁዋላ፣ የአብዴፓ ሊቀመንበር ሆነው በተመረጡት በአቶ ጠሃ ሙሃመድ ቡድንና በአቶ አሊ ሴሮ ቡድን መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል። የውዝግቡ መነሻ አቶ ጠፋ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሊሆኑ …

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በንግድ ስራ የምትደዳረዋ ካሚል ሙሃመድ ታውኒ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አላት በሚል በኬንያ ልዩ ፖሊስ ተይዛ ለሶማሊና ለኢትዮጵያ መንግስታት ተላልፋ መሰጠቷን ተከትሎ ሰቆቃ እንደተፈጸመባት ተናግራለች። ቃሏን ለፍርድ ቤት ስታሰማ እንባዋ ያቋርጣት እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል። ወ/ት ትዌኒ የህክምናዋን ወጪ ለመሸፈን የኬንያ መንግስት የገንዘብ ካሳ እንዲሰጣት ፍርድ ቤትን ጠይቃለች። ፍርድ …

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በማዕከላዊ ሶማሊያ ሂራን ግዛት ራሶ መንደር አቅራቢያ የ20 ና የ25 ዓመት ወጣት የሆኑት ወንድማማቾች ሶማልያዊያንና አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ በአልሸባብ ታጣቂዎች በግፍ ተገለው ተገኝተዋል። ሁለቱ ወንድማማቾች ባለፈው ሳምንት ነበር በቡቃበል ከተማ ውስጥ በድንገት የኢትዮጵያ ወታደሮችና የሶማሊያ መንግስት ሰራዊቶች አካባቢውን ለቀው ሲወጡ በአልሸባብ ሚሊሻዎች ታግተው የተያዙት። የአካባቢው …



አንድ ጆሮና ጊዜ የገጠሙለት ሰው ነበር አሉ፡፡ ሰውዬው የተማረው ትምህርት የለውም፡፡ ሁለት ችሎታ ግን ነበረው፡፡ ሲባል የሰማው እውነትም ይሁን ስሕተት ልቅም አድርጎ ይይዝና ሌላ ቦታ ሄዶ የተማረው ያህል ያንደቀድቀዋል፡፡ ሁለተኛው ችሎታው ደግሞ አፈ ጮሌ ስለሆነ ነገር በምላሱ ይቆላል፡፡ ያንንም ይኼንንም እያቆላመጠ ከተማሩትና ከተመራመሩት በላይ ከብሮና ታፍሮ ይኖራል፡፡ አንድ ቀን የማያውቀውን ቀለም ሲያዜም የሰሙት ሊቅ አፍረው አቀረቀሩ፡፡ እርሱ ግን ከዕውቀት የደነገለ ነበርና አልገባውም፡፡ በኋላ ቀረብ ብሎ ‹ደኅና ነዎት የኔታ› አላቸው፡፡ እርሳቸውም ‹ደኅና ነህ›› ብለው ዝም አሉት፡፡ እርሱም ያላወቁት ስለመሰለው ‹አላወቁኝም መሰል መሪጌታ እኮ ነኝ› አላቸው፡፡ሊቁም ‹ዐዉቄሃለሁ› አሉት፡፡ እንዳቀረቀሩ፡፡ ‹ታድያ ምነው ካወቁኝ ከነ ማዕረጌ ሳይጠሩኝ ቀሩሳ› አላቸው፡፡ ‹አንተን አከብራለሁ ብዬ ሞያውን እንዳልሰድበው ፈርቼ ነው›› አሉት ይባላል፡፡
 
እኔም ‹እርቲስቶቻችን› የሚለው ቃል በትእምርተ ጥቅስ ያደረግኩት ሊቁ የፈሩትን ፈርቼ ነው፡፡ እንዳልተውባቸው ደግሞ ምን ብዬ እንደምጠራቸው ግራ ገብቶኝ፡፡ የአዲስ ዓመት ዋዜማውን መርሐ ግብር በዕለቱ ለማየት ስላልቻልኩ ቪዲዮውን ነው የተመለከትኩት፡፡ ሊነግሩን የፈለጉት ስለ እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ፣ ስለ ሀገራችን ዕድገት፣ ስላለፈው ስኬታችን ቢሆንም እንኳን የቀረበው ዝግጅት ግን አደገች የምትባለውን ኢትዮጵያን የማይመጥን፣ ጥበብ ዞር ብላ ያላየቺው፣ ከንግግር ከፍ፣ ከፉከራ ዝቅ ያለ፤ ከፕሮፓጋንዳ ወረድ፣ ከዲስኩር ራቅ፣ ከድንፋታ ጠጋ ያለ ወለፈንዲ ሆኖ ነው የታየኝ፡፡ 
 
በሀገራችንኮ የልቅሶ ሥነ ሥርዓት እንኳን ወግ አለው፤ ጥበብ አለው፤ ትርዒት አለው፤ ፍሰት አለው፤ ድባብ አለው፤ ፈጠራ አለው፤ ርቀት አለው፣ ምጥቀት አለው፤ ደረጃ አለው፡፡ ይኼኮ ወግ የለው፣ ጥበብ የለው፣ ትርዒት የለው፣ ፍሰት የለው፣ ፈጠራ የለው፣ ደረጃ የለው፡፡ ድፍረት ብቻ፡፡ መሪዎቻችን ግን ለምንድን ነው የጥበብ አማካሪ የማይኖራቸው? ለምንድን ነው ጥበብን ከሚሰድቡ ሰዎች ጋር አብረው የሚቆሙት? ለምን ‹አርቲስቶቹን› እናከብራለን ብለው ሞያውን ይሰድቡታል? ይህቺ ሀገርኮ ሰማየ ሰማያት ደርሰው የመጡ፣ ድንጋዩን አቅልጠው ጥበብ የሚያፈልቁ፣ አራት ጸሐፊ አስቀምጠው አንድ አንድ ምዕራፍ እየነገሩ መጽሐፍ የሚያስጽፉ፤ መሰንቆ እንደ ሰው፣ ክራር እንደ ወፍ፣ በገና እንደ መልአክ የሚያናግሩ፤ ስንትና ስንት ጠቢባን ነበሩባት፡፡ ከሐይቅ ዳር የሸንበቆ ውዝዋዜ ተነሥተው ኅሊና የሚመስጥ አቋቋም የቀመሩ፣ እያዜሙ ሲሄዱ እንኳን ገበሬውን በሬዎቹን የሚያስደምሙ ጠቢባን ነበሩባት፡፡ እንዴት በጥበብ ሀገር በኢትዮጵያ ጠቢብ ነኝ የሚል ሰው ‹ከዕውቀት ርቆ፣ ንጽሕ ጠብቆ› በድፍረት ይኖራል? ይኼኮ ሀገርን መድፈር ነው?  
አገሪቱ አድግበታልሁ፣ እመነደግበታለሁ፣ እለወጥበታለሁ፣ አሰላለፌን አስተካክልበታለሁ ብላ የደከመችበት የአምስት ዓመት ዕቅድ እንዴት በስሕተትና በድፍረት በተሞላ መድረክ እንዲታወጅ ይፈቀዳል? ይህንን ዕቅድ ባስታወስን ቁጥር ያንን ትልቅ ስሕተት እንድናስታውስ ለምን ተፈረደብን? ጥበብ ሳይሆን ድፍረት ትዝ እንዲለን ለምን ተገደድን? 
 
