የኢሕኣፓ ሰራዊት አመራሮች በጅምላ ተረሽነው በጣና በለስ ፕሮጀክት አከባቢ ተቀብረዋል::

ቁጥራቸው ወደ 40 የሚጠጋ የእሕኣፓ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች የሕወሓት/ኢሕኣዴግ ሰራዊት ጎንደር እና ጎጃምን በተቆጣጠረ ጊዜ በውጊያ ከተማረኩ በኋላ በ1983/84( በ1991)ከተረሸኑ በኋላ በጣና በለስ ፕሮጀክት አቅራቢያ በጅምላ መቀበራቸውን ምንጮች ለኢትዮ ሚዲያ ገልጸዋል::

የጅምላ መቃብሩን የቆፈረው ቡልዶዘር የጣና በለስ ፕሮጀክት ንብረት የነበረ ሲሆን ቡልዶዘሩን ሲያንቀሳቅስ የነበረውም ኦፕሬተር ግድያውን እና የጅምላ መቃብሩን በተመለከት ህዝብ ጆሮ እንዳይደርስ ምስጢር ለመጠበቅ ሲባል ወዲያው የተገደለ መሆኑ ምንጮቹ ገልጸው የግድያው ትእዛዝ የሰጡት እና እንዲፈጸም ያደረጉት ሟች መለስ ዜናዊ እና አኦ ስብሃት ነጋ መሆናቸውን አክለው ተናግረዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ በተመሳሳይ ሁኔታ ስምንት የኢሕኣፓ ሰራዊት አመራሮች የነበሩት በሕወሓት ሰራዊት ተይዘው በ ባዶ 6 እስር ቤት ትግራይ መታሰራቸው እና የግድያ ቅጣት ተላልፎባቸው እንደነበር ይታወሳል:: ይህ የኢሕኣፓ ከፍተኛ አመራሮች ጸጋዬ ደብተራው ሃጎስ በርሄ ይሳቅ ደብረጺሆን እና ሌሎችም የተላለፈባቸው የግድያ ቅጣት የተፈጸመው በትግራይ ይሁን በጎንደር አሊያም በጎጃም እስካሁን መረጃው እንዳሌላቸው ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል::
http://www.ethiomedia.com/14store/5563.html