ጥበብ ምንም ዓይነት ይዘት ይኑረው የጥበብን ደረጃ ማሟላት ግን አለበት፡፡ ልማታዊም ሆነ አብዮታዊ፣ ዲሞክራሲያዊም ሆነ አምባገነናዊ፣ ይዘቱ ይለያይ እንጂ የጥበብ ደረጃው ግን አንድ ነው፡፡ ጥበብም የሚያሰኘው የጥበቡ ደረጃ እንጂ የያዘው ይዘት አይደለም፡፡ እንዴት ምግብ ቤቶቻችን ለምግብ አሠራርና አቀራረብ የሚጨነቁትን ያህል ለሀገራዊ መድረክ የሚጨነቅ ይጥፋ? እንዴት የበያይነቱ ምግብ ያህል ጥበብ በሀገራዊ መድረክ ላይ እንጣ?
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹ሀገራችን የራስዋ የሆነ ልዩ የዘመን አቆጣጠር አላት› ብለው ነገሩን፡፡ እውነት ነው ጠቅላይ ሚኒስትራችን የሀገር ባህል ልብስ ለብሰው በነገሩን የሀገራችን ልዩ የዘመን ቆጠራ እንስማማለን፡፡ ‹አርቲስቶቹ›› ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሳስተዋል፤ ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የዘመን አቆጣጠር የላትም›› አሉን፡፡ ‹‹አዲስ ዘመንም የሚብተው እንደ አውሮፓውያን በእኩለ ሌሊት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን የዘመን አቆጣጠራችን የተለየ ነው ያሉት ተሳስተው ነው›› አሉን፡፡ ኧረ እባክዎን ይጠይቁልን? ለምን ‹‹አርቲስቶቹ›› ጠቅላይ ሚኒስትሩን መቃወም ከፈለጉ የፖለቲካ ድርጅት መሥርተው በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው ተቃዋሚ ፓርቲ አያቋቁሙም? ደግሞስ ለሌሎች ያልተፈቀደ እንዴት ለእነርሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የቀጥታ የዓመት በዓል ሥርጭት እንዲቃወሙ ተፈቀደላቸው? እንደ አሜሪካ የምርጫ ክርክር በቀጥታ ሥርጭት ተቃዋሚና መንግሥት በአንድ መድረክ የሚቀርቡ ከሆነማ እውነትም ሀገሬ ተለውጣለች?
 
የዛሬ ዓምስት ዓመት እንዲሁ ያለ ስሕተት ‹አርቲስቶቹ› ሲሠሩ ዐውቀው በድፍረት ሳይሆን ሳያውቁ በስሕተት ነው ተብሎ ታለፈ፡፡ ዘንድሮ እንዳይደገምም ብዙዎች በሚችሉት ሁሉ አስቀድመው አሳሰቡ፡፡ ሰሚም መስሚያም ጠፋና ስሕተቱ በባሰ ሁኔታ ተደገመ፡፡ ሰውና ሰይጣን የተለያዩትኮ ከስሕተት በመታረምና ባለመታረም ነው፡፡ ወደ ሥልጣኔው መሄድ ሲገባን ወደ ስ…   
ጠቅላይ ሚኒስትር ሆይ፤ አሁን ማንን እንመን? እርስዎን እንመን ወይስ ‹አርቲስቶቻችንን››?
  

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “ስለሚያገባን እንጦምራለን” በሚል መሪ ቃል ከዛሬ አራት ዓመት በፊት የተቋቋመው የዞን ፱ ዐምደ መረብ ጸሃፍት የሕገመንግስቱ የመጻፍ ነጻነት በሚፃረረው መልኩ እንደ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በአሸባሪነት ተከሰው ካለ ፍትሕ በእስር ቤት የሚገኙት ጦማሪያኑና የቡድኑ አባላት ለፕሬስ ነፃነት ላደረጉት አስተዋፆ ዓለማቀፉን የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ተሸላሚ አድርጓቸዋል። የጋዜጠኞች መብት …

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የታዋቂዋ አርቲስት የቀብር ስነስርዓት በ ቅድስ ስላሴ ካቴደራል ወዳጅ ዘመዶቿና አድናቂዎቿ በተገኙበት ተፈጽሟል። አርቲስት ሰብለ ተፈራ በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ወሎ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አይቤክስ ሆቴል አካባቢ በግንቦት ወር 1968 ዓም. የተወለደች ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በንፋስ ስልክ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቃለች። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷንም በዛው …

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታጋይ መኮንን ተስፋዬ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት ድርጅቱ ከሚያዚያ እስከ ነሃሴ በነበሩት ወራት ከታች እስከ ላይ የ7 ዓመታት ግምገማ አድርጓል። የሞላ አመራር “ትህዴንን ወደ ድል አላበቃውም ይቀየር” የሚል ጥያቄ በመላ ሰራዊት አባላት መነሳቱን የተነገሩት ምክትል አዛዡ፣ ሞላ አስጎደም አገርህን አድን ከሚለው አዲስ ጥምረት መመስረት ጋር …

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ትህዴን፣ የቀድሞው የድርጅቱ መሪ ሞላ አስገዶም የተወሰኑ ተከታዮቹን በመያዝ በሱዳን በኩል አድርጎ ኢትዮጵያ መግባቱን ተከትሎ በሰጠው መግለጫ ” የተወሰኑ በትግሉ የቆዩና ግላዊ ጥቅማቸው የተነካባቸው ግለሰቦች ትግሉን ባሻቸው መንገድ ሊጠመዝዙት ስላልቻሉና በአብዛናው ታጋይ በመድረክ ተይዘው መፈናፈና ስላጡ ተስፋ ቆርጠው ከትግሉ ጎራ ሸስተዋል” ብሎአል። ንቅናቄው …

የባለፈው ሣምንት በኤርትራ የጋራ ንቅናቄ ከመሠረቱት አራት በትጥቅ ትግል የተሠማሩ ንቅናቄዎች የአንደኛው የትግራይ ሕዝብ የጋራ ንቅናቄ መሪ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተገልጿል፡፡

የግብፅ ፖፕ ቴዎድሮስ ዳግማዊ ለመስቀል በዓል አዲስ አበባ ይገባሉ

የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፖፕና ፓትርያርክ ቴዎድሮስ ዳግማዊ በመስቀል በዓል አከባበር ላይ ለመታደምና የአራት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ፣ መስከረም 15 ቀን 2008 ዓ.ም. አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡

የኮፕቲክ ፓትርያርክ ቴዎድሮስ አራት ቀናት በሚወስደው ቆይታቸው መስከረም 16 ቀን 2008 ዓ.ም. የሚከበረውን የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ከመታደማቸው በተጨማሪ፣ ወደ አክሱምና ላሊበላ አቅንተው ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ሥፍራዎችን እንደሚጎበኙም ታውቋል፡፡ 

ከዚህ በተጨማሪም በሚኖራቸው ቆይታ በአዲስ አበባ የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላትን፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ከታዋቂ ግለሰቦች ጋር እንደሚነጋገሩ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ከፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመና ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ፣ እስካሁን ግን የተረጋገጠ ነገር አለመኖሩን አክለው አብራርተዋል፡፡  

ፓትሪያርኩ የአዲስ አበባ ጉዟቸውን አስመልክቶ ከሳምንት በፊት ከግብፅ የውኃ ሀብት ሚኒስትር ሆሳም አል ሞጋሃዚ ጋር መነጋገራቸው የተዘገበ ሲሆን፣ በውይይታቸውም ወቅት ግብፅ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ ያላትን ጥያቄዎች አንስተው ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናትና ከአቡነ ማትያስ ጋር ውይይት እንዲያደርጉ ሚኒስትሩ መጠየቃቸውና የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ተዘግቧል፡፡ 

ፖፕ ቴዎድሮስ በበኩላቸው ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ሁለቱ ቤተ ክርስቲያናት ባላቸው ታሪካዊ ግንኙነት የተነሳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በዚህ ረገድ እየተባበሯቸው እንደሆነና አስተዋጽአቸውም ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል በማለት ስታር አፍሪካ የተሰኘ ድረ ገጽ ላይ የወጣ ዘገባ ያትታል፡፡

የኢትዮጵያ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ባለፈው ጥር ወር ግብፅን ለስድስት ቀናት በይፋ በጎበኙበትና በካይሮ ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግሥት ከፕሬዚዳንት አልሲሲ ጋር በተወያዩበት ወቅት፣ ፕሬዚዳንቱ የዓባይ ወንዝ ለኢትዮጵያውያን የልማት ምንጭ ቢሆንም ለግብፅ ግን ልማት ብቻ ሳይሆን የደም ሥር መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል፡፡ 

አቡነ ማትያስም በበኩላቸው በጠንካራ ትስስር ላይ የተመሠረተው የሁለቱ አገሮች ግንኙነት፣ ከዓባይ የሚመነጭ ውኃ የማያቋርጥ የጋራ ሀብት በመሆኑ በፍትሐዊነትና በእኩልነት ተጠቃሚ የሚኮንበት ይሆናል ማለታቸውም አይዘነጋም፡፡ 

ፖፕ ቴዎድሮስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. በ1952 ማንሱራ በተሰኘ የግብፅ ከተማ የተወለዱ ሲሆን፣ በ1975 ከኤሌክሳንዳርያ ዩኒቨርሲቲ በፋርማሲ የመጀመሪያ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡ ለጥቂት ዓመታት በመንግሥት ቁጥጥር ሥር የሚገኝ መድኃኒት ፋብሪካን ከአስተዳደሩ በኋላ፣ ቅዱስ ፒስሆግ የተባለ ገዳም በመግባት የሥነ መለኮት ትምህርት በማጥናት እ.ኤ.አ. በ1989 ተመርቀዋል፡፡ 

የአቡነ ሺኖዳ ሕልፈተ ሕይወትን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት 118ኛው የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በመሆን ከሦስት ዓመት ወዲህ በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡   

 

 

    በአለማየሁ አንበሴ የፍቅር አዲስ – “ምስክር” ታዋቂዋ ድምፃዊት ፍቅር አዲስ ነቃጥበብ፤እንደ ብዙዎቹ ድምጻውያን ሁሉ ለብዙ ዓመታት ድምጽዋን ሳንሰማ ቆይተናል፡፡ 2007 ዓ.ም ሊሰናበት ጥቂት ቀናት ሲቀሩትና አዲሱ ዓመት ለመጥባት እየተሽኮረመመ ሲጠባበቅ እሷ በመሃል 8ኛ የዘፈን አልበሟን ይዛ ከተፍ አለች፡፡  …

ፍቅር አዲስ ነቃጥበብ ስምንተኛ አልበሟን አውጥታለች Read more »

ድርጅቱ ችግሩን ቀርፌያለሁ ይላል

የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የክፍያ ሥርዓት ችግር እንደገጠመው ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ድርጅት በበኩሉ ችግር ተፈጥሮ እንደነበር አምኖ በአሁኑ ወቅት መቀረፉን ገልጿል፡፡ 

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ድርጅቱ ማዕከላዊ የክፍያ ሥርዓት (ቢሊንግ ሲስተም) ከሁለት ወራት በፊት በገጠመው ችግር ሳቢያ፣ የደንበኞችን ወርኃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያ ለሁሉ ለተባለው የተቀናጀ የአገልግሎት መክፈያ ማዕከል መላክ እንዳልተቻለ ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ 

ደንበኞች ወደ ክፍያ ለሁሉ በሚሄዱበት ጊዜም ትክክለኛ መረጃ እንደማይነገራቸውና በሌላ ጊዜ እንዲመጡ ብቻ እንደሚገልጹላቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ 

ጉዳዩን በተመለከተ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የክፍያ ለሁሉ የሥራ ኃላፊዎች የተፈጠረው ችግር እነሱን እንደማይመለከት ይገልጻሉ፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሚሰጠን የደንበኞች ወርኃዊ ፍጆታ መረጃ መሠረት ደንበኞችን ማስከፈል ነው ሥራችን፡፡ መረጃ ካልደረሰን ማስከፈል አንችልም፤›› ብለዋል፡፡ 

በመሆኑም ጉዳዩ የበለጠ የሚመለከተው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በዚሁ መሠረት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ድርጅት የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ገብረ እግዚአብሔር ታፈረ ተጠይቀው ችግሩ ተፈጥሮ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ 

የማዕከላዊ የክፍያ ሥርዓት ሰርቨር የመረጃ ካርድ በመቃጠሉ ምክንያት ችግሩ እንደተፈጠረ የተናገሩት የውጭ ግንኙነት ኃላፊው፣ ካርዱ በአገር ውስጥ ስለማይገኝና ከውጭ ተገዝቶ እስኪገባ ድረስ የሐምሌ ወር የኤሌክትሪክ ፍጆታን ደንበኞች ማለትም ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚዎች ከሆኑ ድርጅቶች በስተቀር መክፈል አለመቻላቸውን አስረድተዋል፡፡ 

በአሁኑ ወቅት ግን ችግሩ የተቀረፈ በመሆኑ የሐምሌ ወር የክፍያ ቢል መውጣቱንና ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ ደንበኞች የነሐሴ ወር ፍጆታቸውን መክፈል እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡ 

የቀድሞው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽንን ለሁለት በመክፈል በ64.7 ቢሊዮን ብር የተፈቀደ ካፒታልና በ16.2 ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል የተቋቋመው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማኔጅመንት ፓወር ግሪድ ኮርፖሬሽን ለተባለ የህንድ ኩባንያ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ 

ኩባንያው ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎትን በመስጠት ደንበኞችን ማርካት ዋነኛ ኃላፊነቱ ሲሆን፣ መንግሥት ለሁለት ዓመት 16.7 ሚሊዮን ዶላር በመክፈል የሰጠው የማኔጅመንት ኮንትራት ነሐሴ 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ተጠናቋል፡፡ 

 

በያሬድ ቁምቢና ውብዓለም ተስፋዬ የአዲስ አመት ዋዜማ ጳጉሜ 5 ቱሉ ዲምቱ አቃቂ ደብረ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመገኘት ‹የመዳን ቀን ዛሬ ነው› እና‹ የጅራፍ ንቅሳት› የተሰኙ ሁለት የራሷን ግጥሞች አቅርባለች፡፡ ገና በስራዋ ስትታይ ድንቅ የትወና ብቃትና ፈጠራዋ የብዙዎችን ቀልብ መሳብ የቻለች ብርቅዬ ድንቅ አርቲስት ነበረች …ሰብለ ተፈራ፡፡ ፍጹም ባልተጠበቀ እና ድንገተኛ […]

አርቲስት እንድሪስ አህመድ ከ45 አመታት በፊት ነበር በብሄራዊ ቴዓትር ስራ የጀመሩት። ወሎ ክፍለ ሃገር ቢወለዱም ዳንስ የተማሩት በቅጽል ስሙ ውቤ በርሃ ተብሎ በሚታወቀው ደጃች ውቤ ሰፈር ነበር። አርቲስ እንድሪስ አህመድ ቡጊና ትዊስት ከደነሱበት ብሄራዊ ቴዓትር በጡረታ ቢሰናበቱም አሁን በፊልም ትወና ላይ ተሰማርተዋል።

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ዘረኝነትና ጥላቻ በመንግሥት ደረጃ በሚሰበክበት አገር፣ ድንቁርና እጅግ በተጫናቸው የወያኔ ቱባ ባለሥልጣናት ሕዝብ በሚዘለፍበት፣ ታሪክ ተጣሞ የአንድ ቋንቋ ተናጋሪን የሕብረተሰብ ክፍል በሌላው ላይ ለማነሳሳት ሌት ተቀን የሚደክሙና ጉርጓድ የሚምሱ ቡድኖችና ግለሰቦች ባሉበት አገር፣ ፍርሃትና ጥርጣሬ በነገሱበትና አፈና በበረታበት እንደ ኢትዮጵያ ባለ አገር እንደ ቴውድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ‹ ያሉ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በማሕበረሰቡ ውስጥ ያላቸው ሚና በዘፈን […]

አራት በትጥቅ ትግል የሚያምኑ ድርጅቶች፣ የአፋር ድርጅቶች ንቅናቄ፣ የአማራ ሕዝብ ንቅናቄ፣ የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደሚት) እና የግንቦት ሰባት አርበኞች ንቅናቄ ፣ በዚህ ሳምንት ዉስጥ አገር አድን ንቅናቄ በሚል ስያሜ መቀናጀታቸው በስፋት መዘገቡ ይታወሳል። ዶር ብርሃኑ ነጋ የቅንጁት ሊቀመንበር፣ አቶ ሞላ አስግዶም ደግሞ ም/ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል። የአራቱ ድርጅቶች መቀናጀት ይፋ በሆነ በጥቂት ቀናት ዉስጥ ጳጙሜን […]

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላንን የጠለፈው ረዳት ፓይለት መኪና ለጨረታ ቀረበች

በጥር 2006 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ወደ ሮም ጣሊያን ሲበር የነበረውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 767 አውሮፕላን ጠልፎ ጄኔቫ ስዊዘርላንድ ያሳረፈው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራ ንብረት የሆነች የቤት መኪና በሐራጅ ለጨረታ ቀረበች፡፡ 

የሰሌዳ ቁጥር አአ 2-A32521 መኪና ጨረታ ያቀረበው ዘመን ባንክ ነው፡፡ ረዳት አብራሪው ለመኪና ግዢ ከዘመን ባንክ የተበደረው ብድር ስላልተከፈለው ባንኩ ተሽከርካሪዋን በጨረታ ለመሸጥ መገደዱን አስታውቋል፡፡ 

ባንኩ ተሽከርካሪዋን ለጨረታ ያቀረበው በሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 261,503.37 ነው፡፡ ጨረታው የሚካሄደው በመስከረም ወር 2008 ዓ.ም. ነው፡፡ ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን መኪናዋን የገዛው ከአውሮፕላን መጥለፉ ጥቂት ወራት ቀደም ብሎ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

ኃይለ መድኅን ስዊዘርላንድ ውስጥ የፖለቲካ ጥገኝነት ቢጠይቅም የአገሪቱ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎት ፍርድ ቤት አንድ ጊዜ የቀረበ ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ ጉዳዩ በምን ደረጃ ላይ እንዳለ አይታወቅም፡፡ ለስዊዘርላንድ ኢሚግሬሽን ባለሥልጣን በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ 

ኢትዮጵያ ውስጥ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በግለሰቡ ላይ ክስ መሥርቶ፣ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሌለበት 19 ዓመት ፅኑ እስራት እንደተፈረደበት ይታወሳል፡፡ 

 

የአገሪቱ የነዳጅ ግዢ ጥያቄ ተነሳበት

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዓመታዊ የአገሪቱን የነዳጅ ፍጆታ ለመሸፈን የሚያካሂደውን ዓለም አቀፍ ጨረታ በመተው፣ በድርድር ከኩዌት መንግሥት ለመግዛት የተከተለውን አቅጣጫ ነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች ተቃወሙ፡፡ ድርጅቱ ተቃውሞውን አልተቀበለም፡፡

የአንዳንድ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ተወካዮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የነዳጅ ግዢ ጨረታ ማውጣት በመተው የተለያዩ የነዳጅ ውጤቶችን ከኩዌት በድርድር በመግዛት ላይ ይገኛል፡፡ ዕርምጃውን የተቃወሙት የኩባንያ ተወካዮች ውሳኔው አገሪቱን ዋጋ እንደሚያስከፍላት ይናገራሉ፡፡ 

‹‹አንደኛ ከኩዌት የሚገዛው ነዳጅ ውድ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከኩዌት ለሚገዛው ነዳጅ በበርሜል 0.30 ዶላር ጭማሪ ይከፍላል፡፡ ወይም በአንድ የነዳጅ ጫኝ መርከብ ላይ የ60 ሚሊዮን ብር ጭማሪ አለው፤›› ይላሉ፡፡ 

የኩባንያው ተወካዮች በሁለተኛ ደረጃ የሚያነሱት የነዳጅ ጥራት ጥያቄ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በአሁኑ ወቅት በመግዛት ላይ ያለው ነዳጅ የሊድ (እርሳስ) እና ሰልፈር መጠን ከፍተኛ በመሆኑ በአካባቢ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳድራል ብለዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በበኩሉ የቀረቡትን ወቀሳዎች አስተባብሏል፡፡ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ኃይለ ማርያም ለሪፖርተር በሰጡት ምላሽ፣ ከኩዌት መንግሥት ነዳጅ በቀጥታ መግዛቱ የተለያዩ ጠቀሜታዎች አሉት ብለዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ ዓመታዊ የነዳጅ ፍላጎት ከአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ጋር ተቀራራቢ በሆነ ቁጥር፣ በዓመት አሥር በመቶ በማደግ በአሁኑ ወቅት ሦስት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ደርሷል፡፡ አገሪቱ ለነዳጅ ግዢ የምታወጣው የውጭ ምንዛሪ 2.8 ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡ ከወጪ ንግድ የምታገኘው ደግሞ በዓመት ሦስት ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡ 

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት አገሪቱ ላላት የአውሮፕላን ነዳጅ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ከኩዌት የሚገዛ ሲሆን፣ 50 በመቶ የሚሆነውን የናፍጣ ፍላጎት የምታሟላው ከኩዌት በድርድር በሚገዛ ናፍጣ ነው፡፡ ሰባ አምስት በመቶ የሚሆነው የቤንዚን ፍጆታ ከሱዳን መንግሥት ይሸመታል፡፡ ሃያ አምስት በመቶ የሚሆነው የቤንዚን ፍጆታና 50 በመቶ የናፍጣ ፍጆታ የገዛው በግልጽ ጨረታ ከነዳጅ ነጋዴዎች ነው፡፡ የኩዌቱን ነዳጅ የሚያቀርበው የኩዌት መንግሥት ንብረት የሆነው ኩዌት ፔትሮሊየም ኮርፖሬሽን ሲሆን፣ 20 በመቶ ቤንዚንና 50 በመቶ የሚሆነው ናፍጣ የሚመጣው ሳዑዲ ዓረቢያ ከሚገኘው ያንቡ የድፍድፍ ነዳጅ ማጣሪያ ነው፡፡ 

የኢትዮጵያ የዕለት የቤንዚን ፍጆታ አንድ ሚሊዮን ሊትር፣ ናፍጣ 5.8 ሚሊዮን ሊትር፣ የአውሮፕላን ነዳጅ 1.8 ሚሊዮን ሊትር ነው፡፡ ዓመታዊ የነጭ ጋዝ ፍላጎት ደግሞ 260,000 ሜትሪክ ቶን ነው፡፡ ኅብረተሰቡ የኤሌክትሪክ ምድጃዎች በስፋት መጠቀም በመጀመሩ የነጭ ጋዝ ፍላጎት እየቀነሰ መጥቷል፡፡ በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች በ13 የመጠባበቂያ ነዳጅ ዴፖዎች የሚገኙ ሲሆን፣ 360,000 ሜትር ኪዩብ የማጠራቀም አቅም አላቸው፡፡ 

ኢትዮጵያ ከኩዌት ነዳጅ መግዛት የጀመረችው ከኩዌት መንግሥት ጋር ረዥም ጊዜ የፈጀ ውይይት ከተደረገ በኋላ እንደሆነ አቶ ታደሰ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ሚኒስትሮቻችን ሁለት ሦስት ጊዜ ወደ ኩዌት የተመላለሱ ሲሆን፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ከኩዌት የነዳጅ ሚኒስትር ጋር ተገናኝተው የኢትዮጵያን ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ከስምምነት ላይ በመድረሳቸው ነው፤›› ብለዋል፡፡ 

በተደረሰው ስምምነት መሠረት 70 በመቶ የአውሮፕላን ነዳጅ ፍጆታ፣ 50 በመቶ የናፍጣ ፍጆታ ከኩዌት ፔትሮሊየም ኮርፖሬሽን መገዛት መጀመሩን አቶ ታደሰ አስታውሰዋል፡፡ ባለፈው ዓመት የአውሮፕላን ነዳጅ አቅርቦት ኢትዮጵያ ለኩዌት ባቀረበችው ጥያቄ መሠረት ወደ 100 በመቶ አድጓል፡፡ 

ባለፈው ሳምንት በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ በአቶ አህመድ ሺዴ የሚመራ የኢትዮጵያ መንግሥት ልዑክ ወደ ኩዌት ተጉዞ፣ ከኩዌት የነዳጅ ሚኒስቴር ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ በወቅቱም አቶ አህመድ የኩዌት ፔትሮሊየም ኮርፖሬሽን ለኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የሚያቀርበውን የናፍጣ መጠን እንዲጨምር ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ከተቻለ የኢትዮጵያን 100 በመቶ የናፍጣ ፍላጎት እንዲያሟሉ ካልሆነ ግን 70 በመቶ እንዲሸፍኑ ጥያቅ አቅርበዋል፡፡ 

የኩዌት ባለሥልጣናት በበኩላቸው ቀደም ብለው የገቡዋቸው በርካታ ውሎች ስላሉ፣ 100 በመቶ መሸፈን እንደማይችሉ ገልጸው 70 በመቶ የሚለውን ጥያቄ (በ20 በመቶ ማሳደግ) ግን ገምግመው ምላሽ እንደሚሰጡ ለኢትዮጵያ ልዑክ አስረድተዋል፡፡ 

‹‹ከኩዌት ነዳጅ የመግዛት ዕድልን በብዙ ልምምጥ ያገኘነው ዕድል ነው፤›› የሚሉት አቶ ታደሰ፣ ከኩዌት ነዳጅ መገዛቱ ለኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ያስረዳሉ፡፡ 

‹‹ከኩዌት በምንገዛበት ወቅት 90 ቀናት የመክፈያ ጊዜ ይሰጡናል፡፡ ሱዳን የምትሰጠን 30 ቀናት ነው፡፡ ነዳጅ ነጋዴዎች ከ30 እስከ 45 ቀናት ብቻ ነው የሚሰጡን፡፡ የኩዌት ነዳጅ አቅርቦት አስተማማኝ ነው፡፡ ባሉት ቀነ ገደብ ያቀርባሉ፡፡ የዋጋ ክለሳ እንደ ነጋዴዎቹ በየጊዜው አያደርጉም፡፡ የሚጠቀሙት የራሳቸውን መርከቦች በመሆኑ ርካሽ መርከብ ሲፈልጉ ጊዜ አያቃጥሉም፤›› የሚሉት አቶ ታደሰ፣ የዋጋ ልዩነትን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ዝርዝር ጠቀሜታዎችን መመልከት እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል፡፡ 

‹‹ለምሳሌ እኛ ለኩዌት በበርሜል የምንከፍለው ፕሪሚየም ክፍያ (ትራንስፖርትና አገልግሎት) 4.50 ዶላር ነው፡፡ ለነዳጅ ነጋዴዎች በበርሜል 4.10 ዶላር ነው፡፡ ከነጋዴዎች ስንገዛ ኢንሹራንስ የምንከፍለው ራሳችን ነን፡፡ ነጋዴዎቹን ኢንሹራንስ ጨምሩበት ብንላቸው ዋጋቸው ሰባት ዶላር ይገባል፡፡ የኩዌት ግን ኢንሹራንስን ጨምሮ 4.50 ዶላር ብቻ ነው፤›› ብለዋል አቶ ታደሰ፡፡ 

የነዳጅ ጥራትን አስመልክቶ ለቀረበው ተቃውሞ በሰጡት ምላሽ የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት በአሁኑ ወቅት የሚገዛው ቤንዚን ከእርሳስ ነፃ የሆነ ነው ብለዋል፡፡ ‹‹ሊድ ያለው ቤንዚን መግዛት አቁመናል፡፡ ዓለም ሊድ ያለው ቤንዚን መግዛት አቁሟል፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡ 

‹‹ኢትዮጵያ ከኩዌት የምትገዛው ናፍጣ ውስጥ ያለው የሰልፈር መጠን 0.2 በመቶ ሲሆን፣ ከነጋዴዎች የሚገዛው ናፍጣ 0.05 በመቶ ሰልፈር ይዘት አለው፡፡ የናፍጣ ዋጋ ባለው የሰልፈር መጠን ይወሰናል፡፡ 0.2 በመቶ ሰልፈር ያለው ናፍጣ በበርሜል 57.76 ዶላር፣ 0.05 በመቶ ሰልፈር ያለው 58.76 ዶላር፣ 0.005 በመቶ 60.16 ዶላር፣ 0.001 በመቶ 61.16 ዶላር ዋጋ አለው፤›› ብለዋል፡፡ 

‹‹0.001 በመቶ ሰልፈር ያለውን ናፍጣ ገዝቶ ማምጣት ይቻላል፤›› የሚሉት አቶ ታደሰ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት መኪኖች ዕድሜ ጠገብ በመሆናቸው የሰልፈር ይዘቱ ዝቅተኛ የሆነ ናፍጣ ገዝቶ ማምጣቱ ጠቀሜታ እንደሌለው ይናገራሉ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት መኪኖች በአብዛኛው አሮጌ በመሆናቸው ከፍተኛ የካርቦን ልቀት አላቸው፡፡ 

‹‹በአገራችን ያሉት ብዙዎቹ መኪኖች ሦስት መንግሥታት ያገለገሉ ናቸው፡፡ ከፍተኛ ዋጋ ያለውን ናፍጣ ገዝተን ብናመጣ መኪኖቹ ነዳጁን በአግባቡ መጠቀም የሚችሉ ባለመሆናቸው አላስፈላጊ ዋጋ መክፈል ብቻ ይሆናል፤›› ያሉት አቶ ታደሰ፣ ሌሎች አገሮች ከፍተኛ ዋጋ ያለውን ነዳጅ ሲያስገቡ የመኪና ዕድሜ ገድበው እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ‹‹ኬንያ ከስምንት ዓመት በላይ ዕድሜ ያለውን መኪና ማስገባት አይቻልም፡፡ በናይጄሪያ ከአምስት ዓመት በላይ ያለውን መኪና ማስገባት አይቻልም፡፡ ወደ እኛ አገር ተጨባጭ ሁኔታ ስንመጣ ይህን ማድረግ አይቻልም፡፡ አንድ ኤንትሬ የጭነት መኪና አሥር ቤተሰብ ያስተዳድራል፡፡ ከፍተኛ ዋጋ ያለውን ናፍጣ ከማስመጣታችን በፊት ዕድሜ ጠገብ ተሽከርካሪዎችን ማስወገድ አለብን፡፡ በርካታ ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ አሮጌ መኪኖችን በአሁኑ ወቅት ማስወገድ አይቻልም፡፡ ምናልባት ያን ማድረግ የሚቻለው ወደ መካከለኛ ገቢ አገርነት ስንሸጋገር ይሆናል፤›› ብለዋል፡፡ 

የነዳጅ ኩባንያ ተወካዮች የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት እ.ኤ.አ. ለ2016 የሚውል ነዳጅ ለመግዛት ነሐሴ 17 ቀን ጨረታ ማውጣት የነበረበት ቢሆንም፣ እስካሁን ጨረታውን አለማውጣቱን ይህም የጨረታ ግዢ ሙሉ በሙሉ ቀርቷል የሚል ሥጋት እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል፡፡ 

አቶ ታደሰ ድርጅታቸው ጨረታ ማውጣቱን እንዳልተወ፣ የጨረታ ሒደቱ እንዲዘገይ የተደረገው ከኩዌት የሚገዛው የነዳጅ መጠን እስከሚታወቅ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ 

የኩዌት መንግሥት የሚያቀርበው የነዳጅ መጠን ከታወቀ በኋላ ጨረታው እንደሚወጣ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ተጨማሪ የአውሮፕላን ነዳጅ እንዲያቀርቡ ጠይቀናል፡፡ የሚያቀርቡትን የናፍጣ መጠን የፍጆታችንን 70 በመቶ እንዲሆንም ጠይቀናል፡፡ ምላሻቸውን አይተን ጨረታውን እናወጣለን፤›› ብለዋል፡፡ 

ከሱዳን እስከ 80 በመቶ ቤንዚን የሚገኝ በመሆኑ የተቀረው 20 በመቶ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን፣ ኩዌት ከናፍጣ ፍጆታ 70 በመቶ ልታቀርብ ትችላለች፡፡ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት 800,000 ሜትሪክ ቶን ናፍጣና 60,000 ሜትሪክ ቶን ቤንዚን ለመግዛት ጨረታ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ 

 

የገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ አጋር የሆነው የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ሥራ አስፈጻሚ አባላት መካከል አለመግባባት መፈጠሩ ተሰማ፡፡ በዚህ ምክንያት የክልሉን ቋሚ መስተዳድር መመሥረት እንዳልተቻለ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ 

አለመግባባቱ የተፈጠረው አብዴፓንና የአፋር ክልልን ላለፉት 20 ዓመታት ሲመሩ በቆዩት የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ እስማኤል ዓሊ ሴሮ ቡድንና እሳቸውን ተክተው በተመረጡት የአብዴፓ ሊቀመንበር አቶ ጠሃ መሐመድ ቡድን መካከል መሆኑን፣ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የአብዴፓ ሊቀመንበር አቶ ጠሃ መሐመድ የክልሉ መንግሥት የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ፣ በሌሎች ክልላዊ መንግሥቶች የሥልጣን አወቃቀር መሠረት የፓርቲው ሊቀመንበር እንደመሆናቸው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርም ሊሆኑ ይገባል የሚል ክርክር፣ በአቶ ጠሃ ቡድን አማካይነት መነሳቱን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ይህ ጥያቄ ግን አብላጫ ድምፅ ባለው የአቶ እስማኤል ዓሊ ሴሮ ቡድን በኩል ተቀባይነት ማግኘት አለመቻሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በዚህ ምክንያት አቶ ጠሃ መሐመድና አቶ እስማኤል ዓሊ ሴሮ የሌሉበት የፓርቲው የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ከአንድ ወር በፊት ተካሂዶ፣ አቶ እስማኤል ለተጨማሪ ሦስት ወራት በጊዜያዊ ፕሬዚዳንትነት እንዲቆዩ፣ ካልሆነ ደግሞ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ጊዜያዊ አስተዳደር ይመሥርት በሚለው ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ በስተመጨረሻም ከክልሉ ምክር ቤት ውጪ ሥራ አስፈጻሚው ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት መሾሙን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በዚሁ መሠረት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የውኃ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ አወል አርባ፣ በጊዜያዊ ፕሬዚዳንትነት ለሦስት ወራት መመረጣቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይሁን እንጂ በወደፊቱ ጉዳይ ላይ መግባባት ባለመቻሉ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰሞኑን በአዲስ አበባ እየመከረ እንደነበር፣ በዚህ ስብሰባ ላይም የኢሕአዴግ ተወካዮች ለታዛቢነትና ለማስታረቅ መገኘታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ 

በትጥቅ ትግሉ ወቅት አቶ እስማኤል ዓሊ ሴሮ የሕወሓት አባል የነበሩ ሲሆን፣ በትጥቅ ትግሉ የተሳተፉ የአፋር ክልል ተወላጅ ናቸው፡፡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የአብዴፓ ሊቀመንበር በመሆን ለ20 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ 

በግንቦት ወር 2007 ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ ክልሉን በመወከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት ተመርጠዋል፡፡    

በአብዴፓ ውስጥ የተፈጠረውን አለመግባባትና እየተካሄደ ስለነበረው ድርድርና ምክክር ለአብዴፓ ጽሕፈት ቤት፣ ለክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ፣ ለኢሕአዴግ የውጭ ግንኙነት ጽሕፈት ቤትና ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ጥያቄ ቢቀርብም ምላሽ ማግኘት አልተቻለም፡፡  

 

‹‹ምርመራ ዘመናት የሚያስቆጥር የአርኪዮሎጂ ቁፋሮ አይደለም›› የተጠርጣሪው አቶ ወንድሙ ቢራቱ ጠበቃ

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ነሐሴ 3 ቀን 2007 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ውለው በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣን አቶ ወንድሙ ቢራቱ፣ የአውሮፕላን ትኬት በመግዛት በግብዣ መልክ ለባለሥልጣናት ጉቦ መስጠታቸው ተገለጸ፡፡

አቶ ወንደሙ የተጠረጠሩባቸውን የሙስና ወንጀሎች እየመረመረ የሚገኘው የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት እንዳስረዳው፣ ተጠርጣሪው በሥልጣን ዘመናቸው ወደ ውጭ አገር በመሄድ ምን ያህል ገንዘብ እንዳወጡና ለባለሥልጣናት የአውሮፕላን ትኬት በመቁረጥ በግብዣ መልክ ጉቦ የሰጡበትን ሰነድ ከሚመለከተው ተቋም መጠየቁን አስረድቷል፡፡

መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው፣ ተጠርጣሪው የተጭበረበረ ሰነድ ሕጋዊ በማስመሰል መሬት የሸጡበትና ከባንክ ገንዘብ የተቀበሉበት ሰነድ ተሰብስቧል፡፡ ጉቦ በቼክ የተቀበሉበት ሰነድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተሰብስቧል፡፡ ከሁለት ሰዎች ሦስት ሚሊዮን ብር ጉቦ መቀበላቸውን ከሚያረጋግጡ ሰዎች የምስክርነት ቃል መቀበሉንም ቡድኑ ገልጿል፡፡ ከጉምሩክ ከጠየቀው የማስረጃ ሰነድ ከፊሉን መሰብሰቡን፣ በኦሮሚያ ልዩ ዞኖች ለሚደረገው ምርመራ ደጋፊ ሰነድ በማቅረብ እየተከታተለ እንደሆነና አንድ ተጨማሪ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር አውሎ ቃሉን መቀበሉን መርማሪ ቡድኑ አስረድቷል፡፡

የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት የጠየቀ ሲሆን፣ ምክንያቱንም አስረድቷል፡፡ ተጠርጣሪው ብዙ ቤቶችና ቦታዎች እንዳሏቸው ጥቆማዎች በመምጣታቸው ከአራት ከተሞች ማኅደሮችን መሰብሰብ እንደሚቀረው፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ ያልተሰበሰቡ ማስረጃዎችን መሰብሰብ፣ ተጨማሪ ሰነዶችን ለፎረንሲክ ምርመራ በመላከ ትክክለኛነቱን አረጋግጦ መሰብሰብ፣ ሌሎች ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን አድኖ መያዝና የምስክሮችን ቃል መቀበል ስለሚቀረው መሆኑን አስረድቷል፡፡

አቶ ወንድሙ ቀደም ባሉት ቀጠሮዎች እሳቸው የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባል ከመሆናቸውም በተጨማሪ፣ በእሳቸው ላይ የሚቀርብ ማንኛውንም ተጠያቂነት የመጠየቅ ሥልጣን ያለው የክልሉ መንግሥት መሆኑን በመናገር ሲከራከሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ተጠርጣሪው አሁንም በጠበቃቸው አማካይነት እንደገለጹት፣ የተጠረጠሩበትን የሙስና ወንጀል የማየት ሥልጣን ያለው የኦሮሚያ መንግሥት ብቻ ነው፡፡ የመመርመርና የመክሰስ ሥልጣን ያለው የኦሮሚያ የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ብቻ ነው፡፡ ይሄም በፌዴራል የፀረ ሙስና አዋጅ 433/97 አንቀጽ 7(4) እና በአዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 7(2/4) ተደንግጓል ብለዋል፡፡ ፌዴራል የክልሉን ሥልጣን ማክበር እንዳለበት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 50(8) መደንገጉንም አስረድተዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ የዳኝነት ሥልጣን ስለሌለውና ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መስጠት ስለማይችል፣ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 50(8) እና በወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ 110 መሠረት ክሱን ዘግቶ ተጠርጣሪው እንዲያሰናብታቸው ጠይቀዋል፡፡

የፖሊስ ምርመራ ተጠናቆ ቀዳሚ ምርመራ ውስጥ መግባቱን የጠቆሙት የአቶ ወንድሙ ጠበቃ፣ የምርመራ ሥራ ዘመናት የሚያስቆጥር የአርኪዬሎጂ ቁፋሮ አለመሆኑንና በፍጥነት መፈጸም ያለበት የሕግ ሥራ በመሆኑን በመጠቆም ተጨማሪ ቀጠሮ መሰጠት እንደሌለበት አመልክተዋል፡፡

የወንጀሉ መፈጸም አጠራጣሪ መሆኑንና ተጠርጣሪውን ዋስትና ሊያስከለክላቸው እንደማይችል የገለጹት ጠበቃው፣ ወንጀሎቹ መፈጸማቸውን የሚያስረዳ ምንም ዓይነት ማስረጃ ካለመገኘቱም በተጨማሪ ተጠርጣሪው ወንጀሉን መፈጸማቸውም አጠራጣሪ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አጠራጣሪ ወንጀል የቅጣት ጣሪያው ምንም ያህል ቢሆንም የዋስትና መብት እንደማያስከለክል ጠቁመው፣ መርማሪ ቡድኑ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ታልፎና መዝገቡ ተዘግቶ ከእስር እንዲፈቱ ወይም የመንቀሳቀስ መብታቸው ተገድቦ በዋስ እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡ 

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ በሰጠው ትዕዛዝ፣ የተጠርጣሪው ጠበቃ ቀደም ባለው ቀጠሮ መርማሪ ቡድኑ በጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ምንም እንዳልሠራ መግለጻቸውን በሚመለከት መዝገቡን ተመልክቶ፣ ጠበቃው እንዳሉት ሳይሆን ቡድኑ ምርመራ ማድረጉን ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡ የተጠርጣሪ ጠበቃ የደንበኛቸውን ጉዳይ የፌዴራል መንግሥት ወይም ፍርድ ቤቶች ማየት እንደማይችሉና ሥልጣኑ የክልሉ መሆኑን በመጥቀስ መዝገቡ ተዘግቶ አቶ ወንድሙ በነፃ እንዲሰናበቱ ያቀረቡትን አቤቱታ እንዳልተቀበለው አስረድቷል፡፡ ያልተቀበለበት ምክንያት ቀደም ባሉ ቀጠሮዎች ተመሳሳይ ጥያቄ ቀርቦ ችሎቱ ብይን የሰጠበት መሆኑን በመግለጽ፣ ለመርማሪ ቡድኑ ተጨማሪ ዘጠኝ ቀናትን በመፍቀድ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

አቶ ወንድሙ ሥልጣናቸውን በመጠቀምና ከፌዴራል ባለሥልጣናት ጋር በመመሳጠር አገራዊ ጠቀሜታ ላላቸው የተለየ ክህሎት ለሚጠይቁ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተፈቀደውን ከቀረጥ ነፃ መኪና ማስገባት መብት በመጠቀማቸው፣ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ሀብት በማከማቸት፣ በሕገወጥ መንገድ ያካበቱትን ሀብት ሕጋዊ በማስመሰል፣ በዘመዶቻቸው ስም ሀብት በማስቀመጥ፣ ለመንግሥት መግባት የነበረበትን ታክስና ቀረጥ ለግል መጠቀሚያ በማድረግ፣ ጉቦ በመቀበልና በማቀባበል ወንጀሎች መጠርጠራቸውን የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን ቀደም ባሉት ችሎቶች ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

 

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በመቀሌ ከተማ ባደረገው ስብሰባ ላይ በጥንቃቄ ተመርጠው የተጠሩ ታማኝ ካድሬዎችና አባላት የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰሙ፡፡ የትግራይ ፌስቡክ ተጠቃሚዎች አብዮታዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው መሆኑ በአባይ ወልዱ የሚመራው የህወሓት አንጃ አሳወቀ። አንጃው ይህንን አብዮታዊ እርምጃ እንደሚወስድ ያሳወቀው “12ተኛ ጉባኤ እንዴት አለፈ …?” በሚል አጀንዳ በየመንግሥት መስርያ ቤቶች፣ ከመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች፣ የክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች […]

የትግራይ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ሃላፊና የክልሉ ዳኞች ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማሪያም በሙስና ስለተገመገሙ ከሃላፊነታቸው መውረድ አለባቸው ሲሉ የህወሓት ጉባኤተኞች የወሰኑትን ውሳኔ እስከ አሁን ድረስ እንዳልተተገበረ ተገለፀ። እንደ ምንጮቻችን መረጃ መሰረት የአባይ ወልዱ ሚስት የሆኑት ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማሪያም ላለፉት አመታት የትግራይ ክልል የሲቪል ሰርቪስ ሃላፊ ሆነው በሰሩበት ጊዜ በመስሪያ ቤቱ አዳዲስ ለውጦች ባለማምጣታቸው የተነሳና ጊዜው […]

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድምጻችን ይሰማ የትግል ስትራቴጂውን በአዲስ መንገድ እንደሚቀይስ ማስታወቁን ተከትሎ፣ የመጀመሪያውን ትግል አንድ ቁጥር በመያዝ ትግሉን ጀምሯል። ሙስሊሙ ማህበረሰብ በቅርቡ ፍርድ ቤት በሙስሊም መሪዎች ላይ የሰጠውን ፍርድ ” የተቀበረች ፍትህ ቀባሪዋን ትቀብራለች፣ አምባገነናዊ ፍርድ አንቀበልም” የሚል መፈክር በማሰማት ተቃውሞ አሰምቷል። አሃዱን አሃድ፣ ትግላችን ይቀጥላል፣ ድምጻችን ይሰማ፣ ኮሚቴው ይፈታ፣ …

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አሳይቷል በዘንድሮ የአዲስ አመት ገበያ፣ የዶሮ ዋጋ ከበፊቱ በእጥፍ የጨመረ ሲሆን በአቃቂና በሳሪስ አካባቢ ዶሮ ከ200 ብር እስከ 400 ብር የሚሸጥ ሲሆን፤ በግ ከ1100 እስከ 3500 ብር፣ በሬ ከ4500 እስከ 25ሺ ብር፣ ፍየል ከ750 እስከ 4ሺ ብር እየተሸጡ ነው፡፡ በሾላ ገበያ በግ ከ900 ብር እስከ 4500 ብር፣ …

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል ባጠናው ጥናት ከአዋሳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ የሚወጣው ኬሚካል ሃይቁንና ወንዙን በመበከሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ህይወት አደጋ ላይ ወድቋል። ከፋብሪካው የሚወጣው ውሃ በቀጥታ ወደ ጥቁር ውሃ ወንዝ የሚፈስ ሲሆን፣ ወንዙም ወደ ሃይቁ የሚፈስ በመሆኑ ተጨማሪ ስጋት ፈጥሯል። የኬሚካሉ ወደ ውሃው መግባት የአሳዎችን ስደት እንደሚያስከትል የሚገልጸው …

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመጪው መስከረም ወር 2008 መቶ በመቶ በኢህአዴግና አጋሮቹ በተያዘው ፓርላማ ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ሁለተኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ይፋ ለማድረግ በሚል በእነሠራዊት ፍቅሬ እና ሽዋፈራው ደሳለኝ አጋፋሪነት ከምሽቱ 3 ሰዓት ጅምሮ በሚሌኒየም አዳራሽ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሚገኙበት ታላቅ የፌሽታ በዓል ተዘጋጅቷል፡፡ እነሠራዊት ፍቅሬ …

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከባህርዳር እስረኞችን ጭኖ አዲስ አበባ ወደሚገኘው ማእከላዊ እስር ቤት በመጓዝ ላይ ያለ ሚኒባስ ታክሲ ፣ ማለዳ 1 ሰአት ተኩል አካባቢ ሾላ ሰሜን ሆቴል ወይም መቀጠያ ሃበሻ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ሲደርስ ፣ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በመቆሙ በውስጡ ከነበሩት 13 እስረኞች መካከል 6ቱ ከመኪናው በመውረድ አምልጠዋል። የተቀሩት ከሚኒባስ ባለመውረዳቸው …

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በተጠለሉባቸው የስደተኞች መጠለያዎች ውስጥ የተቀሰቀሰው የኮሌራ ወረሽኝ በአጎራባች የደቡብ ሱዳንና የኢትዮጵያ ድንበሮች አካባቢ ስጋት እየፈጠረ ነው። ይህንን ተላላፊ ገዳይ በሽታ ለመግታት የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅትና ዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን በጥምረት ክትባትና የንጹህ ውሃ አገልግሎት አቅርቦት መስጠት ጀምረዋል።በአስር የስደተኞች መጠለያ …

ከትናንት ሐሙስ አንስቶ ለ 10 ቀናት የሚዘልቅ የፎቶ አውደ ርዕይ ዩናይትድ ስቴትስ- ኒው ዮርክ ከተማ ተከፍቷል። በዚህም አውደ ርዕይ ላይ የ11 ወጣት ኢትዮጵያውያን የፎቶ ስራዎች ለዕይታ ቀርበዋል።